
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ “የአሜሪካ ሠራዊት በመካከለኛው ምሥራቅ ታሪክ ውስጥ ከተፈጸሙት እጅግ ከባድ የቦምብ ድብደባዎች አንዱን ፈጽሟል” ሲሉ ከባድ ጉዳት መድረሱን ተናገሩ።
ጭምቅ ሃሳብ
- ትራምፕ በኢራኗ ወሳኝ ደሴት ላይ የሚገኝ “እያንዳንዱ ወታደራዊ ዒላማ” መውደሙን ተናገሩ
- አምስት የአሜሪካ አውሮፕላኖች ሳዑዲ ውስጥ በኢራን ሚሳዔል ተመቱ
- ሐማስ ኢራን በጎረቤቶቿ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም ጠየቀ
- በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች በየትኞቹ አገራት ይገኛሉ?
- በባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሚሳዔል መመታቱ ተዘገበ
- ኤምሬትስ የሚሳዔል ጥቃት ምሥሎችን የቀረጹ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለች
- ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ጦርነት የሚያበቃበትን ጊዜ መግለጽ እንደማይችሉ ተናገሩ
- ምዕራባውያን አሜሪካ በሩሲያ ነዳጅ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ማንሳቷን ተቹ
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 6 ሰአት በፊትትራምፕ ሳዑዲ ውስጥ የአሜሪካ አውሮፕላኖች መመታታቸውን አስተባበሉ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሳዑዲያ አረቢያ ውስጥ በሚገኘው ልዑል ሱልጣን የአየር ኃይል ሰፈር የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕኖች በኢራን ጥቃት ተመቱ መባሉን አስተበባሉ።ቀደም ሲል የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን የመንግሥት ምንጮችን ጠቅሰው አምስት የጦር ጄቶችን አየር ላይ ነዳጅ መሙላት የሚችሉ አምስት ወታደራዊ አውሮፕላኖች መመታታቸውን ዘግበው ነበር።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በትሩዝ ሶሻል የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ የአየር ኃይል ሰፈሩ ከቀናት በፊት ጥቃት እንደደረሰበት እና አውሮፕላኖቹ “እንዳልተመቱ እና እንዳልተጎዱ” በመግለጽ አስተባብለዋ።”ከአምስቱ አውሮፕላኖች አራቱ ፈጽሞ ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰባቸውም፣ ወደ ሥራቸው ገብተዋል። አንዱ ግን በትንሹ ጉዳት ደርሶበታል፣ ነገር ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ በረራ ይመለሳሉ” በማለት ዘገባውን ያወጡ መገናኛ ብዙኃንን ተችተዋል።ያጋሩ, ትራምፕ ሳዑዲ ውስጥ የአሜሪካ አውሮፕላኖች መመታታቸውን አስተባበሉ - ከ 8 ሰአት በፊትበመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች በየትኞቹ አገራት ይገኛሉ?ሦስተኛ ሳምንቱን በጀመረው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ያልተቋረጠ ጥቃት እያካሄዱ ነው። ኢራንም በበኩሏ በእስራኤል እና የአሜሪካ አጋር በሆኑ የአካባቢው አገራት ላይ የአጸፋ ጥቃት እየፈጸመች ነው።እስራኤል እና ኢራን ወትሮም በጠላትነት የሚፈላለጉ ባላንጣዎች ሲሆኑ፣ ሌሎቹ የመካከለኛውም ምሥራቅ አገራት ለምን የኢራን ዒላማ ሆኑ?ኢራን በዙሪያዋ በሚገኙ የባሕረ ሰላጤው አገራት ላይ አጸፋ መመለስ የጀመረችው ለሚፈጸምባት ጥቃት መነሻ እና ማስተባበሪያ በመሆናቸው ነው።አሜሪካ ጥቅሟን ለማስከበር እና ወዳጇቾን ለመጠበቅ በአካባቢው አገራት ውስጥ ዘመናትን ያስቆጠሩ ወታደራዊ ጦር ሰፈሮች እና የዕዝ ማዕከላት አሏት። በተጨማሪም ወታደሮቿ በትንሽ ቁጥር ቢሆንም የሚገኙባቸው አገራት አሉ።በተለይ የደሴት አገራት በሆኑት እና ለኢራን ቅርብ በሆኑት በባህሬን እና በኳታር ውስጥ ግዙፍ ጦር ሰፈሮች አሏት።በኳታር ውስጥ በመካከለኛው ምሥራቅ ትልቁ የአየር ኃይል ሰፈር ሲኖራት፣ በባሕሬው ውስጥ ደግሞ ግዙፍ የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር ያላት ሲሆን፣ በሁለቱም ውስጥ የጦር አውሮፕላኖች እና መርከቦች ከወታደሮች ጋር ዝግጁ ሆነው ይገኛሉ።ለመሆኑ ለኢራን የሚሳዔል እና የድሮን የአጸፋ ጥቃት የተጋለጡት እና የአሜሪካ ጦር ሰፈር እንዲሁም ወታደሮች የሚገኙባቸው አገራት እነማን ናቸው?
