የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን የአገራቸው የስለላ ሚኒስትር ኢስማኢል ኻቲብ “የፈሪ ግድያ” ባሉት በእስራኤል በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸውን አረጋገጡ። ፕሬዝዳንቱ በእስራኤል በተፈጸሙት በኻቲብ እና በሌሎችም የባለሥልጣኖቻቸው ግድያ ማዘናቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 8 ሰአት በፊትየኢራን ሴት እግር ኳስ ተጨዋቾች የአውስትራሊያ ጥገኝነትን ትተው ወደ አገራቸው ጉዞ ጀመሩኢራናውያኑ እግር ኳስ ተጫዋቾችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ኢራናውያኑ እግር ኳስ ተጫዋቾችለውድድር ወደ አውስትራሊያ ተጉዘው ከነበሩት የኢራን ሴት ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን አባላት መካከል እዚያው በጥገኝነት ለመቆየት ፍላጎት የነበራቸው አምስት ተጫዋቾች ሃሳባቸውን ቀይረው ከቀሪው የቡድኑ አባላት ጋር ወደ አገራቸው ለመመለስ ጉዞ ጀመሩ።ወደ አገራቸው ለመመለስ ከአውስትራሊያ በማሌዢያ እና በኦማን በኩል ወደ ቱርክ የደረሱት ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾቹ፤ በአውቶብስ በድንበር በኩል ወደ ኢራን ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።በእስያ ዋንጫ የመክፍቻ ጨዋታ ላይ የአገራቸው ብሔራዊ መዝሙር በሚዘመርበት ጊዜ ዝም በማለታቸው የበቀል ቅጣት ሊጠብቃቸው እንደሚችል በመስጋት በርካታ የቡድኑ አባላት መጀመሪያ ላይ በአውስትራሊያ ለመቆየት የሚስችላቸውን የሰብአዊነት ከለላ ቪዛ ለማግኘት ፈልገው ነበር።በዚህም ምክንያት ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የአገራቸው ባለሥልጣናት ተጫዋቾቹን “ከሃዲዎች” በማለት ወቅሰዋቸው ነበር። በኋላ ላይ ግን የተደረገባቸውን ጫና ተቋቁመው ወደ አገራቸው ለመመለስ በመወሰናቸው “የጠላትን ዕቅድ” በማክሸፍ እያወደሷቸው ነው።የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ግን ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾቹ የጥገኝነት ጥያቄያቸውን ለመቀልበስ የተገደዱት ኢራን ውስጥ ባሉ በቤተሰቦቻቸው ላይ ጉዳት እንደሚደርስ ማስፈራሪያ እና ጫና ስለተደረገባቸው ነው ይላሉ።ከብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች መካከል ሁለቱ ብቻ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ ወደ አገራቸው ሳይመለሱ ቀርተዋል።ያጋሩ, የኢራን ሴት እግር ኳስ ተጨዋቾች የአውስትራሊያ ጥገኝነትን ትተው ወደ አገራቸው ጉዞ ጀመሩ
  2. 18 መጋቢት 2026የኢራን ፕሬዝዳንት የስለላ ሚኒስትሩን መገደል አረገገጡእስራኤል ትናንት ሌሊት በፈጸመችው ጥቃት የስለላ ሚስትሩ ኢስማኢል ኻቲብን (መሃል) መግደሏን አስታውቃ ነበርየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,እስራኤል ትናንት ሌሊት በፈጸመችው ጥቃት የስለላ ሚስትሩ ኢስማኢል ኻቲብን (መሃል) መግደሏን አስታውቃ ነበርኢራን የስለላ ሚኒስትር ኢስማኢል ኻቲብ መገደላቸውን የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን አረጋገጡ።እስራኤል ትናንት ምሽት በፈጸመችው ጥቃት ከፍተኛ የደኅንነት ኃላፊ የሆኑትን ኻቲብን መግደሏን ገልጻ ነበር።የኢራኑ ፕሬዝዳንት ከሰዓታት በኋላ በኤክስ ገጻቸው በሰፈሩት ጽሁፍ፤ የስለላ ሚኒስትሩን እና ሌሎች ኃላፊዎች “የፈሪ ግድያ” እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋል።ፕሬዝዳንቱ “ውድ ባልደረቦቼ ኢስማኢል ኻቲባ፣ አሊ ላሪጃኒ እና አዚዝ ናስርዛዴህ እንዲሁም የተወሰኑ የቤተሰቦች አባላት እና አብረዋቸው የነበሩ ቡድኖች ላይ የተፈጸመው የፈሪ ግድያ ሐዘን ላይ ጥሎናል” ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ የጠቀሷቸው የኢራን ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አሊ ላሪጃኒ በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት ከትናንት በስቲያ ሌሊት ነበር።የቀድሞው መከላከያ ሚኒስትር አዚዝ ናስርዛዴህ ደግሞ በመጀመሪያው ቀን ጥቃት የጠቅላይ መሪው አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ጋር ከተገደሉ ወታደራዊ አመራሮች መካከል ናቸው።ያጋሩ, የኢራን ፕሬዝዳንት የስለላ ሚኒስትሩን መገደል አረገገጡ
