የኢራን ጦር አዛዥ አሚር ሃታሚ በእስራኤል የአየር ጥቃት የደኅንነት ኃላፊው አሊ ላሪጃኒን መገደላቸውን ተከትሎ “ወሳኝ” የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ ዛቱ። ከኢራን ጦር ኃይል የተለየ ወታደራዊ ክፍል የሆነው እስላማዊው አብዮታዊ ዘብ የላሪጃኒ ሞትን “ለመበቀል” ወደ ማዕከላዊ እስራኤል ሚሳዔሎችን መተኮሱን የኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 30 ደቂቃዎች በፊትከሰባቱ ቁልፍ የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ስድስቱ ተገድለዋልአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሚያካሂዱትን ጥቃት ከጀመሩበት ደቂቃ አንስቶ እስካሁን ድረስ ዋነኛ ዒላማ እያደረጓቸው ያሉት የአገሪቱን ከፍተኛ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ መሪዎችን ነው።በመጀመሪያው ቀን ጥቃት የአገሪቱ ጠቅላይ መሪ የሆኑት አያቶላህ አሊ ኻሜኒን ጨምሮ ሌሎች ቁልፍ ባለሥልጣናት በጽህፈት ቤታቸው እና በመኖሪያቸው ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ተገድለዋል።በአገሪቱ ውስጥ በተለያዩ የሥልጣን ደረጃ ላይ የሚገኙ በርካታ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ባለፉት ዓመታት ጭምር ተገድለዋል። አሁን የተከፈተው ጦርነት ደግሞ ሌሎቹንም የጥቃት ዒላማ አድርጓቸዋል።ለመሆኑ ወሳኝ ከሚባሉት ሰባት የኢራን ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ መሪዎች መካከል በአሁኑ ወቅት ከጥቃት ተርፈው በሕይወት የሚገኙት ፕሬዝዳንቱ መሱድ ፔዜሽኪያን ብቻ ናቸው።ባለሥልጣናትያጋሩ, ከሰባቱ ቁልፍ የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ስድስቱ ተገድለዋል
  2. ከ 56 ደቂቃዎች በፊትአሜሪካ ለምን በአሁኑ ወቅት በኢራን ላይ ከባዱን ቦምብ ተጠቀመች?2270 ኪሎ ግራም የሚመዝነው መሽግ ደርማሽ ቦምብየፎቶው ባለመብት,USAFየምስሉ መግለጫ,2270 ኪሎ ግራም የሚመዝነው መሽግ ደርማሽ ቦምብጦርነቱ ሦስተኛ ሳምንቱን ባገባደደበት በአሁኑ ወቅት አሜሪካ 2270 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን ምሽግ ደርማሽ ቦምብ ጥቅም ላይ ማዋል እንደ ጀመረች እየተዘገበ ነው።ይህ ቦምብ ከመሬት በታች በተገነቡ ጠንካራ ምሽጎች ውስጥ ያሉ ዒላማዎችን በጥልቀት በመግባት የማውደም ከፍተኛ አቅም ያለው ሲሆን፣ አሁን ጥቅም ላይ መዋሉ ኢራን የደበቀችው ጦር መሳሪያ እንዳለ ጥርጣሬ መኖሩን ያሳያል።የአሜሪካ ጦር በኢራን የባሕር ዳርቻ አካባቢ ባሉ የሚሳዔል ማስወንጨፊያዎች ላይ ጥቃቱን መፈጸሙን ያስታወቀ ቢሆንም የትኛውን ዓይነት ቦምብ ጥቅም ላይ እንደዋለ ዝርዝር አልሰጠም።ነገር ግን ሁለት ዓይነት ቦምቦች እንዳሉ ይታወቃል እነሱም፤ በጨረር የሚመራው ጁቢዩ-28 እና አዲሱ ዘመናዊ ጂቢዩ-72 የተባሉት ናቸው። በአሁኑ ጥቃት አዲሱ ቦምብ ጥቅም ላይ ሳይውል እንዳልቀረ ይታመናል።ለሦስት ሳምንት ያህል አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ያልተቋረጠ የሚሳዔል እና የአየር ድብደባዎችን እየፈጸሙ ቢሆንም፤ ኢራንም በበኩሏ ያልተቋረጠ የአጸፋ ጥቃት በእስራኤል እና በአሜሪካ አጋሮች ላይ እየፈጸመች ነው።ባለፉት ቀናት የኢራን የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃቶች ተዳክመው ሊቆሙ ይችላሉ ተብሎ ቢታሰብም አሁንም ከኢራን በኩል የሚሰነዘሩት ጥቃቶች በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ዋነኛ ስጋት ሆነው እንደቀጠሉ ናቸው።ለዚህም ሊሆን ይችላል አሜሪካ ከመሬት በታች ዘልቀው በመግባት የሚያወድሙትን ከባዶቹን ቦምቦች በመጠቀም የኢራንን የሚሳዔል እና የድሮን ክምችቶችን እንዲሁም ማስወንጨፊያዎችን ለመጠቀም የተገደደችው።ቦምቡን የሚጥለው ኤፍ-15ኢ ስትራይክ ኢግል የጦር ጄትየፎቶው ባለመብት,USAFየምስሉ መግለጫ,ቦምቡን የሚጥለው ኤፍ-15ኢ ስትራይክ ኢግል የጦር ጄትያጋሩ, አሜሪካ ለምን በአሁኑ ወቅት በኢራን ላይ ከባዱን ቦምብ ተጠቀመች?