ያጋሩ, በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች በየትኞቹ አገራት ይገኛሉ? - ከ 9 ሰአት በፊትበመካከለኛው ምሥራቅ የደረሱ ጥቃቶችን የሚያሳዩ ምሥሎችበዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ በፉጃይራህ ወደብ በሚገኘው እና በቀጣናው ግዙፍ የሆነው የነዳጅ ማከማቻ በድሮን ጥቃት ከደረሰበት ወዲህ ከፍተኛ ጭስ ታይቷል።በደቡባዊ ሊባኖስ በሃሬት ሳይዳ አካባቢ ሲዶን በተባለ ስፍራ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት የመኖሪያ አፓርታማ በእሳት ተያይዟል።በማዕከላዊ እስራኤል ሾሃም በደረሰ ጥቃት የመኖሪያ ሕንጻ ጣሪያ ሙሉ በሙሉ ወድሟል።የእስራኤል መከላከያ ሌሊቱን ከኢራን የተተኮሱ ሚሳዔሎችን መለየቱን አስታውቆ ነበር።
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በፉጃይራህ ወደብ ካለው የነዳጅ ማከማቻ አቅጣጫ ጭስ ሲወጣ ይታያል
የፎቶው ባለመብት,Shutterstockየምስሉ መግለጫ,በደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ በሲዶና ሃሬት ሳይዳ አካባቢ የእስራኤል ጥቃት
የፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,በማዕከላዊ እስራኤል በሾሃም ከተማ አቅራቢያያጋሩ, በመካከለኛው ምሥራቅ የደረሱ ጥቃቶችን የሚያሳዩ ምሥሎች - ከ 9 ሰአት በፊትባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የተከሰቱ ዋና ዋና ነገሮች
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በከተሞች ላይ የሚፈጸመው የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃት ቀጥሏልአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የጀመሩት ጦርነት ሁለት ሳምንት ሲሞላው ግጭቱ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ተስፋፍቷል። ጦርነቱ በቀናት ውስጥ ተባብሶ የባሕረ ሰላጤው አገራት ከኢራን በሚፈጸምባቸው ጥቃት ምክንያት ራሳቸውን በጦርነቱ ግንባር ውስጥ አግኝተዋል።ጦርነቱ ሦስተኛውን ሳምንት በጀመረበት በዛሬው ዕለት ባለፉት ሁለት ሳምንታት የተከሰቱትን ዋና ዋና ነገሮች መለስ ብለን በአጭሩ እንመልከት፡ጥቃት፣ የአጸፋ ጥቃት እና የኢራን መሪዎች- አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 21/2018 ዓ.ም. በጋራ በኢራን ላይ በከፈቱት ጥቃት ጦርነቱ ተጀመረ። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዘመቻው ዓላማ “ተጨባጭ ስጋቶችን” ለማስወገድ መሆኑን ተናግረው ነበር።
- በምላሹም ኢራን እስራኤልን እና የአሜሪካ ወዳጅ የሆኑ የባሕረ ሰላጤው አገራት ላይ የአጸፋ ጥቃት መሰንዘር ጀመረች።
- ያልተረጋገጡ ወሬዎች ሲዘዋወሩ ቆይተው ከጥቃቱ መጀመር ከአንድ ቀን በኋላ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ኻሜኒ በመኖያቸው ላይ በተፈጸመ ጥቃት መገደላቸው ታውቋል።
- ከዚያ በኋላም ዋና ከተዋ ቴህራን በተከታታይ የአየር ድብደባ ተመትታለች። የሳተላይት ምሥሎችም በኢራን የሚሳዔል እና የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን አሳዩ።
- በኢራን ውስጥ እና በቀጣናው አገራት የሚገኙ የነዳጅ መከማቻዎች እና ማጣሪያዎች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
- እስራኤል በጎረቤቶቿ ሊባኖስ ደበባዊ ክፍል ላይ ጥቃት የከፈተች ሲሆን፣ ኮማንዶዎቿንም ወደ ሊባኖስ ግዛት በማስገባት ጥቃት ፈጽማለች። እርምጃው የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን የሆነው ሔዝቦላህ ትጥቅ እስኪፈታ ድረስ እንደሚቀጥል አስታውቃለች።
- የሟቹ የኢራን መሪ ልጅ ሞጅታባ ኻሜኒ የአገሪቱ ቀጣዩ መሪ መሆናቸው ይፋ ተደረገ። ነገር ግን ከምርጫው በኋላ አስካሁን ድረስ ለሕዝብ በይፋ አልታዩም። ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ሌሎችም ባለሥልጣናት አዲሱ መሪ በተፈጸመባቸው ጥቃት መቁሰላቸውን እየተናገሩ ነው።
የምስሉ መግለጫ,የነዳጅ ማውጫ እና ማጣሪያ ተቋማት ዒላማ ሆነዋልየጦነርቱ ያስከተለው ዳፋ- በጦርነቱ ምክንያት በሰው ላይ የሚደርሰው ጉዳት መጨመሩን የቀጠለ ሲሆን፣ አስካሁንም በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል።
- በኢራን ላይ እየተካሄደ ባለው ዘመቻ አስከሁን 13 የአሜሪካ ወታደሮች ሲሞቱ፣ ከመካከላቸው ስድስቱ የአሜሪካ አየር ኃይል ነዳጅ ጫኝ ወታደራዊ አውሮፕላን ኢራቅ ውስጥ ወድቆ በመከስከሱ የሞቱ ናቸው።
- የነዳጅ ዘይት ዋጋ ከነበረበት በበርሜል ከ70 ዶላር በታች በከፍተኛ ፍጥነት ጭማሪ በማሳየት ከ100 ዶላር በላይ ሆኗል። በዚህም ምክንያት በዓለም ዙሪያ የዋጋ ግሽበት እና የምጣኔ ሀብት አለመረጋጋት ተፈጥሯል።
- በጦርነቱ ምክንያት አገራት የአየር ክልላቸውን በመዝጋታቸው የአውሮፕላን በረራዎች ተቋርጠዋል። ከመካከለኛው ምሥራቅ ለመውጣት የሚፈልጉ የሌሎች አገራት ዜጎች የመውጫ መንገድ እየፈለጉ ነው።
- የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ኢራን ሙሉ ለሙሉ ሽፈንቷን ተቀብላ እጅ ካልሰጠች ጦርነቱ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የምስሉ መግለጫ,አሜሪካ በኢራን ላይ የምትፈጽመው ጥቃት ቀጥሏልያጋሩ, ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የተከሰቱ ዋና ዋና ነገሮች - 14 መጋቢት 2026ሐማስ ኢራን በጎረቤቶቿ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም ጠየቀ
