የኢራን ፕሬዝዳንት ማስዑድ ፔዜሽኪያን በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት፤ ጥቃት የተፈጸመባቸውን ጎረቤት አገራት ይቅርታ ጠይቀዋል። የአገሪቱ ጦር ኃይሎች “ከአሁን በኋላ ቀድመው ካላጠቁ በስተቀር ጎረቤት አገራት ላይ ጥቃት እንዳይፈጽሙ” እንደታዘዙም አስታውቀዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 8 ሰአት በፊትቪዲዮ፡ በዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የድሮን ጥቃት00:47አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት ሰባተኛ ቀኑን ይዟል። ኢራንም በአጸፋው በእስራኤል እና የአሜሪካ አጋር ናቸው ባለቻቸው በሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ላይ የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃት እየፈጸመች ነው። ይህ ቪዲዮ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የተፈጸመን ጥቃት ያሳያል።ተያያዥ ቪዲዮዎችን እዚህ ይመልከቱ፡ ከአሜሪካ፣ ከእስራኤል እና ከኢራን ማን የተሻለ የጦር መሣሪያ ክምችት ያለው ማን ነው?ያጋሩ, ቪዲዮ፡ በዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የድሮን ጥቃት
  2. ከ 9 ሰአት በፊትየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በዛሬው ዕለት 16 ባለስቲክ ሚሳዔል እና 119 ድሮን እንደተተኮሰባት ገለጸችበዛሬው ዕለት ዱባይ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቅጥር ውስጥ ጥቃት ተፈጽሟልየፎቶው ባለመብት,Xየምስሉ መግለጫ,በዛሬው ዕለት ዱባይ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቅጥር ውስጥ ጥቃት ተፈጽሟልየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፤ የኢራን ፕሬዝዳንት ማስዑድ ፔዜሽኪያን ቀድመው በማያጠቁ ጎረቤት አገራት ላይ ጥቃት እንደማይፈጸም በገለጹበት በዛሬው ዕለት የተተኮሱባትን 15 ባለስቲክ ሚሳዔሎች እና 119 ድሮኖች ማክሸፏን ገለጸች።በሌላ በኩል በዱባይ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቅጥር ውስጥ በድሮን የተፈጸመ የሚመስል ጥቃትን የሚያሳይ ቪዲዮ ተሰራጭቷል።የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ፤ የአየር መከላከያ ስርዓቱ 16 ባለስቲክ ሚሳዔሎችን እንደለየ እና ከዚያ ውስጥ 15 ያህሉ ተጠልፈው ባሕር ላይ መውደቃቸውን አስታውቋል።ባለስቲክ ሚሳዔሎች በአብዛኛው በሮኬት የሚታገዙ የረጅም ርቀት መሣሪያዎች ሲሆኑ ለማምረትም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ይጠይቃሉ። ዝቅ ብለው የሚበርሩት ሰው አልባዎቹ ድሮኖች ደግሞ በጣም ባነሰ ዋጋ ይመረታሉ።የኢራን ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ባለው የአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ዩናይትድ አረብ ኤምሬት ውስጥ በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ሦስት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን 112 ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።ዛሬ በኤምሬትስ አየር መንገድ የተፈጸመውም የድሮን ጥቃት ሊሆን እንደሚችል ቢቢሲ ቬሪፋይ ያረጋገጠው ቪዲዮ አሳይቷል።በአየር ማረፊያው ደቡባዊ ክፍል ከሚገኘው የማምረቻ ስፍራ የተቀረጸው ቪዲዮ፤ ከአየር ማረፊያው ተርሚናል ሕንጻ አቅራቢያ ተፈጠረን ፍንዳታ ያሳያል። ቪዲዮውን የቀረጸው ሰው “ሌላ ድሮን” በማለት ሲናገር ይሰማል።ሰው አልባው በራሪ ከመጋጨቱ በፊት በድሮን ሞተር ከሚፈጠር ድምጽ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ድምጽ ይደመጣል። ፍንዳታው ከመፈጠሩ አስቀድሞ አንድ ቁስ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ታች ሲወርድ የሚታይ ቢሆንም ምን እንደሆነ ማረጋገጥ አልተቻለም።ጥቃቱ በተፈጸመበት የአየር መንገዱ ስፍራ አቅራቢያ አራት አውሮፕላኖች እንደቆሙ ቪዲዮው ያሳያል።ኤምሬትስ አየር መንገድ ዛሬ ጠዋት ሥራ እንዳቋረጠ የሚገልጽ መረጃ ካሰራጨ በኋላ አጥፍቶታል። ቀጥሎም እንደገና አገልግሎት መጀመሩን የሚገልጽ ልጥፍ አጋርቷል።ያጋሩ, የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በዛሬው ዕለት 16 ባለስቲክ ሚሳዔል እና 119 ድሮን እንደተተኮሰባት ገለጸች
