
አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ ከተሾሙ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባስተላለፉት መግለጫ፤ ቴህራን በሚናብ የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ጨምሮ የተገደሉ “ኢራናውያንን ደም ለመበቀል” ወደ ኋላ እንደማትል ተናገሩ።
ጭምቅ ሃሳብ
- እስራኤል በቤይሩት ላይ በፈጸመችው ጥቃት ሰዎች ሲገደሉ፣ ሔዝቦላህ ወደ እስራኤል ከ100 በላይ ሮኬቶችን ተኮሰ
- እስካሁን ድረስ ምን ያህል መርከቦች ጥቃት ደረሰባቸው?
- በባሕረ ሰላጤው ሁለት መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ አሻቀበ
- ኤፍቢአይ ኢራን ወደ ካሊፎርኒያ ድሮኖችን ልታስወነጭፍ ትችላላች ሲል አስጠነቀቀ
- በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 1,100 ሕጻናት መቁሰላቸውን ወይም መሞታቸውን ዩኒሴፍ ገለፀ
- አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ጉዳት ደርሶባቸው ከጥቃት መትረፋቸው እየተነገረ ነው
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 4 ሰአት በፊትኢራን የዜጎቿን ደም “እንደምትበቀል” እና የሆርሙዝ ወሽመጥን መዝጋቷን እንደምትቀጥል አዲሱ ጠቅላይ መሪ ተናገሩ
የምስሉ መግለጫ,የጠቅላይ መሪው መግለጫ በቴሌቪዥን ተነብቧልአዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ ከተሾሙ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባስተላለፉት መግለጫ፤ ቴህራን በሚናብ የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ጨምሮ የተገደሉ “ኢራናውያንን ደም ለመበቀል” ወደ ኋላ እንደማትል ተናገሩ።ጠቅላይ መሪው ወሳኝ የመርከብ መተላለፊ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥ መዝጋት እንዲሁም በባሕረ ሰላጤው ላይ የምትፈጽማቸውን ጥቃቶች እንደምትቀጥል ገልጸዋል።በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት የተገደሉትን አባታቸውን አያቶላህ አሊ ኻሜኒን ተክተው የተሾሙት አዲሱ የኢራን መሪ የሰጡት መግለጫ በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ተነብቧል።ሞጅታባ በመግለጫቸው አሜሪካ ከትምህርት ቤት አቅራቢያ በፈጸመችው ጥቃት 110 ሕጻናትን ጨምሮ 168 ሰዎች የተገደሉበትን ክስተት አንስተዋል።“የሰማዕቶቻችንን ደም ከመበቀል ወደ ኋላ እንደማልን ለሁሉም ሰው አረጋግጣለሁ። ልቦናችን ያለው የአጸፋ እርምጃ በታላቁ የአብዮት መሪ ሰማዕትነት ላይ ብቻ የሚያበቃ አይደለም፤ ይልቁንም እያንዳንዱ በጠላት የተሰዋ የአገሪቱ አባል በበቀል መዝገብ ውስጥ ራሱን ችሎ የሚታይ ነው” ብለዋል።ኢራን የምትፈጽመው የበቀል እርምጃ “በተወሰነ መልኩ ተጨባጭ መንገድ” መታየት መጀመሩን የጠቀሱት ጠቅላይ መሪው፤ “ሙሉ በሙሉ እስከሚሳካ ድረስ ይህ መዝገብ ከሁሉም ጉዳዮች በላይ ሆኖ ይቆያል” ሲሉ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን አመልክተዋል።ሞጅታባ ኻሜኒ፤ በሴቶች ትምህርት ቤት ላይ የደረሰውን ጥቃት “ጠላት ሆነ ብሎ የፈጸመው ወንጀል” ሲሉ ገልጸውታል። ይሄ እና ሌሎች “ተመሳሳይ ጉዳዮች በተጠያቂነት ሂደት ውስጥ ልዩ ደረጃ ይይዛሉ” ሲሉም ተናግረዋል።በተጨማሪም ሞጅታባ ከጠላት “ካሳ እንቀበላለን” አልያም “ይዞታቸውን በተመሳሳይ መጠን እናወድማለም” እንዳሉ በቴሌቪዥን የተነበበው መግለጫቸው ላይ ተጠቅሷል።“አጽንኦት መስጠት ያለብኝ [አንድ ጉዳይ]፤ በማንኛውም ሁኔታ ከጠላት ካሳ እንቀበላለን። ፈቃደኛ ካልሆነ ተገቢ ሆኖ ባገኘነው መጠን ይዞታውን እንወስዳለን። ይህ የማይቻል ከሆነ ደግሞ በተመሳሳይ መጠን ይዞታዎቹን እናወድማለን” ብለዋል።ጠቅላይ መሪው ኢራን ከዓለም የነዳጅ ምርት አንድ አምስተኛው የሚተላለፍበትን “የሆርሙዝ ወሽመጥን የመዝጋት አማራጭ” አሁንም ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ገልጸዋል።“የሆርሙዝ ወሽመጥን የመዝጋት አማራጭ በእርግጠኝነት ጥቅም ላይ መዋሉ ይቀጥላል። የጠላት ልምድ ትንሽ በሆነባቸው እና ከፍተኛ ዋጋ የሚኖራቸው ሌሎች ግንባሮችንም ለመክፈት ጥናት ተከናውኗል” ሲሉም ተጨማሪ ጥቃቶች እንደሚኖሩ አመልክተዋል።አዲሶቹ የጥቃት አማራጮች ጥቅም ላይ የሚውሉት “የጦርነት ሁኔታው ከቀጠለ” እንደሆነ ጠቅሰዋል።ያጋሩ, ኢራን የዜጎቿን ደም “እንደምትበቀል” እና የሆርሙዝ ወሽመጥን መዝጋቷን እንደምትቀጥል አዲሱ ጠቅላይ መሪ ተናገሩ - ከ 4 ሰአት በፊትየነዳጅ ዋጋ መናር ለአሜሪካ “ከፍተኛ ገንዘብ” እንደሚያስገኝ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ፕሬዝዳንት ትራምፕአሜሪካ ከእስራኤል ጋር አብራ በኢራን ላይ ጦርነት ከከፈተች በኋላ በመካከለኛው ምሥራቅ በተፈጠረው የነዳጅ ምርት እና ዝውውር መስተጓጎል ምክንያት የታየው የዋጋ መናር ለአገራቸው አትራፊ መሆኑን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ገለጹ።