ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት አያቶላህ አሊ ኻሜኒ የተገደሉባት ኢራን በቀጣይ ማንን በጠቅላይ መሪነት ትመርጣለች የሚለው ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው ለመገናኛ ብዙኃን ተናገሩ። የአያቶላህ ኻሜኒን ፖሊሲዎችን የሚያስቀጥል አዲስ መሪ እንደማይፈልጉ ለአክሲዮስ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህ አይነት ሰው ወደ ሥልጣኑ የሚመጣ ከሆነ “በአምስት ዓመት ውስጥ” አሜሪካ ተመልሳ ወደ ጦርነት እንድትገባ እንደሚያስገድዳት ጠቅሰዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 3 ደቂቃዎች በፊትየኢራን ጦርነት የሩሲያ ነዳጅ ተፈላጊነትን ጨመሩን የአገሪቱ መንግሥት ገለጸየክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔሽኮቭየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት የሩሲያ የኢነርጂ ምርቶች ላይ ያለውን ፍላጎት እንደጨመረ የአገሪቱ መንግሥት ገለጸ።የሩሲያን ነዳጅ የሚገዙት እንደ ቻይና እና ሕንድ ያሉ አገራት ግዢ የሚፈጽሙት በብሔራዊ ጥቅማቸው ተመርተው እንደሆነ መናገሩንም ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።ጦርነቱ መነሳቱን ተከትሎ ኢራን ወሳኝ የነዳጅ መተላለፊያ የሆነውን የሆርሙዝ ሰርጥ ዘግታለች። ይህ አገራት የነዳጅ እና የተጣራ የተፈጥሮ ጋዝ እንዳያገኙ ያደረገ ሲሆን፣ የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምርም ምክንያት ሆኗል።የነዳጅ ገበያውን ለማረጋጋት ጥረት እያደረገች ያለችው አሜሪካ ደግሞ ሕንድ የሩሲያን ነዳጅ እንዳትገዛ ጥላው የነበረውን ዕገዳ ለ30 ቀናት አንስታለች። ይህ ጊዜያዊ ውሳኔ ተግባራዊ የሚሆነው ቀድሞውኑም ጉዞ ከጀመረ በኋላ ባሕር ላይ መንቀሳቀስ ባልቻለ የሩሲያ ነዳጅ ላይ እንደሆነም አስታውቃለች።የሩሲያው ቤተ መንግሥት ክሬምሊን ቃል አቀባይ የሆኑት ዲሜትሪ ፔሽኮቭ፤ “ኢራን ውስጥ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ ለሩሲያ የነዳጅ ሀብቶች ያለው ፍላጎት በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መሆኑን ተመልክተናል” ሲሉ ለጋዜጠኖች ተናግረዋል።አክለውም “የሩሲያ ታማኝ የነዳጅ እና ጋዝ አቅራቢ ነች፤ ሆናም ቀጥላለች” ማለታቸውን የዜና ወኪሉ ዘገባ ያሳያል።ቃል አቀባዩ፤ ሩሲያ “ውል የተፈጸመባቸውን [ምርቶች] እያቀረበች እንደምትቀጥል የማረጋገጥ አቅም” እንዳላትም ገልጸዋል።የአሜሪካን ዕገዳ ተከትሎ ሕንድ ምን ያህል መጠን ያለው ነዳጅ ለመግዛት ጥያቄ እንዳቀረበች ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።ያጋሩ, የኢራን ጦርነት የሩሲያ ነዳጅ ተፈላጊነትን ጨመሩን የአገሪቱ መንግሥት ገለጸ
  2. ከ 54 ደቂቃዎች በፊትኢራን ወደ እስራኤል ሚሳዔል ካስወነጨፈች በኋላ ቴል አቪቭ ውስጥ ፍንዳታ ተሰማከቀናት በፊት ኢራን በአሽኬሎን የከፈተችው ጥቃት በእስራኤል የአየር መከላከያ ስርዓት ከሽፏልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ከቀናት በፊት ኢራን በአሽኬሎን የከፈተችው ጥቃት በእስራኤል የአየር መከላከያ ስርዓት ከሽፏልየእስራኤል ጦር ከኢራን የተወነጨፈ ሚሳዔል ወደ አገሪቱ እየተምዘገዘገ መሆኑን ከገለጸ በኋላ ቴል አቪቭ ውስጥ የፍንዳታ ድምጽ መሰማቱን የዜና ወኪሎቹ ሮይተርስ እና ኤፒ ዘገቡ።የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ዘብ በመሃል ቴልአቪቭ የሚገኙ ስፍራዎችን ዒላማ በማድረግ አዲስ ዙር የሚሳዔል እና ድሮን የጥቃት ዘመቻ መክፈቱን ገልጿል።የሮይተርስ ዘገባ እንደሚያመለክተው፤ አብዮታዊ ዘቡ ‘ኦፕሬሽን ትሩ ፕሮሚስ 4’ ሲል የጠራው ዘመቻ አካል የሆኑ የኼይባር ሚሳዔሎችን ወደ ቴል አቪቭ ማስወንጨፉን ገልጿል።የእስራኤል ጦር በበኩሉ ከኢራን የተተኮሱ ሚሳዔሎች ወደ አገሪቱ እየመጡ መሆኑ እንደለየ እና ለማክሸፍ እየሰራ መሆኑን አስታውቆ ነበር።ጦሩ በቴሌግራም ገጹ ባወጣው መግለጫ፤ “የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ከኢራን ወደ የእስራኤል ግዛት የተወነጨፉ ሚሳዔሎች መኖራቸውን ከአጭር ጊዜ በፊት ለይቷል” ብሏል። “የመከላከያ ስርዓቶች ስጋቱን ለማክሸፍ እየሰሩ” እንደሆነም ገልጿል።የጥቃቱ ስጋት ባለባቸው ስፍራዎች ወደሚገኙ ነዋሪዎች ስልክ “የቅድመ ማስጠንቀቂያ መመሪያ” እንደተላከም አክሏል።የዜና ወኪሎቹ ቴል አቪቭ ውስጥ የፍንዳታ ድምጽ መሰማቱን የዘገቡት የእስራኤል ጦር ይህንን ካስታወቀ በኋላ ነው።ወደ እስራኤል በተወነጨፉት ሚሳዔሎች ምክንያት የደረሰ ጉዳት አለመመዝገቡን የአገሪቱ አደጋ ጊዜ አገልግሎት አስታውቋል። የአደጋ አገልግሎቱ ኃላፊ “በዚህ ደረጃ ምንም የጉዳት መረጃ አልደረሰንም” ብለዋል።የአገሪቱ ጦርም ኋላ ላይ ባወጣው መረጃ ወደ መጠለያ ስፍራዎች የገቡ ዜጎች መውጣት እንደሚችሉ ገልጿል።ያጋሩ, ኢራን ወደ እስራኤል ሚሳዔል ካስወነጨፈች በኋላ ቴል አቪቭ ውስጥ ፍንዳታ ተሰማ
  3. ከ 1 ሰአት በፊትዩናይትድ ኪንግደም ከኢራን ጋር በተያያዘ አራት ሰዎች በቁጥጥር ስር አዋለችየዩናይትድ ኪንግደም ሜትሮፖሊታን ፖሊስ ምልክትየፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየዩናይትድ ኪንግደም ሜትሮፖሊታን ፖሊስ፤ ከኢራን ጋር በተያያዘ በሚያደርገው የፀረ ሽብር ምርመራ አማካኝነት ለንደን ከተማ ውስጥ አራት ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።አንድ ኢራናዊ እንዲሁም ሦስት የብሪታኒያ እና ኢራን ጥምር ዜግነት ያላቸው ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት፤ የውጭ የስለላ ድርጅትን እያገዙ ነው በሚል ተጠርጥረው እንደሆነ ተገልጿል።እንደ ፖሊስ ገለጻ፤ ግለሰቦቹ፤ ለንደን ውስጥ የሚገኙ ከአይሁድ ማኅበረሰብ ጋር የተያያዙ የተለያዩ ስፍራዎች እና ሰዎች ላይ ክትትል በማድረግ ተጠርጥረዋል።ዋትፎርድ፣ ባርኔት እና ዌምብሌይ ውስጥ የሚደረጉት አሰሳዎች እንደቀጠሉም ፖሊስ አክሏል።የ40 እና 55 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የታሰሩት ባርኔት ውስጥ እንደሆነ ተገልጿል።ሃሮው ውስጥ ደግሞ የ52 እና 22 ዓመቶቹ ተጠርጣሪዎች ታስረዋል። ወንጀለኛን በማገዝ የተጠረጠሩ ሌሎች ስድስት ግለሰቦችም በዚሁ ስፍራው በቁጥጥር ስር ውለዋል ተብሏል።አራቱ ግለሰቦች የታሰሩት በአገሪቱ የብሔራዊ ደኅንነት ሕግ አማካንኝነት እንደሆነ ተገልጿል። በአውሮፓውያኑ 2023 የወጣው ይህ ድንጋጌ የስለላ ሕጎችን እና ፀረ የውጭ ጣልቃ ገብነት ሥራዎችን ለማዘመን የወጣ ነው።የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር፤ ኢራን በአሜሪካ እና እስራኤል ከተከፈተባት ጥቃት በኋላ የወሰደችውን የአጸፋ እርምጃ ተቃውመዋል። “በቀጣናው የሚገኙ አጋሮች” ላይ የተከፈተ ነው ሲሉም ኮንነዋል።ያጋሩ, ዩናይትድ ኪንግደም ከኢራን ጋር በተያያዘ አራት ሰዎች በቁጥጥር ስር አዋለች