የምስሉ መግለጫ,ኢራን የአጸፋ ጥቃት የፈጸመችባቸው አገራትየኢራን ወዳጅ የሆነው ፍልስጤማዊው ታጣቂ ቡድን ሐማስ ኢራን በዙሪያዋ ያሉ ጎረቤት አገራትን ዒላማ አድርጋ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም ጠየቀ።በተጨማሪም አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በአሜሪካ-እስራኤል እና በኢራን መካከል የሚደረገው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧለ።ሐማስ በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት “በጣሙን አሳሳቢ” በሆነ ሁኔታ እየተከታተለው መሆኑን በመጥቀስ፣ ሁኔታው “የቀጣናውን እና የዓለምን ሰላም እና መረጋጋትን አደጋ ላይ የሚጥል ነው” በማለት ስጋቱን ገልጿል።ቡድኑ በቴሌግራም ገጹ ላይ ባሠራጨው መግለጫው አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት ዓለም አቀፍ ሕግን እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕጎችን የሚጥስ ነው በማለት፣ በቀጣናው የሚገኙ አገራት በመተባበር በኢራን ላይ የተከፈተውን ጦርነት እዲያስቆሙ ጠይቋል።ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በጋዛ ውስጥ ለሁለት ዓመታት በደረሰ ጥቃት ከባድ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፣ ጋዛም በከፍተኛ ሁኔታ ወድማለች።እስራኤል እና ሐማስ ጋዛ ውስጥ ባካሄዱት ጦርነት ከ70 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።ሐማስ በአሜሪካ፣ በዩናይትድ ኪንግደም እና በሌሎችም ምዕራባውያን አገራት በሽብር ድርጅትነት የተፈረጀ ነው።ያጋሩ, ሐማስ ኢራን በጎረቤቶቿ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም ጠየቀ - 14 መጋቢት 2026ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት ስትከፍት፣ እስራኤል ደግሞ ለኢራናውያን ማስጠንቀቂያ አወጣችበመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ኢራን እና እስራኤል የሚፈጽሙት ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ኢራን በእስራኤል ላይ ተከታታይ ጥቃቶችን መክፈቷን ስታስታውቅ፣ እስራኤል ደግሞ ከአንዳንድ ቦታዎች ኢራናውያን ለቅቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች።የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በዛሬው ዕለት 48ኛውን የጥቃት ማዕበል በእስራኤል ላይ መክፈቱን የኢራን መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።የእስላማዊ ሪፐብሊክ ዜና ወኪል እንዳለው ጥቃቶቹ የተከፈቱት በሊባኖስ ከሚገኘው ሄዝቦላህ ጋር በመቀናጀት በአንድ ላይ ነው።ከዚህ ጋር በተያያዘም የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኝ የሔዝቦላህን የጦር መሳሪያ ማከማቻን መምታቱን እና በኢራን የሚደገፈው ቡድን አባላት ወደ ማከማቻው ሮኬቶችን ሲያጓጉዙ መታየታቸውን ገልጿል።ይህንንም ተከትሎ የእስራኤል አየር ኃይል የጦር መሳሪያ ማከማቻውን በመደብደብ የሔዝቦህ አባላትን “መደምሰሱን” ጦር ኃይሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።በኢራን ላይ ጥቃት እያካሄደው የሚገኘው የእስራኤል ጦር በምዕራባዊ ኢራን ውስጥ በምትገኘው ታብሪዝ ከተማ ውስጥ ባለ የኢንዱስትሪ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።ጥቃት የሚፈጸምበትን አካባቢ ከሚያመለክት ካርታ ጋር ለከተማዋ ነዋሪዎች የተላለፈው ማስጠንቀቂያው፣ በተጠቀሰው ስፍራ የእስራኤል ሠራዊት “በቀጣይ ሰዓታት ውስጥ እርምጃ እንደሚወስድ” ገልጿል።ጨምሮም ጥቃቱ በቅርቡ ከተፈጸሙ ወታደራዊ እርምጃዎች ጋር የሚመሳሰል እና የኢራን አገዛዝን ወታደራዊ መሠረተ ልማት ዒላማ ያደረገ መሆኑንም አስታውቋል።በዚህም ምክንያት በተጠቀሰው አካባቢ ያሉ ሰዎች ለደኅንነታቸው ሲሉ በአስቸኳይ ለቅቀው እንዲወጡ እና በቦታው መቆየት በሕይወት ላይ አደጋ የሚያስከትል መሆኑን አስጠንቅቋል።ያጋሩ, ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት ስትከፍት፣ እስራኤል ደግሞ ለኢራናውያን ማስጠንቀቂያ አወጣች
- 14 መጋቢት 2026በሊባኖስ የሕክምና ባለሙያዎችን ጨምሮ በርካቶችን የገደለው የእስራኤል ጥቃት
የፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,በደቡባዊ ሊባኖስ በሲዶና ሃሬት ሳይዳ አካባቢ የእስራኤል የአየር ጥቃት የደረሰበት አካባቢእስራኤል በደቡብ ሊባኖስ ከሄዝቦላህ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ስፍራዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን የሚገልጹ ዘገባዎች መሰማት ጀምረዋል።የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር ሌሊቱን በቡርጅ ቃላዊያ ከተማ በተፈጸመ ጥቃት ዶክተሮችን እና ነርሶችን ጨምሮ 12 የሕክምና ባለሙያዎች መገደላቸውን አስታውቋል።እስራኤል መንገዶችን እና ድልድዮችን ጨምሮ ሌሎች መሠረተ ልማቶች ላይ ድብደባዎችን መፈጸሟ እየተገለፀ ነው።በአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል እስራኤል ጥቃት ከመፈጸሟ በፊት ነዋሪዎች ለቅቀው እንዲወጡ የተነገረቸው ስፍራ መጠን እጅግ በጣም እየጨመረ ሲሆን፣ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ወደ ሰሜናዊ ሊባኖስ ተሰድደዋል።