
የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ መከናወን የሚጀምር ሲሆን፣ የሚተካቸውም አዲስ መሪ ግብአተ መሪታቸውን ተከትሎ ይፋ እንደሚደረግ የአገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።ምርጫውን የሚያከናውነው ምክር ቤት ጽህፈት ቤቶች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ሲዘገብ፤ እስራኤልም ለደኅንነቷ ስጋት ሆኖ የሚቀጥል መሪ ከተመረጠ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች።
ጭምቅ ሃሳብ
- አሜሪካ ዜጎቿ ከ14 አገራት በአስቸኳይ ለቅቀው እንዲወጡ አዘዘች
- ትራምፕ የዩኬውን ጠቅላይ ሚኒስትር “ተባባሪ አይደሉም” ሲሉ ተቹ
- እስራኤል ወደ ሊባኖስ እግረኛ ጦሯን በማስገባት “ተጨማሪ ቁልፍ አካባቢዎችን” እንደምትይዝ ገለፀች
- በኩዌት የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ተዘጋ
- በሪያድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የድሮን ጥቃት ደረሰበት
- አሜሪካ “ለተራዘመ” ጦርነት የሚበቃ የጦር መሣሪያ ክምችት እንዳላት ትራምፕ ተናገሩ
- ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ የሚንቀሳቀሱ መርከቦችን ለመምታት ዛተች
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኩዌት ሉዓላዊ ግዛት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዙ
- ትራምፕ አያቶላህ አሊ ኻሜኒን ሊተኩ የሚችሉ በርካታ ዕጩዎች በመጀመሪያው ዙር ጥቃት ተገድለዋል አሉ
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 14 ደቂቃዎች በፊትየኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ትራምፕ ድርድሩን “እንደ ሪል ስቴት ንግድ” ነበር የያዙት አሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አግራቺ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው በለጠፉት ጽሑፍ፤ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “በክፋት ተነሳስተው የድርድር ጠረጴዛውን በቦምብ ደብድበዋል” ሲሉ ከሰሱ።“ውስብስብ የሆኑ የኒውክሌር ድርድሮች እንደ ሪል እስቴት ንግድ ሲያዙ፣ እና ትላልቅ ውሸቶች እውነታን በሚጋርዱበት ጊዜ መሬት የማይወርዱ ነገሮች በፍጹም ሊሳኩ አይችሉም” ብለዋል።“ውጤቱስ? በክፋት ተነሳስተው የድርድር ጠረጴዛውን በቦምብ ደብድበዋል” በማለት ጽፈዋል።ጦርነቱ ከመጀመሩ ቀናት አስቀድሞ ጄኔቫ ውስጥ ሲደረግ በነበረው ድርድር ቴህራንን ከወከሉ ተደራዳሪዎች ዋነኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አግራቺ ናቸው።በዚህ የኒውክሌር ድርድር “ጥሩ መሻሻሎች” እንደተመዘገቡ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም ከቀናት በኋላ አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ ጥቃት በመፈጸም ጠቅላይ መሪውን ጨምሮ በርካታ አመራሮችን ገድለዋል።ሐሙስ ዕለት ስዊትዘርላንድ ጄኔቭ ላይ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ድርድር ከተካሄደ በኋላ ቅዳሜ ዕለት ነበር አሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የከፈቱት።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አራግቺ ጨምረውም “ትራምፕ በዲፕሎማሲ ላይ እና በመረጣቸው የአሜሪካ ሕዝብ ላይ ክህደት ፈጽመዋል” በማለት ጽፈዋል።ያጋሩ, የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ትራምፕ ድርድሩን “እንደ ሪል ስቴት ንግድ” ነበር የያዙት አሉ - ከ 1 ሰአት በፊትከኻሜኒ ቀብር በኋላ ተተኪያቸው ይታወቃል፣ እስራኤልም አዲሱ መሪን ዒላማ እንደምታደርግ ዝታለች
የምስሉ መግለጫ,ሟቹ አያቶላ ኻሜኒ እና ይተካቸዋል የሚባለው ልጃቸው ሞጅታባ ኻሜኒየኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ መከናወን የሚጀምር ሲሆን፣ የሚተካቸውም አዲስ መሪ ግብአተ መሪታቸውን ተከትሎ ይፋ እንደሚደረግ የአገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።ምርጫውን የሚያከናውነው ምክር ቤት ጽህፈት ቤቶች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ሲዘገብ፤ እስራኤልም ለደኅንነቷ ስጋት ሆኖ የሚቀጥል መሪ ከተመረጠ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች።የጠቅላይ መሪው የቀብር ሥነ ሥርዓት ሦስት ቀናትን እንደሚወስድ እና ከቀብሩ በኋላ የእስላማዊ ሪፐብሊኩ መሪ የሚሰይሙት መንፈሳዊ እና ፖለቲካዊ ሥልጣን ያላቸው መሪዎች በአካል ተሰብስበው ምርጫውን እንደሚያከናውኑ ፋርስ የተባለው የዜና ወኪል ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።ምርጫውን የሚያካሂደው ምክር ቤት አባላት ለአሜሪካ እና እስራኤል እንዳይጋለጡ “አስፈላጊ የሆነው የደኅንነት ጥበቃ እርምጃዎች በከፍተኛ ደረጃ መወሰዱን” ዘገባዎች እየጠቆሙ ነው።