  4. ከ 2 ሰአት በፊትአሜሪካ ከባድ የተባሉ ጥቃቶችን ኢራን ላይ መፈጸሟን አስታወቀችኢራን ውስጥ የተፈጸመ ጥቃትየፎቶው ባለመብት,EPAአሜሪካ ባለፉት 72 ሰዓታት ኢራን ውስጥ በሚገኙ 200 ገደማ ዒላማዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን፤ በዚህም የቴህራንን የድሮን እና ሚሳዔል አቅም በከፍተኛ ደረጃ ማዳከሟን የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ብራድ ኩፐር ተናገሩ።የአሜሪካ ጦር በአሁኑ ሰዓት የኢራንን ሚሳዔል የማምረት አቅም ለማውደም እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።ዋና አዛዡ፤ አሜሪካ በኢራን የሚሳዔል ማስወንጨፊያዎች እና መሠረተ ልማት ላይ እያካሄደች ስላለው ወታደራዊ ዘመቻ መግለጫ ሰጥተዋል። “ባለፉት 72 ሰዓታት ብቻ አሜሪካ ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች ኢራን ውስጥ በጥልቀት ገብተው 200 ገደማ ዒላማዎችን አጥቅተዋል” ብለዋል“ባለፈው አንድ ሰዓት ብቻ ቢ-2 ቦንብ ጣዮች ባሕር ላይ የሚገኙ የሚሳዔል ማስወንጨፊያ ስፍራዎችን ዒላማ በማድረግ 900 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ በርካታ ቦንቦችን ጥለዋል” ሲሉ ተናግረዋል።ኩፐር “የኢራን ኤሮስፔስ ዕዝንም ዒላማ አድርገናል። ይህ እርምጃ የኢራንን አሜሪካ ላይ ስጋት የመፍጠር አቅም ያዳክማል” ሲሉም አክለዋል።“ያለፉት 24 ሰዓታት ዘመቻን ስንመለከት ከመጀመሪያው ቀን ጋር ሲነጻጸር የኢራን ባለስቲክ ሚሳዔል ጥቃቶች በ90 በመቶ፤ የድሮን ጥቃቶች ደግሞ በ83 በመቶ ቀንሰዋል” ብለዋል።ከሐሙስ ምሽት አንስቶ ካለፉት ቀናት አንጻር “ከባድ” የተባለ ጥቃት በኢራን የተለያዩ አካባቢዎች እና ዋና ከተማው ቴህራን ውስጥ እየተፈጸመ መሆኑ ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።ቢቢሲ ያነጋገረው አንድ የቴህራን ነዋሪም ከተማው ውስጥ ተከታታይ ፍንዳታዎች እየተሰማ መሆኑን ገልጿል። “ቤታችን በተከታታይ በየአምስት ደቂቃው እየተንቀጠቀጠ ነበር። ትናንት ማታ ከሁሉም የከፋው ምሽት ነበር” ብሏል።ሌላ ነዋሪ ደግሞ “አስከፊ ነበር። በጣም እየደበደቡ ስለነበር ሁሉም መስኮቶች ሲንቀጠቀጡ ነበር” ስትል ሁኔታውን አስረድታለች።በሌላ በኩል ኢራንም በቀጣናው አገራት ላይ ጥቃት መፈጸሟን ቀጥላለች። ባህሬን በሁለት የእንግዳ ማረፊያ እና መኖሪያ ሕንጻዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሙን አስታውቃለች። ሳዑዲ አረቢያም እና ኳታርም በተመሳሳይ ወደ አየር ክልላቸው የገቡ ሚሳዔል እና ድሮኖችን መምታታቸውን ገልጸዋል።የጦር መሣሪያ ክምችት መሟጠጥ የኢራን ግጭት ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል?ያጋሩ, አሜሪካ ከባድ የተባሉ ጥቃቶችን ኢራን ላይ መፈጸሟን አስታወቀች
  5. ከ 3 ሰአት በፊትአሜሪካ፤ ሕንድ ከሩሲያ ነዳጅ እንዳትገዛ የጣለችውን እገዳ አነሳችየሆርሙዝ ሰርጥየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት በመቶዎች የሚቆጠሩ መርከቦች እንዲቆሙ እና የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር አድርጓልየአሜሪካ ግምጃ ቤት፤ ሕንድ በባሕር ላይ ሳይንቀሳቀስ የቆየውን የሩሲያን ነዳጅ እንዳትገዛ ጥሎት ነበረውን ማዕቀብ በጊዜያዊነት አነሳ።ለ30 ቀናት የሚቆየው ይህ ማዕቀብ የማንሳት እርምጃ ነዳጅ ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲገባ እንደሚያደርግ የግምጃ ቤት ሚኒስትሩ ስኮት ቤሴንት ተናግረዋል። “ኢራን የዓለም የኃይል አቅርቦትን እገታ ውስጥ ለማስገባት በምታደርገው ሙከራ የሚመጣውን ጫና ይቀንሳል” ብለዋል።ቤሴንት በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ እንደገለጹት፤ እርምጃው “አጭር ጊዜ ቆይታ” እንዲኖረው የተደረገው “ሆነ ተብሎ” ነው። ማዕቀቡ የተነሳው ቀድሞውኑ በባሕር ላይ ጉዞ ጀምሮ መንቀሳቀስ ላልቻለ ነዳጅ በመሆኑ “ለሩሲያ መንግሥት ጉልህ የሆነ የፋይናንስ ጥቅም አያስገኝም” በማለት ገልጸዋል።ሩሲያ ዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን ተከትሎ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሞስኮ ነዳጅ ሽያጭ ላይ ማዕቀብ ጥለዋል። ይህ እርምጃም ገዢዎች ሌላ አማራጭ እንዲፈልጉ አስገድዷቸዋል።አሜሪካ፤ የሩሲያ የኃይል አቅርቦት ዋና ደንበኛ በሆነችው ሕንድ ላይ በተለየ መልኩ ጫና በማሳደር ሕንድ የሩሲያን ነዳጅ እንዳትገዛ በዚህም ወደ ሞስኮ ገንዘብ እንዳይገባ ለማድረግ ሞክሯል።በሌላ በኩል ቻይና ድፍድፍ ነዳጅ እና ከኳታር የተነሳ የተፈጥሮ ጋዝ የጫኑ መርከቦች በሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ በሰላም እንዲያልፉ ከኢራን ጋር ድርድር እያደረገች መሆኑን ሮይተርስ የዜና ወኪል ስማቸው ያልተጠቀሰ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።ሰባተኛ ቀኑን የያዘውን ጦርነት ዋነኛው የዓለም የነዳጅ እና ጋዝ መተላለፊ የሆነው ወሽመጥ እንዲዘጋ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ መርከቦች እንዲቆሙ አድርጓል። አንድ አምስተኛ የሚሆነው የዓለም ነዳጅ እና ጋዝ የሚተላለፍበት ሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋቱ የኤነርጂ ዋጋ እንዲጨምርም ምክንያት ሆኗል።ሮይተርስ እና ብሎምበርግ ያወጡት ዘገባ እንደሚያሳየው፤ የቻይና እንደሆኑ የተገለጹ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ሐሙስ ዕለት በሰርጡ አልፈዋል። ቢቢሲ ይህንን በተናጠል ማረጋገጥ አልቻለም።የኢራን ነዳጅ ዋነኛ ገዢ የሆነችው ቻይና፤ አሜሪካ እና እስራኤል ቴህራን ላይ የከፈቱትን ጥቃት አውግዛለች።ያጋሩ, አሜሪካ፤ ሕንድ ከሩሲያ ነዳጅ እንዳትገዛ የጣለችውን እገዳ አነሳች
