አሜሪካ በሆርሙዝ ላይ የጣለችው እገዳ ተግባራዊ መሆን እንደጀመረ ቢነገረም ከኢራን ጋር ግንኙነተ ያላቸው አራት መርከቦች በወሽመጡ በኩል ማለፋቸውን ቢቢሲ ቬሪፋይ የተነተነው የመርከቦች ጉዞ የትክክል መረጃ አሳየ። ‘ማሪን ትራፊክ’ የተሰኘው መርከቦች ጉዞ መከታተያ ድረ ገጽ መረጃ እንደሚመለክተው ከአራቱ ውስጥ ሁለቱ መርከቦች የኢራን ወደቦችን ጉብኝተው ነበር።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 31 ደቂቃዎች በፊትጣሊያን ከእስራኤል ጋር ያላትን ወታደራዊ ስምምነት እንደማታድስ አስታወቀችየጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጆርጂያ ሜሎኒየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesጣሊያን ከእስራኤል ጋር የገባችውን ወታደራዊ ስምምነት እንደማታድስ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጆርጂያ ሜሎኒ ተናገሩ።ሜሎኒ በየአምስት ዓመቱ ይታደስ የነበረውን የሁለቱን አገራት ወታደራዊ ስምምነት ለማዘግየት የወሰኑት “አሁን ያለውን ሁኔታ ከግምት በማስገባት” እንደሆነ ተናግረዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሯ ስለጉዳዩ በዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል።ነገር ግን ሮም እና ቴል አቪቭ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመካከላቸው ያለው ግንኙነት ንፋስ ገብቶታል።በሊባኖስ የተሰማራው የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ውስጥ እያገለገሉ የሚገኙ ጣሊያናውያን ላይ የማስጠንቀቂያ ተኩስ ከተተኮሰባቸው እና አንድ መኪና ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ባለፈው ሳምንት ጣሊያን በሮም የሚገኙትን የእስራኤል አምባሳደርን ጠርታ አነጋግራለች።ሰኞ ዕለት ደግሞ የጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ እስራኤል በሊባኖስ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈጸመችውን ጥቃት “ተቀባይነት የሌለው” ካሉ በኋላ “እንደ ጋዛ ያለ ግጭት ከመቀስቀሱ በፊት ማንኛውም ዋጋ ተከፍሎ ቢሆን መቆም አለበት” ሲሉ መናገራቸውን ተከትሎ እስራኤል የጣሊያን አምባሳደርን በመጥራት አነጋግራለች።ሌሎች የአውሮፓ አገራት በተመሳሳይ ከእስራኤል ጋር ያላቸውን የጦር መሣሪያ ውጭ ንግድ ገድበዋል ወይንም ለጊዜው አቁመዋል።የጣሊያን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለረዠም ጊዜ አገራቸው ተመሳሳይ እርምጃ እንድትወስድ ሲወተውቱ ነበር።ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጣሊያናውያን እስራኤል በጋዛ የፈጸመችውን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት ተከትሎ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።ሠልፈኞቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ የፍልስጤም ነጻ አገርነትን እንደ ሌሎች ለመቀበል ዳተኛ በመሆን ተችተዋቸዋል።ጣሊያን ከእስራኤል ጦር መሣሪያ ከሚገዙ ሦስት ቀዳሚ አገራት መካከል አንዷ ናት።ከፊት ያሉት ሁለት አገራት አሜሪካ እና ጀርመን ናቸው።ያጋሩ, ጣሊያን ከእስራኤል ጋር ያላትን ወታደራዊ ስምምነት እንደማታድስ አስታወቀች
  2. ከ 1 ሰአት በፊትየኢራን ፕሬዝዳንት ወታደራዊ እርምጃ አሜሪካ “ራሷ የፈጠረችውን ችግር” ያባብሳል አሉፕሬዝዳንት መሱድ ፐዝሽኪያንየፎቶው ባለመብት,IRANIAN PRESIDENCYየኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዝሽኪያን ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ቴህራን የሰላም ንግግሮችን ለመቀጠል ዝግጁ መሆኗን እና ግጭቶችን ለመፍታት የምትመርጠው ዲፕሎማሲያዊ መንገድን እንደሆነ መናገራቸውን የኢራን የዜና አውታሮች ዘገቡ።ፕሬዝዳንቱ ለማክሮን ዛቻዎች፣ ጫናዎች እና ወታደራዊ እርምጃዎች ችግሮችን ለመፍታት “አያግዙም” በማለት ተናግረዋል። አሜሪካ “ራሷ የፈጠረችውን ችግር” የሚያባብስ እንደሚሆንም አሳስበዋልፕሬዝዳንት ፔዝሽኪያን አሜሪካ ለዓለም አቀፍ ሕግ እና መመሪያ ተገዢ እንድትሆን አውሮፓ ማበረታታት አለበት ሲሉም አክለዋል።ያጋሩ, የኢራን ፕሬዝዳንት ወታደራዊ እርምጃ አሜሪካ “ራሷ የፈጠረችውን ችግር” ያባብሳል አሉ
  3. ከ 1 ሰአት በፊትከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው አራት መርከቦች ከአሜሪካ እገዳ በኋላ በሆርሙዝ ወሽመጥ አለፉበሆርሙዝ የሚጓዝ መርከብየፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ በሆርሙዝ ላይ የጣለችው እገዳ ተግባራዊ መሆን እንደጀመረ ቢነገረም ከኢራን ጋር ግንኙነተ ያላቸው አራት መርከቦች በወሽመጡ በኩል ማለፋቸውን ቢቢሲ ቬሪፋይ የተነተነው የመርከቦች ጉዞ የትክክል መረጃ አሳየ።‘ማሪን ትራፊክ’ የተሰኘው መርከቦች ጉዞ መከታተያ ድረ ገጽ መረጃ እንደሚመለክተው ከአራቱ ውስጥ ሁለቱ መርከቦች የኢራን ወደቦችን ጎብኝተው ነበር።’ክርስቲያና’ የተሰኘችው የጭነት መርከብ ወደ ኢራን ባንዳር ኢማን ኮሜኒ ወደብ ተጉዛ የነበረ ሲሆን ሰኞ ዕለት አሜሪካ እገዳ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ ደግሞ በወሽመጡ በኩል ማለፏን መረጃው ያሳያል።