  3. ከ 1 ሰአት በፊትበኢራን ጥቃት ተጎድተው 192 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን እስራኤል አስታወቀችቴል አቪቭየፎቶው ባለመብት,Reutersየእስራኤል ጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ኢራን በፈጸመችው ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸው ቢያንስ 192 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን አስታውቋል።ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው ከተጎጅዎቹ መካከል አራቱ መካከለኛ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው።177 የሚሆኑት ደግሞ ቀላል ጉዳት ያስተናገዱ ሲሆን በሆስፒታል ውስጥ ሕክምና እየወሰዱ ነው ብሏል። ቀሪዎቹ 11 ሰዎች ግን በምን ሁኔታ እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም።ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ እስካሁን 3 ሺህ 727 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው የሕክምና ክትትል ማድረጋቸውን ገልጿል።ያጋሩ, በኢራን ጥቃት ተጎድተው 192 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን እስራኤል አስታወቀች
  4. ከ 2 ሰአት በፊትኢራን ‘ለእስራኤል በመሰለል’ የተከሰሰን ግለሰብ በሞት ቀጣችኢራን ለእስራኤሉ የስለላ ድርጅት “ሞሳድ ሲሰልል” ነበር የሚል ክስ የቀረበበትን ግለሰብ በሞት መቅጣቷን የአገሪቱ መንግሥት የዜና ወኪሎች አስታወቁ።ኩሮሽ ኬይቫኒ የተባለው ግለሰብ በሞት መቀጣቱን በተመለከተ ዜናው ይፋ ሲሆን፣ የቀረበበት ክስ እና ቅጣቱ የተላለፈበትን ሂደት በተመለከተ ምንም ዝርዝር መረጃ አልቀረበም።ነገር ግን ለኢራን አብዮታዊ ዘብ ቅርበት ያለው ፋርስ የዜና ወኪል ባወጣው ዘገባ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው አሁን እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር ሳይሆን፣ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ እስራኤል እና ኢራን ለ12 ቀናት የቆየ ጦርነት ባካሄዱበት ጊዜ ነው።የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የስለላ ክስ የሚቀርብባቸው ሰዎች ራሳቸውን የመከላከል መብታቸውን ኢራን እንደማታከብርላቸው እና ነጻ የሆነ የፍርድ ሂደት እንደማይካሄድ ይከሳሉ።በተጨማሪም የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የሞት ቅጣቶችን በስፋት የሚፈጽመው በተቃዋሚዎቹ እና በሕዝቡ ዘንድ ጭቆናን እና ፍርሃትን ለማንገስ ነው ይላሉ።ያጋሩ, ኢራን ‘ለእስራኤል በመሰለል’ የተከሰሰን ግለሰብ በሞት ቀጣች
  5. ከ 2 ሰአት በፊትአሜሪካ በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ አቅራቢያ የሚገኙ የኢራን የሚሳዔል ጣቢያዎችን ደበደበችየሆረሙዝ የባሕር ወሽመጥን የሚያሳይ የሳተላይት ምስልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የዓለም 20 በመቶ ነዳጅ የመተላለፍበት የሆርሙዝ ባሕር ወሽመጥየአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ላይ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ለማጥቃት የሚውሉ የኢራን የሚሳዔል ጣቢያዎችን መደብደቡን አስታወቀ።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በኤክስ ገፁ ላይ ባወጣው ጽሑፍ ጦሩ በኢራን የባሕር ዳርቻ በሚገኙት “ጠንካራ የኢራን የሚሳዔል ጣቢያዎች ላይ 5,000 ፓውንድ የሚመዝኑ ሰረስረው የሚገቡ ቦምቦችን ተጠቅሞ በተሳካ ሁኔታ ድብደባ ፈጽሟል” ሲል አስታውቋል።”በእነዚህ ቦታዎች ላይ የተተከሉት የኢራን ፀረ-መርከብ ክሩዝ ሚሳዔሎች በባሕረ ሰላጤው ውስጥ ላሉ ዓለም አቀፍ መርከቦች አደጋ ፈጥረዋል” ሲል የአሜሪካ ጦር ተናግሯል።ኢራን 20 በመቶ የሚሆነው የዓለም ነዳጅ የሚጓጓዝበትን የባሕር ወሽመጥ በመዝጋቷ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።ግዙፎቹ ቦምቦች አሜሪካ ባለፈው ዓመት በኢራን ውስጥ የሚገኙ ሦስት የኒውክሌር ጣቢያዎችን ስትደበድብ ከተጠቀመችባቸው ቦምቦች ጋር ተመሳሳይ ሊሆኑ ይችላሉ።እነዚህ ቦምቦች በአየር ወይም በመሬት ላይ በሚገኙ ዒላማዎችን መትተው አይፈነዱም። ከዚያ ይልቅ በጥልቀት የተቀበሩ እና የተጠናከሩ ጉድጓዶችን እና ዋሻዎችን ሰርስሮ በመግባት የማጥቃት አቅም አላቸው።ስድስት ሜትሮች ርዝመት ያለው ይህ ቦምብ ከመፈንዳቱ በፊት በግምት 61 ሜትሮች ወደ ውስጥ ዘልቆ መግባት ይችላል ተብሎ ይታመናል።ያጋሩ, አሜሪካ በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ አቅራቢያ የሚገኙ የኢራን የሚሳዔል ጣቢያዎችን ደበደበች
  6. ከ 3 ሰአት በፊትእስራኤል ሌሊቱን በቤይሩት የፈጸመችው ድብደባ ያደረሰው ውድመት በምሥልእስራኤል ሌሊቱን በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ላይ የፈጸመችው ጥቃትን ተከትሎ ስድስት ሰዎች ሲገደሉ 24 ደግሞ ቆስለዋል።ሊባኖስ ወደዚህ ግጭት ተስባ የገባችው ሄዝቦላህ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒን መገደል ተከትሎ የአጸፋ እርምጃ በሚል ሮኬቶችን እና ድሮኖችን መተኮሱን ተከትሎ ነው።እስራኤል በሄዝቦላህ ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ተደጋጋሚ የአየር ድበደባዎችን እየፈጸመች ሲሆን፣ ውስን የእግረኛ ጦርም ማሰማራቷን አስታውቃለች።በቤይሩት በሚገኝ ሕንጻ ላይ የተፈጸመን ጥቃት ተከትሎ ጥቁር ጭስ ታይቷልየፎቶው ባለመብት,Reutersበቤይሩት ባቾራ በሚባል አካባቢ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የደረሰውን ውድመት ተከትሎ በሕይወት የተረፉትን ለማዳን ሲረባረቡ ታይተዋልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በቤይሩት ባቾራ በሚባል አካባቢ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የደረሰውን ውድመት ተከትሎ በሕይወት የተረፉት ሰዎችን ለማዳን ሲረባረቡ ታይተዋልበቤይሩት ዙቃቅ አል-ብላት ዲስትሪክት የእስራኤል ጥቃትን ተከትሎ የደረሰውን ውድመት አንድ ሰው በረንዳ ላይ ቆሞ ሲመለከትየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በማዕከላዊ ቤይሩት ዙቃቅ አል-ብላት በተባለ ስፍራበማዕከላዊ ቤይሩት ዙቃቅ አል-ብላት ዲስትሪክት በጥቃት የወደመ ሕንጻየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በማዕከላዊ ቤይሩት ዙቃቅ አል-ብላት አካባቢ በጥቃት የወደመ ሕንጻያጋሩ, እስራኤል ሌሊቱን በቤይሩት የፈጸመችው ድብደባ ያደረሰው ውድመት በምሥል