  3. 18 መጋቢት 2026በኢራን የሚገኘው የዓለም ግዙፉ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ስፍራ ጥቃት ተፈጸመበትየኢራን የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበኢራን ደቡብ ፓርስ የጋዝ ማምረቻ ስፍራ የሚገኘው የፔትሮኬሚካል ተቋም የአየር ድብደባ እንደተፈጸመበት ከእስላማዊው አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያለው ታስኒም የዜና ወኪል ዘገበ።ኳታር፤ እስራኤል በተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ስፍራው ላይ የፈጸመችውን ጥቃት “አደገኛ እና ኃላፊነት የጎደለው” ስትል ኮንናለች።የታስኒም ዘገባ እንደሚያመለክተው ጥቃቱ የተፈጸመው ዛሬ ረፋድ አካባቢ ነው። ከፊል ይፋዊው ፋርስ የዜና ወኩል በበኩሉ በቴሌግራም ገጹ ባወጣው ማስጠንቀቂያ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻው በእሳት መያያዙን ገልጿል። የእሳት እና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በስፍራው እንደሚገኙም ጠቅሷል።በዓለም ትልቁ በሆነው የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ስፍራ ደቡብ ፓርስ ውስጥ የኳታር እና ኢራን ማምረቻ ተቋማት ይንቀሳቀሳሉ።ኳታር በመግለጫዋ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻው ስፍራ ላይ ጥቃት የተፈጸመው በእስራኤል እንደሆነ የገለጸች ሲሆን፣ ድርጊቱንም “አደገኛ እና ኃላፊነት የጎደለው” ስትል አውግዛለች።የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ማጅድ አል አንሳሪ፤ በኢነርጂ መሠረተ ልማት ላይ የሚፈጸም ጥቃት “የዓለም የነዳጅ ደኅንነት ላይ ስጋት እንደሚደቅን” ተናግረዋል።“ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ወሳኝ ተቋማትን ዒላማ ከማድረግ መቆጠብ እንደሚስፈልግ እንገልጻለን” ያሉት ቃል አቀባዩ፤ “ሁሉም ወገኖች” ዓለም አቀፍ ሕግን እንዲያከብሩ እና ውጥረቱን ለማርገብ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።ያጋሩ, በኢራን የሚገኘው የዓለም ግዙፉ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ስፍራ ጥቃት ተፈጸመበት
  4. 18 መጋቢት 2026የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሳዑዲ፣ ኤምሬትስ እና ኳታር የነዳጅ ማውጫ ላይ ጥቃት ሊሰነዝር እንደሆነ አስጠነቀቀየኢራን ሚሳዔልየፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ኳታር ውስጥ በሚገኙ የነዳጅ ማውጫዎች ላይ ጥቃት ሊሰነዝር እንደሆነ አስጠነቀቀ።በዚህም ምክንያት በባሕረ ሰላጤው አካባቢ ባሉ የነዳጅ ማምረቻ ተቋማት ውስጥ እና በዙሪያቸው የሚገኙ ሰዎች ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላልፏል።ከአብዮታዊ ዘቡ ጋር ግንኙነት ያለው ታስኒም የዜና ወኪል በቴሌግራም ገጹ ላይ “አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ” በሚል ባወጣው መልዕክት፤ ዜጎች እና ነዋሪዎች በዝርዝር ካስቀመጣቸው የነዳጅ ማዕከላት አቅራቢያ እንዲርቁ አዝዟል። እነዚህም፡-
    • ሳምሬፍ የነዳጅ ማጣሪያ – ሳዑዲ አረቢያ
    • አል-ጁቤይል ፔትሮኬሚካል ማምረቻ እና ማሳኢድ ኩባንያ – ሳዑዲ አረቢያ
    • አል-ሆሳን የጋዝ ማውጫ ቦታ – የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ
    • ራስ ላፋን የነዳጅ ማጣሪያ – ኳታር
    መግለጫው “እነዚህ የነዳጅ ማዕከላት ቀጥተኛ እና ተገቢ ዒላማዎች በመሆናቸው በሚቀጥሉት ሰዓታት ውስጥ ጥቃት ይፈጸምባቸዋል።”ስለዚህም ሁሉም ዜጎች፣ ነዋሪዎች እና ሠራተኞች በአስቸኳይ ከእነዚህ አካባቢዎች ለቅቀው በመውጣት ሳይዘገዩ ደኅንነቱ ወደ ተጠበቀ ርቀት እንዲሄዱ ተጠይቀዋል” ብሏል።ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሳዑዲ፣ ኤምሬትስ እና ኳታር የነዳጅ ማውጫ ላይ ጥቃት ሊሰነዝር እንደሆነ አስጠነቀቀ