በሊባኖስ የሚገኙ በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና መንግሥት የተፈናቃዮች ቁጥር በየጊዜው ስለሚጨምር መቸገራቸውን ይናገራሉ።እስራኤልም ሆነች ሄዝበላህ አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት እንዲሁም የመግለጫ ልውውጣቸው እየተካረረ መምጣቱን ተከትሎ መጠነ ሰፊ ጦርነት አይቀሬ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት ጨምሯል።እስራኤል ዛሬ ማለዳ በደቡባዊ ሊባኖስ የፈጸመችው ጥቃት በሃሬት ሳይዳ አካባቢ የሚገኝ ሕንጻ ላይ ውድመት አድርሷል።በጥቃቱ የሞቱ ሰዎች ስለመኖራቸው እስካሁን ድረስ የታወቀ ነገር ባይኖርም ጦርነቱ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ግን በአጠቃላይ ከ770 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,የሕይወት አድን እና የእሳት አደጋ ሠራተኞች የእስራኤል አየር ጥቃት በደረሰበት ስፍራ ላይ እሳት ለማጥፋት ሲረባረቡያጋሩ, በሊባኖስ የሕክምና ባለሙያዎችን ጨምሮ በርካቶችን የገደለው የእስራኤል ጥቃት - 14 መጋቢት 2026አምስት የአሜሪካ አውሮፕላኖች ሳዑዲ ውስጥ በኢራን ሚሳዔል ተመቱ
የፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,ጉዳት ከደረሰባቸው ጋር የሚመሳሰሉ የአሜሪካ አውሮፕላኖች እስራኤል ውስጥአምስት የአሜሪካ አየር ላይ ነዳጅ የሚሞሉ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በኢራን ተመትተው ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ዎል ስትሪት ጆርናል ዘገበ።አውሮፕላኖቹ በሳዑዲው ልዑል ሱልጣን የአየር ኃይል ሰፈር ውስጥ ሳሉ ከቀናት በፊት ኢራን በፈጸመችው የሚሳዔል ጥቃት መመታታቸውን ጋዜጣው የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።ነዳጅ ጫኝ የሆኑት ወታደራዊ አውሮፕላኖች በደረሰባቸው ጥቃት ጉዳት እንደረሰባቸው ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ አለመውደማቸውን ባሥልጣናት ተናግረው “በአሁኑ ጊዜ ጥገና እየተደረገላቸው” መሆኑን እና በጥቃቱ በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱን መናገራቸውን ዎል ስትሪት ጆርናል ገልጿል።ይህ በአምስት የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላን ላይ ጥቃት መፈጸሙን የሚገልጸው ዘገባ የወጣው ኬሲ-135 ነዳጅ የሚሞላ የአሜሪካ አየር ኃይል አውሮፕላን ባለፈው ሐሙስ በምዕራባዊ ኢራቅ ውስጥ መከስከሱ ከተነገረ በኋላ ነው።በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካንን ወታደራዊ ተልዕኮዎች የሚቆጣጠረው የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ኃይል ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) እንዳረጋገጠው በአደጋው በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ሁሉም ስድስት አባላቱ ሞተዋል።ያጋሩ, አምስት የአሜሪካ አውሮፕላኖች ሳዑዲ ውስጥ በኢራን ሚሳዔል ተመቱ - 14 መጋቢት 2026በኳታር ዶሃ ነዋሪዎች ከከተማዋ ማዕከል እንዲወጡ እየተደረገ ነው
የፎቶው ባለመብት,EPAየኳታር የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ከበርካታ አካባቢዎች ለጥንቃቄ በሚል ነዋሪዎችን እያስወጣ መሆኑን አስታወቀ።እስካሁን ባለው መረጃ የስጋቱ መጠን እና ዓይነት ባይታወቅም ኳታር ሌሊቱን እና ዛሬ ጠዋት ሁለት የሚሳዔል ጥቃቶችን አስተናግዳለች።ኢራን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የአሜሪካ ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን የሚያስተናግዱ አገራት ዒላማዎች እንደሚሆኑ ከተናገረች በኋላ ኳታር የወሰደችው እርምጃ ያንን ለመከላከል ይመስላል።ነዋሪዎች የዶሃ ማዕከላዊ የሙሼይርብ አካባቢን በፍጥነት ለቅቀው እንዲወጡ የስልክ መልዕክት ደርሶቸዋል።አካባቢው የጉግል እና የአሜሪካን ኤክስፕረስ ቢሮዎች የሚገኙበት ነው። የፀጥታ አካላት በማይክሮሶፍት ኳታር ዋና መሥሪያ ቤት አካባቢ እንደሚሰማሩም ተነግሯል።ሮይተርስ የዜና ወኪል በበኩሉ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ስድስት የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ካምፓሶች ከሚገኙበት አካባቢ ነዋሪዎች የተወሰነውን ስፍራ ለቅቀው እንዲወጡ ማድረጋቸውን ዘግቧል።በሌላ የመካከለኛው ምሥራው የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች አሁንም ስጋት ውስጥ ናቸው። በባግዳድ የሚገኙ የደኅንነት ባለሥልጣናት ኤምባሲው ጥቃት እንደደረሰበት ተናግረዋል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደግሞ አስፈላጊ ያልሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች ከኦማን እንዲወጡ እያደረገ ነው።ያጋሩ, በኳታር ዶሃ ነዋሪዎች ከከተማዋ ማዕከል እንዲወጡ እየተደረገ ነው - 14 መጋቢት 2026ከአሜሪካ ጋር የሚሠሩ የነዳጅ ተቋማትን ‘የአመድ ክምር’ እንደምደታርግ ኢራን ዛተች
