አሜሪካ እና እስራኤል ከቴህራን ጋር የጀመሩት ጦርነት አራተኛ ሳምንቱን በያዘበት ወቅት በኢራን የተለያዩ ከተሞች የአየር ድብደባ መፈጸሙ ተሰምቷል። የኩዌት ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን በሚና አል አህማዲ ነዳጅ ማጣሪያ ላይ ኢራን የድሮን ጥቃቶች መፈጸሟን ዘግበዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 14 ደቂቃዎች በፊትየአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት በኢስፋሃን የሚገኙ 21 ታሪካዊ ቅርሶችን ማውደሙ ተገለፀበግጭቱ ጉዳት የደረሰበት ታሪካዊ ሕንጻ በከፊልየፎቶው ባለመብት,mizanplusየኢስፋሃን አስተዳዳሪ መህዲ ጃማልላይጃድ አገራቸው ከእስራኤል እና ከአሜሪካ ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት “21 ታሪካዊ ቅርሶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል” ሲሉ ተናገሩ።የኢራን መገናኛ ብዙኃን ጃማልላይጃድ ጠቅሰው ጉዳቱ “በቅርሶች ላይ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ውድመት” ማድረሱን ዘግበዋል።አስተዳዳሪው የኢስፋሃንን ታሪካዊ ቅርሶች መጠበቅ “ብሔራዊ ኃላፊነት ነው” ማለታቸው የተዘገበ ሲሆን፣ የደረሰውን ጉዳት በሚመለከት “ካሳ እና ለመጠገን የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ሕጋዊ በሆነ መልኩ በሚመለከታቸው አካላት በኩል” እንደሚጠይቁ ተናግረዋል።ያጋሩ, የአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት በኢስፋሃን የሚገኙ 21 ታሪካዊ ቅርሶችን ማውደሙ ተገለፀ
  2. ከ 43 ደቂቃዎች በፊትኢራን የብሪታኒያ ጦር ሠፈሮችን አሜሪካ እንድትጠቀም መፍቀድ “ጠብ አጫሪነት” ነው አለችየኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺየፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን የብሪታኒያ ጦር ሠፈሮችን አሜሪካ እንድትጠቀም መፍቀድ “ጠብ አጫሪነት” ነው ስትል ለዩኬ መናገሯን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።አሜሪካ የዩኬን ወታደራዊ ጦር ሠፈር እንድትጠቀም መፍቀድ “በግጭት ውስጥ እንደመሳተፍ” እንደሚቆጠር ቴህራን ለዩኬ መግለጿን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ ከዩኬ አቻቸው ዪቬት ኩፐር ጋር ባደረጉት ውይይት ዩኬ ለአሜሪካ የምትሰጠው የትኛውም ድጋፍ “ሁኔታው እንዲባባስ” እንደሚያደርግ መናገራቸውን ተጠቅሷል።አራጋቺ ዩኬ እና ሌሎች የአውሮፓ አገራት አሜሪካ እና እስራኤል ለፈጸሙት “ግልጽ ጥቃት” የሚከተሉት “ለአንድ ወገን ያደላ አቀራረብ” መሆኑን በመናገር ወንጅለዋቸዋል።አራጋቺ በተጨማሪም ዩኬ የእስራኤል በሳውዝ ፓርስ የጋዝ ማምረቻ ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ባለማውገዟ መተቸታቸው ተዘግቧል።በጉዳዩ ላይ የዩኬ መንግሥት እስካሁን ድረስ ምንም ያለው ነገር የለም። ቢቢሲ የዩኬ የውጭ ጉዳይ ቢሮን በጉዳዩ ላይ ምላሽ ቢጠይቅም ማግኘት አልቻለም።ያጋሩ, ኢራን የብሪታኒያ ጦር ሠፈሮችን አሜሪካ እንድትጠቀም መፍቀድ “ጠብ አጫሪነት” ነው አለች
  3. ከ 1 ሰአት በፊትየኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ ተገደሉየኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ እና ምክትል ሕዝብ ግንኙነት አሊ ሞሃመድ ናኢኒየፎቶው ባለመብት,Farsየምስሉ መግለጫ,የኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ እና ምክትል ሕዝብ ግንኙነት አሊ ሞሃመድ ናኢኒየኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት መገደላቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ እና ምክትል ሕዝብ ግንኙነት አሊ ሞሃመድ ናኢኒ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃቶች መገደላቸውን የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን አስታውቋል።አሊ ሞሐመድ ናኢኒ የአብዮታዊ ዘቡን ለአራት አስርታት ያገለገሉ ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ ቃል አቀባይ በመሆን ሰርተዋል ሲል ፋርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 21 2018 ዓ.ም. ኢራን ላይ ጦርነት ከከፈቱበት ዕለት አንስቶ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ በርካታ አመራሮች ተገድለዋል።የቀድሞው ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ጦርነቱ በጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የተገደሉ ሲሆን ሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ አመራሮችም የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃት ዒላማ ሆነዋል።ኢራን በ18 ቀናት ውስጥ የትኞቹ ከፍተኛ አመራሮቿ ተገደሉባት?ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ ተገደሉ