ከኢራን ጋር በሚያደርገው የንግድ እንቅስቃሴ ምክንያት በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለበት ‘ሪች ስቴሪ’ የተባለ ሌላ መርከብ ደግሞ ትናንት ሌሊት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሻርጃ በመነሳት በሆርሙዝ በኩል ተጉዟል። መርከቡ መዳረሻው ቻይና እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።በወሽመጡ በኩል ያለፈው ሌላኛው ነዳጅ ጫኝ መርከብ ‘ሙርሊኪሻን’ የሚል ስያሜ የተሰጠው ነው። ይህም መርከብ ከኢራን ጋር ባለው ንግድ ምክንያት አሜሪካ ማዕቀብ ጥላበታለች።መርከቡ ከቻይና ላንሻን እንደተነሳ እና ሌሊቱን በሆርሙዝ በኩል እንዳለፈ መረጃው አሳይቷል። እንደ ማሪን ትራፊክ ከሆነ፤ መርከቡ የታየበት የመጨረሻው ስፍራ ከኢራን ቃሽም ደሴት በስተምስራቅ ያለ አካባቢ ነው።‘ኤልፒስ’ የተባለ ሌላ ነዳጅ ጫኝ መርከብም ማክሰኞ ዕለት ከኢራኑ ቡሼህር ወደብ ተነስቶ በወሽመጡ በኩል ማለፉን የጉዞ መከታተያው ድረ ገጽ መረጃ ይጠቁማል። መዳረሻው ያልታወቀው ይህ መርከብም በአሜሪካ ማዕቀብ ተጥሎበታል።እነዚህ መርከቦች አድራሻቸውን ለመደበቅ ሲሉ የሚገኙበትን ቦታ በተመለከተ የተሳሳተ መረጃ አሰራጭተው ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።የአሜሪካ ጦር ከትናንት ሰኞ 11 ሰዓት ጀምሮ “ወደ ኢራን ወደቦች ለመግባት እና ለመውጣት የሚደረጉ የባሕር ጉዞዎችን በሙሉ” እንደሚያግድ አስታውቆ ነበር።”እገዳው በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወይም ከ[ኢራን] ወዳልሆኑ መዳረሻዎች የሚደረጉ ገለልተኛ የትራንዚት ጉዞዎችን” ግን እንደማያስቆም ገልጾ ነበር።ያጋሩ, ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው አራት መርከቦች ከአሜሪካ እገዳ በኋላ በሆርሙዝ ወሽመጥ አለፉ
  4. ከ 2 ሰአት በፊትቻይና “አደገኛው እና ኃላፊነት የጎደለው” የአሜሪካ እገዳ “ውጥረቱን ያባብሳል” ስትል አስጠነቀቀችየቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ጉኦ ጂያኩንየፎቶው ባለመብት,EPA-EFE/Shutterstockየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሜሪካ ከትናንት ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረችውን ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረግ የጉዞ እገዳ “አደገኛ እና ኃላፊነት የጎደለው” በማለት አወገዘ።ውጤት ያልተገኘበት የአሜሪካ እና ኢራን ንግግር ፓኪስታን ውስጥ ከተካሄደ ከአንድ ቀን በኋላ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ወደ ኢራን ወደቦች ጉዞ እንዳይደረግ ዘግቷል።የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ጉኦ ጂያኩን፤ እገዳው “ውጥረቱን ከማባባስ እና ቀድሞውንም ደካማ የሆነውን የተኩስ አቁም ስምምነት ከመሸርሸር” ያለፈ ውጤት እንደማይኖረው አስጠንቅቀዋል።“ይሄ አደገኛ እና ኃላፊነት የጎደለው ባሕሪ ነው” ሲሉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።ቃል አቀባዩ አክለውም ቻይና ለኢራን አዲስ የአየር መከላከያ ስርዓት እያዘጋጀች ነው የሚሉ ዘገባዎች “ሙሉ በሙሉ ፈጠራ ናቸው” ሲሉ አስተባብለዋል።ይህ ሪፖርት መውጣቱን ተከትሉ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቻይና ለኢራን ወታደራዊ እገዛ የምታደርግ ከሆነ በምርቶቿ ላይ የ50 በመቶ ታሪፍ እንደሚጥሉ ዝተዋል።“አሜሪካ በቻይና ላይ ተጨማሪ ታሪፍ ለመጣል ይህንን እንደ ምክንያት የምትጠቀም ከሆነ፤ ቻይና በእርግጠኝነት ቆራጥ የአጸፋ እርምጃዎችን ትወስዳለች” ብለዋል።ያጋሩ, ቻይና “አደገኛው እና ኃላፊነት የጎደለው” የአሜሪካ እገዳ “ውጥረቱን ያባብሳል” ስትል አስጠነቀቀች
  5. ከ 3 ሰአት በፊትየተባበሩት መንግሥታት የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመዝጋት የሚያስችል ሕጋዊ መሠረት የለም አለየህንድ መርከብ በሆርሙዝ በኩል እየተጓዘየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የማሪታይም ድርጅት፤ ማንም አገር ለዓለም አቀፍ ትራንዚት ጥቅም ላይ በሚውለው የሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚደረግ ጉዞን የማገድ ሕጋዊ መብት እንደሌለው ገለጹ።የዓለም አቀፉ የባሕር ጉዞ ተቋም ዋና ጸሐፊ አርሴኒዮ ዶሚንጌዝ ከቢቢሲ ራዲዮ 4 ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚደረግ ጉዞ መታገዱ አደገኛ ምሳሌን የሚያስቀምጥ እንደሆነ ተናግረዋል።“ግጭት እየተካሄደ እንደሆነ እረዳለሁ፤ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ለዓለም አቀፍ ጉዞ ጥቅም ላይ የሚውልን ማንኛውም ወሽመጥ ለማገድ የሚወሰድ እርምጃ በዓለም አቀፍ ሕግ ሕጋዊ መሠረት የለውም” ብለዋል።ዋና ጸሐፊው ዶሚንጌዝ፤ “ተጨማሪ የአጸፋ እርምጃዎች በተወሰዱ ቁጥር፤ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ መውጫ ያጡት 20 ሺህ ባሕርተኞች እና በዓለም ዙሪያ ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ የበረታባቸው ሰዎች ስጋት ይጨምራል” ሲሉም ተናግረዋል።“ለረጅም ጊዜ በቆየ ቁጥር ተጽዕኖው በሁላችንም ላይ ለተራዘመ ጊዜ ይቆያል” ሲሉም ስጋታቸውን ገልጸዋል።በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የተከፈተባት ኢራን ከዓለም ነዳጅ 20 በመቶው የሚተላለፍበትን የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዝጋት የአጸፋ እርምጃ ወስዳለች።ለእዚህ የኢራን እርምጃ ምላሽ የሰጡት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ በሆርሙዝ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረግ ጉዞን ከትናንት ጀምሮ አግደዋል።ያጋሩ, የተባበሩት መንግሥታት የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመዝጋት የሚያስችል ሕጋዊ መሠረት የለም አለ
