
የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የፀረ ሽብርተኝነት ማዕከል ዳይሬክተር “በኢራን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በበጎ ህሊና መደገፍ አልችልም” በማለት ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባጋሩት መልዕክት አስታወቁ።
ጭምቅ ሃሳብ
- ኢራን ቀይ ባሕር ላይ የሚገኘውን የአሜሪካ ግዙፍ የጦር መርከብን ዒላማ አደርጋለሁ አለች
- ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ “ነዳጅን በቁጠባና እና ለመሠረታዊ ነገሮች” እንዲውል አሳሰቡ
- የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ያሳሰባቸው ትራምፕ ኔቶ እና ሌሎች አገራት እንዲደግፏቸው ጥሪ አቀረቡ
- እስራኤል በኢራን በሺህዎች የሚቆጠሩ ዒላማዎች እንደሚቀሯት ተናገረች
- አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ልጃቸው ሥልጣን በመረከባቸው ላይ ስጋት እንደነበራቸው ተነገረ
- 16ኛ ቀኑን በያዘው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ምን እየሆነ ነው?
- አሜሪካ “ኢራን ድርድር ትፈልጋለች”፤ ኢራን “ፈጽሞ አልጠየቅንም”
- የባሕረ ሰላጤው አገራት ሌሊቱን ከኢራን ተጨማሪ ጥቃቶች እንደተፈጸሙባቸው አስታወቁ
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 3 ሰአት በፊትየአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን በኢራን የሚካሄደውን ጦርነት ተቃውመው ሥልጣን ለቀቁ
የፎቶው ባለመብት,Bloomberg via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ጆ ኬንትየዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የፀረ ሽብርተኝነት ማዕከል ዳይሬክተር “በኢራን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በበጎ ህሊና መደገፍ አልችልም” በማለት ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባጋሩት መልዕክት አስታወቁ።ጆ ኬንት ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ባሳወቁበት ደብዳቤ “ኢራን በአገራችን ላይ ምንም ዓይነት ተጨባጭ ስጋት አልደቀነችም፣ ይህንን ጦርነት የጀመርነው በእስራኤል እና በአሜሪካ ባሏት ኃያል ደጋፊዎቿ ግፊት መሆኑ ግልጽ ነው” ብለዋል።ዶናልድ ትራምፕ ሦስት ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ይዘው የተነሷቸውን ፖሊዎች ደግፈው ከጎናቸው እንደቆሙ ያስታወሱት ጆ፣ አስከ 2025 በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ የተካሄዱት ጦርነቶች የአሜሪካውያንን ሕይወት የቀጠፉ እና የአገሪቱን ሃብት ያሟጠጡ መሆናቸውን ትራምፕ ይረዱ እንደነበር ሲሉ አስታውሰዋል።“በ11 ውጊያዎች ላይ እንደተሳተፈ የቀድሞ ወታደር እና በእስራኤል በተፈበረከ ጦርነት ውድ ሚስቱን እንዳጣ ባል፣ ቀጣዩ ትውልድ ለአሜሪካ ጥቅም በማያስገኝ እና የሚከፈለው ዋጋ አሳማኝ ወዳልሆነ ጦርነት መሄዱን መደገፍ አልችልም” በማለት ጦርነቱን ተቃውመዋል።አሁን ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው የለቀቁት ጆ ኬንት በትራምፕ ተመርጠው በአሜሪካ ሴኔት ለቦታው ብቁ ናቸው ተብለው ተቀባይነት ያገኙት ባለፈው ዓመት ሐምሌ ነበር። የኢራንን ጦርነት ተቃውመው ሥልጣን የለቀቁት የአሜሪካው ከፍተኛ ባለሥልጣን ማን ናቸው?ያጋሩ, የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን በኢራን የሚካሄደውን ጦርነት ተቃውመው ሥልጣን ለቀቁ - ከ 6 ሰአት በፊትበሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ አውሮፓውያን ፊታቸውን ያዞሩባቸው ትራምፕ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዝዳንት ትራምፕ በፋርስ ባሕረ ሰላጤው የሆርሙዝ ሰርጥ የሚተላለፉ ግዙፍ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ለመጠበቅ አጋሮቻቸው እንዲተባበሩ ያቀረቡት ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ ባለማግኘቱ ተቆጥተዋል።ምዕራባውያን ወዳጆቻቸው ይህ የትራምፕ ጥሪ አሜሪካ ከእስራኤል ጋር በመሆን በኢራን ላይ ወደ ከፈተችው ጦርነት የሚያስገባቸው ሊሆን እንደሚችል በማሰብ የባሕር ኃይላቸውን ወደ ጦርነት ቀጣናው ለመላክ አልፈቀዱም።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጦርነት ተከትሎ ከፍተኛ የነዳጅ ምርት የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ሰርጥ በመዘጋቱ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል በአገራት ምጣኔ ሀብት ላይም ተጽእኖው እየተንጸባረቀ ነው።የአሜሪካ የቅርብ አጋሮች የሆኑት ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ እና ጀርመንን ጨምሮ ግሪክ፣ አውስትራሊያ፣ ስፔን፣ ጃፓን እና ሌሎችም በሆርሙዝ ሰርጥ የሚተላለፉ መርከቦችን ደኅንነት ለመጠበቅ በሚል ትራምፕ ባዘጋጁት ዕቅድ ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው በመግለጽ መልስ ሰጥተዋል።በአውሮፓ ታላላቅ ወታደራዊ ኃይል ያላቸው አገራቱ ምንም እንኳን የነዳጅ እንቅስቃሴው መስተጓጎል ቢጎዳቸውም በዚህ ምክንያት ግን ከኢራን ጋር ወደ ቀጥታ ግጭት የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው አሳውቀዋል። ይህም ሦስት ሳምንት ያስቆጠረው ጦርነት የአሜሪካ እና የእስራኤል ጉዳይ መሆኑን በተዘዋዋሪ መልዕክት ያስተላለፉበት ነው።የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር አገራቸው ሆርሙዝን በመጠበቅ ሰበብ ወደ ጦርነት ተስባ እንደማትገባ ሲጠቅሱ፣ የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ደግሞ ትራምፕ አጋሮቻቸው ካልተባበሯቸው ለኔቶ መጥፎ ሁኔታ ይፈጠራል በማለት ለሰጡት ማስጠንቀቂያ “ኔቶ የመከላከያ ስምምነት እንጂ የጣልቃ ገብነት ትብብር አይደለም” ሲሉ መከላከያ ሚኒስትራቸው ደግሞ “የእኛ ጦርነቱ አይደለም፤ እኛም አልጀመርነውም” በማለት እራሳቸውን አርቀዋል።