በመካከለኛው ምሥራቅ የሚካሄደው ጦርነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊሸጋገር ይችላል የሚል ስጋት የገባው የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን በማሰመራት ዘመቻውን ለማጠናከር እያሰበ መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ። ፕሬዝዳንቱ ኢራን ወደ ውጭ ከምትልከው የነዳጅ ምርት 90 በመቶው በሚያልፍበት የኻርግ ደሴት ላይ እግረኛ ሠራዊትን ለማስፈር እያሰቡ መሆናቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 46 ደቂቃዎች በፊትአሜሪካ ወታደሮቿን በኢራን ደሴት እና በሆርሙዝ ወሽመጥ የማሰማራት ሃሳብ እንዳላት ተነገረየአሜሪካ ወታደር እና ታንክየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበመካከለኛው ምሥራቅ የሚካሄደው ጦርነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊሸጋገር ይችላል የሚል ስጋት የገባው የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን በማሰማራት ዘመቻውን ለማጠናከር እያሰበ መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ።የዜና ወኪሉ አንድ ባለሥልጣን እና ሦስት ምንጮችን ጠቅሶ ያወጣው ዘገባ እንደሚያሳየው፤ አሜሪካ በኢራን ላይ እያካሄደች ያለው ጦርነት ሦስተኛ ሳምንት እየተገባደደ ባለበት በአሁኑ ጊዜ አዲስ የሚሰማሩት ወታደሮች አሜሪካ ለምትወስደው እርምጃ ተጨማሪ አማራጮችን ሊሰጣት ይችላል።የአየር እና የባሕር ኃይልን በመጠቀም በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ደኅንነት መጠበቅም ተጨማሪ ወታደሮችን ከማሰማራት ጋር የሚወሰድ እርምጃ ሊሆን ይችላል ተብሏል።ሮይተርስ ያነጋገራቸው ምንጮች እንዳሉት የሆርሙዝ ሰርጥ መተላለፊያን የመጠበቁ ጉዳይ በኢራን የባሕር ዳርቻዎች ላይ ጭምር የአሜሪካ ኃይሎችን ማሰማራትን ሊጨምር ይችላል።በተጨማሪም ኢራን ወደ ውጭ ከምትልከው የነዳጅ ምርት 90 በመቶው በሚያልፍበት የኻርግ ደሴት ላይ እግረኛ ሠራዊትን ለማስፈር እያሰቡ መሆናቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል።አንድ ባለሥልጣን ግን ቦታዎቹ በኢራን የሚሳዔል እና የድሮን ዒላማ ስር በቀላሉ ስለሚወድቁ ይህ የአሜሪካ ወታደሮችን በኢራን ይዞታዎች ላይ የማሰማራት ዕቅድ አደጋ ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።ኢራን ጥቃት መፈጸሟን የምትቀጥል ከሆነ ለኢራን ከፍተኛ የነዳጅ ገቢ የሚያስገኘውን የኻርግ ደሴትን እንደሚያወድሙ ፕሬዝዳንት ትራምፕ አስጠንቅቀዋል።ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ አሜሪካ በወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ጥቃት የፈጸመችበት ኻርግ ደሴት ወሳኝ የነዳጅ መሠረተ ልማቶችን ያያዘ በመሆኑ ከማውደም ይልቅ በቁጥጥር ስር ማዋል የተሻለው አማራጭ እንደሆነ ወታደራዊ ባለሙያዎች ይመክራሉ።ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት ውስጥ እንደማይሳተፉ የገቡትን ቃል በማጠፋቸው በኢራን ላይ ለከፈቱት ጥቃት ከአሜሪካውያን ያገኙት ድጋፍ ዝቅተኛ ነው። በመሆኑም ወታደሮችን ወደ ኢራን የሚያሰማሩ ከሆነ ፕሬዝዳንቱ በአገር ውስጥ ከፍተኛ ፖለቲካዊ አደጋ ይገጥማቸዋል።ያጋሩ, አሜሪካ ወታደሮቿን በኢራን ደሴት እና በሆርሙዝ ወሽመጥ የማሰማራት ሃሳብ እንዳላት ተነገረ
  2. ከ 56 ደቂቃዎች በፊትዌስት ባንክ ውስጥ በሚሳዔል ጥቃት ሦስት ሴቶች ተገደሉጥቃት በደረሰበት ስፍራ የቆሙ ነዋሪዎች እና የጸጥታ ኃይሎችየፎቶው ባለመብት,Reutersየእስራኤል ጦር ኢራን ሚሳዔሎችን ማስወንጨፏን ከገለጸ በኋላ በወረራ በተያዘው ዌስት ባንክ ውስጥ በሚገኝ የውበት ሳሎን ላይ በወደቀ ፍንጣሪ ሦስት ሴቶች መገደላውን የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ አስታወቀ።ቤት አዋ በተባው የዌስት ባንክ አካባቢ በደረሰው ጥቃት ስምንት ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት እንደደረሰ ተገልጿል። የአካል ክፍሉ መቆረጥ ያለበት አንድ ሰው ደግሞ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን የቀይ ጨረቃ መግለጫ ያስረዳል።የውበት ሳሎኑ የተመታው የእስራኤል ጦር ኢራን ሚሳዔሎችን ማስወንጨፏን ካስታወቀ ከአጭር ጊዜ በኋላ ነው።የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ማኅበር እንደገለጸው እስራኤል አካባቢው ላይ ባስቀመጠቻቸው መዝጊያዎች የተነሳ “ሠራተኞቹ አደጋ ወደ ደረሰበት ስፍራ በፍጥነት” መድረስ አልቻሉም። ይህም ሁኔታ “የተጎዱ ሰዎችን ነፍስ ለማዳን የሚደረገው ጥረት ላይ ቀጥታ እና ከፍተኛ ተጽዕኖ” ማሳደሩንም ገልጿል።“ወራሪው ኃይል ኃላፊነቱን እንዲወጣ እንዲሁም የነፍስ አድን ሥራዎችን እንዲያመቻች እና እንዳያሰናክልም” አሳስቧል።ጥቃት በደረሰበት የውበት ሳሎንየፎቶው ባለመብት,HAZEM BADER / AFP via Getty Imagesያጋሩ, ዌስት ባንክ ውስጥ በሚሳዔል ጥቃት ሦስት ሴቶች ተገደሉ