  6. ከ 4 ሰአት በፊትሆርሙዝ በትራምፕ ትዕዛዝ ከተዘጋ በኋላ በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለበት የቻይና መርከብ ማለፉ ተዘገበበሆርሙዝ ወሽመጥ የሚጓዝ መርከብየፎቶው ባለመብት,Ian Forsyth/Getty Imagesየፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከትናንት ጀምሮ በሆርሙዝ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረግ እንቅስቃሴን ካገደ በኋላ በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለበት አንድ የቻይና ነዳጅ ጫኝ መርከብ በወሽመጡ በኩል ማለፉን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ።መዳረሻው ቻይና የሆነው ይህ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ ቆሞ የበረው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ወደብ ላይ እንደነበረ ቢቢሲ የተመለከታቸው መረጃዎች አሳይተዋል።“ሪች ስቴሪ” የተሰኘው ይህ ነዳጅ ጫኝ የአሜሪካ እገዳ ትናንት 11 ሰዓት ላይ ከተጀመረ በኋላ በወሽመጡ በኩል በማለፍ የፋርስ ባሕረ ሰላጤን ቀዝፎ የሄደ መርከብ መሆኑን የባሕር ጉዞ መከታተያ ድረ ገጾች አሳይተዋል ተብሏል።እንደ ሮይተርስ ዘገባ የመርከቡ ባለቤት “ሻንዳይ ዡአንረን ሺፒንግ” የተባለ እና ከኢራን ጋር በሚፈጽመው ንግድ ምክንያት በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለበት ኩባንያ ነው።ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እሁድ ዕለት ባስተላለፉት መልዕክት “ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ ለመግባት ወይም ከዚያ ለመውጣት የሚሞክር ማንኛውም እና ሁሉም መርከቦች” በአሜሪካ ባሕር ኃይል እንደሚታገዱ ገልጸው ነበር።ሰኞ ዕለት ደግሞ እገዳው የሚተገበረው “ወደ ኢራን ወደቦች በሚገቡ እና በሚወጡ” መርከቦች ላይ መሆኑን ተናግረዋል።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝም በተመሳሳይ “ወደ ኢራን ወደቦች ለመግባት እና ለመውጣት የሚደረጉ ሁሉም የባሕር ላይ ጉዞዎች” እንደሚታገዱ አስታውቋል።ይሁን እንጂ “እገዳው በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወይም ከ[ኢራን] ወዳልሆኑ መዳረሻዎች የሚደረጉ ገለልተኛ የትራንዚት ጉዞዎችን አያስቆምም” ብሏል።ቢቢሲ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ እገዳው ሰኞ 11 ሰዓት ላይ ተግባራዊ መሆን ከመጀመሩ አስቀድሞ ባሉት ሰዓታት አራት መርከቦች በወሽመጡ በኩል አልፈዋል።‘ማሪን ትራፊክ’ የተሰኘው የባሕር ጉዞ መከታተያ ድረ ገጽ መረጃ እንደሚያሳየው አራቱም የጭነት መርከቦች ናቸው። ምናልባትም ነዳጅ፣ ጋዝ ወይም ኬሚካል ጭነው እንደሚሆን ተገምቷል።ማክሰኞ ዕለት ጉዞ ያደረገው ብቸኛ መርከብ ‘ሪች ስቴሪ’ ነው። ይህ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ ቆሞ የነበረው በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ወደብ እንደሆነ እና መዳረሻውን ቻይና እንዳደረገ የ‘ማሪን ትራፊክ’ መረጃ ያሳያል።እንደ ሮይተርስ ዘገባ በዚህ መርከብ ላይ ያሉት የቻይና የባሕር ሠራተኞች ናቸው።በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለበት ሌላ መርከብም ወደ ወሽመጡ ማምራቱን የዜና ወኪሉ ‘ኤልኤስኢጂ’ ከተሰኘው የባሕር ጉዞ መከታተያ ድረ ገጽ መመልከቱን ጠቅሷል።ከዚህ ቀደም የሩሲያ እና የኢራን ነዳጅን በማጓጓዝ የሚታወቀው ይህ ሁለተኛ መርከብ፤ ሐሙስ ዕለት ኢራቅ ደርሶ ነዳጅ እንደሚጭን ይጠበቃል ተብሏል።ያጋሩ, ሆርሙዝ በትራምፕ ትዕዛዝ ከተዘጋ በኋላ በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለበት የቻይና መርከብ ማለፉ ተዘገበ
  7. ከ 5 ሰአት በፊትየኢራን አምባሳደር አሜሪካ የኢራን ወደቦችን መዝጋቷ “ከባድ” የሉዓዊነት “ጥሰት” ነው አሉየመርከብ ትራፊክ እንቅስቃሴየፎቶው ባለመብት,MarineTrafficየምስሉ መግለጫ,የመርከብ ትራፊክ የክትትል መረጃዎች በሆርሙዝ ወሽመጥ በጣም ጥቂት መርከቦች እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ያሳያሉበመንግሥታቱ ድርጅት የኢራን አምባሳደር አሜሪካ የኢራን ወደቦችን መዝጋቷን የቴህራን ሉዓላዊነት ላይ የተፈፀመ “ከባድ ጥሰት” ሲሉ አወገዙ።አምባሳደር አሚር ሳይድ ኦራቫኒ ለተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በፃፉት ደብዳቤ “ሕገ ወጥ” የሆነው እግድ “የዓለም አቀፍ የባሕር ሕግ መሠረታዊ መርህዎች ላይ ከባድ ጥሰት የሚፈፅም” ነው ብለዋል።ጉቴሬዝ “ሁሉም ወገኖች” ለዓለም የነዳጅ ዝውውር ቁልፍ በሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የመርከቦችን ነፃ እንቅስቃሴ እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።በአሜሪካ እና ኢራን መካከል በፓኪስታን የተደረገው የሰላም ንግግር ያለ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ የአሜሪካ ጦር ከትናንት ሠኞ ጀምሮ የኢራን ወደቦችን ዘግቷል።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) እግዱ “ያለ ልዩነት” ወደ ኢራን ወደቦች ወይም የባሕር ዳርቻ አካባቢዎች በሚገቡ እና በሚወጡ የሁሉም አገራት መርከቦች ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን አስታውቋል።ሆኖም ጦሩ በሆርሙዝ ወሽመጥ ከኢራን ወደቦች ውጭ የሚንቀሳቀሱ መርከቦችን እንደማይከለክል ገልጿል።ያጋሩ, የኢራን አምባሳደር አሜሪካ የኢራን ወደቦችን መዝጋቷ “ከባድ” የሉዓዊነት “ጥሰት” ነው አሉ
