ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ አሜሪካ ሁለተኛ ሳምንቱን የደፈነውን የኢራን ጦርነት ለመቋጨት የሚያስችል ስምምነት ላይ ለመድረስ ዝግጁ አይደለችም አሉ። ኢራን ስምምነት መፈጸም ፈልጋለች ሲሉ የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ነገር ግን “የቀረቡት የድርድር ነጥቦች ገና በቂ ስላልሆኑ” ንግግር ለማደረግ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 4 ሰአት በፊትየቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ ልጃቸው ሥልጣኑን የመረከቡ ጉዳይ ያሳስባቸው እንደነበር የአሜሪካ የስለላ መረጃ አሳየአያቶላህ አሊ ኻሜኒ እና ሞጅታባ ኻሜኒየፎቶው ባለመብት,Getty Images | Reutersየቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ልጃቸው እርሳቸውን ተክቶ ሥልጣን እንዲይዝ የማድረግ ሀሳብ ላይ ጥርጣሬ እንደነበራቸው የአሜሪካ የስለላ መረጃ ማሳየቱን የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ኒውስ ዘገበ።ይህንን የሚገልጸው የስለላ መረጃ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በዙሪያቸው ላሉ ጥቂት ሰዎች እንደቀረበ ምንጮች መናገራቸውን ዘገባው ያሳያል።የቀድሞው አያቶላህ ልጃቸው ሞጅታባ ኻሜኒ ብሩህ ጭንቅላት አለው የሚባል ባለመሆኑ እንዲሁም ለመሪነት ብቁ የሆነ ሰው ተደርጎ ባለመታየቱ ሥልጣኑን እንዳይረከብ ስጋት እንደነበራቸው የአሜሪካ ስለላ ትንተና አመልክቷል ተብሏል።በተጨማሪም አባት በልጃቸው የግል ሕይወቱ ውስጥ ስላለው ችግር ያውቁ እንደነበር መረጃው እንዳሳየ ምንጮቹ ተናግረዋል።አያቶላህ አሊ ኻሜኒ አሜሪካ እና እስራኤል በከፈቱት ጥቃት መገደላቸውን ተከትሎ ከሳምንት በፊት ልጃቸው ሥልጣኑን ተረክበዋል።አዲሱ ጠቅላይ መሪ በዚህ ሳምንት የሰጡት የመጀመሪያ መግለጫ በአገሪቱ ቴሌቪዥን ቢነበብም ሥልጣኑን ከተረከቡ ወዲህ እስካሁን አልታዩም።ሞጅታባ ሳይጎዱ አልቀሩም የሚሉ መረጃዎች ወጥተዋል። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አግራቺ ግን ጠቅላይ መሪ “ጥሩ ጤንነት ላይ” እንደሚገኙ እና “ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠሩ” መሆኑን በዛሬው ዕለት ተናግረዋል።ያጋሩ, የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ ልጃቸው ሥልጣኑን የመረከቡ ጉዳይ ያሳስባቸው እንደነበር የአሜሪካ የስለላ መረጃ አሳየ
  2. ከ 6 ሰአት በፊትየጦር መርከቦቻቸውን ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲልኩ በትራምፕ የተጠየቁት አገራት ምን ምላሽ ሰጡ?የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢማኑኤል ማክሮንየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ወሳኝ የነዳጅ መተላለፊያ የሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ “ከእንግዲህ” የኢራን “ማስፈራሪያ እንዳይሆን” ለማድረግ አምስት አገራት የጦር መርከቦቻቸውን ይልካሉ ብለው እንደሚጠብቁ ቅዳሜ ዕለት ገልጸዋል።ትራምፕ ‘ትሩዝ ሶሻል’ በተባለው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ የጠቀሷቸው አምስቱ አገራት ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ዩናይትድ ኪንግደም ናቸው።እስካሁን ድረስ እነዚህ አገራት ምን ምላሽ ሰጡ የሚለውን እንመልከት፦ዩናይትድ ኪንግደም – የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ቃል አቀባይ “ከዚህ ቀደም እንደገለጽነው፤ በቀጣናው ያለውን የመርከብ ጉዞ ደኅንነት ለማስጠበቅ ያሉትን አማራጮች በተመለከተ ከአጋሮቻችን ጋር እየተወያየን ነው” ብለዋል።ቻይና – በዋሽንግተን የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ቃል አቀባይ፤ ቤጂንግ በአስቸኳይ ግጭቶች እንዲቆሙ ጥሪ እንደምታቀርብ ገልጸዋል። ቃል አቀባዩ ቻይና የትራምፕን ጥያቄ ተቀብላ ይሁን አይሁን አልተናገሩም።ነገር ግን የተረጋጋ እና ያልተገደበ የኢነርጂ አቅርቦት እንዲኖር የማድረግ ኃላፊነት የሁሉም ወገኖች እንደሆነ ለሲኤንኤን ተናግረዋል። ቻይና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት ማጠናከሯን እንደምትቀጥልም ገልጸዋል።ጃፓን – አሜሪካን የቅርብ አጋሯ አድርጋ የምትቆጥረው ቶኪዮ እስካሁን ድረስ ለትራምፕ ጥያቄ ይፋዊ ምላሽ አልሰጠችም። ይሁን እንጂ የአገሪቱ ባለሥልጣናት፤ ጉዳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰናይ ታካቺ ከመጪው ረቡዕ አንስቶ በአሜሪካ በሚያደርጉት ጉብኝት ወቅት የሚነሳ አጀንዳ እንደሚሆን መናገራቸውን ‘ኤንኤችኬ ሰንደይ’ የተባለው የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።ፈረንሳይ – የፈረንሳይ መንግሥትም በተመሳሳይ በይፋ ምላሽ አልሰጠም። ቅዳሜ ዕለት ትራምፕ ጥያቄውን ካቀረቡ ከሰዓታት በኋላ ግን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይፋዊ የኤክስ ገጽ ፈረንሳይ የጦር መርከቦቿን ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ እየላከች ነው መባሉን አስተባብሏል።የኤክስ አካውንቱ “ትክክል አይለም፤ [የፈረንሳይ] አውሮፕላን ጫኝ መርከብ እና ቡድኑ የሚቆዩት በምሥራቅ ሜዲቲራኒያን [ነው]። አሰላለፋችን አልተቀየረም፤ [አሁንም] መከላከል ላይ ነው” ሲል ጽፏል።ደቡብ ኮሪያ – የፕሬዝዳንት ትራምፕን ጥያቄ በተመለከተ እስካሁን ድረስ ከደቡብ ኮሪያ በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም።ያጋሩ, የጦር መርከቦቻቸውን ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲልኩ በትራምፕ የተጠየቁት አገራት ምን ምላሽ ሰጡ?