ፕሬዝዳንቱ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ እየናረ ካለው የዓለም የነዳጅ ዋጋ አሜሪካ ትርፋማ እንደምትሆን ጠቅሰዋል።ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ “እስካሁን ባለው ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም ላይ በከፍተኛ ልዩነት ትልቋ የነዳጅ አምራች ናት፤ ስለዚህም የነዳጅ ዋጋ ሲያሻቅብ ብዙ ገንዘብ እናገኛለን” በማለት አገራቸው ተጠቃሚ መሆኗን አመልክተዋል።ጨምረውም “ነገር ግን እንደ ፕሬዝዳንትነቴ ለእኔ በጣም ወሳኙ ነገር፣ ክፉዋ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዳይኖራት በማድረግ መካከለኛው ምሥራቅን ብሎም ዓለምን እንዳታወድም ማድረግ ነው። በፍጹም ያ እንዲፈጠር አልፈቅድም” ብለዋል።ያጋሩ, የነዳጅ ዋጋ መናር ለአሜሪካ “ከፍተኛ ገንዘብ” እንደሚያስገኝ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናገሩ - ከ 6 ሰአት በፊትኢራን የአብዮታዊ ዘቧ ከፍተኛ አዛዥ መገደላቸውን አረጋገጠችየኢራን መንግሥት የዜና ወኪል የሆነው ፋርስ የአገሪቱ እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ የአየር እና የህዋ (ኤሮስፔስ) ወታደራዊ ኃይሎች አዛዥ የቀብር ሥነ ሥርዓት መፈጸሙን ዘገበ።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት በከፈቱበት ጊዜ በርካታ የአብዮታዊው ዘብ አመራሮች የተገደሉ ቢሆንም ይፋ አልተደረገም። ነገር ግን ዛሬ የኤሮስፔስ ኃይሎች አዛዡ የቀብር ሥርዓት መፈጸሙን በኢራን መገናኛ ብዙኃን ተዘግቧል።እየወጡ ያሉ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት አዛዡ ኢስማኤል ዴህጋን የተገደሉት መኖሪያቸው ውስጥ “ከባለቤታቸው፣ ከሁለት ልጆቻቸው እና ከሴት አያታቸው ጋር ነው።”ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በፈጸመችው ጥቃት የሄዝቦላህ ራድዋን ወታደራዊ ክፍል አዛዥን እና ከ100 በላይ የቡድኑን አባላት መግደሏን አስታውቃለች።የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አዛዡ አቡ አሊ ራያን የተገደለው ቅዳሜ ዕለት በተፈጸመ ጥቃት መሆኑን ገልጸዋል።ቃል አቀባይዋ አክለውም ከቡድኑ አዛዥ በተጨማሪ ከአንድ መቶ በላይ አባላቱ መገደላቸውን እና ከ60 በላይ የቡድኑ የማዘዣ ማዕከላት መደምሰሳቸውን ተናግረዋል።ያጋሩ, ኢራን የአብዮታዊ ዘቧ ከፍተኛ አዛዥ መገደላቸውን አረጋገጠች
- ከ 6 ሰአት በፊትየአሜሪካ ባሕር ኃይል በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ መርከቦችን ለማጀብ “ዝግጁ እንዳልሆነ” ተገለጸ
የፎቶው ባለመብት,PA Mediaየአሜሪካ ኢነርጂ መሥሪያ ቤት ሚኒስትር የሆኑት ክሪስ ራይት፤ የአገሪቱ ባሕር ኃይል ኢራን በምትቆጣጠረው የሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ለማጀብ ዝግጁ አለመሆኑን ተናገሩ።ሚኒስትሩ ማክሰኞ ዕለት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ግን የአሜሪካ ባሕር ኃይል በወሽመጡ በኩል ያለፈን ነዳጅ ጫኝ በተሳካ ሁኔታ ማጀቡን ተናግረው ነበር።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም ከዚህ ቀደም “አስፈላጊ ከሆነ” አገራቸው በወሽመጡ የሚያልፉ መርከቦችን እንደምታጅብ መግለጻቸው ይታወሳል።የኢነርጂ ሚኒስትሩ ዛሬ ከአሜሪካው የቴሌቪዥን ጣቢያ ‘ሲኤንቢሲ’ ጋር በነበራቸው ቆይታ እጀባው “በአንጻራዊነት በቅርቡ ይሆናል፤ አሁን ግን ሊሆን አይችልም” ብለዋል።“በአሁኑ ሰዓት ሁሉም ወታደራዊ ኃይሎቻችን ትኩረታቸው የኢራንን የማጥቃት አቅሞችን እንዲሁም ለማጥቃት የሚሆን ግብዓት የሚያቀርበውን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪን ማጥፋት ላይ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የተከፈተባት ኢራን ከዓለም ነዳጅ አንድ አምስተኛው የሚተላለፍበትን የሆርሙዝ ወሽመጥ ዘግታለች። “ትዕዛዙን ተላልፈው” በአካባቢው የሚያልፉ መርከቦች ላይም ጥቃት እየፈጸመች ነው።በዚህም ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ አሳይቷል። የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ከአራት ዓመት ገደማ በኋላ 120 ዶላር ገብቶ የነበረ ሲሆን፣ ኋላ ላይ ግን ቀንሷል።ዋይት ሐውስ የአሜሪካ ባሕር ኃይል በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፍ ነዳጅ ጫኝ መርከብን እያጀበ አለመሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ግን ዋጋው ተመልሶ ጭማሪ አሳይቷል።ያጋሩ, የአሜሪካ ባሕር ኃይል በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ መርከቦችን ለማጀብ “ዝግጁ እንዳልሆነ” ተገለጸ - ከ 7 ሰአት በፊትኢራን ባለቤትነቱ የአሜሪካ በሆነው መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸሟን አረጋገጠች
የፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ማክሰኞ ዕለት በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ላይ ባለቤትነቱ የአሜሪካ የሆነው መርከብ ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ኃላፊነት መውሰዱን ከፊል ይፋዊ የሆነው ፋርስ የዜና ወኪል ዘገበ።ከአብዮታዊ ዘቡ ጋር ግንኙነት ያለው ፋርስ ያወጣው ዘገባ እንደሚያሳየው በባሕረ ሰላጤው ሰሜናዊ ክፍል ላይ የአሜሪካ መርከብ ተመትቷል።በኢራቅ የውሃ ክፍል ላይ ባስራ በተባለው ስፍራ አቅራቢያ ጥቃት የተፈጸመባቸው ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ናቸው።ከእነዚህ አንዱ የሆነው ‘ሴፍሲ ቪሽኑ’ የተባለው የአሜሪካ መርከብ ሲጓዝ የነበረው የማርሻል ደሴት ባንዲራን እያውለበለበ ነው።የዜና ወኪሉ ባወጣው ዘገባ በአሜሪካው መርከብ ላይ ጥቃት የተፈጸመበትን ቅጽበት የሚያሳይ ቪዲዮ አካትቷል። ቪዲዮው፤ በእኩለ ሌሊት በውሃ ክፍሉ ላይ እየተጓዘ የነበረው መርከብ ላይ ተፈጠረውን ከፍተኛ ፍንዳታ ያሳያል።የህንድ ባለሥልጣናት ‘ሴፍሲ ቪሽኑ’ ጥቃት የተፈጸመበት “ነጭ ቀለም ባለው፣ ፈንጂ የጫነ ፈጣን ሰው አልባ ጀልባ” እንደሆነ ተናግረው ነበር። ጀልባው “ከመርከቡ ጋር ተጋጭቶ፤ ከፍተኛ እሳት መያያዙንም” ገልጸዋል።በዚህ ጥቃት አንድ ሰው የተገደለ ሲሆን ቀሪዎቹ የመርከቡ ሠራተኞችን ማዳን ተችሏል።ፋርስ የዜና ወኪል በዘገባው፤ መርከቡ ከእስላማዊ አብዮታዊ ዘቡ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ “ማክበር አለመቻሉን” ጠቅሷል።
የፎቶው ባለመብት,FARSየምስሉ መግለጫ,ፋርስ ዜና ወኪል ያወጣው ቪዲዮ ጥቃቱ የደረሰበትን ቅጽበት የሚያሳይ እንደሆነ ገልጿልያጋሩ, ኢራን ባለቤትነቱ የአሜሪካ በሆነው መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸሟን አረጋገጠች - ከ 7 ሰአት በፊትአሜሪካ ዒላማዋን በትክክል ለመምታት ምን ዓይነት መሣሪያ እየተጠቀመች ነው?
የፎቶው ባለመብት,Centcomየአሜሪካ እና የእስራኤል ኃይሎች 13ተኛ ቀኑን በያዘው ጦርነት በኢራን ወታደራዊ ይዞታዎች እንዲሁም ተቋማት ላይ እየፈጸሙ ያሏቸውን ጥቃቶች የሚያሳዩ በርካታ ቪዲዮዎችን ለቅቀዋል።ጥቃት ለመፈጸም ከዋሉት መሣሪያዎች መካከል ‘GBU-31 JDAMs’ ወይም ‘ባንከር በስተርስ’ በሚለው ስያሜ ይበልጥ የሚታወቀው ተተኳሽ ይገኝበታል። ከ907 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝነው ይህ መሣሪያ፤ ጠንካራ ስፍራዎችን ሰብሮ መግባት ይችላል።ብዙውን ጊዜ በእነዚህ መሣሪያዎች ጥቃት የሚፈጸመው በሳተላይት አቅጣጫ ጠቋሚነት በመታገዝ ነው። ረቡዕ ምሽት ግን የአሜሪካ ጦር ቦንቦችን በዒላማው ላይ ለመጣል የጨረር መለያን እየተጠቀመ መሆኑን የሚያመለክት ማስረጃ ታይቷል።በዛሬው ዕለት የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር ውስጥ አርፎ የነበረ አውሮፕላን የፈጸማቸውን ጥቃቶች የሚያሳይ ቪዲዮ ለቅቋል።ቪዲዮው ዒላማው ላይ ጨረር ሲያርፍ በግልጽ ያሳያል። ጨረሩ ጥቃት በሚፈጽመው አውሮፕላን የነዳጅ መያዣ (ፖድ) ላይ የሚቀመጥ ሲሆን፣ አብራሪውም ዒላማው ላይ እንዲያነጣጠር ያደርገዋል።ተተኳሹ ከጄቱ ከወጣ በኋላ በተገጠመለት መቆጣጠሪያ አማካኝነት እየተመራ ጨረሩ ያረፈበት ስፍራ ላይ ያርፋል። ቦምቡ ከብዙ ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ ቢጣልም እንኳ ከዒላማው ፈቀቅ የሚለው በአንድ ወይም ሁለት ሜትር ልዩነት ነው።ይህ የጨረር መከታተያ መሣሪያ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ዒላማዎችን ለመምታትም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፤ ሁሌም ምርጥ ነው ማለት ግን አይደለም።ደመና እና ሌሎች የከባቢ አየር ሁኔታዎች ዒላማውን በትክክል የመምታት አቅሙን በከፍተኛ መጠን ሊቀንሱት ይችላሉ። በጂፒኤስ የሚታገዝ መሣሪያ ጥቅም ላይ የሚለው እንግዲህ በእንዲህ ዓይነቱ ወቅት ነው።ጨረርም፣ ጂፒኤስም በመጠቀል ዒላማ የሚያደርጉ መሣሪያዎች በመኖራቸው እንደ ሁኔታው አመቺነት ተገቢው አማራጭ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።ያጋሩ, አሜሪካ ዒላማዋን በትክክል ለመምታት ምን ዓይነት መሣሪያ እየተጠቀመች ነው? - ከ 8 ሰአት በፊትየእስራኤል ጦር የኢራን “የኒውክሌር መሣሪያ ማምረቻ ግቢን” መትቻለሁ አለ
