
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢራን በወሳኙ የሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፈውን ነዳጅ የያዘችበት መንገድ “የተስማማንበት አይደለም” በማለት ወቀሱ። በሌላ በኩል፤ እስራኤል እና ሊባኖስ በሚቀጥለው ሳምንት ዋሽንግተን ውስጥ ድርድር ይጀምራሉ።
ጭምቅ ሃሳብ
- ትራምፕ ኢራን “ለትክክለኛው ስምምነት” ሙሉ በሙሉ እስክትገዛ ድረስ ጦሩ በተጠንቀቅ እንዲቆይ አዘዙ
- በሊባኖስ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ200 በላይ ሰዎች ተገደሉ
- እስራኤል በሊባኖስ ላይ የፈጸመችውን ጥቃት እነማን አወገዙ?
- ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥ አሜሪካ ጥቃቷን ስታቆም ዳግም ይከፈታል አለች
- የአሜሪካ-ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ‘አጠራጣሪ’ ቢሆንም የኢራን ተደራዳሪዎች ወደ ፓኪስታን አቀኑ
- ትራምፕ ኢራን “ትክክለኛውን ስምምነት” እስክታከብር ድረስ ሲሉ ምን ማለታቸው ነው?
- የአሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ጥርጣሬ ማሳደሩን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ
- የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር የአሜሪካ-ኢራንን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማፅናት በርካታ ሥራዎች ይቀራሉ አሉ
- ኢራን የተኩስ አቁሙ ሦስት አንቀጾች “በግልጽ እና በይፋ ተጥሰዋል” አለች
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 21 ደቂቃዎች በፊትሄዝቦላህ የተኩስ አቁሙ “በመጣሱ” በእስራኤል ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገለጸ
የፎቶው ባለመብት,EPAበሊባኖስ የሚገኘው የሺዓ እስልምና ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ቡድን ሄዝቦላህ፤ እስራኤል በአሜሪካ እና በኢራን ተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት “በመጣሷ” በአገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል የሚገኝ ከተማ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ።ሄዝቦላህ እንደገለጸው ሮኬቶችን የተኮሰው በእስራኤል እና በሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ ወደሚገኘው ኪርያት ሽሞና እንዲሁም በሰሜናዊ እስራኤል ሚስጋቭ አም አካባቢ ነው።“እስራኤል እና አሜሪካ በአገራችን እና በሕዝባችን ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት እስከሚቆም ድረስ ይሄ ምላሽ ይቀጥላል” ብሏል።አሜሪካ እና ኢራን የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነትን ለማስቆም የሁለት ሳምንት ተኩስ አቁም ላይ ቢደርሱም እስራኤል በሊባኖስ ውስጥ የምታካሂደው ጥቃት ቀጥሏል። ኢራን እና አሸማጋይዋ ፓኪስታን የተኩስ አቁሙ ሊባኖስንም እንደሚያካትት ገልጸዋል። አሜሪካ እና እስራኤል በበኩላቸው ሊባኖስ የስምምነቱ አካል እንዳልሆነች እየተናገሩ ነው።እስራኤል የተኩስ አቁሙ በተደረሰ ማግሥት ረቡዕ ዕለት በከፈተችው መጠነ ሰፊ ጥቃት ከ300 በላይ ሰዎች ሲገደሉ፤ ከአንድ ሺህ በላይ ቆስለዋል። እስራኤል አሁንም የደቡባዊ ሊባኖስን ሰፊ መሬት ተቆጣጥራ ይዛለች።የእስራኤሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከሊባኖስ መንግሥት ጋር ቀጥተኛ ድርድር እንደሚደረግ ቢናገሩም፤ “ሊባኖስ ውስጥ ተኩስ አቁም አይኖርም” ሲሉ ጥቃቶች እንደሚቀጥሉ አመልክተዋል።ያጋሩ, ሄዝቦላህ የተኩስ አቁሙ “በመጣሱ” በእስራኤል ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገለጸ - ከ 1 ሰአት በፊትትራምፕ በኢራን ጦርነት ያላቸው ሥልጣን እንዲገደብ የሚያደርገው ሕግ በሪፐብሊካኖች ውድቅ ተደረገ
የፎቶው ባለመብት,Bloomberg via Getty Imagesበአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት የሚገኙ ሪፐብሊካኖች ዋሽንግተን ኢራን ላይ የምትፈጽማቸው ጥቃቶች እንዲቆሙ ለማድረግ በዴሞክራቶች የቀረበውን ሕግ ከመጽደቅ ማገዳቸውን የዜና ወኪሉ ሮይተርስ ዘገበ።ሪፐብሊካኖች የፓርቲያቸው ተመራጭ የሆኑትን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣን ለመገደብ የሚደረጉ ጥረቶች እንዳይሳኩ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።የተወሰኑ ዴሞክራቶች የአሜሪካ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲያበቃ የሚጠይቀውን የውሳኔ ሃሳብ ያለ ግምገማ በሙሉ ድምጽ እንዲጸድቅ ከመጠየቃቸው በፊት ሪፐብሊካኑ የኒው ጀርዚ ተወካይ ክሪስ ስሚዝ ስብሰባው እንዲጠናቀቅ አድርገዋል።ትናንት ሐሙስ የተካሄደው ይህ ስብሰባ በአመዛኙ ከትምህርታዊነት ያለፈ ፋይዳ አልነበረውም። ይሁን እንጂ በምክር ቤቱ እና በሴኔት የሚገኙ ዋነኛ ዴሞክራቶች ኮንግረሱ በሚቀጥለው ሳምንት ከእረፍት ሲመለስ የትራምፕን ሥልጣን ሚገድበው ሕግ በድጋሚ ድምጽ እንዲሰጥበት ለማድረግ ዝተዋል።ዴሞክራቶች የጦርነት ሥልጣንን የተመለከተውን ሕግ ለማጽደቅ ባለፉት ወራት በተደጋጋሚ ሞክረው አልተሳካላቸውም። ዴሞክራቶች በዚህ ሕግ አማካኝነት ትራምፕ ከኮንግረስ ፈቃድ ሳያገኙ ጦርነት እንዳይከፍቱ የማደረግ ፍላጎት አላቸው።በኮንግረስ የሚገኙ ዴሞክራቶች ይህንን ጥረታቸው በድጋሚ አሁን የጀመሩት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ሳምንት “ሙሉ ሥልጣኔ ይወድማል” በማለት ኢራን ላይ ከዛቱ በኋላ ነው።ያጋሩ, ትራምፕ በኢራን ጦርነት ያላቸው ሥልጣን እንዲገደብ የሚያደርገው ሕግ በሪፐብሊካኖች ውድቅ ተደረገ - ከ 4 ሰአት በፊትየእስራኤል እና የሊባኖስ ደርድር በአሜሪካ ሊካሄድ ነው