  3. ከ 7 ሰአት በፊትአዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ “በጥሩ ጤንነት ላይ” እንደሚገኙ ተገለጸየኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ “በጥሩ ጤንነት ላይ” እንደሚገኙ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ተናገሩ።የጠቅላይ መሪው ደኅንነት ጉዳይ ለቀናት መነጋሪያ ሆኖ ነበር። ባለፈው ሳምንት ማገባደጃ ላይ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሞጅታባ ኻሜኒ “ጉዳት ቢደርስባቸውም” በሕይወት እንዳሉ ተናግረዋል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በበኩላቸው ጠቅላይ መሪው በጥሩ ጤንነት ላይ እንዳሉ እና “ነገሮችን ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠሩ” እንደሚገኙ ገልጸዋል።የኢራን ጠቅላይ መሪ ሆነው ከተመረጡ ወዲህ ላለፉት ሰባት ቀናት በአደባባይ አልታዩም።የመጀመሪያ ይፋዊ ንግግራቸው በቴሌቭዥን መሰናዶ አቅራቢ አማካኝነት የተነበበው ከሦስት ቀናት በፊት ነበር።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ጦርነቱን የሚቋጭ ቀጣናዊ የድርድር ጥረትን” እንደሚደግፉ ተናግረዋል።ሆኖም ግን ይሄንን ለማድረግ የሚያስችል ድርድር እየተካሄ አለመሆኑን ገልጸዋል።ትራምፕ በበኩላቸው “ኢራን መደራደር ብትፈልግም አሜሪካ ዝግጁ አይደለችም” ብለዋል።ያጋሩ, አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ “በጥሩ ጤንነት ላይ” እንደሚገኙ ተገለጸ
  4. ከ 7 ሰአት በፊትበእስራኤል በ24 ሰዓታት ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች 108 ሰዎች ተጎዱየተገለበጠ መኪናየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየእስራኤል ጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች 108 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ገለጸ።እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ ከቆሰሉት ሰዎች ውስጥ 96 ያህሉ የደረሰባቸው ጉዳት አነስተኛ ነው። “መጠነኛ” ጉዳት ደርሶባቸዋል የተባሉት ሁለት ሲሆኑ፤ ዘጠኝ ሰዎች ደግሞ አሁንም ሕክምና እየተከታተሉ እንደሆነ ገልጿል።እስራኤል ከአሜሪካ ጋር ሆና ኢራን ላይ ጥቃት ከከፈተችበት ጊዜ አንስቶ 3,195 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል እንደተወሰዱ ተገልጿል። 81 ሰዎች አሁንም ሕክምና ላይ ናቸው ተብሏል።በኢራን እና ሄዝቦላህ ጥቃት ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አልገለጸም።በሌላ በኩል ትናንት ምሽት ከቴል አቪቭ በስተደቡብ በምትገኘው ሆሎን ከተማ በተፈጸመው ጥቃት የደረሰውን ጉዳት የሚያሳዩ ምሥሎች ወጥተዋል።የተገለበጠ መኪና፣ የተበታተኑ ስብርባሪዎች እንዲሁም መኖሪያ ሕንጻ ግድግዳ ላይ የተፈጠረ ትልቅ ጉድጓድ በፎቶዎቹ ታይተዋል።‘ማገን ዴቪድ አዶም’ የተሰኘው የአደጋ ጊዜ ምላሽ አገልግሎት ተቋም፤ ጥቃት በተፈጸመበት አካበቢ አነስተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሰዎች ማከሙን አስታውቋል።ጥቃት የደረሰበት ሕንጻየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesያጋሩ, በእስራኤል በ24 ሰዓታት ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች 108 ሰዎች ተጎዱ
  5. ከ 8 ሰአት በፊትየኢራን አብዮታዊ ዘብ ኔታንያሁን ‘አሳድደን እንገድላለን’ ሲል ዛተየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁየፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን “አሳድደን ለመግደል የምናደርገውን ጥረት እንቀጥላለን” ሲል ዛተ።የኢራን መንግሥት የሚያስተዳድራቸው መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት፤ የአገሪቱ ጦር ባደረሰው 52ኛ ዙር ጥቃት በእስራኤል ያሉ ዒላማዎች እንዲሁም በቀጣናው የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ተጎድተዋል።አብዮታዊ ዘቡ ባወጣው መግለጫ፤ “ጽዮናዊው ወንጀለኛ ጠቅላይ ሚኒስትር አሁንም በሕይወት ካለ፤ እርሱን ለማደን እና ለመግደል በሙሉ ኃይላችን [እርምጃ መውሰድ] እንቀጥላለን” ማለቱን የዜና ወኪሉ አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢራን ኡሪማ ከተማ ውስጥ ለእስራኤል ወታደራዊ እና የፖሊስ እንዲሁም ሌሎችም የደኅንነት መረጃዎችን በማቀበል የተጠረጠሩ 20 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።ለኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ቅርብ የሆነው ታስኒም እንደዘገበው፤ ከእስራኤል ጋር ትስስር ያላቸው አካሎች ላይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን 20 ግለሰቦችም ታስረዋል።ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኔታንያሁን ‘አሳድደን እንገድላለን’ ሲል ዛተ
  6. ከ 8 ሰአት በፊትጥቃት ማስተናገድ የቀጠሉት የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት እንዴት ሰነበቱ?ቅዳሜ ዕለት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶቹ ፉጃኢራህ ወደብ በእሳት ተይይዞ ነበርየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ቅዳሜ ዕለት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶቹ ፉጃኢራህ ወደብ በእሳት ተይይዞ ታይቷልሳዑዲ አረቢያ – የሪያድ መከላከያ ሚኒስትር ትናንት ሌሊት በሙሉ ወደ አገሪቱ ግዛት የተተኮሱ 26 ድሮኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል። የድሮኖቹ ዋነኛ ዒላማ ዋና ከተማዋ ሪያድ እና የአገሪቱ ምሥራቃዊ ግዛቶች እንደሆኑ ተገልጿል።የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች – የአየር መከላከያ ሥርዓቷ ከኢራን የተተኮሱ የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃቶችን ለማክሸፍ እየሠራ መሆኑን አስታውቃለች። የዩኤኢ መንግሥት ይህንን ያስታወቀው በአገሪቱ ምሥራቃዊ የባሕር ዳርቻ የሚገኘው ዋነኛ የነዳጅ ኤክስፖርት መተላለፊያ የሚገንበት የፉጃኢራህ ወደብ ቅዳሜ ዕለት በደረሰበት የድሮን ጥቃት በእሳት ከተያያዘ በኋላ ነው።ባህሬን – ዩኤኢ ላይ ጥቃቶች በደረሱት በተመሳሳይ ጊዜ ባህሬን ውስጥም የአደጋ ጊዜ የደውል ድምጾች ተሰምተዋል። ነዋሪዎችም በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ መጠለያ እንዲሄዱ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል።ኦማን – ውስጥ ባለው የደኅንነት ስጋት ምክንያት አሜሪካ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ያልሆኑ የመንግሥት ቅጥረኞች እና ቤተቦቻቸው አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ አዝዛለች።ኩዌት – የአገሪቱ ብሔራዊ ዘብ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ አምስት የኢራን ድሮኖችን መትቶ መጣሉን በዛሬው ዕለት አስታውቋል።ኳታር – ቅዳሜ ዕለት ቀኑን ሙሉሲተኮሱባት የዋሉትን እና የቀለበሰቻቸውን የሚሳዔል እና ድሮን ጥቃቶች ዝርዝራ ገልጻለች። ሌሊቱን የተፈጸመ አዲስ ጥቃት ስለመኖሩ አልተገለጸም።ያጋሩ, ጥቃት ማስተናገድ የቀጠሉት የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት እንዴት ሰነበቱ?