የፎቶው ባለመብት,AFPየእስራኤል ጦር “ባለፉት ቀናት” በፈጸማቸው ጥቃቶች ቴህራን ውስጥ የሚገኝ የኢራን “ኒውክሌር ማምረቻ ግቢን” መምታቱን ገለጸ።የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት፤ ጥቃት የደረሰበት ስፍራ ኢራን “ወሳኝ” የኒውክሌር መሣሪያ “አቅሞቿን ለማሳደግ” ለማሳደግ ትጠቀምበት ነበር ብሏል።‘ታሌግሃን’ የተባለው ይህ ግቢ የተመታው ባለፉት ቀናት ውስጥ አካባቢው ላይ በተፈጸመው ተከታታይ ጥቃት እንደሆነ ተገልጿል።የእስራኤል ጦር በቴሌግራም ገጹ ባወጣው መግለጫ “የ‘ታሌግሃን’ ግቢ የኒውክሌር መሣሪያዎችን ለማልማት የሚያስችሉ ወሳኝ አቅሞችን ለማሳደግ በአገዛዙ ጥቅም ላይ ውሏል” ብሏል።እንደ እስራኤል ጦር ገለጻ፤ ስፍራው በአውሮፓውያኑ 2000ዎቹ “የምሥጢራዊ የኒውክሌር መሣሪያ ልማት ፕሮግራም” አካል ሆኖ ፈንጂዎችን ለማምረት እና ሙከራዎችን ለማድረግ ይውል ነበር።መግለጫው ባለፈው ዓመት ሐምሌ ውስጥ በኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች የአገሪቱ የኒውክሌር መሣሪያ ፕሮግራም ላይ “ከፍተኛ ጉዳት” እንዳደረሰም አንስቷል።አሁን ጥቃት ተፈጽሞበታል የተባለው ይህ ስፍራ በአውሮፓውያኑ ጥቅምት 2024 ላይም ተመትቶ ነበር።ጦሩ በመግለጫው “ግቢው [በአውሮፓውያኑ] ጥቅምት 2024 ጥቃት ከደረሰበት በኋላ አገዛዙ በድጋሚ መልሶ ለማቋቋም እርምጃዎችን መውሰዱን የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ለይቷል” ብሏል።የእስራኤል መንግሥት ይህንን ቢልም ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ ለማምረት እየሠራች ነው በሚል የሚቀርብባትን ክስ በተደጋጋሚ ውድቅ አድርጋለች። የኒውክሌር ፕሮግራሟ ለሰላማዊ ዓላማ የሚውል እንደሆነም ገልጻለች።ይሁን እንጂ ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ ሳትታጠቅ ለጦር መሣሪያነት በሚውል ደረጃ የበለጸገ ዩራኒየም ያላት ብቸኛዋ አገር ነች።ያጋሩ, የእስራኤል ጦር የኢራን “የኒውክሌር መሣሪያ ማምረቻ ግቢን” መትቻለሁ አለ - ከ 8 ሰአት በፊትቪዲዮ፡ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ በተወንጫፊ ተመትተው የወደሙት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች
00:28ረቡዕ ዕለት ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ከኢራቅ አቅራቢያ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ላይ “ምንነቱ ባልታወቀ” ተወንጫፊ ተመትተው ጉዳት እንደደረሰባቸው ተዘግቦ ነበር። ዛሬ ሐሙስ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸውን መርከቦች የሚያሳዩ ምሥሎች እየወጡ ነው።ያጋሩ, ቪዲዮ፡ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ በተወንጫፊ ተመትተው የወደሙት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች - ከ 9 ሰአት በፊትዴሞክራቶች በኢራን ትምህርት ቤት ላይ ስለተፈጸመው ጥቃት የመከላከያ ሚኒስቴሩ ማብራሪያ ጠየቁ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በሴቶች ትምህርት ቤት ላይ በተፈፀመው ጥቃት 110 ሕጻናትን ጨምሮ 168 ሰዎችን መሞታቸውን የኢራን ባለሥልጣናት ገልጸዋልየአሜሪካ ሴኔት አባላት የሆኑ ዴሞክራቶች የመከላከያ ሚኒስትሩ ፔት ሄግሴት በኢራን በሚገኝ የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ ስለተፈፀመው ጥቃት መልስ እንዲሰጡ ጠየቁ።አሜሪካ እና እስራኤል በቴህራን ላይ ጥቃት በከፈቱበት የመጀመሪያ ቀናት በትምህርት ቤቱ ላይ በደረሰ ጉዳት 110 ሕጻናትን ጨምሮ 168 ሰዎችን መሞታቸውን የኢራን ባለሥልጣናት ገልጸዋል።የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን የፔንታጎን መርማሪዎች በጥቃቱ ጦሩ ተጠያቂ ሊሆን እንደሚችል እምነት እንዳላቸው የዘገቡ ሲሆን ድምዳሜ ላይ ግን አለመድረሳቸው ጠቅሰዋል።ፔንታጎን በጉዳዩ ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ከመግለጽ ባሻገር የሰጠው ዝርዝር መረጃ የለም።በሴኔት ውስጥ አባል የሆኑ ዴሞክራቶች በሙሉ በሚናብ ስለተፈፀመው ጥቃት ለመከላከያ ሚኒስትሩ ሄግሴት ዝርዝር ጥያቄዎችን አቅርበዋል።አሜሪካ በጥቃቱ ላይ ሚና እንደነበራት ከተረጋገጠ ባለፉት አስርት ዓመታት አገሪቱ በመካከለኛው ምሥራቅ በነበራት ተሳትፎ በአንድ ስፍራ ላይ በሚገኙ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ያደረሰችው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሞት ይሆናል።ምንም እንኳን የአሜሪካ ቶማሃውክ ሚሳዔል በትምህርት ቤቱ አቅራቢያ በሚገኘው የኢራን ወታደራዊ ተቋም ላይ ድብደባ የፈጸመ ቢሆንም፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን ምንም ማስረጃ ሳይጠቅሱ ኢራን ጥቃቱን መፈጸሟን ተናግረዋል።ሄግሴት ባለፈው ሳምንት አሜሪካ ሰላማዊ ዜጎችን ዒላማ እንዳላደረገች እና ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ያጋሩ, ዴሞክራቶች በኢራን ትምህርት ቤት ላይ ስለተፈጸመው ጥቃት የመከላከያ ሚኒስቴሩ ማብራሪያ ጠየቁ - ከ 9 ሰአት በፊት13ኛ ቀኑን በያዘው የፋርስ ባሕረሰላጤው ጦርነት ጥቃቶች ቀጥለዋል
