
በፖል አዳምስ፣ የዲፕሎማሲ ዘጋቢ እና የቪዡዋል ጋዜጠኝነት ቡድንመጋቢት 10 ቀን 2018ዓለም
ከተጀመረ ሁለት ሳምንታት ያለፉት “ኦፕሬሽን ኤፒክ ፊዩሪ” በመላው ዓለም ተጽዕኖ እየፈጠረ ነው።
የኢራንን የባለስቲክ ሚሳዔሎች፣ የባሕር ኃይል እና የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ምኞቷን ለማምከን ተብሎ የተጀመረው ዘመቻ አካባቢያዊ አለመረጋጋትን እና ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ተጽዕኖ እየፈጠረ ነው።
ከባድ የአየር ጥቃቶች ቢፈጸሙም የኢራን መንግስት ከሥልጣኑ አልተነሳም። አዲስ እና አደገኛ አካሄዶችም እየታዩ ነው።
ዶናልድ ትራምፕ “አጭር” ይሆናል ባሉት ዘመቻ መካከለኛው እየተናጠ ነው።
በዶናልድ ትራምፕ “መንግሥታችሁን ተቆጣጠሩ” ለተባሉት ኢራናዊያን ጊዜው አስከፊ ሆኗል።
ኢራን ባልተረጋጋው ቀጠና በፈተና ውስጥ ጸንታ ለመቆየት ችላለች።
ኢራን የምትደቅነው አደጋ አለ። ኢራን ከቆዳ ስፋት አንጻር ከጎረቤቶቿ ኢራቅ እና አፍጋኒስታን ድምር ትበልጣለች። በሁለቱ አገራት አሜሪካ የነበራት ዘመቻ ውጥንቅጡ የወጣ እና ዓመታትን ያስቆጠረ ነበር።
እንደኒውክሌር ፕሮግራሞቿ ያሉ የጦር ሃብቷ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተሠራጭተው ከመቀመጣቸውም በላይ አንዳንዶቹም በተራሮች ስር በሚገኙ ማከማቻዎች ተደብቀዋል።

90 ሚሊዮን ሕዝቧ የተለያየ ቢሆንም ግማሽ ያህሉ ፋርስ ነው። አነስተኛ ቁጥር ያላቸው አዘርባጃኖች፣ ኩርዶች እና አረቦችንም ያካተተ ነው።
ከአውሮፓውያኑ 1979 ጀምሮ መንበረ ሥልጣኑን የተቆጣጠረው እስላማዊው መንግሥት በጥልቅ የተሳሰረ፣ በርዕዮተ ዓለም የተዋቀረ እና በደንብ የተደራጀ ጭምር ነው።
ከሚያዝያ 2024 ወዲህ አራት ጊዜ በእስራኤል አንድ ጊዜ ደግሞ በአሜሪካ ከተፈጸመበት ጥቃት በላይ አገዛዙ በታኅሣሥ ወር የተነሳበትን ከፍተኛ ተቃውሞን ቀልብሶ በሥልጣን መቆየት መቻሉን አሳይቷል።
በአካባቢው ግጭት በፍጥነት እየተስፈፋ ነው






ጦርነቱ የተጀመረው በኢራን መከላከያ፣ ሚሳዔሎች እና ድሮኖች ላይ ከፍተኛ ጥቃት በመፈጸም ነው። በባሕረ ሰላጤው እና በአካባቢው በርካታ የኢራን መርከቦች ሰምጠዋል። አያቶላ ኻሜኒ እና በርካታ ቁልፍ ባለሥልጣናት በመጀመሪያው ቀን ተገድለዋል።

ኢራን እስራኤልን ጨምሮ በአካባቢው የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን በማጥቃቷ ግጭቱ በፍጥነት ተስፋፍቷል። ከግጭቱ ውጪ ለመሆን ያለሙት የባሕረ ሰላጤው አገራት ፍላጎታቸው አልተሳካም።

