
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ በተከፈተው ጦርነት ያቀድናቸውን “ግቦች ለማሳካት እጅግ በመቃረባችን” ጦርነቱን “ለማጠቃለል እያሰብን ነው” ሲሉ ተናገሩ። በሌላ በኩል ደግሞ የአሜሪካ ከፍተኛ የጦር አዛዦች የአገሪቱ ምድር ጦር ኢራን ውስጥ የሚሰማራበትን መንገድ በተመለከተ ዝርዝር እቅድ እንዳዘጋጁ እንዲሁም በሺህ ዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እየተጓዙ መሆኑ ተዘግቧል።
ጭምቅ ሃሳብ
- ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን ጦርነትን “ለማጠቃለል እያሰብን ነው” አሉ
- የትራምፕ አስተዳደር ኢራን ውስጥ ሊደረግ ለሚችል የምድር ጦር ስምሪት ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተዘገበ
- አሜሪካ በኢራን ነዳጅ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ በጊዜያዊነት አነሳች
- ዩናይትድ ኪንግደም፤ አሜሪካ የጦር ሰፈሮቿን ተጠቅማ በሆርሙዝ የሚገኙ ኢራን ይዞታዎችን እንድታጠቃ ፈቀደች
- የሆርሙዝ ወሽመጥ፡ የትራምፕ ራስ ምታት
- ኢራን 3,800 ኪሎ ሜትር በሚርቀው የአሜሪካ እና ዩኬ የጦር ሰፈር ላይ ሚሳዔል ማስወንጨፏ ተገለጸ
- ኢራን የብሪታኒያ ጦር ሠፈሮችን አሜሪካ እንድትጠቀም መፍቀድ “ጠብ አጫሪነት” ነው አለች
- የኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ ተገደሉ
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 3 ሰአት በፊትየኢራን ጦርነት፡ ኃያላን ያሻቸውን ማድረግ የሚችሉበት አዲሱ የዓለም ሥርዓት ጅማሬ?
በዩናይትድ ስቴትስ፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት በአዲሱ የዓለም ሥርዓት ውስጥ ከተካሄዱት ዋነኘው ሆኖ ሊታይ ይችላል።በዚህ ሥርዓት ውስጥ ለአስርተ ዓመታት የዓለም አቀፍ ባህሪን የሚቆጣጠሩት ሕጎች የነበራቸውን ተጽዕኖ እያጡ ነው።ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ በኋላ ለረዥም ጊዜ፣ ጦርነት እና ዲፕሎማሲ የሚካሄዱት በዓለም አቀፍ ሕግ፣ በተባበሩት መንግሥታት እና በሌሎች ተቋማት በተቀረጹ ማዕቀፎች ውስጥ ነበር።እነዚህ ደንቦች እና ስምምነቶች ለሚፈለገው ዓላማ እንዲውሉ ተደርገው ቢተረጎሙም፣ መንግሥታት እንቅስቃሴዎቻቸውን በአጠቃላይ በዚያ ሥርዓት ውስጥ ለማሳየት ይጥሩ ነበር።ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በተለምዶ በሕግ ክርክሮች፣ በዲፕሎማሲያዊ ምክክሮች ወይም በዓለም አቀፍ ጥምረት ምሥረታ የታጀቡ ነበሩ።በዚህ ጦርነት ግን እነዚህ ጉዳዮች በጣም ውስን ሚና ብቻ ያላቸው ይመስላሉ።ሙሉውን ትንታኔ እዚህ ያንብቡ ፡ የኢራን ጦርነት፡ ኃያላን ያሻቸውን ማድረግ የሚችሉበት አዲሱ የዓለም ሥርዓት ጅማሬ?ያጋሩ, የኢራን ጦርነት፡ ኃያላን ያሻቸውን ማድረግ የሚችሉበት አዲሱ የዓለም ሥርዓት ጅማሬ? - ከ 6 ሰአት በፊትየኢራን የኒውክሌር ጣቢያ ተመትቷል መባሉን ተከትሎ የተመድ ኒውክሌር ተቆጣጣሪ ተቋም ወታደራዊ እርምጃ እንዲቆም አሳሰበ
የፎቶው ባለመብት,EPA-EFE/REX/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲየተባበሩት መንግሥታት የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ተቋም፤ ኢራን በናታንዝ ኒውክሌር ተቋም ላይ ዛሬ ጠዋት ጥቃት እንደተፈጸመባት ከገለጸች በኋላ ባውጣው መግለጫ፤ “ማንኛውንም የኒውክሌር አደጋ ስጋት ለማስወገድ” ሲባል የጦርነቱ ተሳታፊ አካላት “ወታደራዊ እርምጃ ከመውስድ እንዲቆጠቡ” አሳሰበ።ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ በኤክስ ገጹ ባወጣው መግለጫ፤ የኢራን የኒውክሌር ስፍራ “ዛሬ ጥቃት እንደተፈጸመበት” ከቴህራም መስማቱን ገልጿል።“ከጣቢያው ውጭ ያለው የራዲዬሽን መጠን ላይ ምንም ዓይነት መጨመር አልተመዘገበም። ኤጀንሲው መረጃዎችን እያጣራ ነው” ሲል አስፍሯል።አክሎም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ “ማንኛውንም የኒውክሌር አደጋ ለማስወገድ ወታደራዊ ተዐቅቦ እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪያቸውን ያቀርባሉ” ብሏል።ኢራን ከቁልፍ የኒውክሌር ተቋማቷ አንዱ በሆነው ናታንዝ ላይ ጥቃቶች እንደተፈጸሙበት ያስታወቀችው ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት ነው።ከመሬት ስር ከሚገኙት የኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች አንዱ የሆነው ይህ ስፍራ ባለፈው ሐምሌ ላይ በአሜሪካ ተደብድቦ ነበር።ቴህራን የኒውክሌር ፕሮግራሟ ሙሉ ለሙሉ ለሰላማዊ ጥቅም የሚውል መሆኑን በመግለጽ፤ ኒውክሌር መሳሪያ እየሠራች ነው በሚል የሚቀርብባትን ክስ ውድቅ ታደርጋለች።ይሁን እንጂ ኢራን ለሰላማዊ የኒውክሌር ኃይል ከሚያስፈልገው እጅግ በበለጠ መልኩ የጥራት ደረጃው 60 በመቶ የደረሰ ዩራኒየም አበልጽጋለች። የኢራን ዩራኒየም ለጦር መሣሪያነት ለመዋል ለሚያስፈልገው 90 በመቶ የጥራት ደረጃ የቀረበ ነው።ጦርነቱ ከመጀመሩ ሁለት ቀናት አስቀድሞ ዋሽንግተን እና ቴህራን ስለ ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም እየተደራደሩ ነበር።ያጋሩ, የኢራን የኒውክሌር ጣቢያ ተመትቷል መባሉን ተከትሎ የተመድ ኒውክሌር ተቆጣጣሪ ተቋም ወታደራዊ እርምጃ እንዲቆም አሳሰበ - ከ 7 ሰአት በፊትየኢራን ሚሳዔል የተወነጨፈበት የአሜሪካ እና ዩኬ የጦር ሰፈር ምን ያህል ወሳኝ ስፍራ ነው?
