Dessalegn Chanie Dagnew 

ከ60 ዓመት በላይ በስራ ላይ የቆየው የወንጀል ህግ ስነስርዓት እና የማስረጃ ህጉ ትላንት በህዝብ ተ/ም/ቤት ቀርቦ ነበር። አዋጁ ለመጽደቅ 6 ዓመታትን የወሰደበት ሲሆን አወዛጋቢ ከነበሩ አንቀጾች ውስጥ አንቀጽ 25 (3) ሲሆን አንቀጹም የኦሮምያ ክልል ፍርድ ቤቶችን በአዲስ አበባ የዳኝነት ስልጣን የሚሰጠው አንቀጽ ነው።

አንቀጽ 25 (3) ከኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም አንፃር የሚከተሉት ዋና ዋና አንድምታዎች አሉት፦

• የዳኝነት ሥልጣን ወሰን መደራረብ (Jurisdictional Overlap)፦ በፌዴራል ሥርዓት ውስጥ የዳኝነት ሥልጣን ብዙውን ጊዜ በግዛት ወሰን (Territorial Jurisdiction) ላይ የተመሰረተ ነው። ይህ ድንጋጌ ግን አንድ ክልል ከራሱ የግዛት ወሰን ውጭ በሌላ አስተዳደር (አዲስ አበባ) ውስጥ ባሉ ንብረቶቹ ላይ ሥልጣን እንዲኖረው በማድረጉ፣ የተለመደውን የግዛት ወሰን መርህ የሚጋፋ እና አዲስ አሰራር የሚዘረጋ ነው።

• የአዲስ አበባ ልዩ ሁኔታ፦ አዲስ አበባ የፌዴራሉ መንግሥት መቀመጫ እና የራሷ መስተዳድር ያላት ቢሆንም፣ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 49(5) መሠረት የኦሮሚያ ክልል “ልዩ ጥቅም” እንዳለው ተደንግጓል። ይህ የረቂቅ ሕጉ አንቀጽ 25/3 ድንጋጌ ያንን ልዩ ጥቅም ወደ ዳኝነት ሥልጣን ለማሳደግ የሚደረግ ሙከራ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። በመሠረቱ የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 49(5)ድንጋጌ መንፈስ ከዳኝነት ስልጣን ጋር የሚያገናኘው አንዳች ነገር የለውም።

• የሕግ ተፈፃሚነት እና ቅራኔ፦ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ብዙውን ጊዜ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ወይም በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የሚታዩ ናቸው ። የኦሮሚያ ፍርድ ቤቶች እዚህ ውስጥ ሥልጣን ሲሰጣቸው፣ “የትኛው ሕግ ተፈፃሚ ይሆናል?” (የፌዴራሉ ወንጀል ሕግ ወይስ የክልሉ?) እና “የፖሊስ ምርመራውስ በማን ይካሄዳል?” የሚሉ የሥልጣን ሽኩቻዎችን የሚፈጥር ድንጋጌ ነው።

በተጨማሪም ድንጋጌው የአዲስ አበባን ሉዓላዊነት እና የፌዴራል መንግሥቱን የዳኝነት የበላይነት ይሸረሽራል የሚል ተቃውሞ ሲነሳበት በመቆየቱ ነው 6 ዓመት ሲጓተት ከርሞ በዚህ ምክር ቤት የመጨረሻ ዘመን ላይ እንዲጸድቅ የቀረበው።

አዋጁ እንደተለመደው በሁለት ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል። የእኔ እና የዶ/ር አበባው ተቃውሞ ከታች ያለው ነው።

የገረመኝ የአማራ ብልጽግና ተወካዮች፣ የአዲስ አበባ ህዝብ ተወካዮችና የኢዜማ ተወካዮች መቃወም ቢፈሩ እንኳን ድምጸ ተዓቅቦ ማድረግ አለመቻላቸው ነው።

https://youtu.be/AMv-OdFuMMQ

https://youtu.be/AMv-OdFuMMQ

በአዲስ አበባ በሚገኙ የኦሮሚያ ክልል ተቋማት ሰራተኞች እና ኃላፊዎች ላይ የክልሉ ፍርድ ቤቶች የሚኖራቸው “የዳኝነት ስልጣን” በፓርላማ አከራከረ| Insider

Ethiopia Insider

https://youtu.be/AMv-OdFuMMQ