
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ጦርነት “በፍጥነት” ይጠናቀቃል ሲሉ ዋሺንግተን ደግሞ ገና “አላሸነፍንም” ሲል ተናግሯል። ትራምፕ አክለውም ቴህራን የሆርሙዝ ሰርጥን የምትዘጋ ከሆነ “እሳት ይወርድባታል” ሲሉ ከባድ ጥቃት እንደሚፈጽሙ ዝተዋል። የአብዮታዊው ዘብ በበኩሉ ጦርነቱ የሚያበቃበትን መንገድ የምንወስነው እኛ ነን ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
ጭምቅ ሃሳብ
- ትራምፕ የኢራን ጦርነት ከታቀደለት ጊዜ በፊት “በአብዛኛው እየተጠናቀቀ” እንደሆነ ተናገሩ
- ኔታንያሁ ‘የኢራንን አገዛዝ እየሰባበርነው ነው’ አሉ
- ትራምፕ ከፑቲን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በአንዳንድ አገራት ላይ የተጣለው ማዕቀብ ይነሳል አሉ
- በቤይሩት የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎች ለቅቀው እንዲወጡ ወይም ‘መጠለያ ውስጥ እንዲቆዩ’ አሳሰበ
- የባሕረ ሰላጤው አገራት ሌሊቱን በርካታ ጥቃቶች እንደተፈጸመባቸው ተናገሩ
- አውስትራሊያ የኢራን ብሔራዊ መዝሙርን አንዘምርም ላሉ የአገሪቱ እግር ኳስ ተጫዋቾች ቪዛ ሰጠች
- ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱ በቅርቡ አንደሚጠናቀቅ ከተናገሩ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ አሳየ
- የኢራን አብዮታዊ ዘብ የጦርነቱን መጠናቀቅ የምትወስነው ቴህራን ናት አለ
- ትራምፕ ኢራን ዓለም ዓቀፉን የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመርን ብታስተጓጉል “ሞት፣ እሳት እና ቁጣ” እንደሚጠብቃት አስጠነቀቁ
- የአያቶላህ ኻሜኒ ልጅ ሞጅታባ አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሆነው ተመረጡ
- ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጦርነቱ የሚቋጨው ከኔትያናሁ ጋር በሚተላለፍ “የጋራ” ውሳኔ መሆኑን ተናገሩ
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 1 ሰአት በፊትእስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ከከፈቱ ወዲህ 2,339 እስራኤላውያን መጎዳታቸው ተገለጸአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት ከከፈቱ ወዲህ 2,339 የሚሆኑ ሰዎች መጎዳታቸውን የእስራኤል የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ከተጎዱት ሰዎች መካከል 95 ያህሉ አሁንም ድረስ ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል።ኢራን በሁለቱ አገራት ጥቃት ከተከፈተባት በኋላ በእስራኤል እና ሌሎች በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ አጋር በሆኑ አገራት ላይ የአጸፋ ጥቃት እየፈጸመች ነው።ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 191 ሰዎች ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን፣ አንደኛው ግለሰብ በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል። ሦስት ሰዎች ከባድ ጉዳት ሲደርስባቸው፣ ሁለት ሰዎች መካከለኛ፣ 172 ሰዎች ደግሞ ውስን ጉዳት ደርሶባቸዋል። 10 ሰዎች ደግሞ በጭንቀት ምክንያት ሕክምና እየተሰጣቸው ነው።ዛሬ ከኢራን የተወነጨፈ ሚሳዔል ማክሸፍ እንደተቻለ የተገለጸ ሲሆን፣ ትናንት ሰኞ በተፈጸመ ጥቃት አንድ እስራኤላዊ ሞቷል።ከኢራን ወደ ማዕከላዊ እስራኤል ሚሳዔል እንደተተኮሰ እና አካባቢው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖሪያ እንደሆነ ተገልጿል።ቢቢሲ በዮርዳኖስ መዲና አማን የአደጋ ጊዜ ጥሪ መሰማቱን ዘግቧል።የእስራኤል ከተማ የሆነችው ፓታህ ቲክቫ ከንቲባ ራሚ ግሪንበርግ እንደተናገሩት፣ ሰኞ ዕለት በደረሰ የሚሳዔል ጥቃት ሁለት ሰዎች ሞተዋል። በሌላ አካባቢ ደግሞ አንድ ሰው ከባድ ጉዳት ደርሶበታል።ያጋሩ, እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ከከፈቱ ወዲህ 2,339 እስራኤላውያን መጎዳታቸው ተገለጸ
- ከ 2 ሰአት በፊትከኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ ፊት ያሉት ከባድ ቀናት