  3. 7 መጋቢት 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ “ዛሬ ኢራን እጅግ በኃይለኛው ትመታለች” አሉየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ዛሬ ኢራን እጅግ በኃይለኛው ትመታለች” ሲሉ ከዚህ ቀድም ዒላማ ያልነበሩ የቴህራን ባለሥልጣናት ላይ ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል ገለጹ።ፕሬዝዳንቱ ትሩዝ ሶሻል በተባለው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማስዑድ ፔዜሽኪያን በሰዓታት በፊት ያደረጉትን ንግግር ጠቅሰዋል።ፔዜሽኪያን፤ በኢራን ጥቃት የተፈጸመባቸውን ጎረቤት አገራት ይቅርታ ጠይቀው፤ ከአሁን በኋላ ቀድመው ጥቃት ካልፈጸሙ በስተቀር ጎረቤቶችን እንደማያጠቁ ተናግረው ነበር።ትራምፕ በልጥፋቸው፤ “ኢራን ይቅርታ መጠየቋን እና በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ ጎረቤቶቿ እጅ መስጠቷን፣ እንዲሁም ከአሁን በኋላ ወደ እነርሱ እንደማትተኩስ ቃል መግባቷን” ገልጸዋል።”ይህ ቃል የተገባው በማያቋርጠው የአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት ምክንያት ብቻ ነው” ብለዋል።ኢራን የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትን እንደማታጠቃ ብትናገርም ወደ ጎረቤቶቿ የሚደርሱ ጥቃቶች ሙሉ በሙሉ አልቆሙም።በዱባይ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አቅራቢያ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን የሚያመለክት መረጃ የወጣ ሲሆን ኳታርም የተወነጨፈባትን ሚሳዔል ማክሸፏን ገልጻለች።ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ “ዛሬ ኢራን እጅግ በኃይለኛው ትመታለች” ብለዋል። የአገሪቱ ጦርም ጥቃት የሚፈጸምባቸውን አዲስ ዒላማዎች እየለየ መሆኑን ገልጸዋል።ፕሬዝዳንቱ፤ “ሙሉ በሙሉ የሆነ ውድመት እና እርግጠኛ ሞት” የማድረስን ሀሳብ “በከፍተኛ ሁኔታ እያጤኑት” እንደሆነ ጠቅሰዋል።በአዲሱ እርምጃ ዒላማ የሚሆኑት “እስካሁን ድረስ ጥቃት ሊሰነዘርባቸው ያልታሰቡ አካባቢዎች እና በርካታ ሰዎች” እንደሆኑም ጠቁመዋል። ይህ የሚሆነው “በኢራን መጥፎ ባህሪ” ምክንያት ነው ያሉት ትራምፕ ተጨማሪ መረጃ አልሰጡም።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ “ዛሬ ኢራን እጅግ በኃይለኛው ትመታለች” አሉ
  4. 7 መጋቢት 2026የአሜሪካ ነዳጅ ተቋማት ሠራተኞቻቸውን ከኢራቅ ማስወጣት ጀመሩየነዳጅ ተቋማት ሠራተኞች በሳፍዋን ድንበር በኩል ወደ ኩዌት እየተሻገሩ ነውየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የነዳጅ ተቋማት ሠራተኞች በሳፍዋን ድንበር በኩል ወደ ኩዌት እየተሻገሩ ነውበመካከለኛው ምሥራቅ የሚሠሩ የውጭ አገራት የነዳጅ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውን ከኢራቅ ማስወጣት እንደጀመሩ ተገለጸ።ሮይተርስ የዜና ወኪል ያገኛቸው ምሥሎች፤ የነዳጅ ተቋማት ሠራተኞች በሳፍዋን ድንበር በኩል ወደ ኩዌት ሲሻገሩ ያሳያሉ።ሄሊቡርቶን የተባለው የአሜሪካ ነዳጅ አምራች የፀጥታ ኃላፊ መሐመድ ታሜህ “በኢራቅ ባለው የደኅንነት ስጋት ምክንያት የውጭ አገራት ሠራተኞች እየወጡ ነው። ወደ የት እንደሚሄዱ በቅርቡ እናያለን” በማለት ለሮይተርስ ተናግረዋል።አንድ ሳምንት በዘለው ግጭት ነዳጅ አምራች እና አከፋፋይ ተቋማት የጥቃት ዒላማ ሆነዋል።ኤችኬኤን የተባለው የአሜሪካ ነዳጅ አምራች “በኢራቅ በሚንቀሳቀሱ ሕገ ወጥ ቡድኖች” ጥቃት እንደደረሰበት ከተገለጸ በኋላ በአገሪቱ ያከናውን የነበረውን ሥራ ለማቋረጥ ተገድዷል።ኢራን፤ አሜሪካ እና እስራኤል በጥምረት ለከፈቱባት ጦርነት እየሰጠች ባለችው የአጸፋ ምላሽ ጥቃት ከተፈጸመባቸው ተቋማት መካከል የጦር ሰፈሮች እና ነዳጅ አምራቾች ይጠቀሳሉ።ቀደም ሲል የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል ሲጣልፍ የነበረ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።ያጋሩ, የአሜሪካ ነዳጅ ተቋማት ሠራተኞቻቸውን ከኢራቅ ማስወጣት ጀመሩ
  5. 7 መጋቢት 2026ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ሊያልፍ የነበረ ነዳጅ ጫኝ መርከብ መምታቷን አስታወቀችየኢራን ጦር መርከብየፎቶው ባለመብት,APየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ሲጣልፍ የነበረ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ።አብዮታዊ ዘቡ በቴሌግራም ቻናሉ ባወጣው መረጃ፤ “ፕሪማ” የሚል ስያሜ ያለው ነዳጅ ጫኝ መርከብ በወሽመጡ በኩል “መተላለፍ እንደማይቻል” በባሕር ኃይሉ የተሰጠውን “ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ችላ በማለቱ በድሮን መመታቱን ገልጿል።“ከጠበኛ አገራት ጋር አጋር የሆኑ” ነዳጅ ጫኝ እና የንግድ መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ማለፍ እንደማይፈቀድላቸውም ወታደራዊ ኃይሉ አስገንዝቧል።በዓለም ላይ ካሉ ወሳኝ የኃይል ማጓጓዣ መስመሮች አንዱ የሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ፤ ከዓለም አቀፉ የነዳጅ እና ጋዝ አቅርቦት አንድ አምስተኛ የሚሆነው ይተላልፍበታል።በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የመርከብ መተላለፊያ መስመሩ ሙሉ እንዲቆም አድርጎታል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የኢራን መንግሥት በመስመሩ ለመተላለፉ የሚሞክሩ መርከቦችን “በእሳት እንደሚያያይዝ” ዝቷል።