  8. ከ 6 ሰአት በፊትእስራኤል እና ሊባኖስ ዛሬ በአሜሪካ የሰላም ንግግር ይጀምራሉሊባኖስየፎቶው ባለመብት,Reutersየእስራኤል እና የሊባኖስ አምባሳደሮች ልዩ የተባለ የሰላም ንግግር በዛሬው ዕለት ዋሽንግተን ውስጥ ያደርጋሉ።ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሌላቸው የእስራኤል እና ሊባኖስ ባለሥልጣናት ለቀጥታ ንግግር ፊት ለፊት ሲገናኙ በአስርት ዓመታት ውስጥ ይህ የመጀመሪያው ነው።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ልዩ በሆነው የቀጥታ ንግግር እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።የሁለቱ ጎረቤት አገራት ንግግር አሜሪካ እና ኢራን የመካከለናውን ምሥራቅ ቶርነት ለመቋጨት ያደረጉት ስምምነት ያለ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ የሚደረግ ነው።መቀመጫቸውን በአሜሪካ ያደረጉት የእስራኤል እና ሊባኖስ አምባሳደሮች በአገራቱ መካከል የከፍተኛ ባለሥልጣናት የቀጥታ ንግግር ማድረግ በሚቻልበት መንገድ ላይም ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል።የሊባኖስ ሹማምንት በመጀመሪያ እስራኤል ሄዝቦላህ ላይ የከፈተችው ጦርነት ላይ የተኩስ አቁም እንዲደረስ የማስማማት ፍላጎት አላቸው።ይሁን እንጂ እስራኤል በኢራን የሚደገፈው ቡድን ትጥቁን መፍታት አለበት በሚል ሀሳቡን ውድቅ አድርጋዋለች።ሄዝቦላህ በበኩሉ የሁለቱ አገራትን ንግግር ውድቅ በማድረግ ስምምነት ለሚደረስበት ማንኛውም ጉዳይ እንደማይገዛ አስታውቋል።የአሁኑ የእስራኤል እና ሄዝቦላህ ግጭት ለሊባኖስ አውዳሚ ሆኗል። 500 ሴቶችን፣ ሕፃናትን እና የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ከ2,000 ሠዎች በላይ ሠዎች ሲገደሉ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሠዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል።ያጋሩ, እስራኤል እና ሊባኖስ ዛሬ በአሜሪካ የሰላም ንግግር ይጀምራሉ
  9. ከ 6 ሰአት በፊትየተመድ ዋና ጸሐፊ አሜሪካ እና ኢራን ወደ ድርድር እንዲመለሱ ጠየቁየተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፤ አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱ እንደሚቋጭ ተስፋ በማድረግ በድጋሚ ወደ ድርድር እንዲመለሱ ጥሪ አቀረቡ።ጉቴሬዝ፤ ጦርነቱን ለማብቃት የሚያስችል “ወታደራዊ አማራጭ እንደሌለ ግልጽ” መሆኑን ተናግረዋል።ሁለቱ አገራት ለሁለት ሳምንት የደረሱበት የተኩስ አቁም “ፍጹም መጠበቅ እንዳለበት” ያሳሰቡት ዋና ጸሐፊው፤ “ሁሉም” የስምምነቱ “ጥሰቶች ሊቆሙ እንደሚገባ” ገልጸዋል።“ስምምነት ላይ ለመድረስ ንግግር እንዲጀመር ጥሪ አቀርባለሁ” ብለዋል። የተመድ ዋና ጸሐፊ አክለውም ሁሉም አገራት “በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚደረገውን ጨምሮ የመርከቦች የጉዞ ነጻነትን ማክበር እንዳለባቸው” አስታውሰዋል።ጉቴሬዝ ይህንን ያሉት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ሆርሙዝ ወሽመጥን በመዝጋት የወሰደችውን እርምጃ በመድገም ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ ጉዞዎችን ካገዱ በኋላ ነው። ትራምፕ ይህንን እርምጃ የወሰዱት ኢራን ስምምነት ላይ እንድትደርስ ለማስገደድ መሆኑን ተናግረዋል።ያጋሩ, የተመድ ዋና ጸሐፊ አሜሪካ እና ኢራን ወደ ድርድር እንዲመለሱ ጠየቁ
  10. ከ 6 ሰአት በፊትየአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ኢራንን “በኢኮኖሚያዊ ሽብርተኝነት” ከሰሱየአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ የኢራን መንግሥት የሆርሙዝ ወሽመጥን በመዘጋት “የኢኮኖሚያዊ ሽብርተኝነት” ተግባር እየፈፀመ ነው ሲሉ ክስ አቀረቡ።ጄዲ ቫንስ ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጨዋታውን ሁለቱም አገራት መጫወት እንደሚችሉ አሳይተዋል ሲሉ ትራምፕ ወደ ኢራን ወደቦች መርከቦች እንዳይገቡ እና እንዳይወጡ የወሰዱትን የእግድ እርምጃ አንስተዋል።ኢራናዊያን “ኢኮኖሚያዊ ሽብርተኝነት የሚፈፅሙ” ከሆነ አሜሪካ “ምንም የኢራን መርከቦች እንዳይወጡ የማድረግ” መርኅን ትከተላለች ብለዋል።ምክትል ፕሬዝዳንቱ እርሳቸው የተሳተፉበት እና በፓኪስታን ኢስላማባድ ባለፈው ቅዳሜ የተደረገው ድርድር ትልቅ ለውጦች የታዩበት እንደሆነም አንስተዋል።“ኳሱ ኢራን ሜዳ ውስጥ ነው” ብለዋል። ኢራን ለውጥ በማድረግ “በወሳኝ ጉዳዮች” ላይ የአሜሪካን ፍላጎት መቀበል እንዳለባት ተናግረዋል።አሜሪካ የኢራንን የበለፀገ ዩራኒየም መቆጣጠር እና ቴህራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንደማታለማ ማረጋገጫ ማግኘት ትፈልጋለች።ያጋሩ, የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ኢራንን “በኢኮኖሚያዊ ሽብርተኝነት” ከሰሱ