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,እስራኤል ረቡዕ ዕለት ሊባኖስ ውስጥ በፈጸመችው ጥቃት በ10 ደቂቃ ውስጥ 100 ዒላማዎችን መትታለችባለፉት ቀናት የሄዝቦላህ “ወታደራዊ መሠረተ ልማቶች” ስትል በገለጸቻቸው ዒላማዎች ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ያባባሰችው እስራኤል፤ ከሊባኖስ ጋር የምታደርገው ድርድር በሚቀጥለው ሳምንት ዋሽንግተን ከተማ ውስጥ እንደሚካሄድ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ።አሜሪካ እና ኢራን የደረሱት የተኩስ አቁም ሊባኖስንም የሚያካትት የመሆን፣ አለመሆኑ ጉዳይ ሲያወዛግብ ከቆየ በኋላ በትናንትናው ዕለት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከሊባኖስ ጋር ድርድር እንዲጀመር ማዘዛቸውን አስታውቀዋል።የሊባኖስ ባለሥልጣናት የተኩስ አቁም ተደርጎ ድርድር እንዲጀመር ጠይቀዋል። ከዚህ ጥያቄ በኋላ ለሰሜናዊ እስራኤል ነዋሪዎች መልዕክት ያስተላለፉት ኔታንያሁ ግን “ሊባኖስ ውስጥ የተኩስ አቁም አይኖርም” ብለዋል።እስራኤል በሊባኖስ የምትፈጽማቸው ጥቃቶች ባለፉት ቀናት በከፍተኛ መጠን ጨምረው ከቆዩ በኋላ ከትናንት ምሽት አንስቶ ለጊዜው ጋብ ያለ ይመስላል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለኤንቢሲ ኒውስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፤ እስራኤል የሰላም ንግግሩን ለማገዝ ሲባል የምትፈጽመውን ጥቃት “እየቀነሰች” መሆኑን ገልጸዋል።“ከቢቢ [የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚስትር] ጋር ተነጋግረናል፤ እናም [ጥቃቱን] ይቀንሰዋል። ከዚህም የበለጠ መቀነስ እንዳለብን አስባለሁ” ሲሉ ከኔታንያሁ ጋር በስልክ ካደረጉት ንግግር በኋላ አቋማቸውን አስረድተዋል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው እስራኤል እና ሊባኖስ በሚቀጥለው ሳምንት “ዋሽንግተን ውስጥ እየተተገበረ ስላለው የተኩስ አቁም ድርድር” ይነጋገራሉ።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ትናንት ባስተላለፉት መልዕክት ከሊባኖስ ጋር የሚደረገው ድርድር ሄዝቦላህን እና በኢራን የሚደገፉ አማጺ ቡድኖችን ትጥቅ ማስፈታት ላይ እንደሚያተኩር ገልጸዋል። በሁለቱ አገራት መካከል ሰላማዊ ግንኙነት የመመስረት ጉዳይም የድርድሩ አካል ነው ተብሏል።ይሁን እንጂ የሊባኖስ መንግሥት እና እስራኤል የሚያደርጉት ድርድር ሄዝቦላህ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ እንደሚኖረው ግልጽ አይደለም።የሊባኖስ መንግሥት ከእስራኤል ጋር ጦርነት ከተጀመረበት መጋቢት አንስቶ የሄዝቦላህን ወታደራዊ እንቅስቃሴ አግዷል። ይህ እገዳ ግን ቡድኑ እስራኤል ላይ ሮኬቶችን ከማስወንጨፍ አላገደውም።በተጨማሪም እስራኤል ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ለማድረግ ቁርጠኝነት ባላሳየችበት ሁኔታ ውስጥ የሚደረግ ድርድር ፍሬያማ የመሆኑ ጉዳይ አጠያያቂ ሆኗል።እግረኛ ወታደሮቿን ሊባኖስ ውስጥ ያሰማራችው እስራኤል፤ በአገሪቱ ደብባዊ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ግዛቶችን መውረሯን ቀጥላለች።ባለፉት ቀናትም ሊባኖስ ግዛት ውስጥ የሚገኙ መንደሮችን ሆነ ብላ አውድማለች። የእስራኤላውያን ደኅንነት እስካልተጠበቀ ድረስ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ እንደማትፈቅድ አስታውቃለች።ያጋሩ, የእስራኤል እና የሊባኖስ ደርድር በአሜሪካ ሊካሄድ ነው - ከ 5 ሰአት በፊትፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን የያዘችው “በተስማማንበት” መንገድ አይደለም አሉ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢራን በወሳኙ የሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፈውን ነዳጅ የያዘችበት መንገድ “እጅግ ደካማ ሥራ” ነው አሉ። ፕሬዝዳንቱ ከኢራን ጋር “የደረስነው ስምምነት ይህ አይደለም” ሲሉም ወቅሰዋል።ትራምፕ ከዓለም ነዳጅ እና ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ 20 በመቶ የሚሆነው ስለሚተላለፍበት ወሽመጥ አስተያየት የሰጡት በሶሻል ትሩዝ ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ነው።ትራምፕ፤ “ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ክፍያ እስያከፈለች እንደሆነ ሪፖርቶች እየወጡ ነው” ብለዋል። “እያደረጉ ባይሆን ይሻላቸዋል፤ ከሆነም ቢያቆሙ ይሻላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።