  6. ከ 4 ሰአት በፊትየእስራኤል ጦር በኢራን ላይ የሚያካሂደው “ዘመቻ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ መሸጋገሩን” ገለጸቴህራን ውስጥ የተፈጸመ ጥቃትየፎቶው ባለመብት,EPAየእስራኤል መከላከያ ሠራዊት፤ በኢራን ላይ የሚካሄደው ዘመቻ ወደ “ቀጣዩ ምዕራፍ እየተሸጋገረ” መሆኑን እና የቴህራን “አገዛዝን እና ወታደራዊ አቅምን ከዚህም የበለጠ የመበታተን” እርምጃውን እንደሚገፋበት ገለጸ።አሜሪካ እና እስራኤል በሚፈጽሙት ጥቃት ኢራንን “በስትራቴጂካዊ መንገድ እየነጠሉ” መሆኑን የተናገሩት የእስራኤል ጦር ዋና አዛዥ ሌተናንት ጄነራል ኢያል ዛሚር፤ “ከዚህ ቀደም ባይታየ ደረጃ” እያዳከሟት እንደሆነ ጠቅሰዋል።እስራኤልባለፉት ስድስት ቀናት “ያለ ማቋረጥ” ኢራን ላይ ጥቃት ስትፈጸም መቆየቷን አንስተው፤ “ዘመቻው ባቀድነው ፍጥነት እየሄደ ነው” ብለዋል።ዋና አዛዡ ባወጡት መግለጫ “የአየር የበላይነትን ያረጋገጥንበትን እና የባለስቲክ ሚሳዔል መሠረታቸውን ያዳከምንበትን ድንገተኛ የጥቃት ምዕራፍ ካጠናቀቅን በኋላ፤ አሁን ወደ ቀጣዩ የዘመቻ ምዕራፍ እየተሸጋገርን ነው” ሲሉ ዕቅዳቸውን አስታውቀዋል።”በዚህ ምዕራፍ የኢራንን አገዛዝ እና ወታደራዊ አቅሙን የበለጠ እንበታትናለን። አሁን ይፋ የማላደርጋቸው ተጨማሪ ድንገተኛ እርምጃዎች ወደፊት እንወስዳለን” ሲሉም ጽፈዋል።ወታደራዊ አዛዡ የሊባኖስንም ጉዳይ ባነሱበት በዚህ መግለጫ፤ ሄዝቦላህ ጦርነቱን መቀላቀሉ “ስትራቴጂካዊ ስህተት” እንደሆነ ገልጸዋል። እስራኤል በጦርነት “ግንባርም ሆነ ሊባኖስ ውስጥ በጥልቅ በመግባት በኃይል እያጠቃች” መሆኑን ተናግረዋል።ያጋሩ, የእስራኤል ጦር በኢራን ላይ የሚያካሂደው “ዘመቻ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ መሸጋገሩን” ገለጸ
  7. ከ 4 ሰአት በፊትአሜሪካ በኩዌት የሚገኘው ኤምባሲዋን ዘግታ ሠራተኞቿን አስወጣችሰኞ ዕለት ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ በኤምባሲው አቅራቢያ እሳት ተያይዞ ታይቷልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ሰኞ ዕለት ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ በኤምባሲው አቅራቢያ እሳት ተያይዞ ታይቷልበኩዌት ዋና ከተማ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሥራ እንዲያቆም መደረጉን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።ከዚህ አስቀድሞ በኤምባሲው የሚገኙ ሠራተኞች በሙሉ እንዲወጡ ትዕዛዝ መተላለፉን በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ዘግቦ ነበር።ሠራተኞቹን የማስወጣት ተግባር የተከናወነው ሐሙስ ሌሊት ለአርብ አጥቢያ ነው። የኤምባሲው ሠራተኞች መረጃዎችን በሙሉ እንዲያጠፉ እና ሚስጥራዊ ሰነዶችን የያዙ ሰርቨሮችን እንዲያወድሙ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ሁለት ባለሥልጣናት ለሲቢኤስ ተናግረዋል።ሠራተኞችን የማስወጣት ትዕዛዝ የተሰጠው፤ የኩዌት ጦር ወደ አገሪቱ አየር ክልል ሊገባ የነበረን ሚሳዔል በአየር መከላከያ ስርዓቱ እንዳከሸፈ ከገለጸ በኋላ ነው።የኩዌት ጦር ቃል አቀባይ በኤክስ ገጻቸው በለጠፉት መግለጫ፤ “የማክሸፍ ዘመቻው የተወሰኑ ስብርባሪዎች ወደ መሬት እንዲወድቁ አድርጓል፤ ይህም በተሽከርካሪዎች ላይ የተወሰነ ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል። በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አልተመዘገበም” ብለዋል።እነዚህ መረጃዎች ከተሰሙ በኋላ መግለጫ ያወጣው አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሠራተኞቹ ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ አስታውቋል። በውጭ አገራት የሚገኙ አሜሪካውያን ደኅንነት አሁንም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነ ጠቅሷል።ባለፈው እሁድ ዕለት በኩዌት ፖርት ሹኢባ ወደብ ላይ በደረሰ የአየር ጥቃት ስድስት የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸው ይታወሳል። ጥቃቱ የደረሰው “በሰው አልባ የአውሮፕላን ሥርዓት” እንደሆነ የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ አስታውቋል።ሰኞ ዕለት ደግሞ በኤምባሲው አቅራቢያ ጥቃት ተፈጽሞ የነበረ ሲሆን አካባቢው በእሳት ተያይዞ ታይቷል።ያጋሩ, አሜሪካ በኩዌት የሚገኘው ኤምባሲዋን ዘግታ ሠራተኞቿን አስወጣች
  8. ከ 5 ሰአት በፊትኢራን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በከፍተኛ መጠን እንደሚጨምር የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ተናገሩየአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴትየፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት፤ በኢራን እና በዋና ከተማዋ ቴህራን ላይ የሚፈጸመው “የጥቃት ኃይል በከፍተኛ መጠን ሊጨምር” መሆኑን ተናገሩ።አሜሪካ እና እስራኤል ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ በኢራን ላይ የከፈቱትን ጥቃት በተመለከተ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ የሰጡት መከላከያ ሚኒስትሩ ሄግሴት፤ የማጥቃት ዘመቻው “በቆራጥነት እያደገ” መሆኑን ገልጸዋል።“ኢራን ይህንን [ጥቃት] መቀጠል አንችልም ብላ ተስፋ ታደርጋለች፤ ይህም እጅግ መጥፎ ስሌት ነው” ብለዋል። አሜሪካ “ምንም የተተኳሽ እጥረት” እንደሌለባት እና የማጥቃት ዘመቻውን እስከፈለገች ድረስ ማስቀጥል እንደምትችል ተናግረዋል።“ገና መዋጋት መጀመራችን ነው፤ የምንዋጋውም በቆራጥነት ነው” ሲሉም ተደምጠዋል።ዩናይትድ ኪንግደም ከጅምሩ የአሜሪካ አየር ኃይል ኢራን ላይ ለሚፈጽመው ጥቃት የጦር ሰፈሯ እንዲጠቀም አለመፍቀዷን የተቹች ሄግሴት፤ አሁን ግን ብሪታኒያ መስማማቷ ዘመቻውን ለማጠናከር እንደሚያግዝ አስረድረተዋል።“ተሳክቶልናል፤ እናም አሁን ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን ለማሰማራት እንደ አንድ መንገድ እየተጠቀምንበት ነው” ያሉት መከላከያ ሚኒስትሩ፤ ይህ እርምጃ ኢራን ላይ ለተከፈተው ወታደራዊ ዘመቻ “ተጨማሪ አቅሞች እና ተጨማሪ የመከላከያ ብቃት” እንደሚያስገኝ እንዲሁም “ተደጋጋሚ የቦምብ ጥቃቶች” ለመፈጸም እንደሚያስችል አብራርተዋል።“በኢራን እና ቴህራን ላይ የሚወርደው የጥቃት ኃይል በከፍተኛ መጠን ሊጨምር ነው” ሲሉም አክለዋል። አሜሪካ እና እስራኤል እያጠቁ ያሉት የኢራን ተቃዋሚዎችን ዒላማ የሚያደርጉትን ኃይሎች እንደሆነም ተናግረዋል።“ይህንን በተፈጸመ ቁጥር እንዲሁም ፍላጎት እና አቅማቸው በተዳከመ መጠን፤ ሕዝቡ በድፍረት እንዲቆም ተጨማሪ ዕድል ይፈጠራል” ብለዋል።ያጋሩ, ኢራን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በከፍተኛ መጠን እንደሚጨምር የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ተናገሩ