ኢራን ይህንን ካለች በኋላ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “አስፈላጊ ከሆነ” የአሜሪካ ባሕር ኃይል በዚያ የሚያልፉ መርከቦችን እንደሚያጅብ ተናግረዋል።የኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ በበኩላቸው የአሜሪካ መርከቦች ለእጀባ ወደ አካባቢው እንዲልኩ አደፋፍረዋል።ቃል አቀባዩ አሊመሐመድ ናኢኒ፤ “ኢራን የነዳጅ ማመላለሻ መርከቦችን የማጀብ እርምጃን በደስታ ትቀበላለች። የአሜሪካ ኃይሎችም የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመሻገር በዚያ ይገኛሉ። በነገራችን ላይ እኛም መምጣታቸውን እየተጠባበቅን ነው” ሲሉ ለአገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙኃንን መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።”አሜሪካውያን ማንኛውም ውሳኔ ላይ ከመድረሳቸው በፊት (በአውሮፓውያኑ) 1987 የአሜሪካው ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ‘ብሪጅተን’ ላይ የተፈጠረውን እሳት እንዲሁም በቅርቡ ዒላማ የተደረጉ የነዳጅ ማመላለሻ መርከቦችን እንዲያስታውሱ እንመክራለን” ብለዋል።ያጋሩ, ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ሊያልፍ የነበረ ነዳጅ ጫኝ መርከብ መምታቷን አስታወቀች
  6. 7 መጋቢት 2026ኢራን በተቀናቃኞቿ ላይ ስጋትን የፈጠረችበት አጥፍቶ ጠፊ ድሮንአጥፍቶ ጠፊ ድሮንየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበአሜሪካ እና በእስራኤል የተከፈተባትን ጥቃት ተከትሎ ኢራን በእስራኤል እና በሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ላይ የአጸፋ ጥቃት በሚሳዔል እና በድሮኖች እየፈጸመች ነው።በተለይ ደግሞ ራሷ የምትሠራቸው ድሮኖች በተቀናቃኞቿ ላይ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥረዋል።እነዚህ ሻሂድ-136 የሚባሉት ካሚካዚ (አጥፍቶ ጠፊ) ድሮኖች በአንድ ላይ በብዛት ስለሚወነጨፉ ለመጥለፍ እና ለማምከን አስቸጋሪ ናቸው። ከሌሎች ወታደራዊ ድሮኖች በተለየ ኢራን በርካሽ የምታመርታቸው እነዚህ ድሮኖች የሚያደርሱት ጉዳት ቀላል የሚባል አይደለም። የሻሂድ-136 ድሮን ገጽታን በአጭሩ ምን ይመስላል?ተጨማሪ ያንብቡ፦ አሜሪካን በጦርነት ማሸነፍ የሚከብዳት ኢራን የምትከተለው የፍልሚያ አማራጭሻሂድ-136 ድኦንያጋሩ, ኢራን በተቀናቃኞቿ ላይ ስጋትን የፈጠረችበት አጥፍቶ ጠፊ ድሮን
  7. 7 መጋቢት 2026የተመድ ዋና ጸሐፊ የመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት “ከሁሉም ቁጥጥር ውጪ ሊሆን ይችላል” ሲሉ አስጠነቀቁየተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝየፎቶው ባለመብት,Reutersየተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፤ የመካከለኛው ምሥራቅ ሁኔታ “ከዚህ በላይ አሳሳቢ ሊሆን አይችልም” ሲሉ እየተባባሰ የመጣው ግጭት እንዲቆም ጠየቁ።ዋና ጸሐፊው ኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፤ “በመካከለኛው ምሥራቅ እና ከዚያም ባሻገር የሚፈጸሙት ሕገ ወጥ ጥቃቶች በመላው ቀጣናው የሚገኙ ንጹኃን ላይ ከፍተኛ ስቃይ እና ጉዳይ እያደረሱ ነው” ብለዋል።የቀጣናው ሁኔታ፤ “ለዓለም ኢኮኖሚ፤ በተለይም ተጋላጭ በሆኑ ወገኖች ላይ አስከፊ ስጋት ደቅኗል” ሲሉም አሳስበዋል።”ሁኔታው ከሁሉም ቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ ሊባባስ ይችላል። ውጊያውን አቁሞ ወደ ተጨባጭ የዲፕሎማሲ ንግግር ለመግባት ጊዜ አሁን ነው። [ሁኔታው] ከዚህ በላይ አሳሳቢ ሊሆን አይችልም” ሲሉም አስጠንቅቀዋል።የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች እና የአደጋ ጊዜ እርዳታ ምክትል ዋና ጸሐፊ የሆኑት ቶም ፍሌቸር በበኩላቸው፤ ለጦርነቱ እየዋለ ስላለው “ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ” አንስተዋል።”ፖለቲከኞች እርዳታ ለሚሹ ወገኖች የሚውለውን በጀት በማቋረጥ በሚወስዱት እርምጃ መኩራራታቸውን” የጠቀሱት ፍሌቸር፤ መሪዎቹ ለጦርነት ገንዘብ እያዋሉ መሆኑን በማንሳት ወቅሰዋል።አክለውም፤ “ገዳይ የሆነ ቴክኖሎጂ ላይ እና ያለ ተጠያቂነት የሚፈጸመው ግድያን በተመለከተ ያለው ኅብረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን እየተመለከትን ነው” ብለዋል።ያጋሩ, የተመድ ዋና ጸሐፊ የመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት “ከሁሉም ቁጥጥር ውጪ ሊሆን ይችላል” ሲሉ አስጠነቀቁ