ፕሬዝዳንቱ በሌላ ጽሑፋቸው ደግሞ “ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ነዳጅ እንዲያልፍ መፍቀድን በተመለከተ እያከናወነች ያለችው እጅግ ደካማ ሥራ ነው፤ አንዳንዶች አዋራጅ ብለው ይገልጹታል” ሲሉ ተችተዋል። “ያለን ስምምነት ይህ አይደለም” ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።ለ40 ቀናት ሲዋጉ የቆዩት አሜሪካ እና ኢራን የደረሱበት ተኩስ አቁም ከሚያካትታቸው ነጥቦች አንዱ የሆርሙዝ ወሽመጥ መከፈት ነው።ቢቢሲ ቬሪፋይ ያሰባሰባቸው መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከስምምነቱ በኋላም በወሳኙ የባሕር ኮሪደር በኩል ያለፉ መርከቦች ቁጥር ዘጠኝ ብቻ ነው። ጦርነቱ ከመነሳቱ በፊት በየቀኑ በአማካይ 138 መርከቦች በወሽመጡ በኩል ያልፉ ነበር።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን የያዘችው “በተስማማንበት” መንገድ አይደለም አሉ - 9 ሚያዚያ 2026ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ከሊባኖስ ጋር ድርድር እንዲጀመር አዘዙ
የምስሉ መግለጫ,እስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታኒያሁ እና የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አዎንስየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሠራዊታቸው ከባድ ጥቃት እየፈጸመ ካለባት ሊባኖስ ጋር ሚኒስትሮቻቸው ቀጥተኛ ንግግር እንዲጀምሩ ማዘዛቸውን አስታወቁ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤክስ ገጻቸው ላይ በእብራይስጥ ቋንቋ ባሰፈሩት ጽሁፍ ከሊባኖስ በኩል ቀጥተኛ ድርድር እንዲደረግ ቀረበ ባሉት “ተደጋጋሚ ጥሪ” መሠረት ካቢኔያቸው ንግግሩን “በአስቸኳይ” እንዲጀምር መጠየቃቸውን ገልጸዋል።ኔታኒያሁ ጨምረውም የሚደረገው ንግግር “ሄዝቦላህን ትጥቅ ማስፈታት እንዲሁም በሊባኖስ እና በእስራኤል መካከል ሰላማዊ ግንኙነት እንዲፈጠር ማድረግ” ላይ የሚያተኩር ይሆናል ብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ይህንን ከማሳወቃቸው ቀደም ብሎ የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አዎንስ ብቸኛው መፍትሄ ሁለቱ አገራት ተኩስ አቁም አድርገው “ቀጥተኛ ድርድር” ማካሄድ ነው ሲሉ ተናግረው ነበረ።ፕሬዝዳንቱ የሊባኖስ የፀጥታ ኃይሎች “በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን” ሕግ የማስከበር ሥራቸውን ሙሉ ለሙሉ ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ተናግረዋል።እስራኤል የኢራን አጋር የሆነውን የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህን ዒላማ በማድረግ ከአንድ ወር በላይ ጥቃት እየፈጸመች ሲሆን፣ እግረኛ ወታደሮቿንም በደቡባዊ ሊባኖስ አሰማርታለች።እስራኤል ባለፉት ሁለት ቀናት ዋና ከተማዋ ቤይሩት ውስጥ እና በሌሎች በርካታ የሊባኖስ አካባቢዎች በፈጸመቻቸው ጥቃት ከ200 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።ያጋሩ, ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ከሊባኖስ ጋር ድርድር እንዲጀመር አዘዙ - 9 ሚያዚያ 2026ዴሞክራቶች የትራምፕን ጦርነት የማካሄድ ሥልጣን ለመገደብ እየጣሩ ነው
የፎቶው ባለመብት,Shutterstockፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከእራኤል ጋር በመሆን ኢራን ላይ በከፈቱት ጦርነት ደስተኛ ያልሆኑት ዴሞክራቶች፤ የፕሬዝዳንቱን ጦርነት የማወጅ ሥልጣን የሚገድበው ሕግ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለምክር ቤቱ ሊያቀርቡ ነው።በአሜሪካ ምክር ቤት አባል የሆኑት የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት አገራቸው ከኢራን ጋር ባካሄደችው ጦርነት ላይ ተቃውሞ ሲያሰሙ የቆዩ ሲሆን፣ በተለይ ሰኞ ዕለት ትራምፕ የኢራንን ሥልጣኔ “በአንድ ሌሊት እንደሚያጠፉ” ከዛቱ በኋላ ስጋታቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ መደረሱ ተነግሯል።ከአሜሪካ ምክር ቤት አባላት መካከል ጥቂት የማይባሉትም በፕሬዝዳንቱ ላይ የተሰማቸውን ቁጣ ወደ ሕግ ለመቀየር በአገሪቱ ሕግ መሠረት ፕሬዝዳንቱን ከሥልጣን ለማንሳት የሚያስችለው 25ኛው የሕግ ማሻሻያ ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።ነገር ግን ሕግ አውጪዎቹ ፕሬዝዳቱን ለመቆጣጠር ሊጠቀሙበት የሚችሉት ቁልፍ አሠራር ትራምፕ ጦርነት ለማካሄድ ያላቸው ሥልጣን የሚገድበውን ደንብ ተግባራዊ ማስደረግ ነው።ይህ እርምጃ በምክር ቤቱ ተቀባይነት አግኝቶ ከጸደቀ ኮንግረስ እስካልፈቀደ ድረስ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር በኢራን ላይ ምንም ዓይነት ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ አይችልም።በየካቲት ማብቂያ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ መክፈታቸውን ካሳወቁ በኋላ የፕሬዝዳንቱን ጦርነት የማካሄድ ሥልጣን ለመገደብ በሁለቱም የአገሪቱ ምክር ቤት ድምጽ ቢሰጥም ተቀባይነት የሚያስገኘውን ድጋፍ ሳያገኝ ቀርቷል።