
Yidnekachew Kebede
ስለ ሀገር የቆመ፣ ስለ ወገን የደከመው የመርከቡ ሀይሌ (የመርኬ) ፈገግታ ይመለስ!
ደግነት ለራስ ነው – ዛሬ ለቆመው እንቁም!
መርከቡ ሀይሌ (መርኬ) ለአንዳንዶች የአራት ኪሎ አድባር፣ ለሌሎች ደግሞ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። መርከቡ ከግል ህይወቱ ይልቅ የሀገሩን ክብርና የዜጎችን መብት የሚያስቀድም፣ ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ በሀገራችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሰፍንና ሁሉም በእኩል ተጠቃሚ የሚሆንበት ሥርዓት እውን እንዲሆን የበኩሉን ድርሻ በጽናት ሲወጣ የኖረ ሰላማዊ ታጋይ ነው።
መርከቡ ለሀገሩና ለወገኑ ማነው?
መርከቡ ሰንደቅ ዓላማውን በመውደድና ለሀገሩ በመቆርቆር የሚታወቅ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። የአድዋን የድል በዓልና ሌሎችንም የኢትዮጵያን ክብርና ጀግንነት የሚዘክሩ ታሪካዊ ቀናትን ከነግራማ ሞገሱ በመገኘት በማድመቅ፣ የጀግኖች አባቶቻችንን ታሪክና ስም ከፍ እንዲል በማድረግ ዜግነታዊ ግዴታውን ሲወጣ የኖረ ባለውለታ ነው።
ከሀገር ፍቅሩ ባሻገር መርከቡ ለሰው ደራሽነቱ ምስክር አያስፈልገውም፦
በሃይማኖታዊ በዓላት ላይ ወግና ሥርዓትን በማድመቅ ይታወቃል።
ወገኖቹ ሲታመሙ፣ ሲቸገሩ፣ በጦርነትም ሆነ በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ሲደርስባቸው ቀድሞ ደራሽ ነው።
በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ያሉ ሰዎችን በማስተባበር ለብዙዎች አለኝታነቱን ያስመከረ መልካም ወንድማችን ነው።
የከፈለው መስዋዕትነትና የዝምታ ህመሙ ፤
መርከቡ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ ሰላምና አንድነትን ቢያስቀድምም፣ ጉዞው ግን ውጣ-ወረድ የበዛበትና ከፍላጎቱ ውጪ እስርና እንግልት የጸናበት ነበር። በመላው ሀገራችን በተካሄዱ የጅምላ እስሮች ወቅት በመዓከላዊ፣ በ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ በአዋሽ 7 እና በተለያዩ የማጎሪያ እስር ቤቶች አሰቃቂ ጊዜያትን አሳልፏል፦
በ1993 ዓ.ም፦ በማዕከላዊ እስር ቤት የእግሩ ጥፍሮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተነቅለው ለከፍተኛ ጉዳት ተዳርጓል።
በ1998 ዓ.ም፦ የህዝብ ድምጽ ይከበር በማለቱ ምክንያት በደረሰበት ድብደባ 7 የፊት ጥርሶቹን በጠመንጃ ሰደፍ እንዲያጣ ተደርጓል።
መርከቡ በይሉኝታ ታስሮና በዝምታ የራሱን ህመምና ችግር ደብቆ ለሰዎች ሲደርስ የኖረ ታጋሽ ሰው ነው። ከደረሰበት ድብደባ የተነሳ ጥርሶቹን አጥቶ ፈገግታው ተሸፍኖ፣ ስቃዩን በሆዱ አድርጎ እስከዛሬ ኖሯል። በቅርቡም ባላሰበው ወንጀል ተወንጅሎ በእስር ቆይቶ፣ አሁን በነጻ ተለቋል።
አሁን የእኛ ተራ ነው!
ያ ለሀገሩ ሲል ያጣው ፈገግታውና ጥርሶቹ ዛሬም በህመም ተሸፍነዋል። ህመሙን በዝምታ ችሎ የኖረው መርከቡ፣ አሁን የሁላችንንም እገዛ ይሻል።
የአራት ኪሎ ልጆች፣ ወዳጆቹና በጎ አድራጊ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ መርከቡ የጠፉ ጥርሶቹን ተክቶ፣ ጤንነቱ ተመልሶና ያ ማራኪ ፈገግታው ታይቶ እንድንደሰት የበኩላችንን እንድናደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የድጋፍ ማድረጊያ አካውንት (የግል አካውንቱ)፦
የባንክ አካውንት፦ 1000578444328 (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
የአካውንቱ ስም፦ መርከቡ ሀይሌ Merkebu Haile
ለተጨማሪ መረጃ፦ +251966903926
“የወንድማችንን ፈገግታ በጋራ እንመልስ!”
ይህንን መልዕክት በየግሩፑ እና ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት (Share በማድረግ) የሰብአዊነት አጋርነታችሁን አሳዩ።
አስተባባሪዎች፦
ዳንኤል መሶቤ፣ አሰፋ መቀሌ፣ ኤርሚያስ ሀይሉ Ermias Hailu እና ሲራክ እንዳለ።