የፎቶው ባለመብት,Majid Asgaripour/WANA (West Asia News Agency) via REUTERSየኢራንን ከፍተኛ ሥልጣን የተቆጣጠሩት ሞጅታባ ኻሜኒ ሁኔታዎች ውስብሰብ ናቸው። ኢራን ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከእስራኤል ጋር ውጊያ ውስጥ ገብታለች።ሥርዓቱ በቅርቡ አገዛዙን በመቃወም በመላ አገሪቱ የተካሄደው ሕዝባዊ አመጽ ካስከተለውን ተጽዕኖ በቅጡ አላገገመም።አዲሱ የበላይ መሪ ከአገሪቱ ልሂቃን ያላቸውን ድጋፍ በፍጥነት እያጠናከሩ ቢሄዱም፣ የቅቡልነት ጥያቄዎች ከፊታቸው ተደቅኗል።ከብዙ የሃይማኖት አባቶች በተለየ ሞጅታባ በሃይማኖታዊ ሰዎች ዘንድ አያቶላህ በመባል አይጠሩም።ሞጅታባ የኢራንን ሰፊ ስትራቴጂ ከመቅረጻቸው በፊት፣ አዲሱ መሪ በመጀመሪያ ራሳቸውን በእስላማዊ ሪፐብሊክ ውስብስብ የኃይል መዋቅር ውስጥ ማጽናት አለባቸው።ይህ ደግሞ ለብዙ አሥርተ ዓመታት ከዘለቀው ምስጢራዊነት ብቅ ማለት እና አዲስ በተሾሙ ወታደራዊ አዛዦች፣ በተፎካካሪ የፖለቲካ ቡድኖች እና አሁን ሊቀበሏቸው በማይችሉ የሃይማኖት መሪዎች ላይ ሥልጣን ማሳየት ማለት ነው።እስላማዊ ሪፐብሊክ ከአራት አስርት ዓመታት በላይ ሲንቀሳቀስ የቆየው በፖለቲካ ቡድኖች መካከል ከፍተኛ ፉክክር እንዲኖር በማድረግ እና ለተቋማት አነስተኛ ሥልጣን በመስጠት ነው።ነገር ግን ሁል ጊዜ ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች ላይ የመጨረሻው ይሁንታን የሚሰጡት የበላይ መሪው ናቸው።አሊ ኻሜኒ ከሞቱ በኋላ ያለው ሳምንት ስርዓቱ በአንድ ሰው ላይ ምን ያህል ጥገኛ እንደሆነ አሳይቷል።የበላይ መሪው በሌለበት፣ የውሳኔ አሰጣጡ ቆሟል እና እርግጠኛ አለመሆን በፖለቲካ ሥርዓቱ ውስጥ ሰፍኗል።የሃይማኖት ሊቃውንቱ ሞጅታባን ለመሾም በፍጥነት መንቀሳቀሳቸውም ግልጽ የሆነ ምልክት ለመላክ ይመስላል። በኢራን ምንም መሠረታዊ ነገር አልተለወጠም፤ ባለሥልጣናቱ በግል እንደሚናገሩት “ሕይወት በተለመደው መንገድ ቀጥሏል።”ሆኖም አዲስ መሪን መቀበል ይፋ እንደማድረጉ ቀላል አይደለም። የኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ ፈተናዎች፡ ጦርነት፣ ቅቡልነት እና ሥልጣንያጋሩ, ከኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ ፊት ያሉት ከባድ ቀናት - ከ 2 ሰአት በፊትበሞጅታባ ኻሜኒ ወደ ሥልጣን መምጣት የተከፋፈሉት ኢራናውያን
የፎቶው ባለመብት,Majid Asgaripour/WANA (West Asia News Agency) via Reutersየምስሉ መግለጫ,ሞጅታባ ከኢራን መሪዎች ጀርባ በመሆን ለረዥም ዓመታት ሲሰሩ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን የኢራን ባለሥልጣናትን ፊት ለፊት መጋፈጥ ይጠበቅባቸዋልሞጅታባ ኻሜኒ የኢራን አዲሱ ከፍተኛ መሪ እና ተተኪ ሆነው የተሰየሙት አባታቸው አያቶላህ አሊ ኻሜኒ አሜሪካ እና እስራኤል በአገሪቱ ላይ ጥቃት በከፈቱበት የመጀመሪያ ቀን መገደላቸውን ተከትሎ ነው።አንዳንድ የኢራንን መንግሥት የሚደግፉ ሰዎች ለአብዮታዊ ዘቡ ቅርብ የሆነ ጠንካራ አዛዥ መሾማቸውን በማስመልከት ደስታቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጥተዋል።ነገር ግን ሌሎች ኢራናውያን ለቢቢሲ እንደተናገሩት አዲሱ የበላይ መሪ ለውጥ ያመጣሉ ብለው አያምኑም።በዋና ከተማዋ ቴህራን የሚኖር በ30ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኝ ሰው “ከጸጉር የቀጠነ የለውጥ ዕድል እንኳ በስርዓቱ ውስጥ የለም” ሲል ለቢቢሲ አስተያየቱን ሰጥቷል።88 አባላት ያሉት የሃይማኖት ሊቃውንት ጉባዔ ለአሊ ኻሜኒ ቅርብ ያልሆነ የበላይ መሪ መምረጥ አልቻለም ሲል የተሰማውን ቅሬታ ገልጿል።”ስለዚህ አብዛኛው ነገር ባለበት ይቀጥላል። አዲሱም መሪያቸውን ለመደገፍ እንኳን የሚያሰሙትን መፈክር መቀየር አልፈለጉም” ሲል አክሏል።ለዓመታት በኢራን አስተዳደር ውስጥ ሞጅታባ ኻሜኒ ከጀርባ በመሆን ተጽዕኖ እንደሚያደርጉ ሲነገር ቆይቷል።በርካቶች አዲሱ መሪ የአባታቸውን ጠንካራ ፖሊሲዎች ያስቀጥላሉ ሲሉ ግምታቸውን ተናግረዋል። ኢራናውያን በሞጅታባ ኻሜኒ ወደ ሥልጣን መምጣት ለምን ተከፋፈሉ?ያጋሩ, በሞጅታባ ኻሜኒ ወደ ሥልጣን መምጣት የተከፋፈሉት ኢራናውያን - ከ 2 ሰአት በፊትየፋርስ ባሕረ ሰላጤው ጦርነት 11ኛ ቀኑን ሲይዝ ጥቃቱም ቀጥሏል
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በምዕራብ ቴህራን አዛዲ ታወር አካባቢ የተፈጸመን ጥቃት ተከትሎ አካባቢው በጭስ ተሸፍኗል
የፎቶው ባለመብት,APየምስሉ መግለጫ,የእስራኤል የመከላከያ ስርዓት ሰኞ ሌሊት በሰሜን እስራኤል የተተኮሰ ሚሳኤልን ሲያከሽፍ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤይሩትን ለቅቀው ሲወጡ አንድ ሕጻን መንገድ ዳር ተኝቶያጋሩ, የፋርስ ባሕረ ሰላጤው ጦርነት 11ኛ ቀኑን ሲይዝ ጥቃቱም ቀጥሏል - ከ 3 ሰአት በፊትኤርዶዋን የቱርክን የአየር ክልል መጣስ “ምንም ዓይነት አሳማኝ ምክንያት” ሊቀርብበት አይችልም አሉ