  5. 18 መጋቢት 2026ለተገደሉት ባለሥልጣናት የሽኝት ሥነ ሥርዓት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢራናውያን አደባባይ ወጡማክሰኞ ዕለት በእስራኤል ጥቃት በተገደሉት የኢራን ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አሊ ላሪጃኒ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ መገኘቱን ከቴህራን የሚወጡ መረጃዎች አመለከቱ።በኢራን መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት ከነበራቸው ላሪጃኒ በተጨማሪ በተመሳሳይ በእስራኤል የተገደሉት የአብዮታዊ ዘቡ የሚሊሻ ክንፍ የሆነው የባሲጅ ታጣቂ ኃይል አዛዥ ለጎላምሬዛ ሶሌማኒም እና በአሜሪካ ጥቃት በተፈጸመበት የኢራን የጦር መርከብ ላይ ለተገደሉ 84 ባሕረተኞችም በአንድ ላይ ሽኝት ተደርጓል።00:59ያጋሩ, ለተገደሉት ባለሥልጣናት የሽኝት ሥነ ሥርዓት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢራናውያን አደባባይ ወጡ
  6. 18 መጋቢት 2026የኢራን የሚሳዔል ጥቃት በአሜሪካ ኤምባሲ ላይ00:51አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት ከጀመሩ በኋላ በአጸፋው ኢራን የተለያዩ ዒላማዎችን በሚሳዔሎች እና በድሮኖች እየመታች ነው።ከእነዚህም መካከል በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ የሚገኑ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች እና ሌሎች ተቋማት ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።ይህ ቪዲዮ ማክሰኞ ዕለት ኢራቅ ውስጥ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲን ዒላማ ያደረጉ የሚሳዔል ጥቃትን ያሳያል።ያጋሩ, የኢራን የሚሳዔል ጥቃት በአሜሪካ ኤምባሲ ላይ
  7. 18 መጋቢት 2026ሰበር,እስራኤል የኢራን የደኅንነት ሚኒስትርን መግደሏን አስታወቀችየኢራን የደህንነት ሚኒስትር ኢስማኤል ካሪብየፎቶው ባለመብት,EPA-EFE/REX/Shutterstockየእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ኢዝራኤል ካትዝ የኢራኑ የደኅንነት ሚኒስትር ኢስማኤል ኻቲብ መገደላቸውን ተናገሩ።ካትዝ በመግለጫቸው ላይ “ትናንት ሌሊት የኢራን ደኅንነት ሚኒስትር ኻቲብ ተወግደዋል” ብለዋል።ኢራን ስለሚኒስትሩ መገደል እስካሁን ያለችው ነገር የለም።ኢስማኤል ኻቲብ የኢራን የደኅንነት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት በቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራኢሲ ከአምስት ዓመታት በፊት ነበር።ከሟቹ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ እና ከሌሎችም የኢራን ከፍተኛ መሪዎች ጋር እስላማዊ ሕግን ያጠኑ ሲሆን፣ ቀደም ሲል በደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ውስጥ እንዲሁም በጠቅላይ መሪው ጽህፈት ቤት ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ሠርተዋል።በአውሮፓውያኑ 2022 የደኅንነት ሚኒስትሩ “በአሜሪካ እና በአጋሮቿ ላይ የበይነ መረብ ጥቃት እንዲፈጽም” አመቺ ሁኔታን ፈጥረዋል በሚል በአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።ኻቲብ በኢራን አብዮት ከተካሄደ ከአንድ ዓመት በኋላ ከ45 ዓመታት በፊት የእስላማዊው አብዮታዊ ዘብ አባል በመሆን ነው በመንግሥት ውስጥ ማገለግል የጀመሩት።በተመሳሳይ ትናንት በኢራን መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው የአገሪቱ ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አሊ ላሪጃኒ ተገድለዋል።ያጋሩ, እስራኤል የኢራን የደኅንነት ሚኒስትርን መግደሏን አስታወቀች