  11. ከ 7 ሰአት በፊትኢራን የኒውክሌር እንቅስቃሴዋ ለአምስት ዓመት እንዲታገድ የሚያደርግ የስምምነት እቅድ ማቅረቧ ተዘገበጥቃት የተፈጸመባቸውን የኢራን ስፍራዎች የሚያሳይ ምስልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesኢራን የቅዳሜ ዕለቱ ንግግር ያለ ስምምነት ከተቋጨ በኋላ ዩራኒየም የማበልጸግ ተግባሯን ለአምስት ዓመት እንደምታግድ የሚገልጽ እቅድ ለአሜሪካ ማቅረቧን ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዘገበ።የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ላይ የሚደረገው እገዳ ለ20 ዓመታት እንዲቆይ በድርድሩ ወቅት የጠየቀችው አሜሪካ የቴህራንን እቅድ ውድቅ ማደረጓንም ዘገባው አመልክቷል።የኢራን እና አሜሪካ ባለሥልጣናትን የጠቀሰው የኒው ዮርክ ታይምስ ዘገባ፤ ቴህራን ይህንን እቅድ ለትራምፕ አስተዳደር ያቀረበችው ሰኞ ዕለት እንደነበር ይገልጻል።አሜሪካ ከእገዳው በተጨማሪ እጅግ የተበለጸገው የኢራን ዩራኒየም ከአገሪቱ እንዲወጣ ጠይቃ እንደነበር እና ቴህራን ጥያቄውን ውድቅ ማድረጓ ተዘግቧል።ይሁን እንጂ ኢራን የበለጸገ ዩራኒየሟን ለኒውክሌር ጦር መሣሪያነት እንዳይውል ለማድረግ በከፍተኛ መጠን ለመበረዝ አማራጭ ማቅረቧ ዘገባው ላይ ተጠቅሷል።አሜሪካ እና ኢራን በፓኪስታን በተካሄደው ድርድር የሰላም አማራጮቻቸውን አቅርበው ስምምነት ላይ አልደረሱም። ይሁን እንጁ ሁለተኛ ዙር የፊት ለፊት ንግግር ሊካሄድ እንደሚችል የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ ነው።የኢራን የኒውክሌር ፍላጎት ሁለቱን አካላት ስምምነት ላይ እንዳይደርሱ እንቅፋት እንደሆነ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ እንዲኖራት እንደማይፈቅዱ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል።ያጋሩ, ኢራን የኒውክሌር እንቅስቃሴዋ ለአምስት ዓመት እንዲታገድ የሚያደርግ የስምምነት እቅድ ማቅረቧ ተዘገበ
  12. ከ 7 ሰአት በፊትፕሬዝዳንት ትራምፕ የሆርሙዝን እንቅስቃሴ ያገዱት ኢራን እንድትስማማ ለማስገደድ መሆኑ ተናገሩየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረግ እንቅስቃሴን የዘጉት ቴህራን የሆርሙዝ ወሽመጥን እንድትከፍት እና ጦርነቱን ለመቋጨት የሚደረስ ስምምነትን እንድትቀበል ለማስገደድ መሆኑን ተናገሩ፥ፕሬዝዳንቱ፤ ኢራን ስምምነት ላይ እንድትደርስ ያስቀመጡትን ቀነ ገደብ አለመቀየራቸውም ገልጸዋል። ትራምፕ ትናንት በዋይት ሀውስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ “ኢራን ክፉኛ ስምምነት ላይ መድረስ ትፈልጋለች” ብለዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሰጡት ትዕዛዝ መሠረት ከትናንት 11 ሰዓት ጀምሮ ወደ ኢራን ወደቦች መግባት እና ከወደቦቹ መውጣት ተከልክሏል። ግዙፉን አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ጨምሮ ሦስት የአሜሪካ የጦር መርከቦች ከዚህ ቀደም ባልታየ መጠን ወደ ኦማን ባሕረ ሰላጤ መጠጋታቸው በሳተላይት ምስሎች ተረጋግጧል።ትራምፕ በትናንቱ መግለጫቸው ላይ ስለዚህ ጉዳይ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ “አንድ አገር ዓለምን እንዲያስፈራራ ወይም እንዲያሰቃይ መፍቀድ አንችልም፤ ምክንያቱም እነሱ እያደረጉት ያሉት ይህንን ነው” ሲሉ እገዳውን ያደረጉበትን ምክንያት ጠቅሰዋል።በአሁኑ ሰዓት ከኢራን ጋር እየተካሄደ ያለ “ምንም ዓይነት ውጊያ አለመኖሩን” ጠቀሱት ትራምፕ፤ “እገዳ ጥለናል፤ ምንም ዓይነት የንግድ እንቅስቃሴ እያደረጉ አይደለም” ሲሉ ተናግረዋል።አሜሪካ እና ኢራን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ፓኪስታን ውስጥ ያደረጉት ድርድር የተጠናቀቀው ያለ ስምምነት ነበር። እንደ ትራምፕ ገለጻ ሁለቱን አገራት ያላስማማው የኒውክሌር ጉዳይ ነው።“በብዙ ጉዳዮች ላይ ተስማምተናል፤ እዚያ ጉዳይ ላይ ግን አልተስማሙም” ሲሉ ተደምጠዋል። “ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ አይኖራትም” ሲሉም አቋማቸውን አረጋግጠዋል።ይሁን እንጂ በመጨሻም ከኢራን ጋ ስምምነት ላይ እንደሚደረስ “እርግጠኛ” መሆናቸውን ገልጸዋል። “የማይስማሙ ከሆነ፣ ስምምነት አይኖርም” ብለዋል።አክለውም ግን ኢራን መሪዎች ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚፈልጉ እና “ከተገቢዎቹ ሰዎች” የስልክ ጥሪ እንደደረሳቸው አስታውቀዋል።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሆርሙዝን እንቅስቃሴ ያገዱት ኢራን እንድትስማማ ለማስገደድ መሆኑ ተናገሩ
  13. 13 ሚያዚያ 2026የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጦርነቱን ለማስቆም አሁንም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናገሩየፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሻሪፍየፎቶው ባለመብት,Reutersየቅዳሜ ዕለቱን ድርድር ያስተናገዱት የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሻሪፍ፤ በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የሚደረገውን ጦርነት ለመቋጨት የሚደረገው ጥረት መቀጠሉን ተናገሩ።የሁለቱ አገራት ልዑኮች ከትናንት በስቲያ በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ ተገኝተው ለ21 ሰዓታት የዘለቀ ድርድር ቢያደርጉም ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ተለያይተዋል።የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት “ጉዳዩን ለመፍታት ሙሉ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ልነግራችሁ እፈልጋለሁ” ብለዋል።“የተኩስ አቁሙ አሁንም ዘልቋል፤ አሁን የተናገርኩ ባለሁበት ሰዓት ቀሪ ጉዳዮችን ለመፍታት ጥረቶች እየተደረጉ ነው” ሲሉ ለካቢኔያቸው መናገራቸውን የዜና ወኪሊ አጃንስ ፍራንስ ፕረስ (ኤኤፍፒ) ዘግቧል።ያጋሩ, የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጦርነቱን ለማስቆም አሁንም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናገሩ
  14. 13 ሚያዚያ 2026ትራምፕ ወደ አሜሪካ እገዳ የሚጠጉ የኢራን መርከቦች ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው አስጠነቀቁፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Reutersፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመዝጋት ያስቀመጡት የጊዜ ገደብ መድረሱን ተከትሎ፤ የአሜሪካ ባሕር ኃይል ወደ ጣለውን እገዳ የሚጠጉ የኢራን “የጥቃት መርከቦች ይወገዳሉ” ሲሉ አስጠነቀቁ።ፕሬዝዳንቱ በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ እስካሁን ኢራን ላይ ጥቃት በሚፈጸምበት ወቅት “ፈጣን አጥቂ” ሲሉ የጠሯቸው የኢራን መርከቦች በአሜሪካ አለመመታታቸውን ገልጸዋል።“የኢራን ባሕር ኃይል የባሕሩ ወለል ላይ ተኝቷል፤ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል፤ 158 መርከቦች ወድመዋል” ሲሉ ጽፈዋል።“ያልመታናቸው ‘ፈጣን አጥቂ መርከቦች’ ብለው የሚጠሯቸውን ነው፤ ምክንያቱም እምብዛም ስጋት ናቸው ብለን አንቆጥራቸውም” ብለዋል።አክለውም፤ “ከእነዚህ መርከቦች የትኛውም ወደ ጣልነው እገዳ የሚመጣ ከሆነ፤ ባሕር ላይ በነበሩ የአደንዛዥ እፅ ሻጮች ጀልባዎች ላይ የተጠቀምነው የግድያ ስርዓት በመጠቀም ወዲያውኑ ይወገዳል” በማለት አስጠንቅቀዋል።የትራምፕ አስተዳደር ከመስከረም አንስቶ በካረቢያን ባሕር እና በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ በርካታ ገዳይ ጥቃቶችን ፈጽሟል። በእነዚህ ጥቃቶች አደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪ ናቸው የተባሉ 130 ሰዎች ተገድለዋል።ያጋሩ, ትራምፕ ወደ አሜሪካ እገዳ የሚጠጉ የኢራን መርከቦች ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው አስጠነቀቁ
  15. 13 ሚያዚያ 2026የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚን ጨምሮ ሦስት የጦር መርከቦች በኦማን ባሕረ ሰላጤ አቅራቢያ ታዩየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ኢራን ወደቦች የሚጓዙ እና ከወደቦቹ የሚወጡ መርከቦችን እንቅስቃሴ ለማገድ ያስቀመጡት የጊዜ ገደብ 11 ሰዓት ላይ ተጀምሯል።ቢቢሲ ቬሪፋይ የሳተላይት ምስሎችን በመጠቀም የፕሬዝዳንቱ እገዳ ምን ሊመስል እንደሚችል ለመረዳት ሲሞክር ቆይቷል።ቅዳሜ ዕለት የተነሱ ሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳዩት ግዙፉ የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ‘ዩኤስኤስ አብራሃም ሊንከን’ በኦማን ባሕረ ሰላጤ ምሥራቃዊ ጫፍ በኩል ይገኛል።ግዙፉ የጦር መርከብ ያለበት ርቀት ከኢራን የባሕር ዳርቻዎች ያለው ርቀት 200 ኪሎ ሜትር ገደማ ነው።የኢራን ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ይህ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ የታጠቀ መርከብ በዚህ ልክ ወደ ባሕረ ሰላጤው ቀርቦ ታይቶ አይታወቅም።በሳተላይት ምስሉ ላይ የሚታዩት በቅርብ ያሉ ሌሎች መርከቦች ያላቸው ቅርጽ እና ግዝፈት ከአሜሪካ ባሕር ኃይል የሚሳዔል አውዳሚ መርከቦች ጋር ተመሳሳይ ነው።እነዚህ መርከቦች ከአውሮፕላን ጫኙ ‘ዩኤስኤስ አብራሃም ሊንከን’ ጋር በአንድነት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ እንደሆኑ ይገመታል። ይሁን እንጂ ምስሉ ላይ የሚታዩት የትኛዎቹ መርከቦች እንደሆኑ በትክክል መለየት አልተቻለምየጦር መርከቦቹን የሚያሳይ የሳተላይት ምስልያጋሩ, የአሜሪካ አውሮፕላን ተሸካሚን ጨምሮ ሦስት የጦር መርከቦች በኦማን ባሕረ ሰላጤ አቅራቢያ ታዩ
  16. 13 ሚያዚያ 2026ትንታኔ፡ አሜሪካን የበለጠ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ የሚከትተው የሆርሙዝ ወሽመጥ እገዳበሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚጓዙ መርከብ እና ፈጣን ጀልባየፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረግ ጉዞን የማገድ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቷ በሕጋዊ፣ ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ከዚህ ቀደም ገብታበት የማታውቀው አደገኛ ቀጣና ውስጥ ያስገባታል ይላል የቢቢሲ የደኅንነት ጉዳዮች ዘጋቢው ፍራንክ ጋርድነር።እንደ ጋርድነር ትንተና፤ አሜሪካ እገዳውን ማስፈጸም ብትችልም የተወሰነ ስጋት ይጋረጥባታል።አሁን የአሜሪካ ባህር ኃይል ጦር መርከቦች እንቅስቃሴ እንደ ሴይ፣ ባንዳር አባስ እና ጃስክ ባሉ ወደቦች አቅራቢያ በማንዣበብ ብቻ አያበቃም። ይህ ደግሞ በድሮን፣ በሚሳዔል ወይም በአጥፍቶ ጠፊ ‘ካሚካዚ’ ፈጣን ጀልባዎች ለሚፈጸሙ ጥቃቶች እንዲጋለጡ ያደርጋል።