አሜሪካ፤ የዓለም አንድ አምስተኛው ነዳጅ በሚተላለፍበት ሆርሙዝ ወሽመጥ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ 16 የባሕር ላይ ፈንጂ አጥማጅ መርከቦችን ጨምሮ በርካታ የኢራን ባሕር ኃይል መርከቦችን ማውደሟን አስታወቀች። የአሜረካ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥ ተከፍቶ እንዲቆይ ለማድረግ ሌሎች አማራጮችን እያዘጋጀ እንደሆነ ዋይት ሀውስ ገልጿል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 14 ደቂቃዎች በፊትጉዳት ደርሶባቸዋል የተባሉት አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ደኅና መሆናቸው ተነገረሞጅታባየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ሞጅታባ ጠቅላይ መሪ ሆነው ከተሰየሙ በኋላ በይፋ አልታዩምአዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ ጉዳት ደርሶባቸዋል መባሉን ተከትሎ የኢራን ፕሬዝዳንት ልጅ “በደኅና ሁኔታ” ላይ እንደሚገኙ አስታወቀ።የፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ወንድ ልጅ ይህንን የጠቅላይ መሪውን ደኅንነት የሚያረጋግጥ መረጃን ያወጣው አዲሱ ጠቅላይ መሪ ጉዳት ደርሶባቸዋል የሚል ዜና መሠራጨቱን ተከትሎ ነው።ዩሱፍ ፔዜሽኪያን በቴሌግራም ገጹ ላይ ጠቅላይ መሪው ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚገልጹ “ሪፖርቶችን አይችላሁ” በማለት፣ ነገር ግን ሞጅታባ ደኅና መሆናቸውን ማረጋገጡን ጽፏል።”የቅርብ ግንኙነት ያላቸውን በርካታ ጓደኞቼን ጠይቄ እንደነገሩኝ፣ በፈጣሪ ጸጋ ያለምንም ችግር በደኅና ሁኔታ ላይ ናቸው” ሲል ቴሌግራም ላይ አስፍሯል።ነገር ግን ጠቅላይ መሪው ሥልጣኑን እንዲረከቡ በሊቃውንት ጉባዔ ከተሰየሙ በኋላ በይፋ ለሕዝብ አለመታየታቸው፣ ንግግር አለማድረጋቸው እና መግለጫ አለመስጠታቸው በደኅንነታቸው ላይ ጥያቄን አስነስቷል።ያጋሩ, ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባሉት አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ደኅና መሆናቸው ተነገረ
  2. ከ 1 ሰአት በፊትበኢራን የባሕር ኃይል መርከቦች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት የሚያሳይ ቪዲዮየአሜሪካ ጦር ሠራዊት ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) በባሕር ላይ ፈንጂ የሚያጠምዱ 16 ጀልባዎችን ጨምሮ በርካታ የኢራን ባሕር ኃይል መርከቦችን መደምሰሱን አስታውቋል።በሆርሙዝ ወሽመጥ አቅራቢያ ጥቃት ከተፈጸመባቸው የኢራን ባሕር ኃይል ንብረት ከሆኑ መርከቦች መካከል የተወሰኑት የሚያሳይ ቪዲዮ ወታደራዊ ዕዙ ይፋ አድርጓል።በተያያዘ ዘገባ እዚህ ያንብቡ የኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ ፈተናዎች፡ ጦርነት፣ ቅቡልነት እና ሥልጣን00:34ያጋሩ, በኢራን የባሕር ኃይል መርከቦች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት የሚያሳይ ቪዲዮ
  3. ከ 2 ሰአት በፊትየኢራን ፖሊስ አዛዥ ሰልፍ የሚወጡ ተቃዋሚዎችን እንደ “ጠላት” እንደሚስተናገዱ አስጠነቀቁተቃውሞየፎቶው ባለመብት,Public domainየምስሉ መግለጫ,ታኅሣሥ ላይ በተነሳው ጸረ መንግሥት ተቃውሞ ቢያንስ 7,000 ሰዎች እንደተገደሉ ተገልጿልየኢራን ፖሊስ አዛዥ አህማድሬዛ ራዳን፤ “በጠላት ጥያቄ” መሠረት የአገሪቱን መንግሥት ለመቃወም በጎዳና ላይ ሰልፍ የሚወጡ ኢራናውያንን የሚስተናገዱት እንደ “ጠላት” እንደሚሆን ተናገሩ።“በጠላት ጥያቄ መሠረት የሆነ ሰው የሚመጣ ከሆነ እንደ ተቃዋሚ ወይም እንደ ሌላ አካል አንቆጥራቸውም። ጠላትን እንደምናስተናግደው እነርሱንም እናስተናግዳቸዋለን፤ ለጠላት ምላሽ በምንሰጥበት መንገድ ምላሽ እንሰጣቸዋልን” ሲሉ ለአገሪቱ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።የፖሊስ አዛዡ፤ “ሁሉም ኃይሎቻችን ጣቶቻቸው ቃታው ላይ ነው፤ [አብዮቱን] ለመከላከል ዝግጁ ናቸው”ብለዋል።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እሑድ ዕለት ባስተላለፉት መልዕክት ኢራናውያን የአገሪቱን መንግሥት ለመጋፈጥ እንዲነሱ አሳስበው ነበር። ኔታንያሁን ጨምሮ የተለያዩ የእስራኤል ባለሥልጣናት ጦርነቱ የኢራን መንግሥት እንዲቀየር ሊያደርግ ይችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።ባለፈው ታኅሣሥ ላይ ኢራን ከፍተኛ አገር አቀፍ ጸረ መንግሥት ተቃውሞ አስተናግዳ ነበር። የአገሪቱ መንግሥት ተቃውሞውን ለማፈን በእስላማዊ ሪፐብሊኩ ታሪክ አስከፊ የተባለውን እርምጃ ወስዷል።መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የዜና ወኪል ‘ሂራና’፤ ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ ቢያንስ 7,000 ሰዎች እንደተገደሉ ማረጋገጡን ገልጿል።ያጋሩ, የኢራን ፖሊስ አዛዥ ሰልፍ የሚወጡ ተቃዋሚዎችን እንደ “ጠላት” እንደሚስተናገዱ አስጠነቀቁ