ዛሬም በድጋሚ በምክር ቤቱ የሚገኙ የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት በድጋሚ የትራምፕ ጦርነት የማካሄድ ሥልጣንን የሚገድበው ሕግ ተቀባይነት እዲያገኝ ሙከራ ያደርጋሉ።ውሳኔው አሁንም ተቀባይነት የማግኘቱ ጉዳይ አጠራጣሪ ቢሆንም፣ አሜሪካውያን ለጦርነቱ ያላቸውን አቋም ለማሳየት ያስችላቸዋል ተብሏል።ያጋሩ, ዴሞክራቶች የትራምፕን ጦርነት የማካሄድ ሥልጣን ለመገደብ እየጣሩ ነው - 9 ሚያዚያ 2026ስለ ኢራን ልናውቃቸው የሚገቡ አንዳንድ እውነታዎችከእስላማዊው አብዮቷ በኋላ ከምዕራባውያን በተለይም ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ሆድ እና ጀርባ ሆና የቆየችው ኢራን ለስድስት ሳምንታት ከእነዚሁ አገራት ጋር ከባድ ጦርነት ውስጥ ቆይታለች።በዓለም የሥልጣኔ ታሪክ ውስጥ ከሚጠቀሱት መካከል ፋርስ ተብሎ የሚታወቀው ሥልጣኔ ባለቤት የሆነችው ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ብዙ ሕዝብ ያላት እና በተፈጥሮ ሀብትም የታደለች ናት።ከምዕራባውያን ጋር በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት ጥርስ ውስጥ ገብታ በተለያዩ ማዕቀቦች ጫና ውስጥ ቆይታለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ጥቃት ሲፈጸምባት ቆይቶ የለየለት ጦርነት ተከፍቶባታል።ለ40 ቀናት ያህል ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ስለተፋለመችው ኢራን ልናውቃቸው የሚገቡ ዋና ዋና እውነታዎች እዚህ ይመልከቱ።https://flo.uri.sh/visualisation/27876509/embed?auto=1ያጋሩ, ስለ ኢራን ልናውቃቸው የሚገቡ አንዳንድ እውነታዎች
- 9 ሚያዚያ 2026በጦርነቱ ከ3,000 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ያካሄዱት ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ በነበሩት ሳምንታት ውስጥ ከሦስት ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የኢራን የሕክምና ምርመራ ድርጅት ዋና ኃላፊ የሆኑትን አባስ ማስጄዲ አራኒን ጠቅሰው እንደዘገቡት የካቲት 21/2018 ዓ.ም. በተጀመረው ጦርነት ከ3 ሺህ በላይ ኢራናውያን ሞተዋል።በአሜሪካ መቀመጫውን ያደረገው የሰብአዊ መብቶች ተከራካሪዎች የዜና ተቋም የሆነው ሂራና እንደዘገበው አስከ መጋቢት 29 ድረስ 254 ሕጻናትን ጨምሮ 1,701 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል።የዜና ወኪሉ ጨምሮም 1,221 የኢራን ጦር ሠራዊት አባላት እና 714 ማንነታቸው ያልተለዩ ሰዎች ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ተገድለዋል ብሏል።ዓለም አቀፍ የዜና ተቋማት ሌሎች ድርጅቶች በኢራን ውስጥ ለመንቀሳቀስ ስለማይፈቀድላቸው በሰዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ነው።በተጨማሪም ከጦርነቱ መጀመር አንስቶ በመላው አገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ መረጃዎችን ማግኘት እና ማጣራት አዳጋች ሆኗል።ያጋሩ, በጦርነቱ ከ3,000 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ - 9 ሚያዚያ 2026እስራኤል ነዋሪዎች ከተለያዩ የቤይሩት አካባቢዎች እንዲወጡ አዘዘች
የፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockበሄዝቦላህ “ወታደራዊ መሠረተ ልማቶች” ላይ ላይ ተጨማሪ ጥቃት የመፈጸም ዕቅድ የያዘችው እስራኤል፤ በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ደቡባዊ የከተማ ዳርቻዎች የሚገኙ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላለፈች።የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ አቪቻይ አድራኢ በእነዚ አከባቢዎች ለሚገኙ ነዋሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት፤ እስራኤል “እናንተን የመጉዳት ዕቅድ የላትም… ስለሆነም ለደኅንነታችሁ ሲባል በአስቸኳይ ለቅቃችሁ መውጣት አለባችሁ” ብለዋል።የእስራኤል ጦር የለቅቃችሁ ውጡ ማስጠንቀቂያ የሰጠባቸው፤ ሃሬት ህሬክ፣ ጎቤይሪ፣ አል ሊላኪ፣ ሀዳት፣ ቦርጅ ኤል ባራጅነህ፣ ታህዊታት አል-ጋዲር፣ ሺያህ እና አል-ጃናህ የተባሉት አካባቢዎች ናቸው።እስራኤል ቤይሩት ውስጥ የምትፈጽመውን ጥቃት በከፍተኛ መጠን የጨመረችው አሜሪካ እና ኢራን የደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት ሊባኖስን የማካተቱ ጉዳይ አከራካሪ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ ነው።ኢራን እና ስምምነቱን ያሸማገለችው ፓኪስታን ተኩስ አቁሙ ሊባኖስንም እንደሚያካትት ቢገልጹም እስራኤል አቋሟ በተቃራኒው እንደሆነ አሳውቃለች።ኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ዛሬ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ሊባኖስ ውስጥ የሚፈጸሙት ጥቃቶች የተኩስ አቁም ጥሰት እነደሆኑ ገልጸዋል።ሄዝቦላህ እስራኤል ላይ ተኩስ ካስወነጨፈ በኋላ በተከፈጠው ዘመቻ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሊባኖሳውያን ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።ያጋሩ, እስራኤል ነዋሪዎች ከተለያዩ የቤይሩት አካባቢዎች እንዲወጡ አዘዘች - 9 ሚያዚያ 2026የኢራን ፕሬዝዳንት “ጣቶቻችን አሁንም ቃታው ላይ ናቸው” ሲሉ አስጠነቀቁ