  8. 18 መጋቢት 2026እስራኤል በቤይሩት የሄዝቦላህ ‘የፋይናንስ ክንፍን’ ማጥቃቷን ገለጸችእስራኤል በቤይሩት የፈጸመችው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesእስራኤል ሌሊቱን በቤይሩት በፈጸመችው ጥቃት የሄዝቦላህን ጦር በገንዘብ የሚደግፈው የአል ቋርድ አል ሃሳን ንብረቶችን ዒላማ ማድረጓን አስታወቀች።እስራኤል በቤይሩት በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ አስር ሰዎች መገደላቸውን እና ሌሎች 27 ሰዎች መጎዳታቸውን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።እስራኤል የሄዝቦላህ የፋይናንስ ክንፍ ነው ካለችው አል ቋርድ አል ሃሳን በተጨማሪ በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኝ “የማዘዣ ጣቢያ” መደብደቧንም ገልጻለች።ማክሰኞ ዕለት እስራኤል “ሆን ተብሎ” ሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ ውስጥ የተቀመጠ የጦር መሣሪያ ማከማቻን መደብደቧን ገልጻለች።ያጋሩ, እስራኤል በቤይሩት የሄዝቦላህ ‘የፋይናንስ ክንፍን’ ማጥቃቷን ገለጸች
  9. 18 መጋቢት 2026ከሰባቱ ቁልፍ የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ስድስቱ ተገድለዋልአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሚያካሂዱትን ጥቃት ከጀመሩበት ደቂቃ አንስቶ እስካሁን ድረስ ዋነኛ ዒላማ እያደረጓቸው ያሉት የአገሪቱን ከፍተኛ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ መሪዎችን ነው።በመጀመሪያው ቀን ጥቃት የአገሪቱ ጠቅላይ መሪ የሆኑት አያቶላህ አሊ ኻሜኒን ጨምሮ ሌሎች ቁልፍ ባለሥልጣናት በጽህፈት ቤታቸው እና በመኖሪያቸው ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ተገድለዋል።በአገሪቱ ውስጥ በተለያዩ የሥልጣን ደረጃ ላይ የሚገኙ በርካታ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ባለፉት ዓመታት ጭምር ተገድለዋል። አሁን የተከፈተው ጦርነት ደግሞ ሌሎቹንም የጥቃት ዒላማ አድርጓቸዋል።ለመሆኑ ወሳኝ ከሚባሉት ሰባት የኢራን ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ መሪዎች መካከል በአሁኑ ወቅት ከጥቃት ተርፈው በሕይወት የሚገኙት ፕሬዝዳንቱ መሱድ ፔዜሽኪያን ብቻ ናቸው። ኢራን መሪዎቿን ባጣች ጊዜ እንዴት ሳትንኮታኮት ጸንታ መቀጠል ቻለች?ባለሥልጣናትያጋሩ, ከሰባቱ ቁልፍ የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ስድስቱ ተገድለዋል
  10. 18 መጋቢት 2026አሜሪካ ለምን በአሁኑ ወቅት በኢራን ላይ ከባዱን ቦምብ ተጠቀመች?2270 ኪሎ ግራም የሚመዝነው መሽግ ደርማሽ ቦምብየፎቶው ባለመብት,USAFየምስሉ መግለጫ,2270 ኪሎ ግራም የሚመዝነው መሽግ ደርማሽ ቦምብጦርነቱ ሦስተኛ ሳምንቱን ባገባደደበት በአሁኑ ወቅት አሜሪካ 2270 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን ምሽግ ደርማሽ ቦምብ ጥቅም ላይ ማዋል እንደ ጀመረች እየተዘገበ ነው።ይህ ቦምብ ከመሬት በታች በተገነቡ ጠንካራ ምሽጎች ውስጥ ያሉ ዒላማዎችን በጥልቀት በመግባት የማውደም ከፍተኛ አቅም ያለው ሲሆን፣ አሁን ጥቅም ላይ መዋሉ ኢራን የደበቀችው ጦር መሳሪያ እንዳለ ጥርጣሬ መኖሩን ያሳያል።የአሜሪካ ጦር በኢራን የባሕር ዳርቻ አካባቢ ባሉ የሚሳዔል ማስወንጨፊያዎች ላይ ጥቃቱን መፈጸሙን ያስታወቀ ቢሆንም የትኛውን ዓይነት ቦምብ ጥቅም ላይ እንደዋለ ዝርዝር አልሰጠም።ነገር ግን ሁለት ዓይነት ቦምቦች እንዳሉ ይታወቃል እነሱም፤ በጨረር የሚመራው ጁቢዩ-28 እና አዲሱ ዘመናዊ ጂቢዩ-72 የተባሉት ናቸው። በአሁኑ ጥቃት አዲሱ ቦምብ ጥቅም ላይ ሳይውል እንዳልቀረ ይታመናል።ለሦስት ሳምንት ያህል አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ያልተቋረጠ የሚሳዔል እና የአየር ድብደባዎችን እየፈጸሙ ቢሆንም፤ ኢራንም በበኩሏ ያልተቋረጠ የአጸፋ ጥቃት በእስራኤል እና በአሜሪካ አጋሮች ላይ እየፈጸመች ነው።ባለፉት ቀናት የኢራን የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃቶች ተዳክመው ሊቆሙ ይችላሉ ተብሎ ቢታሰብም አሁንም ከኢራን በኩል የሚሰነዘሩት ጥቃቶች በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ዋነኛ ስጋት ሆነው እንደቀጠሉ ናቸው።ለዚህም ሊሆን ይችላል አሜሪካ ከመሬት በታች ዘልቀው በመግባት የሚያወድሙትን ከባዶቹን ቦምቦች በመጠቀም የኢራንን የሚሳዔል እና የድሮን ክምችቶችን እንዲሁም ማስወንጨፊያዎችን ለመጠቀም የተገደደችው።ቦምቡን የሚጥለው ኤፍ-15ኢ ስትራይክ ኢግል የጦር ጄትየፎቶው ባለመብት,USAFየምስሉ መግለጫ,ቦምቡን የሚጥለው ኤፍ-15ኢ ስትራይክ ኢግል የጦር ጄትያጋሩ, አሜሪካ ለምን በአሁኑ ወቅት በኢራን ላይ ከባዱን ቦምብ ተጠቀመች?