ነገር ግን ‘ቆም’ በምትባለው ከተማ የሚገኘው የከፍተኛ ባለሥልጣናቱ ጉባዔ አባላት ጽህፈት ቤት ማክሰኞ እንዲሁም ቴህራን ውስጥ ስብሰባ የሚያደርጉበት ቦታ ዛሬ በእስራኤል እና በአሜሪካ ጥቃት እንደተፈጸመበት ቢቢሲ ፐርሺያ ዘግቧል።የአያቶላህ ኻሜኒ ቀብር በትክክል የት እንደሚካሄድ እስካሁን ያልተገለጸ ሲሆን፣ የኢራን መገናኛ ብዙኃን ግን ማሻድ በምትባለው ከተማ ውስጥ በሚገኘው ስምንተኛው የሺዓ ኢማም የእምነት ስፍራ ሊሆን እንደሚችል እየዘገቡ ነው።የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ሦስተኛው ጠቅላይ መሪ ማን እንደሚሆን እየተጠበቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት ኒው ዮርክ ታይምስ የኢራን ባለሥልጣናትን ጠቅሶ የሟቹ መሪ ልጅ ሞጅታባ ኻሜኒ አዲሱ መሪ እንዲሆን ከስምምነት ላይ መደረሱን እና ይፋ እንደሚደረግ ዘግቧል።ፋርስ ዜና ወኪል ከኻሜኒ ቀብር በኋላ የመሪው ማንነት ይፋ እንደሚደረግ እና የሹመት ሥነ ሥርዓቱም በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚሆን ገልጿል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ ለአገራቸው ጠላት የሆነ የትኛውም ተተኪ ቢመጣ ዒላማቸው እንደሚሆን ተናግረዋል።“እስራኤልን የማጥፋት ዕቅድን የሚቀጥል፣ አሜሪካን ላይ የሚዝት፣ የኢራንን ሕዝብ የሚጨቁን የትኛውም ተተኪ በማያጠራጥር ሁኔታ ለመደምሰስ ዒላማችን ይሆናል” ብለዋል የመከላከያ ሚኒስትሩ።አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 21/2018 ዓ.ም. በኢራን ላይ በከፈቱት ጥቃት የአገሪቱን ጠቅላይ መሪ ጨምሮ በርካታ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ተገድለዋል።ያጋሩ, ከኻሜኒ ቀብር በኋላ ተተኪያቸው ይታወቃል፣ እስራኤልም አዲሱ መሪን ዒላማ እንደምታደርግ ዝታለች - ከ 1 ሰአት በፊትእስራኤል በቴህራን ወታደራዊ ተቋማት ላይ ጥቃት ስትፈጽም፤ ኢራን በኳታር የሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈርን አጠቃችየመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ለአምስተኛ ቀን በቀጠለበት በዛሬው ዕለት እስራኤል በኢራን ውስጥ የሚገኙ ዒላማዎችን ስትመታ፣ ኢራን ደግሞ ኳታር ውስጥ በሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ፈጽማለች።እስራኤል ቴህራን ውስጥ የሚገኘውን የኢራን አብዮታዊ ዘብ አካል የሆነውን የባሲጅ ሚሊሻ ጽህፈት ቤትን እና ሌሎች ወታደራዊ ተቋማትን ማጥቃቷን የጦሯ ቃል አቀባይ አስታውቋል።በተመሳሳይ ኢራን ኳታር ውስጥ በሚገኘው የአሜሪካ አየር ኃይል ሰፈር ላይ የተነጣጠሩ ሁለት ሚሳዔሎችን መተኮሷን የኳታር የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።አንደኛው ሚሳዔል በኳታር የአየር መከላከያ ሥርዓት ሲከሽፍ ሌላኛው በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ትልቁ የአሜሪካ አየር ኃይል ሰፈር የሆነውን አል ኡዴይዳን መታቱን፣ ነገር ግን በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱ ታውቋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዲት የኢራን መርከብ ከሲሪ ላንካ ደሴት አቅራቢያ የመስመጥ አደጋ ደርሶባት የድረሱልኝ ጥሪ ማቅረቧን የሲሪ ካንካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መናጋራቸው ተዘገበ።መርከቧ 180 ሰዎችን አሳፍራ በመጓዝ ላይ እንደነበረች እና 30 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ከመርከቧ ወርደው ወደ ሆስፒታል እንደተወሰዱም ጨምረው ገልጸዋል።ነገር ግን ለኢራኗ መርከብ መስመጥ ምክንያቱ ምን እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም።ያጋሩ, እስራኤል በቴህራን ወታደራዊ ተቋማት ላይ ጥቃት ስትፈጽም፤ ኢራን በኳታር የሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈርን አጠቃች
- ከ 2 ሰአት በፊትበመካከለኛው ምሥራቅ ትናንት ምሽት የተፈጸሙ ጥቃቶች
የፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,ወደ ቴል አቪቭ የተተኮሰ የጦር መሣሪያአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ለፈጸሙት ጥቃት ቴህራን የአጸፋ ምላሽ መስጠቷን ቀጥላለች። መካከለኛው ምሥራቅን ባዳረሰው ጦርነት ውስጥ ባለፈው ምሽት የተፈጸሙ ጥቃቶች የሚከተሉት ናቸው።ኢራን- የኢራን መከላከያ እንዳለው ባለፉት ጥቂት ሰዓታት አዲስ ጥቃቶች መሰንዘር ቀጥሏል። ከኢራን ሚሳዔሎች መተኮሳቸውን ተከትሎ እስራኤል የድንገተኛ ጊዜ ደውል አሰምታለች።ሊባኖስ- እስራኤል ሄዝቦላህን ዒላማ አድርጋ ጥቃት እየፈጸመች ሲሆን፤ ሄዝቦላህም ትናንት ማምሻውን ሚሳዔሎች ሲተኩስ ነበር። እስራኤል በጥቃቱ የተጎዱ ሰዎች እንደሌሉ ገልጻለች።ኩዌት- መኖሪያ ሰፈር አካባቢ በወደቀ የመሣሪያ ስብርባሪ ሳቢያ የ11 ዓመት ልጅ እንደተገደለች የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የታዳጊዋን እናት ጨምሮ አራት ቤተሰቦቿ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተገልጿል።የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች- የዩናይትድ ኪንግደም የባሕር ንግድ ተቋም እንዳለው፤ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሚገኘው ፉጃራህ ወደብ ላይ “ምንነቱ ያልታወቀ መሣሪያ ስብርባሪ” ወድቋል። መርከብ ላይ ጉዳት ቢደርስም የመርከቡ ሠራተኞች እንዳልተጎዱ ተገልጿል።ያጋሩ, በመካከለኛው ምሥራቅ ትናንት ምሽት የተፈጸሙ ጥቃቶች - ከ 3 ሰአት በፊትኳታር ለኢራን እየሰለሉ ነበር ያለቻቸውን 10 ሰዎች በቁጥጥር ሥር አዋለች