የፎቶው ባለመብት,Reutersእስራኤል በሊባኖስ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት አጠናክራ በቀጠለችበት በአሁኑ ጊዜ ኢራን በተጠንቀቅ ላይ እንደሆነች ፕሬዝዳንቷ አስታወቁ።የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን እስራኤል ሊባኖስ ላይ የምትፈጽመው ጥቃትም “ግልጽ የተኩስ አቁም ጥሰት” ነው ብለዋል።የእስራኤል ጥቃቶች መቀጠላቸው ሊደረስ ለሚችል ስምምነት ቁርጠኝነት እንደሚጎድል የሚሳይ “አደገኛ ምልክት” ነው ሲሉም ወቅሰዋል።የኢራኑ ፕሬዝዳንት ይህንን አስተያየት በኤክስ ገጻቸው ያሰፈሩት የእስራኤል ጦር የሄዝቦላህ ዒላማዎች እንደሆኑ በገለጻቸው የሊባኖስ ስፍራዎች ላይ ከ100 በላይ የአየር ጥቃቶችን በፈጸመ ማግሥት ነው።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያናሁ “አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ” ሄዝቦላህ ላይ ጥቃት እንደሚፈጽሙ በዛሬው ዕለት ተናግረዋል።የኢራኑ ፕሬዝዳንት ፔዜሽኪያን በኤክስ ልጥፋቸው የጥቃቶች መቀጠል ከአሜሪካ ጋር የሚደረገውን ድርድር ወደ “ትርጉም የለሽነት” እንደሚያወርደው ገልጸዋል። የኢራን ጣቶች “ቃታው ላይ ሆነው እንደሚቀጥሉም” ጽፈዋል።የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ በበኩላቸው “የተኩስ አቁም ጥሰቶች ግልጽ ዋጋ” እንደሚያስከፍሉ እና “ጠንካራ ምላሽ” እንደሚያስከትሉ ተናግረዋል።ሊባኖስ “የማትነጠል የተኩስ አቁሙ አካል” መሆኗን ገለጹት አፈ ጉባኤው ሞሐማድ ባገር ጋሊባፍ፤ “ለክህደት እና ማፈግፈግ የሚሆን ቦታ እንደሌለ” አሳስበዋል።“በአስቸኳይ እሳቱን አጥፉ” ሲሉም አክለዋል።ያጋሩ, የኢራን ፕሬዝዳንት “ጣቶቻችን አሁንም ቃታው ላይ ናቸው” ሲሉ አስጠነቀቁ - 9 ሚያዚያ 2026ዩናይትድ ኪንግደም፤ እስራኤል በሊባኖስ የምትፈጽመውን ጥቃት አወገዘች
የፎቶው ባለመብት,PA Mediaየዩናይትድ ኪንግደም መከላከያ ሚኒስትር ጆን ሄሊ አገራቸው የኢራን ጦርነትን ለማስቆም የተደረገውን የተኩስ አቁም እንደምትደግፍ እና እንዲዘልቅ እንደምትፈልግ ገልጸው፤ በሊባኖስ የሚታየውን የጥቃት መባባስ አወገዙ።የሩሲያ ሰርጓጅ መርከቦች እንቅስቃሴን ተመለከተ ዛሬ መግለጫ የሰጡት ሚኒስትሩ፤ የተኩስ አቁሙ ይዘልቃል ብለው ያስቡ እንደሆነ ከቢቢሲ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።“የተኩስ አቁሙን በበጎን እንቀበለዋለን። እንዲዘልቅ እንፈልጋለን። እንዲጠናከር ለማድረግ የራሳችንን ድርሻ እንወጣለን” ብለዋል።መከላከያ ሚኒስትሩ አክለውም፤ “ሊባኖስ ውስጥ የሚታየውን [የጥቃት] መባባስ እናወግዛለን። የእስራኤል ሊባኖስ ግጭት በተኩስ አቁሙ ማዕቀፍ ውስጥ እንዲካተት እንፈልጋለን፤ ምክንያቱም መላው የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና ወደ ትልቅ መረጋጋት ተመልሶ መመልከት እንፈልጋለን” ሲሉ ተናግረዋል።ሄሊ በመግለጫው ዩናይትድ ኪንግደም የኢራን ጦርነትን በተመለከተ የያዘችው አቋም እንደሚቀጥል ገልጸዋል። ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የዩናይትድ ኪንግደም ጦርን ወደ መካለኛው ምሥራቅ ማሰማራት “የብሪታኒያን ብሔራዊ ጥቅም” እንዳልሆነ አስረድተዋል።“በመካከለኛው ምሥራቅ እንደሆነው፤ ቀውስ በከፍተኛ ሁከት እና አደገኛ በሆነ ሁኔታ በሚፈነዳበት ወቅት፤ ሰዎች ለምን የዩኬ ወታደራዊ ይዞታዎች ችግሩን ለመፍታት አልተሰማሩም የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን እረዳለሁ” ብለዋል።“ነገር ግን ይሄ የብሪታኒያ ብሔራዊ ጥቅም አይደለም” ሲሉ ተናግረዋል።“ግዙፎቹ ስጋቶች ብዙውን ጊዜ የማይታዩ እና ድምጽ አልባ መሆናቸውን” የጠቀሱት መከላከያ ሚኒስትሩ፤ የመከላከያ ፍላጎቶች እየጨመሩ በመምጣታቸው የዩናይትድ ኪንግደም “ሀብቶቻችንን የተሻለ ውጤት ባላቸው [ጉዳዮች ላይ] ማሰማራት” አለብን ብለዋል።ያጋሩ, ዩናይትድ ኪንግደም፤ እስራኤል በሊባኖስ የምትፈጽመውን ጥቃት አወገዘች - 9 ሚያዚያ 2026ሆርሙዝ ተከፍቶ የሚቆየው አሜሪካ ጥቃቶችን እስካቆመች ድረስ መሆኑን ኢራን አስታወቀች
አሜሪካ ስታካሂድ የቆየውን “የወረራ ጥቃት” እስካቆመች ድረስ ለሳምንታት ተዘግቶ የቆየው የሆርሙዝ ወሽመጥ መልሶ እንደሚከፈት ኢራን አስታወቀች።የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳኢድ ኻቲብዛዴህ እንደተናገሩት አገራቸው መርከቦች በወሳኙን የባሕር መተላለፊያ በኩል እንዲተላፉ “ደኅንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን” እንደምታደርግ ገልጸዋል።አሜሪካ በኢራን ላይ ጦርነት እስከከፈተችበት ጊዜ ድረስ የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሺዎች ዓመታት ከፍት ሆኖ መቆየቱን ጠቅሰው፤ አሁንም መተላለፊያው ክፍት የሚሆነው እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምትፈጽመውን ጦርነት በመጥቀስ “አሜሪካ በተግባር ወረራው እንዲሆም” ስታደርግ ብቻ ነው ብለዋል።ባለሥልጣኑ ጨምረውም አገራቸው “ለዓለም አቀፍ ሕጎች እና ደንቦች እንድምትገዛ” ነገር ግን ሆርሙዝ የዓለም አቀፍ ውሃ አካል ባለመሆኑ፣ በወሽመጡ በኩል ያለ ችግር ለማለፍ “የኢራን እና የኦማን መልካም ፈቃድ ያስፋልጋል” ብለዋል።