የአሜሪካ ጦርን የመካከለኛው ምሥራቅ እንቅስቃሴን የሚሸፍነው ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም)፤ የትኛዎቹ መርከቦች የኢራን እንደሆኑ እና የትኛዎቹ ከኢራን ወደቦች እንደተነሱ ለማረጋገጥ የሳተላይት ምስል እና ሌሎች የስለላ መረጃዎችን ሊጠቀም ይችላል።መርከቦቹ፤ ጉዟቸውን ለመከታተል የሚያስችለውን የመለያ ስርዓት (AIS – automatic identification system) ቢያጠፉም እንኳ፤ ልክ የኦማን ባሕረ ሰላጤ ውስጥ እንደገቡ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱት የአሜሪካ ጦር መርከቦች መገኘታቸው እና መያዛቸው አይቀርም።ኢራን ይህንን የአሜሪካ ዛቻ የባሕር ላይ ውንብድና ስትል ጠርታዋለች። ቴህራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ስትዘጋ ተመሳሳይ አይነት ክስ ቀርቦባት ነበር።እስላማዊው ሪፐብሊክ በባሕረ ሰላጤው አገራት ወደቦች ላይ አጸፋ እርምጃ እንደሚወስድም አስጠንቅቋል።የኢራን አጋር የሆኑት ቻይና እና ሩሲያ ነገር ሌላኛው ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ ነው። በእርግጥ አሜሪካ ንብረትነቱ የቻይና የሆነ መርከብ ወይም ጭነት ላይ ወታደሮቿ እንዲወጡ ለማድረግ ወይም መርከቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ዝግጁ ነች?ብዙም ሳይርቅ ጅቡቲ ውስጥ ወታደራዊ ሠፈር ያላት ቻይና፤ መርከቦቿን በታጠቀ የባሕር ኃይሏ ለማጀብ ከወሰነችስ ምን ይፈጠራል?ያጋሩ, ትንታኔ፡ አሜሪካን የበለጠ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ የሚከትተው የሆርሙዝ ወሽመጥ እገዳ
  17. 13 ሚያዚያ 2026የአሜሪካ ጦር የሆርሙዝ እገዳን ጥሰው የሚጓዙ መርከቦች “እንደሚጠለፉ” አስጠነቀቀበሆርሙዝ ወሽመጥ የሚጓዝ መርከብየፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካ ጦር፤ በኦማን ባሕረ ሰላጤ እና ከሆርሙዝ ወሽመጥ በስተምሥራቅ በሚገኘው የአረቢያን ባሕር ላይ የተጣለውን እገዳ ለማስፈጸም መዘጋጀቱን እንዲሁም እርምጃው መርከቦች ያነገቡትን ባንዲራ ሳይለይ በሁሉም ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን ማስታወቁ ተዘገበ።የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ ይህንን ያለው ከአንድ ሰዓት በኋላ ተግባራዊ እንደሚሆን የሚጠበቀው ዕገዳ ከመጀመሩ አስቀድሞ ለባሕርተኞች በላከው መልዕክት እንደሆነ የዜና ወኪሉ ሮይተርስ ገልጿል።ሮይተርስ የተመለከተው የዕዙ ማስታወሻ፤ “ፈቃድ ሳያገኝ ዕገዳ ወደተጣለበት አካባቢ የሚገባ ወይም ከዚያ የሚወጣ ማንኛውም መርከብ ለጠለፋ፣ አቅጣጫ ማስቀየር እና በቁጥጥር ስር መዋል እርምጃዎች ይዳረጋል” ይላል።”እገዳው በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወይም ከ[ኢራን] ወዳልሆኑ መዳረሻዎች የሚደረጉ ገለልተኛ የትራንዚት ጉዞዎችን አያስቆምም” ሲልም ያብራራል።የኮንትሮባንድ ጭነት መኖር እና አለመኖሩን ለማረጋገጥ ሲባል ገለልተኛ መርከቦች ፍተሻ ሊደረግባቸው እንደሚችል ለባሕርተኞች የተላከው ማስታወሻ ገልጿል።እንደ ምግብ፣ የህክምና አቅርቦቶች እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች ያሉ ሰብአዊ ጭነቶች ፍተሻ ተደርጎባቸው ጉዞ እንዲያደርጉ እንደሚፈቀድላቸው መግለጹንም ዘገባው ያመለክታል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከዛሬው ዕለት ጀምሮ ይተገበራል ያሉት እገዳ ተፈጻሚ መሆን የሚጀምረው 11 ሰዓት ላይ ነው።የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ በላከው ማስታወሻ፤ እገዳው የኢራንን ወደቦች እና የነዳጅ ማደያ ተርሚናሎችን ጨምሮ መላው “የኢራን የባህር ዳርቻን” እንደሚያካትት አስታውቋል። ሆኖም እርምጃው የኢራንን ወደቦች እና የነዳጅ ማደያ ተርሚናሎች ላይ “ብቻ እንደማይወሰን” ገልጿል።ያጋሩ, የአሜሪካ ጦር የሆርሙዝ እገዳን ጥሰው የሚጓዙ መርከቦች “እንደሚጠለፉ” አስጠነቀቀ
  18. 13 ሚያዚያ 2026እስራኤል፤ አሜሪካ የሆርሙዝ ወሽመጥን መዝጋቷን እንደምትደግፍ አስታወቀችየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔትያናሁየፎቶው ባለመብት,Reutersየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔትያናሁ አሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ የባሕር ጉዞዎችን ማገዷን እንደሚደግፉ ተናገሩ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለካቢኔያቸው በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ፕሬዝዳንት ትራምፕ የባሕር ጉዟቸው ላይ እገዳ ለመጣል ወስነዋል። በእርግጥም ይህንን ጠንካራ አቋም እንደግፋለን” ብለዋል።አሜሪካ እና ኢራን ፓኪስታን ውስጥ ካደረጉት ውጤት አልባው ንግግር በኋላ እሁድ ዕለት ከምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ጋር መነጋገራቸውንም ገልጸዋል።ቫንስ “ዋነኛው ጉዳይ ሁሉንም የበለጸጉ [የኒውክሌር] ቁሶች ማስወገድ እና ምንም ተጨማሪ የማበልጸግ ተግባር እንደማይኖር ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ ነበር” ሲሉ እንደነገሯቸው በኔትያናሁ በቪዲዮ መልዕክታቸው አንስተዋል።እንደ ኔትያናሁ ገለጻ የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ከፓኪስታ የተመለሱበት አውሮፕላን ውስጥ ሆነው የደወሉላቸው ሲሆን ከኢራን ጋር የሚደረገው ንግግር ደረሰበትን ደረጃ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋቸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፤ አሜሪካ እና እስራኤል ያላቸው ግንኙነት በመካከላቸው መራራቅ እንዳለ ከሚጠቁሙ አስተያየቶች “ፍጹም ተቃራኒ” እንደሆነ ተናግረዋል።ያጋሩ, እስራኤል፤ አሜሪካ የሆርሙዝ ወሽመጥን መዝጋቷን እንደምትደግፍ አስታወቀች