  4. ከ 3 ሰአት በፊትበኢራን ጦርነት 140 ገደማ የአሜካ ወታደሮች እንደተጎዱ ተገለጸጥቃት የተፈጸመት በኩዌት የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሠራተኞች እንዲወጡ ተደርጓልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ጥቃት የተፈጸመት በኩዌት የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሠራተኞች እንዲወጡ ተደርጓልአስራ አንደኛ ቀኑን በያዘው የኢራን ጦርነት፤ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ 140 ገደማ የአሜሪካ ወታደሮች እንደተጎዱ የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ገለጸ።የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ሻን ፓርኑል ባወጡት መግለጫ “ኦፕሬሽን ኢፒክ ፊውሪ ከተጀመረ አንስቶ ከ10 በላይ በሚሆኑ ቀናት በተፈጸሙ ተከታታይ ጥቃቶች 140 እንደሚደርሱ የተገመቱ የሠራዊት አባላት ተጎድተዋል” ብለዋል።እንደ ፔንታጎን መረጃ ከእነዚህ ውስጥ “አብዛኛዎቹ ጉዳቶች አነስተኛ የሚባሉ” ናቸው። 108 ያህል የሠራዊት አባላትም ወደ መደበኛ ሥራቸው ተመልሰዋል ተብሏል።“ስምንት የሠራዊት አባላት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ሕክምና እያገኙ ነው” ብለዋል።በአሜሪካ እና እስራኤል ዘመቻ የተከፈተባት ኢራን በወሰደችው የአጸፋ ጥቃት በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ አሜሪካ የጦር ሰፈሮችን ዒላማ አድርጋለች። ጦርነቱ በተጀመረ ማግሥት ኩዌት ውስጥ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ስድስት አሜሪካውያንን መገደላቸው ይታወሳል።ከጦር ሠፈሮችም በተጨማሪ ኢራን በባሕረ ሰላጤው አገራት የሚገኙ ሆቴሎችን፣ አየር ማረፊያዎችን፣ የነዳጅ መሠረተ ልማቶችን አጥቅታለች።ያጋሩ, በኢራን ጦርነት 140 ገደማ የአሜካ ወታደሮች እንደተጎዱ ተገለጸ
  5. ከ 4 ሰአት በፊትየጸጥታው ምክር ቤት ከኢራን ጦርነት ጋር በተያያዘ የቀረቡለት ተፎካካሪ ረቂቆች ላይ ድምፅ ሊሰጥ ነውበተመድ የኢራን አምባሳደር የሆኑት አሚር ሰኢድ ኢራቫኒ የባሕረ ሰላጤው አገራት የቀረበውን ረቂቅ "ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው እና አድሎአዊ" ሲሉ ተችተዋልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በተመድ የኢራን አምባሳደር የሆኑት አሚር ሰኢድ ኢራቫኒ የባሕረ ሰላጤው አገራት የቀረበውን ረቂቅ “ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው እና አድሎአዊ” ሲሉ ተችተዋልየተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት፤ የኢራን ጦርነትን እና በቀጣናው ያለውን ተጽዕኖ በተመለከተ በተለያዩ ወገኖች የቀረቡለትን ተፎካካሪ የውሳኔ ሐሳቦች ዛሬ በሚያደርገው ስብሰባ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።በባሕረ ሰላጤው አገራት ለምክር ቤቱ የቀረበው የመጀመሪያው ውሳኔ ኢራን ዮርዳኖስን ጨምሮ በቀጣናው አገራት ላይ የምትፈጽመውን የአጸፋ ጥቃት የሚያወግዝ ነው።በምክር ቤቱ የኢራን አጋር የሆነችው ሩሲያ ደግሞ ይህንን የሚፎካከር ረቂቅ አቅርባለች። ኢራንን፣ እስራኤልንም ሆነ አሜሪካን በስም የማይጠቅሰው የሩሲያ ረቂቅ፤ በንጹኃን ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በሙሉ ያወግዛል። ሁሉም አካላት ውጊያ እንዲያቆሙ እና ወደ ድርድር እንዲመለሱም ያሳስባል።የጸጥታ ምክር ቤቱ ጦርነቱ እንደተጀመረ ካደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በኋላ የውሳኔ ሐሳቦች ላይ ድምጽ ሲሰጥ ይህ የመጀመሪያው ይሆናል።በመጀመሪያው ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ የፈጸሙት ጥቃት እንዲሁም ኢራን በቀጣናውም አገራት ላይ የወሰደችው የአጸፋ ምላሽ የተመድን ቻርተር የሚጥስ እንደሆነ ገልጸው ነበር።አሁን የቀረበውን ረቂቅ ከ90 በላይ አገራት ድጋፍ ሰጥተውታል። ረቂቁ፤ በኢራን እና በአጋሮቿ አማካኝነት በባሕረ ሰላጤው አገራት እንዲሁም ዮርዳኖስ ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እና ዛቻ በአስቸኳይ እንዲቆም ይጠይቃል።በተጨማሪም ኢራን ወሳኝ በሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚደረገውን ዓለም አቀፍ ጉዞ ለመዝጋት ወይም በጉዞው ላይ ጣልቃ ለመግባት የምትወስዳቸውን ማንኛውም እርምጃ ወይም ማስፈራሪያም ያወግዛል።ያጋሩ, የጸጥታው ምክር ቤት ከኢራን ጦርነት ጋር በተያያዘ የቀረቡለት ተፎካካሪ ረቂቆች ላይ ድምፅ ሊሰጥ ነው