የፎቶው ባለመብት,REUTERS/Dilara Senkayaየምስሉ መግለጫ,ኢራናውያን ማክሰኞ ዕለት በካፒኮይ ድንበር በኩል ወደ ቱርክ ገብተዋልየቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ኢራን የቱርክ የአየር ክልል ላይ የፈጸመችው ጥሰት “ምንም ዓይነት አሳማኝ ምክንያት ሊቀርብበት እንደማይችል” በመግለጽ አስጠንቀቁ።ፕሬዚዳንቱ አክለውም በቀጣናው ባሉ አገሮች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ማንንም እንደማይጠቅሙ ተናግረዋል።ከኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ቱርክ ጦርነቱ እንዲያበቃ የዲፕሎማሲ ጥረቶችን እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል።ኤርዶዋን ትናንት ማታ በነበራቸው የካቢኔ ስብሰባ ላይ “በቀናነት ማስጠንቀቂያዎችን ብንሰጥም፣ እጅግ በጣም የተሳሳቱ እና ጠብ አጫሪ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ቀጥለዋል፤ ይህም የቱርክን ወዳጅነት አደጋ ላይ ይጥላል” ብለዋል።ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት ሰኞ ዕለት ወደ ቱርክ የአየር ክልል የተተኮሰ ሁለተኛውን የኢራን ባላስቲክ ሚሳኤል የኔቶ የአየር መከላከያዎች መትተው ከጣሉ በኋላ ነው።ቱርክ የኔቶ ሁለተኛዋ ትልቁ ጦር ያላት አገር ሲሆን ከኢራን ጋር ረዥም ድንበርት ጋራለች፤ ይህም ላለፉት 500 ዓመታት የተረጋጋ ነበር።በኢራን ውስጥ ካለው አገዛዝ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ጥብቅ ግንኙነት ያለው ሌላ የኔቶ አባል አገር የለም። ኤርዶዋን በዩክሬን፣ በጋዛ እና በሌሎች በርካታ አገራት እንዳደረጉት ሁሉ ራሳቸውን እንደ አስታራቂ ማሳየት ይፈልጋሉ።ያጋሩ, ኤርዶዋን የቱርክን የአየር ክልል መጣስ “ምንም ዓይነት አሳማኝ ምክንያት” ሊቀርብበት አይችልም አሉ - ከ 3 ሰአት በፊትየኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል እና አሜሪካ የጦርነቱ መቋጫ ላይ “ተጨባጭ ግብ የላቸውም” አሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersሰኞ ምሽት የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ አገራቸው ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር እያካሄደች ስላለው ጦርነት ከፒቢኤስ ጋር ሰፊቃለምልልስአድርገዋል።ቁልፍ ነጥቦቹ እነሆ፦- የሞጅታባኻሜኒሹመት – አራግቺ የአሊ ኻሜኒ ልጅ ሹመት የአባታቸው አገዛዝ “ቀጣይነትን” የሚያሳይ እና በተመሳሳይ አገሪቱን “የሚያረጋጋ” እንደሆነ ተናግረዋል።
- ከአሜሪካጋርየተደረገድርድር – ኢራን ጦርነቱ እየተካሄደ ስለ ድርድር ለመነጋገር ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር ግንኙነት ተፈጥሮ እንደሆነ ተጠይቀው፣ አራግቺ ኢራን “ከአሜሪካውያን ጋር በመነጋገር ረገድ መራር ልምድ ስላላት፤ ያ ጠረጴዛው ላይ ይቀርባል” ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል።
- የአሜሪካእናየእስራኤልዓላማዎች – “በአእምሯቸው ውስጥ ስለ ጦርነቱ መቋጫ ተጨባጭ የሆነ ግብ አላቸው ብዬ አላስብም” ያሉት አራግቺ፣ እስካሁን ድረስ ሁሉንም ግቦቻቸውን ማሳካት እንዳልቻሉ እንደሚያምኑም ተናግረዋል።
- የነዳጅዋጋ – አራግቺ የነዳጅ ዋጋ መጨመር “የእኛ ጥፋት አይደለም” በማለት “እስራኤላውያን እና አሜሪካውያን በእኛ ላይ የፈጸሙት ትንኮሳ እና ጥቃት” ውጤት ነው ሲሉ ሁለቱን አገራት ተጠያቂ አድርገዋል። ኢራን የሆርሙዝ የባሕር ሰርጥን “እንዳልዘጋች” እና ነዳጅ ጫኝ መርከቦች “በባሕር ሰርጡ ላይ እንዳይቀዝፉ እያደረግን አይደለም” ሲሉ አስተባብለዋል።
- የሰላማዊ ዜጎችጉዳት – የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አገሪቱ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች “የተወሰኑ ጉዳቶች” ቢደርሱም “ሰላማዊ ሰዎችን የሚያዘወትሯቸውን ስፍራዎች ዒላማ አላደረግንም” ብለዋል።