ነገር ግን ትራምፕ ሰኞ ዕለት እንደተናገሩት “በርካታ አገራት” ጥሪያቸውን ተቀብለው ከጎናቸው እንደሚቆሙ እንደገለጹላቸው ጠቁመው፤ አሜሪካ ስትከላከላቸው የቀዩ አገራት ለቀረበላቸው ጥሪ ምላሽ ካልሰጡ “ምስጋና ቢስነት ነው” ብለዋል።አሜሪካ ሆርሙዝ ሰርጥን በመጠበቅ ከጎኔ ይቆማሉ ብላ የምትጠብቃቸው የአውሮፓ ባለሥልጣናት የኔቶ አባል አገራት ትብብር እራስን የመከላከል ዓላማ መሆኑን አጽንኦት እየሰጡ ነው።ኢራንን እና የኒውክሌር ፕሮግራሟን ዒላማ ማድረግ ግን አሜሪካ እና እስራኤል “በምርጫ የገቡበት ጦርነት ነው” በማለት አገራት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት መግባት እንደማይፈልጉ ግልጽ አድርገዋል።በኔቶ በኩል ዩክሬንን ከሩሲያ ጋር በምታደርገው ጦርነት እየደገፏት የሚገኙት የአውሮፓ አገራት በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረውን የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ለመሸፈን በሩሲያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ትራምፕ በማንሳታቸው ቅሬታቸውን ገልጸዋል።ያጋሩ, በሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ አውሮፓውያን ፊታቸውን ያዞሩባቸው ትራምፕ - ከ 7 ሰአት በፊትእስራኤል የኢራን መሪዎችን “ማደን እቀጥላለሁ” አለች
የፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝየእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ በሰጡት መግለጫ የአገሪቱ ጦር ኢራን መሪዎችን ማደኑን እንዲቀጥል ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትያናሁ ትዕዛዝ መሰጠቱን ተናገሩ።እስራኤል ሰኞ ሌሊት በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ከፍተኛ የኢራን የደኅንነት ኃላፊ የሆኑትን አሊ ላሪጃኒን መግደሏን ገልጻለች። ባለሥልጣኑ የተገደሉት ከልጃቸው ጋር በተደበቁበት አፓርትመንት ውስጥ እንደሆነ የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።በተጨማሪም የእስራኤል ጦር ‘ባሲጅ’ የተባለው የኢራን ታጣቂ ኃይል አዛዥ የሆኑትን ጎላምሬዛ ሶሊማኑን መግደሏን አስታውቃለች። የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያለውን ታጣቂ ቡድን ላለፉት ስድስት ዓመታት ሲመሩ ቆዩትን ወታደራዊ አዛዥ ተገድለዋል ብሏል።አዛዡ የሚመሩት ታጣቂ ቡድን ታኅሣሥ ላይ የነበረውን ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ለማፈን በተወሰደው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበት ዘመቻ ውስጥ ተሳትፎ ነበረው።የመከላከያ ሚኒስትሩ ካትዝ፤ የኢራኑ ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣን መገደላቸውን ባስታወቁበት መግለጫ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና እኔ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የኢራንን የሽብር እና የጭቆና አገዛዝ አመራሮች ማደኑን እንዲቀጥል ትዕዛዝ ሰጥተናል” ብለዋል።“የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን አመራሮች በከፍተኛ መጠን ስለ መለዋወጣቸውን ሲናገሩ ነበር … ከቀሩት ከፍተኛ አመራሮች መካከል ሁለቱ ስለተገደሉ የአመራሮች መለዋወጡ እንደቀጠለ መረጃ እናደርሳቸዋለን” ሲሉ ተናግረዋል።እስራኤል ይሄንን ብትልም እስካሁን ድረስ ላሪጃኒ እና ሶሎማኒ ስለመገደላቸው ከኢራን በኩል ማረጋገጫ አልተሰጠም።የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ቢገደሉም መንግሥቱ ባለበት እንዲቀጥል እንዴት ቻለ የሚለውን ለመረዳር ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ ➤ ኢራን መሪዎቿን ባጣች ጊዜ እንዴት ሳትንኮታኮት ጸንታ መቀጠል ቻለች?ያጋሩ, እስራኤል የኢራን መሪዎችን “ማደን እቀጥላለሁ” አለች - ከ 8 ሰአት በፊትየባሕረ ሰላጤው አገራት የኢራን የመሣሪያ አቅም ሳይዳከም አሜሪካ ጥቃቷን እንዳታቆም እየገፉ ነው ተባለ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየመካከለኛው ምሥራቅ አረብ አገራት፤ አሜሪካ በባሕረ ሰላጤው የነዳጅ መተላlፊያ መስመር እና በዚሁ ላይ በተመሠረተው ኢኮኖሚ ላይ አደጋ የደቀነችው ኢራን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት እንዳታቋርጥ እየወተወቱ መሆኑ ተዘገበ።የዜና ወኪሉ ሮይተርስ የባሕረ ሰላጤውን እና ምዕራባውያን ምንጮችን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ እንዳመለከተው አሜሪካ የቀጣናው አገራት ጦርነቱን እንዲቀላቀሉ ግፊት ስታደርግ ነበር።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ለማግኘት እና በአገር ውስጥ ያላቸውን ድጋፍ ለማጠናከር ሲሉ የቀጣናው አገራት ዘመቻውን እንዲደግፉ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ሦስት ምንጮች ተናግረዋል ተብሏል።የባሕረ ሰላጤው አረብ አገራት መጀመሪያ ላይ አሜሪካ ከኢራን ጋር ጦርነት ውስጥ እንድትገባ ጥያቄ ባያቀርቡም በቴህራን ከደረሰባቸው ጥቃት በኋላ ዋሽንግተን ወደ ኋላ እንዳትል ግፊት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።ኢራን በፈጸመቻቸው ጥቃቶች በስድስት የቀጣናው አገራት ውስጥ የሚገኙ አየር ማረፊያዎች፣ ወደቦች፣ የነዳጅ መሠረተ ልማቶች እንዲሁም የንግድ ማዕከላት ተመትተዋል። በአገራቱ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች እና ኤምባሲዎችም የጥቃት ዒላማ ሆነዋል።ኢራን በእነዚህ ጥቃት አቅሟ ምን ያህል እንደሆነ አሳይታለች። የባሕረ ሰላጤው አገራት በአንጻሩ ኢራን ከፍተኛ የጦር መሣሪያ የማምረት አቅሟን ይዛ ከቀጠለች ውጥረት በተነሳ ቁጥር የቀጣናውን የኢነርጂ መስመር አደጋ ላይ ትጥላለች የሚል ስጋት እንደገባቸው የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል።ያጋሩ, የባሕረ ሰላጤው አገራት የኢራን የመሣሪያ አቅም ሳይዳከም አሜሪካ ጥቃቷን እንዳታቆም እየገፉ ነው ተባለ - ከ 8 ሰአት በፊትእስራኤል የኢራን ቁልፍ የደኅንነት ባለሥልጣን የሆኑት አሊ ላሪጃኒን መግደሏን ተናገረች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አሊ ላሪጃኒ በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ አስታወቁ።ሌሊቱን በተፈጸመ ጥቃት መገደላቸው የተነገረው ላሪጃኒ በኢራን መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት ከነበራቸው መሪዎች መካከል አንዱ ናቸው።የባለሥልጣኑ በእስራኤል ዒላማ መሆን እየተነገረ በነበረበት ጊዜ ቢያንስ ሁለት የኢራን መገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣናትን ጠቅሰው ግለሰቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ መግለጫ ይሰጣሉ ብለው ነበር።አንድ የእስራኤል ወታደራዊ ባለሥልጣን አሊ ላሪጃኒ በእስራኤል መከላከያ ዒላማ መደረጋቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።አሊ ላሪጃኒ በኢራን ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት የሟቹ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ተወካይ እና ዋና ፀሐፊ ሆነው የተሾሙት ባለፈው ዓመት ነሐሴ በፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ነበር።ለ12 ዓመታት የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ የነበሩት ላሪጃኒ “ለዘብተኛ ወግ አጥባቂ” እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፤ በተጨማሪም በኢራን መገናኛ ብዙኃን የጠቅላይ መሪው አማካሪ እንደሆኑ ይጠቀሱ ነበር።እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት መገደላቸው የተነገረው ታዋቂው ኢራናዊ ፖለቲከኛ የፓርላማው አፈ ጉባዔ ከመሆናቸው በፊት ኢራንን ከምዕራባውያን ጋር እያወዛገበ በሚገኘው የኒውክሌር ድርድር ላይ አገራቸውን ወክለው ተደራዳሪ ነበሩ።በኢራን ፖለቲካ ውስጥ አሊ ላሪጃኒ ብቻ ሳይሆኑ ወንድማቸውም ከፍተኛ ተሰሚነት አላቸው። ወንድማቸው ሴዴጌ ላሪጃኒ በኢራን ሁለት ኃያል ምክር ቤቶች የበላይ አካል የሆነው ጉባዔ ሊቀ መንበር ናቸው።ያጋሩ, እስራኤል የኢራን ቁልፍ የደኅንነት ባለሥልጣን የሆኑት አሊ ላሪጃኒን መግደሏን ተናገረች - ከ 9 ሰአት በፊትፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ጦርነት ምክንያት የቻይናው ጉዟቸውን አራዘሙ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ በኢራን ጦርነት ምክንያት ከሁለት ሳምንት በኋላ ሊያደርጉት የነበረውን ተጠባቂውን የቻይና ጉዟቸውን ለአንድ ወር በሚጠጋ ጊዜ ለማራዘም ማቀዳቸውን ተናገሩ።ፕሬዝዳንቱ በዋይት ሐውስ በጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ጉዞውን “በአንድ ወር ወይም እንዲያ አካባቢ ለማዘግየት ጥያቄ አቅርበናል” ብለዋል።ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ሺፒንግ ይገናኙበታል ተብሎ የሚጠበቀው ጉብኝት ከመጋቢት 22 እስከ 24/2018 ዓ.ም. እንዲካሄድ ቀጠሮ ተይዞለታል።እንደ ትራምፕ ገለጻ ጉዞውን ማራዘም ውሳኔ ላይ የተደረሰው ከእስራኤል ጋር በመሆን ኢራን ላይ የከፈቱትን ጦርነቱን ለመምራት አገር ውስጥ መሆን አስፈላጊ በመሆኑ ነው።“በጣም ቀላል ነው። ጦርነት እያካሄድን ነው። እዚህ መሆኔ አስፈላጊ ይመስለኛል” ሲሉ ተናግረዋል። ትራምፕ እዚህ ውሳኔያቸው ውስጥ “ምንም ማታለል” እንደሌለበት አጽንኦት የሰጡ ሲሆን የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጋር መገናኘት እንደሚፈልጉም አክለዋል።ትራምፕ ይህንን ያሉት ከብሪታኒያው ጋዜጣ ፋይናንሻል ታይምስ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፤ ቻይና ሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲከፈት የማታግዝ ከሆነ ጉብኝታቸው ሊያራዝሙ እንደሚችሉ ከተናገሩ በኋላ ነው።በሁለቱ ግዙፍ የዓለም ኢኮኖሚዎች መካከል ያለው ፍትጊያ በኢራን ጦርነት ምክንያት ተባብሷል። የኢራን የኢነርጂ ኤክስፖርት ዋነኛ ገዢ የሆነችው ቻይና አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ ከፈቱትን ጥቃት ተቃውማለች።የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በበኩላቸው “ከፕሬዝዳንት ትራምፕ የቻይና ጉብኝት ቀን እና ተያያዥ ጉዳዮችን” በተመለከተ ቤይጂንግ እና ዋሽንግተን እየተነጋገሩ መሆኑን ማክሰኞ ዕለት ገልጸዋል።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ጦርነት ምክንያት የቻይናው ጉዟቸውን አራዘሙ - 17 መጋቢት 2026የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአገሪቱ ቡድን ጨዋታዎች ሜክሲኮ ውስጥ እንዲካሄዱ እየተደራደረ መሆኑን ገለጸ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን በደኅንነት ስጋት ምክንያት የአገሩ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ወደ ሜክሲኮ እንዲዛወሩ ለማድረግ ከፊፋ ጋር እየተደራደረ መሆኑን አስታወቀ።የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት መህዲ ታጅ በኤክ ገጻቸው ባጋሩት ልጥፍ “ትራምፕ የኢራን ብሔራዊ ቡድንን ደኅንነት ማስጠበቅ እንደማይችሉ በግልጽ በተናገሩበት ሁኔታ በእርግጠኝነት ወደ አሜሪካ አንጓዝም” ብለዋል።አክለውም “በአሁኑ ሰዓት የኢራንን የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ሜክሲኮ ውስጥ ለማድረግ ከፊፋ ጋር እየተደራደርን ነው” ሲሉ ጽፈዋል።አሜሪካ ከእስራኤል ጋር በመሆን ቴህራን ላይ ጥቃት መክፈቷን ተከትሎ፤ ባለፈው ሳምንት የኢራን ስፖርት ሚኒስትር የአገሪቱ ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው መሳተፍ እንደማይችል ተናግረው ነበር።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢራን የዓለም ዋንጫውን ለመሳተፍ እንደምትችል ጠቁመው፤ ነገር ግን “ለራሳቸው ሕይወት እና ደኅንነት ሲባል እዚህ መምጣታቸው ተገቢ አይደለም” የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።በምድብ ሁለት ውስጥ ያለው የኢራን ብሔራዊ ቡድን ሎስ አንጀለስ ውስጥ ጨዋታዎች ያሉት ሲሆን፣ አንድ ጨዋታ ደግሞ ሲያትል ውስጥ እንዲያደርግ ድልድል ወጥቷል።ያጋሩ, የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአገሪቱ ቡድን ጨዋታዎች ሜክሲኮ ውስጥ እንዲካሄዱ እየተደራደረ መሆኑን ገለጸ - 17 መጋቢት 2026እስራኤል የዜጎቼ ደኅንነት ሳይረጋገጥ የሊባኖስ ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያቸው አይመለሱም አለች