  7. 15 መጋቢት 2026አሜሪካ ዜጎቿ ከኢራቅ እና ኦማን እንዲወጡ አሳሰበችትናትን ከተፈጸመው ጥቃት በኋላ ባግዳድ ውስጥ ከሚገኙ ሕንጻዎች ጭስ ሲወጣ ታይቷልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ትናትን ከተፈጸመው ጥቃት በኋላ ባግዳድ ውስጥ ከሚገኙ ሕንጻዎች ጭስ ሲወጣ ታይቷልሁለተኛ ሳምንቱን በተሻገረው የኢራን ጦርነት የሚፈጸሙ ጥቃቶች መቀጠላቸውን ተከትሎ አሜሪካ፤ ኢራቅ እና ኦማን ውስጥ የሚገኙ ዜጎቿ አገራቱን ለቅቀው እንዲወጡ አሳሰበች።ቅዳሜ ዕለት በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ውስጥ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በተፈጸመት ጥቃት በእሳት ተይይዞ ታይቷል።ኤምባሲው ከጥቃቱ በኋላ ባወጣው መግለጫ ዜጎች “በአስቸኳይ” ኢራቅን ለቅቀው እንዲወጡ አሳስቧል። በአገሪቱ ለመቆየት የሚያስብ ማንኛውም አሜሪካዊ ዜጋ ውሳኔውን “በድጋሚ እንዲያጤነውም” መክሯል።ኤምባሲው በኤክስ ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት፤ “ኢራን እና አጋሯ የሆኑ ሽብርተኛ ታጣቂዎች ኢራቅ ውስጥ በሕዝብ ደኅንነት ላይ ትልቅ አደጋ ደቅነዋል። በአሜሪካ ዜጎች፣ በአሜሪካ ይዞታዎች እና ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃቶች ተፈጽመዋል” ብሏል።ኤምባሲው አክሎም፤ “የኢራቅ አየር ክልል ውስጥ ቀጣይነት ያለው የሮኬቶች፣ የድሮኖች እና የሞርታር ስጋት ስላለ ባግዳድ ውስጥ ወደሚገኝ ኤምባሲም ሆነ ኢርቢል ውስጥ ወዳለው ቆንስላ ጽህፈት ቤት ለመምጣት እንዳትሞክሩ” ሲል አስጠንቅቋል።በተጨማሪም አሜሪካ ኦማን ውስጥ የሚገኙ የአደጋ ጊዜ ሠራተኛ ያልሆኑ የመንግሥት ተቀጣሪዎች እና የመንግሥት ሠራተኛ ዘመዶች አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መስጠቷን የዜና ወኪሉ ሮይተርስ ዘግቧል።አሜሪካ እነዚህን ማሳሰቢያዎች የሰጠችው ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ በሚገኙ የአሜሪካ ዒላማዎች ላይ ጥቃቶችን መፈጸሟን ተከትሎ ነው። በኢራን ጥቃት የተነሳም በበርካታ የቀጣናው አገራት የሚገኙ ዜጎቿን ለቅቀው እንዲወጡ አሳስባለች።ያጋሩ, አሜሪካ ዜጎቿ ከኢራቅ እና ኦማን እንዲወጡ አሳሰበች
  8. 15 መጋቢት 2026ኢራን በኢነርጂ ተቋማት ላይ የሚደርስባትን ጥቃት የአሜሪካ ኩባንያዎችን ዒላማ በማድረግ እንደምትመልስ ተናገረችየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesኢራን በኢነርጂ ተቋማቷ ላይ ለደረሰባት ጥቃት በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ኩባንያዎችን በማጥቃት ምላሽ እንደምትሰጥ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ መግለጻቸው ተዘገበ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “የኢራን ተቋማት ዒላማ የሚደረጉ ከሆነ ኃይሎቻችን በቀጣናው ያሉ የአሜሪካ ኩባንያዎችን ወይም አሜሪካ ድርሻ የያዘችባቸው ኩባንያዎችን የጥቃት ዒላማ ያደርጋሉ” ማለታቸውን ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያለው ታስኒም የዜና ወኪል ዘግቧል።“በእርግጠኝነት ለእነዚህ ጥቃቶች ምላሽ እንሰጣለን፤ በተመሳሳይ ጥቅጥቅ ያለ ሕዝብ የሚገኝባቸውን አካባቢዎች ዒላማ ላለማድረግ በጥንቃቄ እንንቀሳቀሳለን” ብለዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት አሜሪካ ለኢራን ወሳኝ በሆነው እና የአገሪቱ 90 በመቶ ነዳጅ ይተላለፍበታል ተብሎ በሚታሰብበው ኻርግ ደሴት ላይ ጥቃት ከፈጸመች በኋላ ነው።የኢራን የዜና ወኪል ባወጣው ዘገባ አሜሪካ የአየር መከላከያዎችን፣ የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር፣ የአየር ማረፊያ መቆጣጠሪያ ህንጻ እንዲሁም የሄሊኮፕተር ማቆሚያ ስፍራ ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታውቋል። በነዳጅ መሠረተ ልማት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩንም ዘገባው አመልክቷል።በተጨማሪም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአሜሪካው መገናኛ ብዙኃን ‘ኤምኤስ ናው’ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ አሜሪካ ኢራን ውስጥ የሚገኙ የሲቪል ዒላማዎች ላይ ጥቃት እየፈጸመች ነው ሲሉ ከስሰዋል። አሜሪካ ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚቀርብባትን ክስ አስተባብላለች።አግራቺ አክለውም ኢራን በቀጣናው የሚገኙ አገራት ውስጥ ዒላማ የምታደርገው የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች እና ይዞታዎችን ነው ሲሉ አገራቸውን ተከላክለዋል። የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት የጥቃት ዒላማ የሆኑት “እንደ አለመታደል ሆኖ” የአሜሪካ ይዞታዎች “የሚገኙት በጎረቤቶች ግዛት ውስጥ” በመሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል።ያጋሩ, ኢራን በኢነርጂ ተቋማት ላይ የሚደርስባትን ጥቃት የአሜሪካ ኩባንያዎችን ዒላማ በማድረግ እንደምትመልስ ተናገረች
