የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር አገራቸው ከኢራን ጋር በተያያዘ ወደ “ሠፊ ጦርነት” ተስባ እንደማትገባ፤ ነገር ግን የሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲከፈት ለማድረግ “ከአጋሮች ጋር እንደምትሠራ” ተናገሩ።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 9 ሰአት በፊትየኢራን ጦር እስራኤል ውስጥ የሚገኙ የጦር መሣሪያ ማምረቻዎችን መትቻለሁ አለየኢራን ሜሳዔል እና ባንዲራየፎቶው ባለመብት,NurPhotoየኢራን ጦር፤ በዛሬው ዕለት እስራኤል ውስጥ የሚገኙ የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪ ማዕከላትን በድሮን ጥቃት መደብደቡን ገለጸ።የኢራን ጦር የሕዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፤ በዛሬው ዕለት እስራኤል ውስጥ የሚገኙ ወሳኝ እና ስትራቴጂክ የጦር መሣሪያ ማዕከላትን ዒላማ ማድረጉን አስታውቋል።ራፋኤል በተሰኘው ኩባንያው እንዲሁም ‘ኢዝራኤል ኤሮስፔስ ኢንደስትሪስ’ የተባለው ተቋምን መምታቱንም ተናግሯል።ራፋኤል የተባለው ኩባንያ እንደ አይረን ዶም እና ዴቪድስ ስሊንግ ያሉ የአየር መከላከያ ሥርዓቶችን የሚሠራ ተቋም ነው። ስፓይክ ሚሳዔሎች እና ወታደራዊ የኤሌክትሮኒክ ቴክኖሎጂዎችም ኩባንያው ውስጥ ይሠራሉ።‘ኢዝራኤል ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪስ’ ደግሞ የውጊያ አውሮፕላኖች፣ ድሮኖች፣ ሚሳዔሎች እና የመከላከያ ሥርዓቶችን ያመርታል። እንደ አሮው ሚሳኤል መከላከያ ያሉ ወሳኝ ሥርዓቶችንም እንደሚያመርት የፋርስ ዜና ወኪል ዘገባ ያመለክታል።ያጋሩ, የኢራን ጦር እስራኤል ውስጥ የሚገኙ የጦር መሣሪያ ማምረቻዎችን መትቻለሁ አለ
  2. 16 መጋቢት 2026ኔቶ በሆርሙዝ ወሽመጥ ጉዳይ ይሳተፋል ብለው እንደማያስቡ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩየጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሃን ዋድፉልየፎቶው ባለመብት,EPAየሰሜን አትላንቲን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በኢራን የተዘጋውን የሆርሙዝ ወሽመጥ የማስከፈት ሂደት ውስጥ ሚና ይኖረዋል ብለው እንደማያስቡ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዩሃን ዋድፉል ተናገሩ።ኢራን ወሳኝ የነዳጅ ምርቶች መተላለፊያ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥ መዝጋቷን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አገራት የባሕር መስመሩን ለማስከፈት እንዲቀሳቀሱ ጥሪ እያቀረቡ ነው።ትራምፕ ከፋይናንሻል ታይምስ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ አጋር አገራት ወሽመጡን ለመቆጣጠር እገዛ የማያደርጉ ከሆነ “ለኔቶ መጻኢ እጅግ መጥፎ” እንደሚሆን ተናግረዋል።የአወሮፓ ኅብረት በዚሁ ጉዳይ ላይ ሊያደርግ ካቀደው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በፊት ንግግር ያደረጉት የጀርመኑ ሚኒስትር፤ የኔቶ ተሳትፎን ጉዳይ አንስተዋል።“ኔቶ በዚህ አቅጣጫ ውሳኔ ማሳለፉ ወይም የሆርሙዝ ወሽመጥን በተመለከተ ኃላፊነት መውሰዱ አይታየኝም። ጉዳዩ ይህ ቢሆን ኖሮ የኔቶ አካላት በዚሁ አኳዃን መፍትሔ ይሰጡት ነበር” ብለዋል።ያልተረጋጋው የመካለኛው ምሥራቅ ሁኔታ ቢኖርም፤ አውሮፓ ደኅንነትን በተመለከተ ቅድሚያ የምትሰጠው የዩክሬንን ጉዳይ እንደሆነ ዋድፉል ተናግረዋል። የነዳጅ እና ጋዝ ዋጋ ሲጨምር የሩሲያ የጦርነት አቅም እንደሚጨምር ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ማዕቀቡን ማላላት የተሳሳተ እርምጃ እንደሆነ ገልጸዋል።በመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ላይ መግለጫ የሰጡት ዩናይትድ ኪንግደሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመርም የሆርሙዝ ወሽመጥን የማስከፈት ጉዳይ የኔቶ ተልዕኮ እንደማይሆን ተናግረዋል።ያጋሩ, ኔቶ በሆርሙዝ ወሽመጥ ጉዳይ ይሳተፋል ብለው እንደማያስቡ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ
  3. 16 መጋቢት 2026ዩኬ ከኢራን ጋር በተያያዘ ወደ “ሰፊ ጦርነት” ተስባ እንደማገትባ አስታወቀችየዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመርየፎቶው ባለመብት,Reutersየዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር አገራቸው ከኢራን ጋር በተያያዘ ወደ “ሠፊ ጦርነት” ተስባ እንደማትገባ፤ ነገር ግን የሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲከፈት ለማድረግ “ከአጋሮች ጋር እንደምትሠራ” ተናገሩ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ በፈጸሙት የመጀመሪያ ጥቃት ዩናይትድ ኪንግደም አለመሳተፏን አንስተው አብራርተዋል።ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቋም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትችት አስነስቶባቸው እንደነበር ይታወሳል። ኋላ ላይ ግን የአሜሪካ ሠራዊት የዩናይትድ ኪንግደምን ጦር ሠፈሮች እንዲጠቀም ተፈቅዶለታል።ስታርመር በጋዜጣዊ መግለጫው፤ የአሜሪካ ዘመቻ “ኢራን ውስጥ የሚገኘው አጸያፊ አገዛዝ’ ወታደራዊ አቅም “በከፍተኛ ሁኔታ አዳክሞታል” ብለዋል።ከጦርነቱ በኋላ ግን ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሟን መልሳ የመገንባት አቅሟን የሚገድብ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የመርከብ ጉዞን ደኅንነት የሚያስጠብቅ የሆነ ዓይነት “በድርድር የሚደረስ ስምምነት” እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።የዓለም አቀፍ “ገበያዎችን መረጋጋት ለማረጋገጥ” እንዲቻል ኢራን የዘጋችው የሆርሙዝ ወሽመጥ በድጋሚ መከፈት እንዳለበትም ገልጸዋል። ነገር ግን ይህንን ማድረግ “ቀላል ሥራ እንዳልሆነ” አክለዋል።ለዚህም ሲባል ዩናይትድ ኪንግደም በቀጣናው የባሕር ጉዞ የማድረግ ነጻነትን ለመመለስ የሚያስችል “ተጨባጭ ዕቅድ” ለማዘጋጀት “ከሁሉም አጋሮቿ ጋር” እየሠራች መሆኑን አስታውቀዋል።በዚህ ጦርነት የተነሳ የሸቀጦች ዋጋ ላይ ጭማሪ መታየቱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ስታርመር፤ በዚህ ምክንያት የመጣውን የኑሮ ውድነት የሚያበርደው ውጤታማ መንገድ ግጭቱን ማርገብ መሆኑንም አክለዋል።ያጋሩ, ዩኬ ከኢራን ጋር በተያያዘ ወደ “ሰፊ ጦርነት” ተስባ እንደማገትባ አስታወቀች
  4. 16 መጋቢት 2026የኢራን አብዮታዊ ዘብ 55 ዙር የድሮን እና የሚሳዔል ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታወቀየኢራን ሚሳዔል ሲተኮስየፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ፤ ‘ኦፕሬሽን ትሩ ፕሮሚስ 4’ በተሰኘው ዘመቻ “ቴል አቪቭ እና ቤን ጉሪኦን” አየር ማረፊያዎች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ማዕከላትን ዒላማ ያደረጉ “55 ዙር” የድሮን እና የሚሳዔል ጥቃቶችን መፈጸሙን ገለጸ።በእነዚህ ጥቃቶች ዒላማ ከተደረጉት ተቋማት መካከል “የኤሮስፔስ መሣሪያዎች ማምረቻ እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ መቅጃ የእገዛ ማዕከላት” እንደሚገኙበት አብዮታዊ ዘቡ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።በዚህ ዘመቻ “ፈታህ፣ ኤማድ፣ ቋድር ሃይፐርሶኒን ሚሳዔሎች እንዲሁም አውዳሚ ድሮኖች” ጥቅም ላይ እንደዋሉም ተነግሯል።አብዮታዊ ዘቡ አክሎም፤ “አል ድሃፍራ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር፣ ጁፍኤር ባሕር ኃይል ጦር ሰፈር እንዲሁም ሼክ ኢሳ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር” ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማትን ዒላማ ማድረጉን አስታውቋል።በጦር ሰፈሮቹ የሚገኙት የአሜሪካ ይዞታዎች ከተመቱባቸው መሣሪያዎች መካከል “ፋተህ፣ ዙልፊቃር፣ ደዝፉል የመካከለኛ ርቀት ሚሳዔል“ ተጠቅሰዋል። “ስማርት እና አውዳሚ ድሮኖችን” ጥቅም ላይ ውለዋል ተብሏል።ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዋና ከተማ አቡ ዳቢ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው አል ድሃፍራ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር፤ የኤምሬቶች አየር ኃይል የውጊያ ዕዝ እና የአሜሪካ አየር ኃይል ዋና መስሪያ ቤቶችን ይዟል።ባህሬን ውስጥ የሚገኘው ጁፍኤር የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር ደግሞ ‘ዩኤስ ፊፍዝ ፍሊት’ የተሰኘው የአሜሪካ ጦር መርከብ ማረፊያ ነው። ሼክ ኢሳ አየር ኃይል ጦር ሰፈርም ባህሬን ውስጥ የሚገኝ ወታደራዊ አየር ማረፊያ ነው።በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት የአሜሪካ እና የእስራኤል ተዋጊ ጄቶቸ በምሥራቃዊ ቴህራን በሚገኙ አካባቢዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን የኢራኑ ፋርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ 55 ዙር የድሮን እና የሚሳዔል ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታወቀ
  5. 16 መጋቢት 2026የእስራኤል ጦር የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪን የግል አውሮፕላን ማውደሙን ተናገረየቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒን ፎቶ እና የኢራን ባንዲራን የያዘ እጅየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየእስራኤል ጦር ቴህራን በሚገኘው መህራባድ አየር ማረፊያ ላይ በፈጸመው ጥቃት የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ይጠቀሙበት የነበረን አውሮፕላን ማውደሙን ተናገረ።የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በፋርስ ቋንቋ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ባወጣው መግለጫ፤ አውሮፕላኑ “በሽብርተኛው የኢራን አገዛዝ መሪ አሊ ኻሜኒ እና በሌሎች የአገዛዙ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲሁም የኢራን ጦር አባላት” ጥቅም ላይ ይውል ነበር ብሏል።ባለሥልጣናቱ “ወታደራዊ ግዢዎችን ለመፈጸም እንዲሁም በአገር ውስጥ እና የውጭ በረራዎች ከተጣማሪ አገራት ጋር የሚደረግ ግንኙነትን ለመምራት” ይጠቀሙበት እንደነበርም ገልጿል።ሰኞ ጠዋት ላይ ቴህራን ውስጥ በርካታ የአየር ጥቃቶች እንደተፈጸሙ ተገልጿል። ነዋሪዎች መህራባድ አየር ማረፊያ አቅራቢያ በርካታ ፍንዳታዎችን እንዲሁም ጥቁር ጭስ ወደላይ ሲጎን መመልከታቸውን ተናግረዋል።በርካታ ተጓዦችን በማስተናገድ ከኢራን አየር ማረፊያዎች ቀዳሚ የሆነው መህራባድ በርካታ የአየር ጥቃቶች ዒላማ ሆኗል።ያጋሩ, የእስራኤል ጦር የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪን የግል አውሮፕላን ማውደሙን ተናገረ
  6. 16 መጋቢት 2026የአውሮፓ ኅብረት ሆርሙዝን ለማስከፈት ምን ማድረግ እንደሚቻል ሊነጋገር ነውግዙፍ የጭነት መርከብየፎቶው ባለመብት,EPAየአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ጦርነት ምክንያት የተዘጋውን የሆርሙዝ ወሽመጥ ለማስከፈት ምን ማድረግ እንደሚቻል ለመነጋገር አንደሚሰበሰቡ የውጭ ፖሊሲ ኃላፊው ተናገሩ።ካያ ካላስ በብራሰልስ ከሚካሄደው የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳዮች ስብሰባ አስቀድመው “የሆርሙዝ ወሽመጥ ክፍት ሆኖ መቀጠሉ ለእኛም ጥቅም ነው” ሲሉ ተናግረዋል።በዚህ 20 በመቶ የሚሆነው የዓለም ነዳጅ በሚያልፍበት የውሃ አካል ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ለማለፍ የሞከሩ በርካታ መርከቦች ጥቃት እንደደረሰባቸው ተዘግቧል።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ አጋሮች የመተላለፊያውን ደኅንነት ለማረጋገጥ ድጋፍ ካላደረጉ “ለኔቶ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በጣም መጥፎ ይሆናል” ብለዋል።እሁድ ዕለት የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ትራምፕ ከሰር ኪር ስታርመር ጋር “በዓለም አቀፍ የመርከብ ጭነት ላይ የሚደርሰውን መስተጓጎል ለማስቆም” የሆርሙዝ ወሽመጥን እንደገና መከፈት አስፈላጊ መሆኑን መነጋገራቸውን አስታውቋል።ያጋሩ, የአውሮፓ ኅብረት ሆርሙዝን ለማስከፈት ምን ማድረግ እንደሚቻል ሊነጋገር ነው
  7. 16 መጋቢት 2026ኢራን ቀይ ባሕር ላይ የሚገኘውን የአሜሪካ ግዙፍ የጦር መርከብን ዒላማ አደርጋለሁ አለችጄራርድ አር. ፎርድ የጦር መርከብየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ጄራርድ አር. ፎርድ የጦር መርከብየኢራን ጦር በቀይ ባሕር አካባቢ የሚገኘው የአሜሪካ ግዙፉ አውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከብ ለአገሩ ስጋት በመሆኑ ተገቢ የጥቃት ዒላማ እንደሚሆን አስታወቀ።የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አንድ አካል የሆነው ኻታም አል-አንቢያ ባወጣው መግለጫ “የአሜሪካ ጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ጄራርድ ፎርድ በቀይ ባሕር መገኘቱ” ለኢራን “ስጋት” ስለሚሆን የመርከቡ የአቅርቦት እና የአገለግሎት ማዕከላት በሙሉ “የኢራን ጦር ኃይሎች ዒላማ” ተደርገው ይቆጠራሉ ብሏል።ሦስት መቶ ሜትር ርዝመት ያለው ይህ ጄራርድ አር. ፎርድ የተባለው የጦር ጄቶች ተሸካሚ የጦር መርከብ በዓለም ላይ ትልቁ የጦር መርከብ ነው።በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ ጦር ሠራዊት ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) ባለፈው ሐሙስ በዚህ የጦር መርከብ አንድ ክፍል ላይ እሳት ተነስቶ እንደነበር አስታውቋል።ነገር ግን እሳቱ በቁጥጥር ስር እንደዋለ እና “በመርከቧ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ላይ መስተጓጎል የሚያስከትል ጉዳት እንዳልደረሰ እና ሙሉ ለሙሉ ሥራውን እያከናወነ” መሆኑን ገልጿል።ማዕከላዊ ዕዙ ጨምሮም በመርከቡ ላይ የተነሳው እሳት “ከጦርነት ጋር በተያያዘ አይደለም” ሲሉ በወታደራዊ እንቅስቃሴ ምክንያት እንዳልሆነ አመልክቷል።የጦር አውሮፕላን ተሸካሚው ዩኤስኤስ ጄራርድ አር. ፎርድ በቬንዙዌላ ከተፈጸውን የአሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ በኋላ በኢራን ላይ የተከፈተው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እንዲንቀሳቀስ ተደርጎ ነው በቀይ ባሕር ላይ የሚገኘው።አሜሪካ ቢሊዮኖችን ስላፈፈሰሰችበት ጄራርድ አር ፎርድ የጦር መርከብ ምን ይታወቃል?ያጋሩ, ኢራን ቀይ ባሕር ላይ የሚገኘውን የአሜሪካ ግዙፍ የጦር መርከብን ዒላማ አደርጋለሁ አለች
  8. 16 መጋቢት 2026የድሮን ጥቃት በዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ00:17ሌሊቱን በዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ምክንያት በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረው በረራ መልሶ እንደሚጀመር ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።በረራዎች እንዲቋረጡ የተደረገው በተፈጸመው ጥቃት ምክንያት በነዳጅ ማጠራቀሚያ ላይ በተነሳ እሳት መሆኑን እና በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱ ተዘግቧል።የዱባይ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ለጥንቃቄ ሲባል ተቋርጦ የነበረውን የአየር ትራንስፖርት “ከዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደተወሰኑ መዳረሻዎች የሚደረጉ በረራዎች ቀስ በቀስ መልሰው እንደሚጀምሩ” አስታውቋል።መንገደኞችም ስለበረራዎቻቸው መረጃዎችን ከሚጠቀሟቸው አየር መንገዶች እንዲያጣሩ ተነግሯቸዋል።ያጋሩ, የድሮን ጥቃት በዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ
  9. 16 መጋቢት 2026ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ “ነዳጅን በቁጠባ እና ለመሠረታዊ ነገሮች” እንዲውል አሳሰቡጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድየፎቶው ባለመብት,Abiy Ahimedጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመካከለኛው ምሥራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት አስራ ስድስተኛ ቀኑን በያዘበት በዛሬው ዕለት “ነዳጅን በቁጠባ” መጠቀም እንደሚያስፈልግ አሳሰቡ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የማኅበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት አጭር መልዕክት ነዳጅን ገዝተው የሚጠቀሙ አገራት መቸገራቸውን ገልጸው፤ “በቁጠባ እና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም” አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።ባለፈው ሳምንቱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተፈጠረው የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ስለማይታወቅ ሕብረተሰቡ እና ተቋማት ነዳጅን “በከፍተኛ ቁጠባ” እንዲጠቀሙ አሳስበው ነበር።በጦርነቱ ምክንያት የታየውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ “አስፈሪ” ሲሉ የገለጹት የገንዘብ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት “በቅርቡ ተጨማሪ የነዳጅ ቁጠባ እርምጃዎችን” ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ የነዳጅ አከፋፋዮችም ሆኑ ተጠቃሚዎች እንዲሁም ማደያዎች ለመሠረታዊ አገልግሎት ቅድሚያ እንዲሠጡ እና በቁጠባ እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።የፋርስ ባሕረ ሰላጤ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ የዓለም 20 በመቶ ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ የተነሳ በተጨማሪም በጦርነቱ የኢራን እና የሌሎች የመካለኛው ምሥራቅ አገራት የነዳጅ መሠረተ ልማቶች ጥቃት ስለተፈጸመባቸው የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።