  9. ከ 6 ሰአት በፊትፕሬዝዳንት ትራምፕ ቀጣዩን የኢራን መሪ የመምረጥ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እንዳለባቸው ተናገሩፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,EPAፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት አያቶላህ አሊ ኻሜኒ የተገደሉባት ኢራን በቀጣይ ማንን በጠቅላይ መሪነት ትመርጣለች የሚለው ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው ለመገናኛ ብዙኃን ተናገሩ።ትራምፕ ከዜና ምንጮቹ ሮይተርስ እና አክሲዮስ ጋር ባደረጓቸው የተለያዩ ቃለ መጠይቆች፤ ቀጣይ መሪ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቁት የአያቶላህ ኻሜኒ ልጅ ወደ ሥልጣኑ እንዲመጡ እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።ፕሬዝዳንቱ፤ ባለፈው ታህሳስ ላይ ወደ ቬንዙዌላ ገብተው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን ከያዙ በኋላ እንዳደረጉት ሁሉ የኢራን ቀጣይ መሪ የመምረጥ ሂደት ላይ ራሳቸው መሳተፍ እንደሚፈልጉ መናገራቸውን የአሜሪካው የዜና ምንጭ አክሲዮስ ዘግቧል።ከሮይተርስ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ደግሞ “ከኢራን ጋር ሆነን [ቀጣዩን መሪ] መምረጥ ይኖርብናል። ያንን ሰው መምረጥ ይኖርብናል” ብለዋል።ባለፈው ቅዳሜ ሌሊት ጠቅላይ መሪው አያቶላህ አሊ ኻሜኒ መገደላቸውን ከተረጋገጠ በኋላ ቀጣዩ መሪ ማን ይሆናል የሚለው ሲያነጋግር ቆይቷል። የቀድሞው መሪ የቀብር ሥነ ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ቀጣዩ መሪ እንደሚመረጥም ተነግሯል።ሥልጣኑን እንደሚረከቡ ከሚጠበቁት መካከል ስማቸው ተደጋግሞ እየተነሱ ያሉት የቀድሞው አያቶላህ ልጅ ሞጅታባ ኻሜኒ ናቸው። ትራምፕ ከአክሲዮስ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የኻሜኒ ልጅ የጠቅላይ መሪነቱን ሥልጣን እንዲቆናጠጡ እንደማይፈልጉ ተናግረዋል።“ለእኔ የኻሜኒ ልጅ [ሥልጣኑን መረከቡ] ተቀባይነት የለውም። የምንፈልገው ለኢራን ስምምነት እና ሰላምን የሚያመጣ ሰው ነው” ብለዋል።ትራምፕ፤ “ጊዜያቸውን እያባከኑ ነው። የኻሜኒ ልጅ ያንን ያህል [ፖለቲካዊ] ክብደት የለውም። በቬንዙዌላ ከዴልሲ [ሮድሪጌዝ] ጋር እንደነበረው ሁሉ ሹመቱ ውስጥ መሳተፍ አለብኝ” ሲሉም ተናግረዋል።የአያቶላህ ኻሜኒን ፖሊሲዎችን የሚያስቀጥል አዲስ መሪ እንደማይፈልጉ ለአክሲዮስ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህ አይነት ሰው ወደ ሥልጣኑ የሚመጣ ከሆነ “በአምስት ዓመት ውስጥ” አሜሪካ ተመልሳ ወደ ጦርነት እንድትገባ እንደሚያስገድዳት ጠቅሰዋል።ትራምፕ ከሮይተርስ ጋር በነበራቸው ቆይታም በተመሳሳይ “በየአምስት ዓመቱ ተመልሰን ይህንን [ጦርነት] ደጋግመን እንዳናደርግ፤ ኢራንን ወደፊት የሚመራውን ሰው በመምረጥ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እንፈልጋለን። ለሕዝቡ እና ለአገሪቱ ታላቅ የሚሆን ሰው እንፈልጋለን” ብለዋል።የቀድሞውን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ኻሜኒን ለመተካት ቀዳሚ ዕጩነት ሆነው የወጡት ልጃቸው ሞጅታባ፤ ቀጣይ መሪ የመሆን ዕድላቸው አነስተኛ ነው የሚል እምነት እንዳላቸውም አስረድተዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቀጣይ መሪ እንዲሆኑ የማይፈልጓቸው የቀድሞው አያቶላህ ልጅ ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ ሞጅታባ ኻሜኒ፡ ቀጣዩ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሊሆኑ ስለሚችሉት የአያቶላህ ኻሜኒ ልጅ የምናውቀውያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቀጣዩን የኢራን መሪ የመምረጥ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እንዳለባቸው ተናገሩ
  10. 5 መጋቢት 2026የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት በኢራን ተፈጽሟል ላሉት የድሮን ጥቃት ምላሽ እንደሚሰጥ ተናገሩፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአዘርባጃን ዛሬ ጠዋት የኢራን ድሮን አየር ማረፊያዋ ላይ ጥቃት ማደረሱን ከገለጸች በኋላ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ለአጸፋ እርምጃ እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ መስጠታቸውን አስታወቁ።በድሮን ጥቃቱ ሁለት ንጹኃን ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። የኢራን መንግሥት በበከሉ ጥቃቱን እንዳልፈጸመ በመግለጽ ክሱን አስተባብሏል።የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው ኢራን እና አርሜኒያን በምታዋስነው የአዘርባጃኗ ግዛት ናክቺቫን እንደሆነ አገሪቱ መንግሥት ገልጿል።የአዘርባጃን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ “አንድ ድሮን በናክቺቫን ራስ ገዝ ሪፐብሊክ የሚገኘውን የአየር ማረፊያ ተርሚናል ሕንጻ መትቷል፤ ሌላኛው ድሮን ደግሞ በሸካራባድ መንደር በሚገኝ ትምህርት ቤት አቅራቢያ ወድቋል” ብሏል።በዚህ የድሮን ጥቃት የአየር ማረፊያው ሕንፃ እንደተጎዳ እና ሁለት ንጹኃን ሰዎች እንደቆሰሉም ተገልጿል።