  19. 13 ሚያዚያ 2026ፈረንሳይ እና ዩናይትድ ኪንግደም የሆርሙዝ ወሽመጥን የተመለከተ ኮንፈረንስ ሊያዘጋጁ ነውየዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር  እና የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንየፎቶው ባለመብት,Reutersየፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፤ አገራቸው እና ዩናይትድ ኪንግደም “በመጪዎቹ ቀናት” በሆርሙዝ “ወሽመጥ ላይ የመርከብ ጉዞ ነጻነት መመለስን የተመለከተ” ኮንፈረንስ እንደሚያዘጋጁ አስታወቁ።ይህ እርምጃ “የመከላከል ተልዕኮ ብቻ” እንደሆነ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ የገለጹት ማክሮን፤ “ከግጭቱ ተዋጊ ወገኖች የተነጠለ” እና “ሁኔታው እንደፈቀደ ተግባራዊ ሊደረግ የታቀደ” መሆኑንም አስረድተዋል።የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመርም በተመሳሳይ ሁለቱ አገራት በጋራ የሚያስተናግዱት ጉባኤ “ግጭቱ ሲያበቃ ዓለም አቀፍ የመርከብ ጉዞን ደኅንነት ለማስጠበቅ የተቀናጀ፣ ገለልተኛ፣ ዓለም አቀፍ እቅድ ለማዘጋጀት” ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል።አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ወይም ከኢራን ወደቦች የሚደረጉ ጉዞዎችን እንደምትዘጋ መግለጿን ተከትሎ በባሕረ ሰላጤው ውጥረቱ አይሏል።ዩናይትድ ኪንግደም አሜሪካ ልትወስድ ያቀደችውን እርምጃ እንደማትደግፍ አስታውቃለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስታርመር “የኢነርጂ ዋጋ በተቻለ ፍጥነት እንዲቀንስ የምናደርግበት መንገድ ይህ ነው” ሲሉ የሚደግፉት የሆርሙዝ ወሽመጥ መከፈትን እንደሆነ ገልጸዋል።ዩናይትድ ኪንግደም ከዚህ ቀደም በወሽመጡ ላይ የጉዞ ነጻነት እንዲረጋገጥ የማድረግ ግብ ያላቸው ከ40 በላይ አገራት ወኪሎችን ሰብስባ እንደነበር ይታወሳል።ያጋሩ, ፈረንሳይ እና ዩናይትድ ኪንግደም የሆርሙዝ ወሽመጥን የተመለከተ ኮንፈረንስ ሊያዘጋጁ ነው
  20. 13 ሚያዚያ 2026ፖፕ ሊዮ የትራምፕ አስተዳደርን “አልፈራም” ሲሉ ከፕሬዝዳንቱ ለቀረበባቸው ከባድ ትችት ምላሽ ሰጡየካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛየፎቶው ባለመብት,Reutersየካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፤ የትራምፕ አስተዳደርን “እንደማይፈሩ” እንዲሁም የኢራን ጦርነትን በተመለከተ በያዙት አቋም ምክንያት ከፕሬዝዳንቱ ያልተለመደ ጥቃት ቢሰነዘርባቸውም ግጭቱን መቃወም እንደሚቀጥሉ ተናገሩ።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው በለጠፉት ጽሑፍ፤ “ወንጀል ላይ ደካማ፣ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ የከፋ” ሲሉ ፖፕ ሊዮን ወቅሰዋል። ቆይተው ደግሞ “አድናቂው አይደለሁም” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።ወደ አልጄሪያ እየተጓዙ የነበሩት ፖፕ ሊዮ በበኩላቸው ከትራምፕ ጋር ክርክር ውስጥ መግባት እንደማይፈልጉ፤ ነገር ግን ስለ ሰላም መናገራቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የኢራን ጦርነት ላይ ብርቱ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። ትራምፕ የኢራንን ሥልጣኔ እንደሚያወድሙ በተናገሩ ጊዜም ዛቻውን “ተቀባይነት የሌለው” በማለት ተችተዋል። ትራምፕ ጦርነቱን ለመቋጨት ሰላማዊ መንገድ እንዲፈልጉም መክረዋል።የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከዓለም መሪዎች ለሚሰጡ አስተያየቶች ቀጥታ ምላሽ መስጠታቸው የተለመደ አይደለም።ፖፕ ሊዮ አካሄዳቸውን እንዲያስተካክሉ የሚገልጽ ጽሑፍ እሁድ ዕለት ማኀበራዊ ሚዲያ ላይ የለጠፉት ትራምፕ፤ “ኒውክሌር መሣሪያ ላይ ደካማ” ነበር ሲሉ አሜሪካ ከኢራን ጋር ጦርነት ያስገባትን ‘ቴህራን የኒውክሌር መሣሪያ ልትገነባ ነው’ የሚል ክስ ጠቅሰዋል።ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪ ሆነው የተመረጡት “አሜሪካዊ ስለሆነ ነው፤ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ ትራምፕ ጋር በተያያዘ መፍትሔ ማግኛው ጥሩ መንገድ ይሄ ነው ብለው አስበው ነበር” ሲሉም ጽፈዋል።ወደ አልጄሪያ በሚጓዙበት አውሮፕላን ውስጥ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ለትራምፕ አስተያየት ምላሽ የሰጡት ፖፕ ሊዮ፤ ራሳቸውን ፖለቲካ ውስጥ ሚና እንዳለው ሰው እንደማይመለከቱ፤ ይልቁንም የሰላም መልዕክትን እንደሚያስተላልፉ ተናግረዋል።“የትራምፕ አስተዳደርን ወይም የወንጌል መልዕክትን ከፍ ባለ ድምጽ መናገርን አልፈራም፤ እዚህ ያለሁትም ይህንን ለማድረግ እንደሆነ ነው የማምነው፤ ቤተ ክርስቲያኗም ለዚሁ ነው ያለችው” ብለዋል።“ዛሬ በዓለም ላይ እጅግ በርካታ ሰዎች እየተሰቃዩ ነው። እጅግ ብዙ ንጹኃን ሰዎች እየተገደሉ ነው። የሆነ ሰው መነሳት እና ‘ይህንን ለማድረግ የተሻለ መንገድ አለ’ ብሎ መናገር አለበት” ሲሉ አቋማቸውን አሳውቀዋል።ያጋሩ, ፖፕ ሊዮ የትራምፕ አስተዳደርን “አልፈራም” ሲሉ ከፕሬዝዳንቱ ለቀረበባቸው ከባድ ትችት ምላሽ ሰጡ