Mengistu Musie

ዝክረ የአለማቀፍ የሴቶች ቀን

ሚስጥረ ስላሴ ታምራት

================

ኢሕአፓ እና የሴቶች ተጋድሎ በሐገራችን ታሪክ የጠበቀ ቁርኝት አለው። ጉልህሚና የተጫወቱ ታጋይ ድርጅት ጠላቶቹ ስም ሰጠቅ የማይጠግቡት ኢሕአፓ ለሕዝብ እና ሐገር ሲሉ ከከተማ እስከ የሜዳው ተጋድሎ ተጉዘው ህይወታቸውን የሰጡትን ነው መዘከር የፈለግሁ። እንደአጋጣሚ ሆኖ ለዘመናት በተከታታይ አንባገነን እና ጭራቅ መሪወች የሐገራችን ታጋይ ሴቶች የታገሉለት እና መስዋእት የከፈሉለት የዴሞክራሲ የተጋድሎ ታሪክ የደበዘዘበት ጨርሶም አሰልስሎ ሊጠፋ በተቃረበበት በዚህ ገጠመኝ አዲት ኮከብ ወጣት ዳግም ብቅ አለች። ወጣቷ ከግማሽ ምእተ አመት ዘለል በታገለው ድርጅት እና አያሌ የሴት እና ወንድ የሕዝብ ልጆችን መስዋዕት ለከፈሉለት አላማውን አምነው “ዴሞክራሲ ያለገደብ” “ሕዝባዊ መንግስት ይቋቋም” የሚሉ መሪ መፈክሮችን አንግበው ከከተማ እስከ በረሐ፤ ከባሌ እስከ ሳሕል፤ ከአብደራፊ እስከ ቀይ ባሕር ተበትነው የወደቁበት ሳይታወቅ ለተሰውት ሴት ታጋዮች አታጋይ ድርጅት በመሪነት እረድፍ ለተከሰተችው ታጋይ ወጣት ምስጋና አድናቆትን ለጋሽ ትሆንልኝ ዘንድ ይህችን አቅርቤአለሁ። የዚህች ታጋይ ወጣትን ዝና ለማጉላት አስቤ ሳይሆን እሷን ባሳየን እና ባየነው በዚህ ድንቅ የትግል አውድማ በትግሉ የተሰው ሴት ታጋይ አርበኖች በሜዳ እና ከተሞች የተሰውትን እነ ድላይን፤ ቆንጅት ተክሉን (ትርሲት)፤ መዝገብነሽን፤አያሌ ሴት የኢሕአፓ ታጋዮችን እዘክራለሁ።

ዝክሬ ሰአማእታት ብቻ ሳይሆን ለትግል ተሰልፈው ድንጋይ ተንተርሰው የወጣት እድሜአቸውን ላይ ታች ያሉትን በህይወት አሁንም ያሉት እና ያልተዘመረላቸው ጀግኖቻችንን እነ አያልነሽን፤ ፍቅርተን፤ መሰእል ታጋዮችን ማስታወሻ ትሆንልኝ ዘንድ እጋብዛለሁ። በተጨማሪም እነዚያን ብርቅየ በህይወት ያሉትን እና በአቃቂ፤ ባሕርዳር፤ ደሴ አዲስ አበባ ሐረር መላ ኢትዮጵያ ፀረ ሕዝብ ስርአትን በሕዝባዊ ስርአት ለመተካት ብርቅ ህይወታቸውን ያውጣጡትን ታጋዮች የመራ ድርጅትን ወክላ ብቅ ያለችው ታጋይ ወጣት “ሚስጥረስላሴን” ምስልነቷን እዘክራለሁ። ዛሬ ምስጋና ለዚህ ለአለማቀፍ የሴቶች ቀን እውን ይሆን ዘንድ አለማቀፍ ግፍን በሴቶች ላይ ይፈጸም የነበረውን ጭቆናን አደባባይ አውጥተው የታገሉት አያሌ አለማቀፍ እና ሐገር አቀፍ ታጋዮች የሚታወሱበት ቀን ነው። ይህ ቀን ሴቶች ከየት ተነስተው የት እንደደረሱ ብቻ የሚዘክር ሳይሆን ቀሪውን እና ፈታኙን የወደፊት የሴቶች መብትን ለማስከበር የሚደረገውን ትግል አሳይ ይሆናል። የአለፉ ታጋዮች የጀርመኗ አታጋይ እና ታጋይ ክላራ ዘትኪን፤ ከአሜሪካ ቤቲ ፍሬዳን፤ግሎሪያ ስቴን አይነት ታጋዮችን የምናክብርበት ቀንም ጭምር ነው። የሴቶች መብት ከጓዳ እስከአደባባይ፤ ከአንድ ሐገር እስከአለማቀፍ ጭቆናው፤ በደሉ እና የመብት እረገጣው ተመሳሳይነት ያለው፤በመሆኑ ይህን አለማቀፍ ቀን ማክበር የተሰሩ የተገኙ መብቶችን ማየት እና ቀሪወቹ እና የመጭው ዘመን መታገያወችን ለማሳየት የተዘየደ አመታዊ ክብረ በአል በመሆኑ የሴቶች ጥያቄ የናቶቻችን፤ የህቶቻችን እና የሁላችንም ጥያቄ መብታቸው የሁላችንም መብት መሆኑን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሊረዳው ግድ ይላል።

