አበይት ዜና

April 8, 2026

Updated: April 8, 2026

ቦርከና ደስክ

World Wide Travel Group
ኢሕአፓ

ቦርከና ዜና

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ( ኢሕአፓ ) በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ ዙሪያ ያለውን ጠንካራ ተቃውሞ ለመግለጽ ለሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አቀረበ። “ምርጫው አምባገነንነትን የሚያጠናክር የመሸወጃ ትርዒት ነው” ሲል የገለጸው ፓርቲው፣ ሰልፉን የጠራባቸውን ዋና ዋና ምክንያቶች በመግለጫው ይፋ አድርጓል፦

ከእነዚህም ውስጥ

የፓርቲው ጥሪና ጥያቄዎች፡

  1. የንጹሐን ጭፍጨፋና አፈና በአስቸኳይ እንዲቆም።
  2. የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ።
  3. የኑሮ ውድነትን የሚገቱ እርምጃዎች እንዲወሰዱ።

ሰልፉ ከአንድ ወር በኋላ ዓርብ ሚያዝያ 30 ቀን በሚከተሉት ከተሞች ይካሄዳል ተብሏል፦
አዲስ አበባ
መቀሌ
ባሕር ዳር
ጎንደር
ሐዋሳ
አሶሳ
አዳማ
አምቦ
ድሬዳዋ
ሐረር
ኢሕአፓ “ለሕዝብ ስቃይ መቀጠል ምክንያት የሚሆንን ሂደት እንቃወማለን” ሲል መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለጥሪው ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።

የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ

– Advertisement –

Advertise here _ borkena

የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena

ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

Ethiopian NewsBorkena English
ኤክስ ፡ @zborkena