በዚህም ምክንያት የነዳጅ ዋጋ ከአውሮፓውያኑ 2022 ወዲህ ከፍተኛ ጭማሪ በማሳየት በበርሜል 120 ዶላር ገብቶ ነበር።ይህንንም ተከትሎ የዓለም አቀፉ ኢነርጂ ኤጀንሲ ከፍተኛ መጠን ያለውን ነዳጅ ከክምችቱ በማውጣት ለእስያ እንዲሁም ኦሺኒያ አገራት በዛሬው ዕለት እንደሚያከፋፍል ይፋ አድርጓል።የዓለም አንድ አምስተኛ የነዳጅ አቅርቦት የሚተላለፍበት የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ መዘጋትን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ መጨመሩን ዛሬም እንደቀጠለ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።እሁድ ዕለት በዓለም አቀፍ ገበያ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ እስከ 3 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በበርሚል 106 ዶላር ተሸጧል።በዛሬው ዕለት ደግሞ ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል 104.63 እየተሸጠ ነው።ማኅበረሰቡ እና ተቋማት ነዳጅን “በከፍተኛ ቁጠባ” እንዲጠቀሙ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሳሰቡያጋሩ, ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ “ነዳጅን በቁጠባ እና ለመሠረታዊ ነገሮች” እንዲውል አሳሰቡ
  10. 16 መጋቢት 2026እስራኤል “ለውስን ዘመቻ” ወታደሮቿን ወደ ሊባኖስ ማስገባቷን አስታወቀችየእስራኤል የመከላከያ ኃይል ወደ ሊባኖስ በመግባት “ቁልፍ የሔዝቦላህ ይዞታዎችን ዒላማ ያደረጉ ውስን ዘመቻዎችን” ማካሄድ መጀመሩን በቴሌግራም ገጹ ላይ አስታውቋል።ሠራዊቱ ወታደሮቹ ወደ ደቡባዊ የሊባኖስ አካባቢዎች ከመግባታች ቀደም ብሎ “በበርካታ የሽብርተኞች ዒላማዎች” ላይ ድብደባ መፈጸሙን እና ዘመቻው “የፊት መስመር የመከላከያ ይዞታን” በማጠናከር ዓላማው በአካባቢው ያሉትን “የሽብርተኞች መሠረተ ልማቶችን ማፈራረስ ነው” ብሏል።የእስራኤል ጦር ጨምሮም ሊባኖስ ውስጥ በሔዝቦላህ ላይ የሚያካሂደውን “ዘመቻ በቁርጠኝነት” እንደሚቀጥል አስታውቋል።ያጋሩ, እስራኤል “ለውስን ዘመቻ” ወታደሮቿን ወደ ሊባኖስ ማስገባቷን አስታወቀች
  11. 16 መጋቢት 2026የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ያሳሰባቸው ትራምፕ ኔቶ እና ሌሎች አገራት እንዲደግፏቸው ጥሪ አቀረቡየቆሙ መርከቦች እና የተቀመጡ ሰዎችየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በሆርሙዝ መዘጋት ምክንያት የመርከቦች እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏልከፋርስ ባሕረ ሰላጤ አገራት የሚወጣው ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ የሚተላለፍበትን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመጠበቅ ኔቶ እና ሌሎች አገራት እንዲተባበሩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥረት እያደረጉ ነው።ግዙፍ መርከቦችን ከኢራን ጥቃት ለመጠበቅ የአገራት ጥምረት ለመፍጠር የአሜሪካ መንግሥት ከሰባት አገራት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን የጠቀሱት ትራምፕ ከእነዚህም መካከል ቻይና እንደምትገኝበት ገልጸዋል።ትራምፕ የሌሎች አገራትን ስም ባይጠቅሱም የኔቶ አባል አገራት “ግዛታቸውን ይከላከላሉ” ብለው እንደሚያምኑ እና አሁን በሆርሙዝ ወሽመጥ የተከሰተው ሁኔታን እንደ ግዛታቸው መመልከት ያለባቸው አገራቱ “ነዳጅ የሚያገኙበት” አካባቢ በመሆኑ እንደሆነ አብራርተዋል።ፕሬዝዳንቱ ከፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ደግሞ ወሳኙን የሆርሙዝ ወሽመጥ ለመጠበቅ አጋሮቻቸው ድጋፍ የማያደርጉ ከሆነ “የኔቶ የወደፊት ዕጣ በጣም መጥፎ ይሆናል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።በተጨማሪም ቻይና ተሳታፊ እንደምትሆን እንደሚጠብቁ፤ ነገር ግን ድጋፍ የማታደርግ ከሆነ ግን በምላሹ ከፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ካር በቅርቡ ሊካሄድ የታቀደውን ስብሰባ ሊያዘገዩት እንደሚችሉ ገልጸዋል።ትራምፕ የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ዩናይትድ ኪንግደም የምትሳተፍበት ሁኔታ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ጋር መነጋገራቸው ተዘግቧል።