  9. 15 መጋቢት 2026ትራምፕ ዩኬ እና ሌሎችም አገራት ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የጦር መርከብ እንዲልኩ ጠየቁበሆርሙዝ ወሽመጥ የሚተላለፍ መርከብየፎቶው ባለመብት,Reutersበመካከለኛው ምሥራቅ ዋነኛው የባሕር መተላለፊያ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመጠበቅ አገራት የጦር መርከቦችን እንዲያሰማሩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠየቁ።ዩናይትድ ኪንግደም፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ጃፓን እና ደቡብ ኮርያ የጦር መርከቦቻቸውን ወደ ቀጣናው ይልካሉ ብለው እንደሚጠብቁ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት መክፈታቸውን ተከትሎ ቴህራን በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚተላለፉ መርከቦች ላይ ጉዳት አድርሳለች።የዓለም 20% ነዳጅ መተላለፊያ የሆነውን የሆርሙዝ ሰርጥ ደኅንነት ለማስጠበቅ አገራት የጦር መርከቦች ማሰማራት እንደሚጠበቅባቸው ትራምፕ ተናግረዋል።ቴህራን የሆርሙዝ ወሽመጥን መዝጋት እንደምትቀጥል አስታውቃለች። በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ ነዳጅ አምራች እና አከፋፋይ ተቋማትንም ዒላማ አድርጋለች።የኢራን “100% ወታደራዊ አቅም ወድሟል” ያሉት ትራምፕ “ብዙ አገራት የሆርሙዝ ወሽመጥን ደኅንነት ለመጠበቅ የጦር መርከቦች ይልካሉ” ሲሉ በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ሚዲያቸው ጽፈዋል።ያጋሩ, ትራምፕ ዩኬ እና ሌሎችም አገራት ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የጦር መርከብ እንዲልኩ ጠየቁ
  10. 15 መጋቢት 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ ኢራን መደራደር ብትፈልግም አሜሪካ ዝግጁ አይደለችም አሉፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ አሜሪካ ሁለተኛ ሳምንቱን የደፈነውን የኢራን ጦርነት ለመቋጨት የሚያስችል ስምምነት ላይ ለመድረስ ዝግጁ አይደለችም አሉ።ትራምፕ ከአሜሪካው ‘ኤንቢሲ’ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት የስልክ ቃለ መጠይቅ፤ ኢራን ስምምነት ለመፈጸም ፈልጋለች ብለዋል። ነገር ግን “የቀረቡት የድርድር ነጥቦች ገና በቂ ስላልሆኑ” ንግግር ለማደረግ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።ፕሬዝዳንቱ በቂ አይደሉም የተባሉት የድርድር ነጥቦች ምን እንደሆኑ ከመናገር ተቆጥበዋል። ነገር ግን ኢራን የኒውክሌር ፍላጎቷን ሙሉ በሙሉ እንድትተው የማድረግ እርምጃ በሁለቱ አገራት መካከል ሊደረስ የሚችል ስምምነት አካል እንደሚሆን ገልጸዋል።በተመሳሳይ፤ የአሜሪካ አጋር የሆኑ የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ጦርነቱን ለመቋጨት ያለመ ዲፕሎማሲያዊ ድርድር እንዲደረግ ያደረጉትን ጥረት የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር ውድቅ ማድረጉን የዜና ወኪሉ ሮይተርስ ዘግቧል።ኢራንም፤ አሜሪካ እና እስራኤል የሚፈጽሙት ጥቃት እስካልቆመ ድረስ ማንኛውንም የተኩስ አቁም እርምጃ እንደማትቀበል ሁለት የኢራን ከፍተኛ ምንጮች ለሮይተርስ ተናግረዋል። በርካታ አገራት ኢራንን ለማሸማገል ጥረት እንዳደረጉም ተገልጿል።አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ ጦርነት የከፈቱት ዋሽንግተን እና ቴህራን ጄኔቫ ውስጥ ድርድር ባደረጉ በቀናት ልዩነት ነበር። ይህንን ድርድር ስታመቻች የነበረችው ኦማን፤ በድጋሚ ግንኙነት እንዲጀመር በርካታ ጊዜያት ጥረት እንዳደረገች ተዘግቧል።ሮይተርስ ሁለት ምንጮችን ጠቅሶ ያወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተው፤ ዋይት ሀውስ ለድርድር ፍላጎት እንደሌለው በግልጽ አሳውቋል።ይህንን ጥረት ያጣጣሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ ትኩረታቸው የቴህራንን ወታደራዊ አቅም ይበልጥ ማዳከም ላይ እንደሆነ ተነግሯል።በተጨማሪም ትራምፕ ከኤንቢሲ ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ የአዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ በሕይወት የመኖር ጉዳይ ላይ ጥያቄ አንስተዋል።የጠቅላይ መሪው የመጀመሪያ መግለጫ በመገናኛ ብዙኃን መነበቡን በማንሳትም፤ “በሕይወት መኖሩን እንኳ አላውቅም። እስካሁን ማንም ሊያሳየው አልቻለም” ብለዋል።“በሕይወት እንደሌለ እየሰማሁ ነው። በሕይወት ካለ ለአገሩ ብልሕነት የተሞላበት ነገር ማድረግ አለበት፤ እርሱም እጅ መስጠት ነው” ብለዋል። ቀጥሎም ግን የጠቅላይ መሪውን ሞት “ወሬ” ሲሉ ገልጸውታል።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ ኢራን መደራደር ብትፈልግም አሜሪካ ዝግጁ አይደለችም አሉ