የፎቶው ባለመብት,WAEL HAMZEH/EPA/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,ቤይሩት ውስጥ በተከፈተው ጥቃት ተፈናቅለው የፕላስቲን መጠለያ ውስጥ የሚኖሩ አዛውንትእስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በሚገኙ የድንበር አካባቢዎች ያሉ ዜጎቿ ደኅንነት እስከሚረጋገጥ ድረስ ሊባኖስ ውስጥ በከፈተችው ወታደራዊ ዘመቻ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደ መኖሪያቸው እንደማይመለሱ ተናገረች።ዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ጣልያን በበኩላቸው በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ ሊባኖስ ውስጥ የተከፈተው የእረኛ ጦር ጥቃት “አስከፊ ሰብአዊ መዘዝ” እንደሚኖረው አስጠንቅቀዋል።የዓለም የፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) መረጃ እንደሚያሳየው በሄዝቦላህ ጥቃት የተሰነዘረባት እስራኤል የከፈተችውን ዘመቻ ተከትሎ የተፈናቀሉ ሰዎች ብዛት ወደ አንድ ሚሊዮን ገደማ ተጠግቷል።የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ የሆኑት ሌተናንት ኮሎኔል ናዳቭ ሾሻኒ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ወታደሮች ሊባኖስ ውስጥ “አዲስ ስፍራዎች” ላይ የእግረኛ ጦር ጥቃት መፈጸም መጀመራቸውን እንደተናገሩ የዜና ወኪሉ ሮይተርስ ዘግቧል። አዲሱን ጥቃት “ውሱን እና ዒላማዎች ላይ ያተኮረ” ሲሉ ገልጸውታል።“ባለፉት ሁለት ሳምንታት በደቡባዊ ሊባኖስ ውስን ዒላማ ያለው የእግረኛ ጦር ዘመቻ ከፍተናል፤ [ዘመቻው] ስጋቱን ከድንበር የመግፋት እና የሰሜናዊ እስራኤል ነዋሪዎችን የረጅም ጊዜ ደኅንነት የማረጋገጥ ዓላማ አለው” ብለዋል።የሊባኖስ ጤና ሚኒስትር እንደሚገልጸው፤ በእስራኤል ጥቃቶች 880 ሰዎች ተገድለዋል። ሚኒስቴሩ ይህ ቁጥር በንጹኃን ላይ ብቻ የደረሰ ጉዳት ስለመሆኑ አላብራራም።ምዕራባውያን አገራት በበኩላቸው ባወጡት የጋራ መግለጫ፤ እስራኤል እና ሊባኖስ ድርድር በማድረግ “ተጨባጭ የፖለቲካ መፍትሔ” ላይ እንዲደርሱ አሳስበዋል። ሊባኖስ ውስጥ ያለው ሰብአዊ ሁኔታም “እጅግ አሳሳቢ” እንደሆነ ገልጸዋል።“ከፍተኛ የሆነው የእስራኤል የእግረኛ ጦር ጥቃት አስከፊ ሰብአዊ መዘዝ ይኖረዋል፤ ወደ ተራዘመ ጦርነትም ሊያመራ ይችላል። መቀልበስ አለበት” ብለዋል።
የፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,የእስራኤል ጥቃት ከተጀመረ አንስቶ የተፈናቀሉ ነዋወዎች ብዛት አንድ ሚሊዮን ተጠግቷል
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ከእስራኤል ጋር በሚጎራበተው ኪያም የተባለ የደቡባዊ ሊባኖስ ስፍራ የተፈጸመ ጥቃት
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በደቡባዊ ቤይሩት የተፈጸመ ጥቃት
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የእስራኤል ወታደሮች በሊባኖስ ድንበር አቅራቢያያጋሩ, እስራኤል የዜጎቼ ደኅንነት ሳይረጋገጥ የሊባኖስ ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያቸው አይመለሱም አለች - 17 መጋቢት 2026የእስያ አገራት ነዳጅ ለመቆጠብ የሥራ ቀናትን ከመቀነስ አንስቶ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesእስያዊቷ አገር ሲሪ ላንካ፤ በኢራን ጦርነት ምክንያት ሊፈጠር የሚችል የነዳጅ እጥረትን ለመቋቋም በየሳምንቱ ረቡዕ ዕለት እንደ የሕዝብ በዓል ተቆጥሮ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እንዲዘጉ ወሰነች። ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችም ምን ያህል ነዳጅ መግዛት እንደሚችሉ የሚወስን የራሽን ካርድ እንዲይዙ ተደርጓል።የሲሪ ላንካ ፕሬዝዳንት አኑራ ኩማራ ዲሳናያኬ ሰኞ ዕለት በተደረገ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ “ለከፋው ነገር መዘጋጀት አለብን፤ ነገር ግን ጥሩ ነገር እንደሚመጣ ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።ሲሪ ላንካ ይህንን እርምጃ የወሰደችው በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠር በርሜል ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋቱን ተከትሎ ሌሎች የእስያ አገራት የቁጠባ ውሳኔዎችን ካሳለፉ በኋላ ነው።ባለፈው ዓመት በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ካለፈው ነዳጅ እና ጋዝ ውስጥ 90 በመቶ የሚጠጋው የደረሰው ወደ እስያ ነው።ሌሎችም የእስያ አገራት በጦርነቱ ምክንያት የነዳጅ እጥረት እንዳይፈጠር በመስጋት እርምጃዎችን ወስደዋል።ምያንማር – የግል ተሽከርካሪዎች እንዲንቀሳቀሱ የሚፈቀድላቸው አንድ ቀን እያለፉ ነው። በየትኛው ቀን የቱ ተሽከርካሪ ይንቀሳቀሳል የሚለው የሚወሰነው በሰሌዳ ቁጥር ነው።ባንግላዴሽ – ነዳጅ እና ኤሌክትሪክ ለመቆጠብ ሲባል እስከ ኢድ አልፈጥር ድረስዩኒቨርሲቲዎች ተዘግተዋል። በመላ አገሪቱ መብራት የሚጠፋባቸው ቀናት እንደሚኖሩም ተገልጿል።ፊሊፒንስ – የመንግሥት ሠራተኞች ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን ከቤት እንዲሰሩ ታዝዘዋል። የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ፈርዲናንድ ማክሮስ ጁኒየር የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ወሳኝ ያልሆኑ ጉዞዎችን እንዳያደርጉ ከልክለዋል።ታይላንድ – የዜጎችየአየር ማቀዝቀዣ አጠቃቀም እንዲቀንስ ሲባል ነዋሪዎች ከሱፍ ይልቅ እጅጌ ጉርድ ልብሶችን እንዲያደርጉ አሳስባለች።ቬትናም – ነዳጅ መቆጠብ እንዲቻል ዜጎች ይበልጥ ቤታቸው መዋልን እንዲያዘወትሩ በአጽንኦት አሳስባለች። ሕዝቡ “አላስፈላጊ ሲሆን የግል መኪና ጠቀምን እንዲገድብ” እንዲሁም “ሳይክል እንዲነዱ፣ ጋሪ እንዲጠቀሙ እንዲሁም በሕዝብ ትራንስፖርት እንዲገለገሉ” ጥሪ ቀርቧል።ያጋሩ, የእስያ አገራት ነዳጅ ለመቆጠብ የሥራ ቀናትን ከመቀነስ አንስቶ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው - 17 መጋቢት 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ ለማገዝ ጉጉት አልታየባቸውም ያሏቸውን አገራት ወቀሱ