  4. ከ 1 ሰአት በፊትበቴህራን መሰማት የቀጠሉት ከባድ ፍንዳታዎችበቴህራን በእስራኤል ጥቃት ቤታቸው የወደመ ቤተሰቦችየፎቶው ባለመብት,NurPhoto via Getty Imagesእስራኤል ኢራናውያን አዲስ ዓመታቸውን በሚያከብሩበት ወቅት በቴህራን ከፍተኛ የአየር ድብደባዎችን መፈጸሟ ተገለፀ።የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ፐርዢያ እንደተናገሩት ከባድ ፍንዳታዎች በዋና ከተማዋ ቴህራን ተሰምቷል። የእስራኤል ጦር “በኢራን በሚገኙ የመንግሥት መሠረተ ልማቶች ላይ” ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታውቋል።ሐሙስ ዕለት እስራኤል በኢራን ላይ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች የሰላማዊ ሰዎች መኖሪያ ስፍራዎች መውደማቸውን ተከትሎ ስጋቶች ጨምረዋል።ሌሊቱን ቴህራን ወደ እስራኤል ሚሳዔሎችን ያስወነጨፈች ሲሆን ቴል አቪቭ ማክሸፏን አስታውቃለች።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ኢራን “መውደሟን” እና ዩራኒየም ማበልጸግም ሆነ ባሌስቲክ ሚሳዔል ማምረት አትችልም ሲሉ ተናግረዋል።በዚህ ሳምንት ቴህራን እስራኤል በሳውዝ ፓር ጋዝ ማምረቻ ስፍራ ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ የአጸፋ እርምጃ የወሰደች ሲሆን ይህም የጋዝ ዋጋ እንዲጨምር አደርጓል።ሐሙስ ዕለት ዩናይትድ ኪንግደም እና ሌሎች አጋር አገራት በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚደረግ የመርከቦች ጉዞን አስተማማኝ ለማድረግ የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ “ዝግጁ” መሆናቸውን በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ ጠቅሰዋል።ያጋሩ, በቴህራን መሰማት የቀጠሉት ከባድ ፍንዳታዎች
  5. ከ 3 ሰአት በፊትበዓለም ግዙፉ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ላይ የደረሰው ውድመት ኳታርን ቢሊዮኖች ያስወጣታል- የኢነርጂ ሚኒስትሩበኳታር የሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በኳታር የሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻየኳታር ኢነርጂ ሚኒስትር ኢራን በራስ ላፋን የጋዝ ማምረቻ ተቋም ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን እና አገሪቱን ቢሊዮኖችን እንደሚያስወጣት ተናግረዋል።ኳታር ወደ ውጭ የምትልከው ፈሳሽ ተፈጥሯዊ ጋዝ (ኤልኤንጂ) በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ብቻ በ17 በመቶ የሚቀንስ ሲሆን አገሪቱ በዓመት 20 ቢሊዮን ዶላር አንድታጣ ያደርጋታል ብለዋል።ሚኒስተሩ አክለውም በኢራን ጥቃት ካሏቸው 14 ማምረቻዎች ሁለቱ ወድመዋል ብለዋል።ኢራን በኳታር ራስ ላፋን የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ላይ ጥቃት የፈጸመችው ረቡዕ ዕለት እስራኤል በሳውዝ ፓርስ የጋዝ ማምረቻ ላይ ድብደባ መፈጸሟን ተከትሎ ነው።ከኳታር የተፈጥሮ ጋዝ የሚያገኙት የእስያ አገራት መካከል ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ሕንድ እና ቻይና ይገኙበታል። ከአውሮፓ ደግሞ ጣሊያን እና ቤልጂየም ዋነኛ አስመጪዎች ናቸው።የዩክሬን ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲሀ ፊታቸውን ከሩሲያ ወደ መካለኛው ምሥራቅ ያዞሩት የእስያ አገራት ከኳታር በሚያገኙት የተፈጥሮ ጋዝ ላይ ጥገኛ ናቸው።በዓለም አቀፉ የተፈጥሮ ጋዝ ግብይት ውስጥ ኳታር ከቀዳሚዎቹ አገራት መካከል አንዷ ናት።ያጋሩ, በዓለም ግዙፉ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ላይ የደረሰው ውድመት ኳታርን ቢሊዮኖች ያስወጣታል- የኢነርጂ ሚኒስትሩ
  6. ከ 3 ሰአት በፊትየኩዌት ነዳጅ ማጣሪያ የድሮን ጥቃቶች ደረሰበትየሚና አል አህማዲ የነዳጅ ማጣሪያየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የሚና አል አህማዲ የነዳጅ ማጣሪያምንም እንኳ ኢራን የምትፈጽማቸውን ጥቃቶች እንድታቆም ጥሪ ቢቀርብም የኩዌት መንግሥት የነዳጅ ድርጅት የሆነው ኬፒሲ ነዳጅ ማጣሪያዎቹ በበርካታ የድሮን ጥቃቶች መመታታቸውን አስታውቋል።እስካሁን ድረስ ስለደረሰው ጉዳት ይፋ የሆነ መረጃ የለም።በሚና አል አህማዲ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ የተቀሰቀሰውን እሳት ለማጥፋት የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች እየተረባረቡ ነው።የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የማጣሪያው የተወሰኑ ክፍሎች መዘጋታቸውን ዘግበዋል።የባሕረ ሰላጤው የነዳጅ መሠረተ ልማቶች በኢራን ተደጋጋሚ ጥቃቶችን አስተናግደዋል።እስራኤል የቴህራንን ጋዝ ማምረቻን ሳውዝ ፓርስን ካጠቃች በኋላ ኢራን በገልፍ ባሕረ ሰላጤው አገራት የሚገኙ የነዳጅ እና የጋዝ ማምረቻዎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ፈጽማለች።መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለአንድ ወር ቆየውን የረመዳን ጾም አጠናቅቀው ዛሬ የኢድ አል ፈጥር በዓልን እያከበሩ ቢሆንም በመካከለኛው ምሥራቅ የተጀመረው ጦርነት የሚቆም አይመስልም።ያጋሩ, የኩዌት ነዳጅ ማጣሪያ የድሮን ጥቃቶች ደረሰበት
  7. ከ 4 ሰአት በፊትየባሕረ ሰላጤው አገራት ላይ የሚፈጸመው የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃትየተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ኩዌት፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ባህሬን ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃቶች እንደተፈጸመባቸው ተናግረዋል።የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የመከላከያ ሚኒስቴር በአሁኑ ጊዜ ከኢራን የተተኮሱ ሚሳዔሎችን እና ድሮኖችን የማክሸፍ ሥራ እየሠራ መሆኑን ተናግሮ፣ የአገሪቱ ዜጎች የአየር መከላከያ ስርዓቶች ጥቃቶችን ሲያከሽፉ የሚፈጠሩ ፍንዳታዎችን ሊሰሙ እንደሚችሉ ተናግረዋል።ኩዌት በአየር መከላከያ ስርዓቷ ምክንያት ስለሚፈጠሩ ፍንዳታዎች ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች፤ እናም ዜጎች ከባለሥልጣናት የተሰጡ የደህንነት መመሪያዎችን እንዲከተሉ ጠይቃለች።የሳዑዲ አረቢያ የመከላከያ ሚኒስቴር በአገሪቱ ምሥራቃዊ አካባቢ አምስት ተጨማሪ ድሮኖች መክሸፋቸውን እና ጥቃት መፈጸማቸውን አስታውቋል።የባህሬን የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የአደጋ ጊዜ ደወል ከተሰማ ነዋሪዎች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ እንዲሄዱ ጠይቋል። ሚሳዔሎቹ “ከኢራን የተተኮሱ” መሆናቸውን እና ስብርባሪው ያደረሰው ፍንዳታ በአንድ መጋዘን ላይ እሳት እንዳስከተለ ጨምሮ አስታውቋል።ያጋሩ, የባሕረ ሰላጤው አገራት ላይ የሚፈጸመው የሚሳዔል እና የድሮን ጥቃት
  8. ከ 4 ሰአት በፊትኤፍቢአይ የኢራን የመረጃ መዝባሪዎች ይጠቀሙበታል ያላቸውን አራት ድረገጾች በቁጥጥር ስር አዋለላፕቶፕ እና ስልክ ላይ የኮምፒውተር ኮድ የሚጽፍ ሰው እጅየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesኤፍቢአይ መቀመጫቸውን ኢራን አድርጎ በአሜሪካ ኩባንያዎች ላይ የሳይበር ጥቃት፣ የመረጃ ምዝበራ እና ምንተፋ የሚያካሄድ ቡድን የሚገለገልባቸውን አራት ድረ ገጾች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ።የአሜሪካ የፍትህ ቢሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው “የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ የስለላ እና የደህንነት ሚኒስቴር የሚያካሄደውን የመረጃ ብርበራ እና የድንበር ተሻጋሪ ምንተፋ እቅዶችን ለማደናቀፍ የሚደረገው ቀጣይነት ያለው ጥረት አካል ነው” ብሏል።የፍትህ ቢሮ እንዳስታወቀው፣ የተያዙት ድረ ገጾች ጋዜጠኞችን፣ የአገዛዙን ተቃዋሚዎች እና የእስራኤልን ሕዝብ እንዲገደሉ ጥሪ ይተላለፍባቸው ነበር ብሏል።“ኢራን አሜሪካውያንን ለማሸበር እና ተቃዋሚዎችን ዝም ለማሰኘት የሐሰት ድረ ገጾችን እና ኪቦርድ ጀርባ ልትደብቅ እንደምትችል አስባ ነበር” ሲሉ የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ካሽ ፓቴል ተናግረዋል።“የዘመቻቸው አራቱን ምሰሶዎች አፍርሰናል፤ አልጨረስንም” ያሉት ፓቴል “ኤፍቢአይ ከእነዚህ ፈሪ የሞት ዛቻዎች እና የሳይበር ጥቃቶች በስተጀርባ ያሉትን ሁሉመም ተዋናዮች ያድናል፤ እንዲሁም የአሜሪካን የሕግ አስከባሪ ኃይሎች ሙሉ ኃይል በእነሱ ላይ ያዘምታል” ብለዋል።ያጋሩ, ኤፍቢአይ የኢራን የመረጃ መዝባሪዎች ይጠቀሙበታል ያላቸውን አራት ድረገጾች በቁጥጥር ስር አዋለ