  11. 14 መጋቢት 2026ትራምፕ ሳዑዲ ውስጥ የአሜሪካ አውሮፕላኖች መመታታቸውን አስተባበሉፕሬዝዳንት ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሳዑዲያ አረቢያ ውስጥ በሚገኘው ልዑል ሱልጣን የአየር ኃይል ሰፈር የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕኖች በኢራን ጥቃት ተመቱ መባሉን አስተበባሉ።ቀደም ሲል የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን የመንግሥት ምንጮችን ጠቅሰው አምስት የጦር ጄቶችን አየር ላይ ነዳጅ መሙላት የሚችሉ አምስት ወታደራዊ አውሮፕላኖች መመታታቸውን ዘግበው ነበር።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በትሩዝ ሶሻል የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ የአየር ኃይል ሰፈሩ ከቀናት በፊት ጥቃት እንደደረሰበት እና አውሮፕላኖቹ “እንዳልተመቱ እና እንዳልተጎዱ” በመግለጽ አስተባብለዋ።”ከአምስቱ አውሮፕላኖች አራቱ ፈጽሞ ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰባቸውም፣ ወደ ሥራቸው ገብተዋል። አንዱ ግን በትንሹ ጉዳት ደርሶበታል፣ ነገር ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ በረራ ይመለሳሉ” በማለት ዘገባውን ያወጡ መገናኛ ብዙኃንን ተችተዋል።ያጋሩ, ትራምፕ ሳዑዲ ውስጥ የአሜሪካ አውሮፕላኖች መመታታቸውን አስተባበሉ
  12. 14 መጋቢት 2026በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች በየትኞቹ አገራት ይገኛሉ?ሦስተኛ ሳምንቱን በጀመረው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ያልተቋረጠ ጥቃት እያካሄዱ ነው። ኢራንም በበኩሏ በእስራኤል እና የአሜሪካ አጋር በሆኑ የአካባቢው አገራት ላይ የአጸፋ ጥቃት እየፈጸመች ነው።እስራኤል እና ኢራን ወትሮም በጠላትነት የሚፈላለጉ ባላንጣዎች ሲሆኑ፣ ሌሎቹ የመካከለኛውም ምሥራቅ አገራት ለምን የኢራን ዒላማ ሆኑ?ኢራን በዙሪያዋ በሚገኙ የባሕረ ሰላጤው አገራት ላይ አጸፋ መመለስ የጀመረችው ለሚፈጸምባት ጥቃት መነሻ እና ማስተባበሪያ በመሆናቸው ነው።አሜሪካ ጥቅሟን ለማስከበር እና ወዳጇቾን ለመጠበቅ በአካባቢው አገራት ውስጥ ዘመናትን ያስቆጠሩ ወታደራዊ ጦር ሰፈሮች እና የዕዝ ማዕከላት አሏት። በተጨማሪም ወታደሮቿ በትንሽ ቁጥር ቢሆንም የሚገኙባቸው አገራት አሉ።በተለይ የደሴት አገራት በሆኑት እና ለኢራን ቅርብ በሆኑት በባህሬን እና በኳታር ውስጥ ግዙፍ ጦር ሰፈሮች አሏት።በኳታር ውስጥ በመካከለኛው ምሥራቅ ትልቁ የአየር ኃይል ሰፈር ሲኖራት፣ በባሕሬው ውስጥ ደግሞ ግዙፍ የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር ያላት ሲሆን፣ በሁለቱም ውስጥ የጦር አውሮፕላኖች እና መርከቦች ከወታደሮች ጋር ዝግጁ ሆነው ይገኛሉ።ለመሆኑ ለኢራን የሚሳዔል እና የድሮን የአጸፋ ጥቃት የተጋለጡት እና የአሜሪካ ጦር ሰፈር እንዲሁም ወታደሮች የሚገኙባቸው አገራት እነማን ናቸው?ካርታያጋሩ, በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች በየትኞቹ አገራት ይገኛሉ?
  13. 14 መጋቢት 2026በመካከለኛው ምሥራቅ የደረሱ ጥቃቶችን የሚያሳዩ ምሥሎችበዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ በፉጃይራህ ወደብ በሚገኘው እና በቀጣናው ግዙፍ የሆነው የነዳጅ ማከማቻ በድሮን ጥቃት ከደረሰበት ወዲህ ከፍተኛ ጭስ ታይቷል።በደቡባዊ ሊባኖስ በሃሬት ሳይዳ አካባቢ ሲዶን በተባለ ስፍራ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት የመኖሪያ አፓርታማ በእሳት ተያይዟል።በማዕከላዊ እስራኤል ሾሃም በደረሰ ጥቃት የመኖሪያ ሕንጻ ጣሪያ ሙሉ በሙሉ ወድሟል።የእስራኤል መከላከያ ሌሊቱን ከኢራን የተተኮሱ ሚሳዔሎችን መለየቱን አስታውቆ ነበር።በፉጃይራ ወደብ ካለው የነዳጅ ማከማቻ አቅጣጫ ጭስ ሲወጣ ይታያልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በፉጃይራህ ወደብ ካለው የነዳጅ ማከማቻ አቅጣጫ ጭስ ሲወጣ ይታያልበደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ በሲዶና ሃሬት ሳይዳ አካባቢ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት የመኖሪያ ሕንጻ ላይ ጉዳት ደርሷልየፎቶው ባለመብት,Shutterstockየምስሉ መግለጫ,በደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ በሲዶና ሃሬት ሳይዳ አካባቢ የእስራኤል ጥቃትበማዕከላዊ እስራኤል በሾሃም ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ የመኖሪያ አካባቢ ትናንት ሌሊት በተፈፀመ የሚሳኤል ጥቃት ጉዳት የደረሰበት ሕንጻየፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,በማዕከላዊ እስራኤል በሾሃም ከተማ አቅራቢያያጋሩ, በመካከለኛው ምሥራቅ የደረሱ ጥቃቶችን የሚያሳዩ ምሥሎች
  14. 14 መጋቢት 2026ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የተከሰቱ ዋና ዋና ነገሮችበከተማ ውስጥ የተፈጸመ ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በከተሞች ላይ የሚፈጸመው የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃት ቀጥሏልአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የጀመሩት ጦርነት ሁለት ሳምንት ሲሞላው ግጭቱ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ተስፋፍቷል። ጦርነቱ በቀናት ውስጥ ተባብሶ የባሕረ ሰላጤው አገራት ከኢራን በሚፈጸምባቸው ጥቃት ምክንያት ራሳቸውን በጦርነቱ ግንባር ውስጥ አግኝተዋል።ጦርነቱ ሦስተኛውን ሳምንት በጀመረበት በዛሬው ዕለት ባለፉት ሁለት ሳምንታት የተከሰቱትን ዋና ዋና ነገሮች መለስ ብለን በአጭሩ እንመልከት፡ጥቃት፣ የአጸፋ ጥቃት እና የኢራን መሪዎች
    • አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 21/2018 ዓ.ም. በጋራ በኢራን ላይ በከፈቱት ጥቃት ጦርነቱ ተጀመረ። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዘመቻው ዓላማ “ተጨባጭ ስጋቶችን” ለማስወገድ መሆኑን ተናግረው ነበር።
