የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢራን ወሳኝ የነዳጅ መተላለፊያ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥ በ48 ሰዓት ውስጥ የማትከፍት ከሆነ የኃይል ማመንጫዎቿን “እንደሚያወድሙ” የሰጡት ማስጠንቀቂያ ከቴህራን በኩል መለሳለስ ሳይታይበት ከ24 ሰዓት ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል። የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን የትራምፕን ዛቻ “የተስፋ መቁረጥ እርምጃ” ሲሉ አጣጥለውታል። የኢራን አብዮታዊ ዘብ በበኩሉ የአገሪቱ የኤሌክትሪክ ማመንጫዎች የሚመቱ ከሆነ በእኩል ደረጃ በቀጣናው አገራት ተቋማት ላይ የአጸፋ ጥቃት እንደሚፈጸም አስጠንቅቋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 25 ደቂቃዎች በፊትየእስራኤል ጦር ከኢራን እና ከሄዝቦላህ ጋር “የበርካታ ሳምንታት ውጊያ” ይቀረናል አለእስራኤል በፈጸመችው አየር ጥቃት ደቡባዊ እና ማዕከላዊ ሊባኖስን የሚያገናኘውን ዋነኛ ድልድይ አውድማለችየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,እስራኤል በፈጸመችው አየር ጥቃት ደቡባዊ እና ማዕከላዊ ሊባኖስን የሚያገናኘውን ዋነኛ ድልድይ አውድማለችየእስራኤል መከላከያ ሠራዊት፤ ከኢራን እና ከሊባኖሱ ሄዝቦላህ ጋር በሚደረገው ጦርነት “የበርካታ ሳምንታት ውጊያ” ይቀረናል አለ።የጦሩ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄነራል ኤፊ ዴፍሪን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ “ኢራን እና ሄዝቦላህ ላይ የተጨማሪ በርካታ ሳምንታት ውጊያ እንደምንጋፈጥ እንጠብቃለን” ብለዋል።የመከላከያ ሠራዊቱ ዋና አዛዥ ኢያል ዛሚር እስራኤል ሄዝቦላህ ላይ የምታካሂደው ዘመቻ እንዲራዘም የሚያደርግ ዕቅድ እንዳጸደቁ ተገልጿል።ዋና አዛዡ “ሄዝቦላህ ላይ የተከፈተው ዘመቻ ገና መጀመሩ ነው። በኢራን ዘመቻ መጨረሻ ሄዝቦላህ ብቻውን እና ተነጥሎ ይቀራል” ብለዋል። “ሄዝቦላህ ላይ የተከፈተው ዘመቻ የተራዘመ ነው፤ ለዚህም ተዘጋጅተናል” ሲሉም አክለዋል።አሁን በጸደቀው ዕቅድ መሠረት፤ የእስራል ጦር ወደ ሊባኖስ ገብቶ የከፈተውን “ውስን ዒላማ ያለው የምድር ዘመቻ እና ጥቃቶች ለማሳደግ” መዘጋጀቱን ዛሚር ጠቅሰዋል።“ስጋቶቹ ከድንበር ተገፍተው እስከሚርቁ ድረስ አናቆምም፤ ለሰሜን እስራኤል ነዋሪዎች የረጅም ጊዜ ደኅንነት ይረጋገጣል” ሲሉም ተደምጠዋል።ይህ ዕቅድ መጽደቁ የተሰማው እስራኤል ሊባኖስ ላይ መጠነ ሰፊ ወረራ ትፈጽማለች የሚል ስጋት ባየለበት ወቅት ነው።አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ ጦርነት መክፈታቸውን ተከትሎ የቴህራን አጋር የሆነው ሄዝቦላህ እስራኤል ላይ ሮኬቶችን ተኩሷል።እስራኤል ይህንን ተከትሎ ሊባኖስ ውስጥ በከፈተችው ጥቃት ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ከዚህ ውስጥ 118 ሕጻናት እና 40 የጤና ሠራተኞች ይኙበታል።ያጋሩ, የእስራኤል ጦር ከኢራን እና ከሄዝቦላህ ጋር “የበርካታ ሳምንታት ውጊያ” ይቀረናል አለ