  9. ከ 5 ሰአት በፊትኔታንያሁ ጦርነቱ “አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ ይቀጥላል” ሲሉ ተናገሩቤንያሚን ኔታንያሁየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ምሽት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኢራን “ከምንጊዜውም በላይ ደካማ ሆናለች” ሲሉ ተናግረዋል።ኢራን ዩራኒየም የማበልጸግም ሆነ ባሌስቲክ ሚሳዔል የመስራት አቅም አይኖራትም ሲሉ ተደምጠዋል።ይሁን አንጂ በኢራን ላይ እያካሄዱት ያለው ወታደራዊ ዘመቻ “አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ” ሊቀጥል ይችላል በማለት መቼ እንደሚያበቃ ከመናገር ተቆጥበዋል። ኔታንያሁ ጦርነቱ ሰዎች ከሚያስቡት ጊዜ ፈጥኖ ይጠናቀቃል ሲሉ ተናግረዋል።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ወታደራዊ ዘመቻ ሦስት ግቦች አሉት ያሉት ኔታንያሁ የኒውክሌር እና የባሌስቲክ ሚሳዔልን ስጋት ማስወገድ እና ኢራናውያን “ነጻነታቸውን እንዲቀዳጁ” የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት መሆናቸውን ተናግረዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እስራኤል አሜሪካን ወደዚህ ጦርነት ስባ አለማስገባቷን የተናገሩ ሲሆን ትራምፕ የራሳቸውን ውሳኔ ይወስናሉ ሲሉ በስፍራው ለተገኙ ጋዜጠኞች ተናግረዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በቅርቡ በኢራን የተፈጥሮ ጋዝ መሠረተ ልማቶች ላይ የፈጸሙትን ጥቃት “እስራኤል ብቻዋን ያካሄደችው ነው” ካሉ በኋላ ትራምፕ ወደፊት የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለጊዜው ገታ አንዲያደርጉ እንደጠየቋቸው ተናግረዋል።ያጋሩ, ኔታንያሁ ጦርነቱ “አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ ይቀጥላል” ሲሉ ተናገሩ
  10. ከ 5 ሰአት በፊትበኢራን የሟቾች ቁጥር 3100 ማለፉን የሰብዓዊ መብቶች ኤጀንሲ አስተወቀመቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የሰብዓዊ መብቶች አክቲቪስቶች የዜና ኤጀንሲ (ሂርና) በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነቱ ከጀመረበት ከየካቲት 21 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በኢራን የሞቱ ሰዎች ቁጥር 3186 መድረሱን አስታውቋል።ከእነዚህ መካከል 1394 ሰላማዊ ሰዎች መሆናቸውን የገለጸ ሲሆን 210 ደግሞ ሕጻናት እንደሆኑ ሂርና ይፋ አድርጓል።በአሜሪካ እና እስራኤል ዒላማ ከተደረጉት መካከል 1153 ወታደራዊ ተቋማት መሆናቸው የገለጸው የዜና ወኪሉ እስካሁን ድረስ የ639 ሰዎች ሞት አልተመዘገበም ብሏል።ያጋሩ, በኢራን የሟቾች ቁጥር 3100 ማለፉን የሰብዓዊ መብቶች ኤጀንሲ አስተወቀ
  11. 19 መጋቢት 2026ትራምፕ እግረኛ ወታደሮችን ወደ ኢራን እንደማያሰማሩ እና ጦርነቱ “ከታቀደለት ጊዜ ፈጥኖ እየተካሄደ ነው” አሉየአሜሪካው ፕሬዚዳነት ዶናልድ ትራምፕ እና የጃፓኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ታካይቺየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የአሜሪካው ፕሬዚዳነት ዶናልድ ትራምፕ እና የጃፓኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ታካይቺየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመካለኛው ምሥራቅ የትኛውም ቦታ የእግረኛ ጦራቸውን እንደማያሰማሩ ተናገሩ።ትራምፕ ሦስት ሳምንት ሊሞላው የተቃረበው በኢራን ላይ የሚካሄደው ጦርነት “ከታቀደለት ጊዜ ፈጥኖ እየተካሄደ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።ፕሬዝዳንቱ የአሜሪካ ወታሮች ይሰማሩ እንደሆነ ጥያቄውን ላቀረቡላቸው ጋዜጠኞች በሰጡት ምላሽ “ብናቅድ እንኳ አልነግርህም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።ትራምፕ ይህንን ያሉት ከጃፓኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ታካኢቺ ጋር በዋይት ሐውስ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።የጃፓኗ ጠቅላይ ሚኒስትር በዓለም ላይ ሰላምን ሊያሳኩ የሚችሉት ትራምፕ “ብቻ ናቸው” ሲሉ ተደምጠዋል።አክለውም ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንድታበለጽግ “በጭራሽ ሊፈቀድላት አይገባም” ብለዋል።ታካኢቺ የጃፓን ባለሥልጣናት ኢራን በኢነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ የምትፈጽማቸውን ጥቃቶች እንድታቆም በቀጥታ መጠየቃቸውን ተናግረዋል።ያጋሩ, ትራምፕ እግረኛ ወታደሮችን ወደ ኢራን እንደማያሰማሩ እና ጦርነቱ “ከታቀደለት ጊዜ ፈጥኖ እየተካሄደ ነው” አሉ
  12. 19 መጋቢት 2026የነዳጅ ማምረቻዎችን ዒላማ እያደረጉ ያሉት ጥቃቶችበባሕረ ሰላጤው የሚካሄደው ጦርነት ሦስተኛ ሳምንቱን ሊደፍን በተቃረበበት ጊዜ ተፋላሚዎቹ ወገኖች የነዳጅ ምርት ማዕከላትን ዒላማ እያደረጉ ነው።ጦርነቱ ሲጀመር በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚተላለፉ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች አደጋ ላይ ይወድቃሉ የሚል ስጋት የነበራቸው ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ መርከቦች ወደ አካባቢው ለመንቀሳቀስ ሳይችሉ ቀርተዋል።የዓለም 20 በመቶ የነዳጅ ምርት በሚተላለፍበት የሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በተፈጠረው መስተጓጎል የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ ነው።አሁን ደግሞ ከፍተኛ ነዳጅ በሚመረትባቸው የፋርስ ባሕረ ሰላጤ አገራት የነዳጅ ማምረቻዎች ላይ አሜሪካ፣ እስራኤል እና ኢራን ጥቃት መፈጸም በመጀመራቸው ዓለምን ስጋት ላይ ጥለዋል።ይህ ቪዲዮ ከአንድ የሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ማጣሪያ አቅራቢያ የተከሰተ ፍንዳታን ያሳያል።00:26ያጋሩ, የነዳጅ ማምረቻዎችን ዒላማ እያደረጉ ያሉት ጥቃቶች