ጃፓን በበኩሏ የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመጠበቅ ወደ ፋርስ ባሕረ ሰላጤ ወታደራዊ መርከቦቿን በመላክ የመሳተፍ “ፍላጎት እንደሌላት” የገለጸች ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሯ በዚህ ሳምንት ወደ አሜሪካ በመሄድ ከትራምፕ ጋር እንደሚነጋገሩ ተገልጿል።በተመሳሳይም አውስትራሊያ ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በጭነት መርከቦች ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ለመከላከል የጦር መርከቦቿን ወደ አካባቢው እንደማታሰማራ በትራንስፖርት ሚኒስትሯ በኩል አሳውቃለች።አዲሱ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ ከተሾሙ በኋላ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ኢራናውያንን ደግሞ ሆርሙዝን በመዝጋት እንደሚበቀሉ አመልክተው ነበር።የዓለም 20 በመቶ የነዳጅ ምርት የሚተላለፍበት ሆርሙዝ ወሽመጥ በጦርነቱ ምክንያት በተፈጠረ ስጋት በዓለም ገበያ ላይ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚተላለፉ የመርከቦች ቁጥር ከጦርነቱ በፊት ከነበረው የ90 በመቶ ቅናሽ ማሳያቱን የቢቢሲ ቬሪፋይ ዘገባ አመለክቷል።ከጦርነቱ መጀመር በኋላ አስካሁን ቢያንስ 19 ከባድ መርከቦች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ወድመዋል ወይም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።በአካባቢው በተፈጠረው ስጋት ምክንያትም 20 ሺህ የሚጠጉ መርከበኞችን እና የመርከብ ሠራተኞችን የያዙ ግዙፍ መርከቦች ለመንቀሳቀስ ተቸግረው ውቅያኖስ ላይ ቆመው የሚገኙ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት የምግብ እና የውሃ እጥረት እያጋጠማቸው ነው።ያጋሩ, የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ያሳሰባቸው ትራምፕ ኔቶ እና ሌሎች አገራት እንዲደግፏቸው ጥሪ አቀረቡ
  12. 16 መጋቢት 2026የባሕረ ሰላጤው አገራት ሌሊቱን ከኢራን ተጨማሪ ጥቃቶች እንደተፈጸሙባቸው አስታወቁየዱባይ አውሮፕላን ማረፊያየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የዱባይ አውሮፕላን ማረፊያየባሕረ ሰላጤው አገራት ከኢራን በኩል ሌሊቱን ተጨማሪ ጥቃቶች እንደተፈጸመባቸው አሳወቁ።የዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጥቃት ከተሰነዘረባቸው መካከል አንዱ ነው። በአውሮፕላን ማረፊያው ላይ በደረሰ የድሮን ጥቃት እሳት ተያይዞ የነበረ ሲሆን፣ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነግሯል።ኢራን ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ 2 ሺህ የሚጠጉ ሚሳዔሎችን እና ድሮኖችን ተኩሳለች። የኤምሬትስ የመከላከያ ሥርዓት አብዛኞቹን ሚሳዔሎች እና ድሮኖች አምክኗል።ሳዑዲ አረቢያም ሌሊቱን በርከት ያሉ የኢራን ድሮኖችን መምታቷን አስታውቃለች። በተመሳሳይ ኢራቅ እና ኩዌትም ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋል።እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት የቀጠሉ ሲሆን፣ በመዲናዋ ቴህራን ከባድ ድብደባ እንደነበር ተገልጿል።በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ከፍተኛ ፍንዳታ ያስከተለ ጥቃት ተፈጽሟል። እስራኤል ጥቃቱን የፈጸመችው የሄዝቦላህን መሠረተ ልማት ለማውደም መሆኑን ገልጻለች።በእስራኤል ከሰሜን የሄዝቦላህ ከደቡብ ደግሞ የኢራን ሚሳዔሎች ይመጣሉ በሚል የአደጋ ጊዜ ደወል መጮሁ ተነግሯል።ያጋሩ, የባሕረ ሰላጤው አገራት ሌሊቱን ከኢራን ተጨማሪ ጥቃቶች እንደተፈጸሙባቸው አስታወቁ
  13. 16 መጋቢት 2026አሜሪካ “ኢራን ድርድር ትፈልጋለች”፤ ኢራን “ፈጽሞ አልጠየቅንም”የአሜሪካ እና የኢራን ባለሥልጣናት እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማስቆም በሁለቱ ወገኖች መካከል ሊደረግ ስለሚችለው ድርድር የሚቃረን አስተያየት እየሰጡ ነው።ሌሊት ላይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን ከአሜሪካ ጋር መደራደር አጥብቃ እንደምትፈልግ እና ዝግጁ መሆኗን በድጋሚ ተናግረዋል። ዲፕሎማሲያዊ ንግግርን በተመለከተም “እየተነጋገርን ቢሆንም እነሱ ግን ዝግጁ የሆኑ አይመስለኝም፣ ነገር ግን ወደዚያው እየቀረቡ ነው” ሲሉ ያለውን ሁኔታ ገልጸዋል።የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ዋነኛ ተደራዳሪ አባስ አራግቺ ግን የትራምፕን ንግግር ተቃርነዋል። ሚኒስትሩ አገራቸው “የተኩስ አቁም እንዲደረግ ፈጽሞ አልጠየቀችም፣ ለመደራደር እንኳን ፈጽሞ አልጠየቅንም” በማለት በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ለሆነው ሲቢኤስ ኒውስ ተናግረዋል።