  2. ከ 1 ሰአት በፊትበተመድ የአሜሪካ አምባሳደር የኢራን የኒውክሌር ተቋማትን መምታት ጭምር ጠረጴዛው ላይ መሆኑ ገለጹየአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ዋልትዝየፎቶው ባለመብት,Reutersበተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ማይክ ዋልትዝ፤ ኢራንን በተመለከተ የኒውክሌር ኃይል ተቋማትን መደብደብን ጨምሮ የትኛውም አማራጭ “ከጠረጴዛው ውጪ” አይደለም አሉ።አምባሳደሩ በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር ከሆነው ሲቢኤስ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፤ ትራምፕ የኢራንን የኢነርጂ መሠረተ ልማቶች “እንደሚያወድሙ” ስለማስጠንቀቃቸው ተጠይቀዋል። ዋልትዝ ምላሽ ሲሰጡ፤ “ለፕሬዝዳንቱ፤ ምንም ነገርን ከጠረጴዛው ውጪ አላደርገውም፤ በተለይም ብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ [ቀርቤ]” ብለዋል።“የኢራን አብዮታዊ ዘብ በአሜሪካ ብቻ ሳይሆን በበርካታ የአውሮፓ አገራት ጭምር ሽብርተኛ ተብሎ ተፈርጇል” ያሉት አምባሳደሩ፤ ወታደራዊ ኃይሉ “በአገሪቱ ከፍተኛ የኢነርጂ መሠረተ ልማት፣ ኢኮኖሚ እና በርካታ የመንግሥት ተቋማት ላይ ሰፊ ቁጥጥር እንዳለው መረዳት አስፈላጊ ይመስለኛል” ብለዋል።”ስለዚህም ወታደራዊ አቅማቸውን እና የመከላከያ ኢንዱስትሪ መሠረታቸውን እስከምናዳክም ድረስ፣ ሁሉም አማራጮች በጠረጴዛው ላይ መሆን አለባቸው፤ ፕሬዝዳንቱም ይህንን በግልጽ አስታውቀዋል” ብለዋል።ያጋሩ, በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር የኢራን የኒውክሌር ተቋማትን መምታት ጭምር ጠረጴዛው ላይ መሆኑ ገለጹ
  3. ከ 2 ሰአት በፊትየኢራን አብዮታዊ ዘብ የኤሌክትሪክ ማመንጫዎች የሚመቱ ከሆነ በእኩል ደረጃ የአጸፋ ጥቃት እንደሚፈጸም አስጠነቀቀየኢራን ሚሳዔል ሲወነጨፍየፎቶው ባለመብት,AFPየኢራን የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ጥቃት የሚፈጸምባቸው ከሆነ፤ የእስራኤል የኃይል ማመንጫዎች እና በቀጣናው አገራት ለሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮች ኤሌክትሪክ የሚያቀርቡ ተቋማት ላይ የአጸፋ ጥቃት እንደሚያደርስ የኢራን አብዮታዊ ዘብ አስታወቀ።የዜና ወኪሉ ሮይተርስ ዘገባ እንደሚያመለክተው አብዮታዊ ዘቡ ያወጣው መግለጫ፤ በቀጣናው የሚገኙ የጨዋማ ውሃ ማጣሪያዎች ላይ ጥቃት እንደሚፈጸም ተገልጾ የነበረውን ዛቻ አላካተተም። እነዚህ ማጣሪያዎች ለባሕረ ሰላጤው አገራት የሚጠጣ ውሃ በማቅረብ ረገድ ወሳኝ ናቸው።በወታደራዊ ኃይሉ ማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ የወጣው መግለጫ፤ “ውሸታም የሆኑት… የአሜሪካ ፕሬዝዳንት፣ የአብዮታዊ ዘቡ የውሃ ማጣሪያ ተቋማትን ለማጥቃት እና በቀጣናው ባሉ አገራት ህዝቦች ላይ ችግር ለመፍጠር አቅዷል በማለት ከስሰዋል” ብሏል።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቴህራን በ48 ሰአታት ውስጥ የሆርሙዝ ወሽመጥን ለሁሉም መርከቦች “ሙሉ በሙሉ ክፍት” ካላደረገች የኢራን የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የጥቃት ዒላማ እንደሚያደርጉ አስጠንቅቀዋል።የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ለትራምፕ ማስጠንቀቂያ በሰጠው ምላሽ፤ “ለማንኛውም አይነት ዛቻ በእኩል ደረጃ ምላሽ ለመስጠት ቁርጠኛ ነን […] የኤሌክትሪክ ማመንጫን ከመታችሁ፣ እኛም የኤሌክትሪክ ማመንጫን እንመታለን” ብሏል።ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ የኤሌክትሪክ ማመንጫዎች የሚመቱ ከሆነ በእኩል ደረጃ የአጸፋ ጥቃት እንደሚፈጸም አስጠነቀቀ