  7. ከ 4 ሰአት በፊትኢራን ቴል አቪቭ ላይ የፈጸመችው ጥቃት በምሥልኢራን በእስራኤል ላይ ሌሊቱን በፈጸመችው የሚሳዔል ትቃት አንድ የ70 ዓመት ወንድ እና ሴት መሞታቸው ተሰምቷል። የደረሰውን ጥቃት የሚያሳዩ ምሥሎች ይፋ ሆነዋል።ሮይተርስ የዜና ወኪል የዐይን እማኝን ጠቅሶ እንደዘገበው ዛሬ ማለዳ በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ባቹራ በሚባል አካባቢ እስራኤል ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰምቷል።የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቴል አቪቭ ራማት ጋን ሰፈር የደረሰ የሚሳዔል ጥቃትን ተከትሎ በቦታው ተገኝተው ምላሽ ሰጥተዋልየፎቶው ባለመብት,Alexi J Rosenfeld via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቴል አቪቭ ራማት ጋን ሰፈር የደረሰ የሚሳዔል ጥቃትን ተከትሎ በቦታው ተገኝተው ምላሽ ሰጥተዋልየአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቴል አቪቭ ራማት ጋን ሰፈር የደረሰ የሚሳዔል ጥቃትን ተከትሎ በቦታው ተገኝተው ምላሽ ሰጥተዋልየፎቶው ባለመብት,Ilia Yefimovich via Getty Imagesከኢራን የተወነጨፉ ሚሳዔሎች በቴል አቪቭ ሰማይ ላይ ታይተዋልየፎቶው ባለመብት,Anadolu via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳዔሎች በቴል አቪቭ ሰማይ ላይ ታይተዋልያጋሩ, ኢራን ቴል አቪቭ ላይ የፈጸመችው ጥቃት በምሥል
  8. ከ 4 ሰአት በፊትኢራን የበቀል ጥቃት ለመፈጸም ስትዝት በእስራኤል የሚሳዔል ጥቃት ሁለት ሰዎችን ገድሏልበቴል አቪቭ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የደረሰ የሚሳዔል ጥቃትን ተከትሎ ምላሽ ለመስጠት ተገኝተዋልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesሦስተኛ ሳምንቱ ላይ በሚገኘው እና አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር በሚያደርጉት ጦርነት የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃቶች ቀጥለዋል። በኢራን እና በአጋሮቿ የሚሊሻ ቡድኖች የሚሰነዘሩ የአጸፋ ጥቃቶች ሌሊቱን ሙሉ የቀጠሉ ሲሆን፣ የሰዎች ሞትም ተመዝግቧል።
    • የኢራን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ተጽዕኖ ፈጣሪው የኢራን ጠቅላይ ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት ጸሐፊ አሊ ላሪጃኒ በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደላቸውን አረጋግጠዋል ። ላሪጃኒ ከጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ሞት ወዲህ ከተገደሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል አንዱ ናቸው።
    • የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ውስጥ የሔዝቦላህ ዒላማዎችን መደብደቡን ቀጥሏል። የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር በማዕከላዊ ቤይሩት በተፈጸሙ የእስራኤል ሁለት ጥቃቶች ቢያንስ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን እና ሌሎች 24 ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጿል።
    • የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አንድ ተተኳሽ የኢራንን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ቢመታም ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳልደረሰበት አስታውቋል።
    • የአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ አቅራቢያ የሚገኙ የኢራን የሚሳኤል ጣቢያዎችን መምታቱን አስታውቋል።
    • ዶናልድ ትራምፕ የኔቶን እና ሌሎች አጋሮችን ተችተዋል፤ ፕሬዚዳንቱ ቀደም ሲል ድጋፍ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም አሜሪካ በኢራን ጦርነት ላይ “ከእንግዲህ ወዲህ እርዳታ አትሻም ወይም አትፈልግም” ብለዋል።
    • በቴል አቪቭ የኢራን የሚሳዔል ጥቃትን ተከትሎ በ 70ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ አንድ ወንድና አንዲት ሴት ተገድለዋል።
    • የኢራን የጦር አዛዥ የላሪጃኒን ግድያ በመበቀል “ወሳኝ፣ የሚያሽመደምድ እና ጸጸት ላይ የሚጥል” ምላሽ እንደሚሰጡ ዝተዋል። ከጦሩ የተለየ ወታደራዊ አካል የሆነው የኢራን አብዮታዊ ዘብ የላሪጃኒን ሞት “ለመበቀል” ወደ ማዕከላዊ እስራኤል ሚሳዔሎችን ማስወንጨፉን ኤኤፍፒ ዘግቧል።
    ያጋሩ, ኢራን የበቀል ጥቃት ለመፈጸም ስትዝት በእስራኤል የሚሳዔል ጥቃት ሁለት ሰዎችን ገድሏል
  9. ከ 5 ሰአት በፊትበኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ዳግም ጥቃቶች ተፈጸሙበኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ዳግም ጥቃቶች ተፈጸሙየፎቶው ባለመብት,Reutersበኢራቅ ዋና ከተማ በባግዳድ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ አዲስ ጥቃት መፈጸሙ ተሰምቷል።ኤኤፍፒ እና የሮይተርስ የዜና ኤጀንሲዎች ረቡዕ ማለዳ በኤምባሲው አካባቢ ፍንዳታ እንደደረሰ ዘግበዋል።ኤጀንሲዎቹ የጸጥታ ምንጮችን እና በከተማው የሚገኙ የኤፍፒ ጋዜጠኞችን ጠቅሰው የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ መገኛ በሆነው አካባቢ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አቅራቢያ ፍንዳታ መስማታቸውን ገልጸዋል።ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የአሜሪካ ኤምባሲ በተደጋጋሚ ጊዜ ጥቃት ደርሶበታል።ያጋሩ, በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ዳግም ጥቃቶች ተፈጸሙ