እየተካሄደ ባለው ጦርነት በኢራን ላይ ድል መቀዳጀታቸውን ለማወጅ እየተዘጋጁ እንደሆነ የተጠየቁት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ ያንን እንደማያደርጉ ነገር ግን አስካሁን ባለው ሁኔታ አሜሪካ በኢራን ላይ ከባድ ውድመት ማድረሷን እና “አሁን ብንተዋቸው እንኳን መልሰው ለመገንባት 10 ዓመት ይፈጅባቸዋል” ብለዋል።ትራምፕ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ባለፈው ሳምንት በቴህራን ውስጥ አዲሱን ጠቅላይ መሪ በመደገፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ መውጣታቸውን እንዲሁም ኢራን በአሜሪካ የጦር መርከብ አብርሃም ሊንከን ላይ ፈጸመችው ስለተባለው “የአጥፍቶ ጠፊ ጀልባ” ጥቃት ተጠይቀው ሁሉም በሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የተፈበረኩ ምሥሎች ናቸው ብለው ቢያጣጥሉም ማስረጃ ግን አልሰጡም።ያጋሩ, አሜሪካ “ኢራን ድርድር ትፈልጋለች”፤ ኢራን “ፈጽሞ አልጠየቅንም”
  14. 16 መጋቢት 202616ኛ ቀኑን በያዘው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ምን እየሆነ ነው?በቴህራን ቤርያናክ አካባቢ የሚገኝ መኖሪያ ቤት እሁድ ዕለት በሚሳዔል ጥቃት ከወደመ በኋላየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በቴህራን ቤርያናክ አካባቢ የሚገኝ መኖሪያ ቤት እሁድ ዕለት በሚሳዔል ጥቃት ከወደመ በኋላአሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱን ሊያስቆም ይችላል በሚባል ድርድር ዙሪያ እርስ በእርሱ የሚጣረስ መረጃ እየሰጡ ነው። ዛሬ አስራ ስድስተኛ ቀኑን በያዘው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ሰላም በቅርብ የሚመጣ አይመስልም። ሌሊቱን የተከናወኑ ዋናዋና ነገሮች እነሆ፡
    • የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ኢራን ለድርድር ዝግጁ ናት ሲሉ የሰጡትን አስተያየት ውድቅ አድርገዋል። ቴህራን “የተኩስ አቁም በጭራሽ አልጠየቀችም፤ ድርድር እንኳ አልጠየቅንም” ሲሉ የቢቢሲ አጋር ለሆነው ሲቢኤስ ተናግረዋል።
    • ኢራናውያን አገራቸው ወደ ፍርስራሽ ክምርነት ትቀየራለች ሲሉ ያላቸውን ስጋት ለቢቢሲ ተናግረዋል። እስራኤል በቴህራን የምትፈጽመውን ጥቃት አስፈታ የቀጠለች ሲሆን፣ በዋና ከተማዋ የተከመረው ፍርስራሽ መንገዶችን ለመጠቀም አስቸጋሪ ማድረጉ ተገልጿል። በኢራን የኢንተርኔት አገልግሎት አሁንም የተቋረጠ ሲሆን፣ ቁልፍ የቴሌኮሚዩኒኬሽን መስመር ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
    • በእስራኤል የአገሪቱ የአደጋ ጊዜ አገልግሎት በኢራን ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 15 መድረሱን ገለጿል። በቴል አቪቭ ክላስተር ቦምብ ጉዳት አድርሷል። የእስራኤል ጦር በኢራን የሚፈጽመውን ጥቃት እያሰፋ መሆኑን በመግለጽ አሁንም “በሺህዎች የሚቆጠሩ” ዒላማዎች እንደሚቀሩት ተናግሯል።
    • በሊባኖስ በእስራኤል ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 850 መድረሱን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የእስራኤል መከላከያ ኃይል በደቡባዊ ቤይሩት ድብደባ ከመፈጸሙ በፊት ከአካባቢው ነዋሪዎች ለቅቀው እንዲወጡ አስጠንቅቋል። የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር ሊኖር የሚችልን የሰላም ንግግር ውድቅ አድርገዋል።
    • ዶናልድ ትራምፕ እና የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር የሆርሙዝን ወሽመጥ ዳግም ስለማስከፈት በስልክ ተወያይተዋል። ሰኞ ዕለት የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የካናዳው አቻቸው ተገናኝተው በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ዙሪያ ይነጋገራሉ ተብሏል።
    • ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ በእስያ እና ኦሺኒያ ከአስቸኳይ ጊዜ ክምችት ነዳጅ በፍጥነት እንደሚለቀቅ ይፋ አድርጓል። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን በሆርሙዝ ወሽመጥ ዙሪያ ከአገራት ጋር በተናጠል ለመነጋገር መንግሥታቸው “ክፍት” መሆኑን ተናግረዋል።
    ያጋሩ, 16ኛ ቀኑን በያዘው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ምን እየሆነ ነው?
