
Yared Hailemariam ·Follow
ኢትዮጵያ በለውጥ ዋዜማ፤
በማይቀረው የሥርዓት ለውጥ እንዴት አገርን መታደግ ይቻላል?
+++++
የብልጽግና ሥልጣን ጣዕረ ሞት ከፊቱ እንደቆመ በጠና የታመመ ሰው አይነት ነፍስ ውጭ፣ ነፍስ ግቢ ትንቅንቅና ጭንቀት ላይ የደረሰበት ሁኔታ መፈጠሩን ብዙ ማሳያ ማቅረብ ቀላል ነው። ነገር ግን ይህን ያፈጠጠና ያገጠጠ እውነት ማንም በቀላሉ የሚረዳው ስለሆነ እሱ ላይ ጊዜ አላጠፋም። ከዛ ይልቅ ይህ እንዳይከርም፣ እንዳያድግ ሆኖ የተፈጠረ ድርጅት ሲንኮታኮት ኢትዮጵያን አብሮ ይዞ ገደል እንዳይገባ ሁሉም አገር ወዳድ ጏይል እንዴት ተረባርቦ አገሩን መታደግና ማዳን ይችላል የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ሁላችንንም ሊያሳስበን ይገባል።
የአገዛዝ ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ የከሸፈ እና እየተንኮታኮተ ለመሆኑ በቅርቡ በአንድ መድረክ ላይ እንደገለጽኩት ቢያንስ በ10 ጉዳዬች ተፈትኖ መውደቁን ገልጬ ነበር። የሕግ የበላይነት በማስከበር፣ ሰብአዊ መብቶችን በማክበር፣ በሙስናን በመዋጋት፣ በአገር ሉዐላዊነት ባለማስደፈር፣ ጠንካራ መንግስታዊ መዋቅር በመዘርጋት፣ ፍትህ በማስፈን፣ የዲሞክራሲ ባህልን በማጎልበት፣ ኢኮኖሚውን በማረጋጋት፣ ድህነትን በመዋጋት፣ ብሔራዊ አንድነትን በመፍጠር እና ጦርነቶችን አቁሞ ሰላም በመፍጠር፣ የውስጥ ፖለቲካዊ መረጋጋትን በማምጣትና ሌሎች ቁልፍ ነጥቦች ተፈትኖ የብልጽግና እና የመሪዎቹ ቁመና ከዜሮ በታች መሆኑን ገልጬ ነበር።
የሚያሳዝነው ከአገዛዙ መፍረክረክ ባልተናነሰ አገሪቱን ሊረከብ የሚችል ጠንካራ እና የተደራጀ የፖለቲካ ጏይል እንዳይኖር በብዙ ሚሊዮን ብር ተመደቦ የተሰራበት አገር ስለሆነ አገር የማዳን ተስፋው በአንድ ድርጅት ላይ የሚጣል ሳይሆን በኢትዮጵያ ጠንካራ አገር ሆና መቀጠል ላይ የሚስማሙ ጏይሎችን ትብብር እና አብሮ መቆምን የሚጠይቀሰ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የተደረሰ ይመስለኛል።
አገሪቱ በአንድ በኩል አስመሳይና ደካማ የሆነ፣ በሙስና የተዘፈቀ የአገዛዝ ሥርዓት፤ በሌላ በኩል የተበታተኑ እና ግራ የተጋቡ የፖለቲካ ሃይሎች በትጥቅም ሆነ በሰላማዊ ትግል የተፋጠጡበት ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች። ከእነዚህ ጏይሎች ውጪ ምናልባትም 90% የሚሆነው የአገሪቱ ሕዝብ እጣ ፈንታውን ቁጭ ብሎ እየተመለከተ ይመስላል።
የእኔም ጥሪ በዝምታ የአገሩን ውድመት እያየ ከፖለቲከኞች ብቻ መፍትሄ የሚጠብቀው አገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ያለው ማህበረሰብ ዝምታውን ሰብሮ፣ ተረባርቦ፣ አብሮ በመቆምና ሰላማዊ ሕዝባዊ እምቢተኝነትን በማጠናከር አገሩን ሊያጠፉበት ካሰፈሰፉት ከብልጽግና እና መሰል ጏይሎች መታደግ አለበት። ብልጽግና በምርጫ ሽፋን ወደ ሌላ ዙሮ የሥልጣን ዘመን የሚሻገርበት እድል እጅግ የጠበበ ቢሆንም የሚያስቆመው ካልተገኘ ግን እየተውተረተረም ቢሆን አገሪቱን ይዞ ቁልቁል ከመንጎድ አይመለስም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ያንንም መፍቀድ የለበትም።
አብይ እንደግለሰብ፣ ብልጽግና እንደ ፖርቲ ከቀጠሉ ኢትዮጵያ አሁን ዛሬ ላይ ከምትገኝበት እጅግ አደገኛና አስከፊ ሁኔታ በብዙ እጥፍ የሚያስንቅ እና ዛሬን የሚያስናፍቅ ሌላ ውጥንቅጥ ሁኔታ ውስጥ እንደምትገባ በድፍረት መናገር ይቻላል።
ኢትዮጵያን ከግፍ አገዛዝ በሕዝባዊ እምቢተኝነት ማላቀቅ እና ከመጪው የከፋ መከራ ለመታደግ መረባረብ እና ሰላማዊ የሽግግር ሂደት እንዲፈጠር የሁላችንንም እርብርብ ይጠይቃል፤ እዳችንም ነው።
