Jawar Mohammed 

በነገራችን ላይ እንደ ኢዜማ ሁሉ ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ግነሰቦችም የምክርቤት ወንበር እንደሚለቀላቸው ቃል በመግባት በምርጫው እንዲሳተፉ ለማሳመን ከፍተኛ የማማለል ዘመቻ ሲካሄድ ነበር። አንዳንዶች ሲቀበሉ ብዙዎቹ እምቢ ብለዋል።

ለምሳሌ ኦፌኮ በምርጫ ከተሳተፈ ከ30-50 የፓርላማ ወንበር እንደሚሰጠው በቀጥታም በሽምግልናም ለማሳመን ተሞክሮ ነበር። የኦፌኮ አመራር መልስ “ የፓርላማ ወንበር በህዝብ ድምጽ የሚሰጥ ውክልና እንጂ አንድ ስልጣን ላይ የተቆናጠጠ ግለሰብ/ ፓርቲ የሚያከፋፈለው ችሮታ አይደለም፤ ወንበር ከፈለግን ተወዳድረን ብህዝቡ ይሁታ ማግኘት እንጂ በአገዛዙ ስጦታ መቀበል አንፈልግም። ፓርላማ መግባት ለኛ ብርቃ አይደለም። ከዚህ በፊትም በፌደራልም በክልልም ተመርጠን አይተንዋል ” የሚል ነበር።

ብልጽግና ለዚህ መደለያ እንዲያግዝ ወደ 45 የፌደራል ፓርላማ የምርጫ ክልሎች ላይ እጩ ባለማቅረቅ ወነበሮቹን በስጦታ ለመቀበል ለተስማሙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ክፍት አድርጓል።

አንድ ተቃዋሚ ነኝ ለሚል ድርጅትም ሆነ ግለሰብ የክልልም ሆነ የፌደራል ምክርቤቶች ወንበርን ከአብይ በስጦታ መቀበል፣ ከሌሎቹ የብልጽግና ፓርቲ ስም ከተሰልፉት “ተመራጮች” ምንም የሚለያቸው ነገር ስለሌ አንደኛውን በቀጥታ ብልጽግና ሆነው መሳተፉ ይሻላል። እንደተመለመደው ከመስከረም በኋላ “ እኛ ነን ስልጣን የሰጠንህ” አያለ እያንጓጠጠና እያዋረደ ተላካላኪ ያደርግሃል። በአግዛዙ ይሁነታ ወንበር ከያዝክ በኋላ በፓርላማ መድረክም እውነተኛ አቋምህንም ሆነ የህዝብ ጥያቄን ለማንጸባረቅ የሚያችል ሞራል እና በራስ መተማመን አይኖርህም።