  3. ከ 1 ሰአት በፊትየኢራንን ጦርነት ተቃውመው ከሥልጣናቸው የለቀቁት የአሜሪካ ባለሥልጣን በኤፍቢአይ እየተመረመሩ መሆኑ ተገለጸጆ ኬንትየፎቶው ባለመብት,CQ-Roll Call, Inc via Getty Imagesየኢራንን ጦርነት ተቃውመው ከሥልጣናቸው የለቀቁት የአሜሪካ ብሔራዊ የፀረ ሽብር ማዕከል የቀድሞ ዳይሬክተር ጆ ኬንት፤ በኤፍቢአይ ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነ ተገለጸ።ምርመራው ምሥጢራዊ መረጃዎችን ለተለያዩ ምንጮች አሹልከዋል በሚል የተከፈተ እንደሆነ በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ኒውስ ለጉዳዩ ቅርበው ያላቸውን ምንጮችን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ ያሳያል።በኤፍቢአይ የወንጀል ክፍል የተያዘው ይህ ምርመራ ባለሥልጣኑ ከኃላፊነት ከመልቀቃቸው አስቀድሞ የተጀመረ እና ለተወሰነ ጊዜ ሲካሄድ የቆየ መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል ተብሏል።የቀድሞው የፀረ ሽብር ኃላፊ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከኃላፊነታቸው የለቀቁት ኢራን “ምንም ድርስ አደጋ” አልደቀነችም እንዲሁም “ጦርነቱ የተጀመረው በእስራኤል እና ጉልበት ባላቸው የአሜሪካ የውትትወታ ተቋማት ግፊት ነው” በሚል ነበር።ረቡዕ ዕለት ከወግ አጥባቂው የፖለቲካ አስተያት ሰጪ ታከር ካርልሰን ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ደግሞ፤ የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ መገደላቸውን ተቃውመዋል። ኻሜኒን መግደል አሜሪካ ልትወስድ ከምትችላቸው እርምጃዎች መካከል “የመጨረሻ” መሆን እንደነበረበት ተናግረዋል።“የኒውክሌር ፕሮግራማቸውን እያለዘበ ነበር፤ የኒውክሌር መሳሪያ እንዳያገኙ እየተከላከላቸው ነበር” ብለዋል።ያጋሩ, የኢራንን ጦርነት ተቃውመው ከሥልጣናቸው የለቀቁት የአሜሪካ ባለሥልጣን በኤፍቢአይ እየተመረመሩ መሆኑ ተገለጸ
  4. ከ 2 ሰአት በፊትየአሜሪካ ከፍተኛ የስለላ ኃላፊ የኢራን መንግሥት “ባለበት” ቢሆንም “በከፍተኛ ሁኔታ ተዳክሟል” አሉየአሜሪካ ብሔራዊ ስለላ መስሪያ ቤት ዳይሬክተር ቱልሲ ጋባርድየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ብሔራዊ ስለላ መሥሪያ ቤት ዳይሬክተር ቱልሲ ጋባርድ፤ የኢራን መንግሥት መዋቅር “እንዳለ ቢሆንም በአመራሩ እና በወታደራዊ አቅሙ ላይ በተፈጸመበት ጥቃም ምክንያት በከፍተኛ መጠን ተዳክሟል” ሲሉ ተናገሩ።ዳይሬክተሯ እና ሌሎች የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከፍተኛ ባለሥልጣናት በኮንግረስ ቀርበው ከሁለት ሰዓት በላይ የቆየ ማብራሪያ ሰጥተዋል።የኢራን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው ይህ ይፋዊ የማብራሪያ መርሃ ግብር የተካሄደው የፀረ ሽብር ከፍተኛ ባለሥልጣን ኢራን አሜሪካ ላይ ድረስ ስጋት አልደቀነችም በሚል ጦርነቱን ተቃውመው ከኃላፊነታቸው በለቀቁ ማግሥት ነው።የአገሪቱን ስለላ ኦፕሬሽኖች የሚያስተባብሩት ዳይሬክተሯ ጋባርድ፤ ኢራን አሜሪካ ላይ ድርስ ስጋት ደቅናለች ብለው ያምኑ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ ግልጽ ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል። “ጉዳዩ ድርስ ስጋት የሚደቅን እንደሆነ እና እንዳልሆነ የሚወስኑት ብቸኛው ሰው ፕሬዝዳንቱ ናቸው” ብለዋል።ዳይሬክተሯ ጦርነቱ ቴህራን ላይ ስላደረሰው ጉዳት ሲናገሩም “የስለላ ማኅበረሰቡ ባለበት ያለ የሚመስለውን የኢራን አገዛዝን ሁኔታ ገምግሟል፤ አመራሩ እና ወታደራዊ አቅሞቹ ላይ በተፈጸሙት ጥቃቶች ምክንያት በከፍተኛ መጠን ተዳክሟል” ሲሉ ተናግረዋል።ኢራን ባለፈው ዓመት ከእስራኤል ጋር በተካሄደው የ12 ቀናት ጦርነት ወቅት “ከፍተኛ ጉዳት” የደረሰበትን የኒውክሌር መሠረተ ልማት “መልሳ ለመገንባት እየሞከረች” ነበር ሲሉ ተደምጠዋል። “ለኒውክሌር ግዴታዎቿን ለመገዛትም ፈቃደኛ አለመሆኗን ቀጥላለች” በማለት ለኮንግረስ ምላሽ ሰጥተዋል።የአሜሪካ ሴንትራል ኢንተለጀንስ ኤጀንሲ (ሲአይኤ) ዳይሬክተር ጆን ራትክሊድ በበኩላቸው “ለረጅም ጊዜያት ኢራን ለአሜሪካ የማያቋርት ስጋት ሆና ቀጥላለች፤ በዚህ ጊዜም አስቸኳይ ስጋት ደቅናለች ብዬ አምናለሁ” ብለዋል።ያጋሩ, የአሜሪካ ከፍተኛ የስለላ ኃላፊ የኢራን መንግሥት “ባለበት” ቢሆንም “በከፍተኛ ሁኔታ ተዳክሟል” አሉ