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ሐሙስ ዕለት እስራኤል በቤይሩት የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ በፍርስራሾች መካከል ጭስ ይታያልአሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ጦርነት 13ኛ ቀኑን በያዘበት ዕለት በቀጣናው የሚፈጸሙ ጥቃቶች ቀጥለዋል።- እስራኤል በኢራን “መጠነ ሰፊ ጥቃት” መፈጸም መጀመሯን ገልጻለች። እስራኤል በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት የፈጸመችውን ድብደባ ተከትሎ ስምንት ሰዎች መሞታቸው ከተገለፀ በኋላ በምሥራቅ ሊባኖስ የሚኖሩ አካባቢያቸውን ለቅቀው እንዲወጡ አዝዛለች።
- ኢራን በቀጠናው የሚገኙ የተለያዩ አገራት ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ቀጥላለች። ጣሊያን በሰሜን ኢራቅ ኢርቢል በሚገኘው የጦር ሠፈሯ ላይ ትናንት ሌሊት ጥቃት መፈጸሙን ገልጻለች። በኩዌት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያም የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ተዘግቧል።
- ሦስት የጭነት መርከቦች ትናንት ሌሊት ጥቃት ደርሶባቸዋል። ሁለቱ በኢራቅ አንዱ ደግሞ በዩኤኢ ወደቦች ላይ ሳሉ ጥቃት የደረሰባቸው ሲሆን የአንድ ሰው ሕእወት ማለፉ ተዘግቧል።
- ሐሙስ ዕለት የነዳጅ ዋጋ በበርሜል 100 ዶላር ደርሷል።
- 12 መጋቢት 2026ኢራን በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ እንደማትሳተፍ አስታወቀች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesኢራን በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ እንደማትሳተፍ አስታወቀች።የኢራን ስፖርት እና ወጣቶች ሚኒስትር አህመድ ዶኒያማሊ አገሪቱ በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ ልትሳተፍ እንደማትችል አስታውቀዋል።ኢራን በመጪው ሰኔ ወር በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ አዘጋጅነት በሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ እንደምትሳተፍ ተገልጾ ነበር።ኢራን ከኒውዚላንድ፣ ቤልጂየም እንዲሁም ግብጽ ጋር ግጥሚያዎችን በሎስ አንጀለስ እና ሲያትል እንደምታደርግ የወጣው መርሐ ግብር ያሳያል።አሜሪካ እና እስራኤል አገሪቱ ላይ ጥቃት ፈጽመው የአገሪቱን የበላይ መሪ ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣኖችን እና ወታደራዊ መሪዎችን መግደላቸውን ተከትሎ የአገሪቱ ተሳትፎ ጥያቄ ውስጥ ወድቋል።ረቡዕ ዕለት የፊፋው ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ኢራን መሳተፍ እንደምትችል እንዳረጋገጡላቸው ተናግረው ነበር።የፊፋው ፕሬዝዳንት በኢንስታግራም ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ከትራምፕ ጋር ተገናኝተው ስለ ዓለም ዋንጫ ዝግጅት መወያየታቸውን ጠቅሰዋል።ነገር ግን ዶኒያማሊ ማክሰኞ ከኢሪብ ስፖርት ኔትወርክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ይህ ብልሹ መንግሥት መሪያችንን ከገደለ በኋላ በምንም ዓይነት ሁኔታ በዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ ተስማሚ ሁኔታዎች የሉንም።”ልጆቻችን ደህንነታቸው የተጠበቀ አይደለም፤ እና ልንሳተፍበት የምንችልበት ሁኔታም የለም።”አክለውም “ባለፉት ስምንትና ዘጠኝ ወራት ውስጥ ሁለት ጦርነቶች ተጭነውብናል፤ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ተገድለዋል፤ ሰማዕት ሆነዋል። ስለዚህ በእርግጠኝነት የመሳተፍ እድል የለንም” ብለዋል።ያጋሩ, ኢራን በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ እንደማትሳተፍ አስታወቀች - 12 መጋቢት 2026በመካለኛው ምሥራቅ ረቡዕ ሌሊት የደረሱ ጥቃቶች በምሥልረቡዕ ሌሊት በመካከለኛው ምሥራቅ የተለያዩ ጥቃቶች ተፈጽመዋል። አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን ላይ በርካታ ጥቃቶችን ሲሰነዝሩ ኢራንም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ድሮኖችን እና ሚሳዔሎችን አስወንጭፋለች።የዩናይትድ ኪንግደም የባሕር መርከብ ንግድ ድርጅት ረቡዕ ሌሊት ሦስት መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል። ሁለቱ መርከቦች ላይ ጥቃት የደረሰው በኢራቅ ወደብ ላይ ሲሆን አንዱ ደግሞ በአረብ ኤምሬትስ ወደብ ላይ መሆኑ ተገልጿል።
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በኢራን በሚደገፈው ታጣቂ ሔዝቦላህ የተተኮሰ ሮኬት በማዕከላዊ እስራኤል ክፋር ዮና አቅራቢያ ወድቋል
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,እስራኤል በማዕከላዊ ቤይሩት የባህር ዳርቻ ላይ በፈጸመችው ጥቃት ጥቃት በትንሹ ስምንት ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በባህሬን ዋና ከተማ ማናማ ዛሬ ማለዳ ላይ ጭስ ታይቷልያጋሩ, በመካለኛው ምሥራቅ ረቡዕ ሌሊት የደረሱ ጥቃቶች በምሥል - 12 መጋቢት 2026እስራኤል በቤይሩት ላይ በፈጸመችው ጥቃት ሰዎች ሲገደሉ፣ ሔዝቦላህ ወደ እስራኤል ከ100 በላይ ሮኬቶችን ተኮሰ
የፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,በእስራኤል ጥቃት የደረሰ ጉዳትእስራኤል በሊባኖስ ላይ ባካሄደችው የአየር ጥቃት በርካታ ሰዎች ሲገደሉ በዋና ከተማዋ ቤይሩት በሚገኝ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ ስምንት ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር እንዳለው ጥቃቱ በአንድ መኪና ላይ በቀጥታ የተፈጸመ ሲሆን ከተገደሉት በተጨማሪ 21 ሰዎች ቆስለዋል። በሁለተኛ ዙር ጥቃት ደግሞ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለመርዳት በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ተጨማሪ ጉዳት ደርሷል።ረቡዕ ሌሊት ዋና ከተማዋ ቤይሩት ከባድ የአየር ድብደባ የተፈጸመባት ሲሆን በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች ውስጥ ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰምቷል። በዚህም የተነሳ ከደቡባዊ የከተማዋ አካባቢ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ጥቃቱን ለመሸሽ ቤታቸውን ጥለው ወጥተዋል።የተለያዩ የከተማዋ ክፍሎችን ዒላማ ያደረጉ ሌሎች የአየር ጥቃቶች ተፈጽመዋል።የእስራኤል ጦር ሠራዊት እንዳለው “መጠነ ሰፊ” ተከታታይ የአየር ጥቃቶችን ሌሊቱን ሊባኖስ ውስጥ መፈጸሙን አረጋግጦ፣ በ30 ደቂቃዎች ውስጥ አስር የሔዝቦላህ ጽሕፈት ቤቶችን ዒላማ ማድረጉን ገልጿል።በምላሹም ሔዝቦላህ ከ100 በላይ ሮኬቶችን ወደ ሃይፋ እና ሌሎች በሰሜን እስራኤል ወደሚገኙ አካባቢዎች ተኩሷል። ይህም ከወዳጁ ኢራን ጋር በመቀናጀት የተፈጸመ ጥቃት ነው ተብሏል።ያጋሩ, እስራኤል በቤይሩት ላይ በፈጸመችው ጥቃት ሰዎች ሲገደሉ፣ ሔዝቦላህ ወደ እስራኤል ከ100 በላይ ሮኬቶችን ተኮሰ - 12 መጋቢት 2026እስካሁን ድረስ ምን ያህል መርከቦች ጥቃት ደረሰባቸው?
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በትናንትናው ዕለት ሦስት መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ ምንነቱ ባልታወቀ ተወንጫፊ ጥቃት ደርሶባቸዋልበአረቢያ ባሕረ ሰላጤ፣ በሆርሙዝ ወሽመጥ እና በኦማን ባሕረ ሰላጤ ከአውሮፓውያኑ ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 11 ድረስ ብቻ 13 መርከቦች ጥቃት እንደደረሰባቸው የዩናይትድ ኪንግደም የባሕር ንግድ ድርጅት አስታወቀ።ሌሊቱን በኢራቅ የባሕር ዳርቻ በባስራ ከተማ በሁም ቃስር ወደብ አቅራቢያ ተጨማሪ ሁለት መርከቦች ላይ ጥቃት ደርሶባቸዋል። በዩኤኢ ወደብ አቅራቢያ ደግሞ አንድ ኮንቴይነር የጫነ መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተገልጿል።በጥቃቱ 38 ሠራተኞችን ከአደጋ ማትረፍ ሲቻል አንድ ሰው መሞቱን የኢራቅ ወደቦችን የሚያስተዳድረው ኩባንያ አስታወቋል።ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ሰሜናዊ ጀበል አሊ ወደብ አቅራቢያ ኮንቴይነር የጫነች መርከብ ምንነቱ ባልታወቀ ተወንጫፊ ጥቃት እንደደረሰባት እና መጠነኛ እሳት መቀስቀሱን የዩኬ ባሕር ንግድ ድርጅት አስታውቋል። አክሎም ጉዳቱን መጠን ለማወቅ ጨለማ በመሆኑ እንዳልተቻለ ተገልጿል።ያጋሩ, እስካሁን ድረስ ምን ያህል መርከቦች ጥቃት ደረሰባቸው? - 12 መጋቢት 2026በባሕረ ሰላጤው ሁለት መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ አሻቀበ
የፎቶው ባለመብት,Reutersረቡዕ ሌሊት በኢራቅ ባስራ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ኡም ቃስር ወደብ ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ጥቃት ጥቃት ተፈጸመ።የኢራቅ ወደብን የሚያስተዳድረው ኩባንያ ከመርከቦቹ ላይ የ38 ሠራተኞችን ሕይወት ማትረፉን እና አንድ ሰው መሞቱን ለአገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን ገልጿል።መርከቦችን የሚከታተሉ ድረገጾች ሁለቱ ነዳጅ ጫኞች ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ የሕይወት አድን ጀልባዎች ከብበዋቸው አሳይተዋል።መርከቦቹ ላይ ፍንዳታው በምን ምክንያት እንደተከሰተ እስካሁን ድረስ ግልጽ አይደለም። በባስራ የሚገኝ የደኅንነት ሠራተኛ ለሲኤንኤን እንደተናገሩት ከሆነ ፈንጂ የተጠመደበት የኢራን ጀልባ ሁለቱ መርከቦችን እንዳጠቃች ይታመናል። ነገር ግን በጉዳዩ ላይ ምርመራ እየተካሄደ እንደሆነ ተናግረዋል።የዩናይትድ ኪንግደም የንግድ መርከብን የሚቆጣጠረው ተቋም ጥቃቱን በተመለከተ ተመሳሳይ መረጃ እንደደረሰው ያስታወቀ ሲሆን፣ የኢራቅ ነዳጅ ዘይት ገበያ ድርጅት በደረሰው አደጋ “በጥልቅ ማዘኑን” ገልጿል።በሁሉም የኢራቅ ወደቦች ለጊዜው ማንኛውም እንቅስቃሴ ተቋርጧል።ረቡዕ ዕለት ሦስት የንግድ መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ “ምንነቱ ባልታወቀ ተወንጫፊ” መመታታቸውን እና ቢያንስ አንዱ በእሳት መያያዙ ተዘግቧል።