የፎቶው ባለመብት,US National Archivesኢራን 3,800 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የአሜሪካ እና የዩናይትድ ኪንግደም የጋራ የጦር ሰፈር ዲዬጎ ጋርሺያ ላይ ሁለት ሚሳዔሎችን ማስወንጨፏን ቢቢሲ ተረድቷል። ይሁን እንጂ ሁለቱም ሚሳዔሎች የጦር ሰፈሩ ላይ አልደረሱም።የዩናይትድ ኪንግደም መከላከያ ሚኒስትር ሚሳዔሎች ስለመወንጨፋቸው ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ አልሰጠም። ነገር ግን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ፤ በመላው ቀጣናው የሚፈጸሙት የኢራን ግድ የለሽ ጥቃቶች “ለብሪታኒያ ጥቅሞች እና ለብሪታኒያ አጋሮች ስጋት ናቸው” ብሏል።አሜሪካ ከዲዬጎ ጋርሺያ የጦር ሰፈር “የመከላከያ የቦንብ ድብደባ” እንድትፈጽም ዩናይትድ ኪንግደም ፈቃድ ሰጥታለች። አሜሪካ እስካሁን የዩኬ ሉዐላዊ ግዛት ከሆነው የጦር ሰፈር ጥቃት ስለመፈጸሟ የወጣ መረጃ የለም።በህንድ ውቅያኖስ ላይ ከሚገኙ የቻጎስ ደሴቶች ውስጥ ትልቁ የሆነው ዲዬጎ ጋርሺያ የአሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም ጦር ኃይሎች በጋራ የሚጠቀሙበት ነው።ዲዬጎ ጋርሺያ ለአብዛኛዎቹ ሲቪሊያን ሰዎች ፈጽሞ ዝግ ሆነ ስፍራ ነው። ከደሴቱ ቅርብ የሆነው የመሬት ክፍል 1,609 ኪሎ ሜትር ይርቃል።ዩናይትድ ኪንግደም እና ሞሪሺየስ ለረጅም ጊዜ በዚህ ሩቅ ደሴት ሲወዛገቡ ቆይተዋል። ባለፈው ዓመት ግንቦት ላይ ዩናይትድ ኪንግደም ዲዬጎ ጋርሺያን ለ99 ዓመት በሚቆይ ሊዝ በዓመት 101 ሚሊዮን ፓውንድ እየከፈለች ለመከራየት ተስማምታለች።ዩናይትድ ኪንግደም ደሴቱን ለሞሪሺየስ መልሳ በድጋሚ ለመከራየት ማሰቧን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተቃውመው ነበር።ተጨማሪ ያንብቡ፦ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዩኬየቻጎስ ደሴቶችን ለሞሪሺየስ ለመመለስ መወሰኗን ተቹያጋሩ, የኢራን ሚሳዔል የተወነጨፈበት የአሜሪካ እና ዩኬ የጦር ሰፈር ምን ያህል ወሳኝ ስፍራ ነው? - ከ 7 ሰአት በፊትፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ “የኢራን ታማኝ ወዳጅ ሆና ትቀጥላለች” አሉ
የፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንየሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኢራንን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለአገሪቱ መሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ሞስኮ የቴህራን ታማኝ ወዳጅ ሆና ትቀጥለላች አሉ።የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ክሬምሊን እንዳለው ፑቲን ለጠቅላይ መሪው ሞጅታባ ኻሜኒ እና ለፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ “ኢራናውያን ይህንን አስቸጋሪ ጊዜ በክብር ያልፉታል” ብለዋል።ሩሲያ ከዚህ ቀደም አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጥቃት መላውን መካከለኛው ምሥራቅ ወደ ውድመት አፋፍ በመውሰድ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ ፈጥሯል ብለው ነበር።በተጨማሪም የሩሲያው ፕሬዝዳንት አሜሪካ እና እስራኤል የኢራኑን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒን ለመግደል የወሰዱትን እርምጃ በጽኑ አውግዘዋል።ነገር ግን ሩሲያ እየተካደሄ ባለው ጦርነት ውሰጥ ለኢራን እደያረገች ነው በሚባለው ድጋፍ ዙሪያ አተስማማኝ መረጃ የለም።አንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን ግን ሩሲያ ለኢራን የመረጃ ድጋፍ እንደምትሰጥ ዘግበዋል። የአሜሪካው ጋዜጣ ዎል ስትሪት ጆርናል ሩሲያ ለኢራን የሳተላይት ምሥሎችን እና ዘመናዊ የድሮን ቴክኖሎጂ ታጋራለች ብሎ የዘገበውን የፕሬዝዳንቱ ጽፈህት ቤት አስተባብሎታል።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ “የኢራን ታማኝ ወዳጅ ሆና ትቀጥላለች” አሉ - ከ 9 ሰአት በፊትአሜሪካ የኢራንን የኒውክሌር ቁሶች ‘ለመቆጣጠር’ እያሰበች ነው፤ ዛሬ አንድ ተቋም ተመትቷል
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የናታንዝ የኒውክሌር ኃይል ማብላያ ማዕከል፣ ከሁለት ሳምንት በፊት የተነሳ ፎቶየትራምፕ አስተዳደር፤ አሜሪካ የኢራን የኒውክሌር ቁሶችን ለመቆጣጠር ወይም ለማስወገድ የምትችበልትን መንገድ እየፈተሸ መሆኑ ሲነገር፤ ዛሬ ጠዋት ደግሞ አንድ የኒውክሌር ተቋም መመታቱን የኢራን መንግሥት አስታወቀ።የተለያዩ ምንጮች በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ለሆነው ሲቢኤስ ኒውስ እንደተናገሩት ወሳኞቹን የኢራን የኒውክሌር ተቋማት ቁሶችን ከአገሪቱ እጅ ለማስወጣት ሃሳብ አለ።እየተዘጋጁ ያሉት ዕቅዶች “የልዩ ተልዕኮ ዕዝ” የተባለውን ልዩ የጦር ክፍል አባላትን ማሰማራት ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን ሁለት ምንጮች ተናግረዋል። ይህ ዕዝ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልጉ ተልዕኮዎችን የሚወጣ የአሜሪካ ሠራዊት ክፍል ነው።ሌላ ምንጭ ደግሞ ፕሬዝዳት ዶናልድ ትራምፕ የኒውክሌር ቁሶችን ለመቆጣጠር የሚወሰደውን እርምጃ በተመለከተ በወጣው ዕቅድ ላይ አስካሁን ምንም ዓይነት ውሳኔ እንዳልሰጡ ገልጸዋል።