የፎቶው ባለመብት,Reutersየኳታር የፀጥታ ኃይሎች ለኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ሲሰልሉ የነበሩ “ሁለት የስለላ ሕዋሶችን” ረቡዕ ዕለት በቁጥጥር ሥር ማዋሏን የአገሪቱ የመንግሥት የዜና ወኪል ዘገበ።ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ሰባቱ “የአገሪቱን ወሳኝ እና ወታደራዊ መሠረተ ልማቶች የተመለከተ መረጃ የመሰብሰብ የስለላ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው” እንደነበረ ዘገባው አመልክቷል።በስለላ የተጠረጠሩት ቀሪዎቹ ሦስት ሰዎች ደግሞ “የድሮን አጠቃቀም ሥልጠና የወሰዱ” እንደሆኑ ተገልጿል።የዜና ወኪሉ፤ “ተጠርጣሪዎቹ በተደረገባቸው ምርመራ ከኢራን አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው አምነዋል፤ የስለላ እና የማዳከም ተልዕኮ ተሰጥቷቸው እንደነበር ተናግረዋል” በማለት ዘግቧል።በአሜሪካ እና ኢራን ጥቃት የተከፈተባት ኢራን በሰጠችው የአጸፋ ምላሽ ዒላማ ካደረገቻቸው የቀጣናው አገራት አንዷ ኳታር ነች። ኢራን በፈጸመችው ጥቃት የኳታር ዋነኛ የጋዝ ማምረቻ ተቋም ጉዳት እንደደረሰበት የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።ሁለት የኢራን ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ ሰባት ሚሳዔሎችን እና አምስት ድሮኖችንም መትቶ እንደጣለ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጿል።የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ትናንት በሰጡት መግለጫ “ሁሉም ቀይ መስመሮች ታልፈዋል” ብለው ነበር።ጦርነቱ በተጀመረበት ቅዳሜ ዕለት ብቻ ኢራን 65 ሚሳዔሎችን እና 12 ድሮኖችን ወደ ኳታር ማስወንጨፏን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀው ነበር።ያጋሩ, ኳታር ለኢራን እየሰለሉ ነበር ያለቻቸውን 10 ሰዎች በቁጥጥር ሥር አዋለች - ከ 3 ሰአት በፊትእስራኤል “60 የሚገመቱ የሄዝቦላህ ዒላማዎች” ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች
የፎቶው ባለመብት,EPAለኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ግድያ የአጸፋ ምላሽ እየሰጠ ያለው ሄዝቦላህ እና እስራኤል አንዳቸው ሌላኛቸው ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ቀጥለዋል።የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ባወጣው መረጃ “ ወደ 60 በሚገመቱ የሄዝቦላህ ዒላማዎች” ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።የእስራኤል ጦር የጥቃት ዒላማ እንደሆኑ ከገለጻቸው መካከል፤ “የጦር መሣሪያ ማከማቻዎች፣ የዕዝ ማዕከላት፣ ሚሳዔል ማስወንጨፊያዎች እና ተጨማሪ የሽብር መሠረተ ልማቶች” ይገኙበታል።በተጨማሪም ጦሩ፤ በደቡባዊ ሊባኖስ ሁለት አካባቢዎች ውስጥ በሚገኙ የሄዝቦላህ ዒላማዎች ላይ ሌሎች ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታውቋል።ሄዝቦላህ በበኩሉ በሰሜን እስራኤል በሚገኘው ሀይፋ የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል።የእስራኤል ጦር፤ ሄዝቦላህ ይህንን ካስታወቀ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ባወጣው መረጃ ወደ አገሪቱ የተወነጨፉ በርካታ ተተኳሾች እየመጡ መሆናቸው እንደታወቀ እና አብዛኛዎቹ ተመትተው እንደወደቁ ተናግሯል።ከእኩለ ሌሊት በኋላ ደግሞ በሊባኖስ መዲና ቤይሩት ውስጥ ከፍተኛ ፍንዳታ መሰማቱን የዜና ወኪሉ ኤኤፍፒ ዘጋቢ ገልጿል።በተጨማሪም እስራኤል በበርካታ የሊባኖስ መንደሮች እና ከተማዎች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች አካባቢዎቹን ለቅቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች። እስራኤል በዘረዘረቻቸው 13 አካባቢዎች ውስጥ ሄዝቦላህን ዒላማ ያደረገ ጥቃት እንደምትፈጽም ገልጻለች።ያጋሩ, እስራኤል “60 የሚገመቱ የሄዝቦላህ ዒላማዎች” ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች - ከ 4 ሰአት በፊትኢራን ውስጥ ከ1,000 በላይ ንጹኃን መገደላቸውን የሰብአዊ መብቶች ቡድን ገለጸ
የፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,ከኢራን የውጭ ፕሬስ ክፍል የተገኘ ፎቶግራፍ በሚናብ የሴቶች ትምህርት ቤት ለተገደሉ ሰዎች መቃብሮች እየተዘጋጁ አሳይቷልአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት መፈጸም ከጀመሩበት ቅዳሜ የካቲት 21 አንስቶ ባሉት ቀናት ውስጥ በኢራን ከ1,000 በላይ ንጹኃን መገደላቸውን መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የዜና ወኪል ‘ሂራና’ ዘገበ።የዜና ወኪሉ ዘገባ እንደሚያመለክተው ከተገደሉት ሰዎች ውስጥ 181 ያህሉ ዕድሜያቸው ከ10 ዓመት በታች የሆነ ሕጻናት ናቸው። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ደግሞ 5,402 መሆናቸውን የገለጸው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኑ፤ ከእነዚህ ወስጥ 100 ያህሉ ሕጻናት መሆናቸውን አክሏል።ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ኢራን ውስጥ ቢያንስ 104 ጥቃቶች መፈጸማቸውን ቡድኑ ገልጿል። እንደ ቡድኑ ዘገባ፤ እነዚህ ጥቃቶች ወታደራዊ ካምፖችን፣ የሕክምና ማዕከላትን እና የመኖሪያ አካባቢዎችን መትተዋል።ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ስለመሞታቸው የደረሱ መረጃዎች እየተመረመሩ እንደሆነም ተገልጿል።ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ እስራኤል እና አሜሪካ ጥቃት በከፈቱበት ቅዳሜ ዕለት በሴቶች ትምህርት ቤት ላይ በደረሰ የአየር ጥቃት የሞቱ ሰዎችን የቀብር ሥነ ሥርዓት የሚያሳዩ ምሥሎች ወጥተዋል።ሚናብ በተባለው የኢራን ከተማ በሚገኝ የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመው የአየር ጥቃት ከ160 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ባለሥልጣናት ገልጸዋል። ትምህርት ቤቱ ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ካምፕ አቅራቢያ እንደሚገኝ ተነግሯል።ቢቢሲ በዚህ ጥቃት ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ በገለልተኛነት አላረጋገጠም። የአሜሪካ ጦር ክስተቱን በተመለከተ ስለሚወጡ መረጃዎችን እያጣራ መሆኑን ገልጿል። የእስራኤል ጦር በበኩሉ በአካባቢው ላይ ስለተካሄደ ማንኛውም ዘመቻ “እንደማያውቅ” ተናግሯል።
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በዚህ ጥቃት ከተገደሉ ሰዎች ውስጥ የተወሰኑት ማክሰኞ ዕለት የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ተከናውኗል
የፎቶው ባለመብት,Reutersያጋሩ, ኢራን ውስጥ ከ1,000 በላይ ንጹኃን መገደላቸውን የሰብአዊ መብቶች ቡድን ገለጸ - ከ 5 ሰአት በፊትሳዑዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኝ የሲአይኤ ጣቢያ በድሮን መመታቱ ተዘገበ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ሪያድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሁለት ድሮኖች እንደተመታ አሜሪካ እና ሳዑዲ አረገግጠዋልሳዑዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኝ የአሜሪካው የስለላ መሥሪያ ቤት ‘ሴንትራል ኢንተለጀንስ ኤጀንሲ’ (ሲአይኤ) ጣቢያ በድሮን እንደተመታ ተዘገበ። ጥቃቱን ያደረሱት ድሮኖች የኢራን ናቸው የሚል ጥርጣሬ እንዳለ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ በሪያድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሁለት ድሮኖች ጥቃት እንደተፈጸመበት አረጋግጠዋል። ነገር ግን የስለላ ማዕከሉ የጥቃት ዒላማ ስለመሆኑ የሚያረጋገጥ ምልክት እንደሌለ የዜና ወኪሉ ሮይተርስ ዘግቧል።የአሜሪካው ጋዜጣ ዋሽንግተን ፖስት በበኩሉ፤ ጥቃቱ የተወሰነውን የኤምባሲውን ጣሪያ “ማፍረሱን” እንዲሁም የሕንጻው ውስጥ በጭስ “መበከሉን” የሚገልጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማስጠንቀቂያ መልዕክት ማግኘቱን አስነብቧል።በተጨማሪም ኤምባሲው “መዋቅራዊ ጉዳት” እንደደረሰበት እና ሠራተኞች “ባሉበት መጠለላቸውን እንዲቀጥሉ” እንደተነገራቸው የጋዜጣው ዘገባ ያመለክታል።የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ከዚህ ጥቃት መዘገብ በኋላ ባወጣው መግለጫ፤ የአገሪቱን ደኅንነት ለመከላከል እና ነዋሪዎቹ ለመጠበቅ አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።የሳዑዲ ካቢኔ አጋር አገራት ከኢራን ሊሰነዘር ለሚችል ለማንኛውም ጥቃት የሚሰጡትን ምላሽ “ለመደገፍ ሁሉንም አቅሞች ለማንቀሳቀስ ያለውን ዝግጁነት” እንዳረጋገጠ የአገሪቱ የዜና ወኪል ዘገባ አመልክቷል።የሳዑዲ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ፤ ከዋና ከተማዋ ሪያድ በስተደቡብ አቅጣጫ ላይ ሁለት ክሩዝ ሚሳዔሎችን ማክሸፉን እንደተናገረ የዜና ወኪሎቹ ሮይተርስ እና ኤኤፍፒ ዘግበዋል።