  11. 18 መጋቢት 2026በኢራን ጥቃት ተጎድተው 192 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን እስራኤል አስታወቀችቴል አቪቭየፎቶው ባለመብት,Reutersየእስራኤል ጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ኢራን በፈጸመችው ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸው ቢያንስ 192 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን አስታውቋል።ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው ከተጎጅዎቹ መካከል አራቱ መካከለኛ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው።177 የሚሆኑት ደግሞ ቀላል ጉዳት ያስተናገዱ ሲሆን በሆስፒታል ውስጥ ሕክምና እየወሰዱ ነው ብሏል። ቀሪዎቹ 11 ሰዎች ግን በምን ሁኔታ እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም።ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ እስካሁን 3 ሺህ 727 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው የሕክምና ክትትል ማድረጋቸውን ገልጿል።ያጋሩ, በኢራን ጥቃት ተጎድተው 192 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን እስራኤል አስታወቀች
  12. 18 መጋቢት 2026ኢራን ‘ለእስራኤል በመሰለል’ የተከሰሰን ግለሰብ በሞት ቀጣችኢራን ለእስራኤሉ የስለላ ድርጅት “ሞሳድ ሲሰልል” ነበር የሚል ክስ የቀረበበትን ግለሰብ በሞት መቅጣቷን የአገሪቱ መንግሥት የዜና ወኪሎች አስታወቁ።ኩሮሽ ኬይቫኒ የተባለው ግለሰብ በሞት መቀጣቱን በተመለከተ ዜናው ይፋ ሲሆን፣ የቀረበበት ክስ እና ቅጣቱ የተላለፈበትን ሂደት በተመለከተ ምንም ዝርዝር መረጃ አልቀረበም።ነገር ግን ለኢራን አብዮታዊ ዘብ ቅርበት ያለው ፋርስ የዜና ወኪል ባወጣው ዘገባ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው አሁን እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር ሳይሆን፣ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ እስራኤል እና ኢራን ለ12 ቀናት የቆየ ጦርነት ባካሄዱበት ጊዜ ነው።የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የስለላ ክስ የሚቀርብባቸው ሰዎች ራሳቸውን የመከላከል መብታቸውን ኢራን እንደማታከብርላቸው እና ነጻ የሆነ የፍርድ ሂደት እንደማይካሄድ ይከሳሉ።በተጨማሪም የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የሞት ቅጣቶችን በስፋት የሚፈጽመው በተቃዋሚዎቹ እና በሕዝቡ ዘንድ ጭቆናን እና ፍርሃትን ለማንገስ ነው ይላሉ።ያጋሩ, ኢራን ‘ለእስራኤል በመሰለል’ የተከሰሰን ግለሰብ በሞት ቀጣች
  13. 18 መጋቢት 2026አሜሪካ በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ አቅራቢያ የሚገኙ የኢራን የሚሳዔል ጣቢያዎችን ደበደበችየሆረሙዝ የባሕር ወሽመጥን የሚያሳይ የሳተላይት ምስልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የዓለም 20 በመቶ ነዳጅ የመተላለፍበት የሆርሙዝ ባሕር ወሽመጥየአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ላይ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ለማጥቃት የሚውሉ የኢራን የሚሳዔል ጣቢያዎችን መደብደቡን አስታወቀ።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በኤክስ ገፁ ላይ ባወጣው ጽሑፍ ጦሩ በኢራን የባሕር ዳርቻ በሚገኙት “ጠንካራ የኢራን የሚሳዔል ጣቢያዎች ላይ 5,000 ፓውንድ የሚመዝኑ ሰረስረው የሚገቡ ቦምቦችን ተጠቅሞ በተሳካ ሁኔታ ድብደባ ፈጽሟል” ሲል አስታውቋል።”በእነዚህ ቦታዎች ላይ የተተከሉት የኢራን ፀረ-መርከብ ክሩዝ ሚሳዔሎች በባሕረ ሰላጤው ውስጥ ላሉ ዓለም አቀፍ መርከቦች አደጋ ፈጥረዋል” ሲል የአሜሪካ ጦር ተናግሯል።ኢራን 20 በመቶ የሚሆነው የዓለም ነዳጅ የሚጓጓዝበትን የባሕር ወሽመጥ በመዝጋቷ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።ግዙፎቹ ቦምቦች አሜሪካ ባለፈው ዓመት በኢራን ውስጥ የሚገኙ ሦስት የኒውክሌር ጣቢያዎችን ስትደበድብ ከተጠቀመችባቸው ቦምቦች ጋር ተመሳሳይ ሊሆኑ ይችላሉ።እነዚህ ቦምቦች በአየር ወይም በመሬት ላይ በሚገኙ ዒላማዎችን መትተው አይፈነዱም። ከዚያ ይልቅ በጥልቀት የተቀበሩ እና የተጠናከሩ ጉድጓዶችን እና ዋሻዎችን ሰርስሮ በመግባት የማጥቃት አቅም አላቸው።ስድስት ሜትሮች ርዝመት ያለው ይህ ቦምብ ከመፈንዳቱ በፊት በግምት 61 ሜትሮች ወደ ውስጥ ዘልቆ መግባት ይችላል ተብሎ ይታመናል።ያጋሩ, አሜሪካ በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ አቅራቢያ የሚገኙ የኢራን የሚሳዔል ጣቢያዎችን ደበደበች