  5. ከ 4 ሰአት በፊትየአሜሪካ መከላከያ በኢራን ለሚካሄደው ጦርነት ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ በጀት ጠየቀየጦር አውሮፕላንየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር በኢራን ለሚካሄደው ጦርነት የ200 ቢለዮን ተጨማሪ በጀት እንዲጸድቅለት ለፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር ጥያቄ ማቅረቡን አንድ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ለዋሽንግተን ፖስት ተናገሩ።የተጠየቀው ገንዘብ የትራምፕ አስተዳደር እስካሁን ካወጣው የመከላከያ ገንዘብ የበለጠ ሲሆን፣ በጣም ወሳኝ የሆኑ እና “በአስቸኳይ” የሚፈለጉ የጦር መሳሪያዎች ምርትን ለመጨመር እንደሚውል ተገልጿል።ይህ ከፍተኛ የመከላከያ በጀት ጭማሪ ጥያቄ በቀጥታ በፕሬዝዳንቱ የሚጸድቅ አይደለም፤ በአገሪቱ ምክር ቤት በኩል አልፎ ይሁንታን ማግኘት ይኖርበታል።ባለፈው ታኅሣሥ ላይ የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ከፍተኛ ነው የተባለውን 901 ቢሊየን ዶላር የመከላከያ በጀት ያጸደቁ ሲሆን፣ በወቅቱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያቀረቡት የበጀት ጥያቄ ከዚህም ከፍ ያለ ነበር።ፕሬዝዳንቱ አሁን ያለንበትን ጊዜ “የተረበሸ እና አደገኛ ወቅት” በማለት በቀጣዩ የአውሮፓውያን ዓመት የአሜሪካ የመከላከያ በጀት 1.5 ትሪሊየን ዶላር እንዲደርስ ጥረት እያደረጉ ነው።ከፍተኛው በጀት የሚፈቀድ ከሆነ አሜሪካ “ታይቶ የማይታወቅ ሠራዊት” በመገንባት አገሪቱን “ደኅንነቷ የተጠበቀ” ያደርጋታል ሲሉ ባለፈው ጥር ወር ላይ ተናግረው ነበር።ሦስት ሳምንት የሆነው የኢራን ጦርነት አሜሪካን ምን ያህል እንዳስወጣት በይፋ የተባለ ነገር የለም። ነገር ግን የተለያዩ የዜና ተቋማት አሜሪካ ኢራን ላይ በፈጸመችው የመጀመሪያ ሳምንት ጥቃት ከ11 ቢሊየን ዶላር በላይ ማውጣቷን ዘግበዋል።ያጋሩ, የአሜሪካ መከላከያ በኢራን ለሚካሄደው ጦርነት ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ በጀት ጠየቀ
  6. ከ 4 ሰአት በፊትፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን የጋዝ ማምረቻ ስፍራ “በከፍተኛ መጠን እንደሚያጋዩ” አስጠነቀቁየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢራን በኳታር ራስ ላፋን የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ላይ በድጋሚ ጥቃት የምትፈጽም ከሆነ፤ የቴህራንን የጋዝ ማምረቻ ስፍራ “ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ” መጠን “እንደሚያጋዩ” አስጠነቀቁ።ትራምፕ ይህንን ያሉት ደቡብ ፓርስ ውስጥ የሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ስፍራ በእስራኤል ጥቃት የተመታባት ኢራን፤ ኳታር ውስጥ በሚገኝ ተመሳሳይ የኢነርጂ መሠረተ ልማት ላይ የሚሳዔል እና የሮኬት ጥቃት ከፈጸመች በኋላ ነው።በኳታር የአጸፋ ጥቃት የተፈጸመበት ራስ ላፋን የተሰኘው የኢንዱስትሪ ስፍራ በዓለም ትልቁ የሆነውን የተጣራ የተፈጥሮ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ይዟል።ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ረዘም ያለ ጽሁፍ፤ እስራኤል በኢራን የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ላይ ስለፈጸመችው ጥቃት አሜሪካ “ምንም እንደማታውቅ” ገልጸዋል። እስራኤል“በመካከለኛው ምሥራቅ እየተፈጠረ ባለው ነገር ተናድዳ”፤ በኃይል” እርምጃ መውሰዷን አንስተዋል።“አሜሪካ ስለዚህኛው ጥቃት የምታውቀው ነገር አልነበረም፤ ኳታርም በየትኛውም መንገድ እና ቅርጽ ተሳትፎ አልነበራትም፤ ሊፈጸም እንደነበረም ምንም ሀሳብ አልነበራትም” ሲሉ ተከላክለዋል።ኳታር እና አሜሪካ ተሳትፎ እንደሌላቸው ኢራን አላወቀችም ያሉት ትራምፕ፤ ራስ ላፋን ላይ “አግባብ ያልሆነ እና ኢፍትሐዊ” ጥቃት ፈጽማለች በማለት ጽፈዋል።ኢራን “ሌላ ንፁህ አገርን ለማጥቃት ብልህ ያልሆነ ውሳኔ እስካላሳለፈች ድረስ” ከአሁን በኋላ እስራኤል ኢራን ውስጥ የሚገኘውን የደቡብ ፓርስ የጋዝ ማምረቻ ስፍራ እንደማታጠቃ ገልጸዋል።ፕሬዝዳንቱ፤ ኢራን በድጋሚ ኳታር ላይ ጥቃት ከፈጸመች ግን አሜሪካ “የደቡብ ፓርስ የጋዝ ስፍራን በሙሉ ኢራን አይታው በማታውቀው የጥንካሬ እና የኃይል መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ታጋየዋለች” ሲሉ ዝተዋል።ትራምፕ አክለውም፤ ኢራን ላይ “ረጅም ጊዜ የሚቆይ ተጽዕኖ” የሚኖረውን “በዚህ ደረጃ ያለ ጥቃት እና ውድመት” እንዲፈጸም ማዘዝ እንደማይፈልጉ ጠቅሰዋል። “የኳታር የተጣራ ተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻን በድጋሚ ካጠቃች ግን [ጥቃቱ እንዲፈጸም ለማዘዝ] አላንገራግርም” ብለዋል።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን የጋዝ ማምረቻ ስፍራ “በከፍተኛ መጠን እንደሚያጋዩ” አስጠነቀቁ