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ኢራብ ን ባለፉት ቀናት በቀጣናው የሚገኙ የነዳጅ ተቋማትን ዒላማ አድርጋለችከአሜሪካ ተቋማት ጋር የሚሠሩ የነዳጅ እና የጋዝ አምራች ድርጅቶችን የኢራን ጦር ሠራዊት “በማውደም ወደ አመድ ክምርነት እንደሚለውጣቸው” መግለጹን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።ይህ በኢራን የዜና ወኪሎች ፋርስ እና ታስሚን የተዘገበው የሠራዊቱ መግለጫ የወጣው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላስተለላፉት መልዕክት “ምላሽ” መሆኑ ተገልጿል።በትሩዝ ሶሻል ላይ ፕሬዝዳንቱ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ የአሜሪካ ኃይሎች በኻርጅ ደሴት እና ከፍተኛ መጠን ያለው የዓለም የነዳጅ ምርት በሚያልፍበት በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚገኙ የኢራን ወታደራዊ ተቋማት “ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል” ብለዋል።ተጨማሪ የአሜሪካ የባሕር ኃይል ወታደሮች እና የጦር መርከቦች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሊሰማሩ መሆኑን ቀደም ሲል በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ሆነው ሲቢኤስ ቴሌቪዥን ዘግቧል።ባለሥልጣናትም ዝግጁ ከሆኑ የባሕር ላይ ወታደራዊ ቡድኖች እና የባሕር አሳሽ ኃይሎች በኢራን አካባቢ ያለውን አሜሪካ ጦር ለማጠናከር ከሌሎች አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል።ተያያዥ ዘገባ ያንብቡ በኢራን ጦርነት የትኞቹ አገራት ሊያተርፉ ይችላሉ? የሚጎዱትስ እነማን ናቸው?ያጋሩ, ከአሜሪካ ጋር የሚሠሩ የነዳጅ ተቋማትን ‘የአመድ ክምር’ እንደምደታርግ ኢራን ዛተች - 14 መጋቢት 2026ምዕራባውያን አሜሪካ በሩሲያ ነዳጅ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ማንሳቷን ተቹ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየአውሮፓ መሪዎች አሜሪካ ሩሲያ ወደ ውጭ በምትልከው ነዳጅ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ለጊዜው ለማላላት መወሰኗን ተቹ።ይህ የአሜሪካ ውሳኔ አገራት በመርከቦች ላይ ተጭኖ ያለ ነገር ግን በማዕቀብ ምክንያት ያልተሸጠ የሩሲያ ነዳጅን እንዲገዙ ያስችላቸዋል።የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አንቶኒዮ ኮስታ አርብ ዕለት”የአውሮፓን ደኅንነት ስለሚጎዳ” የአሜሪካ ውሳኔ “በጣም አሳሳቢ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።“የማዕቀቦቹ መላላት ሩሲያ ሀብቶቿን በዩክሬን ላይ ጦርነት ለማካሄድ ዳግም ታውላቸዋለች” ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት እንደተናገሩት በዚህ እርምጃ ሩሲያ 10 ቢሊዮን ዶላር ታገኛለች ማለት ሊሆን ይችላል ሲሉ “ለሰላም አይረዳም” ብለዋል።የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከዜሌንስኪ ጋር በመሆን የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋቱ “በምንም መልኩ” ማዕቀቡን ለማንሳት ምክንያት እንደማይሆን ተናግረዋል።የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ ቀደም ሲል በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሲናገሩ፣ የካናዳ አቋም “በሩሲያ ላይ የተጣሉትን ማዕቀቦች ማስቀጠል” እንደሆነ ተናግረዋል።የጀርመን ቻንስለር ፍሬድሪሽ ሜርዝ ቀደም ሲል በሰጡት መግለጫ ላይ ውሳኔውን “ስህተት” ብለዋል።ያጋሩ, ምዕራባውያን አሜሪካ በሩሲያ ነዳጅ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ማንሳቷን ተቹ - 14 መጋቢት 2026ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ጦርነት የሚያበቃበትን ጊዜ መግለጽ እንደማይችሉ ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጥቃት ሦስተኛ ሳምንቱን በጀመረበት በአሁኑ ወቅት ጦርነቱ የሚያበቃበትን የጊዜ ገድብ ማስቀመጥ እንደማይችሉ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናገሩ።በወሳኟ የኢራን ደሴት ላይ የተፈጸመውን ከባድ ጥቃት ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ ጦርነቱ የሚያበቃበትን ጊዜ እርግጠኛ ሆነው መናገር እንደማይችሉ ገልጸዋል።ጨምረውም “በእርግጥ መቼ እንደሚሆን ሃሳቡ አለኝ፣ ነገር ግን እሱን መናገሩ ምን ጥቅም አለው? ይህ ጦርነት አስፈላጊ እስከሆነበት ጊዜ ድረስ ይቀጥላል። [ኢራኖች] ከባድ ውድመት ነው የደረሰባቸው።”ምን ማለታቸው እንደሆነ እንዲያብራሩ ሲጠየቁም “የኢራን ባሕር ኃይል፣ አየር ኃይል እና ከፍተኛው የአገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ወድሟል” በማለት “በቀላሉ ለማስቀመጥ፣ ከዚህ ቀደም ማንም አይቶት በማያውቅ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት የበላይነቱን ይዘናል” ብለዋል።ከሁለት ሳምንት በፊት ጥቃቱ በጀመረበት ጊዜ ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ሌሎች ባለሥልጣኖቻቸው ጦርነቱ በሳምንታት ውስጥ እንደሚቋጭ በእርግጠኝነት ሲናገሩ የነበረ ቢሆንም አሁን ሁለተኛው ሳምንት ተጠናቆ ሦስተኛው ጀምሯል።የጦርነቱን ግብ በተመለከተ በእርሳቸው እና በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር መካከል ተመሳሳይ ዓላማ እንዳለ በአንድ ጋዜጠኛ ለቀረበላቸው ጥያቄ ተጨማሪ ማብራሪያ ሳይሰጡ “የእነሱ በትንሹ ለየት ያለ ይመስለኛል” ሲሉ መልሰዋል።ነገር ግን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር “ዩናይትድ ስቴትስ ያላትን ኃይል የሚያክል ፈጽሞ እንደሌለ ሊነግራችሁ ይችላል” ሲሉ ተናግረዋል።ያጋሩ, ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ጦርነት የሚያበቃበትን ጊዜ መግለጽ እንደማይችሉ ተናገሩ - 14 መጋቢት 2026ኤምሬትስ የሚሳዔል ጥቃት ምሥሎችን የቀረጹ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለች
የፎቶው ባለመብት,AFPየተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የአገሪቱ መከላከያ ወደ ግዛቲቱ የሚወነጨፉ ሚሳዔሎችን ሲያመክን የሚያሳዩ ምሥሎችን የቀረጹ 10 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለ።የዩኤኤ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ ከዚህ በተጨማሪም ጥቃቶችን እና ፍንዳታዎችን የሚያሳዩ ሐሰተኛ ምሥሎችን ያሠራጩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።የመገናኛ ብዙኃን በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች የተፈጸሙ ትክክለኛ ጥቃቶችን እንዲሁም በሰው ሠራሽ አስተውሎት የተሠሩ ምሥሎችን ያጋሩ ናቸው።ዘገባው አክሎም ግለሰቦቹ “የተፋጠነ ፍትሕ” ይሰጣቸዋል መባሉን ዘግቧል።የአቡዳቢ ፖሊስ 45 “የተለያዩ አገራት ዜጎችን” አገሪቱ ላይ ጥቃት ሲፈጸም ተንቀሳቃሽ ምሥልን በመቅረጽ እና “ሐሰተኛ መረጃ በማሠራጨት” በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጿል።ባለፈው ሳምንት የ60 ዓመቱ ብሪታኒያዊ የኢራን ሚሳዔሎች በከተማዋ ላይ ሲወነጨፉ የሚያሳይ ምሥል መቅረጹን ተከትሎ በዱባይ የሳይበር ወንጀል ሕግ መሠረት ክስ ተመሥርቶበታል።በዩኤኢ የሳይበር ወንጀል ሕግ ስር 21 ሰዎች የተከሰሱ ሲሆን፣ ይህም “በቅርቡ ከደረሱ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ በቀረጿቸው ቪዲዮዎች እና ባጋሯቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፎች” ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።ያጋሩ, ኤምሬትስ የሚሳዔል ጥቃት ምሥሎችን የቀረጹ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለች - 14 መጋቢት 2026በባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሚሳዔል መመታቱ ተዘገበ
የፎቶው ባለመብት,Gettyየምስሉ መግለጫ,በባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የድሮን ጥቃት ከደረሰበት በኋላ ጭስ ታይቷልበኢራቅ ዋና ከተማ በባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የሚሳዔል ጥቃት እንደተፈጸመበት ተሰምቷል።በባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሚሳዔል ከተመታ በኋላ ጭስ መታየቱን ሮይተርስ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።አሶሼትድ ፕሬስ በበኩሉ በአሜሪካ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ መጫወቻ ሜዳ በሚሳዔል ተመትቷል ሲል ዘግቧል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ኤኤፍፒ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው በኤምባሲው ላይ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት መሆኑን አመልክቷል።ጥቃቱ የተፈፀመው ሁለት በኢራን የሚደገፉ ተዋጊዎች ከተገደሉ በኋላ መሆኑን ኤኤፍፒ በርካታ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።ያጋሩ, በባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሚሳዔል መመታቱ ተዘገበ - 14 መጋቢት 2026ትራምፕ በኢራኗ ወሳኝ ደሴት ላይ የሚገኝ “እያንዳንዱ ወታደራዊ ዒላማ” መውደሙን ተናገሩ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ “የአሜሪካ ሠራዊት በመካከለኛው ምሥራቅ ታሪክ ውስጥ ከተፈጸሙት እጅግ ከባድ የቦምብ ድብደባዎች አንዱን ፈጽሟል” ሲሉ ከባድ ጉዳት መድረሱን ተናገሩ።ፕሬዝዳንቱ የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ አካሄደው ባሉት ከባድ የቦምብ ድብደባ ለኢራን ወሳኝ በሆነችው በኻርግ ደሴት ላይ ያለ እያንዳንዱ ወታደራዊ ዒላማ ሙሉ በሙሉ መውደሙን አሰውቀዋል።ኻርግ ከኢራን የባሕር ዳርቻ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ ትንሽ ደሴት ናት። ደሴቲቱ የኢራን “የነዳጅ ሕይወት መስመር” እንደሆነች ይታመናል።በደሴቲቱ ጥቂት ነዋሪዎች ቢኖሩም፣ 90 በመቶ የሚሆነው ወደ ውጭ የሚላከው የኢራን ድፍድፍ ነዳጅ በዚህች ደሴት በኩል ያልፋል።ትላልቅ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ወደ ደሴቲቱ ከሄዱ በኋላ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ እና በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ በኩል በማድረግ ወደ ቻይና እና ሌሎች አገራት ጉዟቸውን ያደርጋሉ።ወደ ደሴቲቱ የሚወስደው መንገድ ከተቋረጠ የእስላማዊ ሪፐብሊክ ኢኮኖሚ በእጅጉ ይዳከማል።”በደሴቲቱ ላይ ያለውን የነዳጅ መሠረተ ልማት አለማጥፋት መርጫለሁ። ሆኖም ግን፣ ኢራን ወይም ሌላ ማንኛውም አካል በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦች ነፃ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ምንም ነገር ቢደረግ” የኢራን የነዳጅ መሠረተ ልማቶች ዒላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ፕሬዝዳንቱ አስጠንቅቀዋል።ኢራን የጦር መሳሪያዎቿን እንድትፈታ እና “ከአገራቸው እንዲያድኑ” ሲሉ ለባለሥልጣናቱ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ጥሪ አቅርበዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደሴቲቱን ለመቆጣጠር የልዩ ኃይል አባላትን ለማሰማራት እያሰቡ እንደነበር በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ አክሲዮስ ዘግቧል ።