    • በምላሹም ኢራን እስራኤልን እና የአሜሪካ ወዳጅ የሆኑ የባሕረ ሰላጤው አገራት ላይ የአጸፋ ጥቃት መሰንዘር ጀመረች።
    • ያልተረጋገጡ ወሬዎች ሲዘዋወሩ ቆይተው ከጥቃቱ መጀመር ከአንድ ቀን በኋላ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ኻሜኒ በመኖያቸው ላይ በተፈጸመ ጥቃት መገደላቸው ታውቋል።
    • ከዚያ በኋላም ዋና ከተዋ ቴህራን በተከታታይ የአየር ድብደባ ተመትታለች። የሳተላይት ምሥሎችም በኢራን የሚሳዔል እና የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን አሳዩ።
    • በኢራን ውስጥ እና በቀጣናው አገራት የሚገኙ የነዳጅ መከማቻዎች እና ማጣሪያዎች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
    • እስራኤል በጎረቤቶቿ ሊባኖስ ደበባዊ ክፍል ላይ ጥቃት የከፈተች ሲሆን፣ ኮማንዶዎቿንም ወደ ሊባኖስ ግዛት በማስገባት ጥቃት ፈጽማለች። እርምጃው የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን የሆነው ሔዝቦላህ ትጥቅ እስኪፈታ ድረስ እንደሚቀጥል አስታውቃለች።
    • የሟቹ የኢራን መሪ ልጅ ሞጅታባ ኻሜኒ የአገሪቱ ቀጣዩ መሪ መሆናቸው ይፋ ተደረገ። ነገር ግን ከምርጫው በኋላ አስካሁን ድረስ ለሕዝብ በይፋ አልታዩም። ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ሌሎችም ባለሥልጣናት አዲሱ መሪ በተፈጸመባቸው ጥቃት መቁሰላቸውን እየተናገሩ ነው።
    የተቃጠለ የነዳጅ ጫኝ መኪና ላይየምስሉ መግለጫ,የነዳጅ ማውጫ እና ማጣሪያ ተቋማት ዒላማ ሆነዋልየጦነርቱ ያስከተለው ዳፋ
    • በጦርነቱ ምክንያት በሰው ላይ የሚደርሰው ጉዳት መጨመሩን የቀጠለ ሲሆን፣ አስካሁንም በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል።
    • በኢራን ላይ እየተካሄደ ባለው ዘመቻ አስከሁን 13 የአሜሪካ ወታደሮች ሲሞቱ፣ ከመካከላቸው ስድስቱ የአሜሪካ አየር ኃይል ነዳጅ ጫኝ ወታደራዊ አውሮፕላን ኢራቅ ውስጥ ወድቆ በመከስከሱ የሞቱ ናቸው።
    • የነዳጅ ዘይት ዋጋ ከነበረበት በበርሜል ከ70 ዶላር በታች በከፍተኛ ፍጥነት ጭማሪ በማሳየት ከ100 ዶላር በላይ ሆኗል። በዚህም ምክንያት በዓለም ዙሪያ የዋጋ ግሽበት እና የምጣኔ ሀብት አለመረጋጋት ተፈጥሯል።
    • በጦርነቱ ምክንያት አገራት የአየር ክልላቸውን በመዝጋታቸው የአውሮፕላን በረራዎች ተቋርጠዋል። ከመካከለኛው ምሥራቅ ለመውጣት የሚፈልጉ የሌሎች አገራት ዜጎች የመውጫ መንገድ እየፈለጉ ነው።
    • የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ኢራን ሙሉ ለሙሉ ሽፈንቷን ተቀብላ እጅ ካልሰጠች ጦርነቱ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
    ጥቃቶች እንደቀጠሉ ነውየምስሉ መግለጫ,አሜሪካ በኢራን ላይ የምትፈጽመው ጥቃት ቀጥሏልያጋሩ, ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የተከሰቱ ዋና ዋና ነገሮች
  15. 14 መጋቢት 2026ሐማስ ኢራን በጎረቤቶቿ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም ጠየቀካርታየምስሉ መግለጫ,ኢራን የአጸፋ ጥቃት የፈጸመችባቸው አገራትየኢራን ወዳጅ የሆነው ፍልስጤማዊው ታጣቂ ቡድን ሐማስ ኢራን በዙሪያዋ ያሉ ጎረቤት አገራትን ዒላማ አድርጋ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም ጠየቀ።በተጨማሪም አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በአሜሪካ-እስራኤል እና በኢራን መካከል የሚደረገው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧለ።ሐማስ በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት “በጣሙን አሳሳቢ” በሆነ ሁኔታ እየተከታተለው መሆኑን በመጥቀስ፣ ሁኔታው “የቀጣናውን እና የዓለምን ሰላም እና መረጋጋትን አደጋ ላይ የሚጥል ነው” በማለት ስጋቱን ገልጿል።ቡድኑ በቴሌግራም ገጹ ላይ ባሠራጨው መግለጫው አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት ዓለም አቀፍ ሕግን እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕጎችን የሚጥስ ነው በማለት፣ በቀጣናው የሚገኙ አገራት በመተባበር በኢራን ላይ የተከፈተውን ጦርነት እዲያስቆሙ ጠይቋል።ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በጋዛ ውስጥ ለሁለት ዓመታት በደረሰ ጥቃት ከባድ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፣ ጋዛም በከፍተኛ ሁኔታ ወድማለች።እስራኤል እና ሐማስ ጋዛ ውስጥ ባካሄዱት ጦርነት ከ70 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።ሐማስ በአሜሪካ፣ በዩናይትድ ኪንግደም እና በሌሎችም ምዕራባውያን አገራት በሽብር ድርጅትነት የተፈረጀ ነው።ያጋሩ, ሐማስ ኢራን በጎረቤቶቿ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም ጠየቀ