  10. ከ 5 ሰአት በፊትየኢራን ጦር አዛዥ እስራኤል የደኅንነት ኃላፊው ላሪጃኒን መገደሏን ተከትሎ ‘ወሳኝ’ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወሰዱ ዛቱየኢራን ጦር አዛዥ አሚር ሃታሚየፎቶው ባለመብት,Anadolu via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የኢራን ጦር አዛዥ አሚር ሃታሚየኢራን ጦር አዛዥ አሚር ሃታሚ በእስራኤል የአየር ጥቃት የደኅንነት ኃላፊው አሊ ላሪጃኒን መገደላቸውን ተከትሎ “ወሳኝ” የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ ዛቱ።”ለወንጀለኛዋ አሜሪካ እና ደም የተጠማው የጽዮናውያን አገዛዝ በተገቢው ጊዜ እና ቦታ ወሳኝ፣ የሚያሽመደምድ፣ ጸጸት ውስጥ የሚጥል ምላሽ እንሰጣለን” ሲሉ ሃታሚ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል።የላሪጃኒ እና የሌሎች “ሰማዕታት ሞት እንበቀላለን” በማለት አክለዋል።ከኢራን ጦር ኃይል የተለየ ወታደራዊ ክፍል የሆነው እስላማዊው አብዮታዊ ዘብ የላሪጃኒ ሞትን “ለመበቀል” ወደ ማዕከላዊ እስራኤል ሚሳዔሎችን መተኮሱን የኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።የኢራን ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አሊ ላሪጃኒ ሰኞ ለማክሰኞ ሌሊት በእስራኤል በተፈጸመባቸው ጥቃት ከልጃቸው ጋር መገደላቸው ተነግሯል።ላሪጃኒ በኢራን መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት እና ከሟቹ ጠቅላይ መሪ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ካላቸው የአገሪቱ ተጽእኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች መካከል ቀዳሚው ናቸው።እስራኤል የላሪጃኒን መገደል ቀድማ ያሳወቀች ሲሆን፣ የመከላከያ ሚኒስትሯም ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣናትን እያደኑ ማጥፋታቸወን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።ያጋሩ, የኢራን ጦር አዛዥ እስራኤል የደኅንነት ኃላፊው ላሪጃኒን መገደሏን ተከትሎ ‘ወሳኝ’ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወሰዱ ዛቱ
  11. 17 መጋቢት 2026የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን በኢራን የሚካሄደውን ጦርነት ተቃውመው ሥልጣን ለቀቁጆ ኬንትየፎቶው ባለመብት,Bloomberg via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ጆ ኬንትየዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የፀረ ሽብርተኝነት ማዕከል ዳይሬክተር “በኢራን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በበጎ ህሊና መደገፍ አልችልም” በማለት ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባጋሩት መልዕክት አስታወቁ።ጆ ኬንት ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ባሳወቁበት ደብዳቤ “ኢራን በአገራችን ላይ ምንም ዓይነት ተጨባጭ ስጋት አልደቀነችም፣ ይህንን ጦርነት የጀመርነው በእስራኤል እና በአሜሪካ ባሏት ኃያል ደጋፊዎቿ ግፊት መሆኑ ግልጽ ነው” ብለዋል።ዶናልድ ትራምፕ ሦስት ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ይዘው የተነሷቸውን ፖሊዎች ደግፈው ከጎናቸው እንደቆሙ ያስታወሱት ጆ፣ አስከ 2025 በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ የተካሄዱት ጦርነቶች የአሜሪካውያንን ሕይወት የቀጠፉ እና የአገሪቱን ሃብት ያሟጠጡ መሆናቸውን ትራምፕ ይረዱ እንደነበር ሲሉ አስታውሰዋል።“በ11 ውጊያዎች ላይ እንደተሳተፈ የቀድሞ ወታደር እና በእስራኤል በተፈበረከ ጦርነት ውድ ሚስቱን እንዳጣ ባል፣ ቀጣዩ ትውልድ ለአሜሪካ ጥቅም በማያስገኝ እና የሚከፈለው ዋጋ አሳማኝ ወዳልሆነ ጦርነት መሄዱን መደገፍ አልችልም” በማለት ጦርነቱን ተቃውመዋል።አሁን ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው የለቀቁት ጆ ኬንት በትራምፕ ተመርጠው በአሜሪካ ሴኔት ለቦታው ብቁ ናቸው ተብለው ተቀባይነት ያገኙት ባለፈው ዓመት ሐምሌ ነበር። የኢራንን ጦርነት ተቃውመው ሥልጣን የለቀቁት የአሜሪካው ከፍተኛ ባለሥልጣን ማን ናቸው?ያጋሩ, የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን በኢራን የሚካሄደውን ጦርነት ተቃውመው ሥልጣን ለቀቁ
  12. 17 መጋቢት 2026በሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ አውሮፓውያን ፊታቸውን ያዞሩባቸው ትራምፕትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዝዳንት ትራምፕ በፋርስ ባሕረ ሰላጤው የሆርሙዝ ሰርጥ የሚተላለፉ ግዙፍ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ለመጠበቅ አጋሮቻቸው እንዲተባበሩ ያቀረቡት ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ ባለማግኘቱ ተቆጥተዋል።ምዕራባውያን ወዳጆቻቸው ይህ የትራምፕ ጥሪ አሜሪካ ከእስራኤል ጋር በመሆን በኢራን ላይ ወደ ከፈተችው ጦርነት የሚያስገባቸው ሊሆን እንደሚችል በማሰብ የባሕር ኃይላቸውን ወደ ጦርነት ቀጣናው ለመላክ አልፈቀዱም።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጦርነት ተከትሎ ከፍተኛ የነዳጅ ምርት የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ሰርጥ በመዘጋቱ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል በአገራት ምጣኔ ሀብት ላይም ተጽእኖው እየተንጸባረቀ ነው።