በጉዳዩ ላይ አስተያየት የተጠየቁት የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ ለሲቢኤስ በሰጡት ምላሽ፤ እንዲህ ያለው ኃላፊነት የሚመለከተው የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴርን (ፔንታገን) ነው ብለዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራን አውቶሚክ ኤነርጂ ድርጅት በዛሬው ዕለት ናታንዝ የሚገኘው የአገሪቱ የኒውክሌር ተቋም በድጋሚ የጥቃት ዒላማ መሆኑን አስታውቋል።ጥቃቱን ተከትሎ የራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገር አፈትልኮ እንደሆነ ግምገማ ተደርጎ በአካባቢው ለሚኖሩ ሰዎች የሚያሰጋ ሁኔታ እንደሌለ መረጋገጡን ድርጅቱ እንዳስታወቀ በኢራን የዜና ምንጮች ላይ የቀረበው መግለጫ ያሳያል።የኒውክሌር ተቋሙ ከሁለት ሳምንት በፊት ጥቃት ተፈጽሞበት የነበረ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ሰኔ ላይም እንዲሁ ከሌሎች የአገሪቱ የኒውክሌርተቋማት ጋር በአሜሪካ ከባድ ቦምቦች ተመትቶ ነበር።በወቅቱ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም “ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጪ ሆኗል” ብለው ነበር።ያጋሩ, አሜሪካ የኢራንን የኒውክሌር ቁሶች ‘ለመቆጣጠር’ እያሰበች ነው፤ ዛሬ አንድ ተቋም ተመትቷል - ከ 9 ሰአት በፊት“አሜሪካ ጦርነቱን ለማቆም የተዘጋጀች አትመስልም” – የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ የሚካሄደውን ዘመቻ ለማጠናቀቅ እያሰቡ መሆናቸው መነገሩን ተከትሎ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሜሪካ ግን ለዚያ የተዘጋጀች አትመስልም አሉ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ “ይህ ጦርነት በኢራን ላይ የተጫነ” መሆኑን በመጥቀስ ጦርነቱን ሙሉ ለሙሉ የሚያስቆም “የትኛውንም ተነሳሽነት” እንደምትቀበለው ተናግረዋል።ሚኒስትሩ ኪዮዶ ለተባለው የጃፓን መገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት ኢራን ጦርነቱን ለማስቆም የሚቀርቡ “ሃሳቦችን ለመስማት እና ለማጤን ዝግጁ ናት” ብለዋል።ነገር ግን ምንም እንኳን አንዳንድ አገራት በመካከለኛው ምሥራቅ ለተከሰተው ጦርነት መፍትሄ እየፈለጉ ቢሆንም፤ “አሜሪካ ግን ጠብ ጫሪነቷን ለመተው የተዘጋጀች አትመስምልም” ሲሉ ተናግረዋል።አራግቺ ጨምረውም ኢራን የምትፈልገው ተኩስ ማቆም ሳይሆን “የተሟላ፣ ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ የጦርነት ማቆም” ስምምነት መሆኑን አሳውቀዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስሩ ከጃፓኑ መገናኛ ብዙኃን ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በቴሌግራም አካውንታቸው ላይ የጋሩ ሲሆን፣ ከኢራን መንግሥት የፕሮፓጋንዳ ተቋማ ጋር ግንኙነት ያለው ሜህርስ የዜና ወኪል የቃለ ልምልልሱን የጽሁፍ ግልባጭ አትሞታል።ያጋሩ, “አሜሪካ ጦርነቱን ለማቆም የተዘጋጀች አትመስልም” – የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር - 21 መጋቢት 2026ኢራን 3,800 ኪሎ ሜትር በሚርቀው የአሜሪካ እና ዩኬ የጦር ሰፈር ላይ ሚሳዔል ማስወንጨፏ ተገለጸ
ኢራን፤ ዲዬጎ ጋርሺያ በተባለው የአሜሪካ እና የዩናይትድ ኪንግደም ጋራ የጦር ሰፈር ላይ ሁለት መካከለኛ ርቀት ተወንጫፊ ባለስቲክ ሚሳዔሎችን መተኮሷን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።ዎል ስትሪት ጆርናል ጋዜጣ በርካታ ምንጮችን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ፤ የተተኮሱት ሁለቱም ሚሳዔሎች በሕንድ ውቅያኖስ ላይ የሚገኘውን ጦር ሰፈር እንዳልመቱት አስታውቋል።ሴኤንኤን በበኩሉ፤ ሚሳዔሎቹ የተተኮሱት በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር አርብ ንጋት ላይ እንደሆነ ከአሜሪካ ባለሥልጣን መስማቱን ዘግቧል።ከኢራን እስከ ዲዬጎ ጋርሺያ ያለው ርቀት 3,800 ኪሎ ሜትር ገደማ ነው። የቀድሞው ኢራን ጠቅላይ መሪ የአገሪቱ ሚሳዔል የሚወነጨፍበት ርቀት ከ2,000 እንዳይበልጥ ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር።ቢቢሲ ስለ ጥቃቱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ለአሜሪካ ፔንታገን እና ለዩናይትድ ኪንግደም መከላከያ ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቧል። የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስቴር ፔንታጎን “በአሁኑ ሰዓት ማቅረብ የሚችለው ምንም ነገር እንደሌለ” ገልጿል።