መሠረቱን ሊባኖስ ያደረገው እና ለረዥም ጊዜ ከእስራኤል ጋር በባላንጣት የሚፋለመው ሄዝቦላህ የኢራን የቅርብ አጋር ነው።

ግጭቱ ከመካከለኛው ምሥራቅም አልፏል። በቀናት ውስጥ ቆጵሮስ የሚገኘው የብሪታንያው አክሮቲር የጦር ሰፈር ተመታ። ስሪ ላንካ አካባቢ የነበረ የኢራን መርከብ ደግሞ በአሜሪካ የባሕር ኃይል ተመቷል። ወደ ቱርክ የተተኮሱ ሚሳዔሎችን ማክሸፍ ተችሏል። አዘርባጃን ላይ የድሮን ጥቃት ተሰንዝሯል።

“ጦርነት በተወሰኑ ድንበሮች ውስጥ ብቻ አይገደብም” ቶም ፍሌቸር፣ የተበባሩት መንግሥታት የሰብአዊ የአርዳታ አስተባባሪ፣ መጋቢት 2
ፍርሃት እና ድንጋጤ የተስፋን ቦታ ሲይዙ
በታኅሣሥ ወር ተቃዋሚ ሰልፈኞች በሚገደሉበት ወቅት ትራምፕ “እርዳታ እየመጣ ነው” ማለታቸውን ሰምተዋል።
ጥር መጨረሻ ላይ እርዳታው ሲደርስ አንዳንዶች ደስታቸውን ገለጹ። የጠቅላይ መሪው የመገደልን ዜና በደስታ የተቀበሉ ኢራናዊያንን የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ወተጥዋል።
የሲቪሎች ሞት ሲጨመር ግን ተስፋው ለድንጋጤ እና ፍርሃት ቦታውን መልቀቅ ጀመረ። በሚናብ በተፈጸመ የአየር ጥቃት አብዛኞቹ ሕጻናት ሆኑ 160 ሰዎ ችተገደሉ። በሌላ በኩል ደግሞ በምሥራቅ ቴህራን ከወደመ ሕንጻ ስር የተረፉ ሰዎችን ለማዳን ፍለጋው ቀጥሏል።
በቴህራን ሬሳላት አደባባይ የሚገኝ ሕንጻ የአየር ጥቃት ከደረሰበት በኋላ
በጦርነቱ ምክንያት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 3.2 ሚሊዮን ሰዎች እስካሁን መፈናቀላቸውን አሳውቋል። በደቡብ ሊባኖስ ደግሞ የእስራኤልን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ቢያነስ 800 ሺህ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናለቅዋል።
ጦርነቱን የጀመሩትም ገፈቱን መቅመስ ጀምረዋል። አሜሪካ እና እስራኤል አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን ወታደሮች አጥተዋል። ኢራን በቤይት ሼሜሽ የሚገኝ መጠለያን መምታቷን ተከትሎ ዘጠኝ እስራኤላዊያን መገደላቸው ገፈቱ ለሲቪሎችም መትረፉን ያሳለል።
ከዚህ ሁሉ ፍርሃት እና ኪሳራ በኋላም የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ አገዛዝ በመንበሩ ላይ ቀጥሏል።
ከኻራጅ ኢራን የመጣች ሴት
የአሜሪካ ጥንካሬ በኢራን ድሮኖች እና ሌሎች መሣሪያዎች ተፈትኗል
አሜሪካ ከ2003 የኢራቅ ጦርነት በኋላ የጦር መርከቦችን ጨምሮ ተዋጊ ጄቶችን ያካተተ ትልቅ የተባለውን የጦር ዝግጅት ለሳምንታት በኢራን አቅራቢያ ስታደርግ ቆይታለች።
እስራኤል እና አሜሪካ ምድር ላይ አለ የሚባል መሣሪያን ታጥቀዋል። የኢራንን መከላከያ ለማውደም ከርቀት የሚወነጨፉ እና ዒላማቸውን የማይስቱ ሚሳዔሎችን ታጥቀዋል። ያላቸው የቦምብ ክምችትም የሚያልቅ አይመስልም።
የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር
ይህ በየትኛው መመዘኛ ተመጣጣኝ ፍልሚያ ሊሆን አይችልም
ፔት ሄግሴት
የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር
ኢራን በርካታ ባለስቲክ ሚሳዔሎች እና ድሮኖችን ታጥቃለች። ለመቆጠብ ይሁን አይሁን ባይታወቅም ከሁለት ሳምንታት በኋላ ግን የምትጠቀመውን ቁጥር ቀንሳለች።
ከሰሞኑ በባሕር ላይ እንደተጠቀመቻቸው አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ዓይነት መሣሪያዎችም ባለቤት ናት። እነዚህን መለየት አስቸጋሪ በመሆኑ ለማውደምም አዳጋች ናቸው። በዚህም ምክንያት ጦርነቱ ሊራዘም ይችላል።
የዋጋ መናር አገራት የተለያየ እርምጃ እንዲወስዱ እያደረገ ነው
የጦርነቱ መዘዝ በአሜሪካ መንግሥት ባልተጠበቀ መልኩ የዓለምን ኢኮኖሚ ማናወጥ ጀምሯል።
20 በመቶ የሚሆነው የዓለም ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ወሽመጥ ተዘግቷል።