ይፋዊው የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ በበኩሉ ዘጠኝ ድሮኖች እንዲከሽፉ መደረጋቸውን አስታውቋል።በተጨማሪም ይፋዊው የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ዘጠኝ ድሮኖች መመታታቸውን ዘግቧል። የሳዑዲ ባለሥልጣናት እንዲከሽፉ የተደረጉት ሚሳዔሎች እና ድሮኖች ከየት እንደተተኮሱ አልገለጹም።ያጋሩ, ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኝ የሲአይኤ ጣቢያ በድሮን መመታቱ ተዘገበ - 3 መጋቢት 2026አሜሪካ ኢራን ውስጥ ከ1,700 በላይ ዒላማዎችን መምታቷን አስታወቀች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በባሕረ ሰላጤው ለጥቃት የተሰማራ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብቅዳሜ ዕለት በኢራን ላይ በተከፈተው ጥቃት በሦስት ቀናት ውስጥ ከ1,700 በላይ ዒላማዎችን ኢራን ውስጥ መምታቱን የአሜሪካ ሠራዊት ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) ያወጣው መረጃ አመለከተ።በጥቃቶቹ ዒላማ ከተደረጉት ስፍራች መካከል የሚሳዔል ማስወንጨፊያዎች፣ የባሕር ኃይል መርከቦች፣ ባሕር ሰርጓጅ መርከቦች እና የመቆጣጠሪያ ማዕከላት ይገኙባቸዋል።ማዕከላዊ ዕዙ ጨምሮም ለእነዚህ ጥቃቶች በርካታ ተዋጊ ጄቶችን ጨምሮ የጦር አውሮፕላኖች፣ ሚሳዔሎች እና የጦር መርከቦች ጥቅም ላይ ውለዋል።መረጃው በ72 ሰዓታት ውስጥ በኢራን ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ዝርዝር ያወጣ ሲሆን፣ በቅድሚያ ዒላማ የተደረጉት “ለዘመቻው እንቅፋት የሚሆኑ ስፍራዎች” እንደሆኑ ተጠቅሷል።ያጋሩ, አሜሪካ ኢራን ውስጥ ከ1,700 በላይ ዒላማዎችን መምታቷን አስታወቀች - 3 መጋቢት 2026
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የሄዝቦላህ ተዋጊዎችእስራኤል ከአሜሪካ ጋር በመቀናጀት በኢራን ላይ ጥቃት በከፈተችበት ዕለት ድንበር በምትጎራበታት ሊባኖስ ውስጥ በሚገኘው የኢራን አጋር በሆነው ሄዝቦላህ ላይም ጥቃት ከፍታለች።በጥቃቱ የቡድኑን የደኅንነት ኃላፊ እና ሌሎች አባላቱን መግደሏን የገለጸች ሲሆን፣ ሄዝቦላህም በአጸፋው በሰሜናዊ እስራኤል ላይ ሮኬቶችን ተኩሷል።በሄዝቦላህ ዳፋ በእስራኤል የሚፈጸመው ጥቃት ያሰጋው የሊባኖስ መንግሥትም ቡድኑ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ማገዱን አስታውቋል።ለመሆኑ በመካከለኛው ምሥራቅ ኃያል የሚባለው እና ለእስራኤል ዋነኛ የራስ ምታት የሆነው እንዲሁም በዋነኛ ባላንጣዋ ኢራን የሚደገፈው የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ ማነው?ሙሉውን ዘገባ እዚህ ያንብቡ፡ በእስራኤል ጥቃት የተከፈተበት የኢራን አጋር የሆነው ሄዝቦላህ ማን ነው?ያጋሩ, - 3 መጋቢት 2026አባታቸው፣ ሚስታቸው እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው የተገደሉባቸው የኻሜኒ ልጅ
የፎቶው ባለመብት,Isnaየምስሉ መግለጫ,የአያቶላ ኻሜኒ ሥልጣን ወራሽ ይሆናሉ የሚባሉት ልጃቸው ሞጅታባ ኻሜኒባለፈው ቅዳሜ የተገደሉት የኢራን ጠቅላይ መሪ ሥልጣን ተረካቢ ይሆናሉ የተባሉት ልጃቸው ሞጅታባ ኻሜኒ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው በደኅና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተዘገበ።ሞጅታባ ቅዳሜ ዕለት በተፈጸመው የእስራኤል እና የአሜሪካ ጥቃት አባታቸውን፣ የእንጀራ እናታቸውን፣ ሚስታቸውን፣ እህታቸውን፣ የእህታቸውን ባል እና ሌሎችም የቅርብ የቤተሰብ አባሎቻቸው ተገድለውባቸዋል።ሜህር የተባለው የኢራን ዜና ወኪል እንዳለው ሞጅታባ ኻሜኒ “በአሁኑ ጊዜ የተሰዉ የቤተሰብ አባሎቻቸውን ጉዳይ በመከታተል፣ በማማከር እና የአገሪቱን ጠቃሚ ጉዳዮችን በማከናወን ላይ ናቸው።”ከአራት ቀናት በፊት የአገሪቱ ጠቅላይ መሪ ቤት እና ጽሕፈት ቤታቸው ላይ በተፈጸመ ጥቃት አባታቸው ሲገደሉ፤ የእንጀራ እናታቸው ማንሱሬህ ኾጃስትህ ባግህርዛዴህ ደግሞ በጥቃቱ ክፉኛ ተጎድተው ኮማ ውስጥ ከቆዩ በኋላ ሕይወታቸው አልፏል።እንዲሁም ሚስታቸው ዛሃራ ሃዳድ አዴል፣ ሴት ልጃቸው፣ የልጃቸው ባል እና የልጃቸው ልጅ በጥቃቱ ተገድለውባቸዋል።የ53 ዓመቱ ሞጅታባ የሟቹ ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ሁለተኛ ልጅ ሲሆኑ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኢራንን የመሪነት ሥልጣን ይይዛሉ ተብለው በተደጋጋሚ ሲነሱ ቆይተዋል።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ከመክፈታቸው ከሳምንት በፊት በወጡ ዘገባዎች ላይ አሜሪካ ጦርነት የምትጀምር ከሆነ ቀዳሚ ዒላማ የምታደርገው የአገሪቱን መሪዎች እንደሚሆን፣ ዋነኞቹ ደግሞ አያቶላህ ኾሜኒ እና ልጃቸው ሞጅታባ ኾሜኒ እንደሆኑ ተጠቅሶ ነበር።ተጨማሪ እዚህ ይመልከቱ፡ በእስራኤል እና በአሜሪካ የወራት ዕቅድ የተገደሉት የኢራኑ ጠቅላይ መሪያጋሩ, አባታቸው፣ ሚስታቸው እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው የተገደሉባቸው የኻሜኒ ልጅ - 3 መጋቢት 2026ጦርነቱ እስከ መቼ ሊቀጥል ይችላል?