  8. 7 መጋቢት 2026ኢራን ከአሁን በኋላ “አስቀድመው ካላጠቁ” በስተቀር ጎረቤቶቿ ላይ ጥቃት እንደማትፈጸም አስታወቀችየኢራን ፕሬዝዳንት ማስዑድ ፔዜሽኪያንየፎቶው ባለመብት,IRNAየኢራን ፕሬዝዳንት ማስዑድ ፔዜሽኪያን በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ጥቃት የተፈጸመባቸውን ጎረቤት አገራት ይቅርታ ጠየቁ።“ጥቃት የደረሰባቸውን አገራት ይቅርታ መጠየቅን አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።“ጎረቤት አገራትን የመውረር ሐሳብ የለንም” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ “ሰላም እና መረጋጋትን ለማስፈን” ሲባል ቀጣናዊ ትብብር እንዲኖር ጠይቀዋል።ፔዜሽኪያን አክለውም የአገሪቱ አመራር ጎረቤቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃትን በተመለከተ ውሳኔ ማሳለፉን ተናግረዋል። የአገሪቱ ጦር ኃይሎች “ከአሁን በኋላ ቀድመው ካላጠቁ በስተቀር ጎረቤት አገራት ላይ ጥቃት እንዳይፈጽሙ” እንደታዘዙ አስታውቀዋል።“ከአሁን ጀምሮ፣ እነዚያ አገራት ካልተጠቃን በስተቀር ጎረቤት አገራትን ማጥቃት ወይም ሚሳዔል መተኮስ የለባቸውም። ይህንን በዲፕሎማሲ መፍታት አለብን ብዬ አስባለሁ” ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ አክለው ጥቃቶቹ የተፈጸሙት በወታደራዊ አመራሮች መካከል በተፈጠረ የመረጃ ልውውጥ ስህተት ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።ይሁን እንጂ ይህ የፕሬዝዳንቱ ንግግር የተላለፈው ኢራን ቅዳሜ ጠዋት ላይ በባህሬን፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ከፈጸመች በኋላ እንደሆነ የዜና ወኪሉ አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።በተጨማሪም የኢራኑ ፕሬዝዳንት “ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ኢራን ላይ ጥቃት ለመፈጸም እያሰቡ ያሉ [አካላት] የኢምፔሪያሊዝም አሻንጉሊት እንዳይሆኑ” ሲሉ ተናግረዋል። እስራኤል እና አሜሪካን መደገፍ “የክብር እና የነጻነት መንገድ አይደለም” ሲሉም ተደምጠዋል።ያጋሩ, ኢራን ከአሁን በኋላ “አስቀድመው ካላጠቁ” በስተቀር ጎረቤቶቿ ላይ ጥቃት እንደማትፈጸም አስታወቀች
  9. 7 መጋቢት 2026እስራኤል በሊባኖስ የሚገኝ የተመድ ይዞታ ላይ በፈጸመችው ጥቃት ሰላም አስከባሪዎች ቆሰሉበዋና ከተማዋ ቤይሩት ደቡባዊ ክፍሎች የአየር ጥቃት ተፈጽሟልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በዋና ከተማዋ ቤይሩት ደቡባዊ ክፍሎች የአየር ጥቃት ተፈጽሟልሊባኖስ ውስጥ የምትፈጽመውን ጥቃት ያጠናከረችው እስራኤል፤ በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል የሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ኃይል ይዞታን መምታቷን የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን ገለጹ።በጥቃቱ ሰላም አስከባሪ ኃይሉ ውስጥ እያገለገሉ ያሉ ጋናውያን ወታደሮች መጎዳታቸውን ፕሬዝዳንቱ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።የጋና ጦር ኃይል በበኩሉ ሁለት ወታደሮች በጥቃቱ ከፍተኛ አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግሯል። የሰላም አስከባሪዎቹ መመገቢያ ማዕከል በጥቃቱ ሙሉ በሙሉ እንደተቃጠለም ተገልጿል።የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እስራኤል የተባበሩት መንግሥታት ይዞታ ላይ ጥቃት መፈጸሟን አውግዘዋል።“የተባበሩት መንግሥታት ኃይሎች በደቡባዊ ሊባኖስ መረጋጋት ለማምጣት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ፤ ዛሬ የአስከባሪው አባላት ላይ የተፈጸመውን ተቀባይነት የሌለው ጥቃት አወግዛለሁ ብለዋል።ከሊባኖሱ ፕሬዝዳንት ጋር የተነጋገሩት የሶርያው መሪ አሕመድ አልሻራ በበኩላቸው የሁለቱም አገራት “ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት” መከበር እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።እስራኤል፤ በሊባኖስ የሚገኘው ሄዝቦላህ ላይ የከፈተችውን ጥቃት ተከትሎ በዋና ከተማዋ ቤይሩት ውስጥ ከፍተኛ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል። የአየር ጥቃቱን ተከትሎ በመቶ ሺህዎች ሚቀጠሩ ነዋሪዎች ደቡባዊውን የከተማውን ክፍል ለቅቀው እንዲወጡ በእስራኤል ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል።እስራኤል ከሰኞ አንስቶ ሊባኖስ ውስጥ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች 217 ሰዎች እንደተገደሉ እና 798 ሰዎች እንደቆሰሉ የአገሪቱ ጤና ሚኒስትር አስታውቋል።በሊባኖስ ዋና ከተማ የተፈጸመው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በሊባኖስ ዋና ከተማ የተፈጸመው ጥቃትያጋሩ, እስራኤል በሊባኖስ የሚገኝ የተመድ ይዞታ ላይ በፈጸመችው ጥቃት ሰላም አስከባሪዎች ቆሰሉ