- ከ 3 ሰአት በፊትኔታንያሁ ‘የኢራንን አገዛዝ እየሰባበርነው ነው’ አሉ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከኢራን ጋር ስለሚያካሂዱት ጦርነት በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት የቴህራንን አገዛዝ “እየሰባበርነው ነው” አሉ።ዋና ዓላማችን የኢራንን ሕዝብ ከአገዛዙ [እስላማዊ አብዮት] ማላቀቅ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ “የመጨረሻው ውሳኔ ግን የእነርሱ ነው” ብለዋል።“ምንም ጥርጥር የለውም እስካሁን በተወሰደው እርምጃ ሰባብረናቸዋል፤ አሁንም እርምጃችንን እንደቀጠለ ነው” በማለት በይፋዊ የኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።ያጋሩ, ኔታንያሁ ‘የኢራንን አገዛዝ እየሰባበርነው ነው’ አሉ - ከ 4 ሰአት በፊትትራምፕ ከፑቲን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በአንዳንድ አገራት ላይ የተጣለው ማዕቀብ ይነሳል አሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersሰኞ ዕለት ዶናልድ ትራምፕ ባደረጓቸው በርካታ ቃለ መጠይቆች እና ጋዜጣዊ መግለጫ የነዳጅ ዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር በአንዳንድ አገራት ላይ የተጣለው ማዕቀብ ሊነሳ እንደሚችል ተናገሩ።ትራምፕ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ “በአንዳንድ አገራት ላይ ማዕቀብ ጥለናል። ይህ ሁኔታ እስኪስተካከል ድረስ ማዕቀቡን እናነሳለን” ብለዋል።ከዚያ በኋላ “አይታወቅም። ምናልባት ማዕቀቡን ላንመልሰው እንችላለን። ብዙ ሰላም ይኖራል” በማለት አክለዋል።በተመሳሳይ ጋዜጣዊ መግለጫ ከሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር “በጣም ጥሩ” ብለው የገለጹትን የስልክ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ጠቃሚ እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል።በእርግጥ ትራምፕ የትኛውን ማዕቀብ እና በየትኛው አገር ላይ የተጣለውን ለማንሳት እንዳሰቡ በዝርዝር አልተናገሩም። ከቀናት በፊት ሕንድ ከሩሲያ ነዳጅ እንድትገዛ አሜሪካ መፍቀዷ ይታወሳል።ያጋሩ, ትራምፕ ከፑቲን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በአንዳንድ አገራት ላይ የተጣለው ማዕቀብ ይነሳል አሉ - ከ 4 ሰአት በፊትበቤይሩት የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎች ለቅቀው እንዲወጡ ወይም ‘መጠለያ ውስጥ እንዲቆዩ’ አሳሰበ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የሊባኖስ ሲቪል መከላከያ አባላት ሰኞ ዕለት እስራኤል በቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻዎች ላይ ባደረገችው ጥቃት ምክንያት የተጎዳ ሕንፃን ጎብኝተዋልበቤይሩት የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ ከሊባኖስ ለቅቀው የማይወጡ ከሆነ “መጠለያ ውስጥ እንዲቆዩ” አሳሰበ።ኤምባሲው ዛሬ ጠዋት በሰጠው የደህንነት ማስጠንቀቂያ የአሜሪካ ዜጎች ከቤሩት ራፊክ ሃሪሪ አውሮፕላን ማረፊያ የሚነሱ የመካከለኛው ምሥራቅ አየር መንገድ በረራዎችን በመጠቀም አገሪቱን ለቅቀው ለመውጣት “በጥብቅ” ማሰብ እንዳለባቸው አስታውቋል።ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ እስራኤል በኢራን የሚደገፈው ሔዝቦላህን ዒላማ ማድረግ ከጀመረች በኋላ በቤይሩት እና ደቡባዊ ሊባኖስ ተከታታይ የቦምብ ድብደባ እየፈጸመች ነው።ያጋሩ, በቤይሩት የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎች ለቅቀው እንዲወጡ ወይም ‘መጠለያ ውስጥ እንዲቆዩ’ አሳሰበ - ከ 4 ሰአት በፊትየባሕረ ሰላጤው አገራት ሌሊቱን በርካታ ጥቃቶች እንደተፈጸመባቸው ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በኤርቢል በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ቆንስላ ጽ/ቤት ላይ በደረሰው ጥቃት ምክንያት የእሳት ቃጠሎ ተነስቷልአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የአየር ድብደባቸውን ሲቀጥሉ እስራኤል ደግሞ ሊባኖስ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት አጠናክራለች።የባሕረ ሰላጤው አገራት ከኢራን የሚሰነዘርባቸውን የበቀል ጥቃት ሲመክቱ ማደራቸውን ተናግረዋል።- ሳዑዲ አረቢያ ሌሊቱን የባለስቲክ ሚሳኤል እና አምስት የድሮን ጥቃቶች ማምከኗን ገልጻለች።
- የኩዌት ጦር ስድስት ድሮኖችን በተሳካ ሁኔታ መመከቱን እና መትቶ መጣሉን አስታውቋል።