የአሜሪካ የቅርብ አጋሮች የሆኑት ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ እና ጀርመንን ጨምሮ ግሪክ፣ አውስትራሊያ፣ ስፔን፣ ጃፓን እና ሌሎችም በሆርሙዝ ሰርጥ የሚተላለፉ መርከቦችን ደኅንነት ለመጠበቅ በሚል ትራምፕ ባዘጋጁት ዕቅድ ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው በመግለጽ መልስ ሰጥተዋል።በአውሮፓ ታላላቅ ወታደራዊ ኃይል ያላቸው አገራቱ ምንም እንኳን የነዳጅ እንቅስቃሴው መስተጓጎል ቢጎዳቸውም በዚህ ምክንያት ግን ከኢራን ጋር ወደ ቀጥታ ግጭት የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው አሳውቀዋል። ይህም ሦስት ሳምንት ያስቆጠረው ጦርነት የአሜሪካ እና የእስራኤል ጉዳይ መሆኑን በተዘዋዋሪ መልዕክት ያስተላለፉበት ነው።የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር አገራቸው ሆርሙዝን በመጠበቅ ሰበብ ወደ ጦርነት ተስባ እንደማትገባ ሲጠቅሱ፣ የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ደግሞ ትራምፕ አጋሮቻቸው ካልተባበሯቸው ለኔቶ መጥፎ ሁኔታ ይፈጠራል በማለት ለሰጡት ማስጠንቀቂያ “ኔቶ የመከላከያ ስምምነት እንጂ የጣልቃ ገብነት ትብብር አይደለም” ሲሉ መከላከያ ሚኒስትራቸው ደግሞ “የእኛ ጦርነቱ አይደለም፤ እኛም አልጀመርነውም” በማለት እራሳቸውን አርቀዋል።ነገር ግን ትራምፕ ሰኞ ዕለት እንደተናገሩት “በርካታ አገራት” ጥሪያቸውን ተቀብለው ከጎናቸው እንደሚቆሙ እንደገለጹላቸው ጠቁመው፤ አሜሪካ ስትከላከላቸው የቀዩ አገራት ለቀረበላቸው ጥሪ ምላሽ ካልሰጡ “ምስጋና ቢስነት ነው” ብለዋል።አሜሪካ ሆርሙዝ ሰርጥን በመጠበቅ ከጎኔ ይቆማሉ ብላ የምትጠብቃቸው የአውሮፓ ባለሥልጣናት የኔቶ አባል አገራት ትብብር እራስን የመከላከል ዓላማ መሆኑን አጽንኦት እየሰጡ ነው።ኢራንን እና የኒውክሌር ፕሮግራሟን ዒላማ ማድረግ ግን አሜሪካ እና እስራኤል “በምርጫ የገቡበት ጦርነት ነው” በማለት አገራት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት መግባት እንደማይፈልጉ ግልጽ አድርገዋል።በኔቶ በኩል ዩክሬንን ከሩሲያ ጋር በምታደርገው ጦርነት እየደገፏት የሚገኙት የአውሮፓ አገራት በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረውን የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ለመሸፈን በሩሲያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ትራምፕ በማንሳታቸው ቅሬታቸውን ገልጸዋል።ያጋሩ, በሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ አውሮፓውያን ፊታቸውን ያዞሩባቸው ትራምፕ
  13. 17 መጋቢት 2026እስራኤል የኢራን መሪዎችን “ማደን እቀጥላለሁ” አለችየእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝየፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝየእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ በሰጡት መግለጫ የአገሪቱ ጦር ኢራን መሪዎችን ማደኑን እንዲቀጥል ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትያናሁ ትዕዛዝ መሰጠቱን ተናገሩ።እስራኤል ሰኞ ሌሊት በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ከፍተኛ የኢራን የደኅንነት ኃላፊ የሆኑትን አሊ ላሪጃኒን መግደሏን ገልጻለች። ባለሥልጣኑ የተገደሉት ከልጃቸው ጋር በተደበቁበት አፓርትመንት ውስጥ እንደሆነ የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።በተጨማሪም የእስራኤል ጦር ‘ባሲጅ’ የተባለው የኢራን ታጣቂ ኃይል አዛዥ የሆኑትን ጎላምሬዛ ሶሊማኑን መግደሏን አስታውቃለች። የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያለውን ታጣቂ ቡድን ላለፉት ስድስት ዓመታት ሲመሩ ቆዩትን ወታደራዊ አዛዥ ተገድለዋል ብሏል።አዛዡ የሚመሩት ታጣቂ ቡድን ታኅሣሥ ላይ የነበረውን ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ለማፈን በተወሰደው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበት ዘመቻ ውስጥ ተሳትፎ ነበረው።የመከላከያ ሚኒስትሩ ካትዝ፤ የኢራኑ ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣን መገደላቸውን ባስታወቁበት መግለጫ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና እኔ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የኢራንን የሽብር እና የጭቆና አገዛዝ አመራሮች ማደኑን እንዲቀጥል ትዕዛዝ ሰጥተናል” ብለዋል።“የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን አመራሮች በከፍተኛ መጠን ስለ መለዋወጣቸውን ሲናገሩ ነበር … ከቀሩት ከፍተኛ አመራሮች መካከል ሁለቱ ስለተገደሉ የአመራሮች መለዋወጡ እንደቀጠለ መረጃ እናደርሳቸዋለን” ሲሉ ተናግረዋል።እስራኤል ይሄንን ብትልም እስካሁን ድረስ ላሪጃኒ እና ሶሎማኒ ስለመገደላቸው ከኢራን በኩል ማረጋገጫ አልተሰጠም።የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ቢገደሉም መንግሥቱ ባለበት እንዲቀጥል እንዴት ቻለ የሚለውን ለመረዳር ተጨማሪ እዚህ ያንብቡ ➤ ኢራን መሪዎቿን ባጣች ጊዜ እንዴት ሳትንኮታኮት ጸንታ መቀጠል ቻለች?ያጋሩ, እስራኤል የኢራን መሪዎችን “ማደን እቀጥላለሁ” አለች