የምስሉ መግለጫ,በተለያዩ አገራት ውስጥ የተፈጸሙ ጥቃቶችየኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ አሜሪካ እና እስራኤል በጋራ በፈጸሙት ጥቃት መገደላቸውን ተከትሎ በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት እየተስፋፋ ነው።ኢራን በበኩሏ በቀጣናው ወደሚገኙ አገራት ሚሳዔሎችን እና ድሮኖችን ተጠቅማ ጥቃት መፈጸም ጀምራለች።በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የዓለማችን ዋነኛ የነዳጅ ማውጫ፣ ማጣሪያ እና ማስተለላፊያ ተቋማት እንዲሁም የባሕር መስመሮች የኢራን ጥቃት ዒላማ በመሆናቸው መስተጓጎል ገጥሟል።አሁን እየተነሳ ያለው ጥያቄ ጦርነቱ ምን ያህል ጊዜ ሊወስድ ይችላል? የሚለው ሆኗል።አሜሪካ እና አስራኤል ያቀዱትን እስከሚያሳኩ እንደሚቀጥሉ እየገለጹ ሲሆን፣ ኢራን ደግሞ የተፈጸመባትን ጥቃት በመቀልበስ ጠላቶቿን ዋጋ እንደምታስከፍል እየዛተች እና የአጸፋ እርምጃም እየወሰደችው ነው።ለመሆኑ ጦርነቱ እስከመቼ ሊቆይ ይችል? የሚለውን ለመረዳት ዝርዝሩን እዚህ ያንብቡ፦ ጦርነቱ ለምን ያህል ጊዜ ሊካሄድ ይችላል?ያጋሩ, ጦርነቱ እስከ መቼ ሊቀጥል ይችላል? - 3 መጋቢት 2026የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት የምግብ ዋጋን እንደሚያንር ተገለጸበመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ የነዳጅ ዋጋ ከመጨመሩ ባሻገር የምግብ ዋጋም ሊንር እንደሚችል ተጠቆመ።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን የከፈቱትን ጥቃት ተከትሎ ኢራን በባሕረ ሰላጤው አገራት ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰድ መቀጠሏ ዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ጫና አሳድሯል።ይህም በሰብል እህሎች ምርት እንዲሁም ዝውውር ላይ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ባለሙያዎች ይገልጻሉ።የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት የበቆሎ፣ የስንዴ እና የሩዝ ዋጋ እንዲንር ያደርጋል። በሌላ በኩል ማዳበሪያ ለመሥራት የሚውለው ኬሚካል (ዩሪያ) እጥረት ሊከሰት እንደሚችል ባለሙያዎች ገልጸዋል።ከዩሪያ ምርት አንድ ሦስተኛው የሚዘዋወረው በባሕር ላይ ነው።ከማዳበሪያ አምራች ድርጅቶች ሁለተኛ ትልቁ የሆነው ‘ያራ’ ኃላፊ የሆኑት ስቬን ቶሬ ሆልስተር “አንዳንድ የሰብል ዓይነቶች ምርታቸው 50% ሊቀንስ ይችላል” ብለዋል።የሆርሙዝ ሰርጥ የተዘጋበት ጊዜ አርሶ አደሮች ማዳበሪያ የሚፈልጉበት ወቅት መሆኑ ደግሞ ችግሩን እንደሚያባብሰውም አክለዋል።ያጋሩ, የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት የምግብ ዋጋን እንደሚያንር ተገለጸ
- 3 መጋቢት 2026“አሁን ከአሜሪካ ጋር መደራደር ውጤታማነቱ አጠራጣሪ ነው”- ኢራን
የፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,በተባበሩት መንግሥታት የኢራን አምባሳደር አሊ ባህሬኒበተባበሩት መንግሥታት የኢራን አምባሳደር የሆኑት አሊ ባህሬኒ፤ ከአሜሪካ ጋር አሁን ላይ ድርድር ማድረግ “ውጤታማነቱ አጠራጣሪ ነው” አሉ።ቀደም ሲል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የኢራን ባለሥልጣናት ከአሜሪካ ጋር የመነጋገር ፍላጎት እንዳላቸው፤ ነገር ግን ጊዜው እንዳለፈባቸው እንደነገሯቸው ገልጸዋል።የኢራኑ አምባሳደር በበኩላቸው “ከአሜሪካ ጋር ድርድር ማድረግ ውጤታማነቱ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ አለን” ማለታቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት የኢራን ወሳኝ ተቋማት እና መሪዎች መመታታቸውን ጠቅሰው “ለንግግር ጊዜው አልፏል” ማለታቸው ይታወሳል።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት መክፈታቸውን ተከትሎ ኢራን የአጸፋ እርምጃ መውሰዷን ቀጥላለች።የኢራን እስላማዊው አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄነራል አሊሞሐማድ ናኢም፤ በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ “የሲኦል በሮች ይከፈታሉ” ብለው ዝተዋል።ያጋሩ, “አሁን ከአሜሪካ ጋር መደራደር ውጤታማነቱ አጠራጣሪ ነው”- ኢራን - 3 መጋቢት 2026ኢራን፤ በኩዌት ወታደራዊ ሰፈር በፈጸመችው ጥቃት ስድስት የአሜሪካ ወታደሮች ተገደሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን እሑድ ዕለት በኩዌት በሚገኝ የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈር ላይ በፈጸመችው ጥቃት ስድስት አሜሪካውያን ወታደሮች መገደላቸው ተረጋገጠ።