  10. 7 መጋቢት 2026ሚሳዔሎች የጫነ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ዩናይትድ ኪንግደም ደረሰየአሜሪካ የጦር አውሮፕላንየፎቶው ባለመብት,Reuters24 ሚሳዔሎች የጫነ ግዙፍ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ዩናይትድ ኪንግደም ደረሰ። ‘ቢ-1 ላንሰር’ የተባለው የአሜሪካ ቦምብ እና ሚሳዔል ጫኝ የጦር አውሮፕላን ዩኬ፣ ግላውስታሼር በሚገኘው የአሜሪካ አየር ኃይል ያረፈው ትናንት አርብ ነው።አሜሪካ በዩኬ የጦር አውሮፕላኗን እንድታሳርፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ፈቅደዋል።ሮያል ኤርፎርስ ኤርፊልድ በተባለው ጦር ሰፈር ያረፈው የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ጥቅም ላይ መዋል የሚችለው የኢራንን የሚሳዔል ጥቃት ለመከላከል ብቻ እንደሆነ ዩኬ አስታውቃለች።የጦር አውሮፕላኑ አራት አብራሪዎች ያሉት ሲሆን 41.8 ሜትር ርዝመት እና 86 ቶን ክብደት አለው። ቦይንግ እንደሚለው፤ አሜሪካ ካሏት የአየር መሣሪያዎች ፈጣኑ ሲሆን፤ በሰዓት 1,448.4 ኪሎሜትር ይበራል።የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት “በኢራን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እጅጉን ሊባባስ ነው” ሲሉ ያለፈው ሐሙስ አስጠንቅቀዋል።“ተጨማሪ ተዋጊ ጀቶች ይሰማራሉ፤ የመከላከል ሥራውንም ያጠናክራሉ። ጥቃት የሚፈጽሙበት ፍጥነት እና ጊዜም ይጨምራል” ብለዋል።ያጋሩ, ሚሳዔሎች የጫነ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ዩናይትድ ኪንግደም ደረሰ
  11. 7 መጋቢት 2026ሩሲያ የአሜሪካ ጦርን ለማጥቃት የሚውል መረጃ ለኢራን ማቅረቧ ተዘገበሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ  እና ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesሩሲያ፤ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር መርከቦች እና ሌሎች ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ጥቃት ለመፈጸም ሊውል የሚችል መረጃ ለኢራን ማቅረቧን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለሥልጣናት እንደነገሩት የዜና ወኪሉ አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘገበ።በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ሆነው ሲቢኤስ ኒውስ ያነጋገራቸው ሌላ የአሜሪካ ባለሥልጣንም፤ ሩሲያ ዋሽንግተን በቀጣናው ያላትን ይዞታ የተመለከተ መረጃ ለኢራን እያቀረበች መሆኑን ተናግረዋል።ስለዚህ ጉዳይ የተጠየቁት አሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት በበኩላቸው፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ማን ማንን እያናገረ እንደሆነ ያውቃሉ” ብለዋል።ኤፒ ያነገጋገራቸው ምንጮች ይህንን ቢናገሩም፤ ሩሲያ መረጃ በማቅረብ የኢራንን እርምጃ እየመራች ነው የሚለው በአሜሪካ የስለላ መረጃ የተረጋገጠ እንዳልሆነ አክለዋል ተብሏል።ይህ መረጃ፤ ሩሲያ ከሳምንት በፊት አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ በከፈቱት ጥቃት ውስጥ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላት የሚጠቁም የመጀመሪያ ምልክት ተደርጎ መወሰዱን ዘገባው ያመለክታል።በኒውክሌር ፕሮግራሟ ምክንያት ለረዥም ጊዜ መገለል ከደረሰባት ኢራን ጋር ወዳጅነታቸውን ካስቀጠሉ አገራት አንዷ ሩሲያ ነች።የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሄግሴት ከሲቢኤስ ኒውስ ’60 ሚኒትስ’ የተሰኘው ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፤ ሩሲያ በቀጣናው ስለሚገኘው የአሜሪካ ጦር እንቅስቃሴ ለኢራን መረጃ እያቀረበች ነው ስለመባሉ ተጠይቀዋል።ሚኒስትሩ ምላሽ ሲሰጡ አሜሪካ “ሁሉንም ነገር እየተከታተለች” እንዲሁም በውጊያ ዕቅዷ ውስጥ እያካተተች እንደሆነ ተናግረዋል።“የአሜሪካ ሕዝብ፤ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዡ ማን ማንን እያነጋገረ እንደሆነ እንደሚያውቁ እርግጠኛ መሆን ይችላል” ብለዋል። “በይፋ የሚደረግም ሆነ በጀርባ የሚከወን፤ መፈጠር የሌለበትን ማንኛውም ነገር እየተጋፈጥን ነው፣ በኃይል እየተጋፈጥነው ነው” ሲሉም ለሲቢኤስ ኒውስ ምላሽ ሰጥተዋል።በሌላ በኩል የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከኢራኑ ፕሬዝዳንት ማስዑድ ጋር መነጋገራቸው እና ሐዘናቸውን መግለጻቸውን ክሬምሊን አስታውቋል። ሩሲያ የኃይል እርምጃዎች መቆም አለባቸው የሚል አቋም እንዳላትም ገልጸዋል ተብሏል።የፑቱን ጽሕፈት ቤት ያወጣው መረጃ እንደሚያመክተው፤ ሁለቱ አካላት ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል ተስማምተዋል።ያጋሩ, ሩሲያ የአሜሪካ ጦርን ለማጥቃት የሚውል መረጃ ለኢራን ማቅረቧ ተዘገበ