የፎቶው ባለመብት,EPAየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን በተዘጋው የሆርሙዝ ሰርጥ በኩል የሚያልፈውን ነዳጅ ለማጀብ የጦር መርከቦቻቸውን እንዲልኩ ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ ያደረጉን ምዕራባውያን አጋሮቻቸውን በምስጋና ቢስነት ወቀሱ።ትራምፕ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም እና የኔቶ አባላት ያሉ አጋሮች በጦርነቱ ከአሜሪካ ጋር ለመሰለፍ አንገራግረዋል ሲሉ ተችተዋል። በተለይም ዩናይትድ ኪንግደም ጦርነቱን በተመለከተ ባሳየችው አቋም “እጅግ መገረማቸውን” ተናግረዋል።ትራምፕ፤ “ከሁለት ሳምንት በፊት ‘ለምን ተጨማሪ መርከቦችን አትልኩም’ አልኩ። [የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር] እውነትም ማድረግ አልፈለገም ነበር” ሲሉ የዩናይትድ ኪንግደሙን መሪ ኪር ስታርመር ወቅሰዋል።“አካባቢው ላይ ፈንጂ የሚቀርብ መርከብ እንዳላቸው ይነግሩናል፤ ማድረግ ግን አይፈልጉም፤ ይሄ መጥፎ ነው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በዩናይትድ ኪንግደም “ደስተኛ አይደለሁም” ሲሉም ተደምጠዋል። “ሊሳተፉ እንደሚችሉ አስባለሁ፤ ነገር ግን በጉጉት መሳተፍ አለባቸው” ብለዋል።በአሜሪካ እና እስራኤል ጦርነት የተከፈተባት ኢራን ከዓለም ነዳጅ 20 በመቶ ገደማው የሚተላለፍበትን የሆርሙዝ ሰርጥን ዘግታለች። ሊያልፉ የሞከሩ መርከቦች ላይም ጥቃት ተፈጽሟል።ወሳኙ መተላለፊያ እንዲከፈት የሚደረገውን ጥረት ቢያንስ አምስት አገራት ይቀላቀላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ትራምፕ ተናግረው ነበር። ጀርመን፣ ስፔን እና ጣልያንን ጨምሮ በርካታ የአሜሪካ አጋር አገራት አሁን ወደ ሰርጡ የጦር መርከብ የመላክ እቅድ እንደሌላቸው ተናግረዋል።ትራምፕ ትናንት በዋይት ሀውስ ባደረጉት ንግግር አገራት እገዛ ለማድረግ መንገድ ላይ ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። የትኛዎቹ አገራት ድጋፍ እንደሚደርጉ ባይጠቅሱም፤ በቅርቡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይገልጻል ብለዋል።“የተወሰኑ አገራት [እገዛ ለማድረግ] ጉጉት አላቸው፤ የተወሰኑት ደግሞ የላቸውም” ሲሉ ተናግረዋል። “አንዳንድ አገራትን ለብዙ፣ ብዙ ዓመታት አግዘናቸዋል፤ ከመጥፎ የውጪ አካል ጠብቀናቸዋል፤ እናም ግን [እኛን ለማገዝ] ጉጉት አልነበራቸውም። ምን ያህል ጓጉተዋል የሚለው ለእኔ ዋጋ አለው” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ ለማገዝ ጉጉት አልታየባቸውም ያሏቸውን አገራት ወቀሱ - 17 መጋቢት 2026ኢራቅ ውስጥ “ከባድ” የሮኬት እና የድሮን ጥቃት ተፈጽሞ የአሜሪካ ኤምባሲ ተመታ
የፎቶው ባለመብት,reuበኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሮኬቶች እና አምስት ድሮኖች እንደተወነጨፉበት ገለጸ። የኢራን ጦርነት ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ኢራቅ ላይ ከተፈጸሙ ጥቃቶች ከባዱ ነው የተባለው ሮኬት እና ድሮን የተወነጨፈው በባግዳድ ከተማ ዙሪያ ካሉ አከባቢዎች እንደሆነ የዜና ወኪሉ ሮይተርስ ዘግቧል።የዜና ወኪሉ ያነጋገራቸው የዓይን እማኞች ቢያንስ ሦስት ድሮኖች ወደ ኤምባሲው አቅጣጫ ሲያመሩ መመልከታቸውን ገልጸዋል። ‘ሲ-ራም’ የተሰኘው የአየር መከላከያ ስርዓት ሁለቱን ድሮኖች መትቶ ሲጥላቸው ሦስተኛው የኤምባሲውን ግቢ እንደመታ ገልጸዋል።ቀጥሎም ከኤምባሲው ግቢ እሳት እና ጭስ ሲወጣ ይታይ ነበር ተብሏል። ሌላ የዓይን እማኝ ደግሞ በኢራቅ ዋና ከተማ የፍንዳታ ድምጽ መሰማቱን እንደተናገሩ ተዘግቧል።ሌላኛው የዜና ወኪል አሶሺየትድ ፕሬስ በበኩሉ ኤምባሲውን ዒላማ ያደረጉት አራቱም ድሮኖች በአየር መከላከያ ስርዓቱ ተተመትተው መውደቃቸውን ሁለት የኢራቅ ባለሥልጣናት እንደነገሩት ዘግቧል። ይሁን እንጂ ድሮኖቹ ሲመቱ የነበረው ስብርባሪ ኤምባሲውን እንደመታው ገልጸዋል።በሌላ በኩል ባግዳድ ውስጥ በሚገኘው አል ጃድሪያ አካባቢ ውስጥ የሚገኘው እና ከፍተኛ የጥቃት መከላከያ የተደረገለት ፕሬዝዳንታዊ ግቢ ውስጥ ያለን ቤት ዒላማ ያደረገ የአየር ጥቃት እንደተፈጸመ የኤፒ ዘገባ ያመለክታል።የመንግሥት ህንጻዎች እና የውጭ ኤምባሲዎች በሚገኙበት የባግዳዱ ‘ግሪን ዞን’ አካባቢ በተፈጸመው የድሮን ጥቃት በእሳት የተያያዘው ቅንጡ ሆቴል እንደሆነ ተነግሯል።ጥቃቱን ማን እንደፈጸመው እንደማይታወቅም ዘገባው አክሏል። ሮይተርስ በበኩሉ በኢራን የሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖች ኢራቅ ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ይዞታዎች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ መሆኑን ገልጿል።ከኢራን ጋር ግንኙነት ያለው ሄዝቦላህ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዡ እና ቃል አቀባዩ መገደላቸውን አስታውቋል። ሌላኛው ታጣቂ ቡድን ‘ፖፑላር ሞቢላይዜሽን ፎርስስ’ ደግሞ ከሶሪያ አቅራቢያ በምትገኘው የኢራቋ አል ቃኢም ከተማ በተፈጸመ የአየር ጥቃት ስምንት ተዋጊዎቹ መገደሉን ገልጿል።ያጋሩ, ኢራቅ ውስጥ “ከባድ” የሮኬት እና የድሮን ጥቃት ተፈጽሞ የአሜሪካ ኤምባሲ ተመታ - 16 መጋቢት 2026የኢራን ጦር እስራኤል ውስጥ የሚገኙ የጦር መሣሪያ ማምረቻዎችን መትቻለሁ አለ