ያጋሩ, ኢራን 3,800 ኪሎ ሜትር በሚርቀው የአሜሪካ እና ዩኬ የጦር ሰፈር ላይ ሚሳዔል ማስወንጨፏ ተገለጸ - 21 መጋቢት 2026የሆርሙዝ ወሽመጥ፡ የትራምፕ ራስ ምታትኢራን ላይ የሚካሄደው የአሜሪካ እና የእስራኤል ዘመቻ ከተጀመረ በኋላ ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋቱ የጦርነቱ ተጽእኖ በመላው ዓለም እንዲሰማ አድርጓል።ለፕሬዝዳንት ትራምፕም ዋነኛ ራስ ምታት የሆነው የባሕር መተላለፊያው መስመር ጉዳይ ነው። አጋር አገራት ሆርሙዝን በመጠበቅ እንዲያግዟቸው ቢጠይቁም ሰሚ ሳያገኙ ቀርተዋል።ትራምፕ መርከቦች በሆርሙዝ በኩል እንዲያልፉ ለማድረግ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ ያሳወቁ ሲሆን ሊረዷቸው ፈቃደኛ ያልሆኑትን የኔቶ አጋሮቻቸውን ደግሞ ክፉኛ ተችተዋል።ኢራንም ለተከፈተባት ጥቃት አጸፋ በጠባቡ የባሕር መተላለፊያ ላይ የሚገኝን ማንኛውንም መርከብ “እንደምታጋይ” ማሳወቋን ተከትሎ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ “አስፈላጊ ከሆነ አሜሪካ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን በባሕር ኃይሏ ታጅባለች” ብለው ነበር።ቀጥለው ደግሞ ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚተላለፈውን ነዳጅ “ለማስቆም ማንኛውንም ነገር የምታደርግ ከሆነ፤ ከተፈጸመባት ድብደባ ከሃያ እጥፍ በላይ በሆነ ኃይል ትመታለች” ብለዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ በተጨማሪም አጋሮቻቸው የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማስከፈት እንዲተባበሩ የጠየቁ ሲሆን፣ “በርካታ አገራት በተለይም በመዘጋቱ የተጎዱት የጦር መርከቦችን ይልካሉ” ብለው ነበር።ነገር ግን የቅርብ አጋሮቻቸው የሆኑት የኔቶ አባላት እስራኤል እና አሜሪካ በከፈቱት ጦርነት ውስጥ የመሳተፍ ፍላጎት እንደሌላቸው በመግለጽ እራሳቸውን አርቀዋል።በዚህም የተነሳ የኔቶ አጋሮቻቸውን “ፈሪዎች” ሲሉ ዘልፈዋል። “የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ በማለት ያማርራሉ፤ ነገር ግን በቀላል ወታደራዊ ስምሪት የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማስከፈት መተባበር አይፈለጉም” ሲሉም ተችተዋቸዋል።
ያጋሩ, የሆርሙዝ ወሽመጥ፡ የትራምፕ ራስ ምታት - 21 መጋቢት 2026ዩናይትድ ኪንግደም፤ አሜሪካ የጦር ሰፈሮቿን ተጠቅማ በሆርሙዝ የሚገኙ ኢራን ይዞታዎችን እንድታጠቃ ፈቀደች
የፎቶው ባለመብት,EPAዩናይትድ ኪንግደም፤ አሜሪካ በወሳኙ የባሕር መተላለፊያ ሆርሙዝ ወሽመጥ የሚገኙ የኢራን ይዞታዎች ላይ ለምትፈጽማቸው ጥቃቶች የጦር ሰፈሮቿን እንድትጠቀም ፈቀደች። ኢራን፤ ይህ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ውሳኔ “የብሪታኒያ ዜጎችን ሕይወት አደጋ ላይ ይጥላል” በማለት አስጠንቅቃለች።የአገሪቱ መንግሥት ከዚህ ቀደም ኢራን የብሪታኒያን ጥቅም እና ዜጎች የሚጎዳ የሚሳዔል ጥቃት እንዳትፈጽም ለመከላከል በሚከናወኑ ዘመቻዎች ወቅት የአሜሪካ ኃይሎች የብሪታኒያ የጦር ሠፈሮችን እንዲጠቀሙ ፈቅዶ ነበር።የዩናይትድ ኪንግደም ሚኒስትሮች አርብ ምሽት ባደረጉት ስብሰባ፤ አሜሪካ የጦር ሠፈሮቹን የምትጠቀምበትን ዓላማ አስፍተዋል።በዚህም በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ መርከቦችን መጠበቅን ጨምሮ ለዘመቻዎቿ እንድትትጠቀም ፈቅደዋል።ይህ ውሳኔ ቢተላለፍም አሁንም ዩናይትድ ኪንግደም ጦርነቱ ውስጥ በቀጥታ እንደማትሳተፍ የአገሪቱ መንግሥት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። “ዩናይትድ ኪንግደም ጦርነቱን በተመለከተ ከያዘችው አቋም ጀርባ ያሉት መርሆዎች ተመሳሳይ ሆነው ይቀጥላሉ” ብሏል።የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ እንደተናገሩት የጦር ሰፈሮቹ “በሆርሙዝ ወሽመጥ በመርከቦች ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሚውሉ አቅሞችን” ዒላማ በማድረግ ለሚከናወኑ “የአሜሪካ የመከላከያ ዘመቻዎች” ጥቅም ላይ እንዲውሉ ሚኒስትሮቹ ተስማምተዋል።ስለዚህ ውሳኔ አስተያየት የሰጡት የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር አሜሪካ የብሪታኒያ ጦር ሰፈሮችን እንድትጠቀም በመፍቀዷ “የብሪታኒያ ዜጎችን ሕይወት አደጋ ላይ ጥለዋል” ብለዋል።ኢራን “ራሷን የመከላከል መብቷን ትጠቀማለች” ሲሉም አሳስበዋል። አራግቺ በኤክስ ገጻቸው ባጋሩት ልጥፍ “በርካታው የብሪታኒያ ሕዝብ እስራኤል እና አሜሪካ ኢራን ላይ በወሰዱት የጦርነት ምርጫ በምንም መልኩ መሳተፍ አይፈልግም” ብለዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ስታርመር የራሱነ ሕዝብ ችላ ብሎ የዩናይትድ ኪንግደም የጦር ሠፈሮች በኢራን ላይ ለሚፈጸም ጥቃት ጥቅም እንዲውሉ በመፍቀድ የብሪታኒያውያንን ሕይወት አደጋ ላይ ጥሏል” በማለት ጽፈዋል።ያጋሩ, ዩናይትድ ኪንግደም፤ አሜሪካ የጦር ሰፈሮቿን ተጠቅማ በሆርሙዝ የሚገኙ ኢራን ይዞታዎችን እንድታጠቃ ፈቀደች - 21 መጋቢት 2026አሜሪካ በኢራን ነዳጅ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ በጊዜያዊነት አነሳች