  6. ከ 4 ሰአት በፊትአሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የኢራን ፈንጂ አጥማጅ መርከቦችን መምታቷን አስታወቀችየአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴትየፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ፤ የዓለም አንድ አምስተኛ ነዳጅ በሚተላለፍበት ሆርሙዝ ወሽመጥ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ 16 የባሕር ላይ ፈንጂ አጥማጅ መርከቦችን ጨምሮ በርካታ የኢራን ባሕር ኃይል መርከቦችን ማውደሟን አስታወቀች።የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ ባወጣው መረጃ፤ በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚንቀሳቀሱ 16 ፈንጂ አጥማጆች “ተወግደዋል” ብሏል። ማዕከላዊ ዕዙ፤ መርከቦቹ ጥቃት ሲፈጸምባቸው ያሳያል የተባለ ቪዲዮም ለቅቋል።የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋት የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ያደረገ ሲሆን የአሜረካ ጦር ወሽመጡ ተከፍቶ እንዲቆይ ለማድረግ ሌሎች አማራጮችን እያዘጋጀ እንደሆነ ዋይት ሀውስ ገልጿል።አሜሪካ የአሁኑን ጥቃት የፈጸመችው የመከላከያ ሚኒስትሩ ፒት ሄግሴት በትናንትናው ዕለት እስካሁን ጥቃት ከተፈጸመባቸው ቀናት “እጅግ የከበደው” ቀን እንደሚሆን ከተናገሩ በኋላ ነው።አንድ ከፍተኛ የኢራን የደኅንነት ኃላፊ ግን አገራቸው በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ረብ የለሽ ዛቻ” እንደማትሸበር ተናግረው ነበር።መከላከያ ሚኒስቴትሩ ሄግሴት፤ አሜሪካ የኢራንን የሚሳዔል ክምችት፣ የሚሳዔል ማስወንጨፊያ እና የመከላከያ ኢንዱስትሪዎችን የማውደም እቅድ እንደያዘች ተናግረዋል። የኢራን ባሕር ኃይልን ማውደም እና ኢራን በቋሚነት የኒውክሌር መሣሪያ እንዳይኖራት ማድረግም ከግቦቹ መካከል ተጠቅሰዋል።ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ኢራን የተኮሰቻቸው መሣሪያዎች ብዛት ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ዝቅተኛው ሆኖ እንደተመዘገበም ገልጸዋል።የአሜሪካ ጥምር ጦር አዛዦች ሊቀመንበር የሆኑት ጄነራል ዳን ኬይንም በተመሳሳይ፤ የኢራን የባለስቲክ ሚሳዔል ጥቃቶች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን ገልጸዋል።ጥቃቶቹ “ከተጀመሩበት ጊዜ አንጻር በ90 በመቶ ቀንሰዋል፤ የአንድ አቅጣጫ ተዋጊ ድሮኖች ደግሞ ዘመቻው ከተጀመረ ወዲህ በ83 በመቶ ቀንሰዋል” ብለዋል።የመከላከያ ሚኒስትሩ ሄግሴት፤ ጦርነቱ ሊያበቃ የሚችልበትን ጊዜ ከመግለጽ ተቆጥበዋል። “አቅማችን ማለቂያ የለሽ ነው” ያሉት ሚኒስትሩ ጦርነቱ ምን ያህል ይቆያል የሚለው የሚወሰነው ግን በፕሬዝዳንቱ እንደሆነ ገልጸዋል።ያጋሩ, አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የኢራን ፈንጂ አጥማጅ መርከቦችን መምታቷን አስታወቀች
  7. 10 መጋቢት 2026ቪዲዮ፡ የኢራን ጥቃት በባህሬን ነዳጅ ማጣሪያ ላይኢራን በዙሪያዋ በሚገኙ የአሜሪካ ሠራዊት ጦር ሰፈርን በሚያስተናግዱ እና የአሜሪካ ወዳጅ በሆኑ አገራት ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ቀጥላለች።የኢራን ጥቃት የተለያዩ ተቋማትን ዒላማ ያደረጉ ናቸው። ከእነዚህ መካከል የነዳጅ ማውጫዎች፣ ማጣሪያዎች እና ማስተላለፊያዎች ዋነኞቹ ናቸው።የአሜሪካ ባሕር ኃይል ሰፈር የሚገኝባት ትንሿ የደሴት አገር ባህሬን ከጦርነቱ መጀመር አንስቶ በኢራን ጥቃት ሲፈጸምባት ቆይቷል።ይህ ቪዲዮ ባህሬን በሚገኘው ሲትራ አካባቢ ባለው የነዳጅ ማጣሪያ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የፈጠረውን ከባድ ጭስ ያሳያል።00:28ያጋሩ, ቪዲዮ፡ የኢራን ጥቃት በባህሬን ነዳጅ ማጣሪያ ላይ