  14. 18 መጋቢት 2026እስራኤል ሌሊቱን በቤይሩት የፈጸመችው ድብደባ ያደረሰው ውድመት በምሥልእስራኤል ሌሊቱን በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ላይ የፈጸመችው ጥቃትን ተከትሎ ስድስት ሰዎች ሲገደሉ 24 ደግሞ ቆስለዋል።ሊባኖስ ወደዚህ ግጭት ተስባ የገባችው ሄዝቦላህ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒን መገደል ተከትሎ የአጸፋ እርምጃ በሚል ሮኬቶችን እና ድሮኖችን መተኮሱን ተከትሎ ነው።እስራኤል በሄዝቦላህ ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ተደጋጋሚ የአየር ድበደባዎችን እየፈጸመች ሲሆን፣ ውስን የእግረኛ ጦርም ማሰማራቷን አስታውቃለች።በቤይሩት በሚገኝ ሕንጻ ላይ የተፈጸመን ጥቃት ተከትሎ ጥቁር ጭስ ታይቷልየፎቶው ባለመብት,Reutersበቤይሩት ባቾራ በሚባል አካባቢ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የደረሰውን ውድመት ተከትሎ በሕይወት የተረፉትን ለማዳን ሲረባረቡ ታይተዋልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በቤይሩት ባቾራ በሚባል አካባቢ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የደረሰውን ውድመት ተከትሎ በሕይወት የተረፉት ሰዎችን ለማዳን ሲረባረቡ ታይተዋልበቤይሩት ዙቃቅ አል-ብላት ዲስትሪክት የእስራኤል ጥቃትን ተከትሎ የደረሰውን ውድመት አንድ ሰው በረንዳ ላይ ቆሞ ሲመለከትየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በማዕከላዊ ቤይሩት ዙቃቅ አል-ብላት በተባለ ስፍራበማዕከላዊ ቤይሩት ዙቃቅ አል-ብላት ዲስትሪክት በጥቃት የወደመ ሕንጻየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በማዕከላዊ ቤይሩት ዙቃቅ አል-ብላት አካባቢ በጥቃት የወደመ ሕንጻያጋሩ, እስራኤል ሌሊቱን በቤይሩት የፈጸመችው ድብደባ ያደረሰው ውድመት በምሥል
  15. 18 መጋቢት 2026ኢራን ቴል አቪቭ ላይ የፈጸመችው ጥቃት በምሥልኢራን በእስራኤል ላይ ሌሊቱን በፈጸመችው የሚሳዔል ትቃት አንድ የ70 ዓመት ወንድ እና ሴት መሞታቸው ተሰምቷል። የደረሰውን ጥቃት የሚያሳዩ ምሥሎች ይፋ ሆነዋል።ሮይተርስ የዜና ወኪል የዐይን እማኝን ጠቅሶ እንደዘገበው ዛሬ ማለዳ በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ባቹራ በሚባል አካባቢ እስራኤል ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰምቷል።የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቴል አቪቭ ራማት ጋን ሰፈር የደረሰ የሚሳዔል ጥቃትን ተከትሎ በቦታው ተገኝተው ምላሽ ሰጥተዋልየፎቶው ባለመብት,Alexi J Rosenfeld via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቴል አቪቭ ራማት ጋን ሰፈር የደረሰ የሚሳዔል ጥቃትን ተከትሎ በቦታው ተገኝተው ምላሽ ሰጥተዋልየአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቴል አቪቭ ራማት ጋን ሰፈር የደረሰ የሚሳዔል ጥቃትን ተከትሎ በቦታው ተገኝተው ምላሽ ሰጥተዋልየፎቶው ባለመብት,Ilia Yefimovich via Getty Imagesከኢራን የተወነጨፉ ሚሳዔሎች በቴል አቪቭ ሰማይ ላይ ታይተዋልየፎቶው ባለመብት,Anadolu via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳዔሎች በቴል አቪቭ ሰማይ ላይ ታይተዋልያጋሩ, ኢራን ቴል አቪቭ ላይ የፈጸመችው ጥቃት በምሥል
  16. 18 መጋቢት 2026ኢራን የበቀል ጥቃት ለመፈጸም ስትዝት በእስራኤል የሚሳዔል ጥቃት ሁለት ሰዎችን ገድሏልበቴል አቪቭ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች የደረሰ የሚሳዔል ጥቃትን ተከትሎ ምላሽ ለመስጠት ተገኝተዋልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesሦስተኛ ሳምንቱ ላይ በሚገኘው እና አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር በሚያደርጉት ጦርነት የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃቶች ቀጥለዋል። በኢራን እና በአጋሮቿ የሚሊሻ ቡድኖች የሚሰነዘሩ የአጸፋ ጥቃቶች ሌሊቱን ሙሉ የቀጠሉ ሲሆን፣ የሰዎች ሞትም ተመዝግቧል።
    • የኢራን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ተጽዕኖ ፈጣሪው የኢራን ጠቅላይ ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት ጸሐፊ አሊ ላሪጃኒ በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደላቸውን አረጋግጠዋል ። ላሪጃኒ ከጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ሞት ወዲህ ከተገደሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል አንዱ ናቸው።
    • የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ውስጥ የሔዝቦላህ ዒላማዎችን መደብደቡን ቀጥሏል። የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር በማዕከላዊ ቤይሩት በተፈጸሙ የእስራኤል ሁለት ጥቃቶች ቢያንስ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን እና ሌሎች 24 ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጿል።
    • የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አንድ ተተኳሽ የኢራንን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ቢመታም ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳልደረሰበት አስታውቋል።
    • የአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ አቅራቢያ የሚገኙ የኢራን የሚሳኤል ጣቢያዎችን መምታቱን አስታውቋል።
    • ዶናልድ ትራምፕ የኔቶን እና ሌሎች አጋሮችን ተችተዋል፤ ፕሬዚዳንቱ ቀደም ሲል ድጋፍ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም አሜሪካ በኢራን ጦርነት ላይ “ከእንግዲህ ወዲህ እርዳታ አትሻም ወይም አትፈልግም” ብለዋል።
    • በቴል አቪቭ የኢራን የሚሳዔል ጥቃትን ተከትሎ በ 70ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ አንድ ወንድና አንዲት ሴት ተገድለዋል።
    • የኢራን የጦር አዛዥ የላሪጃኒን ግድያ በመበቀል “ወሳኝ፣ የሚያሽመደምድ እና ጸጸት ላይ የሚጥል” ምላሽ እንደሚሰጡ ዝተዋል። ከጦሩ የተለየ ወታደራዊ አካል የሆነው የኢራን አብዮታዊ ዘብ የላሪጃኒን ሞት “ለመበቀል” ወደ ማዕከላዊ እስራኤል ሚሳዔሎችን ማስወንጨፉን ኤኤፍፒ ዘግቧል።
    ያጋሩ, ኢራን የበቀል ጥቃት ለመፈጸም ስትዝት በእስራኤል የሚሳዔል ጥቃት ሁለት ሰዎችን ገድሏል
  17. 18 መጋቢት 2026በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ዳግም ጥቃቶች ተፈጸሙበኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ዳግም ጥቃቶች ተፈጸሙየፎቶው ባለመብት,Reutersበኢራቅ ዋና ከተማ በባግዳድ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ አዲስ ጥቃት መፈጸሙ ተሰምቷል።ኤኤፍፒ እና የሮይተርስ የዜና ኤጀንሲዎች ረቡዕ ማለዳ በኤምባሲው አካባቢ ፍንዳታ እንደደረሰ ዘግበዋል።ኤጀንሲዎቹ የጸጥታ ምንጮችን እና በከተማው የሚገኙ የኤፍፒ ጋዜጠኞችን ጠቅሰው የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ መገኛ በሆነው አካባቢ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አቅራቢያ ፍንዳታ መስማታቸውን ገልጸዋል።ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የአሜሪካ ኤምባሲ በተደጋጋሚ ጊዜ ጥቃት ደርሶበታል።ያጋሩ, በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ዳግም ጥቃቶች ተፈጸሙ
  18. 18 መጋቢት 2026የኢራን ጦር አዛዥ እስራኤል የደኅንነት ኃላፊው ላሪጃኒን መገደሏን ተከትሎ ‘ወሳኝ’ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወሰዱ ዛቱየኢራን ጦር አዛዥ አሚር ሃታሚየፎቶው ባለመብት,Anadolu via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የኢራን ጦር አዛዥ አሚር ሃታሚየኢራን ጦር አዛዥ አሚር ሃታሚ በእስራኤል የአየር ጥቃት የደኅንነት ኃላፊው አሊ ላሪጃኒን መገደላቸውን ተከትሎ “ወሳኝ” የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ ዛቱ።”ለወንጀለኛዋ አሜሪካ እና ደም የተጠማው የጽዮናውያን አገዛዝ በተገቢው ጊዜ እና ቦታ ወሳኝ፣ የሚያሽመደምድ፣ ጸጸት ውስጥ የሚጥል ምላሽ እንሰጣለን” ሲሉ ሃታሚ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል።የላሪጃኒ እና የሌሎች “ሰማዕታት ሞት እንበቀላለን” በማለት አክለዋል።ከኢራን ጦር ኃይል የተለየ ወታደራዊ ክፍል የሆነው እስላማዊው አብዮታዊ ዘብ የላሪጃኒ ሞትን “ለመበቀል” ወደ ማዕከላዊ እስራኤል ሚሳዔሎችን መተኮሱን የኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።የኢራን ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አሊ ላሪጃኒ ሰኞ ለማክሰኞ ሌሊት በእስራኤል በተፈጸመባቸው ጥቃት ከልጃቸው ጋር መገደላቸው ተነግሯል።ላሪጃኒ በኢራን መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት እና ከሟቹ ጠቅላይ መሪ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ካላቸው የአገሪቱ ተጽእኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች መካከል ቀዳሚው ናቸው።እስራኤል የላሪጃኒን መገደል ቀድማ ያሳወቀች ሲሆን፣ የመከላከያ ሚኒስትሯም ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣናትን እያደኑ ማጥፋታቸወን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።ያጋሩ, የኢራን ጦር አዛዥ እስራኤል የደኅንነት ኃላፊው ላሪጃኒን መገደሏን ተከትሎ ‘ወሳኝ’ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወሰዱ ዛቱ