ይህ ጥቃት የተፈጸመው አሜሪካ በአካባቢው በነበሩ በርካታ የኢራን ባሕር ኃይል መርከቦች ላይ ጥቃት ፈጽማ ማውደሟን ካሳወቀች ከሰዓታት በኋላ ነው።የዩኬ የባሕር ንግድ መርከብ ጨምሮ እንዳስታወቀው “ያልታወቀ ተወንጫፊ” የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የጭነት መርከቦች ከሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲወጡ ተደርጓል።ኢራን አሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት መፈጸማቸውን እስካላቆሙ ድረስ በወሽመጡ በኩል ነዳጅ አያልፍም ስትል አስጠንቅቃለች።ያጋሩ, በባሕረ ሰላጤው ሁለት መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ አሻቀበ - 12 መጋቢት 2026ኤፍቢአይ ኢራን ወደ ካሊፎርኒያ ድሮኖችን ልታስወነጭፍ ትችላላች ሲል አስጠነቀቀባለፈው ሳምንት ኤፍቢአይ ለሎስ አንጀለስ የሕግ አስከባሪ አካላት በጻፈው የውስጥ ማስታወሻ ኢራን ወደ ካሊፎርኒያ ድሮኖች ልታስወነጭፍ እንደምትችል ማስጠንቀቁ ተዘገበ።በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ እንደዘገበው ከሆነ ኢራን በካሊፎርኒያ ላይ “ድንገተኛ ጥቃት” ለመፈጸም ከባሕር ላይ ድሮን ልታስወነጭፍ ትችላለች ሲል አስጠንቅቋል።የአሜሪካ መንግሥት እና ካሊፎርኒያ ግዛት ሕግ አስከባሪ የደኅንነት ባለሥልጣናት ለዜና ተቋሙ እንደተናገሩት ማስታወሻው ላይ እንደሰፈረው የሚታወቅ ወይንም የተለየ ስጋት የለም።የሎስ አንጀለስ የሕግ አስከባሪ አካላት መረጃውን ያገኙት በኢራን ላይ አሜሪካ እና እስራኤል ጦርነት ከመክፈታቸው በፊት ነው።የካሊፎርኒያ አስተዳዳሪ ጋቪን ኒውሰም በኤክስ ገጻቸው ላይ እንደጻፉት “በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት የተለየ ስጋት እንዳለ ባናውቅም በግዛታችን ለሚከሰት ማንኛውም አደጋ ዝግጁ ሆነን እንጠብቃለን” ብለዋል።ያጋሩ, ኤፍቢአይ ኢራን ወደ ካሊፎርኒያ ድሮኖችን ልታስወነጭፍ ትችላላች ሲል አስጠነቀቀ
- 12 መጋቢት 2026በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 1,100 ሕጻናት መቁሰላቸውን ወይም መሞታቸውን ዩኒሴፍ ገለፀበመካከለኛው ምሥራቅ የተከሰተው ጦርነት “በቀጣናው ለሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናት እሰቃቂ ነው” ሲል የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት ኤጀንሲ (ዩኒሴፍ) አስታወቀ።አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 21/2018 ዓ.ም. ኢራን ላይ ጥቃት ከከፈቱበት ዕለት አንስቶ ከ1,100 በላይ ሕጻናት ጉዳት ወይም ሞት እንደደረሰባቸው ዩኒሴፍ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።መግለጫው አክሎም ይህ መረጃ በኢራን የተገደሉ 200፣ በሊባኖስ 91፣ በእስራኤል አራት እንዲሁም በኩዌት አንድ ሕፃናትን ያጠቃልላል።ዩኒሴፍ “የሕፃናትን መገደል እና የአካልጉዳት ማድረስ ወይም ሕጻናት የሚገለገሉባቸውን አስፈላጊ አገልግሎቶች ማውደም እና መቋረጥ ምንም ምከንያት የሚቀርብበት ነገር አይደለም “ ብሏል።ድርጅቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተዋጊ አካላት “ጦርነቱን ቆሞ ወደ ዲፕሎማሲ ድርድር እንዲመጡ” ያቀረቡትን ጥሪ በድጋሚ እንደሚያቀርብ አስታውቋል።በተጨማሪም በጦርነት የሚሳተፉ አካላት “በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ፣ ይህም ሕፃናትን የሚጎዱ ፈንጂዎችን ከመጠቀም መቆጠብን ጨምሮ፣ የጦር መሳሪያዎችን በመምረጥ ረገድ ሁሉንም አስፈላጊ ጥንቃቄዎች እንዲወስዱ” ጥሪ አቅርቧል።ያጋሩ, በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 1,100 ሕጻናት መቁሰላቸውን ወይም መሞታቸውን ዩኒሴፍ ገለፀ
- 11 መጋቢት 2026ጦርነቱ “እንዲያበቃ በፈለግኩ ጊዜ ያበቃል” – ፕሬዝዳንት ትራምፕ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካውፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለአክሲዮስ የዜና ወኪል ከኢራን ጋር የሚደረገው ጦርነት “በቅርቡ” ያበቃል ሲሉ ተናግረው “ምንም ዒላማ የሚደረግ የቀረ ነገር የለም” አሉ።በኢራን ላይ የሚካሄደው ጦርነት “እንዲያበቃ በፈለግኩ ጊዜ ሁሉ ያበቃል” ሲሉ ትራምፕ መናገራቸውን የዜና አውታሩ ዘግቧል።አሜሪካ ከእስራኤል ጋር በመሆን ኢራን ላይ ጥቃት መፈጸም የጀመረችው የካቲት 21/2018 ዓ.ም. ነበር።የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ ረቡዕ ዕለት ጦርነቱ “ያለምንም የጊዜ ገደብ ይቀጥላል” ብለው ነበር።ካትዝ እንዳሉት ጦርነቱ አስፈላጊ እስከሆነበት ጊዜ ድረስ እና የእስራኤል እና የአሜሪካ የጋራ ዘመቻ ሁሉም ዓላማዎች እስኪሳኩ ድረስ ይቀጥላል ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ እና ዘ ታይምስ ኦፍ ኢዝራኤል ዘግበዋል።ያጋሩ, ጦርነቱ “እንዲያበቃ በፈለግኩ ጊዜ ያበቃል” – ፕሬዝዳንት ትራምፕ - 11 መጋቢት 2026አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ጉዳት ደርሶባቸው ከጥቃት መትረፋቸው እየተነገረ ነው
