ኢሕአፓ/eprp 

ልዩ የበዓል ዜና

የትብብሩ አመራሮች የትንሣኤ በዓልን ከፖለቲካ እሥረኖች ጋር አብረው እያከበሩ ይገኛሉ።

ቂሊንጦ የሚገኙ እነአቶ ክርስቲያን ታደለና ሌሎችም በሚገኙበት ከጠዋት ያሳለፉ ሲኾን በተለይ አቶ ዮሐንስና ዶ/ር ካሳን ጨምሮ የጤና እክል ገጥሟቸው የነበሩ እሥረኞችን ጠይቀዋል። በቂሊንጦ 15(አሥራ አምስት) የሚጠጉ እስረኞች ጋር ያከበሩ ሲኾን የበርካቶቹ መንፈሰ ጠንካራነትና ለሕዝብ ሕልውና የሚከፈል ዋጋ አድርገው እንደሚቆጥሩት የታዘብን ሲኾን በአንጻሩ የጤናቸው ኹኔታ ከፍተኛ ክትትል እንደሚያስፈልገው ተገንዝበናል።

ከሰዓት በኋላ መሥከረም አበራና ገነት አስማማው በሚገኙበት ቃሊቲ በርከት ያሉ አመራሮች እንዲኹ ተገኝተው በዓሉን ያሳለፉ ሲኾን ኹለቱም እንሥቶች መንፈሰ ጠንካራነታቸው የሚያስተምር ነው። ኾኖም የወ/ት ገነት የጤና ኹኔታ አኹንም ብዙ አልተሻሻለም። የመሥከረም ሕጻናት ልጆችም ትምህርት ቤት አንሄድም ከእናታችን ጋር ውሰዱን የሚለው ኹኔታቸው በከፍተኛ ኹኔታ ጫና እንዳሰደረባትና ለደም ግፊትና ተያያዥ የጤና እክሎች እንዳጋለጣት ታዝበናል።

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የእሥረኞች ኹኔታ ከምርጫው ጋር የማይነጣጠል አድርጎ የሚወስደው ሲኾን መንግሥት መያዣ ከማድረግ ወጥቶና ፖለቲካዊ መፍትሔ ሰጥቶ ቢያንስ ውጣ ውረድ የሌለበትንና የሌላ ወገን ፈቃድን የማይሽትባቸውን በእጁ የሚገኙ እሥረኞችን ያለምንም ቅድመ ኹኔታ እንዲፈታና ሰላም ትንሹን ግዴታውን በተግባር እንዲወጣ በአጽንዖት እንጠይቃለን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት – ለኢትዮጵያ

ሚያዝያ ፬ ቀን 2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

******

👍 ገጾቻችንን ይወዳጁ👍