
Kassim Adam
** ማን ያውራ የነበረ፣
ማን ያርዳ የቀበረ።
ቆይ ቆይ !!! አቻምየለህ ታምሩ የሚባለውን ሰው እኔ አላውቀውም። ፅሁፎቹንን ሳነብ የሚአጅበኝ ነገር አላየሁም። ያም ሆነ ይህ የማደንቀውም የምንቀውም ሰው አይደለም።
አሁን ግን በቅርብ ጊዜ ፣ ኢሕአፓን በተመለከተ ፣ እየለቀቀ ያለውን መረጃ ስመለከት ፣ አቻምየለህ ፣ ከወያኔ ትውልድ በፊት የነበረውን የኢትዮጵያ ታሪክ የሚያጤን አቅም እንደሌለው ነው የተገነዘብኩት።
ብዙውን ክስ ፣ ውንጀላ እና ፍርጃ በድፍረት መረጃ ብሎ ሲያቀርብ ያየሁት ፣ ዴሞክራሲያ በመባል ይታወቅ ከነበረው የኢሕአፓ ልሳን እትሞች ላይ በመነሳት ነው። እርግጥ ነው ዴሜክራሲያ የኢሕአፓ official እንደነበር ማንም የሚያውቀው ነው። ይህ ማለት እኔ እስከማውቀው ድረስ ፣ ዴሞህራሲያ ፣ የኢሕአፓን ወቅታዊ እና አንገብጋቢ አጀንዳዎች እና የድርጅቱን ምን መደረግ አለበት አቋም የምናይበት ሃዋርያ ነበር ማለት ነው። ነገር ግን አንድ ተራ የታሪክ መምህር ይሁን ተማሪ ፣ የድርጅት ልሳኖች በሙሉ ፣ የየድርጅቱ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎች መሆናቸውን መገንዘብ የግድ ይለዋል። ተፈፃሚ የሚሆነው የድርጅቶች ፕሮግራም እንጅ ፣ በእስትራቴጅ እና ታክቲክ ውስጥ የሚጠቃለሉ የመግለጫ መድረኮች አይደሉም።
አቻምየለህ ፣ ስለኢሕአፓ ፀረ-አማራነት ደጋግሞ ይናገራል። ኢሕአፓ ፣ አማራ የሚባል በአንድ የተከለለ ቦታ ላይ እንዲኖር የተገደደ ህዝብ ባልነበረበት ጊዜ ነው መስዋእትነት የከፈለው። በጊዜው አማራ ሲባል ፣ የመሳፍንቱን አገዛዝ እና ስርአት እንጅ ፣ አንድን ህዝብ ለይቶ ለመወንጀል ተብሎ ሲነገር እኔ የሰማሁበት ጊዜ የለም። የስርአቱን ወግ ልምድ እና ባህል በተመለከተ ከሆነ ደግሞ ፣ ይባል የነበረው ፣ አማራ እና ትግሬ ነው የነበረው። ወያኔዌች ናቸው ትግሬ የምትለዋን ደልዘው ፣ አማራ የምትለዋን አገላለፅ በሰፊው ያራመዱት። ይህ አመለካከት በነገራችን ላይ ፣ በነዋለልኝ መኮንን ተሰርቶ ለንባብ ሲበቃ ፣ ያኔ ኢሕአፓ የሚባል ድርጅት አልነበረም። በዛን ጊዜ እንኳን ቢሆን ዋለልኝ የከተበው ፅሁፍ አማራ እና ትግሬ እያለ ነው። አቻምየለህ ከፈለገ ፣ ይህን ፅሁፍ አሁንም ኢንተርኔት ላይ ገብቶ መመልከት ይችላል ።
ኢሕአፓን መተቸት መበረታታት አለበት። እኔ ይህን እደግፋለሁ። ኢሕአፓ የስራተኞች ፓርቲ ነው። አንድ ወጥ ድርጅት ግን አልነበረም። እየታገለ የነበረው ፣ ተማሪዎች ፣ መምህራን ፣ ሙያተኞች እና አርሶአድሮችን ሁሉ በሚያጠቃልል ፕሮግራም ነው። ይቅር እና መላውን ኢትዮጵያ አስተባብሮ መምራት ይቅር እና ፣ አንድ አላማ አለው የምንለውን ፋኖ በጋራ ግምባር ማምጣት ንን ያህል እንዳስቸገረን ማንም የሚያውቀው ነው። እንደ ዶክተር ታየ ወልደ ሰማያት አይነት የመምህራን ማህበር መሪዎች ፣ የኢሕአፓ እንጥልጥል ጌጥ አልነበሩም። ማህበራቸውም የተመሰረተው ከኢሕአፓ ብዙ ጊዜ ቀድሞ ነው። ዶክተር ታየ በእስር ላይ እያሉ ፣ በምትካቸው ቦታውን የተረከበው ጋሸ አሰፋ ማሩ ፣ ወደ ስራው በእግሩ እየሄደ እያለ ፣ አገር እያየ ፣ በወያኔ ኮማንዶዎች በጠራራ ፀሃይ ተረሽኗል። ብቻ ይህን ነገር ስፅፍ በቃ ሙዴ ተበላሸ።
ኢሕአፓን ለሚተቹ ወንድሞቻችን ፣ ጥያቄ በጥያቄ እንነጋገር ። በህይወት ያለን ሰዎች የምናውቀውን ያህል መልስ እንሰጥበታለን። ባጠፋንበትም ቦታ ሁሉ ተወቃሽነትን አንሸሽም።