አዘርባጃን ውስጥ የሚገኙት የኢራን አምባሳደር በክስተቱ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ መጠራታቸውን የገለጸው ሚኒስቴሩ “ለኢራን ጠንካራ ተቃውሞ ይገለጻል፤ የተቃውሞ ደብዳቤም ይቀርባል” ብሏል።የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ፤ ጥቃቱን በአገራቸው ላይ የተፈጸመ “የሽብር ድርጊት” እንደሆነ ተናግረዋል። ኢራን “ተጠያቂ” እንድትሆን ጥሪ ማቅረባቸውን የአገሪቱ መንግሥት የዜና ወኪል ኤፒኤ ዘግቧል።ፕሬዝዳንቱ በአገሪቱ የደኅንነት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ “በአዘርባጃን ላይ የተፈጸመውን ይህንን መሠረተ ቢስ የሽብር እና የወረራ ድርጊት አንታገስም” ብለዋል።“የጦር ኃይሎቻችን የአጸፋ እርምጃዎችን እንዲያዘጋጁ እና እንዲተገብሩ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል” ሲሉም እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመዋል።የአገሪቱ “ጦር ኃይሎቻች፣ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የድንበር ጥበቃ እና ሁሉም ኃይሎች” ዝግጁነታቸውን ወደ ውጊያ ደረጃ እንዲያሳድጉ መደረጉን ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።የጦር ኃይሎቹ “ማንኛውንም ዘመቻ ለማካሄድ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው” መናገራቸውን የዜና ወኪሉ ዘግቧል።የአዘርባጃን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ናክቺቫን በራስ ገዝ ግዛት የተፈጸመውን የድሮን ጥቃት በተመለከተ የወንጀል ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።የድሮን ጥቃቱ በናክቺቫን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ላይ “ከፍተኛ ጉዳት” እንዳደረሰ የገለጸው ዐቃቤ ሕግ፤ የተቋሙን ሥራ “ሆን ተብሎ እና በሕገ ወጥ መንገድ” ማስተጓጎሉንም ጠቅሷል።የድሮኖቹን “ምንጭ እና የበረራ መስመር” በተመለከተ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ገልጿል። ይሁን እንጂ “ጥቃቱ የተፈጸመው ከኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ግዛት ውስጥ” እንደሆነ ከስሷል።ቢቢሲ ፐርሺያ ያነጋገራቸው የኢራን ጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ ግን ቴህራን በዚህ ክስተት ውስጥ ተሳትፎ አላት መባሉን አስተባብለዋል። “እነዚህ ድርጊቶች በእስራኤል እየተፈጸሙ ያሉት በሙስሊም አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለመረበሽ ነው” ብለዋል።ያጋሩ, የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት በኢራን ተፈጽሟል ላሉት የድሮን ጥቃት ምላሽ እንደሚሰጥ ተናገሩ
  11. 5 መጋቢት 2026ቪዲዮ፡ የቴህራንን ሰማይ በጭስ የሸፈኑት ፍንዳታዎች በከፊልለስድስተኛ ቀን በቀጠለው አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ በሚፈጽሙት ጥቃት ዛሬ ሐሙስ ከፍተኛ ፍንዳታዎች በዋና ከተማዋ ውስጥ ተከስቷል። በከተማዋ አብዛኛው ክፍል ሰማይ ላይም ጭስ ተንሰራፍቶ ታይቷል። ይህ ቪዲዮም በከፊል ይህንን ክስተት ያሳያል። ከጦርነቱ ጋር የተያያዙ ተጨማሪ ቪዲዮዎችን ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይከተሉ፦ https://bbc.in/4rg4L8e00:26ያጋሩ, ቪዲዮ፡ የቴህራንን ሰማይ በጭስ የሸፈኑት ፍንዳታዎች በከፊል
  12. 5 መጋቢት 2026ከባድ ፍንዳታ ቴህራንን ሲያናውጥ፣ ኢራን በእስራኤል ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሚሳዔሎችን ተኮሰችበቴህራን ጉዳት የደረሰበት ሕንጻየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በቴህራን ጉዳት የደረሰበት ሕንጻአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት በከፈቱበት ስድስተኛ ቀን ላይ በቴህራን እና በሌሎችም የኢራን ከተሞች ውስጥ ከባድ ፍንዳታዎች ሲሰሙ፣ ከኢራን በኩል ደግሞ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ሚሳዔሎች በእስራኤል ላይ መተኮሳቸውን ጦር ሠራዊቷ አስታወቀ።ዛሬ ጠዋት በተፈጸሙ ጥቃቶች ምክንያት የዋና ከተማዋ አብዛኛው ሰማይ በጥቁር ጭስ ተሽፍኖ የሚታይ ሲሆን፣ ከቴህራን በስተምዕራብ የምትገኘው ካራጅ ከተማ በድጋሚ በእስራኤል እና በአሜሪካ ጥቃት ተመትታለች። ቡካን እና ሳናንዳጅ ከተሞችም እንዲሁ ከባድ ጥቃት የተፈጸመባቸው ናቸው።በተመሳሳይ ኢራን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሚሳዔሎችን ወደ እስራኤል መተኮሷን የእስራኤል ጦር ሠራዊት አስታውቆ፣ ሚሳዔሎቹን ለማክሸፍ ጥረት እያደረገ መሆኑን እና የማስጠንቀቂያ መልዕክት በዜጎቹ ስልክ በኩል እየላከ ነው።የማስጠንቀቂያው መልዕክት የደረሳቸው ሰዎች ሌላ መልዕክት እስከሚደርሳቸው ድረስ በመሸሸጊያ ቦታዎች ውስጥ እንዲቆዩ ተመክረዋል።ኢየሩሳሌም ከተማ የሚገኙ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ኤኤፍፒ ዘጋቢዎች የጥቃት ማስጠንቀቂያ ደውሎች እና ፍንዳታዎችን መስማታቸውን ዘግቧል።በተጨማሪም ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ በኢራን ሚሳዔል እና ድሮኖች በተከታታይ ጥቃት እየተፈጸመባት ያለችው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በዛሬው ዕለት ሚሳዔሎችን እና ከ100 በላይ ድሮኖችን እንደተተኮሱባት አሳውቃለች።የቢቢሲ መረጃ ማጣሪያ ‘ቢቢሲ ቬሪፋይ’ ያገኛቸው የሳተላይት ምሥሎች ከቅዳሜ ጀምሮ በኢራን ላይ እየተፈጸመ ባለው ጥቃት የኢራን ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አመራር ተቋማት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው አሳዩ።በተመሳሳይም ኢራን ባህሬን ላይ በፈጸመችው ጥቃት ሰማይ ጠቀስ የመኖሪያ ሕንጻ ተመትቶ ጉዳት እንደደረሰበት የሳተላይት ምሥሎች አመለከቱ።ቫንተር በተባለው የመረጃ ተቋም ረቡዕ ዕለት የተነሱት የሳተላይት ምሥሎች በምዕራባዊ ቴህራን የሚገኘው የአገሪቱ አየር ኃይል ዋና መሥሪያ ቤት ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት አሳይቷል።