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ ሦስት ወታደሮች መሞታቸውን አስታውቆ ነበር።ተጎድቶ የነበረ ወታደር ከሞተ እና ሁለት ተጨማሪ ወታደሮች አስከሬናቸው ከፍርስራሽ ሥር ከተገኘ በኋላ የሟቾች ቁጥር ስድስት ደርሷል።የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግዜት እንደተናገሩት፤ ኢራን በኩዌት በሚገኝ የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈር ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰንዝራለች።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት ከከፈቱ ወዲህ በኩዌት የተገደሉት ስድስት አሜሪካውያን ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።“ኃይለኛ መሣሪያ የታክቲክ ኦፕሬሽን ማዕከል ላይ ተተኩሷል” ሲሉ የመከላከያ ሚስሩ ተናግረዋል።የቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ ያነጋገራቸው የአሜሪካ ወታደራዊ ባለሥልጣት እንደገለጹት፤ ወታደሮቹ በኩዌት ጊዜያዊ ቢሮ ውስጥ ነበሩ።በባሕረ ሰላጤው አገራት ወታደራዊ ሰፈሮች ያሏት አሜሪካ በኩዌትን 13,000 ወታደሮች አስፍራለች።ኢራን እየወሰደች ባለችው የአጸፋ እርምጃ ባህሬን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኦማን እና ኳታር ላይ ጥቃት ፈጽማለች።ያጋሩ, ኢራን፤ በኩዌት ወታደራዊ ሰፈር በፈጸመችው ጥቃት ስድስት የአሜሪካ ወታደሮች ተገደሉ - 3 መጋቢት 2026“ኢራኖች መነጋገር ቢፈልጉም፣ እኔ ‘በጣም ዘገያችሁ!’ አልኳቸው”- ፕሬዝዳንት ትራምፕ
የፎቶው ባለመብት,Reutersፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የኢራን ባለሥልጣናት ከአሜሪካ ጋር የመነጋገር ፍላጎት እንዳላቸው፤ ነገር ግን ጊዜው እንዳለፈባቸው እንደነገሯቸው ገለጹ።ፕሬዝዳንት ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት የኢራን ወሳኝ ተቋማት እና መሪዎች መመታታቸውን ጠቅሰው ነው ለንግግር ጊዜው እንዳለፈ የጻፉት።”የአየር መከላከያቸው፣ የአየር እና የባሕር ኃይላቸው እንዲሁም አመራራቸው በሙሉ የሉም” ሲሉ ነው ፕሬዝዳንቱ የጻፉት።ፕሬዝዳንቱ ይህንን ጽሑፍ ዋሽንግተን ፖስት ላይ ከወጣ “የትራምፕ መርኅ መወለድ” በሚል ርዕስ ከወጣ ጽሑፍ ሊንክ ጋር አያይዘው ነው ያሰፈሩት።”እነሱ መነጋገር ፈልገው ነበር፤ እኔ ግን ‘በጣም ዘገየ!’ አልኳቸው” ሲሉ ጽፈዋል።ያጋሩ, “ኢራኖች መነጋገር ቢፈልጉም፣ እኔ ‘በጣም ዘገያችሁ!’ አልኳቸው”- ፕሬዝዳንት ትራምፕ - 3 መጋቢት 2026በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ “የሲኦል በሮች ይከፈታሉ” – የኢራን አብዮታዊ ዘብ
የፎቶው ባለመብት,Tasnim News Agencyየምስሉ መግለጫ,ብርጋዴር ጄነራል አሊሞሐማድ ናኢምየኢራን መንግሥት ዋነኛው ወታደራዊ ኃይል እስላማዊው አብዮታዊ ዘብ በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ “የሲኦል በሮች ይከፈታሉ” ሲል ዛተ።መሪው ቴህራን ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት የተገደሉበት የአብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄነራል አሊሞሐማድ ናኢም “ጠላት” ባሏቸው በእስራኤል እና በአሜሪካ ላይ ሠራዊታቸው ቀጣይነት ያለው ጥቃት እንደሚፈጽም ተናግረዋል።ጄነራሉ ታስኒም ለተባለው የአገሪቱ ዜና ወኪል በሰጡት ቃል ኢራን ለተከፈተባት ጥቃት በታጠቀቻቸው ዘመናዊ ሚሳዔሎች “የሲኦል በሮች በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ይከፈታሉ” ብለዋል።አራተኛ ቀኑን በያዘው እና ኢራን ለተፈጸመባት ጥቃት በእስራኤል እንዲሁም በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ በሚገኙ የአሜሪካ ወዳጅ አገራት ላይ የምትፈጽመውን የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃቶችን ቀጥላለች።አብዮታዊ ዘቡም አዲስ በተሾሙለት አዛዡ አሕመድ ቫሂዲ መሪነት ተልዕኮውን በሙሉ ኃይሉ ያለማቋረጥ በመቀጠል ጠላቶቹን እንደሚበቀል ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።በአሜሪካ እና በእስራኤል ዋነኛ ዒላማ ከተደረጉት የኢራን ወታደራዊ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው አብዮታዊው ዘብ አዛዦች እና አባላት የተገደሉባቸውን “ሰማዕታቶች ደም” በመበቀል “ጠላቶቻችንን አሳፋሪ ሽንፈት እናከናንባቸዋለን” ብለዋል ብ/ጄነራል አሊሞሐማድ።