  12. 7 መጋቢት 2026በኢራን ዋና አየር ማሪፊያ ከፍተኛ ፍንዳታ መታየቱን የዐይን እማኞች ተናገሩመህራባድ አየር ማረፊያ ላይ የደረሰው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesበኢራን ዋና ከተማ ቴህራን ውስጥ የሚገኘው እና ከዋነኛዎቹ የንግድ አየር ማረፊያዎች አንዱ የሆነው መህራባድ አየር ማረፊያ ከፍተኛ ጥቃት እንደደረሰበት የሚያመለክቱ መረጃዎች ወጡ።በርካታ ሰዎችን በማስተናገድ ቀዳሚ እና የአገር ውስጥ በረራ ማዕከል በሆነው መህራባድ አየር ማረፊያ ውስጥ የሚቃጠል አውሮፕላን እና ወደላይ የሚወጣ ከፍተኛ ጭስ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተሰራጭተዋል።አርብ ዕለት የተነሳ የሳተላይት ምሥል አየር ማረፊያው ውስጥ በርካታ አውሮፕላኖች እንደነበሩ አሳይቷል። የኢራን መንግሥት መገናኛ ብዙኃንም የአየር መንገዱ የተወሰነ ክፍል የጥቃት ዒላማ መደረጉን ዘግቧል።አየር ማረፊያው የመመታቱ ዜና የተሰማው የእስራኤል ጦር ኢራን ውስጥ “አዲስ ዙር መጠነ ሰፊ ጥቃት” መክፈቱን ካስታወቀ በኋላ ነው።ረቡዕ ዕለትም አየር ማረፊያውን ዒላማ አድርጎ የነበረው የእስራኤል ጦር፤ በዚህ ጥቃት ለእስራኤል አየር ኃይል ስጋት የሆኑ የመከላከያ እና የጥቃት መለያ ሥርዓቶችን መደምሰሱን ገልጾ ነበር። በጥቃቱ ዒላማ ከተደረጉት መካከል ሄሊኮፕተር የሚመረትበት የአየር ማረፊያው ክፍል ይገኝበታል።በአሁኑ ጥቃት የትኛው የአየር ማረፊያ ክፍል እንደተደበደበ ግልጽ አይለም። የዐይን እማኞች በበኩላቸው ከቀናት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የትናንት ምሽቱ ጥቃት እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል።መህራባድ አየር ማረፊያ ላይ የደረሰው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesያጋሩ, በኢራን ዋና አየር ማሪፊያ ከፍተኛ ፍንዳታ መታየቱን የዐይን እማኞች ተናገሩ
  13. 7 መጋቢት 2026ትራምፕ የአሜሪካን የመሣሪያ ምርት በአራት እጥፍ ለማሳደግ ከአምራቾች ጋር መስማማታቸውን ተናገሩGetty Imagesየፎቶው ባለመብት,ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕከዋነኛ የአሜሪካ የጦር መሣሪያ አምራቾች ጋር ስብሰባ ያደረጉት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የመከላከያ ኩባንያዎቹ ” ‘ከፍተኛ ደረጃ’ የሆኑ የጦር መሣሪያዎችን ምርት በአራት እጥፍ ለማሳደግ” መስማማታቸውን አስታወቁ።ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተባለው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ “ለምሳሌ ኢራን ውስጥ የምንጠቀማቸው እና በቅርቡ ቬንዙዌላ ውስጥ የተጠቀምናቸው መካከለኛ እና ከፍ ያለ መካከለኛ ደረጃ ያላቸው ተተኳሾች አቅርቦታችን ገደብ የለሽ ነው” ብለዋል።ሳምንቱን ከደፈነው የኢራን ጦርነት ጋር በተያያዘ እየተነሱ ካሉ ጉዳዮች አንዱ ሁሉም አካላት ጦርነቱን ለማስቀጠል የሚያስችል የመሣሪያ ክምችት አላቸው ወይ የሚለው ነው። የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት ሐሙስ ዕለት በሰጡት መግለጫ ይህንኑ ጉዳይ አንስተው ነበር።ሚኒስትሩ፤ አሜሪካ “ምንም የተተኳሽ እጥረት” እንደሌለባት እና የማጥቃት ዘመቻውን እስከፈለገች ድረስ ማስቀጠል እንደምትችል ተናግረዋል።ይህንኑ ሐሳብ የደገሙት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በበኩላቸው “ይሄም ቢሆን ግን በእነዚህ ደረጃዎች ያሉ (መካከለኛ እና ከፍ ያለ መካከለኛ ደረጃ ተተኳሾች) ትዕዛዞችን ከፍ እንዲሉ አድርገናል” ብለዋል።ትራምፕ በልጥፋቸው ‘ከፍተኛ ደረጃ’ በማለት የገለጹት የመሣሪያ ዓይነት ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው ይበልጥ ልዩ፣ ውድ ወይም በቴክኒክ የረቀቁ መሣሪያዎችን እንደሆነ የዜና ወኪሉ አሶሺዬትድ ፕሬዝ ዘግቧል።ከመደበኛ ተተኳሾች አንጻር ብዛታቸው አነስተኛ እንደሆነ የሚታሰቡት እንደ ሃይፐርሶኒክ ሚሳዔሎች ወይም ረዥም ርቀት የአየር ጠላፊዎች ያሉት መሣሪያዎች በዚህ ውስጥ እንደሚካተቱም ተገልጿል።ነገር ግን ትራምፕ በትክክል የትኛዎቹ መሣሪያዎች የምርት መጠናቸው እንደሚጨምር ዝርዝር መረጃ አላቀረቡም።አሜሪካ አሁን እያካሄደች ያለችውን የአጭር ርቀት ውጊያ “ማብቂያ የሌለው ለሚባል ጊዜ” ያህል ልታስቀጥል እንደምትችል መቀመጫውን ዋሽንግተን ባደረገው የስትራቴጂክ እና ዓለም አቀፍ ጥናት ማዕከል የሚሠሩት የቀድሞው የአሜሪካ ጦር ኮሎኔል ማርክ ካንሲያን ለቢቢሲ ተናግረዋል።ጦርነቱ በተራዘመ ቁጥር ግን ጥቃት የሚፈጸምባቸው ዒላማዎች ብዛት እያነሰ መሄዱ አይቀርም። ይህም አሜሪካ የከፈተችው ወታደራዊ ዘመቻ የሚጓዝበትን ፍጥነት ይቀንሳል።ተጨማሪ ያንብቡ ፦ የጦር መሣሪያ ክምችት መሟጠጥ የኢራን ግጭት ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል?ያጋሩ, ትራምፕ የአሜሪካን የመሣሪያ ምርት በአራት እጥፍ ለማሳደግ ከአምራቾች ጋር መስማማታቸውን ተናገሩ
  14. 6 መጋቢት 2026ቪዲዮ፡ የእስራኤል ጥቃት በቤይሩት ከተማ ውስጥእስራኤል ከኢራን በተጨማሪ ሊባኖስ ውስጥ ለተከታታይ ቀናት ጥቃቶችን እየፈጸመች ነው። የኢራን አጋር የሆነውን ሄዝቦላህን ዒላማ እንዳደረገች የምትገልጸው አስራኤል፣ በዋና ከተማዋ ቤይሩት ውስጥ ሳይቀር ከባድ ጥቃቶችን ፈጽማለች። ይህ ቪዲዮ ዛሬ አርብ የተፈጸመ ጥቃትን ያሳያል።ከአሜሪካ፣ ከእስራኤል እና ከኢራን ማን የተሻለ የጦር መሣሪያ ክምችት ያለው ማን ነው?00:24ያጋሩ, ቪዲዮ፡ የእስራኤል ጥቃት በቤይሩት ከተማ ውስጥ