  15. 16 መጋቢት 2026አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ልጃቸው ሥልጣን በመረከባቸው ላይ ስጋት እንደነበራቸው ተነገረአያቶላህ ሞጅታባ ኻሜኒየፎቶው ባለመብት,Tasnim News Agencyየኢራን የቀድሞ የጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ልጃቸው እርሳቸውን ስለመተካታቸው ጥርጣሬ እንደነበራቸው የአሜሪካ ደኅንነት መረጃ እንደነበረው ምንጮች ለቢቢሲ የአሜሪካ የሚዲያ አጋር ሲቢኤስ ኒውስ ተናገሩ።መረጃው ኻሜኒ ልጃቸው ሞጅታባ ኻሜኒ “ብቃት እንደሌለው” እና ለመሪነት “ብሩህ አይደለም” ተብሎ ስለሚታሰብ ሥልጣን መረከቡ ላይ ስጋት ነበራቸው ተብሏል።በተጨማሪም ሟቹ የበላይ መሪ ልጃቸው “በግል ሕይወቱ ውስጥ ችግሮች እንዳሉበት” እንደሚያውቁ ተጠቅሷል።ሲቢኤስ እንደዘገበው መረጃው አስቀድሞ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና “በዙሪያቸው ላሉ ጥቂት ሰዎች” ደርሷል።የ56 ዓመቱ አያቶላህ ሞጅታባ ኻሜኒ ከአንድ ሳምንት በፊት የኢራን የበላይ መሪ እንዲሆኑ መመረጣቸው ይታወሳል።ያጋሩ, አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ልጃቸው ሥልጣን በመረከባቸው ላይ ስጋት እንደነበራቸው ተነገረ
  16. 16 መጋቢት 2026እስራኤል በኢራን በሺህዎች የሚቆጠሩ ዒላማዎች እንደሚቀሯት ስትናገር ትራምፕ ከስታርመር ጋር ስለ ሆርሙዝ መከሩየእስራኤል ጦር በኢራን ውስጥ “በሺህዎች” የሚቆጠሩ ዒላማዎችን ገና መደብደብ እንደሚቀረው የአገሪቱ ጦር ቃል አቀባይ ኤፊ ደርፊን ተናገሩ።ቃል አቀባዩ በቴሌቪዥን በተላለፈው መግለጫቸው ላይ “በየዕለቱ አዳዲስ ዒላማዎችነ እየለየን ነው” ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።ሮይተርስ አክሎም የእስራኤል ጦር “ኢራን እና ሔዝቦላህ ላይ የሚፈጽማቸውን ጥቃቶች ስጋቱ እስኪወገድ እና የዘመቻው ዓላማዎች እስኪሳኩ ድረስ ይቀጥላል” ማለታቸውን ዘገቧል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመካለኛው ምሥራቅ ስላለው ሁኔታ እና የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥን ማስከፈት አሰፈላጊነት ላይ መወያየታቸውን የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።ሁለቱ መሪዎች ያደረጉት የስልክ ውይይት ለ15 ደቂቃ የዘለቀ ነው የተባለ ሲሆን፣ ከሆርሙዝ ወሽመጥ በተጨማሪ ስታርመር “በጦርነቱ ሕይወታቸውን ላጡ አሜሪካውያን ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል” ተብሏል።የካናዳው ጠቅላይ ሚኒሲትር ካርኒ እንዲሁ ከስታርመር ጋር “እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዙሪያ “ለመነጋገር መስማማታቸው ተገልጿል።ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,EPAያጋሩ, እስራኤል በኢራን በሺህዎች የሚቆጠሩ ዒላማዎች እንደሚቀሯት ስትናገር ትራምፕ ከስታርመር ጋር ስለ ሆርሙዝ መከሩ