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የግምጃ ቤት ሚኒስትሩ ስኬት ቤሴንትበከፍተኛ መጠን የጨመረው የነዳጅ ዋጋ እንዲቀንስ እየጣረ ያለው የአሜሪካ መንግሥት ግምጃ ቤት፤ ቀድሞውኑም ባሕር ላይ ያለ የኢራን ነዳጅ ለ30 ቀናት በማዕቀብ ነጻ እንዲሆን ወሰነ።የግምጃ ቤት ሚኒስትሩ ስኮት ቤሴንት “ይህ የአጭር ጊዜ ፈቃድ” 140 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ወደ ዓለም የኢነርጂ ገበያ እንዲገባ እንደሚያደርግ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል።ይሁን እንጂ ኢራን ከነዳጅ ሽያጩ የሚገኘውን ትርፍ “ለማግኘት አዳጋች” እንደሚሆንባት ቤሴንት ተናግረዋል።የማዕቀብ ማንሳት ውሳኔው “ቀድሞውኑ እየተጓጓዘ ያለ ነዳጅ ላይ ብቻ ተገደበ” መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ “አዲስ ግዢን ወይም ምርት አይፈቅድም” ብለዋል።“በመሠረቱ የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ የኢራንን በርሜሎች በራሷ በቴህራን ላይ እንጠቀማለን” በማለት ጸፈዋል።የኢራን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ እንዲሁም ቴህራን በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ የኢነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ከፈጸመች በኋላ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኘ መጠን ጨምሯል።የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ አርብ ዕለት የ3 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በበርሜል 113 ዶላር ገብቷል። ይህ ዋጋ ካባለፈው ዓመት ጋር ሲጻጸር የ53 በመቶ ጭማሪ አለው።ያጋሩ, አሜሪካ በኢራን ነዳጅ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ በጊዜያዊነት አነሳች - 21 መጋቢት 2026የትራምፕ አስተዳደር ኢራን ውስጥ ሊደረግ ለሚችል የምድር ጦር ስምሪት ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተዘገበ
የፎቶው ባለመብት,EPAየአሜሪካ መከላከያ መሥሪያ ቤት (ፔንታጎን) ባለሥስልጣናት የአገሪቱ እግረኛ ጦር ኢራን ውስጥ የሚሰማራበትን መንገድ በተመለከተ ዝርዝር ዕቅድ ማዘጋጀታቸውን በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ኒውዝ ዘገበ።በሌላ በኩል በሺህዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች እና ሦስት ተጨማሪ የጦር መርከቦች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እየተሰማሩ መሆኑን የዜና ወኪሎቹ አሶሺዬትድ ፕሬስ እና ሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።ሲቢኤስ ኒውስ በጉዳዩ ላይ ገለጻ የተደረገላቸውን ምንጮች ጠቅሶ ያወጣው ዘገባ እንደሚያሳየው፤ ከፍተኛ የአሜሪካ የጦር አዛዦች ኢራን ውስጥ እግረኛ ወታደሮችን የማሰማራትን አማራጭ በተመለከተ ዝግጅት ለማድረግ ጥያቄ አቅርበዋል።ምንጮች እንደገለጹት፤ ትራምፕ በቀጣናው የምድር ጦር ማሰማራትን በተመለከተ እያሰቡበት ነው። ፕሬዝዳንቱ በምን ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ እግረኛ ወታደሮችን ሊጠቀሙ ይችላሉ የሚለው ግልጽ እንዳልሆነ ዘገባው ያመለክታል።ትራምፕ ሐሙስ ዕለት በዋይት ሐውስ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ግን “ወታደሮችን ወደ የትም አላሰማራም” ብለው ነበር።ፕሬዝዳንቱ እግረኛ ጦር ሊያሰማሩ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ “ቢሆን በእርግጠኝነት እነግራችሁ ነበር” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።ፕሬዝዳንቱ ይሄንን ቢሉም ተጨማሪ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እየተጓዙ እንደሆነ አሶሺዬትድ ፕሬስ እና ሮይተርስ ዘግበዋል።የኤፒ ዘገባ እንደሚያመለክተው ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚላኩት ሦስት ተጨማሪ የባሕር ላይ ጥቃት ፈጻሚ የጦር መርከቦች እና 2,500 ወታደሮች ናቸው።የሚሰማሩት ወታደሮች ወደፊት ሊከናወን በሚችል ዘመቻ ላይ እገዛ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሮይተርስ ዘገባ ያሳያል። የዜና ወኪሉ በዘገባው፤ ትራምፕ ኢራን ውስጥ ወታደሮችን የማሰማራት ሀሳብን በተመለከተ ውሳኔ ላይ አልደረሱም ብሏል።ያጋሩ, የትራምፕ አስተዳደር ኢራን ውስጥ ሊደረግ ለሚችል የምድር ጦር ስምሪት ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተዘገበ - 21 መጋቢት 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን ጦርነትን “ለማጠቃለል እያሰብን ነው” አሉ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ በተከፈተው ጦርነት ያቀድናቸውን “ግቦች ለማሳካት እጅግ በመቃረባችን” ጦርነቱን “ለማጠቃለል እያሰብን ነው” ሲሉ ተናገሩ።ኢራን የዘጋችውን የሆርሙዝ ወሽመጥ የማስከፍት ጉዳይ ግን የመርከብ መተላለፊያ መስመሩን “የሚጠቀሙት አገራት” ኃላፊነት መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።ትራምፕ ‘ትሩዝ ሶሻል’ በተባለው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ “ግቦቻችንን ለማሳካት በጣም እየተቃረብን በመሆኑ፤ ሽብርተኛውን የኢራን አገዛዝ በተመለከተ፤ በመካከለኛው ምሥራቅ የምናደርገውን ታላቅ ወታደራዊ ጥረት ለማቆም እያሰብን ነው” ብለዋል።እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ ኢራን ላይ የተከፈተው ጥቃት አምስት ዓላማዎች ነበሩ። በቀዳሚነት የጠቀሱት “የኢራንን ሚሳዔል አቅም፣ ማስወንጨፊያዎች እና ተያያዥነት ያላቸው ነገሮችን በጠቅላላ ሙሉ በሙሉ ማዳከም” የሚለውን ነው።