- ሰኞ ዕለት በባህሬን ዋና ከተማ ማናማ ላይ በተፈጸመ ጥቃት የ29 ዓመት ሴት መሞቷን ተከትሎ ፣ ባህሬን የማስጠንቀቂያ ደወል ያሰማች ሲሆን ነዋሪዎችም ወደ መጠለያ እንዲገቡ ጥሪ አቅርባለች።
- የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (ዩኤኢ) መከላከያ ሚኒስቴር ማክሰኞ ማለዳ ላይ ከኢራን የሚነሱ “የሚሳኤል እና የድሮን ስጋቶችን” ማክሸፉን እንደቀጠለ እና የአየር መከላከያ ስርዓቶችን እና የጦር ጄቶችን ማሰማራቱን አስታውቋል።
- የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሰሜናዊ ኢራቅ፣ ኢርቢል የሚገኘው ቆንስላ ጽ/ቤቷ በድሮን ዒላማ ተደርጎ ውድመት ቢደርስም የተጎዳ ሰው አለመኖሩን አስታውቃለች።
- ከ 5 ሰአት በፊትዶናልድ ትራምፕ በኢራን ትምህርት ቤት ላይ ስለተፈጸመው ጥቃት ገና ምርመራ እየተደረገ ነው አሉየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ውስጥ በሚናብ የወታደራዊ ካምፕ አቅራቢያ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ስለተፈጸመው ጥቃት ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ተናገሩ።ትራምፕ በጥቃቱ ስለሞቱት 168 ሰዎች ኃላፊነት ይወስዱ እንደሆን ተጠይቀው ነበር። ከሞቱት መካከል 110 የሚሆኑት ሕጻናት ናቸው።ፕሬዝዳንቱ በዚህ ጥቃት ጥቅም ላይ የዋለው ቶማሃውክስ የተባለው ሚሳኤል መሆኑን ገልጸዋል። ሚሳኤሉ በአሜሪካ የተሠራ ሲሆን ኢራንን ጨምሮ ሌሎች አገራትም ይጠቀሙበታል ብለዋል።በትምህርት ቤቱ ላይ ጥቃት የፈጸመው ሚሳኤል በአሜሪካ ተመርቶ ሌሎች አገራትም ታጥቀውታል የሚለውን ሃሳብ በመስጠት ትራምፕ ብቸኛው ባለሥልጣን ናቸው።ባለሙያዎች ደግሞ እስራኤልም ሆነች ኢራን ቶማውክስ ሚሳኤል አለመታጠቃቸውን ገልጸዋል።“ስለጉዳዩ በበቂ አላውቅም” ያሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ ጉዳዩ በመጣራት ላይ ነው ብለዋል።“የሚመጣው ሪፖርት ምንም ይሁን ምን ሪፖርቱን ለመቀበል ዝግጁ ነኝ” በማለት አክለዋል ፕሬዝዳንት ትራምፕ።ያጋሩ, ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ትምህርት ቤት ላይ ስለተፈጸመው ጥቃት ገና ምርመራ እየተደረገ ነው አሉ
- ከ 5 ሰአት በፊትትራምፕ ሰኞ ዕለት ስለ ኢራን ምን አሉ?
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesትራምፕ ሰኞ ዕለት ከበርካታ የመገናኛ ብዙኃን ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉ ሲሆን በተጨማሪም በሪፐብሊካን ጉባዔ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፤ ጋዜጣዊ መግለጫም ሰጥተዋል። በእነዚህ ወቅቶች ትራምፕ አሜሪካ ከኢራን ጋር እያካሄደች ስላለችው ጦርነት በርካታ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።ትራምፕ ትናንትና ባደረጓቸው ንግግሮች ላይ ስለ ኢራን ምን አሉ?- ለሲቢኤስ ኒውስ ” ጦርነቱ በጣም እየተጠናቀቀ ይመስለኛል፤ እንደዚያ ማለት ይቻላል” ያሉ ሲሆን አክለውም “አሜሪካ ከተያዘለት ጊዜ በጣም ቀድማለች” ብለዋል።
- ከኤንቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ደግሞ፣ የኢራንን ነዳጅ የመቆጣጠር ዕድል ክፍት እንደሆነ በመግለጽ “ሰዎች ስለእርሱ አውርተዋል” ብለዋል።
- ከኒውዮርክ ፖስት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዲሁ አስተዳደሩ የአሜሪካ እግረኛ ጦር ወደ ኢራን እንዲገባ የሚያደርግ ውሳኔ ለመወሰን ዝግጁ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
- ትራምፕ ለሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች ባደረጉት ንግግር ደግሞ አሜሪካ “አንዳንድ በጣም ክፉ ሰዎችን ለማስወገድ” በኢራን ውስጥ “የአጭር ጊዜ” ወታደራዊ ዘመቻ ውስጥ መግባቷን ተናግረዋል። በመቀጠልም “በብዙ መንገዶች አሸንፈናል፤ ግን በበቂ ድል አላደረግንም” ብለዋል።
- ትራምፕ ለኒውዮርክ ፖስት እንደተናገሩት፣ በኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ “ደስተኛ አይደለሁም” ያሉ ሲሆን ነገር ግን በኋላ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ማን እንዲተካ እንደሚፈልጉ ወይም ይህ እንዴት እንደሚሳካ ግልጽ አላደረጉም።
- ትራምፕ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በኢራን የተፈፀመው ዘመቻ “እጅግ በጣም ስኬታማ” መሆኑን በድጋሚ ገልጸው፣ ነገር ግን ኢራን “ለረጅም ጊዜ” የኑክሌር ጦር መሳሪያ መገንባት አለመቻሏን ማረጋገጥ እንደሚፈልጉ ያም በጣም ትልቅ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።
- ትራምፕ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት አሜሪካ አሁንም በኢራን በሚገኙ ዒላማዎች ላይ ድብደባ እየፈጸመች ነው። አክለውም ዒላማዎቹ “በአንድ ቀን” ድምጥማጣቸው ሊጠፋ ይችላል ብለዋል።
- ያም ሆኖ ጦርነቱ “በቅርቡ ያበቃል” ብለዋል።
- ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ በጻፉት ጽሑፍ ደግሞ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ውስጥ የሚደረገውን የነዳጅ ፍሰትን ካስቆመች “ሞት፣ እሳት እና ቁጣ በእነርሱ ላይ ይወርዳል” ሲሉ ዝተዋል።
- ከ 6 ሰአት በፊትአውስትራሊያ የኢራን ብሔራዊ መዝሙርን አንዘምርም ላሉ የአገሪቱ እግር ኳስ ተጫዋቾች ቪዛ ሰጠች
የፎቶው ባለመብት,AFP Via Getty Imagesአውስትራሊያ ለኢራን የሴት እግር ኳስ ተጫዋች ቡድን አባላት የሰብዓዊ ቪዛ ሰጠች።በአውስትራሊያ በሚካሄደው የእስያ ዋንጫ ጨዋታ ላይ ተሳትፈው ከውድድሩ ከተሰናበቱት የኢራን ሴት ብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል አምስቱ የሰብዓዊ ቪዛ ማግኘታቸውን የአውስትራሊያ መንግሥት አስታውቋል።ተጫዋቾቹ ወደ አገራቸው ሊመለሱ የነበረ ቢሆንም ባለፈው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታቸውን ከደቡብ ኮሪያ ጋር ሲያደርጉ የብሔራዊ መዝሙር አንዘምርም በማለታቸው ምክንያት ችግር ሊደርስባቸው ይችላል በማለት ደጋፊዎች ስጋታቸውnእ ገልጸው ነበር።ይህ ድርጊታቸውም ቴህራን ውስጥ ትችት ያስከተለ ሲሆን አንድ የመንግሥት አካልም “ድርጊቱ በጦርነት ወቅት የተደረገ ክህደት ነው፤ ከባድ ቅጣት ሊቀጡ ይገባል” በማለት መንግሥትን ጠይቋል። በዚህም ምክንያት የተጫዋቾቹ ጉዳይ የብዙ አካላት አጀንዳ ሆኗል።ተጫዋቾቹ ደህንነቱ ወደተጠበቀ ቦታ መወሰዳቸውን የአውስትራሊያ የማስታወቂያ ሚንስትር ቶኒ ቡርኬ ተናግረዋል። ሌሎቹ የቡድኑ አባላትም ግብዣ ተደርጎላቸው እንደነበር ሚንስትሩ ተናግረዋል።“የፖለቲካ አክቲቪስት አለመሆናቸውን በመግለጽ ከምንም ነገር ጋር የማይገናኙ ተጫዋች ብቻ መሆናቸውን” ተናግረዋል ያሉት ሚንስትሩ ለቀናት ንግግር እንዳደረጉም አስረድተዋል።ያጋሩ, አውስትራሊያ የኢራን ብሔራዊ መዝሙርን አንዘምርም ላሉ የአገሪቱ እግር ኳስ ተጫዋቾች ቪዛ ሰጠች - ከ 7 ሰአት በፊትዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱ በቅርቡ አንደሚጠናቀቅ ከተናገሩ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ አሳየየዓለም የነዳጅ ዋጋ ማክሰኞ ማለዳ በእስያ ገበያ ቅናሽ ማሳየቱ ተገለፀ።ብሬንት በ8.5 በመቶ ቅናሽ አሳይቶ በበርሜል 92̋ ዶላር ሲሸጥ ወደ አሜሪካ የተደረገው የነዳጅ ግብይትም እንዲሁ የ9 በመቶ ቅናሽ በማሳየት በ88.60 ዶላር ተሸጧል።የዓለም የነዳጅ ዋጋ አሁንም የፋርስ ባሕረ ሰላጤው ጦርነት ሲጀመር ከነበረበት የ30 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ነው።ዛሬ ማለዳ በእስያ ገበያ ላይ የታየው ቅናሽ የተመዘገበው ዶናልድ ትራምፕ “በጣም በቅርቡ” ጦርነቱ ይጠናቀቃል ማለታቸውን ተከትሎ ነው።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፍሎሪዳ ንግግር ሲያደርጉ ምንም እንኳን አሜሪካ በኢራን ብዙ ወታደራዊ ድሎችን ብታስመዘግብም ጦርነቱ በቅርቡ ይጠናቀቃል ሲሉ ተናግረዋል።የእስያ አብዛኛው አገራት የነዳጅ ዘይት የሚያስገቡት ከመካከለኛው ምሥራቅ ነው። በዚህም የተነሳ በቀጣናው እየተካሄደ ያለው ጦርነት ገበያውን ክፉኛ ጎድቶታል።የእስያ የአክሲዮን ገበያም ዛሬ ማለዳ ማንሰራራት ማሳየቱ ተጠቅሷል።ያጋሩ, ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱ በቅርቡ አንደሚጠናቀቅ ከተናገሩ በኋላ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ አሳየ
- ከ 8 ሰአት በፊትየኢራን አብዮታዊ ዘብ የጦርነቱን መጠናቀቅ የምትወስነው ቴህራን ናት አለ