  15. 6 መጋቢት 2026“ጦርነቱ የሚቋጨው ኢራን ያለ ቅድመ ሁኔታ እጅ ከሰጠች ብቻ ነው”- ትራምፕዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,EPAየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ የሚደረስበት ዕድል እንደሌለ ገልጸው፤ ጦርነቱ የሚቋጨው “ኢራን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እጅ ከሰጠች ብቻ” እንደሆነ ተናገሩ።ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ “ኢራን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እጅ ካልሰጠች በስተቀር ምንም ዓይነት ስምምነት አይኖርም” ብለዋል።ጦርነቱ ከተገባደደ በኋላ “ተቀባይነት ያለው መሪ” ሥልጣን እንደሚይዝም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።አሜሪካ እና አጋሮቿ ኢራንን “ከውድቀት ለመታደግ ያለመታከት እንደሚሠሩ” ትራምፕ ተናግረዋል። የኢራን ምጣኔ ሃብት “ከመቼውም ጊዜ በላይ ያንሰራራል” ሲሉም አክለዋል።ፕሬዝዳንቱ “ኢራንን ወደ ታላቅነቷ እንመልሳት. . . የወደፊት እጣ ፈንታዋ ብሩህ ነው” በማለትም ተናግረዋል።ቀደም ሲል የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዤሽኪያን አገራቸው እና አሜሪካንን “አንዳንድ አገራት ለማደራደር ጥረት ጀምረዋል” ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ የትኞቹ አገራት ለድርድር ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ግን በይፋ አልተናገሩም።ያጋሩ, “ጦርነቱ የሚቋጨው ኢራን ያለ ቅድመ ሁኔታ እጅ ከሰጠች ብቻ ነው”- ትራምፕ
  16. 6 መጋቢት 2026ለተከታታይ ቀናት በእስራኤል ጥቃት እየደረሰባት ያለችው ቤይሩትየእስራኤል ጦር ለተከታታይ ቀናት በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ላይ በቀጠለው ጥቃት የደረሱ ከባድ ጉዳቶችን የሚያሳዩ ምሥሎች እየወጡ ነው።ቢቢሲ ከደረሱት ምሥሎች መካከል አንዳንዶቹ በከተማዋ ዳርቻ ደቡባዊ ክፍል ሰማይ ላይ ጭስ ሲታይ፤ ጎዳናዎችም በፍርስራሾች ተሞልተው ያሳያሉ።የቤይሩት ከተማ ነዋሪዎች እየተፈጸመ ባለው ጥቃት የተፈጠረባቸውን ፍርሃት እና ግራ መጋባት ለቢቢሲ እየገለጹ ነው።የእስራኤል ሠራዊት ግን በጥቃቱ ዒላማ እያደረገ ያለው “የሄዝቦላህ የዕዝ ማዕከላትን” እና የድሮን ማከማቻ ሥፍራዎችን እንደሆነ ገልጿል።ከከተማዋ ሕንጻዎች መካከል ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሚነሳ ነጭ ጭስየፎቶው ባለመብት,Reutersከከተማዋ ሕንጻዎች መካከል ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሚነሳ ጥቁር ጭስየፎቶው ባለመብት,Reutersጥቃት ተፈጽሞበት በጭስ የተሸፈኑ ሁለት ሕንጻዎችየፎቶው ባለመብት,Reutersበፍርስራሽ የተሸፈነ ጎዳና ላይ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችየፎቶው ባለመብት,Reutersበፍርስራሽ ተሸፍኖ የሚታይ መኪናየፎቶው ባለመብት,Reutersያጋሩ, ለተከታታይ ቀናት በእስራኤል ጥቃት እየደረሰባት ያለችው ቤይሩት
  17. 6 መጋቢት 2026ለኢራን ባለሥልጣናት የተሠራ ከመሬት በታች ያለ ምሽግን ማውደሟን እስራኤል አስታወቀችአርብ ዕለት ቴህራን ላይ የተፈጸመ ጥቃት የፈጠረው ጭስየፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,አርብ ዕለት ቴህራን ላይ የተፈጸመ ጥቃት የፈጠረው ጭስየቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ ጥቃት በሚፈጸም ጊዜ ይጠለሉበታል ተብሎ የተሠራ ነው የተባለን ከመሬት በታች ያለ ምሽግን ማውደሙን የእስራኤል ጦር አስታወቀ።በከፍተኛ ሁኔታ ለደኅንነት ጥበቃ አመቺ እንዲሆን ተሠርቷል የተባለውን ከጥቃት የሚከላከለውን ምሽግ ለማውደም 50 የአየር ኃይል ተዋጊ ጄቶች መሳተፋቸውን የእስራኤል መከላከያ ኃይል ገልጿል።ጨምሮም ይህ ለሟቹ የኢራን ጠቅላይ መሪ “በአደጋ ጊዜ ደኅንነቱ የተጠበቀ የዕዝ ማዕከል ይሆናል” ተብሎ ወደታሰበው ምሽግ ከመዘዋወራቸው በፊት “ተደምስሰዋል” ብሏል።ምሽጉ በቴህራን ማዕከላዊ ክፍል ውስጥ ካሉ በርካታ ጎዳናዎች ጋር የተሳሰረ መሆኑን እና “የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናትም ይጠቀሙበታል” ተብሎ እንደነበር የእስራኤል ጦር አስታውቋል።ያጋሩ, ለኢራን ባለሥልጣናት የተሠራ ከመሬት በታች ያለ ምሽግን ማውደሟን እስራኤል አስታወቀች