  19. 17 መጋቢት 2026የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን በኢራን የሚካሄደውን ጦርነት ተቃውመው ሥልጣን ለቀቁጆ ኬንትየፎቶው ባለመብት,Bloomberg via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ጆ ኬንትየዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የፀረ ሽብርተኝነት ማዕከል ዳይሬክተር “በኢራን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በበጎ ህሊና መደገፍ አልችልም” በማለት ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ባጋሩት መልዕክት አስታወቁ።ጆ ኬንት ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ባሳወቁበት ደብዳቤ “ኢራን በአገራችን ላይ ምንም ዓይነት ተጨባጭ ስጋት አልደቀነችም፣ ይህንን ጦርነት የጀመርነው በእስራኤል እና በአሜሪካ ባሏት ኃያል ደጋፊዎቿ ግፊት መሆኑ ግልጽ ነው” ብለዋል።ዶናልድ ትራምፕ ሦስት ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ይዘው የተነሷቸውን ፖሊዎች ደግፈው ከጎናቸው እንደቆሙ ያስታወሱት ጆ፣ አስከ 2025 በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ የተካሄዱት ጦርነቶች የአሜሪካውያንን ሕይወት የቀጠፉ እና የአገሪቱን ሃብት ያሟጠጡ መሆናቸውን ትራምፕ ይረዱ እንደነበር ሲሉ አስታውሰዋል።“በ11 ውጊያዎች ላይ እንደተሳተፈ የቀድሞ ወታደር እና በእስራኤል በተፈበረከ ጦርነት ውድ ሚስቱን እንዳጣ ባል፣ ቀጣዩ ትውልድ ለአሜሪካ ጥቅም በማያስገኝ እና የሚከፈለው ዋጋ አሳማኝ ወዳልሆነ ጦርነት መሄዱን መደገፍ አልችልም” በማለት ጦርነቱን ተቃውመዋል።አሁን ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው የለቀቁት ጆ ኬንት በትራምፕ ተመርጠው በአሜሪካ ሴኔት ለቦታው ብቁ ናቸው ተብለው ተቀባይነት ያገኙት ባለፈው ዓመት ሐምሌ ነበር። የኢራንን ጦርነት ተቃውመው ሥልጣን የለቀቁት የአሜሪካው ከፍተኛ ባለሥልጣን ማን ናቸው?ያጋሩ, የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን በኢራን የሚካሄደውን ጦርነት ተቃውመው ሥልጣን ለቀቁ
  20. 17 መጋቢት 2026በሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ አውሮፓውያን ፊታቸውን ያዞሩባቸው ትራምፕትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዝዳንት ትራምፕ በፋርስ ባሕረ ሰላጤው የሆርሙዝ ሰርጥ የሚተላለፉ ግዙፍ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ለመጠበቅ አጋሮቻቸው እንዲተባበሩ ያቀረቡት ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ ባለማግኘቱ ተቆጥተዋል።ምዕራባውያን ወዳጆቻቸው ይህ የትራምፕ ጥሪ አሜሪካ ከእስራኤል ጋር በመሆን በኢራን ላይ ወደ ከፈተችው ጦርነት የሚያስገባቸው ሊሆን እንደሚችል በማሰብ የባሕር ኃይላቸውን ወደ ጦርነት ቀጣናው ለመላክ አልፈቀዱም።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጦርነት ተከትሎ ከፍተኛ የነዳጅ ምርት የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ሰርጥ በመዘጋቱ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል በአገራት ምጣኔ ሀብት ላይም ተጽእኖው እየተንጸባረቀ ነው።የአሜሪካ የቅርብ አጋሮች የሆኑት ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ እና ጀርመንን ጨምሮ ግሪክ፣ አውስትራሊያ፣ ስፔን፣ ጃፓን እና ሌሎችም በሆርሙዝ ሰርጥ የሚተላለፉ መርከቦችን ደኅንነት ለመጠበቅ በሚል ትራምፕ ባዘጋጁት ዕቅድ ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው በመግለጽ መልስ ሰጥተዋል።በአውሮፓ ታላላቅ ወታደራዊ ኃይል ያላቸው አገራቱ ምንም እንኳን የነዳጅ እንቅስቃሴው መስተጓጎል ቢጎዳቸውም በዚህ ምክንያት ግን ከኢራን ጋር ወደ ቀጥታ ግጭት የመግባት ፍላጎት እንደሌላቸው አሳውቀዋል። ይህም ሦስት ሳምንት ያስቆጠረው ጦርነት የአሜሪካ እና የእስራኤል ጉዳይ መሆኑን በተዘዋዋሪ መልዕክት ያስተላለፉበት ነው።የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር አገራቸው ሆርሙዝን በመጠበቅ ሰበብ ወደ ጦርነት ተስባ እንደማትገባ ሲጠቅሱ፣ የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ደግሞ ትራምፕ አጋሮቻቸው ካልተባበሯቸው ለኔቶ መጥፎ ሁኔታ ይፈጠራል በማለት ለሰጡት ማስጠንቀቂያ “ኔቶ የመከላከያ ስምምነት እንጂ የጣልቃ ገብነት ትብብር አይደለም” ሲሉ መከላከያ ሚኒስትራቸው ደግሞ “የእኛ ጦርነቱ አይደለም፤ እኛም አልጀመርነውም” በማለት እራሳቸውን አርቀዋል።ነገር ግን ትራምፕ ሰኞ ዕለት እንደተናገሩት “በርካታ አገራት” ጥሪያቸውን ተቀብለው ከጎናቸው እንደሚቆሙ እንደገለጹላቸው ጠቁመው፤ አሜሪካ ስትከላከላቸው የቀዩ አገራት ለቀረበላቸው ጥሪ ምላሽ ካልሰጡ “ምስጋና ቢስነት ነው” ብለዋል።አሜሪካ ሆርሙዝ ሰርጥን በመጠበቅ ከጎኔ ይቆማሉ ብላ የምትጠብቃቸው የአውሮፓ ባለሥልጣናት የኔቶ አባል አገራት ትብብር እራስን የመከላከል ዓላማ መሆኑን አጽንኦት እየሰጡ ነው።ኢራንን እና የኒውክሌር ፕሮግራሟን ዒላማ ማድረግ ግን አሜሪካ እና እስራኤል “በምርጫ የገቡበት ጦርነት ነው” በማለት አገራት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት መግባት እንደማይፈልጉ ግልጽ አድርገዋል።በኔቶ በኩል ዩክሬንን ከሩሲያ ጋር በምታደርገው ጦርነት እየደገፏት የሚገኙት የአውሮፓ አገራት በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረውን የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ለመሸፈን በሩሲያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ትራምፕ በማንሳታቸው ቅሬታቸውን ገልጸዋል።ያጋሩ, በሆርሙዝ ሰርጥ ጉዳይ አውሮፓውያን ፊታቸውን ያዞሩባቸው ትራምፕ