በኢራን ላይ ጥቃት ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ 1,045 ሰዎች መገደላቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ከእነዚህም መካከል በአንድ የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ በመጀመሪያው ዕለት በተፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ያልተቋረጠ ጥቃት እየፈጸሙ ባለበት ጊዜ ኢራን በበኩሏ በእስራኤል እና በሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ላይ የሚሳዔል እና የድሮን የአጸፋ ጥቃቶችን እየፈጸመች ነው።በቴህራን ጉዳት የደረሰበት ሕንጻየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesያጋሩ, ከባድ ፍንዳታ ቴህራንን ሲያናውጥ፣ ኢራን በእስራኤል ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሚሳዔሎችን ተኮሰች
  13. 5 መጋቢት 2026ዩኤኢ በሚሳዔል ስትመታ፤ እስራኤል የኢራን ሚሳዔሎች እንደተወነጨፉባት አስታወቀችየዱባዩ ጀበል አሊ ወደብ በከሸፈ ሚሳዔል ስብርባሪበመመታቱ በመርከብ ማቆሚያዎች ላይ የእሳት አደጋ ደርሶ ነበርየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የዱባዩ ጀበል አሊ ወደብ በከሸፈ ሚሳዔል ስብርባሪ በመመታቱ በመርከብ ማቆሚያዎች ላይ የእሳት አደጋ ደርሶ ነበርበዛሬው ዕለት ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የተወነጨፉ ስድስት ባለስቲክ ሚሳዔሎችን እና 131 ድሮኖችን ማክሸፉ እና ማውደም መቻሉን የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። አንድ ሚሳዔል እና ስድስት ድሮኖች ግን አገሪቱ ውስጥ መውደቃቸውን መከላከያ ሚኒስቴሩ ገልጿል።የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግሥት፤ “ግልጽ የሆነው የኢራን ጥቃት ከተጀመረበት” ቅዳሜ ዕለት አንስቶ 196 ባሊስቲክ ሚሳዔሎች ወደ አገሪቱ መወንጨፋቸው እንደታወቀ አስረድቷል። ስምንት ክሩዝ ሚሳዔሎች ደግሞ እንደተለዩ እና እንደወደሙ አስታውቋል።የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ውስጥ በተፈጸመው ጥቃት የፓኪስታን፣ የኔፓል እና የባንግላዲሽ ዜግነት ያላቸው ሦስት ሰዎች እንደተገደሉ እና 94 ሰዎች እንደቆሰሉ መከላከያ ሚኒስቴሩ ገልጿል።የእስራኤል ጦር በበኩሉ አገሪቱን ዒላማ ያደረጉ ተከታታይ የኢራን ሚሳዔሎች መወንጨፋቸውን እና ወደ አገሪቱ እየመጡ መሆኑ እንደተለየ ገልጿል።የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ባወጣው መረጃ፤ የአገሪቱ የመከላከያ ሥርዓቶች ሚሳዔሎቹን ለማክሸፍ እየሠሩ መሆኑን አስታውቋል። ጥቃት ሊደርስባቸው በሚችሉ አካባቢዎች ወደሚገኙ ሞባይል ስልኮችን የማስጠንቀቂያ መልዕክት መላኩንም አክሏል።የማስጠንቀቂያ መልዕክት የደረሳቸው ሰዎች ተጨማሪ መመሪያ እስከሚሰጥ ድረስ በተጠበቁ መጠለያዎች ውስጥ እንዲቆዩ ተነግሯቸዋል ተብሏል።ያጋሩ, ዩኤኢ በሚሳዔል ስትመታ፤ እስራኤል የኢራን ሚሳዔሎች እንደተወነጨፉባት አስታወቀች
  14. 5 መጋቢት 2026በርካታ የአውሮፓ አገራት ቆጵሮስን ለመጠበቅ የባሕር ኃይላቸውን መላክ ጀመሩቆጵሮስ ውስጥ የሚገኘው የዩናይትድ ኪንግደም ጦር ሰፈር እሁድ ዕለት የድሮን ጥቃት ተፈጽሞበት ነበርየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ቆጵሮስ ውስጥ የሚገኘው የዩናይትድ ኪንግደም ጦር ሰፈር እሁድ ዕለት የድሮን ጥቃት ተፈጽሞበት ነበርየአውሮፓ ኅብረት አባል የሆቸውን ቆጵሮስ ውስጥ የሚገኝ የዩናይትድ ኪንግደም ጦር ሰፈር ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በርካታ የአውሮፓ አገራት ደሴቲቷን ለመጠበቅ የባሕር ኃይላቸውን መላክ ጀመሩ።የጣልያን መከላከያ ሚኒስትር ጊዶ ክሮሴቶ አገራቸው ቆጵሮስን ለመከላከል ከስፔን፣ ፈረንሳይ እና ኔዘርላንድስ ጋር በመሆን “የባሕር ኃይል መሣሪያዎችን” እንደምትልክ ተናግረዋል።የባሕር ኃይሎቹ ስምሪት በመጪዎቹ ቀናት ውስጥ እንደሚከናወንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።የፈረንሳይ መንግሥትም ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከጣልያን እና ግሪክ መሪዎች ጋር የስልክ ንግግር እንዳደረጉ እና አገራቱ ጦራቸውን ወደ ቆጵሮስ ለመላክ እንደተስማሙ የፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ከደቂቃዎች በፊት በሜዲትራኒያን ደሴት በምትገኘው ቆጵሮስ ውስጥ የዩናይትድ ኪንግደም ጦር ሰፈር ባለበት አክሮቲሪ ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል የሚገልጽ የማስጠንቀቂያ ደውል ተሰምቷል።ለአካባቢው ነዋሪዎች የተሰማው ማስጠንቀቂያ ድምጽ ለ10 ደቂቃ ገደማ ቆይቷል። ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰማው የዩናይትድ ኪንግደም መከላከያ ሚኒስትር ጆን ሄሊ ሳይፕረስን እየጎበኙ ባለበት በዛሬው ዕለት ነው።አገሪቱ መንግሥት ኋላ ላይ በሰጠው ማብራሪያ፤ አንድ ቁስን በተመለከተ የደረሰውን መረጃ እየመረመረ እንደነበር ገልጿል። ቁሱ ወደ ብሪታኒያ የጦር ሰፈር እያመራ መሆኑን የሚያሳይ ምንም ምልክት እንደሌለም አስታውቋል።የዩናይትድ ኪንግደም ጦር ሰፈር የሚገኝበት ይህ ስፍራ እሁድ ዕለት የድሮን ጥቃት ተፈጽሞበት ነበር።ያጋሩ, በርካታ የአውሮፓ አገራት ቆጵሮስን ለመጠበቅ የባሕር ኃይላቸውን መላክ ጀመሩ