  16. 14 መጋቢት 2026ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት ስትከፍት፣ እስራኤል ደግሞ ለኢራናውያን ማስጠንቀቂያ አወጣችበመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ኢራን እና እስራኤል የሚፈጽሙት ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ኢራን በእስራኤል ላይ ተከታታይ ጥቃቶችን መክፈቷን ስታስታውቅ፣ እስራኤል ደግሞ ከአንዳንድ ቦታዎች ኢራናውያን ለቅቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች።የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በዛሬው ዕለት 48ኛውን የጥቃት ማዕበል በእስራኤል ላይ መክፈቱን የኢራን መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።የእስላማዊ ሪፐብሊክ ዜና ወኪል እንዳለው ጥቃቶቹ የተከፈቱት በሊባኖስ ከሚገኘው ሄዝቦላህ ጋር በመቀናጀት በአንድ ላይ ነው።ከዚህ ጋር በተያያዘም የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኝ የሔዝቦላህን የጦር መሳሪያ ማከማቻን መምታቱን እና በኢራን የሚደገፈው ቡድን አባላት ወደ ማከማቻው ሮኬቶችን ሲያጓጉዙ መታየታቸውን ገልጿል።ይህንንም ተከትሎ የእስራኤል አየር ኃይል የጦር መሳሪያ ማከማቻውን በመደብደብ የሔዝቦህ አባላትን “መደምሰሱን” ጦር ኃይሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።በኢራን ላይ ጥቃት እያካሄደው የሚገኘው የእስራኤል ጦር በምዕራባዊ ኢራን ውስጥ በምትገኘው ታብሪዝ ከተማ ውስጥ ባለ የኢንዱስትሪ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።ጥቃት የሚፈጸምበትን አካባቢ ከሚያመለክት ካርታ ጋር ለከተማዋ ነዋሪዎች የተላለፈው ማስጠንቀቂያው፣ በተጠቀሰው ስፍራ የእስራኤል ሠራዊት “በቀጣይ ሰዓታት ውስጥ እርምጃ እንደሚወስድ” ገልጿል።ጨምሮም ጥቃቱ በቅርቡ ከተፈጸሙ ወታደራዊ እርምጃዎች ጋር የሚመሳሰል እና የኢራን አገዛዝን ወታደራዊ መሠረተ ልማት ዒላማ ያደረገ መሆኑንም አስታውቋል።በዚህም ምክንያት በተጠቀሰው አካባቢ ያሉ ሰዎች ለደኅንነታቸው ሲሉ በአስቸኳይ ለቅቀው እንዲወጡ እና በቦታው መቆየት በሕይወት ላይ አደጋ የሚያስከትል መሆኑን አስጠንቅቋል።ያጋሩ, ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት ስትከፍት፣ እስራኤል ደግሞ ለኢራናውያን ማስጠንቀቂያ አወጣች
  17. 14 መጋቢት 2026በሊባኖስ የሕክምና ባለሙያዎችን ጨምሮ በርካቶችን የገደለው የእስራኤል ጥቃትበደቡባዊ ሊባኖስ በሲዶና ሃሬት ሳይዳ አካባቢ የእስራኤል የአየር ጥቃት የደረሰበት አካባቢየፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,በደቡባዊ ሊባኖስ በሲዶና ሃሬት ሳይዳ አካባቢ የእስራኤል የአየር ጥቃት የደረሰበት አካባቢእስራኤል በደቡብ ሊባኖስ ከሄዝቦላህ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ስፍራዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን የሚገልጹ ዘገባዎች መሰማት ጀምረዋል።የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር ሌሊቱን በቡርጅ ቃላዊያ ከተማ በተፈጸመ ጥቃት ዶክተሮችን እና ነርሶችን ጨምሮ 12 የሕክምና ባለሙያዎች መገደላቸውን አስታውቋል።እስራኤል መንገዶችን እና ድልድዮችን ጨምሮ ሌሎች መሠረተ ልማቶች ላይ ድብደባዎችን መፈጸሟ እየተገለፀ ነው።በአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል እስራኤል ጥቃት ከመፈጸሟ በፊት ነዋሪዎች ለቅቀው እንዲወጡ የተነገረቸው ስፍራ መጠን እጅግ በጣም እየጨመረ ሲሆን፣ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ወደ ሰሜናዊ ሊባኖስ ተሰድደዋል።በሊባኖስ የሚገኙ በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና መንግሥት የተፈናቃዮች ቁጥር በየጊዜው ስለሚጨምር መቸገራቸውን ይናገራሉ።እስራኤልም ሆነች ሄዝበላህ አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት እንዲሁም የመግለጫ ልውውጣቸው እየተካረረ መምጣቱን ተከትሎ መጠነ ሰፊ ጦርነት አይቀሬ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት ጨምሯል።እስራኤል ዛሬ ማለዳ በደቡባዊ ሊባኖስ የፈጸመችው ጥቃት በሃሬት ሳይዳ አካባቢ የሚገኝ ሕንጻ ላይ ውድመት አድርሷል።በጥቃቱ የሞቱ ሰዎች ስለመኖራቸው እስካሁን ድረስ የታወቀ ነገር ባይኖርም ጦርነቱ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ግን በአጠቃላይ ከ770 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።የሕይወት አድን እና የእሳት አደጋ ሠራተኞች የእስራኤል አየር ጥቃት በደረሰበት ስፍራ ላይ እሳት ለማጥፋት ሲረባረቡየፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,የሕይወት አድን እና የእሳት አደጋ ሠራተኞች የእስራኤል አየር ጥቃት በደረሰበት ስፍራ ላይ እሳት ለማጥፋት ሲረባረቡያጋሩ, በሊባኖስ የሕክምና ባለሙያዎችን ጨምሮ በርካቶችን የገደለው የእስራኤል ጥቃት