በሰላም በሆርሙዝ በኩል ማለፍ ማለትን በተመለከተ ኢራን የውሃ አካሉ “ሰላማዊ” እንዲሆን እንደምትፈልግ ነገር ግን ይህ የሚሆነው ሌላውም አካል ተመሳሳዩን ሲያደርግ እንደሆነ እና አገራቸው ባሕረ ሰላጤውን “የጦር መርከቦች”ያላግባብ እንዲጠቀሙበት አትፍቅድም ብለዋል።ያጋሩ, ሆርሙዝ ተከፍቶ የሚቆየው አሜሪካ ጥቃቶችን እስካቆመች ድረስ መሆኑን ኢራን አስታወቀች - 9 ሚያዚያ 2026ስታርመር ለባሕረ ሰላጤው አገራት ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን እንደ መደራደሪያ መያዝ የለባትም አሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ኪር ስታርመር የገልፍ ጉብኝታቸውን በመቀጠል የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ገብተዋልየተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የገቡት የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ኢራን “የሆርሙዝ ወሽመጥን መደራደሪያ” ማድረግ የለባትም አሉ።ስተርመር ከባሕረ ሰላጤው አገራት የመከላከያ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ንግግር አገራቸው በጦርነቱ ላይ ቋሚ አቋም ማንፀባረቋን ያነሱ ሲሆን፤ ግጭቱ እንዲረግብ እና ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ አቅርበዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሆርሙዝ ወሽመጥ ጉዳይ አገራት በአንድ ላይ በመስራት መፍትሔ መፈለግ ይገባቸዋል ብለዋል።አሜሪካ እና ኢራን ተኩስ የማቆም ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ያለፈቃድ የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማለፍ የሚፈልግ መርከብ ዒላማ እንደሚደረግ እና ጉዞው እንደሚዘገይ አስታውቋል።የዋይት ሐውስ ፕሬስ ኃላፊ ካሮሊን ሌቬት ግን የሆርሙዝ ወሽመጥ ተዘግቷል የሚሉ ሪፖርቶች ሐሰተኛ ናቸው ብለዋል።ያጋሩ, ስታርመር ለባሕረ ሰላጤው አገራት ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን እንደ መደራደሪያ መያዝ የለባትም አሉ - 9 ሚያዚያ 2026ኔታንያሁ እስራኤል “አስፈላጊ በሆነ ጊዜ” ሄዝቦላህ ላይ ጥቃት እንደምትፈጽም ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እስራኤል “አስፈላጊ በሆነ ጊዜ” ሄዝቦላህ ላይ ጥቃት እንደምትፈጽም ተናገሩ።እስራኤል ከዚህ ቀደም አሜሪካ እና ኢራን የደረሱት የተኩስ አቁም ስምመምነት ሊባኖስን እንደማያካትት ተናግረው ነው።ኢራን ግን እስራኤል ሊባኖስ ላይ የፈጸመችው ጥቃት የስምምነቱ “ከባድ ጥሰት” ነው ብላለች።ኔታንያሁ “መልዕክታችን ግልጽ ነው። ማንም ከእስራኤል ሰላማዊ ዜጎቻችን በተቃራኒ የቆመ ዒላማ ይሆናል” ብለዋል።“በሰሜን የሚገኙ ነዋሪዎችን ሙሉ ደኅንነት እስክናረጋግጥ ድረስ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ሄዝቦላህን እንደበድባለን።”ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት የእስራኤል መከላከያ የሄዝቦላህ ዋና ፀሐፊ ናይም ቃሰም የወንድም ልጅ የሆነውን አሊ ዩሱፍ ሃርሺን መገደሉን ካስታወቀ በኋላ ነው።ያጋሩ, ኔታንያሁ እስራኤል “አስፈላጊ በሆነ ጊዜ” ሄዝቦላህ ላይ ጥቃት እንደምትፈጽም ተናገሩ - 9 ሚያዚያ 2026በሊባኖስ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ200 በላይ ሰዎች ተገደሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰዓታት በመላ አገሪቱ የተፈጸመ የእስራኤል ጥቃትን ተከትሎ 203 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ1000 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን ገለጸ።ኢራን በበኩሏ በሊባኖስ ላይ እየተፈጸመ የሚገኘው ድብደባ ከአሜሪካ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የተፈጸመ “ከባድ ጥሰት” ነው ስትል ተናግራለች።የኢራን ውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር በሊባኖስ ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ከአሜሪካ ጋር ረቡዕ ምሽት በአደራዳሪዋ ፓኪስታን በኩል ንግግሮች እንደነበሩ ተናግረዋል።አሜሪካ እና ኢራን ለሁለት ሳምንት የሚቆይ ጊዜየዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጋቸወን ተከትሎ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ “ሊባኖስን አያካትትም” በማለት መጠነ ሰፊ ጥቃት ከፍተዋል።ይህንንም ተከትሎ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ “በተቻለ መጠን ጥቃቱን እንዲየስቆምላቸው” ተማጽኖ አቅርበዋል።ናዋፍ ሳላም የእስራኤል ጦር ጥቃቶች ለዓለም አቀፍ ሕግ “ፍፁም ቸልተኝነት” አሳይተዋል በማለት “ሁሉም የሊባኖስ ወዳጆች እነዚህን ጥቃቶች በሁሉም መንገዶች ለማስቆም እንዲረዱን ጥሪ እናቀርባለን” ብለዋል።ያጋሩ, በሊባኖስ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ200 በላይ ሰዎች ተገደሉ - 9 ሚያዚያ 2026እስራኤል በሊባኖስ ላይ የፈጸመችውን ጥቃት እነማን አወገዙ?