ያጋሩ, በአሜሪካ እና በእስራኤል ላይ “የሲኦል በሮች ይከፈታሉ” – የኢራን አብዮታዊ ዘብ - 3 መጋቢት 2026እስራኤል በኢራን ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ላይ ጥቃት ፈጸመች፤ እስካሁን 787 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ጥቃት የተፈጸመበት ጋንዲ ሆስፒታልየእስራኤል መከላከያ ኃይል የቴህራን አመራሮች በሚገኙበት አካባቢ በፈጸመው የአየር ድብደባ የፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ላይ ጉዳት ማድረሱን አስታወቀ።የእስራኤል መከላከያ በቴግራም ገጽ ላይ ባወጣው መግለጫ፤ በፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት እና በኢራን ከፍተኛ ብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ላይ “በርካታ ድብደባ” መፈጸሙን አስታውቋል።ወታደራዊ የሥልጠና ተቋማት እና ሌሎችም “የኢራን መንግሥት ቁልፍ መሠረተ ልማቶች” ላይ ጥቃት መድረሱም ተገልጿል።በእስራኤል እና በአሜሪካ ጥቃት የተገደሉት የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ሥራቸውን ያከናውኑ የነበረው አሁን ድብደባ በደረሰበት ቅጥር ጊቢ ውስጥ እንደነበር የእስራኤል መከላከያ አመልክቷል።በተያያዘም፤ እስራኤል እና አሜሪካ ኢራን ላይ ጥቃት መፈጸም ከጀመሩበት ቀን አንስቶ ቢያንስ 787 ሰዎች መገደላቸውን የኢራን ቀይ ጨረቃ ማኅበር አስታውቋል።‘ሂውማን ራይትስ አክቲቪስትስ ኢን ኢራን’ የተባለው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳለው 176 ሕጻናትን ጨምሮ 742 ሰዎች ተገድለዋል።የኢራን ምክር ቤት የጤና ኮሚሽን አባል የሆኑት ፋጢማ ሞሐመድባጊ እንደተናገሩት፤ ትናንት ሰኞ ዘጠኝ ሆስፒታሎች በእስራኤል እና አሜሪካ ጥቃት ዒላማ ተደርገዋል።የእስራኤል መከላከያ በበኩሉ በቴህራን የጋንዲ ሆስፒታል ላይ ጥቃት ፈጽሟል የሚለውን ክስ አስተባብሎ “ሆስፒታሉ ዒላማ አልተደረገም” ብሏል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ እስራኤል እና አሜሪካ በዚህ ሆስፒታል ላይ አነጣጥረው ጥቃት ማድረሳቸውን አስታውቋል።ያጋሩ, እስራኤል በኢራን ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ላይ ጥቃት ፈጸመች፤ እስካሁን 787 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ - 3 መጋቢት 2026በኢራን የሟቾች ቁጥር 787 መድረሱን ቀይ ጨረቃ አስታወቀ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesእስራኤል እና አሜሪካ በጥምረት ባለፈው ቅዳሜ ጥቃት መፈጸም ከጀመሩ ወዲህ የሞቱት ኢራናውያን ቁጥር 787 መድረሳቸውን የቀይ ጨረቃ አስታወቀ።በሌላ በኩል መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ቡድን ያወጣው መረጃ ደግሞ 176 ሕጻናትን ጨምሮ 742 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ይፋ አድርጓል።ፋተሜህ ሞሃማድቤጊ የተባሉ የኢራን የፓርላማ አባል እንደገለጹት ደግሞ የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃት በኢራን ውስጥ ዘጠኝ ሆስፒታሎችን ዒላማ አድርገዋል።የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቴህራን ውስጥ የጋንዲ ሆስፒታልን ዒላማ ስለማድረጉ ተጠይቆ “ዒላማችን ሆስፒታሉ አልነበረም” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆስፒታሉ በእስራኤል ጥቃት ዒላማ መሆኑን ገልጿል።ያጋሩ, በኢራን የሟቾች ቁጥር 787 መድረሱን ቀይ ጨረቃ አስታወቀ - 3 መጋቢት 2026እስራኤል በቤይሩት በፈጸመችው ጥቃት የደረሰውን ውድመት የሚያሳይ ምስልእስራኤል ዛሬ በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በቤይሩት እና ቴህራን ጥቃት መፈጸሟን ቀጥላለች።እስራኤል በሁለቱም አገራት “ወታደራዊ ዒላማዎች” ናቸው ባለቻቸው ስፍራዎች የአየር ድብደባ ማካሄዷን ተናግራለች።ሊባኖስ ውስጥ በኢራን የሚደገፈው ሔዝቦላህ ዒላማዎች ናቸው ባለቻቸው ስፍራዎች ነው ጥቃቶቹን የፈጸመችው።ቤይሩት ውስጥ የተፈጸሙት ጥቃቶች ያደረሷቸውን ጉዳቶች የሚያሳዩ ምስሎች እነሆ።
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በደቡባዊ ቤይሩት የእስራኤል ጦር በፈጸመው ጥቃት የወደመ ሕንጻ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በደቡባዊ ቤይሩት በጥቃቱ የወደመን ስፍራ የሚመለከት ሰው
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በቤይሩት በመኖሪያ ስፍራ የተፈጸመን ጥቃት ተከትሎ የተቀሰቀሰ የእሳት ቃጠሎን የሚያጠፉ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችያጋሩ, እስራኤል በቤይሩት በፈጸመችው ጥቃት የደረሰውን ውድመት የሚያሳይ ምስል