  18. 14 መጋቢት 2026አምስት የአሜሪካ አውሮፕላኖች ሳዑዲ ውስጥ በኢራን ሚሳዔል ተመቱጉዳት ከደረሰባቸው ጋር የሚመሳሰሉ የአሜሪካ አውሮፕላኖች እስራኤል ውስጥየፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,ጉዳት ከደረሰባቸው ጋር የሚመሳሰሉ የአሜሪካ አውሮፕላኖች እስራኤል ውስጥአምስት የአሜሪካ አየር ላይ ነዳጅ የሚሞሉ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በኢራን ተመትተው ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ዎል ስትሪት ጆርናል ዘገበ።አውሮፕላኖቹ በሳዑዲው ልዑል ሱልጣን የአየር ኃይል ሰፈር ውስጥ ሳሉ ከቀናት በፊት ኢራን በፈጸመችው የሚሳዔል ጥቃት መመታታቸውን ጋዜጣው የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።ነዳጅ ጫኝ የሆኑት ወታደራዊ አውሮፕላኖች በደረሰባቸው ጥቃት ጉዳት እንደረሰባቸው ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ አለመውደማቸውን ባሥልጣናት ተናግረው “በአሁኑ ጊዜ ጥገና እየተደረገላቸው” መሆኑን እና በጥቃቱ በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱን መናገራቸውን ዎል ስትሪት ጆርናል ገልጿል።ይህ በአምስት የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላን ላይ ጥቃት መፈጸሙን የሚገልጸው ዘገባ የወጣው ኬሲ-135 ነዳጅ የሚሞላ የአሜሪካ አየር ኃይል አውሮፕላን ባለፈው ሐሙስ በምዕራባዊ ኢራቅ ውስጥ መከስከሱ ከተነገረ በኋላ ነው።በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካንን ወታደራዊ ተልዕኮዎች የሚቆጣጠረው የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ኃይል ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) እንዳረጋገጠው በአደጋው በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ሁሉም ስድስት አባላቱ ሞተዋል።ያጋሩ, አምስት የአሜሪካ አውሮፕላኖች ሳዑዲ ውስጥ በኢራን ሚሳዔል ተመቱ
  19. 14 መጋቢት 2026በኳታር ዶሃ ነዋሪዎች ከከተማዋ ማዕከል እንዲወጡ እየተደረገ ነውዶሃየፎቶው ባለመብት,EPAየኳታር የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ከበርካታ አካባቢዎች ለጥንቃቄ በሚል ነዋሪዎችን እያስወጣ መሆኑን አስታወቀ።እስካሁን ባለው መረጃ የስጋቱ መጠን እና ዓይነት ባይታወቅም ኳታር ሌሊቱን እና ዛሬ ጠዋት ሁለት የሚሳዔል ጥቃቶችን አስተናግዳለች።ኢራን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የአሜሪካ ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን የሚያስተናግዱ አገራት ዒላማዎች እንደሚሆኑ ከተናገረች በኋላ ኳታር የወሰደችው እርምጃ ያንን ለመከላከል ይመስላል።ነዋሪዎች የዶሃ ማዕከላዊ የሙሼይርብ አካባቢን በፍጥነት ለቅቀው እንዲወጡ የስልክ መልዕክት ደርሶቸዋል።አካባቢው የጉግል እና የአሜሪካን ኤክስፕረስ ቢሮዎች የሚገኙበት ነው። የፀጥታ አካላት በማይክሮሶፍት ኳታር ዋና መሥሪያ ቤት አካባቢ እንደሚሰማሩም ተነግሯል።ሮይተርስ የዜና ወኪል በበኩሉ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ስድስት የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ካምፓሶች ከሚገኙበት አካባቢ ነዋሪዎች የተወሰነውን ስፍራ ለቅቀው እንዲወጡ ማድረጋቸውን ዘግቧል።በሌላ የመካከለኛው ምሥራው የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች አሁንም ስጋት ውስጥ ናቸው። በባግዳድ የሚገኙ የደኅንነት ባለሥልጣናት ኤምባሲው ጥቃት እንደደረሰበት ተናግረዋል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደግሞ አስፈላጊ ያልሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች ከኦማን እንዲወጡ እያደረገ ነው።ያጋሩ, በኳታር ዶሃ ነዋሪዎች ከከተማዋ ማዕከል እንዲወጡ እየተደረገ ነው
  20. 14 መጋቢት 2026ከአሜሪካ ጋር የሚሠሩ የነዳጅ ተቋማትን ‘የአመድ ክምር’ እንደምደታርግ ኢራን ዛተችየሚቃጠል የነዳጅ ማከማቻየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ኢራብ ን ባለፉት ቀናት በቀጣናው የሚገኙ የነዳጅ ተቋማትን ዒላማ አድርጋለችከአሜሪካ ተቋማት ጋር የሚሠሩ የነዳጅ እና የጋዝ አምራች ድርጅቶችን የኢራን ጦር ሠራዊት “በማውደም ወደ አመድ ክምርነት እንደሚለውጣቸው” መግለጹን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።ይህ በኢራን የዜና ወኪሎች ፋርስ እና ታስሚን የተዘገበው የሠራዊቱ መግለጫ የወጣው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላስተለላፉት መልዕክት “ምላሽ” መሆኑ ተገልጿል።በትሩዝ ሶሻል ላይ ፕሬዝዳንቱ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ የአሜሪካ ኃይሎች በኻርጅ ደሴት እና ከፍተኛ መጠን ያለው የዓለም የነዳጅ ምርት በሚያልፍበት በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚገኙ የኢራን ወታደራዊ ተቋማት “ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል” ብለዋል።ተጨማሪ የአሜሪካ የባሕር ኃይል ወታደሮች እና የጦር መርከቦች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሊሰማሩ መሆኑን ቀደም ሲል በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ሆነው ሲቢኤስ ቴሌቪዥን ዘግቧል።ባለሥልጣናትም ዝግጁ ከሆኑ የባሕር ላይ ወታደራዊ ቡድኖች እና የባሕር አሳሽ ኃይሎች በኢራን አካባቢ ያለውን አሜሪካ ጦር ለማጠናከር ከሌሎች አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል።ተያያዥ ዘገባ ያንብቡ በኢራን ጦርነት የትኞቹ አገራት ሊያተርፉ ይችላሉ? የሚጎዱትስ እነማን ናቸው?ያጋሩ, ከአሜሪካ ጋር የሚሠሩ የነዳጅ ተቋማትን ‘የአመድ ክምር’ እንደምደታርግ ኢራን ዛተች