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በቴህራን የአዲሱን የበላይ መሪ መመረጥ በማስመልከት ድጋፋቸውን ለመግለጽ አደባባይ የወጡ ኢራናውያንየኢራን አብዮታዊው ዘብ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱ በቅርብ ያበቃል ሲሉ ለሰጡት አስተያየን ምላሽ ሰጠ።አብዮታዊ ዘቡ በመግለጫው “የጦርነቱን ፍጻሜ እንወስናለን” በማለት በመካከለኛው ምሥራቅ ከተጀመረ አስራ አንደኛ ቀኑ ላይ የሚገኘውን ጦርነት የሚያበቃበትን ሁኔታ የምትወስነው ቴህራን መሆኗን ገልጿል።አብዮታዊ ዘቡ የእስራኤል እና አሜሪካ ጥቃት የሚቀጥል ከሆነ “አንድ ሊትር ነዳጅ” ከቀጠናው እንዲወጣ ቴህራን አትፈቅድም ሲል በመግለጫው ማስጠንቀቁን ሮይተርስ ዘግቧል።በሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ ላይ ያለው ውጥረት ከተባባሰ ወዲህ የዓለም የነዳጅ ዘይት ዋጋ መዋዠቅ አሳይቷልየዓለም አንድ አምስተኛ ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ሰርጥ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይፈጥራል።ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ የጦርነቱን መጠናቀቅ የምትወስነው ቴህራን ናት አለ - ከ 8 ሰአት በፊትትራምፕ ኢራን ዓለም ዓቀፉን የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመርን ብታስተጓጉል “ሞት፣ እሳት እና ቁጣ” እንደሚጠብቃት አስጠነቀቁ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ላይ የሚካሄደውን የመርከብ ጉዞ ብታስተጓጉል ከባድ ጥቃት እንደሚጠብቃት አስጠነቀቁ።ትራምፕ በኦንላየን ባወጡት መግለጫ “ኢራን በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ የሚጓጓዘውን የነዳጅ ፍሰት የሚያስቆም ማንኛውንም ነገር ብታደርግ፣ እስካሁን ከተጎዳችው በላይ በዩናይትድ ስቴትስ ሃያ እጥፍ ከባድ ጥቃት ይደርስባታል” ብለዋል።ወደ 20 በመቶ የሚሆነው የዓለም የነዳጅ ዘይት በባህረ ሰላጤው ውስጥ የሚያልፍ ሲሆን ጦርነቱም የባህር ላይ እንቅስቃሴውን በእጅጉ ቀንሶታል፤ የዓለም የነዳጅ ዋጋም ከፍ ብሏል።“በተጨማሪም፣ ኢራን እንደ አገር ዳግም መገንባት ፈጽሞ የማትችላቸውን እና በቀላሉ ሊጠፉ የሚችሉ ዒላማዎችን እንመታለን። ሞት፣ እሳት እና ቁጣ በላያቸው ላይ ይወርዳል። ግን ይህ እንዳይሆን ተስፋ አደርጋለሁም እጸልያለሁ!” ሲሉ ዝተዋል።ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ብትዘጋ በቀሪው ዓለም ላይ ምን ሊከሰት ይችላል?ያጋሩ, ትራምፕ ኢራን ዓለም ዓቀፉን የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመርን ብታስተጓጉል “ሞት፣ እሳት እና ቁጣ” እንደሚጠብቃት አስጠነቀቁ - ከ 8 ሰአት በፊትትራምፕ የኢራን ጦርነት ከታቀደለት ጊዜ በፊት “በአብዛኛው እየተጠናቀቀ” እንደሆነ ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesዶናልድትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ጦርነት በቅርቡ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ጠቁመው ለቢቢሲ የአሜሪካ የሚዲያ አጋር ሲቢኤስ ኒውስ “ጦርነቱ በአብዛኛው፤ በጣም እየተጠናቀቀ ነው ብዬ አስባለሁ” ብለዋል።አሜሪካ “ከተያዘለት ጊዜ በጣም ቀድማለች” በማለት ኢራን “የባሕር ኃይል፣ የመገናኛ አገልግሎት፣ የአየር ኃይል የላትም” ሲሉ አክለዋል፤ ሚሳኤሎቻቸውም “ብትንትናቸው ወጥቷል” ብለዋል።ትራምፕ ጦርነቱ በቅርቡ ሊጠናቀቅ ይችላል ብለው ያስቡ እንደሆን ተጠይቀው “በአእምሮዬ ውስጥ ያለው ማጠናቀቅ የሚለው ነው” በማለት መልሰዋል።ዋይት ሐውስ ቀደም ሲል አስር ቀን የሞላው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ከአንድ ወር በላይ ሊቆይ እንደሚችል አመልክቷል።ያጋሩ, ትራምፕ የኢራን ጦርነት ከታቀደለት ጊዜ በፊት “በአብዛኛው እየተጠናቀቀ” እንደሆነ ተናገሩ - 9 መጋቢት 2026ትራምፕ ወደ ኢራን እግረኛ ሠራዊት የማሰማርት ሐሳብ እንደሌላቸው ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesከእስራኤል ጋር በመቀናጀት በኢራን ላይ መጠነ ሰፊ የአየር እና የሚሳዔል ጥቃት እያካሄዱ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እግረኛ ሠራዊት ወደ ኢራን የማሰማራት ዕቅድ እንደሌላቸው ጠቆሙ።ፕራምፕ ለኒው ዮርክ ፖስት እንደተናገሩት እስካሁን ባለው ሁኔታ የአሜሪካ ወታደሮችን ወደ ኢራን እንዲዘምቱ ከሚያደርስ ውሳኔ ላይ እንዳልደረሱ ተናግረዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ያላትን የዩራኒየም ክምችት ደኅንነት ለመጠበቅ እግረኛ ወታደሮችን ለማሰማራት እያሰቡ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ “በዚያ ላይ ምንም ዓይነት ውሳኔ ላይ አልደረስንም። ወደዚያ ውሳኔ ከሚያደርሰን ሁኔታ አልተቃረብንም” ሲሉ ወታደር የመላክ ሃሳብ እንደሌለ ገልጸዋል።የኢራን ቀጣይ መሪን በመወሰን ላይ ሚና እንዲኖራቸው እንደሚፈልጉ ባለፉት ቀናት ሲናገሩ የነበሩት ትራምፕ የኢራን የሊቃውንት ቡድን የቀድሞውን ሟቹን ጠቅላይ መሪ ልጅ ቦታውን እንዲይዝ በመምረጣቸው “ደስተኛ እንዳልሆኑ” ተናግረዋል።ያጋሩ, ትራምፕ ወደ ኢራን እግረኛ ሠራዊት የማሰማርት ሐሳብ እንደሌላቸው ተናገሩ - 9 መጋቢት 2026የቀጠሉት ጥቃቶች፣ የነዳጅ ዋጋ ንረት እና አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ
የፎቶው ባለመብት,Reutersበኢራን ላይ የተከፈተው ጥቃት ተባብሶ አስረኛ ቀኑ ላይ በደረሰባት በዛሬው ዕለት ሰኞ በመካከለኛው ምሥራቅ ባሉ አገራት ውስጥ ፍንዳታዎች በስፋት ተሰምተዋል፤ ጉዳትም አድርሰዋል።- በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት ስር በምትገኘው በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን እና በእስራኤል ጥቃት የሚፈጸምባት የሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ውስጥ ከባድ ፈንዳታ ተሰምቷል።
- ኢራን በእስራኤል ላይ እየወሰደችው ባለው የአጸፋ እርምጃ ቴል አቪቭ ውስጥ አንድ ሰው መገደሉን የአገሪቱ መንግሥት አስታውቋል።
- ቱርክ ደግሞ በበኩሏ ወደ አየር ክልሏ የገባን የኢራን ሚሳዔል ማውደሟን ስታስታውቅ፣ የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ መከላከያ ሚኒስቴር በአስሮች የሚቆጠሩ ድሮኖችን መለየቱን ገልጿል።
- ጥቃቶች በተለያዩ አገራት ውስጥ መቀጠላቸው እየተነገረ ባለበት በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ዋጋ ማሻቀቡን ቀጥሏል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ ከከፈተች ወዲህ የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ ደርሷል።
- አገራት ይህንን ለመቆጣጠር የመጠባበቂያ ነዳጃቸውን ለመጠቀም እንዲሁም የዋጋ ጭማሪን ለመቆጣጠር እርምጃ እየወሰዱ ነው።
- የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ጦርነቱ የሚራዘም ከሆነ ቤተሰቦች እና የንግድ ተቋማት በከፍተኛ ሁኔታ ጫና እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል።
- ዶናልድ ትራምፕ ግን ከፍተኛውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ለዓለም ሰላም ሲባል የሚከፈል “በጣም ትንሽዬ ዋጋ ነው” ብለዋል።
- የኢራን ጠቅላይ መሪን በመተካት የሟቹ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ልጅ ሞጅታባ ኻሜኒ መመረጣቸውን ተከትሎ እስራኤል እና አሜሪካ ተተኪውን መሪ ዒላማ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። ይህም ጦርነቱ በቅርቡ አይቋጭም የሚል ስጋትን ፈጥሯል።
- 9 መጋቢት 2026አዲሱን ጠቅላይ መሪ የሚደግፍ ሰልፍ በቴህራን ተደረገ
የፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,በቴህራን የተደረገ የድጋፍ ሰልፍየኢራን ጠቅላይ መሪ ቦታን በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ልጅ መረከባቸውን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ቴህራን የድጋፍ ሰልፍ ተደረገ።አደባባይ የወጡት የመንግሥት ደጋፊዎች የሟቹን ጠቅላይ መሪ እና የልጃቸውን ፎቶግራፎችን ከኢራን ባንዲራ ጋር አድርገው ይዘው ታይተዋል።የፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ እንደዘገበው በሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን በዋና ከተማዋ ማዕከላዊ ክፍል ወደሚገኘው አደባባይ በመውጣት ለአዲሱ ጠቅላይ መሪ ታማኝነታቸውን ገልጸዋል።የአዲሱን መሪ ምርጫ በመደገፍ አደባባይ ከወጡት ኢራናውያን በተጨማሪ ሌሎች ደግሞ አዲሱ ጠቅላይ መሪ “ከአባታቸው የከፉ ናቸው” በሚል ለቢቢሲ የፋርስ ቋንቋ አገልግሎት ተናግረዋል።ኢራን ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ወደ አገሯ ገብተው እንዳይዘግቡ ጥብቅ የቪዛ ቁጥጥር ስለምታደርግ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ለማወቅ የሚያስችሉ መረጃዎችን ማግኘት አዳጋች ነው።ያጋሩ, አዲሱን ጠቅላይ መሪ የሚደግፍ ሰልፍ በቴህራን ተደረገ