  7. ከ 5 ሰአት በፊትየተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ የተመታባት ኢራን በኳታር የነዳጅ ማውጫ ላይ የሚሳዔል እና የሮኬት ጥቃት ፈጸመችየኳታር ነዳጅ ማውጫየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበግዛቷ ውስጥ የሚገኘው የዓለም ትልቁ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ስፍራ በእስራኤል የተመታባት ኢራን፤ የኳታር የነዳጅ ኩባንያ ላይ የሜሳዔል እና የሮኬት ጥቃቶችን ፈጸመች።ይህንን ጥቃት ተከትሎ ኳታር ኢራንን “ለቀጣናው ብሔራዊ ደኅንነት እና መረጋጋት ቀጥተኛ ስጋት” ስትል የገለጸች ሲሆን ሁለት የቴህራን ዲፕሎማቶችንም አባርራለች።ትናንት እስራኤል ደቡብ ፓርስ የሚገኘው የፔትሮኬሚካል ተቋም የአየር ድብደባ ከፈጸመች በኋላ ኢራን፤ ኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ውስጥ የሚገኙ የነዳጅ ማውጫ ስፍራዎች ላይ የአጸፋ ጥቃት እንደምትፈጽም አስጠንቅቃ ነበር።የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ደቡብ ፓርስ የጋዝ ስፍራ ላይ ከደረሰው ጥቃት በኋላ ባደረጉት ንግግር የዚህ ጥቃት “መዘዝ ከቁጥጥር ውጪ” እንደሚወጣ አሳስበዋል።ምሽት ላይ በኳታር ‘ራስ ላፋን ኢንዱስትሪያል’ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ዋነኛ የነዳጅ ማቀነባበሪያ ስፍራ በሚሳዔሎች እንደተመታ በአገሪቱ መንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ‘ኳታር ኢነርጂ’ ኩባንያ አስታውቋል። በጥቃቱ የተነሳ ስፍራው በእሳት እንደተያያዘ እና ተቋሙ ላይ “ከፍተኛ ጉዳት” እንደደረሰም ገልጿል።ኩባንያው ዛሬ ንጋት ባወጣው መረጃ ደግሞ ኢራን በፈጸመችው ሌላ የሚሳዔል ጥቃት የኢነርጂ ተቋሙ ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቋል።ኳታር የኢራንን ጥቃት “ለቀጣናው ብሔራዊ ደኅንነት እና መረጋጋት ቀጥተኛ ስጋት” ስትል ገልጻዋለች። “የኢራን ወገን ቀጠናውን ወደ ገደል የሚወስደው እና የዚህ ቀውስ አካል ያልሆኑ አገራትን ወደ ግጭት አዙሪት የሚስበውን የማባባስ ፖሊሲ ቀጥሎበታል” ብላለች።“ምላሽ የመስጠት መብት እንዳላት” የገለጸችው ኳታር፤ “ሉዐላዊነቷን፣ ደኅንነቷን እና የዜጎቿን ደኅንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ በሙሉ ከመውሰድ ወደ ኋላ እንደማትል” አስጠንቅቃለች።ከሰዓታት በኋላም ኳታር ሁለት የኢራን ዲፕሎማቶች በ24 ሰዓት ውሰጥ አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ አዝዛለች። ለቅቀው እንዲሄዱ የታዘዙት የኢራን ወታደራዊ እና የደኅንነት አታሼዎች እንደሆኑ የኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።ያጋሩ, የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ የተመታባት ኢራን በኳታር የነዳጅ ማውጫ ላይ የሚሳዔል እና የሮኬት ጥቃት ፈጸመች
  8. 18 መጋቢት 2026የኢራን ሴት እግር ኳስ ተጨዋቾች የአውስትራሊያ ጥገኝነትን ትተው ወደ አገራቸው ጉዞ ጀመሩኢራናውያኑ እግር ኳስ ተጫዋቾችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ኢራናውያኑ እግር ኳስ ተጫዋቾችለውድድር ወደ አውስትራሊያ ተጉዘው ከነበሩት የኢራን ሴት ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን አባላት መካከል እዚያው በጥገኝነት ለመቆየት ፍላጎት የነበራቸው አምስት ተጫዋቾች ሃሳባቸውን ቀይረው ከቀሪው የቡድኑ አባላት ጋር ወደ አገራቸው ለመመለስ ጉዞ ጀመሩ።ወደ አገራቸው ለመመለስ ከአውስትራሊያ በማሌዢያ እና በኦማን በኩል ወደ ቱርክ የደረሱት ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾቹ፤ በአውቶብስ በድንበር በኩል ወደ ኢራን ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።በእስያ ዋንጫ የመክፍቻ ጨዋታ ላይ የአገራቸው ብሔራዊ መዝሙር በሚዘመርበት ጊዜ ዝም በማለታቸው የበቀል ቅጣት ሊጠብቃቸው እንደሚችል በመስጋት በርካታ የቡድኑ አባላት መጀመሪያ ላይ በአውስትራሊያ ለመቆየት የሚስችላቸውን የሰብአዊነት ከለላ ቪዛ ለማግኘት ፈልገው ነበር።በዚህም ምክንያት ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የአገራቸው ባለሥልጣናት ተጫዋቾቹን “ከሃዲዎች” በማለት ወቅሰዋቸው ነበር። በኋላ ላይ ግን የተደረገባቸውን ጫና ተቋቁመው ወደ አገራቸው ለመመለስ በመወሰናቸው “የጠላትን ዕቅድ” በማክሸፍ እያወደሷቸው ነው።የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ግን ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾቹ የጥገኝነት ጥያቄያቸውን ለመቀልበስ የተገደዱት ኢራን ውስጥ ባሉ በቤተሰቦቻቸው ላይ ጉዳት እንደሚደርስ ማስፈራሪያ እና ጫና ስለተደረገባቸው ነው ይላሉ።ከብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች መካከል ሁለቱ ብቻ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ ወደ አገራቸው ሳይመለሱ ቀርተዋል።ያጋሩ, የኢራን ሴት እግር ኳስ ተጨዋቾች የአውስትራሊያ ጥገኝነትን ትተው ወደ አገራቸው ጉዞ ጀመሩ
  9. 18 መጋቢት 2026የኢራን ፕሬዝዳንት የስለላ ሚኒስትሩን መገደል አረገገጡእስራኤል ትናንት ሌሊት በፈጸመችው ጥቃት የስለላ ሚስትሩ ኢስማኢል ኻቲብን (መሃል) መግደሏን አስታውቃ ነበርየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,እስራኤል ትናንት ሌሊት በፈጸመችው ጥቃት የስለላ ሚስትሩ ኢስማኢል ኻቲብን (መሃል) መግደሏን አስታውቃ ነበርኢራን የስለላ ሚኒስትር ኢስማኢል ኻቲብ መገደላቸውን የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን አረጋገጡ።እስራኤል ትናንት ምሽት በፈጸመችው ጥቃት ከፍተኛ የደኅንነት ኃላፊ የሆኑትን ኻቲብን መግደሏን ገልጻ ነበር።የኢራኑ ፕሬዝዳንት ከሰዓታት በኋላ በኤክስ ገጻቸው በሰፈሩት ጽሁፍ፤ የስለላ ሚኒስትሩን እና ሌሎች ኃላፊዎች “የፈሪ ግድያ” እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋል።ፕሬዝዳንቱ “ውድ ባልደረቦቼ ኢስማኢል ኻቲባ፣ አሊ ላሪጃኒ እና አዚዝ ናስርዛዴህ እንዲሁም የተወሰኑ የቤተሰቦች አባላት እና አብረዋቸው የነበሩ ቡድኖች ላይ የተፈጸመው የፈሪ ግድያ ሐዘን ላይ ጥሎናል” ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ የጠቀሷቸው የኢራን ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አሊ ላሪጃኒ በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት ከትናንት በስቲያ ሌሊት ነበር።የቀድሞው መከላከያ ሚኒስትር አዚዝ ናስርዛዴህ ደግሞ በመጀመሪያው ቀን ጥቃት የጠቅላይ መሪው አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ጋር ከተገደሉ ወታደራዊ አመራሮች መካከል ናቸው።ያጋሩ, የኢራን ፕሬዝዳንት የስለላ ሚኒስትሩን መገደል አረገገጡ
  10. 18 መጋቢት 2026በኢራን የሚገኘው የዓለም ግዙፉ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ስፍራ ጥቃት ተፈጸመበትየኢራን የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበኢራን ደቡብ ፓርስ የጋዝ ማምረቻ ስፍራ የሚገኘው የፔትሮኬሚካል ተቋም የአየር ድብደባ እንደተፈጸመበት ከእስላማዊው አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያለው ታስኒም የዜና ወኪል ዘገበ።ኳታር፤ እስራኤል በተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ስፍራው ላይ የፈጸመችውን ጥቃት “አደገኛ እና ኃላፊነት የጎደለው” ስትል ኮንናለች።የታስኒም ዘገባ እንደሚያመለክተው ጥቃቱ የተፈጸመው ዛሬ ረፋድ አካባቢ ነው። ከፊል ይፋዊው ፋርስ የዜና ወኩል በበኩሉ በቴሌግራም ገጹ ባወጣው ማስጠንቀቂያ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻው በእሳት መያያዙን ገልጿል። የእሳት እና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በስፍራው እንደሚገኙም ጠቅሷል።በዓለም ትልቁ በሆነው የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ስፍራ ደቡብ ፓርስ ውስጥ የኳታር እና ኢራን ማምረቻ ተቋማት ይንቀሳቀሳሉ።ኳታር በመግለጫዋ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻው ስፍራ ላይ ጥቃት የተፈጸመው በእስራኤል እንደሆነ የገለጸች ሲሆን፣ ድርጊቱንም “አደገኛ እና ኃላፊነት የጎደለው” ስትል አውግዛለች።የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ማጅድ አል አንሳሪ፤ በኢነርጂ መሠረተ ልማት ላይ የሚፈጸም ጥቃት “የዓለም የነዳጅ ደኅንነት ላይ ስጋት እንደሚደቅን” ተናግረዋል።“ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ወሳኝ ተቋማትን ዒላማ ከማድረግ መቆጠብ እንደሚስፈልግ እንገልጻለን” ያሉት ቃል አቀባዩ፤ “ሁሉም ወገኖች” ዓለም አቀፍ ሕግን እንዲያከብሩ እና ውጥረቱን ለማርገብ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።ያጋሩ, በኢራን የሚገኘው የዓለም ግዙፉ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ስፍራ ጥቃት ተፈጸመበት
  11. 18 መጋቢት 2026የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሳዑዲ፣ ኤምሬትስ እና ኳታር የነዳጅ ማውጫ ላይ ጥቃት ሊሰነዝር እንደሆነ አስጠነቀቀየኢራን ሚሳዔልየፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ኳታር ውስጥ በሚገኙ የነዳጅ ማውጫዎች ላይ ጥቃት ሊሰነዝር እንደሆነ አስጠነቀቀ።በዚህም ምክንያት በባሕረ ሰላጤው አካባቢ ባሉ የነዳጅ ማምረቻ ተቋማት ውስጥ እና በዙሪያቸው የሚገኙ ሰዎች ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላልፏል።ከአብዮታዊ ዘቡ ጋር ግንኙነት ያለው ታስኒም የዜና ወኪል በቴሌግራም ገጹ ላይ “አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ” በሚል ባወጣው መልዕክት፤ ዜጎች እና ነዋሪዎች በዝርዝር ካስቀመጣቸው የነዳጅ ማዕከላት አቅራቢያ እንዲርቁ አዝዟል። እነዚህም፡-
    • ሳምሬፍ የነዳጅ ማጣሪያ – ሳዑዲ አረቢያ
    • አል-ጁቤይል ፔትሮኬሚካል ማምረቻ እና ማሳኢድ ኩባንያ – ሳዑዲ አረቢያ
    • አል-ሆሳን የጋዝ ማውጫ ቦታ – የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ
    • ራስ ላፋን የነዳጅ ማጣሪያ – ኳታር
    መግለጫው “እነዚህ የነዳጅ ማዕከላት ቀጥተኛ እና ተገቢ ዒላማዎች በመሆናቸው በሚቀጥሉት ሰዓታት ውስጥ ጥቃት ይፈጸምባቸዋል።”ስለዚህም ሁሉም ዜጎች፣ ነዋሪዎች እና ሠራተኞች በአስቸኳይ ከእነዚህ አካባቢዎች ለቅቀው በመውጣት ሳይዘገዩ ደኅንነቱ ወደ ተጠበቀ ርቀት እንዲሄዱ ተጠይቀዋል” ብሏል።ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሳዑዲ፣ ኤምሬትስ እና ኳታር የነዳጅ ማውጫ ላይ ጥቃት ሊሰነዝር እንደሆነ አስጠነቀቀ
  12. 18 መጋቢት 2026ለተገደሉት ባለሥልጣናት የሽኝት ሥነ ሥርዓት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢራናውያን አደባባይ ወጡማክሰኞ ዕለት በእስራኤል ጥቃት በተገደሉት የኢራን ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አሊ ላሪጃኒ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ መገኘቱን ከቴህራን የሚወጡ መረጃዎች አመለከቱ።በኢራን መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት ከነበራቸው ላሪጃኒ በተጨማሪ በተመሳሳይ በእስራኤል የተገደሉት የአብዮታዊ ዘቡ የሚሊሻ ክንፍ የሆነው የባሲጅ ታጣቂ ኃይል አዛዥ ለጎላምሬዛ ሶሌማኒም እና በአሜሪካ ጥቃት በተፈጸመበት የኢራን የጦር መርከብ ላይ ለተገደሉ 84 ባሕረተኞችም በአንድ ላይ ሽኝት ተደርጓል።00:59ያጋሩ, ለተገደሉት ባለሥልጣናት የሽኝት ሥነ ሥርዓት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢራናውያን አደባባይ ወጡ
  13. 18 መጋቢት 2026የኢራን የሚሳዔል ጥቃት በአሜሪካ ኤምባሲ ላይ00:51አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት ከጀመሩ በኋላ በአጸፋው ኢራን የተለያዩ ዒላማዎችን በሚሳዔሎች እና በድሮኖች እየመታች ነው።ከእነዚህም መካከል በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ የሚገኑ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች እና ሌሎች ተቋማት ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።ይህ ቪዲዮ ማክሰኞ ዕለት ኢራቅ ውስጥ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲን ዒላማ ያደረጉ የሚሳዔል ጥቃትን ያሳያል።ያጋሩ, የኢራን የሚሳዔል ጥቃት በአሜሪካ ኤምባሲ ላይ
  14. 18 መጋቢት 2026ሰበር,እስራኤል የኢራን የደኅንነት ሚኒስትርን መግደሏን አስታወቀችየኢራን የደህንነት ሚኒስትር ኢስማኤል ካሪብየፎቶው ባለመብት,EPA-EFE/REX/Shutterstockየእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ኢዝራኤል ካትዝ የኢራኑ የደኅንነት ሚኒስትር ኢስማኤል ኻቲብ መገደላቸውን ተናገሩ።ካትዝ በመግለጫቸው ላይ “ትናንት ሌሊት የኢራን ደኅንነት ሚኒስትር ኻቲብ ተወግደዋል” ብለዋል።ኢራን ስለሚኒስትሩ መገደል እስካሁን ያለችው ነገር የለም።ኢስማኤል ኻቲብ የኢራን የደኅንነት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት በቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራኢሲ ከአምስት ዓመታት በፊት ነበር።ከሟቹ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ እና ከሌሎችም የኢራን ከፍተኛ መሪዎች ጋር እስላማዊ ሕግን ያጠኑ ሲሆን፣ ቀደም ሲል በደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ውስጥ እንዲሁም በጠቅላይ መሪው ጽህፈት ቤት ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ሠርተዋል።በአውሮፓውያኑ 2022 የደኅንነት ሚኒስትሩ “በአሜሪካ እና በአጋሮቿ ላይ የበይነ መረብ ጥቃት እንዲፈጽም” አመቺ ሁኔታን ፈጥረዋል በሚል በአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።ኻቲብ በኢራን አብዮት ከተካሄደ ከአንድ ዓመት በኋላ ከ45 ዓመታት በፊት የእስላማዊው አብዮታዊ ዘብ አባል በመሆን ነው በመንግሥት ውስጥ ማገለግል የጀመሩት።በተመሳሳይ ትናንት በኢራን መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው የአገሪቱ ብሔራዊ የደኅንነት ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ አሊ ላሪጃኒ ተገድለዋል።ያጋሩ, እስራኤል የኢራን የደኅንነት ሚኒስትርን መግደሏን አስታወቀች