  13. 19 መጋቢት 2026አሜሪካ በኢራን ነዳጅ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ለማንሳት እያሰበች መሆኑ ተገለጸየአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንትየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንትየአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንት አሜሪካ የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት በኢራን ነዳጅ ላይ የጣለችወን ማዕቀብ ልታነሳ እንደምትችል ተናገሩ።ባለሥልጣኑ ለፎክስ ቢዝነስ በሰጡት ቃለ ምልልስ ወቅት ይህ እርምጃ በመርከብ ላይ ተጭኖ ያለ 140 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅን ተጠቃሚ ሊያደርግ እንደሚችል ተናግረዋል።የዓለም ሕዝብ በቀን 100 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ይጠቀማል ተብሎ ይገመታል።ቤሴንት የነዳጅ ዘይት አቅርቦትን ለማሻሻል በሩሲያ ነዳጅ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ለማንሳት እንዲሁም ከመጠባበቂያ ክምችት 172 ሚሊዮን በርሜል ለዓለም ገበያ ለመልቀቅ በመፍትሄነት መቀመጣቸውን ተናግረዋል።ቤሴንት ቀደም ሲል ጦርነት እየተካሄደ ቢሆንም አሜሪካ የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከቦች እንዲያልፍ እንደምትፈቅድ ተናግረው ነበር።ይህ የአሜሪካ እርምጃ በዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ እንድሚኖረው ግልጽ አይደለም።ቤሴንት አሜሪካ ይህ እርምጃዋ ጠላቷን በገንዘብ ይደግፋል የሚል ስጋት የላትም ወይ ተብለው ሲጠየቁ አሜሪካ በሚቀጥሉት 10 እና 14 ቀናት የነዳጅ ዋጋን በመቀነስ “የኢራንን ነዳጅ ከኢራን በተቃራኒ እንዲቆም” ታደርጋለች ብለዋል።ያጋሩ, አሜሪካ በኢራን ነዳጅ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ለማንሳት እያሰበች መሆኑ ተገለጸ
  14. 19 መጋቢት 2026የዩኬ መከላከያ ሚኒስትር ኢራን በባሕረ ሰላጤው የኢነርጂ ተቋማት ላይ የፈጸመችው ጥቃት ግጭቱን “የበለጠ የሚያባብስ” ነው አሉየዩኬ መከላከያ ሚኒስትር ጆን ሂሌይየፎቶው ባለመብት,PA Mediaየምስሉ መግለጫ,የዩኬ መከላከያ ሚኒስትር ጆን ሂሌይኢራን በአካባቢው የሚገኙ የነዳጅ ማምረቻ ጣቢያዎችን ካጠቃች በኋላ ብሪታንያ ለባሕረ ሰላጤው አገራት የመከላከያ ድጋፏን “እያጠናከረች” ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ ጆን ሂሌይ ተናገሩ።ቴህራን ሌሊቱን የፈጸመችው ጥቃት “ቀጣናውን የበለጠ ለማወክ” የሚያሰጋ እና ግጭቱን “የበለጠ የሚያባብስ” እንደሆነ ጨምረው ተናግረዋል።”እዚህ በኑሮ ውድነት እና በነዳጅ ዋጋ ላይ ያለውን ተጽእኖ ማየት እንችላለን፤ ስለዚህ ወሽመጡን እንደገና ለመክፈት በሚደረገው ጥረት ውስጥ መሳተፍ ከሚፈልጉ ሌሎች ብዙ አገራት ጋር የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አስፈላጊ ነው” ሲል ሄሊይ ለፔንስልቬንያ የዜና ወኪል ተናግረዋል።በዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ በጣም ጥሩው መንገድ “ግጭቱን ማርገብ እና ማቆም” እንደሆነ ተናግረዋል።ያጋሩ, የዩኬ መከላከያ ሚኒስትር ኢራን በባሕረ ሰላጤው የኢነርጂ ተቋማት ላይ የፈጸመችው ጥቃት ግጭቱን “የበለጠ የሚያባብስ” ነው አሉ
  15. 19 መጋቢት 2026ምዕራባውያን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመጠበቅ ፈቃደኝነታቸውን ገለጹየነዳጅ ጫኝ መርከብየፎቶው ባለመብት,Reutersዩናይትድ ኪንግደም እና አምስት አገራት በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ላይ የሚደረግ የነዳጅ መርከቦች ጉዞን ደኅንነት ለመጠበቅ “ተገቢ ጥረቶችን” ለማድረግ “ዝግጁ” መሆናቸውን ገለጹ።ዩናይትድ ኪንግደም እና አጋሮቿ በጋራ ባወጡት መግለጫ ኢራን በሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ የምታደርሰውን ጥቃት አውግዘዋል።በተጨማሪም በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ላይ የሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የምትፈጥረውን ስጋት እንድታቆም ጥሪ አቅርበዋል።”