በዚህ ዝክረ “የአለማቀፍ የሴቶች ቀን” በግል ሳከብር ከሁሉም በሐገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ግዜ የሴት መብትን ማክበር ብቻ ሳይሆን በመሪ ሾፌርነት ግንባር ቀደም አርጎ ያስቀመጠውን ታጋይ ድርጅት “ኢሕአፓን” በኩራት እየዘከርሁም ጭምር ነው። ዛሬም እንደትናንቱ ተራማጅነቱን በላቀ ሁኔታ ያሳየው ይህ ድርጅት እንደ የድርጅቱ የመጀመሪያዋ ጸሐፊ “ደስታ ጥላሁን” ተከትሎም እሷን የተካችው “ሚስጥረ ስላሴን” በመሪነት ያስቀመጠ እና አሁንም ለግንባር ቀደም ተራማጅነት ፋና ወጊ መሆኑን በተግባር የተረጎመ በመሆኑ በግሌ ዝቅ ብየ ክብር ለአታጋዩ ለሰማእታቱ ድርጅት ይሆንልኝ ዘድ ክብሬን እገልጣለሁ። በመጨረሻ ለሐጩን ያዝረበረበውን “ለገሰ ቱሉ” የተባለ የዘረኛው ፋሽስት ቡድን አካል፡ “ኢሕአፓን” የኤርትራን በህገወጥ መገንጠልን። የህወሓት የዘር ፖለቲካን ከከተማ እስከ ሜዳው በመሳርሪያ ትግል ተፋልሞ ለዘመናት ታግለው ያታገሉ መሪወቹን በዚሁ ትግል የሰዋውን ድርጅት ሊወቅስ ሲንደፋደፍ በማየቴ “ወይ ግዜ? እንድል አርጎኛል!! በዚህ ከህወሓት/ሻብያ ግንባር ቆመው የተሰውትንም ጸጋየ ገ/መድህን (አበበ ደብተራው)፤ ይስሐቅ ደብረጽዮን፡ ገለብ ዳፍላን፤ ጋይምን እና ሌሎች አያሌ መሪወችን ለልሐጫሙ ሳልጠቁመው አላልፍም!!

ለዘመናት፤ በጭቆና ማጥ በግፍ ሰንሰለት ታስሬ፡

መብቴን ላስከብር ጨቋኝን ልሽር ተነስቻለሁ ዛሬ!!

ይኸው ታጥቄአለሁ ዛሬ፡

ባንድ እንደሚነሳ ተጭቋኙ ሁሉ

ለማያጠራጥር ድሉ

ፍፁም ነው እምነቴ፤ ለትግሉ ነው ህይወቴ፡

ልጓዝ በድል ጎዳና፤ በወደቁት ጓዶች ፋና!!