Haileyesus Adamu ·Follow

“የኦሮሞ መንግስት” እያለ ራሱን የሚጠራው ብልፅግና ማህበራዊ መሰረቱ የት ነው?

1 . የብልፅግና ማህበራዊ መሰረቶች የት ናቸው?

ከለውጡ ግዜ ጀምሮ ሚዛኑን እና የፖለቲካ መካከለኝነቱን ለመጠበቅ ሲቸገር የነበረው ብልፅግና “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው” ከሚለው አቋሙ ወደ “ኦሮሞ ተረኛ ነው ” የሚል ሌላ ዋልታ ረገጥ የፖለቲካ መስመር መግባቱን እያየን ነው።

ብልፅግና “የኦሮሞ ተረኛ መንግስት ነኝ ” በማለት ማህበራዊ መሰረቱን ኦሮሞ ላይ ለመትከል እየሞከረ ቢሆንም አሁን ላይ በተጨባጭ የብልፅግና ማህበራዊ መሰረቶች የሚከተሉት ይመስሉኛል ።

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ፦

፨ የሸዋ ኦሮሞ ፦ አብዛኛው የሸዋ ኦሮሞ ልሂቅ በብልፅግና ዙሪያ እየተሰባሰበ ይገኛል

፨ የጅማ ኦሮሞ ፦ ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ አካባቢ ሲሆን በአመዛኙ ለብልፅግና ድጋፍ የሚሰጥ ነው።

ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ፦

፨ የደቡብ ኢትዮጵያ የፕሮቴስታንት አማኝ ማህበረሰብ ፦ በሃድያ እና በሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢ ያለው የፕሮቴስታንት አማኝ ጠ/ሚሩ ፕሮቴስታንት ስለሆኑ እና ፓርቲው በብልፅግና ወንጌል አራማጆች እየተመራ ነው ብለው በማሰብ ድጋፍ እያደረጉለት ነው።

አማራ ክልል ውስጥ ፦

፨ ደቡብ ወሎ በዋናነት ደሴ ፣ ኮምቦልቻና ከሚሴ አካባቢ ያሉ ሙስሊሞች ፦ እነዚህ አካላት ፋኖን ከክርስትና ጋር በማያያዝ የሚፈሩና ብልፅግናን የሚደግፉ ናቸው።

፨ ወልቃይት ጠገዴ ፦ እዚህ አካባቢ የወልቃይት ህዝብ በብልፅግና ዘመን በአንፃራዊነት ራሴን በራሴ ማስተዳደር ችያለሁ በሚልና በቀጣይም ከህወሓት ስጋት አለብኝ በሚል እምነት ለብልፅግና ድጋፍ እየሰጠ ያለ ነው።

ሶማሌ ክልል ፦

፨ የክልሉ ፕሬዝዳንት አንፃራዊ መረጋጋትና ልማት ለማምጣት ስለሞከረ ከተወሰኑ ጎሳዎች ውጭ በአመዛኙ ለብልፅግና ድጋፍ ያደርጋል።

2. የብልፅግና ተቀዋሚዎች ማህበራዊ መሰረት የት ነው?

ኦሮሚያ ክልል ፦

፨ አርሲ ፣ ሐረርጌና ባሌ ፦ እዚህ አካባቢ ያለው በአብዛኛው ሙስሊም ኦሮሞ ከበፊትም የነ ጃዋር ጠንካራ ህዝባዊ መሰረት ነው። በብልፅግና የረባ የፖለቲካ ስልጣንም ሆነ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አላገኘንም ብሎ ያስባል።

፨ ወለጋ ፦ ይህ አስቀድሞ የኦነግ ጠንካራ ቀጠና ሲሆን አሁን ላይም የኦላ ማህበራዊ ድጋፍ መሰረት ነው።

አማራ ክልል ፦

የፋኖ ትጥቅ የሚደረግበት አብዛኛው የገጠር ቀበሌ ከብልፅግና ቁጥጥር ውጭ የሆነበት ክልል ነው።

፨ ጎጃም ፦ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ብልፅግናን የሚቃወም ነው። የፋኖ የፖለቲካ አስኳል ነው ተብሎ ይታመናል።

፨ ወሎ (ቤተ አማራ) ፦ ከላይ ከተጠቀሱት የወሎ አካባቢዎች ውጭ አብዛኛው የቤተ አማራ አካባቢ ብልፅግናን አይደግፍም ። ጠንካራ የፋኖ ሰራዊት ያለበትና የፋኖ ወታደራዊ እምብርት ተደርጎ ይወሰዳል።

፨ ጎንደር ፦ ከወልቃይት ውጭ አብዛኛው የጎንደር አካባቢ ብልፅግናን የሚቃወም ነው። በቁጥር ደረጃ ብዙ የፋኖ ሰራዊት ያለበት ነው።

፨ ሸዋ ፦ አብዛኛው የሸዋ አማራ የብልፅግና ተቃዋሚ ነው። በመንዝ አካባቢም ጠንካራ የፋኖ ሀይል አለ።

ትግራይ ክልል ፦

፨ ሙሉ በሙሉ የብልጽግና ተቃዋሚ ነው። ህወሓትን በሚመለከት በድጋፍና በተቃውሞ የተሰለፈ አቋም በአካባቢው ልሂቅን በኩል ሲንፀባረቅ ይታያል። ቲዲፍን ግን በአብዛኛው ይደግፉታል።

ጋምቤላ እና ቤንሻንጉል ፦

፨ የተለያዩ የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ ያለባቸው አካባቢዎች ናቸው።

አፋር ፦

፨ የተወሰኑ የተቃውሞ ድምፆች ይሰማሉ።

ደቡብ ኢትዮጵያ ፦

፨ ከፕሮቴስታንቶች ውጭ በአመዛኙ የብልጽግና ተቃዋሚ ነው።

የኦርቶዶክስ አማኞች ፦

፨ አብዛኛው የኦርቶዶክስ አማኝ የብልፅግና ተቃዋሚ ነው።

ለመደምደም ያህል ፦

ብልፅግና በአማራ ብልፅግና ጥፋት ሚዛኑን ስቶ በትርክት ደረጃ ወደ ኦሮሞ ተረኛ መንግስትነት ቢቀየርም በተጨባጭ ግን ሙሉውን የኦሮሞ ማህበረሰብ በደጋፊነት ማሰለፍ አልቻለም ። በሌላ በኩል ከደቡብ ኢትዮጵያ የፕሮቴስታንት አማኞች አካባቢ ድጋፍ ለማግኘት ሲሞክር የሚታይ ሲሆን በአማራ ክልል ውስጥ ደግሞ ከሙስሊሙ ድጋፍ ለማግኘት እየሰራ ይገኛል ።

ብልፅግና የብሔርና የሀይማኖት አሰላለፍን እየቀላቀለ አሁን በሚከተለው “የኦሮሞ ተረኛ መንግስት” የሚል ዋልታ ረገጥ የፖለቲካ መስመር ሀገሪቱን አረጋግቶ ለመምራት አይችልም ። ሁሉንም የኢትዮጵያ ብሔሮች እና የእምነት ተከታዮች በዜግነትና በእኩልነት የማያስተናግድ ስርዓተ ማህበር አሁን ያለውን የርስበርስ ጦርነት ከማባባስ እና የበለጠ እልቂት ከመፍጠር የዘለለ ውጤት አይኖረውም ።