ወደ ቀይ ባሕር የሚሄድ የሳዑዲ የነዳጅ መስመር እና ወደ ኦማን ባሕረ ሰላጤ የሚወስድ ትንሽ መንገድ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በኩል በቅርቡ ይህንን እንቅፋት ለማስወገድ ይረዳል። እስከዚያው ድረስ ግን በዓለም ዙሪያ በነዳጅ እና በጋዝ አቅርቦት ላይ መስተጓጎል ተፈጥሯል።
ከአቪዬሽን እስከ ግብርና፤ ከፕላስቲክ እስከ ጭነት ማመለሻዎች ድረስ የዚህ ቀውስ ውጤት እስካሁን ያልተሰማበት የዓለም ኢኮኖሚ ጥግ የለም።
በፊሊፒንስ አንዳንድ ባለሥልጣናት ጉዞ ለመቀነስ በሳምንት ለአራት ቀናት እየሠሩ ነው። በታይላንድ የኤሌክትሪክ ፍጆታን ለመገደብ በመንግሥት ቢሮዎች የአየር ማቀዝቀዣዎች ሥራቸው እንዲቀንስ እንዲሆኑ ተደርጓል። የምያንማር ወታደራዊው መንግሥት የግል ተሽከርካሪዎች አንድ ቀን እያረፉ በተለዋጭ ቀናት ብቻ እንዲንቀሳቀሱ አዝዟል።
በብሪታንያ እና በአውሮፓ፣ የኃይል ኩባንያዎች ከቀውሱ ትርፍ ለማግኘት እየሠሩ ነው በሚል ስጋት፣ መንግሥታት የዋጋ ጭማሪን እንደሚቆጣጠሩ ተናግረዋል።
ትራምፕ የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ ቃል ቢገቡም፣ በአሜሪካ የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ ነው።
ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ማዕከላት የሆኑትን ኳታር እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን ጨምሮ በሌሎችም አገራት ቱሪዝም በከፍተኛ ሁኔታ ተስተጓጉሏል። በ2025 የመጀመሪያው አጋማሽ በየቀኑ ሩብ ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተናገደው የዱባዩ አየር ማረፊያ በኢራን ድሮኖች በተደጋጋሚ ተመትቷል።
ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ቱሪስቶች እና ነዋሪዎች ከአካባቢው ሸሽተዋል።
ባለፉት ቀናት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች በኢራን ሚሳዔሎች እና ፈጣን ጀልባዎች ሲመቱ አይተናል። ከእስራኤል እና ከአሜሪካ ከፍተኛ ጥቃት ጋር የምትጋፈጠው ኢራን ቀላል፣ በአንጻራዊነት ርካሽ ግን ከፍተኛ ተጽዕኖ በሚፈጥር መንገድ ጥቃቱን ለመመከት ወስናለች።
የአሜሪካ አጋሮች በከፍተኛ ሁኔታ ስጋት ውስጥ ገብተው ፊታቸውን እያዞሩ ነው።

ይህን ጦርነት የፈለጉት ሁለት አገሮች ብቻ ነበሩ። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ብዙ እስራኤላውያን ለአይሁድ መንግሥት ኅልውና ስጋት አድርገው የሚመለከቷትን አገር ለማሸነፍ ለአስርተ ዓመታት የዘለቀ ፍላጎታቸውን አልደበቁም። ዶናልድ ትራምፕ የኢራን የኑክሌር ምኞቶች ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲከሽፉ ይፈልጋሉ።
ሁለቱ መሪዎች አንድ ዋና ዓላማ ቢኖራቸውም፣ ከዚያ በኋላ ስለሚሆነው ነገር ብዙ ስለማሰባቸው ግልጽ አይደለም። ሁለቱም የኢራን ሕዝብ የራሱን ዕጣ ፈንታ እንዲቆጣጠር ግልጽ ባልሆነ መንገድ ቢናገሩም ጦርነቱ ሊያስነሳው የሚችለው ትርምስ ግን ስጋት የሚሆባቸው አይመስልም።

