ኢሕአፓ/eprp 

እንኳን ለ130ኛው የዓድዋ የድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የዓድዋ አባቶቻችን አንድነት ኢትዮጵያን በቀኝ ለመግዛት እና ኢትዮጵያውያንን ባርያ የማድረግ ዓላማ ይዞ የመጣውን ወራሪ ኃይል በአንድ ቀን ጦርነት እንዲያሸንፉ አድርጎአቸዋል።

ኢትዮጵያ አገራችን ዛሬ በቋንቋ ላይ በተመሰረተው የብሔር ፖለቲካ ምክንያት አንገቷን ደፍታለች። ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ያለ አንዳች ወንጀል በእስር ቤት እንዲማቅቁ ተፈርዶባቸዋል። ንጹሀን በማንነታቸው ዒላማ ተደርገው በሀገራቸው ባይተዋር ሆነዋል። ተገድለዋል፤ እየተገደሉም ነው። ውድ ኢትዮጵያውያን! አገራችን ሰላም አንድነቷን አስጠብቃ የምትቀጥለው ከብሔር ፖለቲካ ነጻ ስትወጣ እና እኩል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ስትሆን ስለሆነ ከኢሕአፓ ጋር በመቆም አገራችንን ለማዳን ቆርጣችሁ እንድትነሱ የአብሮነት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

እንደ ዓድዋ አባቶቻችን ሁሉ፤ ዛሬም፤ ሁላችንም ስለ ሰውነት ክብር በጋራ ልንቆም ይገባል።

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ – ኢሕአፓ ለመላው ኢትዮጵያውያን መልካም የዓድዋ ድል በዓል እንዲሆን ይመኛል።