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ከኢራን የባህር ዳርቻ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ውስጥ የምትገኘው የኻርግ ደሴት የሳተላይት ምስልያጋሩ, ትራምፕ በኢራኗ ወሳኝ ደሴት ላይ የሚገኝ “እያንዳንዱ ወታደራዊ ዒላማ” መውደሙን ተናገሩ - 13 መጋቢት 2026ኢራን ከሄዝቦላህ ጋር በመተባበር እስራኤል ላይ የሚሳዔል ጥቃት መክፈቷን አስታወቀችየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ከሄዝቦላህ ጋር በመተባበር እስራኤል ላይ የሚሳዔል ጥቃት መክፈቱን ከኢራን መንግሥት ጋር ትስስር ያለው ታስሚን የተባለው የመገናኛ ብዙኃን ዘገበ።የኢራን መንግሥት ወታደራዊ ክንፍ የሆነው አብዮታዊው ዘብ እንዳው፤ በእስራኤል ላይ በተከፈተው ጥቃት የባሕር ኃይሉ እና የሰው አልባ አውሮፕላን ክፍሉ ተሳትፈዋል።በጥቃቱ የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ ኢራንን ደግፎ እየተሳተፈ መሆኑም ተገልጿል።በቴል አቪቭ እና በእስራኤል የወረራ ይዞታ ሥር ባለው ዌስት ባንክ አንዳንድ አካባቢዎች የአየር ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል የሚጠቁም የአደጋ ጊዜ ደውል ተሰምቷል።አሁን ላይ ኢራን እና ሄዝቦላህ በከፈቱት ተከታታይ ጥቃት ሳቢያ የሞቱ ወይም የተጎዱ ሰዎች ስለመኖራቸው ሪፖርት አልወጣም።ያጋሩ, ኢራን ከሄዝቦላህ ጋር በመተባበር እስራኤል ላይ የሚሳዔል ጥቃት መክፈቷን አስታወቀች
- 13 መጋቢት 2026ትራምፕ ጦርነቱ የሚያበቃው “እርግጠኛ ስሆን ነው” አሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከእስራኤል ጋር በመሆን በኢራን ላይ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በተመለከተ ፎክስ ኒውስ ከተባለ የአገራቸው ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ በዛሬው ዕለት ቀርቧል።ፕሬዝዳንቱ በቃለ ምልልሱ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ጦርነት መቼ እንደሚያበቃ፡ ትራምፕ ጦርነቱ መቼ ማብቃት እንዳለበት ያውቁ እንደሆነ በተጠየቁበት ጊዜ “ይበቃል ብዬ ሳስብ እና እርግጠኛ ስሆን” በማለት መልሰዋል።በአዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ላይ ስለደረሰው፡ “የተጎዳ ይመስለኛል፤ ነገር ግን በሕይወት ያለ ይመስለኛል”፤ ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም ሞጅታባ ኻሜኒ በይፋ ለሕዝብ አልታዩም ብለዋል።የሆርሙዝ ወሽመጥን በተመለከተ፡ “ማድረግ ካለብን” በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚተላለፉ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን እናጅባለን፤ ነገር ግን ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ይሄዳሉ። ምን እንደሚሆን እናያለን” ብለዋል።በኢራን ላይ ስለሚፈጸመው ጥቃት፡ “ክፉኛ እንመታቸዋለን” በማለት “እስካሁንም በመጥፎ ሁኔታ አውድመናቸዋል፤መልሰው ለመገንባትም ዓመታትን ይወስድባቸዋል” ሲሉ ገልጸዋል።ስለ ባሕረ ሰላጤው አጋሮቻቸው፡ ከብዙዎቹ ጋር መነጋገራቸውን እና “ያለው አንድነት ጠንካራ ነው” ብለዋል። አገራቱም እራቸሳውን ለመጠበቅ “ጥሩሥራ እየሠሩ ነው” በማለት አወድሰዋቸዋል።ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ፡ አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ምን ያህል ሊቆይ ይችላል?ያጋሩ, ትራምፕ ጦርነቱ የሚያበቃው “እርግጠኛ ስሆን ነው” አሉ - 13 መጋቢት 2026በወር 3 ሺህ መርከቦች እና በቀን 20 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ የሚተላለፍበት ሆርሙዝ
የምስሉ መግለጫ,መካከለኛው ምሥራቅ እና ሆርሙዝለሁለት ሳምንት በቀጠለው ጥቃት ምክንያት በፋርስ ባሕረ ሰላጤ አገራት የሚመረተው ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ወሽመጥ ደኅንነት አደጋ ላይ ወድቋል። በዚህም ምክንያት በዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ተመዝግቧል።አሜሪካ እና እስራኤል የከፈቱባት ጥቃት እስኪቆም ድረስ ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦችን በሙሉ ዒላማ እንደምታደርግ አሳውቃለች።ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በርካታ መርከቦች በከባድ የጥቃት ስጋት ውስጥ ናቸው። አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ አገራቸው ወሽመጡን “በመዝጋት ያላትን አቅም” መጠቀሟን እንደምትቀጥል ተናግረዋል።ዓለማችን ከሚያስፈለጋት የነዳጅ ምርት ውስጥ 20 በመቶ የሚሆነው በሆርሙዝ በኩል ነው የሚያልፈው። በየወሩም ሦስት ሺህ የመሆኑ መርከቦች ጠባቡን መተላለፊያ ያቋርጣሉ። ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት በየቀኑ 20 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ በወሽመጡ በኩል አልፈው ወደተለያዩ አገራት ደርሷል።መተላለፊያው ምንም እንኳን ጠባብ ቢሆንም ለግዙፎቹ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች እንቅስቃሴ አመቺ የሆነ ጥልቀት አለው። በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ ዋነኛ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ አገራት እና ገዢዎች የሆርሙዝ ወሽመጥን ምርቱን ለማስተለላፍ ይጠቀሙበታል።ተጨማሪ እነዚህ ያንብቡ፡ ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ብትዘጋ በቀሪው ዓለም ላይ ምን ሊከሰት ይችላል?ያጋሩ, በወር 3 ሺህ መርከቦች እና በቀን 20 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ የሚተላለፍበት ሆርሙዝ - 13 መጋቢት 2026“የኢራን የሚሳዔል አቅም በ90% ተዳክሟል” – የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር
የፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሜሪካ እና እስራኤል የኢራንን ወታደራዊ ኃይል “እየፈረካከሱት” እንደሚገኙ ተናገሩ።የኢራን መንግሥት በአገሪቱ ሰማይ ላይ “[የአሜሪካ ሰንደቅ አላማን] ከዋክብት እና የዳዊት ኮከብን” እየተመለከተ መሆኑን ጠቅሰው “ይህም በከፍተኛ መጠን የሚፈሩት ነገር ነው” ብለዋል።የኢራን ጦር መሣሪያ የማምረት አቅም እንደተዳከመ ገልጸዋል። የኢራን መንግሥት “እንደ አይጥ” ከመሬት በታች እየተሽሎከሎከ ነው ሲሉም ተደምጠዋል።አሜሪካ በኢራን ላይ የምትወስደውን “ጠንካራ እርምጃ” እንደምትቀጥል በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ጠቁመዋል።ኢራን በአሁኑ ወቅት አገልግሎት የሚሰጥ የአየር ኃይል እና የባሕር ኃይል እንደሌላት ገልጸዋል። የኢራን የሚሳዔል አቅም በ90 በመቶ መቀነሱንም አክለዋል።ኢራን ተጨማሪ የጦር መሣሪያ የመገንባት አቅም እንደሌላት እና ሁሉም የመከላከያ ተቋማት በቅርቡ “እንደሚወድሙ” ተናግረዋል።አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ “ተጎድተዋል” ሲሉም መከላከያ ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል። ቀደም ሲል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም ተመሳሳይ መረጃ ለፎክስ ኒውስ መስጠታቸው ይታወሳል።በኢራን የሴቶች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ስለደረሰው ጥቃት መከላከያ ሚኒስትሩ ተጠይቀው “አሜሪካ እና እስራኤል ንጹኃንን ዒላማ አያደርጉም” ሲሉ መልሰዋል።ከፒት ሄግሴት ጋር በጋራ መግለጫ የሰጡት የአሜሪካ ወታደራዊ ኃላፊ ጄነራል ዳን ኬን በበኩላቸው አገራቸው ቅድሚያ የምትሰጠው ለሆርሙዝ ሰርጥ መሆኑን ጠቅሰዋል።የመከላከያ ሚኒስትሩም የሆርሙዝ ሰርጥ በቅርቡ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተናግረዋል።ያጋሩ, “የኢራን የሚሳዔል አቅም በ90% ተዳክሟል” – የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር - 13 መጋቢት 2026በኢራን ተቃውሞ ከተነሳ “የከፋ እርምጃ ይወሰዳል” ሲል አብዮታዊ ዘቡ አስጠነቀቀ
የፎቶው ባለመብት,Telegramየምስሉ መግለጫ,በዛሬው ዕለት የኢራን መንግሥት ደጋፊዎች አደባባይ በወጡበት ጊዜ ፍንዳታ አጋጥሞ ነበርየኢራን አብዮታዊ ዘብ የደኅንነት ክፍል ባወጣው መግለጫ የአደባባይ ተቃውሞዎች የሚካሄዱ ከሆነ “ከታኅሣሡ የከፋ እርምጃ እንደሚወሰድ” አስጠነቀቀ።ባለፈው ታኅሣሥ ወር በበርካታ የኢራን አካባቢዎች ውስጥ ከተካሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን እና በአስር ሺዎች የሚሆኑት ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል።አሁንም አሜሪካ እና እስራኤል በአገሪቱ ላይ ጥቃት እየፈጸመች ባለችበት ጊዜ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ማድረግ ከባድ ቅጣትን እንደሚያስከትል ባለሥልጣናት እያስጠነቀቁ ነው.የአገሪቱ አብዮታዊ ዘብም ተቃዋሚዎች አውሮፓውያኑ ታኅሣሥ 8 ከተወሰደው “የከፋ” እርምጃ እንደሚወሰድ ይፋ ባደረገበት መግለጫው “የአደባባይ ነውጥ ለወታደራዊ ጥቃት ሽፋን መሆኑን አስታውቀናል። አሁን የጠላት ኃይሎች የውጊያ ዓላማቸውን ለማሳካት ፍርሃት እና ብጥብጥ እየነዙ ነው” ብሏል።ታኅሣሥ ላይ ለተቃውሞ የወጡትን “አዲስ አይኤስአይኤስ” ያላቸው ሲሆን፤ ተመልሰው አደባባይ ከወጡ ከዚህ በፊት ከታየው “የበለጠ እርምጃ ይጠብቃቸዋል” ሲል አስጠንቅቋል።ከወራት በፊት በኢራን በተካሄደው ተቃውሞ የሰብአዊ መብት ተቋሙ ‘ሂውማን ራይትስ አክቲቪስትስ ኒውስ ኤጀንስ’ ከ7,000 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ሲገልጽ፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 32,000 ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል።የኢራን መንግሥት የሞቱት 3,117 ሰዎች መሆናቸውን ገልጾ የስም ዝርዝራቸውን ይፋ አድርጓል። በኢራን ተቃውሞ ወቅት ኢንተርኔት እና ስልክ ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራን መንግሥት ደጋፊዎች ዛሬን ጨምሮ በተለያዩ ቀናት ለድጋፍ አደባባይ መውጣታቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ያጋሩ, በኢራን ተቃውሞ ከተነሳ “የከፋ እርምጃ ይወሰዳል” ሲል አብዮታዊ ዘቡ አስጠነቀቀ