በባሕር ላይ የመቅዘፍ ነፃነት የዓለም አቀፍ ሕግ መሠረታዊ መርኅ ነው” ሲሉ የዩኬ፣ የፈረንሳይ፣ የጀርመን፣ የጣልያን፣ የኔዘርላንድስ እና የጃፓን መሪዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ ጠቅሰዋል።“የኢራን ድርጊት ውጤት በሁሉም የዓለም ክፍሎች በተለይም በጣም ተጋላጭ የሆኑት እንዲሰማቸው ያደርጋል።”ቡድኑ በተጨማሪም የዓለም 20 በመቶ ነዳጅ መተላለፊያ በሆነው የባሕር ወሽመጥ ላይ ደኅንነቱ እንዲጠበቅ ለማድረግ “ተገቢ ጥረቶችን” ለማድረግ “ዝግጁነቱን” ገልጿል።አገራቱ አክለውም “በዝግጅት ዕቅድ ላይ የተሳተፉ አገራት ያላቸውን ቁርጠኝነት በደስታ እንቀበላለን” ብለዋል።ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን መዝጋቷን ተከትሎ የዓለም አቀፍ የነዳጅ እና ጋዝ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።በእስራኤል እና በአሜሪካ ለሚፈጸምባት ጥቃት አጸፋ ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የነዳጅ መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት እየፈጸመች ነው።ይህንንም ተከትሎ ዋና ዋና አገራት በኢራን ላይ የሚካሄደው ጦርነት ያስከተለውን ተጽእኖ ለመግታት በሚል ለድንገተኛ ጊዜ ካስቀመጡት ክምችታቸው ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ ለመልቀቅ ተስማምተዋል።ቀደም ሲል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ የሚደረግ ጉዞን ለመጠበቅ አገራት የባሕር ኃይላቸውን እንዲያዋጡ ጥሪ አቅርበው ነበር።ያጋሩ, ምዕራባውያን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመጠበቅ ፈቃደኝነታቸውን ገለጹ
  16. 19 መጋቢት 2026የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር በኢራን ላይ እየተካሄደ ስላለው ጦርነት ምን አሉ?የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴትየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት ከአገሪቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ዳን ኬይን ጋር በመሆን አገራቸው በኢራን ላይ ከእስራኤል ጋር በመሆን እያካሄደች ስላለው ጦርነት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫው ላይ የተነሱት ዋና ዋና ነጥቦች የትኞቹ ናቸው?
    • የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር አገሪቱ በጦርነቱ ላይ “በዕቅዷ” እና “በዒላማዋ” ላይ መሆኗን ተናግረዋል። ነገር ግን ጦርነቱ መቼ ሊያበቃ እንደሚችል የጊዜ ገደብ ሳያስቀምጡ ቀርተዋል። ግልጽ ለመሆን በማለትም “ቁርጥ ያለ የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ አንፈልግም” ብለዋል።
    • አሜሪካ በቴህራን ላይ እያካሄደች ያለው ጦርነት ዓላማዎችም ዳግመኛ ሲናገሩ ሚሳዔሎቿን እና የባሕር ኃይሏን ማውደም እንዲሁም “ኢራን ዳግም የኒውክሌር ጦር መሣሪያ አለማግኘቷን ማረጋገጥ” መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
    • አሜሪካ እስከ ዛሬ ድረስ 7000 የኢራን ዒላማዎችን አጥቅታለች ያሉ ሲሆን፣ “ምን እንደምናጠቃ እና ለምን እንደምናጠቃ ግልጽ ነው” ብለዋል።
    ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ዳን ኬይንየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ዳን ኬይን
    • ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ዳን ኬይን ለጋዜጠኞች የአሜሪካ ጦር በኢራን የአየር ክልል ምሥራቃዊ አካባቢ ዘልቆ በመግባት እና ኤኤች 64 አፓቼ ሂሊኮፕተሮችን በመጠቀም አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን “የማደን እና የማውደም” ሥራ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
    • ኬይን አክለውም ኢራን “ወደዚህ ጦርነት የገባችው በርካታ ጦር መሣሪያዎችን ታጥቃ ነው” ካሉ በኋላ፤ አሜሪካ የምትፈጽማቸው ጥቃቶች በተቻለ መጠን “ተከታታይ እና ጫን ያለ” የሆኑት ለዚያ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ኢራን አሁንም “የተወሰነ” ወታደራዊ አቅም አንዳላት ገልጸዋል።
    • በስተመጨረሻም ሄግሴት ፔንታጎን በኢራን ለሚካሄደው ጦርነት የ200 ቢለዮን ተጨማሪ በጀት ኮንግረሱ እንዲያጸድቅለት ስለመጠየቁ ሲናገሩ “ሊጨምር ይቸላል” ካሉ በኋላ “መጥፎ ሰዎችን ለመግደል ገንዘብ ይጠይቃል” ብለዋል።
    ያጋሩ, የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር በኢራን ላይ እየተካሄደ ስላለው ጦርነት ምን አሉ?