  15. 5 መጋቢት 2026የኢራን መንግሥት፤ አሜሪካ እና እስራኤል “የሲቪሊያን አካባቢዎችን ዒላማ” አድርገዋል አለየኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኤስማኢል ባቃኢየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ አሜሪካ እና እስራኤል በአገሪቱ በሚፈጽሟቸው ጥቃቶች ሆነ ብለው የሲቪሊያን አካባቢዎችን ዒላማ እያደረጉ ነው ሲል ከሰሰ።የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ኤስማኢል ባቃኢ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ የሚፈጸሙት ጥቃቶች “ተጽዕኗቸው በዓለም አቀፉ ገበያ እየተሰማ፣ የኢነርጂ ዋጋን እየጨመሩ፣ የገንዘቦችን ተመን እያናጉ” እንደሆነ ገልጸዋል። “በዓለም ዙሪያ ያሉ መደበኛ ሰዎችን የመግዛት አቅም እያዳከሙ” መሆኑንም አንስተዋል።“ለእኛ ለኢራናውያን ግን ጉዳቱ ሊለካ በማይችል ደረጃ ከፍተኛ ነው” ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ።“ወራሪዎቹ ሆነ ብለው የሲቪል አካባቢዎችን እንዲሁም ማድረስ የሚቻለው ከፍተኛ ስቃይ እና የሕይወት መጥፋት መፈጸም የሚችሉበትን ማንኛውም ቦታ ዒላማ በማድረጋቸው ህዝባችን በጭካኔ እየተገደለ ነው” ሲሉ ከስሰዋል።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ በተከፈተው ዘመቻ የአገሪቱን የባለስቲክ ሚሳዔል አቅም እና የኒውክሌር መሣሪያ የመገንባት ችሎታ ለማውደም እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።አሜሪካ እና እስራኤል ዘመቻ በከፈቱበት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ሚናብ በተባለው የኢራን ከተማ በሚገኝ የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት ከ160 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአገሪቱ ባለሥልጣናት ገልጸዋል።ከቅዳሜ ዕለት አንስቶ እስከ ረቡዕ ባሉት ቀናትም በኢራን ከ1,000 በላይ ንጹኃን መገደላቸውን መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የዜና ወኪል ‘ሂራና’ ዘግቧል።የዜና ወኪሉ ዘገባ እንደሚያመለክተው ከተገደሉት ሰዎች ውስጥ 181 ያህሉ ዕድሜያቸው ከ10 ዓመት በታች የሆነ ሕጻናት ናቸው።የአሜሪካ ጦር በሴቶች ትምህርት ቤት ላይ ተፈጽሟል የተባለውን ጥቃት በተመለከተ እያጣራ መሆኑን ሲያስታውቅ፤ የእስራኤል ጦር ደግሞ በአካባቢው ላይ ስለተካሄደ ማንኛውም ዘመቻ “እንደማያውቅ” ገልጿል።ያጋሩ, የኢራን መንግሥት፤ አሜሪካ እና እስራኤል “የሲቪሊያን አካባቢዎችን ዒላማ” አድርገዋል አለ
  16. 5 መጋቢት 2026ባህሬን ከ70 በላይ የኢራን ሚሳዔሎችን ማክሸፏን አስታወቀችኢራን በባህሬን ዋና ከተማ ማናማ በተደጋጋሚ ጥቃት ፈጽማለችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ኢራን በባህሬን ዋና ከተማ ማናማ በተደጋጋሚ ጥቃት ፈጽማለችአሜሪካ እና እስራኤል ጦርነት ከከፈቱበት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ ከኢራን የተወነጨፉ 75 ሚሳዔሎች እና 123 ድሮኖችን ማውደሟን ባህሬን አስታወቀች።የባህሬን መከላከያ ሠራዊት በኢንስታግራም ገጹ ባወጣው መረጃ፤ “ተከታታይ እና አስከፊ የሆኑትን የኢራን የሽብር ጥቃቶች መመከት” መቀጠሉን ገልጿል። ነዋሪዎች አስፈላጊ ካልሆነ በቀር ከቤታቸው እንዳይወጡም አሳስቧል።በሲቪል ዒላማዎች ሚሳዔል እና ድሮኖችን መጠቀም “ግልጽ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕግጋትን ጥሰት” እንዲሁም “የቀጠናዊ ሰላም እና ደኅንነት” ስጋት እንደሆነም ጠቅሷል።የኢራን ጥቃት ዒላማ ካደረጋቸው የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት መካከል አንዷ ባህሬን ነች። ባለፉት ስድስት ቀናት ውስጥ የባህሬን ዋና ከተማ ማናማ በተደጋጋሚ የኢራን ጥቃቶች ዒላማ ሆኗል።ኢራን፤ ባህሬን ውስጥ የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ፈጽማለች። ቅዳሜ ዕለት በአገሪቱ የሚገኘው የአሜሪካ ባሕር ኃይል “ለሚሳዔል ጥቃት እንደተዳረገ” ተገልጿል።እሁድ ዕለት በባሕር ኃይሉ ጣር ሰፈር ላይ በተፈጸመ ጥቃት ደግሞ ከባድ እሳት ተከስቶ ነበር። ኢራን በአገሪቱ በፈጸመችው ጥቃት አራት ሰዎች እንደተጎዱ የባህሬን መንግሥት አስታውቋል።ያጋሩ, ባህሬን ከ70 በላይ የኢራን ሚሳዔሎችን ማክሸፏን አስታወቀች
  17. 5 መጋቢት 2026ቻይና ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ልዩ መልዕክተኛ ልትልክ ነውኢራን በቴህራን በፈጸመችው ጥቃት የወደመ አካባቢየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesቻይና ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ልዩ መልዕክተኛዋን እንደምትልክ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ረቡዕ ዕለት ተናገሩ።ልዩ መልዕክተኛው በመካከለኛው ምሥራቅ እስራኤል እና አሜሪካ ከኢራን ጋር የጀመሩትን ጦርነት ያሸማግላሉ ተብሎ ይጠበቃል።ቤይጂንግ የኢራን የቅርብ አጋር ስትሆን ቴህራን ሉዓላዊነቷን ለመጠበቅ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ ተናግራለች። በተጨማሪም ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል ጥቃታቸውን እንዲያቆሙም አሳስባለች።ቻይና ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ልዩ መልዕክተኛዋን በመላክ “እንደምታሸማግል” ዋንግ ከሳዑዲ አረቢያ አቻቸው ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ወቅት ተናግረዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጫ ልዩ መልዕክተኛው ማን እንደሆኑ እና ወደ የትኛው የመካከለኛው አገራት እንደሚጓዙ የተባለ ነገር የለም።ዋንግ ቤይጂንግ “ምንጊዜም የሰላም ኃይል ናት፤ እንዲሁም ገንቢ ሚናዋን መጫወቷን ትቀጥላለች” ብለዋል።ቻይና ሁሉም ወገኖች ተጨማሪ ውጥረትን ለማስወገድ በተቻለ ፍጥነት ወደ ውይይት እና ድርድር እንዲመለሱም ጥሪ አቅርባለች።ያጋሩ, ቻይና ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ልዩ መልዕክተኛ ልትልክ ነው
  18. 5 መጋቢት 2026ስድስተኛ ቀኑን በያዘው አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያካሄዱት ጦርነት ምን ምን ዐበይት ጉዳዮች ተከናወኑ?እስራኤል በኢራን የፈጸመችው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,የእስራኤል መከላከያ በቆም ከተማ የሚገኝ የባለስቲክ ማስወንጨፊያ እና በኢስፋሃን የአየር መከላከያ ስርዓት ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋልአሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ በጋራ ጥቃት ከከፈቱ ስድስተኛ ቀናቸውን የያዙ ሲሆን በባህረ ሰላጤው ውስጥ ያለው ውጥረትም ጨምሯል።