የፎቶው ባለመብት,NurPhotoየኢራን ጦር፤ በዛሬው ዕለት እስራኤል ውስጥ የሚገኙ የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪ ማዕከላትን በድሮን ጥቃት መደብደቡን ገለጸ።የኢራን ጦር የሕዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ፤ በዛሬው ዕለት እስራኤል ውስጥ የሚገኙ ወሳኝ እና ስትራቴጂክ የጦር መሣሪያ ማዕከላትን ዒላማ ማድረጉን አስታውቋል።ራፋኤል በተሰኘው ኩባንያው እንዲሁም ‘ኢዝራኤል ኤሮስፔስ ኢንደስትሪስ’ የተባለው ተቋምን መምታቱንም ተናግሯል።ራፋኤል የተባለው ኩባንያ እንደ አይረን ዶም እና ዴቪድስ ስሊንግ ያሉ የአየር መከላከያ ሥርዓቶችን የሚሠራ ተቋም ነው። ስፓይክ ሚሳዔሎች እና ወታደራዊ የኤሌክትሮኒክ ቴክኖሎጂዎችም ኩባንያው ውስጥ ይሠራሉ።‘ኢዝራኤል ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪስ’ ደግሞ የውጊያ አውሮፕላኖች፣ ድሮኖች፣ ሚሳዔሎች እና የመከላከያ ሥርዓቶችን ያመርታል። እንደ አሮው ሚሳኤል መከላከያ ያሉ ወሳኝ ሥርዓቶችንም እንደሚያመርት የፋርስ ዜና ወኪል ዘገባ ያመለክታል።ያጋሩ, የኢራን ጦር እስራኤል ውስጥ የሚገኙ የጦር መሣሪያ ማምረቻዎችን መትቻለሁ አለ - 16 መጋቢት 2026ኔቶ በሆርሙዝ ወሽመጥ ጉዳይ ይሳተፋል ብለው እንደማያስቡ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,EPAየሰሜን አትላንቲን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በኢራን የተዘጋውን የሆርሙዝ ወሽመጥ የማስከፈት ሂደት ውስጥ ሚና ይኖረዋል ብለው እንደማያስቡ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዩሃን ዋድፉል ተናገሩ።ኢራን ወሳኝ የነዳጅ ምርቶች መተላለፊያ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥ መዝጋቷን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አገራት የባሕር መስመሩን ለማስከፈት እንዲቀሳቀሱ ጥሪ እያቀረቡ ነው።ትራምፕ ከፋይናንሻል ታይምስ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ አጋር አገራት ወሽመጡን ለመቆጣጠር እገዛ የማያደርጉ ከሆነ “ለኔቶ መጻኢ እጅግ መጥፎ” እንደሚሆን ተናግረዋል።የአወሮፓ ኅብረት በዚሁ ጉዳይ ላይ ሊያደርግ ካቀደው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በፊት ንግግር ያደረጉት የጀርመኑ ሚኒስትር፤ የኔቶ ተሳትፎን ጉዳይ አንስተዋል።“ኔቶ በዚህ አቅጣጫ ውሳኔ ማሳለፉ ወይም የሆርሙዝ ወሽመጥን በተመለከተ ኃላፊነት መውሰዱ አይታየኝም። ጉዳዩ ይህ ቢሆን ኖሮ የኔቶ አካላት በዚሁ አኳዃን መፍትሔ ይሰጡት ነበር” ብለዋል።ያልተረጋጋው የመካለኛው ምሥራቅ ሁኔታ ቢኖርም፤ አውሮፓ ደኅንነትን በተመለከተ ቅድሚያ የምትሰጠው የዩክሬንን ጉዳይ እንደሆነ ዋድፉል ተናግረዋል። የነዳጅ እና ጋዝ ዋጋ ሲጨምር የሩሲያ የጦርነት አቅም እንደሚጨምር ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ማዕቀቡን ማላላት የተሳሳተ እርምጃ እንደሆነ ገልጸዋል።በመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ላይ መግለጫ የሰጡት ዩናይትድ ኪንግደሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመርም የሆርሙዝ ወሽመጥን የማስከፈት ጉዳይ የኔቶ ተልዕኮ እንደማይሆን ተናግረዋል።ያጋሩ, ኔቶ በሆርሙዝ ወሽመጥ ጉዳይ ይሳተፋል ብለው እንደማያስቡ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ - 16 መጋቢት 2026ዩኬ ከኢራን ጋር በተያያዘ ወደ “ሰፊ ጦርነት” ተስባ እንደማገትባ አስታወቀች
የፎቶው ባለመብት,Reutersየዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር አገራቸው ከኢራን ጋር በተያያዘ ወደ “ሠፊ ጦርነት” ተስባ እንደማትገባ፤ ነገር ግን የሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲከፈት ለማድረግ “ከአጋሮች ጋር እንደምትሠራ” ተናገሩ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ በፈጸሙት የመጀመሪያ ጥቃት ዩናይትድ ኪንግደም አለመሳተፏን አንስተው አብራርተዋል።ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቋም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትችት አስነስቶባቸው እንደነበር ይታወሳል። ኋላ ላይ ግን የአሜሪካ ሠራዊት የዩናይትድ ኪንግደምን ጦር ሠፈሮች እንዲጠቀም ተፈቅዶለታል።ስታርመር በጋዜጣዊ መግለጫው፤ የአሜሪካ ዘመቻ “ኢራን ውስጥ የሚገኘው አጸያፊ አገዛዝ’ ወታደራዊ አቅም “በከፍተኛ ሁኔታ አዳክሞታል” ብለዋል።ከጦርነቱ በኋላ ግን ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሟን መልሳ የመገንባት አቅሟን የሚገድብ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የመርከብ ጉዞን ደኅንነት የሚያስጠብቅ የሆነ ዓይነት “በድርድር የሚደረስ ስምምነት” እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።የዓለም አቀፍ “ገበያዎችን መረጋጋት ለማረጋገጥ” እንዲቻል ኢራን የዘጋችው የሆርሙዝ ወሽመጥ በድጋሚ መከፈት እንዳለበትም ገልጸዋል። ነገር ግን ይህንን ማድረግ “ቀላል ሥራ እንዳልሆነ” አክለዋል።ለዚህም ሲባል ዩናይትድ ኪንግደም በቀጣናው የባሕር ጉዞ የማድረግ ነጻነትን ለመመለስ የሚያስችል “ተጨባጭ ዕቅድ” ለማዘጋጀት “ከሁሉም አጋሮቿ ጋር” እየሠራች መሆኑን አስታውቀዋል።በዚህ ጦርነት የተነሳ የሸቀጦች ዋጋ ላይ ጭማሪ መታየቱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ስታርመር፤ በዚህ ምክንያት የመጣውን የኑሮ ውድነት የሚያበርደው ውጤታማ መንገድ ግጭቱን ማርገብ መሆኑንም አክለዋል።ያጋሩ, ዩኬ ከኢራን ጋር በተያያዘ ወደ “ሰፊ ጦርነት” ተስባ እንደማገትባ አስታወቀች - 16 መጋቢት 2026የኢራን አብዮታዊ ዘብ 55 ዙር የድሮን እና የሚሳዔል ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታወቀ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ፤ ‘ኦፕሬሽን ትሩ ፕሮሚስ 4’ በተሰኘው ዘመቻ “ቴል አቪቭ እና ቤን ጉሪኦን” አየር ማረፊያዎች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ማዕከላትን ዒላማ ያደረጉ “55 ዙር” የድሮን እና የሚሳዔል ጥቃቶችን መፈጸሙን ገለጸ።በእነዚህ ጥቃቶች ዒላማ ከተደረጉት ተቋማት መካከል “የኤሮስፔስ መሣሪያዎች ማምረቻ እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ መቅጃ የእገዛ ማዕከላት” እንደሚገኙበት አብዮታዊ ዘቡ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።