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,እስራኤል በቤይሩት ታሌት ኤል ኻህያት የፈጸመችውን ጥቃትተከትሎ የወደመ መኪናው አጠገብ የቆመ ሰውየዩኬ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዬቬት ኩፐር እስራኤል በሊባኖስ ላይ የፈጸመቸውን ጥቃት “ሙሉ በሙሉ ስህተት” ሲሉ ገልጸውታል። ሌሎች የአውሮፓ አገራትም የአየር ድብደባውን አውግዘዋል።የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዢን ኖኤል ባሮት “ተቀባይነት የሌለው” ሲሉ ያወገዙት ሲሆን፣ ኢራንም የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ለመታጠቅ የምታደርገውን ጥረት እንዲሁም ለሄዝቦላህ እና ለሐማስ የምትሰጠውን ድጋፍ መተው አለባት ብለዋል። የእስራኤል ጥቃት “በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የተደረሰውን ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ዝቅ የሚያደርግ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም” ሲሉ አክለዋል።የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በበኩላቸው “መመለሻ የሌለው ነጥብ ላይ ደርሰናል፤ አሁን ግን በቁርጠኝነት ሊተገበር የሚገባው የሰላም ተስፋ እየጠበበ ነው” ብለዋል።ስፔን በቴህራን የሚገኘው ኤምባሲዋን ዳግም ልትከፍት መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ሆዜ ማኑኤል አልባሬሰ “የተኩስ አቁሙን በግልጽ ጥሳለች” ሲሉ እስራኤልን ወንጅለዋል። አክለውም “የዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት ነው” ሲሉ ኮንነውታል።ያጋሩ, እስራኤል በሊባኖስ ላይ የፈጸመችውን ጥቃት እነማን አወገዙ? - 9 ሚያዚያ 2026የኢራን ሚኒስትር እስራኤል በሊባኖስ የፈጸመችው ድብደባ የተኩስ አቁሙ “ከባድ ጥሰት ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳይድ ኻቲብዛድ ከቢቢሲ ቱደይ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቆይታ እስራኤል ረቡዕ ዕለት በሊባኖስ የፈጸመችው ድብደባ የተኩስ አቁሙ “ከባድ ጥሰት ነው” አሉ።ሚኒስትሩ አሜሪካ ኢራን ላይ ጦርነት ከመክፈቷ በፊት ለዘመናት ክፍት ሆኖ ለዘለቀው የሆርሙዝ ወሽመጥ ቴህራን “ደኅንነቱ የጠበቀ እንቅስቃሴ” እንደምትሰጥ ገልጸዋል።ሆኖም ወሽመጡ ዳግም የሚከፈተው “አሜሪካ በትክክል ከጥቃቷ ስትታቀብ” እንደሆነ እስራኤል ሊባኖስ ላይ የፈፀመችውን ጥቃት በማመልከት ገልፀዋል።ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኢራን “ለዓለም አቀፍ መርኅ እና ሕግ ተገዢ” እንደምትሆን ጠቅሰው፤ ሆኖም ግን የሆርሙዝ ወሽመጥ ዓለም አቀፍ ውሃ እንዳልሆነ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ “በኢራን እና ኦማን መልካም ፈቃድ” ላይ የተመሠረተ ነው ብለዋል።ሚኒስትሩ ደኅንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ ማለት ኢራን በእያንዳንዱ መርከብ ክፍያ መጣል ወይም ለመደብደብ ማስፈራራት ማለት ነው ተብለው ተጠይቀዋል።ሚኒስትሩ በምላሻቸው ኢራን ወሽመጡ “ሰላማዊ” እንዲሆን እንደምትሻ ጠቁመው፤ ሆኖም ደኅንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ ሁለት ወገን እንደሆነ እና ሰርጡ “ለጦር መርከቦች ያለአግባብ ጥቅም ላይ እንዲውል” አንፈቅድም ብለዋል።ኢራን እና አሜሪካ የተኩስ አቁም ላይ መድረሳቸው ይፋ ቢደረግም እስራኤል ሊባኖስ ላይ ጥቃት መፈጸም በመቀጠሏ ትናንት ለዋይት ሐውስ ጠቅለል ያለ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።“በአንድ ግዜ ኬክ ሊኖርህም ልትበላው አትችልም” በማለት የተኩስ አቁም ላይ ተደርሶ ሊባኖስን መደብደብ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል።አክለውም በስምምነቱ ላይ ሊባኖስ መጠቀሷን በማንሳት የአሜሪካ አጋር የሆችው እስራኤል ግን “ጭፍጨፋ” መፈጸሟን በመጥቀስ ወንጅለዋል።አሜሪካ ጦርነት ወይም ሰላም እንደምትፈልግ “መምረጥ አለባት” ያሉት ሚኒስትሩ ሁለቱም በተመሳሳይ ወቅት ሊኖራት አይችልም ብለዋል።እስራኤል በሊባኖስ የምታካሄደውን ድብደባ ከቀጠለች ከስምምነቱ ይወጡ እንደሆን የተጠየቁት ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “በአጠቃላይ መካከለኛው ምሥራቅ ደህንት ላይ ነው ትኩረታችን” ሲሉ መልሰዋል።ኢራን ሄዝቦላህ ሮኬት መተኮሱን እንዲያቆም ታደርግ እንደሆን ሲጠየቁ ስምምነቱ ሊባኖስን ያካተተ ነው ኢራን እና አጋሮቿ “የተኩስ አቁሙን ለመቀበል” ፈቃደኞች ናቸው ብለዋል።