  14. 17 መጋቢት 2026የባሕረ ሰላጤው አገራት የኢራን የመሣሪያ አቅም ሳይዳከም አሜሪካ ጥቃቷን እንዳታቆም እየገፉ ነው ተባለየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ውስጥ የተፈጸመ ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Reutersየመካከለኛው ምሥራቅ አረብ አገራት፤ አሜሪካ በባሕረ ሰላጤው የነዳጅ መተላlፊያ መስመር እና በዚሁ ላይ በተመሠረተው ኢኮኖሚ ላይ አደጋ የደቀነችው ኢራን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት እንዳታቋርጥ እየወተወቱ መሆኑ ተዘገበ።የዜና ወኪሉ ሮይተርስ የባሕረ ሰላጤውን እና ምዕራባውያን ምንጮችን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ እንዳመለከተው አሜሪካ የቀጣናው አገራት ጦርነቱን እንዲቀላቀሉ ግፊት ስታደርግ ነበር።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ለማግኘት እና በአገር ውስጥ ያላቸውን ድጋፍ ለማጠናከር ሲሉ የቀጣናው አገራት ዘመቻውን እንዲደግፉ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ሦስት ምንጮች ተናግረዋል ተብሏል።የባሕረ ሰላጤው አረብ አገራት መጀመሪያ ላይ አሜሪካ ከኢራን ጋር ጦርነት ውስጥ እንድትገባ ጥያቄ ባያቀርቡም በቴህራን ከደረሰባቸው ጥቃት በኋላ ዋሽንግተን ወደ ኋላ እንዳትል ግፊት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።ኢራን በፈጸመቻቸው ጥቃቶች በስድስት የቀጣናው አገራት ውስጥ የሚገኙ አየር ማረፊያዎች፣ ወደቦች፣ የነዳጅ መሠረተ ልማቶች እንዲሁም የንግድ ማዕከላት ተመትተዋል። በአገራቱ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች እና ኤምባሲዎችም የጥቃት ዒላማ ሆነዋል።ኢራን በእነዚህ ጥቃት አቅሟ ምን ያህል እንደሆነ አሳይታለች። የባሕረ ሰላጤው አገራት በአንጻሩ ኢራን ከፍተኛ የጦር መሣሪያ የማምረት አቅሟን ይዛ ከቀጠለች ውጥረት በተነሳ ቁጥር የቀጣናውን የኢነርጂ መስመር አደጋ ላይ ትጥላለች የሚል ስጋት እንደገባቸው የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል።ያጋሩ, የባሕረ ሰላጤው አገራት የኢራን የመሣሪያ አቅም ሳይዳከም አሜሪካ ጥቃቷን እንዳታቆም እየገፉ ነው ተባለ
  15. 17 መጋቢት 2026እስራኤል የኢራን ቁልፍ የደኅንነት ባለሥልጣን የሆኑት አሊ ላሪጃኒን መግደሏን ተናገረችየኢራን ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አሊ ላሪጃኒ በእስራኤልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አሊ ላሪጃኒ በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ አስታወቁ።ሌሊቱን በተፈጸመ ጥቃት መገደላቸው የተነገረው ላሪጃኒ በኢራን መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት ከነበራቸው መሪዎች መካከል አንዱ ናቸው።የባለሥልጣኑ በእስራኤል ዒላማ መሆን እየተነገረ በነበረበት ጊዜ ቢያንስ ሁለት የኢራን መገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣናትን ጠቅሰው ግለሰቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ መግለጫ ይሰጣሉ ብለው ነበር።አንድ የእስራኤል ወታደራዊ ባለሥልጣን አሊ ላሪጃኒ በእስራኤል መከላከያ ዒላማ መደረጋቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።አሊ ላሪጃኒ በኢራን ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት የሟቹ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ተወካይ እና ዋና ፀሐፊ ሆነው የተሾሙት ባለፈው ዓመት ነሐሴ በፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ነበር።ለ12 ዓመታት የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ የነበሩት ላሪጃኒ “ለዘብተኛ ወግ አጥባቂ” እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፤ በተጨማሪም በኢራን መገናኛ ብዙኃን የጠቅላይ መሪው አማካሪ እንደሆኑ ይጠቀሱ ነበር።እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት መገደላቸው የተነገረው ታዋቂው ኢራናዊ ፖለቲከኛ የፓርላማው አፈ ጉባዔ ከመሆናቸው በፊት ኢራንን ከምዕራባውያን ጋር እያወዛገበ በሚገኘው የኒውክሌር ድርድር ላይ አገራቸውን ወክለው ተደራዳሪ ነበሩ።በኢራን ፖለቲካ ውስጥ አሊ ላሪጃኒ ብቻ ሳይሆኑ ወንድማቸውም ከፍተኛ ተሰሚነት አላቸው። ወንድማቸው ሴዴጌ ላሪጃኒ በኢራን ሁለት ኃያል ምክር ቤቶች የበላይ አካል የሆነው ጉባዔ ሊቀ መንበር ናቸው።ያጋሩ, እስራኤል የኢራን ቁልፍ የደኅንነት ባለሥልጣን የሆኑት አሊ ላሪጃኒን መግደሏን ተናገረች
  16. 17 መጋቢት 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ጦርነት ምክንያት የቻይናው ጉዟቸውን አራዘሙትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ሺፒንግየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ በኢራን ጦርነት ምክንያት ከሁለት ሳምንት በኋላ ሊያደርጉት የነበረውን ተጠባቂውን የቻይና ጉዟቸውን ለአንድ ወር በሚጠጋ ጊዜ ለማራዘም ማቀዳቸውን ተናገሩ።ፕሬዝዳንቱ በዋይት ሐውስ በጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ጉዞውን “በአንድ ወር ወይም እንዲያ አካባቢ ለማዘግየት ጥያቄ አቅርበናል” ብለዋል።ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ሺፒንግ ይገናኙበታል ተብሎ የሚጠበቀው ጉብኝት ከመጋቢት 22 እስከ 24/2018 ዓ.ም. እንዲካሄድ ቀጠሮ ተይዞለታል።እንደ ትራምፕ ገለጻ ጉዞውን ማራዘም ውሳኔ ላይ የተደረሰው ከእስራኤል ጋር በመሆን ኢራን ላይ የከፈቱትን ጦርነቱን ለመምራት አገር ውስጥ መሆን አስፈላጊ በመሆኑ ነው።“በጣም ቀላል ነው። ጦርነት እያካሄድን ነው። እዚህ መሆኔ አስፈላጊ ይመስለኛል” ሲሉ ተናግረዋል። ትራምፕ እዚህ ውሳኔያቸው ውስጥ “ምንም ማታለል” እንደሌለበት አጽንኦት የሰጡ ሲሆን የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጋር መገናኘት እንደሚፈልጉም አክለዋል።ትራምፕ ይህንን ያሉት ከብሪታኒያው ጋዜጣ ፋይናንሻል ታይምስ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፤ ቻይና ሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲከፈት የማታግዝ ከሆነ ጉብኝታቸው ሊያራዝሙ እንደሚችሉ ከተናገሩ በኋላ ነው።በሁለቱ ግዙፍ የዓለም ኢኮኖሚዎች መካከል ያለው ፍትጊያ በኢራን ጦርነት ምክንያት ተባብሷል። የኢራን የኢነርጂ ኤክስፖርት ዋነኛ ገዢ የሆነችው ቻይና አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ ከፈቱትን ጥቃት ተቃውማለች።የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በበኩላቸው “ከፕሬዝዳንት ትራምፕ የቻይና ጉብኝት ቀን እና ተያያዥ ጉዳዮችን” በተመለከተ ቤይጂንግ እና ዋሽንግተን እየተነጋገሩ መሆኑን ማክሰኞ ዕለት ገልጸዋል።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ጦርነት ምክንያት የቻይናው ጉዟቸውን አራዘሙ