  17. 19 መጋቢት 2026ኢራን እና እስራኤል የኢነርጂ ጣቢያዎችን ማጥቃታቸውን ተከትሎ የጋዝ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል፤ እስካሁን ምን እናውቃለን?ነዳጅ የሚቀዳ እጅየፎቶው ባለመብት,EPA
    • የጋዝ ዋጋ ጭማሪ፡- ሐሙስ ዕለት በነበረው የኢነርጂ ግብይት የጋዝ ዋጋ ከ25 በመቶ በላይ ከፍ ብሏል። አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት ከከፈቱ ወዲህ በአውሮፓ የነዳጅ ዋጋ በፊት ከነበረው በእጥፍ ጭማሪ አሳይቷል።
    • በኢነርጂ ጣቢያዎች ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶች፡- ኢራን በኳታር የሚገኘውን የራስ ላፋን የጋዝ ማመንጫ ጣቢያ መትታ “ሰፊ ጉዳት” አድርሳለች። ቴህራን ጥቃት የፈፀመችው እስራኤል በኢራን እና በኳታር መካከል በሚገኘው የደቡብ ፓርስ የነዳጅ ማደያ ጣቢያ ላይ ለፈጸመችው ድብደባ ምላሽ ለመስጠት ነው። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሃብሻን የነዳጅ ማመንጫ ጣቢያ እና የጋዝ ማምረቻዎች ኢራን የበቀል እርምጃ ከወሰደች በኋላ ለመዝጋት ተገድዳለች። ሳውዲ አረቢያ ደግሞ በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል እና በዋና ከተማዋ ሪያድ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ማክሸፏ ተዘግቧል።
    • አሜሪካ “ምንም እንደማታውቅ” ናገራለች፡- ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል በደቡብ ፓርስ ላይ ስለፈጸመችው ጥቃት እንደማታውቅ ተናግረዋል። በተጨማሪም ኢራን በኳታር ላይ ተጨማሪ ጥቃቶችን እንዳትፈጽም አስጠንቅቀዋል።
    • የኢራን እና እስራኤል የሚሳዔል ተኩሶች፡- በመካከለኛው ምሥራቅ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ቀጥለዋል፤ የእስራኤል ጦር ቀደም ሲል ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳዔሎች መኖራቸውን አስታውቋል። የአገሪቱ የአደጋ ጊዜ አገልግሎት ስለደረሰ ጉዳት ምንም ያለው ነገር የለም። ይህ የሆነው የእስራኤል ጦር ረቡዕ ዕለት በሰሜን ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ በዒላማዎች ላይ የአየር ድብደባ መጀመሩን ከተናገረ በኋላ ነው።
    • የሆርሙዝ ወሽመጥ፦ የኢራን ፓርላማ አባላት በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦች የአገልግሎት ክፍያ እና ታክስ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ሕግ ላይ መወያየታቸው ተዘግቧል። 20 በመቶ የሚሆነው የዓለም ነዳጅ የሚተላለፈው በወሽመጡ በኩል ቢሆንም ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ኢራን ለማለፍ የሚሞክሩ መርከቦችን “በእሳት እለኩሳቸዋለሁ” ማለቷን ተከትሎ እንቅስቃሴዎች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል።
    ያጋሩ, ኢራን እና እስራኤል የኢነርጂ ጣቢያዎችን ማጥቃታቸውን ተከትሎ የጋዝ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል፤ እስካሁን ምን እናውቃለን?
  18. 19 መጋቢት 2026ኢራን የነዳጅ ተቋማቷ ዳግም ከተጠቁ የባሕረ ሰላጤውን ኢነርጂ መሠረተ ልማት እንደምታወድም ዛተችኢራን ዳግም የኢነርጂ ተቋማቷ ጥቃት የሚደርስባቸው ከሆነ የአሜሪካ እና የእስራኤል አጋር የሆኑ የባሕረ ሰላጤው አገራት የኢነርጂ መሠረተ ልማቶቸን “ሙሉ በሙሉ እስኪወድሙ ድረስ” እንደምትደበድብ አስጠነቀቀች።ቴህራን እስራኤል በደቡብ ፓርስ የሚገኝ የጋዝ ማምረቻ ላይ ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ በባሕረ ሰላጤው በሚገኙ የጋዝ እና ነዳጅ ዘይት ማምረቻ እና ማከማቻዎች ላይ ተከታታይ ጥቃት ፈጽማለች ብላለች።የኢራን ጦር ማዕከላዊ ዕዝ ቃል አቀባይ “የጠላቶቻችን ኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ የኢነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት በመፈጸማቸው ትልቅ ስህተት መሥራታቸውን አስጠንቅቀናቸዋል” ማለታቸውን ከጦሩ ጋር ግንኙነት ያለው የፋርስ ዜና ወኪል ዘግቧል።“ይሀ የሚደገም ከሆነ በእናንተ እና በአጋሮቻችሁ የኢነርጂ መሠረተ ልማት ላይ የምንፈጽመው ተከታታይ ጥቃት ሙሉ በሙሉ እስኪወድም ድረስ አይቋረጥም” ሲሉ ዝተዋል።አክለውም የኢራን ምላሽ ከዚህ ቀደም ከነበረው ጥቃት “በጣም ከባድ ሊሆን እንደሚችል” አስጠንቅቀዋል።ያጋሩ, ኢራን የነዳጅ ተቋማቷ ዳግም ከተጠቁ የባሕረ ሰላጤውን ኢነርጂ መሠረተ ልማት እንደምታወድም ዛተች