    • ኢራን የባህረ ሰላጤ አገሮች ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት በመቀጠል በባህሬን እና በኳታር ፍንዳታዎች መከሰታቸው ተዘግቧል።
    • የአዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢራን ድሮኖች ጥቃት መፈጸማቸውን እና ሁለት ሰላማዊ ዜጎች መቁሰላቸውን አስታውቋል። አንደኛው የአየር ማረፊያ ተርሚናል ሕንፃ ላይ ሲወድቅ ሌላኛው ደግሞ በትምህርት ቤት ሕንፃ አቅራቢያ ወድቋል።
    • ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራን የመንግሥት ቴሌቪዥን በባህረ ሰላጤው ውስጥ ያለ አንድ የአሜሪካ ነዳጅ ጫኝ መርከብ በኢራን ባሕር ኃይል ጥቃት እንደደረሰበት እና “በእሳት እንደተያያዘ” ገልጿል። ይህ የሆነው የዩኬ የባሕር ኃይል ድርጅት አንድ ነዳጅ ጫኝ መርከብ በኩዌት የባህር ዳርቻ ላይ መመታቱን ካስታወቀ በኋላ ነው።
    • አሜሪካ እና እስራኤል በቴህራን አዳዲስ ጥቃቶችን ፈጽመዋል። በኢራን ዋና ከተማ ላይ ጭስ የታየ ሲሆን ነዋሪዎች ጥቃቶቹን ሲመለከቱ የሚያሳዩ ፎቶዎች ተጋርተዋል።
    • የእስራኤል መከላከያ በቆም ከተማ የሚገኝ የባለስቲክ ማስወንጨፊያ እና በኢስፋሃን የአየር መከላከያ ስርዓት ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።
    • ኢራን ወደ ቴል አቪቭ የምታስወነጭፈውን ሚሳዔል ብትቀጥልም የአገሪቱ ባለሥልጣናት ግን የአየር ክልሉ በከፊል እንዲከፈት ወስነዋል። ይህንንም ተከትሎ የቤን ጉሪዮን አውሮፕላን ማረፊያ ከአምስት ቀናት በኋላ ዳግም ተከፍቷል ። ወደ ቴል አቪቭ እስራኤላውያን የጫነ አውሮፕላን መድረሱም ተዘግቧል።
    • ከመካከለኛው ምሥራቅ ዜጎችን ወደ ዩኬ የሚያጓጉዝ አውሮፕላን በ”ቴክኒክ ችግር” ምክንያት መዘግየቱን ተከትሎ ዛሬ ኦማንን ለቅቆ እንደሚወጣ ተገልጿል።
    • የኳታር አየር መንገድ ደግሞ ከሙስካት፣ ኦማን የሚነሱ የሰብዓዊነት በረራዎችን እንደሚኖሩ ሲገልጽ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስም ውስን በረራዎች እንደሚደረጉ አስታውቃለች።
    ያጋሩ, ስድስተኛ ቀኑን በያዘው አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያካሄዱት ጦርነት ምን ምን ዐበይት ጉዳዮች ተከናወኑ?
  19. 5 መጋቢት 2026በመካከለኛው ምሥራቅ ለቀናት ተቋርጠው የነበሩ አንዳንድ የአውሮፕላን በረራዎች ተጀመሩየሉፍታንዛ አውሮፕላን ከሙስካት ኦማን አውሮፕላን ማረፊያ የጀርመን ቱሪስቶችን አሳፍሮ  በርሯልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የሉፍታንዛ አውሮፕላን ከሙስካት ኦማን አውሮፕላን ማረፊያ የጀርመን ቱሪስቶችን አሳፍሮ በርሯልስድስተኛ ቀኑን በያዘው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ለቀናት ተቋርጠው የነበሩ በረራዎች መጀመራቸው እየተሰማ ነው።አንዳንድ በረራዎች በመካከለኛው ምስራቅ ከቀናት በኋላ መስተጓጎላቸውን ተከትሎ እንደገና ይቀጥላሉ።የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ብሪታኒያውያንን ከኦማን ለመመለስ ያዘጋጀው በረራ ረቡዕ ምሽት በቴክኒክ ችግር ምክንያት ሳይበር ቀርቷል።”በረራው ዛሬ ዘግይቶ እንደሚነሳ ይጠበቃል” ሲል የዩኬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሐሙስ ዕለት አስታውቋል።ጀርመን፣ ስፔን፣ ኔዘርላንድስ እና ሌሎች የአውሮፓ አገራት ከመካከለኛው ምሥራቅ ዜጎቻቸውን በተሳካ ሁኔታ ማውጣት ችለዋል።በዩኤኢ ኤምሬትስ እና ኢታሃድ አየር መንገዶች የተወሰነ ቁጥር ያላቸውን በረራዎችን እያደረጉ ነው። የተወሰኑ በረራዎች በዛይድ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መጀመራቸውን የአቡ ዳቢ መገናኛ ብዙኃን ቢሮ አስታውቋል።የኳታር አየር መንገድ ዛሬ ጠዋት ከኦማን፣ ከሙስካት ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የሚደረጉ የሰብዓዊ ድጋፍ በረራዎችን እንደሚያካሂድ አስታውቋል።ከእነዚህም መካከል ወደ ለንደን፣ በርሊን፣ ኮፐንሃገን፣ ማድሪድ፣ ሮም እና አምስተርዳም የሚደረጉ በረራዎች ይገኙበታል።አየር መንገዱ ከዋና ከተማዋ ዶሃ የሚያደርጋቸው በረራዎች “የኳታር የአየር ክልል በመዘጋቱ ምክንያት ለጊዜው ተቋርጠዋል” ሲል በኤክስ ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።የእስራኤል የትራንስፖርት ሚኒስቴርን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው፣ የእስራኤል ዜጎችን የጫነ አውሮፕላን በቴል አቪቭ አርፏል። በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን ያህል ገቢ አጣ?ያጋሩ, በመካከለኛው ምሥራቅ ለቀናት ተቋርጠው የነበሩ አንዳንድ የአውሮፕላን በረራዎች ተጀመሩ
  20. 5 መጋቢት 2026በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን ያህል ገቢ አጣ?የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ አውሮፕላንየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበመካከለኛው ምሥራቅ አሜሪካ እና እስራኤል ቅዳሜ ዕለት በኢራን ላይ የከፈቱትን ጦርነት ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስር መዳረሻዎች የሚያደርጋቸውን በረራዎች መሰረዙን ለቢቢሲ ገለፀ።የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት በሳምንት እስከ 137 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ገቢ እንደሚያጣ ለቢቢሲ ተናግሯል።የአየር መንገዱ የንግድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያዴቻ ስድስተኛ ቀኑን በያዘው አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ጦርነት በአየር መንገዱ ላይ ትልቅ ጉዳት እንደሚያስከትል ተናግረዋል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገራት መንገደኞችን እንዲሁም ጭነቶችን ያመላልሳል።በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን ያህል ገቢ አጣ?ያጋሩ, በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን ያህል ገቢ አጣ?