ሳዑዲ አረቢያን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትን ጨምሮ የዋሽንግተን የባሕረ ሰላጤው አጋሮች የሆኑት አገራት ጦርነቱ እጅግ አስደንጋጭ ሆኖባቸዋል። አብዛኞቹ ኢራንን በጥርጣሬ እና በፍርሃት ቢመለከቱም ከአክራሪ ጎረቤታቸው ጋር የመኖር ዘዴን ለምደዋል። ኢራን ዓለም አቀፍ አለመረጋጋትን የማስከተል አቅም እንዳላት በሚገባ ቢያውቁም በኃይል ከመጠቀም ይልቅ በድርድር መፍትሄዎችን ማግኘትን ይመርጣሉ። ኦማን በኒውክሌር አጀንዳ ዙሪያ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ስምምነት አንዲደረስ ያስቻለች መስላ ነበር። ጥቃቶቹ ከመጀመራቸው ከሰዓታት በፊት ግጭቱን ለማስወገድ ተስፋ በማድረግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በአሜሪካ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው ስምምነቱ “በእኛ እጅ ውስጥ ነው” ብለው ነበር።

ሌሎች የአሜሪካ አጋሮች ደግሞ ከባድ የምርጫ ፈተና እያጋጠሟቸው ነው። ከጦርነቱ ለመራቅ እና የዩናይትድ ኪንግደምን እና አጋሮቿን ጥቅም ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት መካከል የተሻለውን አማራጭ ለመከተል እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር የታገለ የለም። የጦር መርከቦችን ወደ ክልሉ የመላክ አስፈላጊነት በሕጋዊ መንገድ ሊብራራ ቢችልም፣ ይህን ማድረግ ግን በጣም ከባድ መሆኑ በአንድ ወቅት ስመ ገናና የነበረውን የብሪታንያ የባሕር ኃይል ያለበትን ሁኔታ አጉልቶ ያሳያል።

ከቴህራን አጋሮች መካከል በኢራን ላይ ለደረሰው ጉዳት ልትጸጸት የምትችለው ሩሲያ ብትሆንም ግን ያልተጠበቀው የነዳጅ ገቢ መጨመር፤ ሞስኮ በዩክሬን ለጀመረችው እና ከፍተኛ ወጪ ለሚጠይቀው ጦርነት የሚያስፈልጋትን ገንዘብ እንድታገኝ ዕድል ይሰጣታል።
በዓለም ላይ ትልቋ የኢራን ነዳጅ ገዢ የሆነችው ቻይና፤ አሁን በከፍተኛ ዋጋ አማራጭ የነዳጅ ምንጮችን እየፈለገች ነው። ቤይጂንግ “ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት” ባላት ወዳጇ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃትም መከላከል አልቻለችም።
በተከታታይ የተመረጡ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች በእስያ ላይ “ማተኮር” እና እያደገች ባለችው ቻይና የሚያጋጥሟትን ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ተግዳሮቶች ለመቋቋም መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። በኢራን የተደረገው ጦርነት መካከለኛው ምሥራቅ አሜሪካንን ወደ ውስጥ የመሳብ ሰፊ መንገድ እንዳለው በድጋሚ ያሳያል። ባለፈው ኅዳር ወር የታተመው የትራምፕ ብሔራዊ የደኅንነት ስትራቴጂ ኢራን በከፍተኛ ሁኔታ ተዳክማለች፤ በዚህ ምክንያትም መካከለኛው ምሥራቅ ብዙም ችግር የማይፈጠርበት ክልል እንደሆነ ገልጿል።
“መካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካን የውጭ ፖሊሲ በረጅም እና በአጭር ጊዜ የበላይነት ይዘው የሚቆዩበት ቀናት አክትመዋል” ሲል ዘገባው አክሎ ገልጿል።