  8. 10 መጋቢት 2026በአሜሪካ እና በእስራኤል የተፈጸሙ ጥቃቶች በኢራን መገናኛ ብዙኃንበቴህራን የተፈጸመ ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በቴህራን የተፈጸመ ጥቃትየኢራን መገናኛ ብዙኃን በዛሬው ዕለት እስራኤል እና አሜሪካ በማዕከላዊ ቴህራን በሚገኝ “አውራ ጎዳና” ላይ ጥቃት ፈጽመው አምስት ሰዎች መገደላቸውን እና ሰባት መኪኖች መቃጠላቸውን ገለጹ። በዚህም ሳቢያ አውራ ጎዳናው ለእንቅስቃሴ ዝግ ሆኗል ተብሏል።በተጨማሪም አንድ ባለሥልጣን እንደተናገሩት በጥቃቱ ሲቪል አካባቢዎች ዒላማ መሆናቸውን በመጥቀስ 265 መኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።አካባቢው በእስራኤል እና በአሜሪካ ዒላማ የተደረገው የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጦር ሰፈር እና የሚሳዔል ማምረቻ ስላለ ነው ሲሉ ገልጸዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤል ሠራዊት በኤክስ ገጹ ላይ ቴህራን ውስጥ በሚገኘው የኢማም ሁሴን ዩኒቨርስቲ ውስጥ ከሚገኝ የመሬት በታች መዋቅር ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል።ዩኒቨርስቲው ሰኞ ሌሊት ዒላማ የሆነው ከመሬት በታች በሚገኝ ክፍል ውስጥ ተወንጫፊ ጥናት የሚደረግበት እና የሚመረትበት በመሆኑ እንደሆነ ሠራዊቱ ጽፏል።የኢማም ሁሴን ዩኒቨርስቲ ከኢራን አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያለው ሲሆን፣ የእስራኤል ጦር ደግሞ “የጦር መሳሪያ ምርምር እና ግንባታ የሚካሄድበት ነው” በሚል ይከሳል።ጭስየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ቴህራንያጋሩ, በአሜሪካ እና በእስራኤል የተፈጸሙ ጥቃቶች በኢራን መገናኛ ብዙኃን
  9. 10 መጋቢት 2026በኢራን የአጸፋ ጥቃት በሚሳዔል እና በድሮን የተመቱ አገራት እነማን ናቸው?በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት ከተከፈተባት ሁለት ሳምንት የሆናት ኢራን የአጸፋ ጥቃት በዙሪያዋ በሚገኙ አገራት ላይ መፈጸሟን ቀጥላለች።ኢራን ጥቃት ከከፈቱባት አገራት መካከል አንዷ በሆነችው እስራኤል ላይ በሚሳዔል እና በድሮን ስትደበድብ ቆይታለች። በተጨማሪም የአሜሪካ ጦር ሠራዊትን አስጠግተዋል እንዲሁም የአሜሪካ የቅርብ ወዳጅ ናቸው ባለቻቸው የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ላይ ጥቃት መፈጸሟን ቀጥለላች።ቅዳሜ የካቲት 21/2018 ዓ.ም. ጥቃት የተፈጸመባት ኢራን ከፍተኛ ጉዳት ደሶባታል። ጠቅላይ መሪዋን ጨምሮ ሌሎች የአገሪቱ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ መሪዎች ተገድለዋል።አሜሪካ ጦርነቱን ለማቆም ኢራን ሙሉ ለሙሉ እጅ መስጠት እንዳለባት ብትገልጽም ኢራን ግን ለሚፈጸምባት ጥቃት አጸፋውን መመለስ ቀጥላለች።ከታች ባለው ካርታ ውስጥ ኦማን እና ቱርክ ያተካተቱ ሲሆን፣ እስካሁን የኢራን የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃት የተፈጸመባቸው አገራት የትኞቹ ናቸው?ተጨማሪ ዘገባ እዚህ ያንብቡ፡ አሜሪካን በጦርነት ማሸነፍ የሚከብዳት ኢራን የምትከተለው የፍልሚያ አማራጭካርታያጋሩ, በኢራን የአጸፋ ጥቃት በሚሳዔል እና በድሮን የተመቱ አገራት እነማን ናቸው?
  10. 10 መጋቢት 2026ዛሬ በኢራን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት ከሌላው ቀን “በጣም የከበደ” መሆኑን አሜሪካ አስታወቀችፔት ሄግሴትየምስሉ መግለጫ,የመከላከያ ሚኒስትር ፔት ሄግሴትአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጥቃት 11ኛ ቀኑን በያዘበት በዛሬው ዕለት በአሜሪካ በኩል እየተፈጸመ ያለው ጥቃት ከሌሎች ቀናት “በበለጠ ከባድ” መሆኑን የአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ተናገሩ።ፔት ሄግሴት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በኢራን ላይ የሚካሄደው ዘመቻ በተጀመረበት መጠን እንደሚቀጥል እና የዛሬው ከፍተኛ መሆኑን አመልክተው፤ በኢራን በኩል የሚሰጠው የአጸፋ ጥቃት እየቀነሰ መሆኑን ገልጸዋል።በኢራን ላይ የተከፈተው ጥቃት የአገሪቱን ወታደራዊ አቅም እና ተቋማትን የመደምሰስ እና የማዳካም ግብ እንዳለው የመከላከያ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በዚህም፡
    • የኢራንን የሚሳዔል ክምችት፣ የሚሳዔል ማስወንጨፊያዎችን እና ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎቿን ማውደም
    • የኢራንን ባሕር ኃይል መደምሰስ
    • ኢራን በዘላቂነት የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንዳይኖራት መድረግ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
    • በተጨማሪም ሄግሴት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቀደም ሲል የተናገሩትን በማስረገጥ፤ በአሜሪካ እርምጃ ያለማቋረጥ “የጠላትን ኃይል እየደመሰስን ነው” ብለዋል።