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,አዲሱ ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒየኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ መሪ ሆነው የተመረጡት የቀድሞው መሪ ልጅ ሞጅታባ ኻሜኒ ያሉበት የጤናን ሁኔታ በተመለከተ የሚወጡ መረጃዎች አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸውን ዘገባዎች እያመለከቱ ነው።የአዲሱ ጠቅላይ መሪ ደኅንነት እንዲሁም ከተመረጡ በኋላ ለሕዝብ በይፋ አለመታየታቸው አጠያያቂ ከመሆኑ በተጨማሪ ለኢራን መንግሥት ቅርበት ያላቸው ምንጮች የሚሰጧቸው መረጃዎች የሞጅታባ ጤንነት ላይ ጥያቄ ፈጥሯል።በቆፕሮስ የኢራን አምባሳደር የሆኑት አሊሬዛ ሳላሪያን ለብሪታኒያው ጋዜጣ ‘ዘ ጋርዲያን’ ጠቅላይ መሪው “እግር እና እጆቻቸው ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው ሰምቻለሁ… የመቁሰል ጉዳት ስለደረሰባቸው ሆስፒታል እንደሆኑ አስባለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።የሞጅታባ ደኅንነት ጉዳይ አነጋጋሪ መሆኑን ተከትሎ የፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በቴሌግራም ገጹ ላይ ጠቅላይ መሪው ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚገልጹ “ሪፖርቶችን አይቻለሁ” በማለት፣ ነገር ግን ሞጅታባ ደኅና መሆናቸውን ማረጋገጡን ጽፏል።በተጨማሪም ሰኞ ዕለት የሞጅታባ መመረጥ ዜና ከወጣ በኋላ የኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበር ቢጠቅስም ምንም ዓይነት ዝርዝር ግን ሳይሰጥ ቀርቷል።ቆፕሮስ ያሉት የኢራን አምባሳደር ጨምረው እንዳብራሩት ሞጅታባ ኻሜኒ ጉዳት የደረሰባቸው አባታቸውን እና ሌሎች አምስት የቤተሰባቸው አባላት በተገደሉበት ጥቃት መሆኑን አመልክተዋል።ሞጅታባ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሆነው ከተሰየሙ ሦስት ቀናት ያለፏቸው ቢሆንም እስካሁን ከእሳቸው በኩል ምንም ዓይነት መልዕክትም አልተሰማም፤ በአደባባይ አልታዩም ወይም ንግግር አላደረጉም ።አምባሳደሩ ይህንን በተመለከተ ለ ዘ ጋርዲያን እንደተናገሩት “በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ንግግር ለማድረግ የሚፈልጉ አይመስለኝም” ብለዋል።በመጀመሪያው ቀን የአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የተገደሉ ወታደራዊ አዛዦች የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት የተፈጸመ ሲሆን፣ ነገር ግን ጠቅላይ መሪው ሞጅታባ ኻሜኒ አልተገኙም።በቆጵሮስ የኢራን አምባሳደር ለጋዜጣው ሟቹ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ በሕይወት እያሉ የሃይማኖት መሪዎች ልጃቸው እንዲተካቸው ጥያቄ ቢቀርብላቸውም የቤተሰብ ሥርዓት እንዲሆን እንደማይፈልጉ በመግለጽ መቃወማቸውን ተናገረዋል።ነገር ግን ከአባታቸው መገደል በኋላ የከፍተኛ ሊቃውንቱ ጉባኤ ሞጅታባን ለመሪነት በመሰየም “ኃላፊነቱ የአንተ ነው መቀበል አለብህ” በማለት ለመሪነት እንደመረጧቸው ገልጸዋል።የአያቶላህ ኻሜኒ ግድያን በተመለከተም መኖሪያ ቤታቸው ከፕሬዝዳንታዊው ቤተ መንግሥት አቅራቢያ ስለነበረ ጥቃቱ ሲፈጸም ሚስታቸው፣ ሴት ልጃቸው፣ ባሏ እና የ14 ዓመት ልጇ ጭምር መገደላቸውን አረጋግጠዋል።ያጋሩ, አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ጉዳት ደርሶባቸው ከጥቃት መትረፋቸው እየተነገረ ነው - 11 መጋቢት 2026ኢራን ‘አንድ ሊትር ነዳጅ’ በሆርሙዝ በኩል እንዲያልፍ እንደማትፈቅድ ገለጸችኢራን የአፀፋ ጥቃት የመሰንዘር ፖሊሲዋ መለወጡን የአብዮታዊ ዘብን እና የአገሪቱን ጦር የሚያስተባብረው ወታደራዊ ማዘዣ ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ ተናገሩ።የቴህራን ፖሊሲ አሁን “ጥቃትን በጥቃት መመለስ” ይሆናል ሲሉ ቃል አቀባዩ ኢብራሂም ዞልፋካሪ ተናግረዋል።ቴህራን “አንድ ሊትር ነዳጅ እንኳን” የሆርሙዝ ወሽመጥን አቋርጦ አሜሪካ፣ እስራኤል እና አጋሮቿ ዘንድ እንዲደርስ አትፈቅድም ሲሉ ዞልፋካሪ አክለው ተናግረዋል።”ከእነሱ ጋር የተያያዘ ማንኛውም መርከብ ወይም ነዳጅ ጫኝ ዒላማ ይሆናል።””የአንድ በርሜል ነዳጅ ዋጋ 200 ዶላር እንደሚሆን ጠብቁ፤ ምክንያቱም የነዳጅ ዋጋ የሚወሰነው ሰላሙን ባደፈረሳችሁት ቀጣና ደኅንነት ላይ ነው” ሲሉ ቃል አቀባዩ አክለዋል።ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ብትዘጋ በቀሪው ዓለም ላይ ምን ሊከሰት ይችላል?
የፎቶው ባለመብት,Gallo Images via Getty Imagesያጋሩ, ኢራን ‘አንድ ሊትር ነዳጅ’ በሆርሙዝ በኩል እንዲያልፍ እንደማትፈቅድ ገለጸች