  17. 17 መጋቢት 2026የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአገሪቱ ቡድን ጨዋታዎች ሜክሲኮ ውስጥ እንዲካሄዱ እየተደራደረ መሆኑን ገለጸየዓለም እግር ኳስ ዋንጫየፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን በደኅንነት ስጋት ምክንያት የአገሩ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ወደ ሜክሲኮ እንዲዛወሩ ለማድረግ ከፊፋ ጋር እየተደራደረ መሆኑን አስታወቀ።የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት መህዲ ታጅ በኤክ ገጻቸው ባጋሩት ልጥፍ “ትራምፕ የኢራን ብሔራዊ ቡድንን ደኅንነት ማስጠበቅ እንደማይችሉ በግልጽ በተናገሩበት ሁኔታ በእርግጠኝነት ወደ አሜሪካ አንጓዝም” ብለዋል።አክለውም “በአሁኑ ሰዓት የኢራንን የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ሜክሲኮ ውስጥ ለማድረግ ከፊፋ ጋር እየተደራደርን ነው” ሲሉ ጽፈዋል።አሜሪካ ከእስራኤል ጋር በመሆን ቴህራን ላይ ጥቃት መክፈቷን ተከትሎ፤ ባለፈው ሳምንት የኢራን ስፖርት ሚኒስትር የአገሪቱ ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው መሳተፍ እንደማይችል ተናግረው ነበር።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢራን የዓለም ዋንጫውን ለመሳተፍ እንደምትችል ጠቁመው፤ ነገር ግን “ለራሳቸው ሕይወት እና ደኅንነት ሲባል እዚህ መምጣታቸው ተገቢ አይደለም” የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።በምድብ ሁለት ውስጥ ያለው የኢራን ብሔራዊ ቡድን ሎስ አንጀለስ ውስጥ ጨዋታዎች ያሉት ሲሆን፣ አንድ ጨዋታ ደግሞ ሲያትል ውስጥ እንዲያደርግ ድልድል ወጥቷል።ያጋሩ, የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአገሪቱ ቡድን ጨዋታዎች ሜክሲኮ ውስጥ እንዲካሄዱ እየተደራደረ መሆኑን ገለጸ
  18. 17 መጋቢት 2026እስራኤል የዜጎቼ ደኅንነት ሳይረጋገጥ የሊባኖስ ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያቸው አይመለሱም አለችቤይሩት ውስጥ በተከፈተው ጥቃት ተፈናቅለው የፕላስቲን መጠለያ ውስጥ የሚኖሩ አዛውንትየፎቶው ባለመብት,WAEL HAMZEH/EPA/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,ቤይሩት ውስጥ በተከፈተው ጥቃት ተፈናቅለው የፕላስቲን መጠለያ ውስጥ የሚኖሩ አዛውንትእስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በሚገኙ የድንበር አካባቢዎች ያሉ ዜጎቿ ደኅንነት እስከሚረጋገጥ ድረስ ሊባኖስ ውስጥ በከፈተችው ወታደራዊ ዘመቻ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደ መኖሪያቸው እንደማይመለሱ ተናገረች።ዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ጣልያን በበኩላቸው በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ ሊባኖስ ውስጥ የተከፈተው የእረኛ ጦር ጥቃት “አስከፊ ሰብአዊ መዘዝ” እንደሚኖረው አስጠንቅቀዋል።የዓለም የፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) መረጃ እንደሚያሳየው በሄዝቦላህ ጥቃት የተሰነዘረባት እስራኤል የከፈተችውን ዘመቻ ተከትሎ የተፈናቀሉ ሰዎች ብዛት ወደ አንድ ሚሊዮን ገደማ ተጠግቷል።የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ የሆኑት ሌተናንት ኮሎኔል ናዳቭ ሾሻኒ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ወታደሮች ሊባኖስ ውስጥ “አዲስ ስፍራዎች” ላይ የእግረኛ ጦር ጥቃት መፈጸም መጀመራቸውን እንደተናገሩ የዜና ወኪሉ ሮይተርስ ዘግቧል። አዲሱን ጥቃት “ውሱን እና ዒላማዎች ላይ ያተኮረ” ሲሉ ገልጸውታል።“ባለፉት ሁለት ሳምንታት በደቡባዊ ሊባኖስ ውስን ዒላማ ያለው የእግረኛ ጦር ዘመቻ ከፍተናል፤ [ዘመቻው] ስጋቱን ከድንበር የመግፋት እና የሰሜናዊ እስራኤል ነዋሪዎችን የረጅም ጊዜ ደኅንነት የማረጋገጥ ዓላማ አለው” ብለዋል።የሊባኖስ ጤና ሚኒስትር እንደሚገልጸው፤ በእስራኤል ጥቃቶች 880 ሰዎች ተገድለዋል። ሚኒስቴሩ ይህ ቁጥር በንጹኃን ላይ ብቻ የደረሰ ጉዳት ስለመሆኑ አላብራራም።ምዕራባውያን አገራት በበኩላቸው ባወጡት የጋራ መግለጫ፤ እስራኤል እና ሊባኖስ ድርድር በማድረግ “ተጨባጭ የፖለቲካ መፍትሔ” ላይ እንዲደርሱ አሳስበዋል። ሊባኖስ ውስጥ ያለው ሰብአዊ ሁኔታም “እጅግ አሳሳቢ” እንደሆነ ገልጸዋል።“ከፍተኛ የሆነው የእስራኤል የእግረኛ ጦር ጥቃት አስከፊ ሰብአዊ መዘዝ ይኖረዋል፤ ወደ ተራዘመ ጦርነትም ሊያመራ ይችላል። መቀልበስ አለበት” ብለዋል።የእስራኤል ጥቃት ከተጀመረ አንስቶ የተፈናቀሉ ነዋወዎች ብዛት አንድ ሚሊዮን ተጠግቷልየፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,የእስራኤል ጥቃት ከተጀመረ አንስቶ የተፈናቀሉ ነዋወዎች ብዛት አንድ ሚሊዮን ተጠግቷልከእስራኤል ጋር በሚጎራበተው ኪያም የተባለ የደቡባዊ ሊባኖስ ስፍራ የተፈጸመ ጥቃትየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ከእስራኤል ጋር በሚጎራበተው ኪያም የተባለ የደቡባዊ ሊባኖስ ስፍራ የተፈጸመ ጥቃትበደቡባዊ ቤይሩት የተፈጸመ ጥቃትየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በደቡባዊ ቤይሩት የተፈጸመ ጥቃትየእስራኤል ወታደሮች በሊባኖስ ድንበር አቅራቢያየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የእስራኤል ወታደሮች በሊባኖስ ድንበር አቅራቢያያጋሩ, እስራኤል የዜጎቼ ደኅንነት ሳይረጋገጥ የሊባኖስ ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያቸው አይመለሱም አለች
  19. 17 መጋቢት 2026የእስያ አገራት ነዳጅ ለመቆጠብ የሥራ ቀናትን ከመቀነስ አንስቶ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነውነዳጅ ማደያ አካባቢ የተሰለፉ ሞተር ሳይክሎችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesእስያዊቷ አገር ሲሪ ላንካ፤ በኢራን ጦርነት ምክንያት ሊፈጠር የሚችል የነዳጅ እጥረትን ለመቋቋም በየሳምንቱ ረቡዕ ዕለት እንደ የሕዝብ በዓል ተቆጥሮ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እንዲዘጉ ወሰነች። ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችም ምን ያህል ነዳጅ መግዛት እንደሚችሉ የሚወስን የራሽን ካርድ እንዲይዙ ተደርጓል።የሲሪ ላንካ ፕሬዝዳንት አኑራ ኩማራ ዲሳናያኬ ሰኞ ዕለት በተደረገ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ “ለከፋው ነገር መዘጋጀት አለብን፤ ነገር ግን ጥሩ ነገር እንደሚመጣ ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።ሲሪ ላንካ ይህንን እርምጃ የወሰደችው በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠር በርሜል ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋቱን ተከትሎ ሌሎች የእስያ አገራት የቁጠባ ውሳኔዎችን ካሳለፉ በኋላ ነው።ባለፈው ዓመት በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ካለፈው ነዳጅ እና ጋዝ ውስጥ 90 በመቶ የሚጠጋው የደረሰው ወደ እስያ ነው።ሌሎችም የእስያ አገራት በጦርነቱ ምክንያት የነዳጅ እጥረት እንዳይፈጠር በመስጋት እርምጃዎችን ወስደዋል።ምያንማር – የግል ተሽከርካሪዎች እንዲንቀሳቀሱ የሚፈቀድላቸው አንድ ቀን እያለፉ ነው። በየትኛው ቀን የቱ ተሽከርካሪ ይንቀሳቀሳል የሚለው የሚወሰነው በሰሌዳ ቁጥር ነው።ባንግላዴሽ – ነዳጅ እና ኤሌክትሪክ ለመቆጠብ ሲባል እስከ ኢድ አልፈጥር ድረስዩኒቨርሲቲዎች ተዘግተዋል። በመላ አገሪቱ መብራት የሚጠፋባቸው ቀናት እንደሚኖሩም ተገልጿል።ፊሊፒንስ – የመንግሥት ሠራተኞች ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን ከቤት እንዲሰሩ ታዝዘዋል። የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ፈርዲናንድ ማክሮስ ጁኒየር የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ወሳኝ ያልሆኑ ጉዞዎችን እንዳያደርጉ ከልክለዋል።ታይላንድ – የዜጎችየአየር ማቀዝቀዣ አጠቃቀም እንዲቀንስ ሲባል ነዋሪዎች ከሱፍ ይልቅ እጅጌ ጉርድ ልብሶችን እንዲያደርጉ አሳስባለች።ቬትናም – ነዳጅ መቆጠብ እንዲቻል ዜጎች ይበልጥ ቤታቸው መዋልን እንዲያዘወትሩ በአጽንኦት አሳስባለች። ሕዝቡ “አላስፈላጊ ሲሆን የግል መኪና ጠቀምን እንዲገድብ” እንዲሁም “ሳይክል እንዲነዱ፣ ጋሪ እንዲጠቀሙ እንዲሁም በሕዝብ ትራንስፖርት እንዲገለገሉ” ጥሪ ቀርቧል።ያጋሩ, የእስያ አገራት ነዳጅ ለመቆጠብ የሥራ ቀናትን ከመቀነስ አንስቶ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው
  20. 17 መጋቢት 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ ለማገዝ ጉጉት አልታየባቸውም ያሏቸውን አገራት ወቀሱየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,EPAየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን በተዘጋው የሆርሙዝ ሰርጥ በኩል የሚያልፈውን ነዳጅ ለማጀብ የጦር መርከቦቻቸውን እንዲልኩ ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ ያደረጉን ምዕራባውያን አጋሮቻቸውን በምስጋና ቢስነት ወቀሱ።ትራምፕ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደ ዩናይትድ ኪንግደም እና የኔቶ አባላት ያሉ አጋሮች በጦርነቱ ከአሜሪካ ጋር ለመሰለፍ አንገራግረዋል ሲሉ ተችተዋል። በተለይም ዩናይትድ ኪንግደም ጦርነቱን በተመለከተ ባሳየችው አቋም “እጅግ መገረማቸውን” ተናግረዋል።ትራምፕ፤ “ከሁለት ሳምንት በፊት ‘ለምን ተጨማሪ መርከቦችን አትልኩም’ አልኩ። [የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር] እውነትም ማድረግ አልፈለገም ነበር” ሲሉ የዩናይትድ ኪንግደሙን መሪ ኪር ስታርመር ወቅሰዋል።“አካባቢው ላይ ፈንጂ የሚቀርብ መርከብ እንዳላቸው ይነግሩናል፤ ማድረግ ግን አይፈልጉም፤ ይሄ መጥፎ ነው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በዩናይትድ ኪንግደም “ደስተኛ አይደለሁም” ሲሉም ተደምጠዋል። “ሊሳተፉ እንደሚችሉ አስባለሁ፤ ነገር ግን በጉጉት መሳተፍ አለባቸው” ብለዋል።በአሜሪካ እና እስራኤል ጦርነት የተከፈተባት ኢራን ከዓለም ነዳጅ 20 በመቶ ገደማው የሚተላለፍበትን የሆርሙዝ ሰርጥን ዘግታለች። ሊያልፉ የሞከሩ መርከቦች ላይም ጥቃት ተፈጽሟል።ወሳኙ መተላለፊያ እንዲከፈት የሚደረገውን ጥረት ቢያንስ አምስት አገራት ይቀላቀላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ትራምፕ ተናግረው ነበር። ጀርመን፣ ስፔን እና ጣልያንን ጨምሮ በርካታ የአሜሪካ አጋር አገራት አሁን ወደ ሰርጡ የጦር መርከብ የመላክ እቅድ እንደሌላቸው ተናግረዋል።ትራምፕ ትናንት በዋይት ሀውስ ባደረጉት ንግግር አገራት እገዛ ለማድረግ መንገድ ላይ ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። የትኛዎቹ አገራት ድጋፍ እንደሚደርጉ ባይጠቅሱም፤ በቅርቡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይገልጻል ብለዋል።“የተወሰኑ አገራት [እገዛ ለማድረግ] ጉጉት አላቸው፤ የተወሰኑት ደግሞ የላቸውም” ሲሉ ተናግረዋል። “አንዳንድ አገራትን ለብዙ፣ ብዙ ዓመታት አግዘናቸዋል፤ ከመጥፎ የውጪ አካል ጠብቀናቸዋል፤ እናም ግን [እኛን ለማገዝ] ጉጉት አልነበራቸውም። ምን ያህል ጓጉተዋል የሚለው ለእኔ ዋጋ አለው” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ ለማገዝ ጉጉት አልታየባቸውም ያሏቸውን አገራት ወቀሱ