    “ዛሬ [ማክሰኞ] በድጋሚ በኢራን ውስጥ በጣም ከባዱ ጥቃት የተፈጸመበት ነው። አብዛኞቹ ተዋጊ ጄቶች፣ አብዛኞቹ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች፣ አብዛኛው ድብደባ እየተፈጸመ ነው። የምናገኘው መረጃም የተጣራ እና ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ነው።”የመከላከያ ሚኒስትሩ በተጨማሪም ባለፉት 24 ሰዓታት ኢራን ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ዝቅተኛውን ሚሳዔል እንደተኮሰች ተናግረዋል።ከሰዓት በኋላ በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የመከላከያ ሚኒስትር ሄግሴት፤ ከጦርነቱ መጠናቀቅ በኋላ ያለው ሁኔታ “በአሜሪካ ፍላጎት ላይ የሚወሰን” እንደሚሆን እና ኢራን “በኒውክሌር የምታስፈራራበት ገጽታ” አይኖርም ብለዋል።ያጋሩ, ዛሬ በኢራን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት ከሌላው ቀን “በጣም የከበደ” መሆኑን አሜሪካ አስታወቀች
  11. 10 መጋቢት 2026እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ከከፈቱ ወዲህ 2,339 እስራኤላውያን መጎዳታቸው ተገለጸአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት ከከፈቱ ወዲህ 2,339 የሚሆኑ ሰዎች መጎዳታቸውን የእስራኤል የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ከተጎዱት ሰዎች መካከል 95 ያህሉ አሁንም ድረስ ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል።ኢራን በሁለቱ አገራት ጥቃት ከተከፈተባት በኋላ በእስራኤል እና ሌሎች በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ አጋር በሆኑ አገራት ላይ የአጸፋ ጥቃት እየፈጸመች ነው።ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 191 ሰዎች ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን፣ አንደኛው ግለሰብ በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል። ሦስት ሰዎች ከባድ ጉዳት ሲደርስባቸው፣ ሁለት ሰዎች መካከለኛ፣ 172 ሰዎች ደግሞ ውስን ጉዳት ደርሶባቸዋል። 10 ሰዎች ደግሞ በጭንቀት ምክንያት ሕክምና እየተሰጣቸው ነው።ዛሬ ከኢራን የተወነጨፈ ሚሳዔል ማክሸፍ እንደተቻለ የተገለጸ ሲሆን፣ ትናንት ሰኞ በተፈጸመ ጥቃት አንድ እስራኤላዊ ሞቷል።ከኢራን ወደ ማዕከላዊ እስራኤል ሚሳዔል እንደተተኮሰ እና አካባቢው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖሪያ እንደሆነ ተገልጿል።ቢቢሲ በዮርዳኖስ መዲና አማን የአደጋ ጊዜ ጥሪ መሰማቱን ዘግቧል።የእስራኤል ከተማ የሆነችው ፓታህ ቲክቫ ከንቲባ ራሚ ግሪንበርግ እንደተናገሩት፣ ሰኞ ዕለት በደረሰ የሚሳዔል ጥቃት ሁለት ሰዎች ሞተዋል። በሌላ አካባቢ ደግሞ አንድ ሰው ከባድ ጉዳት ደርሶበታል።ያጋሩ, እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ከከፈቱ ወዲህ 2,339 እስራኤላውያን መጎዳታቸው ተገለጸ
  12. 10 መጋቢት 2026ከኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ ፊት ያሉት ከባድ ቀናትየሞጅታብ ኻሜኒን እና የአባታቸውን ምስል ያዙ ደጋፊዎችየፎቶው ባለመብት,Majid Asgaripour/WANA (West Asia News Agency) via REUTERSየኢራንን ከፍተኛ ሥልጣን የተቆጣጠሩት ሞጅታባ ኻሜኒ ሁኔታዎች ውስብሰብ ናቸው። ኢራን ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከእስራኤል ጋር ውጊያ ውስጥ ገብታለች።ሥርዓቱ በቅርቡ አገዛዙን በመቃወም በመላ አገሪቱ የተካሄደው ሕዝባዊ አመጽ ካስከተለውን ተጽዕኖ በቅጡ አላገገመም።አዲሱ የበላይ መሪ ከአገሪቱ ልሂቃን ያላቸውን ድጋፍ በፍጥነት እያጠናከሩ ቢሄዱም፣ የቅቡልነት ጥያቄዎች ከፊታቸው ተደቅኗል።ከብዙ የሃይማኖት አባቶች በተለየ ሞጅታባ በሃይማኖታዊ ሰዎች ዘንድ አያቶላህ በመባል አይጠሩም።ሞጅታባ የኢራንን ሰፊ ስትራቴጂ ከመቅረጻቸው በፊት፣ አዲሱ መሪ በመጀመሪያ ራሳቸውን በእስላማዊ ሪፐብሊክ ውስብስብ የኃይል መዋቅር ውስጥ ማጽናት አለባቸው።ይህ ደግሞ ለብዙ አሥርተ ዓመታት ከዘለቀው ምስጢራዊነት ብቅ ማለት እና አዲስ በተሾሙ ወታደራዊ አዛዦች፣ በተፎካካሪ የፖለቲካ ቡድኖች እና አሁን ሊቀበሏቸው በማይችሉ የሃይማኖት መሪዎች ላይ ሥልጣን ማሳየት ማለት ነው።እስላማዊ ሪፐብሊክ ከአራት አስርት ዓመታት በላይ ሲንቀሳቀስ የቆየው በፖለቲካ ቡድኖች መካከል ከፍተኛ ፉክክር እንዲኖር በማድረግ እና ለተቋማት አነስተኛ ሥልጣን በመስጠት ነው።ነገር ግን ሁል ጊዜ ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች ላይ የመጨረሻው ይሁንታን የሚሰጡት የበላይ መሪው ናቸው።አሊ ኻሜኒ ከሞቱ በኋላ ያለው ሳምንት ስርዓቱ በአንድ ሰው ላይ ምን ያህል ጥገኛ እንደሆነ አሳይቷል።የበላይ መሪው በሌለበት፣ የውሳኔ አሰጣጡ ቆሟል እና እርግጠኛ አለመሆን በፖለቲካ ሥርዓቱ ውስጥ ሰፍኗል።የሃይማኖት ሊቃውንቱ ሞጅታባን ለመሾም በፍጥነት መንቀሳቀሳቸውም ግልጽ የሆነ ምልክት ለመላክ ይመስላል። በኢራን ምንም መሠረታዊ ነገር አልተለወጠም፤ ባለሥልጣናቱ በግል እንደሚናገሩት “ሕይወት በተለመደው መንገድ ቀጥሏል።”ሆኖም አዲስ መሪን መቀበል ይፋ እንደማድረጉ ቀላል አይደለም። የኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ ፈተናዎች፡ ጦርነት፣ ቅቡልነት እና ሥልጣንያጋሩ, ከኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ ፊት ያሉት ከባድ ቀናት
  13. 10 መጋቢት 2026በሞጅታባ ኻሜኒ ወደ ሥልጣን መምጣት የተከፋፈሉት ኢራናውያንሞጅታባ ከኢራን መሪዎች ጀርባ በመሆን ለረዥም ዓመታት ሲሰሩ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን የኢራን ባለሥልጣናትን ፊት ለፊት መጋፈጥ ይጠበቅባቸዋልየፎቶው ባለመብት,Majid Asgaripour/WANA (West Asia News Agency) via Reutersየምስሉ መግለጫ,ሞጅታባ ከኢራን መሪዎች ጀርባ በመሆን ለረዥም ዓመታት ሲሰሩ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን የኢራን ባለሥልጣናትን ፊት ለፊት መጋፈጥ ይጠበቅባቸዋልሞጅታባ ኻሜኒ የኢራን አዲሱ ከፍተኛ መሪ እና ተተኪ ሆነው የተሰየሙት አባታቸው አያቶላህ አሊ ኻሜኒ አሜሪካ እና እስራኤል በአገሪቱ ላይ ጥቃት በከፈቱበት የመጀመሪያ ቀን መገደላቸውን ተከትሎ ነው።አንዳንድ የኢራንን መንግሥት የሚደግፉ ሰዎች ለአብዮታዊ ዘቡ ቅርብ የሆነ ጠንካራ አዛዥ መሾማቸውን በማስመልከት ደስታቸውን ለመግለጽ አደባባይ ወጥተዋል።ነገር ግን ሌሎች ኢራናውያን ለቢቢሲ እንደተናገሩት አዲሱ የበላይ መሪ ለውጥ ያመጣሉ ብለው አያምኑም።በዋና ከተማዋ ቴህራን የሚኖር በ30ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኝ ሰው “ከጸጉር የቀጠነ የለውጥ ዕድል እንኳ በስርዓቱ ውስጥ የለም” ሲል ለቢቢሲ አስተያየቱን ሰጥቷል።88 አባላት ያሉት የሃይማኖት ሊቃውንት ጉባዔ ለአሊ ኻሜኒ ቅርብ ያልሆነ የበላይ መሪ መምረጥ አልቻለም ሲል የተሰማውን ቅሬታ ገልጿል።”ስለዚህ አብዛኛው ነገር ባለበት ይቀጥላል። አዲሱም መሪያቸውን ለመደገፍ እንኳን የሚያሰሙትን መፈክር መቀየር አልፈለጉም” ሲል አክሏል።ለዓመታት በኢራን አስተዳደር ውስጥ ሞጅታባ ኻሜኒ ከጀርባ በመሆን ተጽዕኖ እንደሚያደርጉ ሲነገር ቆይቷል።በርካቶች አዲሱ መሪ የአባታቸውን ጠንካራ ፖሊሲዎች ያስቀጥላሉ ሲሉ ግምታቸውን ተናግረዋል። ኢራናውያን በሞጅታባ ኻሜኒ ወደ ሥልጣን መምጣት ለምን ተከፋፈሉ?ያጋሩ, በሞጅታባ ኻሜኒ ወደ ሥልጣን መምጣት የተከፋፈሉት ኢራናውያን
  14. 10 መጋቢት 2026የፋርስ ባሕረ ሰላጤው ጦርነት 11ኛ ቀኑን ሲይዝ ጥቃቱም ቀጥሏልበምዕራብ ቴህራን አዛዲ ታወር አካባቢ የተፈጸመን ጥቃት ተከትሎ አካባቢው በጭስ ተሸፍኗልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በምዕራብ ቴህራን አዛዲ ታወር አካባቢ የተፈጸመን ጥቃት ተከትሎ አካባቢው በጭስ ተሸፍኗልየእስራኤል የመከላከያ ስርዓት ሰኞ ሌሊት በሰሜን እስራኤል የተተኮሰ ሚሳኤልን ሲያከሽፍየፎቶው ባለመብት,APየምስሉ መግለጫ,የእስራኤል የመከላከያ ስርዓት ሰኞ ሌሊት በሰሜን እስራኤል የተተኮሰ ሚሳኤልን ሲያከሽፍበሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤይሩትን ለቅቀው ሲወጡ አንድ ሕጻን መንገድ ዳር ተኝቶየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤይሩትን ለቅቀው ሲወጡ አንድ ሕጻን መንገድ ዳር ተኝቶያጋሩ, የፋርስ ባሕረ ሰላጤው ጦርነት 11ኛ ቀኑን ሲይዝ ጥቃቱም ቀጥሏል
  15. 10 መጋቢት 2026ኤርዶዋን የቱርክን የአየር ክልል መጣስ “ምንም ዓይነት አሳማኝ ምክንያት” ሊቀርብበት አይችልም አሉኢራናውያን ማክሰኞ ዕለት በካፒኮይ ድንበር በኩል  ወደ ቱርክ ገብተዋልየፎቶው ባለመብት,REUTERS/Dilara Senkayaየምስሉ መግለጫ,ኢራናውያን ማክሰኞ ዕለት በካፒኮይ ድንበር በኩል ወደ ቱርክ ገብተዋልየቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ኢራን የቱርክ የአየር ክልል ላይ የፈጸመችው ጥሰት “ምንም ዓይነት አሳማኝ ምክንያት ሊቀርብበት እንደማይችል” በመግለጽ አስጠንቀቁ።ፕሬዚዳንቱ አክለውም በቀጣናው ባሉ አገሮች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ማንንም እንደማይጠቅሙ ተናግረዋል።ከኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ቱርክ ጦርነቱ እንዲያበቃ የዲፕሎማሲ ጥረቶችን እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል።ኤርዶዋን ትናንት ማታ በነበራቸው የካቢኔ ስብሰባ ላይ “በቀናነት ማስጠንቀቂያዎችን ብንሰጥም፣ እጅግ በጣም የተሳሳቱ እና ጠብ አጫሪ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ቀጥለዋል፤ ይህም የቱርክን ወዳጅነት አደጋ ላይ ይጥላል” ብለዋል።ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት ሰኞ ዕለት ወደ ቱርክ የአየር ክልል የተተኮሰ ሁለተኛውን የኢራን ባላስቲክ ሚሳኤል የኔቶ የአየር መከላከያዎች መትተው ከጣሉ በኋላ ነው።ቱርክ የኔቶ ሁለተኛዋ ትልቁ ጦር ያላት አገር ሲሆን ከኢራን ጋር ረዥም ድንበርት ጋራለች፤ ይህም ላለፉት 500 ዓመታት የተረጋጋ ነበር።በኢራን ውስጥ ካለው አገዛዝ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ጥብቅ ግንኙነት ያለው ሌላ የኔቶ አባል አገር የለም። ኤርዶዋን በዩክሬን፣ በጋዛ እና በሌሎች በርካታ አገራት እንዳደረጉት ሁሉ ራሳቸውን እንደ አስታራቂ ማሳየት ይፈልጋሉ።ያጋሩ, ኤርዶዋን የቱርክን የአየር ክልል መጣስ “ምንም ዓይነት አሳማኝ ምክንያት” ሊቀርብበት አይችልም አሉ
  16. 10 መጋቢት 2026የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል እና አሜሪካ የጦርነቱ መቋጫ ላይ “ተጨባጭ ግብ የላቸውም” አሉየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺየፎቶው ባለመብት,Reutersሰኞ ምሽት የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ አገራቸው ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር እያካሄደች ስላለው ጦርነት ከፒቢኤስ ጋር ሰፊቃለምልልስአድርገዋል።ቁልፍ ነጥቦቹ እነሆ፦
    • የሞጅታባሜኒሹመት – አራግቺ የአሊ ኻሜኒ ልጅ ሹመት የአባታቸው አገዛዝ “ቀጣይነትን” የሚያሳይ እና በተመሳሳይ አገሪቱን “የሚያረጋጋ” እንደሆነ ተናግረዋል።
    • ከአሜሪካጋርየተደረገድርድር – ኢራን ጦርነቱ እየተካሄደ ስለ ድርድር ለመነጋገር ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር ግንኙነት ተፈጥሮ እንደሆነ ተጠይቀው፣ አራግቺ ኢራን “ከአሜሪካውያን ጋር በመነጋገር ረገድ መራር ልምድ ስላላት፤ ያ ጠረጴዛው ላይ ይቀርባል” ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል።
    • የአሜሪካእናየእስራኤልዓላማዎች – “በአእምሯቸው ውስጥ ስለ ጦርነቱ መቋጫ ተጨባጭ የሆነ ግብ አላቸው ብዬ አላስብም” ያሉት አራግቺ፣ እስካሁን ድረስ ሁሉንም ግቦቻቸውን ማሳካት እንዳልቻሉ እንደሚያምኑም ተናግረዋል።
    • የነዳጅዋጋ – አራግቺ የነዳጅ ዋጋ መጨመር “የእኛ ጥፋት አይደለም” በማለት “እስራኤላውያን እና አሜሪካውያን በእኛ ላይ የፈጸሙት ትንኮሳ እና ጥቃት” ውጤት ነው ሲሉ ሁለቱን አገራት ተጠያቂ አድርገዋል። ኢራን የሆርሙዝ የባሕር ሰርጥን “እንዳልዘጋች” እና ነዳጅ ጫኝ መርከቦች “በባሕር ሰርጡ ላይ እንዳይቀዝፉ እያደረግን አይደለም” ሲሉ አስተባብለዋል።
    • ሰላማዊ ዜጎችጉዳት – የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አገሪቱ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች “የተወሰኑ ጉዳቶች” ቢደርሱም “ሰላማዊ ሰዎችን የሚያዘወትሯቸውን ስፍራዎች ዒላማ አላደረግንም” ብለዋል።
    ያጋሩ, የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል እና አሜሪካ የጦርነቱ መቋጫ ላይ “ተጨባጭ ግብ የላቸውም” አሉ
  17. 10 መጋቢት 2026ኔታንያሁ ‘የኢራንን አገዛዝ እየሰባበርነው ነው’ አሉቤንያሚን ኔታንያሁየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከኢራን ጋር ስለሚያካሂዱት ጦርነት በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት የቴህራንን አገዛዝ “እየሰባበርነው ነው” አሉ።ዋና ዓላማችን የኢራንን ሕዝብ ከአገዛዙ [እስላማዊ አብዮት] ማላቀቅ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ “የመጨረሻው ውሳኔ ግን የእነርሱ ነው” ብለዋል።“ምንም ጥርጥር የለውም እስካሁን በተወሰደው እርምጃ ሰባብረናቸዋል፤ አሁንም እርምጃችንን እንደቀጠለ ነው” በማለት በይፋዊ የኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።ያጋሩ, ኔታንያሁ ‘የኢራንን አገዛዝ እየሰባበርነው ነው’ አሉ
  18. 10 መጋቢት 2026ትራምፕ ከፑቲን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በአንዳንድ አገራት ላይ የተጣለው ማዕቀብ ይነሳል አሉዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Reutersሰኞ ዕለት ዶናልድ ትራምፕ ባደረጓቸው በርካታ ቃለ መጠይቆች እና ጋዜጣዊ መግለጫ የነዳጅ ዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር በአንዳንድ አገራት ላይ የተጣለው ማዕቀብ ሊነሳ እንደሚችል ተናገሩ።ትራምፕ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ “በአንዳንድ አገራት ላይ ማዕቀብ ጥለናል። ይህ ሁኔታ እስኪስተካከል ድረስ ማዕቀቡን እናነሳለን” ብለዋል።ከዚያ በኋላ “አይታወቅም። ምናልባት ማዕቀቡን ላንመልሰው እንችላለን። ብዙ ሰላም ይኖራል” በማለት አክለዋል።በተመሳሳይ ጋዜጣዊ መግለጫ ከሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር “በጣም ጥሩ” ብለው የገለጹትን የስልክ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ጠቃሚ እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል።በእርግጥ ትራምፕ የትኛውን ማዕቀብ እና በየትኛው አገር ላይ የተጣለውን ለማንሳት እንዳሰቡ በዝርዝር አልተናገሩም። ከቀናት በፊት ሕንድ ከሩሲያ ነዳጅ እንድትገዛ አሜሪካ መፍቀዷ ይታወሳል።ያጋሩ, ትራምፕ ከፑቲን ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በአንዳንድ አገራት ላይ የተጣለው ማዕቀብ ይነሳል አሉ
  19. 10 መጋቢት 2026በቤይሩት የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎች ለቅቀው እንዲወጡ ወይም ‘መጠለያ ውስጥ እንዲቆዩ’ አሳሰበየሊባኖስ ሲቪል መከላከያ አባላት ሰኞ ዕለት እስራኤል በቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻዎች ላይ ባደረገችው ጥቃት ምክንያት የተጎዳ ሕንፃን ጎብኝተዋልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የሊባኖስ ሲቪል መከላከያ አባላት ሰኞ ዕለት እስራኤል በቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻዎች ላይ ባደረገችው ጥቃት ምክንያት የተጎዳ ሕንፃን ጎብኝተዋልበቤይሩት የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ ከሊባኖስ ለቅቀው የማይወጡ ከሆነ “መጠለያ ውስጥ እንዲቆዩ” አሳሰበ።ኤምባሲው ዛሬ ጠዋት በሰጠው የደህንነት ማስጠንቀቂያ የአሜሪካ ዜጎች ከቤሩት ራፊክ ሃሪሪ አውሮፕላን ማረፊያ የሚነሱ የመካከለኛው ምሥራቅ አየር መንገድ በረራዎችን በመጠቀም አገሪቱን ለቅቀው ለመውጣት “በጥብቅ” ማሰብ እንዳለባቸው አስታውቋል።ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ እስራኤል በኢራን የሚደገፈው ሔዝቦላህን ዒላማ ማድረግ ከጀመረች በኋላ በቤይሩት እና ደቡባዊ ሊባኖስ ተከታታይ የቦምብ ድብደባ እየፈጸመች ነው።ያጋሩ, በቤይሩት የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎች ለቅቀው እንዲወጡ ወይም ‘መጠለያ ውስጥ እንዲቆዩ’ አሳሰበ
  20. 10 መጋቢት 2026የባሕረ ሰላጤው አገራት ሌሊቱን በርካታ ጥቃቶች እንደተፈጸመባቸው ተናገሩበኤርቢል በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ቆንስላ ጽ/ቤት ላይ በደረሰው ጥቃት ምክንያት የእሳት ቃጠሎ ተነስቷልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በኤርቢል በሚገኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ቆንስላ ጽ/ቤት ላይ በደረሰው ጥቃት ምክንያት የእሳት ቃጠሎ ተነስቷልአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የአየር ድብደባቸውን ሲቀጥሉ እስራኤል ደግሞ ሊባኖስ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት አጠናክራለች።የባሕረ ሰላጤው አገራት ከኢራን የሚሰነዘርባቸውን የበቀል ጥቃት ሲመክቱ ማደራቸውን ተናግረዋል።
    • ሳዑዲ አረቢያ ሌሊቱን የባለስቲክ ሚሳኤል እና አምስት የድሮን ጥቃቶች ማምከኗን ገልጻለች።
    • የኩዌት ጦር ስድስት ድሮኖችን በተሳካ ሁኔታ መመከቱን እና መትቶ መጣሉን አስታውቋል።
    • ሰኞ ዕለት በባህሬን ዋና ከተማ ማናማ ላይ በተፈጸመ ጥቃት የ29 ዓመት ሴት መሞቷን ተከትሎ ፣ ባህሬን የማስጠንቀቂያ ደወል ያሰማች ሲሆን ነዋሪዎችም ወደ መጠለያ እንዲገቡ ጥሪ አቅርባለች።
    • የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (ዩኤኢ) መከላከያ ሚኒስቴር ማክሰኞ ማለዳ ላይ ከኢራን የሚነሱ “የሚሳኤል እና የድሮን ስጋቶችን” ማክሸፉን እንደቀጠለ እና የአየር መከላከያ ስርዓቶችን እና የጦር ጄቶችን ማሰማራቱን አስታውቋል።
    • የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሰሜናዊ ኢራቅ፣ ኢርቢል የሚገኘው ቆንስላ ጽ/ቤቷ በድሮን ዒላማ ተደርጎ ውድመት ቢደርስም የተጎዳ ሰው አለመኖሩን አስታውቃለች።
    ያጋሩ, የባሕረ ሰላጤው አገራት ሌሊቱን በርካታ ጥቃቶች እንደተፈጸመባቸው ተናገሩ