በዚህ ዘመቻ “ፈታህ፣ ኤማድ፣ ቋድር ሃይፐርሶኒን ሚሳዔሎች እንዲሁም አውዳሚ ድሮኖች” ጥቅም ላይ እንደዋሉም ተነግሯል።አብዮታዊ ዘቡ አክሎም፤ “አል ድሃፍራ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር፣ ጁፍኤር ባሕር ኃይል ጦር ሰፈር እንዲሁም ሼክ ኢሳ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር” ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማትን ዒላማ ማድረጉን አስታውቋል።በጦር ሰፈሮቹ የሚገኙት የአሜሪካ ይዞታዎች ከተመቱባቸው መሣሪያዎች መካከል “ፋተህ፣ ዙልፊቃር፣ ደዝፉል የመካከለኛ ርቀት ሚሳዔል“ ተጠቅሰዋል። “ስማርት እና አውዳሚ ድሮኖችን” ጥቅም ላይ ውለዋል ተብሏል።ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዋና ከተማ አቡ ዳቢ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው አል ድሃፍራ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር፤ የኤምሬቶች አየር ኃይል የውጊያ ዕዝ እና የአሜሪካ አየር ኃይል ዋና መስሪያ ቤቶችን ይዟል።ባህሬን ውስጥ የሚገኘው ጁፍኤር የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር ደግሞ ‘ዩኤስ ፊፍዝ ፍሊት’ የተሰኘው የአሜሪካ ጦር መርከብ ማረፊያ ነው። ሼክ ኢሳ አየር ኃይል ጦር ሰፈርም ባህሬን ውስጥ የሚገኝ ወታደራዊ አየር ማረፊያ ነው።በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት የአሜሪካ እና የእስራኤል ተዋጊ ጄቶቸ በምሥራቃዊ ቴህራን በሚገኙ አካባቢዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን የኢራኑ ፋርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ 55 ዙር የድሮን እና የሚሳዔል ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታወቀ - 16 መጋቢት 2026የእስራኤል ጦር የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪን የግል አውሮፕላን ማውደሙን ተናገረ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየእስራኤል ጦር ቴህራን በሚገኘው መህራባድ አየር ማረፊያ ላይ በፈጸመው ጥቃት የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ይጠቀሙበት የነበረን አውሮፕላን ማውደሙን ተናገረ።የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በፋርስ ቋንቋ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ባወጣው መግለጫ፤ አውሮፕላኑ “በሽብርተኛው የኢራን አገዛዝ መሪ አሊ ኻሜኒ እና በሌሎች የአገዛዙ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲሁም የኢራን ጦር አባላት” ጥቅም ላይ ይውል ነበር ብሏል።ባለሥልጣናቱ “ወታደራዊ ግዢዎችን ለመፈጸም እንዲሁም በአገር ውስጥ እና የውጭ በረራዎች ከተጣማሪ አገራት ጋር የሚደረግ ግንኙነትን ለመምራት” ይጠቀሙበት እንደነበርም ገልጿል።ሰኞ ጠዋት ላይ ቴህራን ውስጥ በርካታ የአየር ጥቃቶች እንደተፈጸሙ ተገልጿል። ነዋሪዎች መህራባድ አየር ማረፊያ አቅራቢያ በርካታ ፍንዳታዎችን እንዲሁም ጥቁር ጭስ ወደላይ ሲጎን መመልከታቸውን ተናግረዋል።በርካታ ተጓዦችን በማስተናገድ ከኢራን አየር ማረፊያዎች ቀዳሚ የሆነው መህራባድ በርካታ የአየር ጥቃቶች ዒላማ ሆኗል።ያጋሩ, የእስራኤል ጦር የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪን የግል አውሮፕላን ማውደሙን ተናገረ - 16 መጋቢት 2026የአውሮፓ ኅብረት ሆርሙዝን ለማስከፈት ምን ማድረግ እንደሚቻል ሊነጋገር ነው
የፎቶው ባለመብት,EPAየአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ጦርነት ምክንያት የተዘጋውን የሆርሙዝ ወሽመጥ ለማስከፈት ምን ማድረግ እንደሚቻል ለመነጋገር አንደሚሰበሰቡ የውጭ ፖሊሲ ኃላፊው ተናገሩ።ካያ ካላስ በብራሰልስ ከሚካሄደው የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳዮች ስብሰባ አስቀድመው “የሆርሙዝ ወሽመጥ ክፍት ሆኖ መቀጠሉ ለእኛም ጥቅም ነው” ሲሉ ተናግረዋል።በዚህ 20 በመቶ የሚሆነው የዓለም ነዳጅ በሚያልፍበት የውሃ አካል ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ለማለፍ የሞከሩ በርካታ መርከቦች ጥቃት እንደደረሰባቸው ተዘግቧል።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ አጋሮች የመተላለፊያውን ደኅንነት ለማረጋገጥ ድጋፍ ካላደረጉ “ለኔቶ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በጣም መጥፎ ይሆናል” ብለዋል።እሁድ ዕለት የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ትራምፕ ከሰር ኪር ስታርመር ጋር “በዓለም አቀፍ የመርከብ ጭነት ላይ የሚደርሰውን መስተጓጎል ለማስቆም” የሆርሙዝ ወሽመጥን እንደገና መከፈት አስፈላጊ መሆኑን መነጋገራቸውን አስታውቋል።ያጋሩ, የአውሮፓ ኅብረት ሆርሙዝን ለማስከፈት ምን ማድረግ እንደሚቻል ሊነጋገር ነው - 16 መጋቢት 2026ኢራን ቀይ ባሕር ላይ የሚገኘውን የአሜሪካ ግዙፍ የጦር መርከብን ዒላማ አደርጋለሁ አለች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ጄራርድ አር. ፎርድ የጦር መርከብየኢራን ጦር በቀይ ባሕር አካባቢ የሚገኘው የአሜሪካ ግዙፉ አውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከብ ለአገሩ ስጋት በመሆኑ ተገቢ የጥቃት ዒላማ እንደሚሆን አስታወቀ።የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አንድ አካል የሆነው ኻታም አል-አንቢያ ባወጣው መግለጫ “የአሜሪካ ጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ጄራርድ ፎርድ በቀይ ባሕር መገኘቱ” ለኢራን “ስጋት” ስለሚሆን የመርከቡ የአቅርቦት እና የአገለግሎት ማዕከላት በሙሉ “የኢራን ጦር ኃይሎች ዒላማ” ተደርገው ይቆጠራሉ ብሏል።ሦስት መቶ ሜትር ርዝመት ያለው ይህ ጄራርድ አር. ፎርድ የተባለው የጦር ጄቶች ተሸካሚ የጦር መርከብ በዓለም ላይ ትልቁ የጦር መርከብ ነው።በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ ጦር ሠራዊት ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) ባለፈው ሐሙስ በዚህ የጦር መርከብ አንድ ክፍል ላይ እሳት ተነስቶ እንደነበር አስታውቋል።ነገር ግን እሳቱ በቁጥጥር ስር እንደዋለ እና “በመርከቧ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ላይ መስተጓጎል የሚያስከትል ጉዳት እንዳልደረሰ እና ሙሉ ለሙሉ ሥራውን እያከናወነ” መሆኑን ገልጿል።ማዕከላዊ ዕዙ ጨምሮም በመርከቡ ላይ የተነሳው እሳት “ከጦርነት ጋር በተያያዘ አይደለም” ሲሉ በወታደራዊ እንቅስቃሴ ምክንያት እንዳልሆነ አመልክቷል።የጦር አውሮፕላን ተሸካሚው ዩኤስኤስ ጄራርድ አር. ፎርድ በቬንዙዌላ ከተፈጸውን የአሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ በኋላ በኢራን ላይ የተከፈተው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እንዲንቀሳቀስ ተደርጎ ነው በቀይ ባሕር ላይ የሚገኘው።አሜሪካ ቢሊዮኖችን ስላፈፈሰሰችበት ጄራርድ አር ፎርድ የጦር መርከብ ምን ይታወቃል?ያጋሩ, ኢራን ቀይ ባሕር ላይ የሚገኘውን የአሜሪካ ግዙፍ የጦር መርከብን ዒላማ አደርጋለሁ አለች - 16 መጋቢት 2026የድሮን ጥቃት በዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ ላይሌሊቱን በዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ምክንያት በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረው በረራ መልሶ እንደሚጀመር ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።በረራዎች እንዲቋረጡ የተደረገው በተፈጸመው ጥቃት ምክንያት በነዳጅ ማጠራቀሚያ ላይ በተነሳ እሳት መሆኑን እና በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱ ተዘግቧል።የዱባይ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ለጥንቃቄ ሲባል ተቋርጦ የነበረውን የአየር ትራንስፖርት “ከዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደተወሰኑ መዳረሻዎች የሚደረጉ በረራዎች ቀስ በቀስ መልሰው እንደሚጀምሩ” አስታውቋል።መንገደኞችም ስለበረራዎቻቸው መረጃዎችን ከሚጠቀሟቸው አየር መንገዶች እንዲያጣሩ ተነግሯቸዋል።ያጋሩ, የድሮን ጥቃት በዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ
- 16 መጋቢት 2026ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ “ነዳጅን በቁጠባ እና ለመሠረታዊ ነገሮች” እንዲውል አሳሰቡ
የፎቶው ባለመብት,Abiy Ahimedጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመካከለኛው ምሥራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት አስራ ስድስተኛ ቀኑን በያዘበት በዛሬው ዕለት “ነዳጅን በቁጠባ” መጠቀም እንደሚያስፈልግ አሳሰቡ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የማኅበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት አጭር መልዕክት ነዳጅን ገዝተው የሚጠቀሙ አገራት መቸገራቸውን ገልጸው፤ “በቁጠባ እና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም” አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።ባለፈው ሳምንቱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተፈጠረው የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ስለማይታወቅ ሕብረተሰቡ እና ተቋማት ነዳጅን “በከፍተኛ ቁጠባ” እንዲጠቀሙ አሳስበው ነበር።በጦርነቱ ምክንያት የታየውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ “አስፈሪ” ሲሉ የገለጹት የገንዘብ ሚኒስትሩ፤ መንግሥት “በቅርቡ ተጨማሪ የነዳጅ ቁጠባ እርምጃዎችን” ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ የነዳጅ አከፋፋዮችም ሆኑ ተጠቃሚዎች እንዲሁም ማደያዎች ለመሠረታዊ አገልግሎት ቅድሚያ እንዲሠጡ እና በቁጠባ እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።የፋርስ ባሕረ ሰላጤ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ የዓለም 20 በመቶ ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ የተነሳ በተጨማሪም በጦርነቱ የኢራን እና የሌሎች የመካለኛው ምሥራቅ አገራት የነዳጅ መሠረተ ልማቶች ጥቃት ስለተፈጸመባቸው የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።በዚህም ምክንያት የነዳጅ ዋጋ ከአውሮፓውያኑ 2022 ወዲህ ከፍተኛ ጭማሪ በማሳየት በበርሜል 120 ዶላር ገብቶ ነበር።ይህንንም ተከትሎ የዓለም አቀፉ ኢነርጂ ኤጀንሲ ከፍተኛ መጠን ያለውን ነዳጅ ከክምችቱ በማውጣት ለእስያ እንዲሁም ኦሺኒያ አገራት በዛሬው ዕለት እንደሚያከፋፍል ይፋ አድርጓል።የዓለም አንድ አምስተኛ የነዳጅ አቅርቦት የሚተላለፍበት የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ መዘጋትን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ መጨመሩን ዛሬም እንደቀጠለ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።እሁድ ዕለት በዓለም አቀፍ ገበያ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ እስከ 3 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በበርሚል 106 ዶላር ተሸጧል።በዛሬው ዕለት ደግሞ ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል 104.63 እየተሸጠ ነው።ማኅበረሰቡ እና ተቋማት ነዳጅን “በከፍተኛ ቁጠባ” እንዲጠቀሙ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሳሰቡያጋሩ, ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ “ነዳጅን በቁጠባ እና ለመሠረታዊ ነገሮች” እንዲውል አሳሰቡ