“የኢራንን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ሰፈርን ማውደም” እንዲሁም የአገሪቱን “የባሕር እና የአየር ኃይል፣ የፀረ-አውሮፕላን የጦር መሣሪያዎችን ጭምር ማጥፋት” የሚለውን ከግቦቹ መካከል ጠቅሰዋል።ትራምፕ በአራተኛነት የጠቀሱት ግብ “ኢራን ፈጽሞ ወደ ኒውክሌር አቅም እንዳትቀርብ ማድረግ” እና አድርጋ ከተገኘችም አሜሪካ “በፍጥነት እና በኃይል ምላሽ መስጠት የምትችልበት ደረጃ” ላይ እንድትሆን ማድረግን ነው።እንዲሁም እስራኤል፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኳታር፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ባህሬን፣ ኩዌት እና ሌሎችንም የመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ አጋሮችን “በከፍተኛ ደረጃ መጠበቅ” ከግቦቹ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።ፕሬዝዳንቱ በዚህ ልጥፋቸው የተለያዩ አገራትን እገዛ ጠይቀው በጎ ምላሽ ስላላገኙበት የሆርሙዝ ወሽመጥ ጉዳይም አንስተዋል።“እንደ አስፈላጊነቱ የሆርሙዝ ወሽመጥ በሚጠቀሙበት ሌሎች አገራት ሊጠበቅ እና ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል፤ አሜሪካ ግን አትጠቀምበትም!” ሲሉ የባሕር መስመሩን ማስከፈት የአገራቸው ኃላፊነት እንዳልሆነ አመልክተዋል።ይሁን እንጂ ወሽመጡን የሚጠቀሙበት አገራት የአሜሪካንን እገዛ ፈልገው ጥያቄ የሚያቀርቡ ከሆነ ግን “እናግዛቸዋለን” ብለዋል።“ነገር ግን አንዴ የኢራን ስጋት ከተወገደ በኋላ ግን [የሆስሙዝ ወሽመጥን መጠበቅ] አስፈላጊ አይሆንም። ቀላል ወታደራዊ ዘመቻ ይሆንላቸዋል” ሲሉ ጽፈዋል።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን ጦርነትን “ለማጠቃለል እያሰብን ነው” አሉ - 20 መጋቢት 2026ትራምፕ የኔቶ አጋሮቸውን ‘ፈሪዎች’፣ ኔቶን ደግሞ ‘የወረቀት ላይ ነብር’ ሲሉ ወረፉ
የፎቶው ባለመብት,Gettyየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኔቶ አጋሮቻቸው የሆርሙዝ ወሽመጥን ከኢራን ጥቃት ለመጠበቅ እንዲተባበሯቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ባለመቀበላቸው “ፈሪዎች” ሲሉ፣ ማኅበሩን ደግሞ አሜሪካ ባትኖርበት ደካማ ይሆን ነበር ሲሉ ተቹ።ፕሬዝዳንቱ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚተላለፉ መርከቦችን መጠበቅ ለኔቶ አባል አገራት “ቀላል” ይሆን ነበር በማለት ለመሳተፍ ባለመፍቀዳቸው “ፈሪዎች” በማለት ተችተዋቸዋል።ትራምፕ በትሩዝ የማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሠራጩት ጽሁፍ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን አገራት ማኅበር ኔቶን እና አባላቱን ክፉኛ አብጠልጥለዋቸዋል።”ካለ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ኔቶ የወረቀት ላይ ነብር ነው። ኢራን ኒውክሌር እንዳትታጠቅ በሚደረገው ፍልሚያ ውስጥ ለመሳተፍ አልፈለጉም።”አሁን ጦርነቱን በወታደራዊ ኃይል አሸንፈናል፣ እነሱ [የኔቶ አባላት] በነዳጅ ዋጋ መጨመር እያማረሩ ነው። ነገር ግን የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ለመጨመሩ ብቸኛው ምክንያት የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥን በቀላል ወታደራዊ ስሪት ለማስከፈት ለማገዝ ፈቃደኛ አልነበሩም” ሲሉ ወቅሰዋል።”በትንሽ ዋጋ በቀላሉ የሚፈጽሙት ነገር ነበር። ፈሪዎች፣ አንረሳውም!” በማለት የኔቶ አጋሮቻቸውን አጥብቀው ወርፈዋል።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጥቃት ተከትሎ ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በሚያልፉ ግዙፍ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ጥቃት በመፈጸሟል የነዳጅ ምርት መንቀሳቀስ ባለመቻሉ በዓለም ዙሪያ ዋጋው ጨምሯል።አሜሪካም የኔቶ አባል አገራት በወሽመጡ በኩል የሚያልፉ መርከቦችን ደኅነንት በመጠበቅ እንዲያግዙ ብትጠይቅም ወደ ጦርነቱ መግባት እንደማይፈልጉ በመለግጽ ጥያቄውን ሳይቀበሉት በመቅረታቸው ትራምፕ ተቆጥተው ቆይተዋል።ያጋሩ, ትራምፕ የኔቶ አጋሮቸውን ‘ፈሪዎች’፣ ኔቶን ደግሞ ‘የወረቀት ላይ ነብር’ ሲሉ ወረፉ - 20 መጋቢት 2026ኢራን የአሜሪካ እና የእስራኤል ባለሥልጣናትን በየትኛም ቦታ ዒላማ እንደምታደርግ ዛተች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት በርካታ ባለሥልጣናቷ የተገደሉባት ኢራን በአጸፋው የአሜሪካንን እና የእስራኤልን ባለሥልጣናት እንዲሁም ወታደራዊ አዛዦችን በየትኛውም ቦታ ላይ ዒላማ እንደምታደርግ ዛተች።ዛሬ አርብ የኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ የአገሪቱ ጦር ኃይሎች ቃል አቀባይ የሆኑትን አቦልፋዚል ሼካርቺን ጠቅሶ እንደዘገበው በሁለቱ አገራት ባለሥልጣናት ላይ ለሚፈጽሙት ጥቃት የአገሪቱ ሠራዊት ክትትል እያደረገ መሆን አመልክቷል።ቃል አቀባዩ “ፈሪዎቹን ባለሥልጣኖቻችሁን፣ የጦር አዛዦቻችሁን፣ ፓይለቶቻችሁን እና ወታደሮቻችሁን በዐይነ ቁራኛ እየተከታተልናቸው ነው” ብለዋል።አክለውም “በዓለም ዙሪያ ባሏችሁ ፓርኮች፣ የመዝናኛ ቦታዎች እና ቱሪስቶች ውስጥ ባለን መረጃ መሠረት ከዚህ በኋላ ደኅንነታችሁ የተጠበቀ አይሆንም” በማለት ዒላማ እንደሚያደርጓቸው ዝተዋል።ሦስት ሳምንት በሆነው ጦርነት የአገሪቱን ጠቅላይ መሪን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ኢራን ተገድለውባታል።ያጋሩ, ኢራን የአሜሪካ እና የእስራኤል ባለሥልጣናትን በየትኛም ቦታ ዒላማ እንደምታደርግ ዛተች - 20 መጋቢት 2026በጦርነት ውስጥ ሆነው አዲስ ዓመታቸውን የተቀበሉት ኢራናውያን
የፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,በዋና ከተማዋ ቴህራን ለበዓል ሸመታ ሐሙስ ዕለት ገበያ የወጡ ኢራናውያንአሜሪካ እና እስራኤል የከፈቱባትን ጥቃት ተከትሎ ሦስት ሳምንት በሆነው ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ኢራን በራሷ የዘመን አቆጣጠር መሠረት ዛሬ አርብ አዲስ ዓመቷን ጀምራለች።‘ኖውሩዝ’ በመባል የሚጠራውን የፋርስ አዲስ ዓመት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ላይ እየተጸመ ባለው ጥቃት እና ኢራን በበኩሏ በአጸፋው በምትሰነዝረው ጥቃት የጦርነት ስጋት ስር ሆነው ኢራናውያን እየተቀበለው ነው።በስጋት ውስጥ ያሉት ኢራናውያን አዲሱ ዓመት ምን ይዞ እንደሚመጣ እርግጠኛ አይደሉም።አሚር እንደለሚው “በጦርነቱ ምክንያት ሰዎች ሥራቸውን እያጡ ነው። ከሁሉ የሚያሳስበን የአገራችን መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው ጉዳት ነው” ብሏል።ለሦስት ሳምንታት በዘለቀው ያልተቋረጠ ጥቃት በርካታ የኢራን ተቋማት ዒላማ ሆነዋል።በዚህም ምክንያተ “በሚታየው ሁኔታ ብዙ የሚተርፍ ነገር የሚኖር አይመለስኝም። ይሄ የመጨረሻችን አዲስ ዓመት እንዲሆን አልፈልግም” በማለት አሚር ስጋቱን ገልጿል።ይህ የአዲስ ዓመት አከባበር ለጥንታዊቷ አገር ኢራን ዜጎች ታሪካቸው እና ብሔራዊ መለያቸው ሲሆን፣ ላለፉት ሦስት ሺህ ዓመታት ሲከበር የዘለቀ መሆኑ ይነገራል።ለወትሮው በአዲሱ የኢራን አዲስ ዓመት ወቅት በአገሪቱ የሚገኙ የገበያ ቦታዎች፣ የገበያ ማዕከላት እና መንገዶች በሕዝብ ተሞልተው የሚደምቁ ሲሆን፣ የዘንድሮው ግን ለየት ብሏል።ዘንድሮ የአዲስ ዓመት ድባቡ ቀዝቀዝ ያለ ቢሆንም፤ አንዳንድ ኢራናውያን በለመዱት መንገድ ለአዲሱ ዓመት በዓል አከባበር መዘጋጀታቸው ተዘግቧል።የዋና ከተማዋ ቴህራን ነዋሪ የሆነችው ፓርሚስ በዚህ ሁሉ ውስጥ ለበዓሉ ከተዘጋጁት መካከል ናት።”እንደ እኔ ሁሉ አንዳንዶች በዚህ ሁሉ ውስጥ የለመዱትን ማከናወን ቀጥለዋል። ለምሳሌ ከባድ ፍንዳታ በተከሰተበት ጊዜ የውበት ሳሎን ውስጥ ነበርኩ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ማንም ንቅንቅ አላለም” በማለት በዙሪያዋ ያሉ ሰዎች ካለው ሁኔታ ጋር እየተላመዱ መሆናቸውን ገልጻለች።*በዘገባው ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ስም ለደኅንነታቸው ሲባል ተቀይሯል።ያጋሩ, በጦርነት ውስጥ ሆነው አዲስ ዓመታቸውን የተቀበሉት ኢራናውያን - 20 መጋቢት 2026የአቡ ዳቢ ፖሊስ ከ100 በላይ የተለያዩ አገራት ዜጎችን በቁጥጥር ስር አዋለ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,አቡ ዳቢ በኢራን የአጸፋ ጥቃት ከተመቱ የባሕረ ሰላጤው ከተሞች አንዷ ናትበዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የአቡ ዳቢ ፖሊስ የተለያዩ አገራት ዜግነት ያላቸው ከ100 በላይ ሰዎች በአገሪቱ ላይ ከሚፈጸመው ጥቃት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ቦታዎችን “በመቅረጽ እና አሳሳች መረጃን” በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በማጋራት መያዙን አሳወቀ።ፖሊስ በኤክስ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ የተለያዩ 109 ሰዎች በሕዝቡ መካከል የተሳሳተ አመለካከትን የሚፈጥሩ እና ያልተረጋገጡ ወሬዎችን በማሠራጨት በቁጥጥር ስር አውሏል።ፖሊስ ጨምሮም ማኅበራዊ ሚዲያን ተገቢ ላልሆነ ዓላማ የሚጠቀሙ ሰዎችን በመከታተል የአገሪቱ የደኅንነት ባለሥልጣን አስፈላጊው ሕጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።የአገሪቱ ዜጎች ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት እና ከሚታመኑ ምንጮች ብቻ መረጃ እንዲያገኙ በማሳሰብ የሕዝብ ጥቅምን እና አሠራሮችን በማክበር ከአንዳንድ ቦታዎች “ፎቶ ከማንሳት እና ቪዲዮ ከመቅረጽ እንዲሁም ከማጋራት እንዲቆጠቡ” አሳስቧል።ያጋሩ, የአቡ ዳቢ ፖሊስ ከ100 በላይ የተለያዩ አገራት ዜጎችን በቁጥጥር ስር አዋለ - 20 መጋቢት 2026አንድ የእስራኤል ሠራዊት አባል ለኢራን በመሰለል ተጠርጥሮ ተያዘ