  19. 19 መጋቢት 2026ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚተላለፉ መርከቦችን ለማስከፈል እያሰበች ነውበሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ የቆሙ መርከቦችየፎቶው ባለመብት,EPAኢራን በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ በኩል የሚተላለፉ መርከቦች የአገልግሎት ክፍያ እና ታክስ ለኢራን እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ሕግ በአገሪቱ ፓርላማ አባላት መነጋገሪያ መሆኑ ተገለጸ።በኢራን ፓርላማ (መጅሊስ) ውስጥ የዋና ከተማዋ ቴህራን ተወካይ የሆኑት ሶማያህ ራፌ የሆርሙዝ ወሽመጥ ደኅንነቱ ተጠብቆ የመርከቦች፣ የነዳጅ እና የምግብ ምርቶች መተላለፊያ እንዲሆን ከተፈለገ ኢራን አስፈላጊውን ጥቅም እንድታገኝ የሚያደርግ ሕግ ላይ እየተሠራ መሆኑን አመልክተዋል።ኢስና የተባለው የኢራን ዜና አገልግሎት የፓርላማ አባሉ ቴህራን ውስጥ በሚገኝ አደባባይ ላይ ለሕዝብ ባደረጉት ንግግር ኢራን በሆርሙዝ ላይ የሚኖራትን የባለቤትነት ሥልጣንን አስረድተዋል።ኢራን “የሆርሙዝ ወሽመጥን ደኅንነት ማረጋገጥ እና የአገሪቱን ጥቅም መጠበቅ” ቀዳሚ አጀንዳዋ መሆኑን ጠቅሰው “አሁን ጠላቶቻችንን ያለችግር በምቾት ሲጠቀሙበት የነበረውን ነጥቀናቸዋል፤ ነገር ግን ይህንን እውነታ ለመቀበል አልቻሉም፤ ሊወጡት የሚችሉት አይደለም” በማለት በወሽመጡ መዘጋት የተፈጠረውን ሁኔታ አመልክተዋል።ጨምረውም “በፈጣሪ ፈቃድ በኢራን ወሳኝ እና እርግጠኛ ድል ጦርነቱ ይጠናቀቃል፤ ከዚያ በኋላም በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ማለፍ ለጠላቶቻችን ፈተና ይሆናል” ብለዋል።ያጋሩ, ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚተላለፉ መርከቦችን ለማስከፈል እያሰበች ነው
  20. 19 መጋቢት 2026አሜሪካ ወታደሮቿን በኢራን ደሴት እና በሆርሙዝ ወሽመጥ የማሰማራት ሃሳብ እንዳላት ተነገረየአሜሪካ ወታደር እና ታንክየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበመካከለኛው ምሥራቅ የሚካሄደው ጦርነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊሸጋገር ይችላል የሚል ስጋት የገባው የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን በማሰማራት ዘመቻውን ለማጠናከር እያሰበ መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ።የዜና ወኪሉ አንድ ባለሥልጣን እና ሦስት ምንጮችን ጠቅሶ ያወጣው ዘገባ እንደሚያሳየው፤ አሜሪካ በኢራን ላይ እያካሄደች ያለው ጦርነት ሦስተኛ ሳምንት እየተገባደደ ባለበት በአሁኑ ጊዜ አዲስ የሚሰማሩት ወታደሮች አሜሪካ ለምትወስደው እርምጃ ተጨማሪ አማራጮችን ሊሰጣት ይችላል።የአየር እና የባሕር ኃይልን በመጠቀም በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ደኅንነት መጠበቅም ተጨማሪ ወታደሮችን ከማሰማራት ጋር የሚወሰድ እርምጃ ሊሆን ይችላል ተብሏል።ሮይተርስ ያነጋገራቸው ምንጮች እንዳሉት የሆርሙዝ ሰርጥ መተላለፊያን የመጠበቁ ጉዳይ በኢራን የባሕር ዳርቻዎች ላይ ጭምር የአሜሪካ ኃይሎችን ማሰማራትን ሊጨምር ይችላል።በተጨማሪም ኢራን ወደ ውጭ ከምትልከው የነዳጅ ምርት 90 በመቶው በሚያልፍበት የኻርግ ደሴት ላይ እግረኛ ሠራዊትን ለማስፈር እያሰቡ መሆናቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል።አንድ ባለሥልጣን ግን ቦታዎቹ በኢራን የሚሳዔል እና የድሮን ዒላማ ስር በቀላሉ ስለሚወድቁ ይህ የአሜሪካ ወታደሮችን በኢራን ይዞታዎች ላይ የማሰማራት ዕቅድ አደጋ ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።ኢራን ጥቃት መፈጸሟን የምትቀጥል ከሆነ ለኢራን ከፍተኛ የነዳጅ ገቢ የሚያስገኘውን የኻርግ ደሴትን እንደሚያወድሙ ፕሬዝዳንት ትራምፕ አስጠንቅቀዋል።ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ አሜሪካ በወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ጥቃት የፈጸመችበት ኻርግ ደሴት ወሳኝ የነዳጅ መሠረተ ልማቶችን ያያዘ በመሆኑ ከማውደም ይልቅ በቁጥጥር ስር ማዋል የተሻለው አማራጭ እንደሆነ ወታደራዊ ባለሙያዎች ይመክራሉ።ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት ውስጥ እንደማይሳተፉ የገቡትን ቃል በማጠፋቸው በኢራን ላይ ለከፈቱት ጥቃት ከአሜሪካውያን ያገኙት ድጋፍ ዝቅተኛ ነው። በመሆኑም ወታደሮችን ወደ ኢራን የሚያሰማሩ ከሆነ ፕሬዝዳንቱ በአገር ውስጥ ከፍተኛ ፖለቲካዊ አደጋ ይገጥማቸዋል።ያጋሩ, አሜሪካ ወታደሮቿን በኢራን ደሴት እና በሆርሙዝ ወሽመጥ የማሰማራት ሃሳብ እንዳላት ተነገረ