  15. 18 መጋቢት 2026እስራኤል በቤይሩት የሄዝቦላህ ‘የፋይናንስ ክንፍን’ ማጥቃቷን ገለጸችእስራኤል በቤይሩት የፈጸመችው ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesእስራኤል ሌሊቱን በቤይሩት በፈጸመችው ጥቃት የሄዝቦላህን ጦር በገንዘብ የሚደግፈው የአል ቋርድ አል ሃሳን ንብረቶችን ዒላማ ማድረጓን አስታወቀች።እስራኤል በቤይሩት በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ አስር ሰዎች መገደላቸውን እና ሌሎች 27 ሰዎች መጎዳታቸውን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።እስራኤል የሄዝቦላህ የፋይናንስ ክንፍ ነው ካለችው አል ቋርድ አል ሃሳን በተጨማሪ በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኝ “የማዘዣ ጣቢያ” መደብደቧንም ገልጻለች።ማክሰኞ ዕለት እስራኤል “ሆን ተብሎ” ሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ ውስጥ የተቀመጠ የጦር መሣሪያ ማከማቻን መደብደቧን ገልጻለች።ያጋሩ, እስራኤል በቤይሩት የሄዝቦላህ ‘የፋይናንስ ክንፍን’ ማጥቃቷን ገለጸች
  16. 18 መጋቢት 2026ከሰባቱ ቁልፍ የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ስድስቱ ተገድለዋልአሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሚያካሂዱትን ጥቃት ከጀመሩበት ደቂቃ አንስቶ እስካሁን ድረስ ዋነኛ ዒላማ እያደረጓቸው ያሉት የአገሪቱን ከፍተኛ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ መሪዎችን ነው።በመጀመሪያው ቀን ጥቃት የአገሪቱ ጠቅላይ መሪ የሆኑት አያቶላህ አሊ ኻሜኒን ጨምሮ ሌሎች ቁልፍ ባለሥልጣናት በጽህፈት ቤታቸው እና በመኖሪያቸው ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ተገድለዋል።በአገሪቱ ውስጥ በተለያዩ የሥልጣን ደረጃ ላይ የሚገኙ በርካታ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ባለፉት ዓመታት ጭምር ተገድለዋል። አሁን የተከፈተው ጦርነት ደግሞ ሌሎቹንም የጥቃት ዒላማ አድርጓቸዋል።ለመሆኑ ወሳኝ ከሚባሉት ሰባት የኢራን ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ መሪዎች መካከል በአሁኑ ወቅት ከጥቃት ተርፈው በሕይወት የሚገኙት ፕሬዝዳንቱ መሱድ ፔዜሽኪያን ብቻ ናቸው። ኢራን መሪዎቿን ባጣች ጊዜ እንዴት ሳትንኮታኮት ጸንታ መቀጠል ቻለች?ባለሥልጣናትያጋሩ, ከሰባቱ ቁልፍ የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ስድስቱ ተገድለዋል
  17. 18 መጋቢት 2026አሜሪካ ለምን በአሁኑ ወቅት በኢራን ላይ ከባዱን ቦምብ ተጠቀመች?2270 ኪሎ ግራም የሚመዝነው መሽግ ደርማሽ ቦምብየፎቶው ባለመብት,USAFየምስሉ መግለጫ,2270 ኪሎ ግራም የሚመዝነው መሽግ ደርማሽ ቦምብጦርነቱ ሦስተኛ ሳምንቱን ባገባደደበት በአሁኑ ወቅት አሜሪካ 2270 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን ምሽግ ደርማሽ ቦምብ ጥቅም ላይ ማዋል እንደ ጀመረች እየተዘገበ ነው።ይህ ቦምብ ከመሬት በታች በተገነቡ ጠንካራ ምሽጎች ውስጥ ያሉ ዒላማዎችን በጥልቀት በመግባት የማውደም ከፍተኛ አቅም ያለው ሲሆን፣ አሁን ጥቅም ላይ መዋሉ ኢራን የደበቀችው ጦር መሳሪያ እንዳለ ጥርጣሬ መኖሩን ያሳያል።የአሜሪካ ጦር በኢራን የባሕር ዳርቻ አካባቢ ባሉ የሚሳዔል ማስወንጨፊያዎች ላይ ጥቃቱን መፈጸሙን ያስታወቀ ቢሆንም የትኛውን ዓይነት ቦምብ ጥቅም ላይ እንደዋለ ዝርዝር አልሰጠም።ነገር ግን ሁለት ዓይነት ቦምቦች እንዳሉ ይታወቃል እነሱም፤ በጨረር የሚመራው ጁቢዩ-28 እና አዲሱ ዘመናዊ ጂቢዩ-72 የተባሉት ናቸው። በአሁኑ ጥቃት አዲሱ ቦምብ ጥቅም ላይ ሳይውል እንዳልቀረ ይታመናል።ለሦስት ሳምንት ያህል አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ያልተቋረጠ የሚሳዔል እና የአየር ድብደባዎችን እየፈጸሙ ቢሆንም፤ ኢራንም በበኩሏ ያልተቋረጠ የአጸፋ ጥቃት በእስራኤል እና በአሜሪካ አጋሮች ላይ እየፈጸመች ነው።ባለፉት ቀናት የኢራን የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃቶች ተዳክመው ሊቆሙ ይችላሉ ተብሎ ቢታሰብም አሁንም ከኢራን በኩል የሚሰነዘሩት ጥቃቶች በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ዋነኛ ስጋት ሆነው እንደቀጠሉ ናቸው።ለዚህም ሊሆን ይችላል አሜሪካ ከመሬት በታች ዘልቀው በመግባት የሚያወድሙትን ከባዶቹን ቦምቦች በመጠቀም የኢራንን የሚሳዔል እና የድሮን ክምችቶችን እንዲሁም ማስወንጨፊያዎችን ለመጠቀም የተገደደችው።ቦምቡን የሚጥለው ኤፍ-15ኢ ስትራይክ ኢግል የጦር ጄትየፎቶው ባለመብት,USAFየምስሉ መግለጫ,ቦምቡን የሚጥለው ኤፍ-15ኢ ስትራይክ ኢግል የጦር ጄትያጋሩ, አሜሪካ ለምን በአሁኑ ወቅት በኢራን ላይ ከባዱን ቦምብ ተጠቀመች?