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የተያዘው ወታደር የእስራኤል የአየር ጥቃት መከላከያ አባል ነበርየእስራኤል ፖሊስ አንድ የአገሪቱ ጦር ተጠባባቂ አባል ለኢራን ሲሰልል ነበር በሚል ጥርጣሬ በቁጥጥር ስር መዋሉን ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።የፈረንሳይ ዜና ወኪል የፖሊስ መግለጫን ጠቅሶ እንደዘገበው “ራዝ ኮኽን የተባለው የ26 ዓመቱ የኢየሩሳሌም ነዋሪ፣ ከኢራን ሰላዮች ጋር በመገናኘት በእነሱ መመሪያ መሠረት የስለላ ተግባር ማከናወንን ጨምሮ ሌሎች የደኅንነት ጥሰቶችን ፈጽሟል በሚል ተይዟል።”ተጠባባቂ ወታደሩ በእስራኤል የአየር ጥቃት መከላከያ ምድብ ውስጥ ተሰማርቶ የነበረ ሲሆን፣ “ከኢራን የስለላ አባላት ጋር ግንኙነት በመመሥረት በተለይ በሥራ አጋጣሚ የሚያገኘውን ጥብቅ መረጃ አሳልፎ በመስጠት እና ሌሎች ተግባራትን በመፈጸም” ተጠርጥሯል።ወታደሩ “ከኢራን ወኪሎች ጋር ግንኙነት እያደረገ እንደነበር” እንደሚያውቅ እና ገንዘብም ይከፈለው እንደነበር በተደረገበት ምርመራም መታወቁም ተገልጿል።ፖሊስ እና የእስራኤል የአገር ውስጥ ደኅንነት አገልግሎት (ሺም ቤት) የኢራን የስለላ ተቋም እስራኤላውያንን በመመልመል ወደ ተቋሞች ሰርጎ ለመግባት ጥረቶች እንደሚያደርግ በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት ሲያስጠነቅቁ ነበር።ያጋሩ, አንድ የእስራኤል ሠራዊት አባል ለኢራን በመሰለል ተጠርጥሮ ተያዘ - 20 መጋቢት 2026የአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት በኢስፋሃን የሚገኙ 21 ታሪካዊ ቅርሶችን ማውደሙ ተገለፀ
የፎቶው ባለመብት,mizanplusየኢስፋሃን አስተዳዳሪ መህዲ ጃማልላይጃድ አገራቸው ከእስራኤል እና ከአሜሪካ ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት “21 ታሪካዊ ቅርሶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል” ሲሉ ተናገሩ።የኢራን መገናኛ ብዙኃን ጃማልላይጃድ ጠቅሰው ጉዳቱ “በቅርሶች ላይ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ውድመት” ማድረሱን ዘግበዋል።አስተዳዳሪው የኢስፋሃንን ታሪካዊ ቅርሶች መጠበቅ “ብሔራዊ ኃላፊነት ነው” ማለታቸው የተዘገበ ሲሆን፣ የደረሰውን ጉዳት በሚመለከት “ካሳ እና ለመጠገን የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ሕጋዊ በሆነ መልኩ በሚመለከታቸው አካላት በኩል” እንደሚጠይቁ ተናግረዋል።ያጋሩ, የአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት በኢስፋሃን የሚገኙ 21 ታሪካዊ ቅርሶችን ማውደሙ ተገለፀ - 20 መጋቢት 2026ኢራን የብሪታኒያ ጦር ሠፈሮችን አሜሪካ እንድትጠቀም መፍቀድ “ጠብ አጫሪነት” ነው አለች
የፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን የብሪታኒያ ጦር ሠፈሮችን አሜሪካ እንድትጠቀም መፍቀድ “ጠብ አጫሪነት” ነው ስትል ለዩኬ መናገሯን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።አሜሪካ የዩኬን ወታደራዊ ጦር ሠፈር እንድትጠቀም መፍቀድ “በግጭት ውስጥ እንደመሳተፍ” እንደሚቆጠር ቴህራን ለዩኬ መግለጿን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ ከዩኬ አቻቸው ዪቬት ኩፐር ጋር ባደረጉት ውይይት ዩኬ ለአሜሪካ የምትሰጠው የትኛውም ድጋፍ “ሁኔታው እንዲባባስ” እንደሚያደርግ መናገራቸውን ተጠቅሷል።አራጋቺ ዩኬ እና ሌሎች የአውሮፓ አገራት አሜሪካ እና እስራኤል ለፈጸሙት “ግልጽ ጥቃት” የሚከተሉት “ለአንድ ወገን ያደላ አቀራረብ” መሆኑን በመናገር ወንጅለዋቸዋል።አራጋቺ በተጨማሪም ዩኬ የእስራኤል በሳውዝ ፓርስ የጋዝ ማምረቻ ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ባለማውገዟ መተቸታቸው ተዘግቧል።በጉዳዩ ላይ የዩኬ መንግሥት እስካሁን ድረስ ምንም ያለው ነገር የለም። ቢቢሲ የዩኬ የውጭ ጉዳይ ቢሮን በጉዳዩ ላይ ምላሽ ቢጠይቅም ማግኘት አልቻለም።ያጋሩ, ኢራን የብሪታኒያ ጦር ሠፈሮችን አሜሪካ እንድትጠቀም መፍቀድ “ጠብ አጫሪነት” ነው አለች - 20 መጋቢት 2026የኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ ተገደሉ
የፎቶው ባለመብት,Farsየምስሉ መግለጫ,የኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ እና ምክትል ሕዝብ ግንኙነት አሊ ሞሃመድ ናኢኒየኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት መገደላቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ እና ምክትል ሕዝብ ግንኙነት አሊ ሞሃመድ ናኢኒ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃቶች መገደላቸውን የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን አስታውቋል።አሊ ሞሐመድ ናኢኒ የአብዮታዊ ዘቡን ለአራት አስርታት ያገለገሉ ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ ቃል አቀባይ በመሆን ሰርተዋል ሲል ፋርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 21 2018 ዓ.ም. ኢራን ላይ ጦርነት ከከፈቱበት ዕለት አንስቶ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ በርካታ አመራሮች ተገድለዋል።የቀድሞው ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ጦርነቱ በጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የተገደሉ ሲሆን ሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ አመራሮችም የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃት ዒላማ ሆነዋል።ኢራን በ18 ቀናት ውስጥ የትኞቹ ከፍተኛ አመራሮቿ ተገደሉባት?ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ ቃል አቀባይ ተገደሉ