  4. ከ 3 ሰአት በፊትየአሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም መሪዎች የሆርሙዝ ወሽመጥ መከፈት አስፈላጊነት ላይ መስማማታቸው ተገለጸየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመርየፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር ስለ መካከለኛው ምሥራቅ ግጭት በስልክ በተነጋገሩበት ወቅት በኢራን ስለተዘጋው የሆርሙዝ ወሽመጥ መከፈት አስፈላጊነት ተወያዩ።ከሦስት ሳምንት በፊት ጦርነት የተከፈተባት ኢራን በርካታ መርከቦችን ከሚያስተናግዱ የዓለም የባሕር መተላለፊያዎች አንዱ የሆነው ሆርሙዝን ወሽመጥን ዘግታለች። ይህንን ተከትሎ በአካባቢው ይደረግ የነበረው የመርከብ ጉዞ በ95 በመቶ ቀንሷል።ሁለቱ መሪዎች እሁድ ምሽት ባደረጉት የስልክ ንግግር “በመካከለኛው ምሥራቅ ስላለው ሁኔታ መወያየታቸውን” የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ገልጸዋል።በተለይም “ለዓለም የመርከብ ጉዞን ለማስጀመር የሆርሙዝ ወሽመጥ መከፈትን አስፈላጊነት” እንደተነጋገሩ አስረድተዋል።ቃል አቀባዩ አክለውም፤ “የሆርሙዝ ወሽመጥ ዳግም መከፈት የዓለም ኢነርጂ ገበያ መረጋጋትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ተስማምተዋል” ብለዋል።ስታርመር እና ትራምፕ “በቅርቡ በድጋሚ ለመነጋገር እንደተስማሙም” ተገልጿል።ያጋሩ, የአሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም መሪዎች የሆርሙዝ ወሽመጥ መከፈት አስፈላጊነት ላይ መስማማታቸው ተገለጸ
  5. ከ 4 ሰአት በፊትየኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን “ዛቻ አንድነታችንን ያጠናክረዋል” አሉየኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያንየፎቶው ባለመብት,Iran’s Presidential website/WANA/Reutersየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በ48 ሰዓታት ውስጥ የማትከፍት ከሆነ የኃይል ማመንጫዎቿን እንደሚያወድሙ መታዛቸውን ተከትሎ፤ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን “ዛቻ እና ሽብር የሚያጠናክሩት አንድነታችንን ብቻ ነው” አሉ።ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን የተዘጋው ወሳኙ የባሕር መተላለፊያ እንዲከፈት የሰጡት ማስጠንቀቂያ ከ24 ሰዓታት ያነሰ ጊዜ ቢቀረውም ከቴህራን በኩል መለሳለስ አልታየም። የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ መሐመድ ባገር ጋሊባፍ አገሪቱ የኃይል ማመንጫዎች ጥቃት የሚፈጸምባቸው ከሆነ በቀጠናው የሚገኙ ወሳኝ መሠረተ ልማቶች፣ የኢነርጂ እና የነዳጅ ዘይት ተቋማት እንደ “ሕጋዊ ዒላማዎች” ይቆጠራሉ ብለዋል።የኢራኑ ፕሬዝዳንት ፔዜሽኪያንም በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ “የሆርሙዝ ወሽመጥ መሬታችንን ከሚደፍሩት በስተቀር ለሁሉም ክፍት ነው” ብለዋል።የአሜሪካን ዛቻ “ኢራንን ከካርታው ላይ የማጥፋት ቅዥት” ሲሉ የጠሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህ ማስፈራሪያ “ታሪክ ሰሪ ከሆነው የህዝብ ፈቃድ ተቃራኒ የሆነ ተስፋ መቁረጥን” ያሳያል ብለዋል። ፔዜሽኪያን አክለውም፤ “የማይረቡ ዛቻዎችን ጦር ሜዳ ላይ በጽናት እንመክታለን” በማለት ጽፈዋል።ያጋሩ, የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን “ዛቻ አንድነታችንን ያጠናክረዋል” አሉ