  18. 18 መጋቢት 2026በኢራን ጥቃት ተጎድተው 192 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን እስራኤል አስታወቀችቴል አቪቭየፎቶው ባለመብት,Reutersየእስራኤል ጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ኢራን በፈጸመችው ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸው ቢያንስ 192 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን አስታውቋል።ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው ከተጎጅዎቹ መካከል አራቱ መካከለኛ ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው።177 የሚሆኑት ደግሞ ቀላል ጉዳት ያስተናገዱ ሲሆን በሆስፒታል ውስጥ ሕክምና እየወሰዱ ነው ብሏል። ቀሪዎቹ 11 ሰዎች ግን በምን ሁኔታ እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም።ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ እስካሁን 3 ሺህ 727 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው የሕክምና ክትትል ማድረጋቸውን ገልጿል።ያጋሩ, በኢራን ጥቃት ተጎድተው 192 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን እስራኤል አስታወቀች
  19. 18 መጋቢት 2026ኢራን ‘ለእስራኤል በመሰለል’ የተከሰሰን ግለሰብ በሞት ቀጣችኢራን ለእስራኤሉ የስለላ ድርጅት “ሞሳድ ሲሰልል” ነበር የሚል ክስ የቀረበበትን ግለሰብ በሞት መቅጣቷን የአገሪቱ መንግሥት የዜና ወኪሎች አስታወቁ።ኩሮሽ ኬይቫኒ የተባለው ግለሰብ በሞት መቀጣቱን በተመለከተ ዜናው ይፋ ሲሆን፣ የቀረበበት ክስ እና ቅጣቱ የተላለፈበትን ሂደት በተመለከተ ምንም ዝርዝር መረጃ አልቀረበም።ነገር ግን ለኢራን አብዮታዊ ዘብ ቅርበት ያለው ፋርስ የዜና ወኪል ባወጣው ዘገባ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋለው አሁን እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር ሳይሆን፣ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ እስራኤል እና ኢራን ለ12 ቀናት የቆየ ጦርነት ባካሄዱበት ጊዜ ነው።የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የስለላ ክስ የሚቀርብባቸው ሰዎች ራሳቸውን የመከላከል መብታቸውን ኢራን እንደማታከብርላቸው እና ነጻ የሆነ የፍርድ ሂደት እንደማይካሄድ ይከሳሉ።በተጨማሪም የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የሞት ቅጣቶችን በስፋት የሚፈጽመው በተቃዋሚዎቹ እና በሕዝቡ ዘንድ ጭቆናን እና ፍርሃትን ለማንገስ ነው ይላሉ።ያጋሩ, ኢራን ‘ለእስራኤል በመሰለል’ የተከሰሰን ግለሰብ በሞት ቀጣች
  20. 18 መጋቢት 2026አሜሪካ በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ አቅራቢያ የሚገኙ የኢራን የሚሳዔል ጣቢያዎችን ደበደበችየሆረሙዝ የባሕር ወሽመጥን የሚያሳይ የሳተላይት ምስልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የዓለም 20 በመቶ ነዳጅ የመተላለፍበት የሆርሙዝ ባሕር ወሽመጥየአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ላይ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ለማጥቃት የሚውሉ የኢራን የሚሳዔል ጣቢያዎችን መደብደቡን አስታወቀ።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በኤክስ ገፁ ላይ ባወጣው ጽሑፍ ጦሩ በኢራን የባሕር ዳርቻ በሚገኙት “ጠንካራ የኢራን የሚሳዔል ጣቢያዎች ላይ 5,000 ፓውንድ የሚመዝኑ ሰረስረው የሚገቡ ቦምቦችን ተጠቅሞ በተሳካ ሁኔታ ድብደባ ፈጽሟል” ሲል አስታውቋል።”በእነዚህ ቦታዎች ላይ የተተከሉት የኢራን ፀረ-መርከብ ክሩዝ ሚሳዔሎች በባሕረ ሰላጤው ውስጥ ላሉ ዓለም አቀፍ መርከቦች አደጋ ፈጥረዋል” ሲል የአሜሪካ ጦር ተናግሯል።ኢራን 20 በመቶ የሚሆነው የዓለም ነዳጅ የሚጓጓዝበትን የባሕር ወሽመጥ በመዝጋቷ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።ግዙፎቹ ቦምቦች አሜሪካ ባለፈው ዓመት በኢራን ውስጥ የሚገኙ ሦስት የኒውክሌር ጣቢያዎችን ስትደበድብ ከተጠቀመችባቸው ቦምቦች ጋር ተመሳሳይ ሊሆኑ ይችላሉ።እነዚህ ቦምቦች በአየር ወይም በመሬት ላይ በሚገኙ ዒላማዎችን መትተው አይፈነዱም። ከዚያ ይልቅ በጥልቀት የተቀበሩ እና የተጠናከሩ ጉድጓዶችን እና ዋሻዎችን ሰርስሮ በመግባት የማጥቃት አቅም አላቸው።ስድስት ሜትሮች ርዝመት ያለው ይህ ቦምብ ከመፈንዳቱ በፊት በግምት 61 ሜትሮች ወደ ውስጥ ዘልቆ መግባት ይችላል ተብሎ ይታመናል።ያጋሩ, አሜሪካ በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ አቅራቢያ የሚገኙ የኢራን የሚሳዔል ጣቢያዎችን ደበደበች