  18. 6 መጋቢት 2026“አንዳንድ አገራት ለማደራደር ጥረት ጀምረዋል” – የኢራን ፕሬዝዳንትየኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዤሽኪያንየፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዤሽኪያን አገራቸው እና አሜሪካን “አንዳንድ አገራት ለማደራደር ጥረት ጀምረዋል” ሲሉ ተናገሩ።ፕሬዝዳንቱ የትኞቹ አገራት ለድርድር ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ግን በይፋ አልተናገሩም።በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ “አንዳንድ አገራት ለማደራደር ጥረት ጀምረዋል። በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ቁርጠኛ መሆናችን ግልጽ መሆን አለበት። ሆኖም ግን የአገራችንን ክብር እና ሉዓላዊነት ከማስከበር ወደኋላ አንልም” ብለዋል።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ሰባተኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን፣ ቴህራን በባሕረ ሰላጤው አገራት በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮች እና በእስራኤል ላይ የአጸፋ ጥቃት መፈጸሟን ቀጥላለች።የአገሪቱ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው “የድርድር ትኩረት መሆን ያለባቸው የኢራንን ሕዝብ የናቁ እና ይሄንን ግጭት ያስነሱት አካላት ላይ ነው” ብለዋል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ከኤቢሲ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “የእግረኛ ሠራዊት ወረራን ጨምሮ ለየትኛውም ዓይነት ወታደራዊ ፍልሚያ ዝግጁ ነን” ማለታቸው አይዘነጋም።ያጋሩ, “አንዳንድ አገራት ለማደራደር ጥረት ጀምረዋል” – የኢራን ፕሬዝዳንት
  19. 6 መጋቢት 2026ኢራን የእግረኛ ወረራ ከተከፈተባት መቅሰፍት እንደሚፈጠር አስጠነቀቀችአባስ አራግቺየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ የእግረኛ ሠራዊት ወረራን ጨምሮ ለየትኛውም ዓይነት ወታደራዊ ፍልሚያ ኢራን ዝግጁ መሆኗን እና እንዲህ ያለው እርምጃ በጠላቶቻቸው ላይ መቅሰፍትን እንደሚያስከትል ተናገሩ።ሚኒስትሩ ከኤቢሲ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ የአገራቸው ጦር ኃይሎች የትኛውንም ዓይነት ከአሜሪካ እና ከእስራኤል የሚሰነዘር ጥቃት ለመጋፈጥ ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።“የእግረኛ ሠራዊት ወረራን ጨምሮ ለየትኛውም ዓይነት ጥቃት ዝግጁ ነን” በማለት “እየጠበቅናቸው ነው። የሚመጣውን ባለን አቅም እንደምንጋፈጥ እርግጠኞች ነን፤ ከባድ መቅሰፍት ይጠብቃቸዋል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ ድርድር መቀመጣቸውን ያነሱት አራግቺ “ሁለት ጊዜም ድርድር ላይ እያለን ጥቃት ፈጽመውብናል” ብለው፤ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ለመድረስ ኢራን ፍላጎት እንደሌላት ተናግረዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጨምረውም በአሁኑ ወቅት ኢራን ከፍተኛ የነዳጅ ምርት የሚተላለፍበት ሆርሙዝ ሰርጥን የመዝጋት ፍላጎት እንደሌላት ነገር ግን ጦርነቱ የሚባባስ ከሆነ እርምጃውን ከመውሰድ እንደማትቆጠብ ጠቁመዋል።ያጋሩ, ኢራን የእግረኛ ወረራ ከተከፈተባት መቅሰፍት እንደሚፈጠር አስጠነቀቀች
  20. 6 መጋቢት 2026ተመድ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት ምክንያት “ሰላም የመስፈን ዕድሉ ጠባብ ነው” አለየተመድ ጽሕፈት ቤትየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesእስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ እየፈጸሙ ያሉት ጥቃት በመቀጠሉ ምክንያት በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም የመስፈን ዕድሉ ጠባብ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት አስታወቀ።የተመድ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ፤ በመካከለኛው ምሥራቅ “ለሰላም ዕድል ሊሰጥ ይገባል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ዛሬ አርብ ሰባተኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን፤ ኮሚሽነሩ ተፋላሚ ኃይሎች ሰላም እንዲያወርዱ አሳስበዋል።የፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ እንደዘገበው ኮሚሽነሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ይሄንን እሳት ለማጥፋት ዓለም እርምጃዎችን መውሰድ አለበት። አሁን እያየን ያለነው ነገሮችን ማቀጣጠል፣ ማጋጋል፣ ማፈንዳት፣ ማውደም እና መግደል ነው” ብለዋል።“ሁሉም ተዋጊዎች ለሰላም ዕድል እንዲሰጡ እጠይቃለሁ። ሌሎች አገራትም ተዋጊዎቹ እንዲታቀቡ ማሳሰብ አለባቸው። ንጹኃን የበለጠ እንዳይጎዱ እና ቀውሱ እንዳይባባስ ማድረግ አለብን” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።ያጋሩ, ተመድ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት ምክንያት “ሰላም የመስፈን ዕድሉ ጠባብ ነው” አለ