ያጋሩ, የኢራን ሚኒስትር እስራኤል በሊባኖስ የፈጸመችው ድብደባ የተኩስ አቁሙ “ከባድ ጥሰት ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናገሩ - 9 ሚያዚያ 2026የአሜሪካ-ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ‘አጠራጣሪ’ ቢሆንም የኢራን ተደራዳሪዎች ወደ ፓኪስታን አቀኑ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን ተደራዳሪዎች ልዑክ ከአሜሪካ ጋር ጦርነቱን ለማቆም ወደ ፓኪስታን ማምራቱን በፓኪስታን የኢራን አምባሳደር አረጋግጠዋል።ልዑኩ ቅዳሜ ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዴ ቫንስ ጋር ይገናኛል።በፓኪስታን የኢራን አምባሳደር ሬዛ አሚሪ ሞግሃደም በኤክስ ገፃቸው ድርድሩ “ኢራን ባቀረበችው ባለ 10 ነጥብ ምክረ ሐሳብ” ላይ መሆኑን ተናግረዋል።ድርድሩ በየትኛው አገር ባቀረበው ነጥብ ላይ ነው የሚለው አወዛጋቢ ጉዳይ ሆኗል።አምባሳደሩ ንግግሩ የእስራኤል አገዛዝ የዲፕሎማቲክ ጥረቶችን ለማሰናከል በተደጋጋሚ የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ ኢራናውያን ጥርጣሬ ባደረባቸው ሰዓት እንደሚካሄድም ጠቅሰዋል።ያጋሩ, የአሜሪካ-ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ‘አጠራጣሪ’ ቢሆንም የኢራን ተደራዳሪዎች ወደ ፓኪስታን አቀኑ - 9 ሚያዚያ 2026ትራምፕ ኢራን “ትክክለኛውን ስምምነት” እስክታከብር ድረስ ሲሉ ምን ማለታቸው ነው?
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአሜሪካ እና ኢራን ያወጁት ለሁለት ሳምንት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነው።አለመግባባቱ የመጣው ባለ አስር ነጥብ ዕቅድ በሚል እየተዘዋወረ ካለው ሰነድ ጋር ተያይዞ ነው።ትራምፕ “በዩናይትድ ስቴትስ ተቀባይነት ያለው እና አንድ ትርጉም ያለው” ስምምነት ብቻ መኖሩን ተናግረዋል።ይህንንም ትክክለኛ ስምምነት በሚል በመጥራት “የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎች እንደማይኖር እንዲሁም የሆርሙዝ ወሽመጥ ይከፈታል፤ ደህንነቱም የይጠባቃል” የሚል መሆኑን ጠቅሰዋል።በኢራን ወገን ግን የተለያዩ የስምምነት ሰነዶች ይገኛሉ።የኢራን ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን በኢራን፣ ኢራቅ፣ የመን እና ሊባኖስ የሚካሄደውንው ውግያ የሚያስቆም እንዲሁም የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መክፈት እና አሜሪካ ማዕቀቦችን ለማንሳት ሙሉ ቁርጠኝነት እንዳላት የሚግለጽ ሰነድን አቅርቧል።በኋላ ላይ ደግሞ የኢራን ጠቅላይ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ይፋ ያደረገው ባለ አስር ነጥብ ዕቅድ ዩራኒየም ማበልጸግ እና ቴህራን የሆርሙዝ ወሽመጥን እንደምትቆጣጠር የሚሉ ሃሳቦችን ይዞ መጥቷል።በደህንነት ምክር ቤቱ መግለጫ ውስጥ በእንግሊዘኛ የቀረበው መግለጫ ላይ ዩራኒየም ማበልጸግ የሚለው ሃሳብ በኋለ ላይ እነዲወጣ ተደርጓል።ትራምፕ የማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፋቸው ላይ በተኩስ አቁሙ ሊባኖስ ስለመካተቷ ያሉት ነገር የለም። ነገር ገን በተኩስ አቁሙ ዙሪያ ላለመግባባት ምክንያት ከሆኑት ጉዳዮች መካከል አንዱ ግን የሊባኖስ አለመካተት ነው።ያጋሩ, ትራምፕ ኢራን “ትክክለኛውን ስምምነት” እስክታከብር ድረስ ሲሉ ምን ማለታቸው ነው? - 9 ሚያዚያ 2026የአሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ጥርጣሬ ማሳደሩን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአሜሪካ ኢራንን ለሁለት ሳምንት ላለማጥቃት ከተስማማች በኋላ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ አሳይቶ የነበረ ቢሆንም ሐሙስ ጠዋት ግን ዳግም ጨምሯል።በዓለም አቀፍ ገበያ ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በበርሚል 2.2 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 96.70 ዶላር ገብቷል። በአሜሪካ ገበያ ደግሞ ከዚህም ከፍ በማለት በ2.8 በመቶ በመጨመር 96.90 ዶላር ገብቷል።እስራኤል በሊባኖስ ላይ ተከታታይ ጥቃት መክፈቷን ተከትሎ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ላይ ቀዳዳዎች እንዲታዩ አድርጓል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስምምነቱን ካበሰሩ በኋላ ረቡዕ ዕለት ብሬንት ነዳጅ በ15 በመቶ በመቀነስ አንድ በርሜል 92 ዶላር ገብቶ ነበር። በኋላ ላይ ግን የነዳጅ ዋጋ ከዚህ ትንሽ ከፍ ብሏል።የነዳጅ ዋጋ ጦርነቱ የካቲት 21/ 2018 ዓ.ም. ከመጀመሩ በፊት ከነበረበት ዋጋ በጣም ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።ያጋሩ, የአሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ጥርጣሬ ማሳደሩን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ
