የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የጀመሩት ድርድር በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በፓኪስታን እንደሚቀጥል ተናገሩ። ምክትላቸው ጄዲ ቫንስ በበኩላቸው አሜሪካ ከኢራን ጋር “ትልቅ ስምምነት” ማድረግ ትፈልጋለች ብለዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 1 ሰአት በፊትየፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ከአሜሪካ እና ኢራን የኢዝላማባድ ንግግር በኋላ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኳታር እና ቱርክን ለመጎብኘት አቀኑምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ  እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሻሪፍየፎቶው ባለመብት,Reuterየምስሉ መግለጫ,የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በኢራን ጉዳይ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ሻሪፍን አነጋግረዋልየፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሻባዝ ሻሪፍ የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትን እና ቱርክን ለመጎብኘት የአራት ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት መጀመራቸውን የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳዑዲ አረቢያ እና ኳታርን እንደሚጎበኙም ተገልጿል።ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የመጣው ኢዝላማባድ ሁለተኛ ዙር የአሜሪካ እና ኢራንን የሰላም ንግግር ለማዘጋጀት እየተሰናዳች ባለችበት ጊዜ ነው።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት ለኒው ዮርክ ፖስት ጋዜጠኛ “በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ በኢዝላማባድ የሆነ ነገር ይከሰት ይሆናል” ብለዋል።የጠቅላይ ሚኒስትር ሻቲፍ የሳዑዲ አረቢያ እና ኳታር ጉብኝት “በሁለትዮሽ አውድ” እንደሚካሄድ የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቱርክ በአንታላያ የዲፕሎማሲ ፎረም የሚሳተፉ ሲሆን፤ ከፎረሙ ጎን ለጎን ከቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲጵ ጣይፕ ኤርዶጋን እና ከሌሎች መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።ያጋሩ, የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ከአሜሪካ እና ኢራን የኢዝላማባድ ንግግር በኋላ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኳታር እና ቱርክን ለመጎብኘት አቀኑ
  2. ከ 1 ሰአት በፊትትራምፕ የካቶሊኩ ርዕሳነ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ሊዮ ላይ የሚሰነዝሩትን ትችት ቀጥለዋልፖፕ ሊዮ 14ተኛ እና ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Reutersፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በካቶሊክ ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳስ ፖፕ ሊዮ 14ተኛ ላይ በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ የትትስር ገፅ ‘ኢራን 42 ሺህ ንፁሃንን እንደገደለች እባካችሁ ንገሯቸው’ በማለት ሰሞነኛ ትችታቸውን ቀጠሉ።“እባካችሁ አንድ ሠው ለፖፕ ሊዮ ኢራን ባለፉት ሁለት ወራት 42 ሺህ ምንም ያልታጠቁ፣ ተቃዋሚ፣ ንፁኃንን ገድላለች፤ ኢራን የኒውክሌር ቦምብ ባለቤት መሆኗ በፍፁም ተቀባይነት የለውም ብላችሁ ንገሯቸው” ብለዋል።“ለጉዳዩ ትኩረት ስለሰጡት እናመሰግናለን። አሜሪካ ተመልሳለች” ሲሉም የትችት ጽሑፋቸውን አሳርገዋል።ፖፕ ሊዮ ስለ ኢራን ጦርነት አስተያየት ከሰጡ በኋላ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለጋዜጠኞች የርዕሳነ ሊቀ ጳጳሱ “አድናቂ” እንዳልሆኑ በመግለፅ፤ “ወንጀል ላይ ደካማ እና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የማይችሉ” ሲሉ ተችተዋቸዋል።ፖፕ ሊዮ በበኩላቸው የትራምፕ አስተዳደር ላይ “ፍርሃት” እንደሌላቸው እና ለመናገር ወደ ኋላ እንደማይሉ ገልፀዋል።ትራምፕ ቱሩዝ ሶሾል በተባለው ማኅበራዊ የትስስር ገፃው ላይ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) በሚመለከት ጽሑፍ ያጋሩ ሲሆን፤ “ኔቶ [እርዳታ በጠየቅን ጊዜ] ከእኛ ጋር አልነበረም፤ እናም በቀጣይም ከእኛ ጋር አይሆኑም” ብለዋል።ያጋሩ, ትራምፕ የካቶሊኩ ርዕሳነ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ሊዮ ላይ የሚሰነዝሩትን ትችት ቀጥለዋል
  3. ከ 1 ሰአት በፊትከእስራኤል እና ሊባኖስ የዋሽንግተን ንግግር በኋላ እስራኤል ሄዝቦላህን ማጥቃቷን ቀጠለችበሊባኖስ የወደሙ ሕንፃዎችየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በደቡባዊ ሊባኖስ እስራኤል ማክሰኞ ዕለት በፈፀመችው ጥቃት ሕንፃዎች ወድመዋልእስራኤል እና ሊባኖስ ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ካደረጉ ከአንድ ቀን በኋላ የእስራኤል ጦር ሊባኖስን ማጥቃቱን ቀጠለ።እስራኤል በንግግሩ ያልታሳተፈውን ሄዝቦላህን በመጠቆም መንግሥታዊ ያልሆኑ የሽብር ቡድኖችን ትጥቅ ማስፈታት እንደምትፈልግ ገልፃለች።የእስራኤል መከላከያ ኃይል (አይዲኤፍ) ባለፉት ጥቂት ቀናት ሄዝቦላህ የሽብር እና ወታደራዊ መሠረተ ልማቶችን መምታቱን አስታውቋል። ጦሩ “በሄዝቦላህ የሽብር ቡድን ላይ ጥቃት መፈፀም እንቀጥላለን” ብሏል።ትናንት ረቡዕ በዋሽንግተን የተደረገውን የእስራኤል-ሊባኖስ ንግግርን በማስመልከት አሜሪካ ባወጣችው መግለጫ አገራቱን ለታሪካዊ ምዕራፍ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት በቀጣይ ንግግሮች እንዲደረጉ ድጋፏን እንደምትቀጥል ገልፃለች።“የሊባኖስ መንግሥት የኃይሉን ብቸኝነት ለመመለስ ለያዘው ዕቅድ እና የኢራንን ከመጠን ያለፈ ተፅዕኖ ለመቋጨት” ዋሽንግተን ድጋፍ እንደምታደርግም ጠቅሳለች።ያጋሩ, ከእስራኤል እና ሊባኖስ የዋሽንግተን ንግግር በኋላ እስራኤል ሄዝቦላህን ማጥቃቷን ቀጠለች
  4. ከ 2 ሰአት በፊትአሜሪካ የኢራን ወደቦችን በዘጋች በቀናት ውስጥ በሁለቱ አገራት መካከል ሁለተኛ ዙር ንግግር በቅርቡ ሊካሄድ ነውባሕር ላይ ያለ መርከብየፎቶው ባለመብት,Reutersበመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት የተከሰቱ አዲስ ሁነቶች፡
    • የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የገቡትን ጦርነቱን ለማስቆም የሚደረው ንግግር በዚህ ሳምንት ሊጀምር እንደሚችል ጠቁመዋል።
    • የኢራን መገናኛ ብዙኃን ኢርና ግን ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ስለውይይቱ “ምንም መረጃ” እንደሌለ ዘግቧል። ሆኖም የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ንግግሮች ዳግም ሊጀመሩ የሚችሉበት ከፍተኛ ዕድል እንዳለ ተናግረዋል።
    • በአሜሪካ የሊባኖስ አምባሳደር በአገራቸው እና በእስራኤል መካከል በዋሽንግተን የተደረገውን የመጀመሪያ ንግግር “ፍሬያማ” ብለውታል። በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ደግሞ ንግግሩ ሦስቱ አገራት “ተመሳሳይ ገፅ ላይ መሆናቸውን” ያሳየ ነው ብለዋል።
    • አሜሪካ ኢራን ወደቦች ላይ የጣለችው የእንቅስቃሴ እግድ ተግባራዊነቱ የቀጠለ ሲሆን፤ አሜሪካ የኢራን ነዳጅ ላይ ሙሉ ማዕቀብ እንደምትጥል አስታውቃለች። እርምጃው አሜሪካ እና ኢራን በፓኪስታን ያደረጉት የሰላም ድርድር ያለ ውጤት በመጠናቀቁ የተወሰደ ነው።
    • አሜሪካ በመጀመሪያዎቹ 24 ሰዓታት ውስጥ ከኢራን ወደቦች እና የባሕር ዳርቻዎች ምንም ዓይነት መርከቦች እንዳላለፉ ገልፃለች። በቢቢሲ የተረጋገጠው የመርከቦች መረጃ እግዱ ከጀመረ በኋላ ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው አራት መርከቦች የሆርሙዝ ወሽመጥን ማለፋቸውን አሳይቷል።
    • የአሜሪካ እግድ በሚቀጥለው ሳምንት የሚያበቃው የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት በታወጀበት ወቅት የተጣለ ነው። ኢራን የካቲት 21/2018 ዓ.ም. ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ሆርሙዝ ወሽመጥን ዘግታለች።
    ያጋሩ, አሜሪካ የኢራን ወደቦችን በዘጋች በቀናት ውስጥ በሁለቱ አገራት መካከል ሁለተኛ ዙር ንግግር በቅርቡ ሊካሄድ ነው
  5. ከ 3 ሰአት በፊትየአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ‘ትልቅ ስምምነት’ ማድረግ እንደሚፈልጉ ተናገሩየአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስየፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ፣ ትራምፕ ከኢራን ጋር “ትልቅ ስምምነት” ማድረግ እንደሚፈልጉ መናገራቸውን የቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ ኒውስ ዘግቧል።ቫንስ በአቴንስ፣ ጆርጂያ በተካሄደው የተርኒንግ ፖይንት ዩኤስኤ ዝግጅት ላይ ለታዳሚዎቹ እንደተናገሩት በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በፓኪስታን የተካሄደው ድርድር “እጅግ በጣም ብዙ እድገት አሳይቷል” ብለዋል።ነገር ግን ትራምፕ ከኢራን ጋር “ትንሽ ስምምነት” እንደማይፈልጉ እና በምትኩ “ትራምፕ ታላቅ ስምምነት” ለማድረግ እንደሚፈልጉ ሲቢኤስ ዘግቧል።ቫንስ በሁለቱ አገሮች መካከል ከፍተኛ አለመተማመን እንደነበር ተናግረዋል።አክለውም “ያንን ችግር በአንድ ጀምበር መፍታት አትችሉም” ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።ያጋሩ, የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ‘ትልቅ ስምምነት’ ማድረግ እንደሚፈልጉ ተናገሩ
  6. ከ 3 ሰአት በፊትትራምፕ የኢራን ጦርነት “ሊያበቃ ተቃርቧል” አሉየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የጀመሩት ጦርነት “ሊያበቃ ተቃርቧል” ሲሉ ለፎክስ ኒውስ ተናገሩ።ትራምፕ ለፎክስ ኒውስ የሰጡት ቃለ ምልልስ የሚተላለፈው 7፡00 ላይ ቢሆንም በማስታወቂያው ላይ ግን ጦርነቱ “ሊያበቃ የተቃረበ ይመስለኛል” ሲሉ ተደምጠዋል።ትራምፕ ይህንን ያሉት በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ከኢራን ጋር ኢዝላማባድ ተገናኝተው የተጀመረውን ውይይት እንደሚቀጥሉ ከተናገሩ በኋላ ነው።ፎክስ ኒውስ ኦንላይን በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ በለቀቀው የቃለ ምልልሱ ማስታወቂያ ላይ ትራምፕን ጦርነቱ አብቅቶ እንደሆነ ጠይቋቸዋል።“ሊያበቃ የተቃረበ ይመስለኛል። አዎ” ሲሉ መልሰዋል። “እኔ እንደማየው በጣም ሊያበቃ መቃረቡን ነው” ብለዋል።ያጋሩ, ትራምፕ የኢራን ጦርነት “ሊያበቃ ተቃርቧል” አሉ
  7. 14 ሚያዚያ 2026ትራምፕ አሜሪካ እና ኢራን “በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ” ሊወያዩ እንደሚችሉ ተናገሩዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,EPAዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል “በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ” ንግግር ሊጀመር እንደሚችል ለኒውዮርክ ፖስት ተናገሩ።“በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ የሆነ ነገር ሊከሰት ይችላል። እና እኛ የበለጠ ወደዚያ [ፓኪስታን] የመሄድ ዝንባሌ አለን” ማለታቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።ሁለቱ አገራት የተኩስ አቁም ከደረሱ በኋላ በፓኪስታን ተገናኝተው ለረዥም ሰዓት የተወያዩት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ነበር።በወቅቱ የአሜሪካን ልዑክ የመሩት ምክትል ፕሬዜዳንቱ ጄዲ ቫንስ ሲሆኑ የኢራን ልዑክ ደግሞ የተመራው በአፈ ጉባዔ ሞሐመድ ባገር ጋሊባፍ ነበር።ነገር ግን ውይይቱ ያለምንም ስምምነት ተቋጭቷል።ዛሬ የኢራን መገናኛ ብዙኃን በፓኪስታን እና ቴህራን መካከል የመልዕክተት ልውውጥ መኖሩን ዘግበው ከአሜሪካ ጋር ቀጣይ ውይይት ለማድረግ ስምምነት ስለመደረሱ ግን “ምንም መረጃ የለም” ብለው ነበር።ያጋሩ, ትራምፕ አሜሪካ እና ኢራን “በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ” ሊወያዩ እንደሚችሉ ተናገሩ
  8. 14 ሚያዚያ 2026የሊባኖስ ፕሬዚዳንት ውይይቱ “የመጨረሻው መጀመሪያ” ይሆናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናገሩየሊባኖስ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ አውንየፎቶው ባለመብት,Reutersየሊባኖስ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ አውን አገራቸው ከእስራኤል ጋር የምታደርገው ውይይት የስቃይዋ “የመጨረሻው መጀመሪያ” ይሆናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናገሩ።እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ “ወረራዋን በመቀጠሏ” መረጋጋት “እንደማይመለስ” ጨምረው ተናግረዋል።የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሊባኖስ የደህንነት ቀጠና ለመገንባት በሚል ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደ ነው።ጦርነቱ ካበቃም በኋላ የእስራኤል ጦር መሬቱን በወረራ ይዞ ሊቀጥል ይችላል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ ተፈጥሯል።ከአስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ የእስራኤል እና ሊባኖስ አምባሳደሮች በአሜሪካ ተገናኝተው ውይይታቸውን ጀምረዋል።ሁለቱ አገራት ምንም ዓይነት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የላቸውም።ይህ ውይይት እስራኤል የሄዝቦላህ ወታደራዊ ይዞታዎች ናቸው በሚል የምትፈጽመውን ድብደባ ያስቆማል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።እስራኤል፣ አሜሪካ እና በርካታ ሊባኖሳውያን ሄዝቦላህ ትጥቅ እንዲፈታ ይፈልጋሉ። ነገር ግን በቤይሩት የሚገኘው መንግሥት ይህንን ያለ ሄዝቦላህ ይሁንታ ማስፈጸም አይችልም።ነገር ግን የእስራኤል ጥቃትም ቢሆን ግጭቱን ከማባባስ ባሻገር ዘላቂ መፍትሄ ስለማምጣቱ ማንም እርግጠኛ አይደለም።የሄዝቦላህ ደጋፊዎች የታጠቃቸው የጦር መሣሪያዎች ራሱን ከእስራኤል ጥቃት የሚከላከልበት ነው የሚሉ ሲሆን ቡድኑም ቢሆን በየትኛወም ውሳኔ እንደማይገዛ አስታውቋል።ያጋሩ, የሊባኖስ ፕሬዚዳንት ውይይቱ “የመጨረሻው መጀመሪያ” ይሆናል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናገሩ
  9. 14 ሚያዚያ 2026የእስራኤል እና ሊባኖስ ልዑካን ቡድኖች በዋሺንግተን ዲሲ ውይይታቸውን ጀመሩየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ (መካከል) የውጪ ጉዳይ  አማካሪ ሚካኤል ኒድሃም (በስተግራ) እና በሊባኖስ የአሜሪካ አምባሳደር ሚሼል ኢሳ (በስተቀኝ)የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ (መካከል) የውጪ ጉዳይ አማካሪ ሚካኤል ኒድሃም (በስተግራ) እና በሊባኖስ የአሜሪካ አምባሳደር ሚሼል ኢሳ (በስተቀኝ)የእስራኤል እና ሊባኖስ ልዑካን ቡድን ከአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በመሆን በዝግ ውይይታቸውን ጀምረዋል።እስራኤል እና ሊባኖስ ፊት ለፊት ተገናንተው ውይይት ሲያደርጉ ይህ ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።ከአሜሪካ ወገን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ ጋር በሊባኖስ የአሜሪካ አምባሳደር ሚሼል ኢሳ እንዲሁም በመንግሥታቱ ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ዋልዝ ተገኝተዋል።በአሜሪካ የሊባኖስ አምባሳደር ናዳ ሃምዴህ እና የእስራኤሉ አምባሳደር ይቼል ሌይተር አገራቸውን በመወከል በውይይቱ ላይ እየተሳተፉ ነው።የሁለቱ አገራት ውይይት ከመጀመሩ በፊት ማርኮ ሩቢዮ ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ሲሉ ተናግረዋል።ሩቢዮ አክለውም ውይይቱ ከተኩስ አቁም “በላይ ነው” በማለት የሄዝቦላህ ተጽዕኖ “በቋሚነት እንዲያበቃ የሚያደርግ” ነው ብለውታል።አክለውም ለአስርት ዓመታት በቀጠለ ውስብሰብ ሁኔታ ውስጥ እየሰሩ መሆናቸውን እንደሚረዱ ገልጸው ቀጥሎ በሚደረገው ረዥም ውይይት አይፈታም ብለዋል።ነገር ግን ቋሚ እና ዘላቂ የሆነ ሰላም ለማምጣት የሚያስችል ማዕቀፍ ለመንደፍ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።የሁለቱ አገራት ውይይት በእስራኤል እና ሄዝቦላህ መካከል ለወራት ከተካሄደው ውጊያ በኋላ የሚደረግ ሲሆን ጦርነቱን ሊያስቆም እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ሄዝቦላህ የኢራን ጦርነት ከተከፈተ ከሳምንታት በኋላ በሰሜናዊ እስራኤል የሮኬት እና የድሮን ጥቃት በመፈፀም ጦርነቱን ተቀላቅሏል።እስራኤልም የቡድኑን ወታደራዊ አቅም ለማዳከም የአየር ጥቃት እና የምድር ላይ ዘመቻ በመጀመሯ ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።ያጋሩ, የእስራኤል እና ሊባኖስ ልዑካን ቡድኖች በዋሺንግተን ዲሲ ውይይታቸውን ጀመሩ
  10. 14 ሚያዚያ 2026አሜሪካ በመጀመሪያዎቹ 24 ሰዓታት ውስጥ ምንም ዓይነት መርከብ እገዳውን እንዳላለፈ ገለጸችነዳጅ ጫኝ መርከብየፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ በመጀመሪያዎቹ 24 ሰዓታት ውስጥ ከኢራን ወደቦችና የባህር ዳርቻ አካባቢዎች የተጣለውን እገዳ አልፎ ምንም ዓይነት መርከብ አለማለፉን ገለጸች።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንቲኮም) ከ10,000 በላይ ወታደሮች፣ በርካታ የጦር መርከቦችና አውሮፕላኖች እገዳውን ለማስፈጸም መሰማራታቸውን ገልጿል።ስድስት የንግድ መርከቦች “ከአሜሪካ ኃይሎች የተሰጠውን መመሪያ ተቀብለው” ወደ ኢራን ወደብ “እንዲመለሱ” ማድረጉን ጨምሮ አስታውቋል።ቢቢሲ የክትትል መረጃዎችን በመመልከት አራት ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው መርከቦች እገዳው ከተጀመረ በኋላ የሆርሙዝ ባሕረ ወሽመጥን አቋርጠው መሄዳቸውን አረጋግጧል።ሴንቲኮም እገዳው ወደ ኢራን ወደቦች በሚገቡ ወይም በሚወጡ በሁሉም አገር መርከቦች ላይ እየተተገበረ መሆኑን ገልጿል።አክሎም ወደ ኢራን የማይሄዱ ወይም ከዚያ የማይመጡ መርከቦች “የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ መደገፉችንን” እንቀጥላለን ብሏል።ያጋሩ, አሜሪካ በመጀመሪያዎቹ 24 ሰዓታት ውስጥ ምንም ዓይነት መርከብ እገዳውን እንዳላለፈ ገለጸች
  11. 14 ሚያዚያ 2026እስራኤል እና ሊባኖስ ለድርድር እየተዘጋጁ ባለበት ወቅት ውጊያ መቀጠሉ ተሰማእስራኤል እና ሊባኖስ በአሜሪካ ለመነጋገር እየተዘጋጁ ባለበት በአሁኑ ወቅት በእስራኤል ጦር እና በሄዝቦላህ መካከል ውጊያ እየተካሄደ ነው።የእስራኤል ጦር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ በደቡብ ሊባኖስ “የሄዝቦላህ የሽብር ድርጅት ዒላማዎች” ያላቸውን 150 ስፍራዎች መደብደቡን አስታውቋል።ሄዝቦላህ በበኩሉ ወደ እስራኤል ሮኬት ማስወንጨፉን በመግለጽ መግለጫ አውጥቷል።እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ የፈጸመችው ጥቃት የሚያሳዩ ምስሎች እነሆ፦በቅላሊሌህ ታየር ከተማ የእስራኤል ጥቃት ከተፈፀመ በኋላየፎቶው ባለመብት,Reutersናባቲህ ላይ ድብደባ ከተፈጸመ በኋላ ጭስ ታይቷልየፎቶው ባለመብት,Anadolu via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በሊባኖስ ናባቲህ ላይ ድብደባ ተፈጽሟልበሊባኖስ ታየር የአየር ድብደባ ሲፈጸም የዓሣ አጥማጆች ጀልባቸውን ሲቀዝፉ ይታያሉየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በሊባኖስ ታየር የአየር ድብደባ ሲፈጸም የዓሣ አጥማጆች ጀልባቸውን ሲቀዝፉ ይታያሉያጋሩ, እስራኤል እና ሊባኖስ ለድርድር እየተዘጋጁ ባለበት ወቅት ውጊያ መቀጠሉ ተሰማ
  12. 14 ሚያዚያ 2026ትራምፕ የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር “ድፍረት” ይጎላታል በማለት ተቹየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በኢራን ጦርነት ላይ “ድፈረት” ይጎላቸዋል አሉ።“በእሷ በጣም ደንግጫለሁ። ድፍረት ያላት መስሎኝ ነበር። ነገር ግን ተሳስቻለሁ” ሲሉ ለጣሊያኑ ጋዜጣ ኮሬሬ ዴላ ሴራ ተናግረዋል።አክለውም ሜሎኒ “አሜሪካ እርሷን በመወከል ስራዎችን እንድትሰራ ታስባለች” ብለዋል።ፕሬዚዳንቱ ጠቅላይ ሚኒስትሯን የተቹት ሜሎኒ ትራምፕ የካቶሊኩ ጳጳስ ላይ የሰነዘሩትን ትችት “ተቀባይነት የለውም” ካሉ በኋላ ነው።ትራምፕ “እርሷ ናት ተቀባይነት የሌላት፤ ምክንያቱም ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ቢኖራት እና ጣሊያንን እድሉን አግኝታ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ብታጠፋት ግድ አይሰጣትም” ብለዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው በለጠፉት ጽሑፍ፤ “ወንጀል ላይ ደካማ፣ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ የከፋ” ሲሉ ፖፕ ሊዮን ወቅሰዋል። ቆይተው ደግሞ “አድናቂው አይደለሁም” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፤ የትራምፕ አስተዳደርን “እንደማይፈሩ” እንዲሁም የኢራን ጦርነትን በተመለከተ በያዙት አቋም ምክንያት ከፕሬዝዳንቱ ያልተለመደ ጥቃት ቢሰነዘርባቸውም ግጭቱን መቃወም እንደሚቀጥሉ መናገራቸው ይታወሳል።ያጋሩ, ትራምፕ የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር “ድፍረት” ይጎላታል በማለት ተቹ
  13. 14 ሚያዚያ 2026ትንታኔ፡ ቻይና የአሜሪካን እገዳ ብትኮንንም ትራምፕን ግን ከዚህ በላይ መግፋት አትፈልግምየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቻይናው ዢ ጂንፒንግ እአአ በጥቅምት 2025 በተካሄደው የእስያ-ፓሲፊክ ኢኮኖሚ ትብብር ጉባኤ ላይ በተገናኙበት ወቅትየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቻይናው ዢ ጂንፒንግ እአአ በጥቅምት 2025 በተካሄደው የእስያ-ፓሲፊክ ኢኮኖሚ ትብብር ጉባኤ ላይ በተገናኙበት ወቅትየቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሜሪካ የኢራንን ወደቦች መዝጋቷን “አደገኛ እና ኃላፊነት የጎደለው” በማለት ኮንኗል።ይህ አስተያየቷ የተሰማው በየቀኑ የተኩስ አቁም እንዲደረግ በመወትወት በፓኪስታን የሚደረገውን የሰላም ንግግር ድጋፍ እያደረገች ባለበት ወቅት ነው።ቢቢሲ የቻይና ባለሥልጣናት ኢራን ዳግም ወደ ድርድር ጠረጴዛው እንድትመለስ እየጎተጎቱ መሆኑን መረዳት ችሏል።የኢራንን 80 በመቶ ነዳጅ የሚገዛው የቻይና መንግሥት ከኢራን ጋር ለአስርት ዓመታት የዘለቀ ወዳጅነት አለው።ነገር ግን ቻይና ከቴህራን ጋር ያላት ወዳጅነት በንግድ ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው።ቤይጂንግ ለቴህራን የንግድ ስምምነቶችን እንጂ ወታደራዊ ድጋፍ አታቀርብም። ከኢራን ጋርም ምንም ዓይነት ወታደራዊ ስምምነት የላትም።ቻይና በኢራን ጦርነት ወቅት ሁለቱም ተፋላሚ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በመጠየቅ የገለልተኝነት ሚና ይዛ መቆየት መርጣለች።የቤይጂንግ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዋሺንግተንን እርምጃ ሊኮንን ቢችልም ዶናልድ ትራምፕን ግን ከዚህ በላይ መግፋት አይፈልግም።ቻይና የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት በሚቀጥለው ወር ለመቀበል ሽር ጉድ እያለች ነው። በዚህ የዶናልድ ትራምፕ ጉብኝት ወቅት የተጣሉባትን ታሪፎች ለማስነሳት ትደራደራለች።ከዚህ በተጨማሪ ቤይጂንግ ለረዥም ዓመታት በሌሎች አገራት ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት ፖሊሲን ስትከተል ቆይታለች። በዚህ ጦርነት ውስጥ መዘፈቅም አትፈልግም።ቻይና በፖለቲካው እና ወታደራዊ መስክ ያላት ኃያልነት ቢሆንም ገደቦች አሉበት።ስለዚህ ቤይጂንግ ነፍጥ ካነገቡት ፊት ከመሆን ይልቅ ከጎን ሆና ቀውሱን ለማረገብ መስራት ትመርጣለች።ያጋሩ, ትንታኔ፡ ቻይና የአሜሪካን እገዳ ብትኮንንም ትራምፕን ግን ከዚህ በላይ መግፋት አትፈልግም
  14. 14 ሚያዚያ 2026አሜሪካ የኢራን ወደቦችን ለመዝጋት ምን ልትጠቀም ትችላለች?ዩኤስኤስ አብርሃም ሊንከን በአሁኑ ወቅት በሆርሙዝ ባህር ዳርቻ ከሚገኙት 14 የአሜሪካ የባሕር ኃይል መርከቦች አንዷ ናትየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ዩኤስኤስ አብርሃም ሊንከን በአሁኑ ወቅት በሆርሙዝ ባህር ዳርቻ ከሚገኙት 14 የአሜሪካ የባሕር ኃይል መርከቦች አንዷ ናትአሜሪካ የኢራንን ወደቦች ዘግታ ስለምታቆይበት መንገድ የሚገልጹ ዝርዝር መረጃዎች እምበዛም አይገኝም። ቢቢሲ ቬሪፋይ ግን በዚህ ዘመቻ ወቅት ምን ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ለመመልከት ሞክሯል።ቢያንስ 14 የአሜሪካ ጦር መርከቦች በባሕረ ሰላጤው እና በአረብ ባሕር ላይ መሰማራታቸውን የአሜሪካ ባሕር ኃይል ኢንስቲትዮት መረጃ ያሳያል።እነዚህ የጦር መርከቦች ዩኤስኤስ አብርሃም ሊንከን አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብን እንዲሁም 2500 ባሕረኞችን እና ቀዛፊዎችን የያዙ ጥቃት ፈጻሚዎችን ያካትታሉ።በከፊል ሰርጓጅ የሆኑ መርከቦች በቀጣናው ሊሰማሩ የሚችሉ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ይፋ የሆኑ መረጃዎች ግን የሉም።የኢራን ወደቦችን ዘግቶ ለማቆት የጦር አውሮፕላኖች ጥቅም ላይ ይውላሉ። ነገረ ግን የተሰማሩት አውሮፕላኖችን ዓይነት እና የሄዱባቸውን መንገዶች ለማወቅ የሚያስችል የክትትል መረጃ ይፋ አይደለም።ሌሎች በቀጣናው ተሰማርተዋል ወይንም በአቅራቢያው ናቸው የተባሉ የጦር መርከቦችም አሉ።እነዚህም ወደቦቹን ለመዝጋት ድጋፍ እንዲሰጡ ጥሪ ሊደረግላቸው ይችላል።አውሮፕላን ተሸካሚ የሆነችው ዩኤስኤስ ጄራልድ ኤች ደብሊው ቡሽ በሦስት አውዳሚ መረከቦች ታጅባ በደቡብ አፍሪካ አካባቢ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ እየቀዘፈች መሆኑን የባሕር ኃይል ኢንስቲትዩት መረጃ ያሳያል።ሌላ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ዩኤስኤስ ጄራልድ አር ፎርድ በምሥራቃዊ ሜዲትራኒያን በአራት አውዳሚ መርከብ ታጅባ እየቀዘፈች ነው።ፎርድ በጦርነቱ መጀመሪያ ሳምንታት ውስጥ ቁልፍ ሚና የተጫወተች ሲሆን በአሁኑ ወቅት በግሪክ ጥገና ላይ ነች።ያጋሩ, አሜሪካ የኢራን ወደቦችን ለመዝጋት ምን ልትጠቀም ትችላለች?
  15. 14 ሚያዚያ 2026የኢራን ጦርነት የሚቀጥል ከሆነ የዓለም ምጣኔ ኃብት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ አይኤምኤፍ አስጠነቀቀበኢራን ጦርነት ወቅት እንደ ኢራቅ ባሉ አገራት የምግብ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በኢራን ጦርነት ወቅት እንደ ኢራቅ ባሉ አገራት የምግብ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷልየዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በመካከለኛው ምሥራቅ የሚካሄደው የኢራን ጦርነት ካልቆመ እና የነዳጅ ዋጋ መጨመሩ ከቀጠለ የዓለም ምጣኔ ኃብት የመንኮታኮት አደጋ እንደተጋረጠበት አስጠነቀቀ።አይኤምኤፍ የኢራን ጦርነት የሚቀጥል ከሆነ ከፍተኛ የነዳጅ፣ የጋዝ እና የምግብ ዋጋ ጭማሪ ስለሚታይ የዓለም ምጣኔ ኃብት እድገት ዝቅ እንዲል ያስገድዳል ሲል ገልጿል።የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የዓለም ምጣኔ ኃብትን በተነበየበት ሪፖርቱ ላይ እንዳመለከተው፣ የነዳጅ፣ የጋዝ እና የምግብ ዋጋ እየጨመረ የሚቀጥል ከሆነ እአአ በ2026 የዓለም ምጣኔ ኃብት እድገት ከ2 በመቶ በታች ሊሆን ይችላል ብሏል።”ይህ ማለት ዓለም እአአ ከ1980 ወዲህ አራት ጊዜ ብቻ ወደ ተከሰተው የኢኮኖሚ ቀውስ እየሄደች ነው ማለት ነው” ሲል ድርጅቱ ገልጿል።ዓለም በቅርብ ጊዜ የኢኮኖሚ ቀውስ ያጋጠማት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጊዜ ነው።የኢራን ጦርነት ከጀመረበት ከስድስት ሳምንታት ወዲህ ዋናው የነዳጅ ዘይት መተላለፊያ የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ እንዲሁም በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተደረገው የሰላም ድርድር ያለውጤት በመጠናቀቁ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት “በድጋሚ የዓለም ኢኮኖሚ ከመስመሩ ውጪ የመሆን አደጋ ተጋርጦበታል፤ በዚህ ወቅት በየካቲት 2018 ዓ.ም. በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት በመቀስቀሱ ነው።”በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊያስከትሉ ከሚችሉት እጅግ አስከፊ ሁኔታዎች መካከል አንዱ የሆነው የነዳጅ ዋጋ መጨመር በዚህ ኣመት ታይቷል።አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት ከከፈቱ ወዲህ አንድ በርሜል የነዳጅ ዘይት በአማካይ 110 ዶላር ደርሷል።እአአ በ2027 ደግሞ 125 ዶላር እንደሚደርስ ተገምቷል።በእነዚህ ግምቶች ላይ በመመስረት አይኤምኤፍ በሚቀጥለው ዓመት የዋጋ ግሽበት እስከ 6 በመቶ ሊደርስ እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል። ይህ ደግሞ ብሔራዊ ባንኮች የዋጋ ጭማሪን ፍጥነት ለመቀነስ የወለድ ተመኖችን ከፍ እንዲያደርጉ ሊያስገድዳቸው ይችላል።በኢራን ግጭት ወቅት የነዳጅ ዋጋ ወደ 120 ዶላር ከፍ ብሎ የነበረ ቢሆንም ማክሰኞ ዕለት አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ 98.85 ዶላር ተሸጧል።ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ግጭቱ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ከተፈታ እና ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚወጣው የነዳጅ ምርት እና የውጭ ንግድ በዚህ ዓመት አጋማሽ ላይ መደበኛ መሆን ከጀመረ በ2026 የዓለም እድገት በ3.1 በመቶ ብቻ እንደሚቀንስ ግምቱን አስቀምጧል።ያጋሩ, የኢራን ጦርነት የሚቀጥል ከሆነ የዓለም ምጣኔ ኃብት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ አይኤምኤፍ አስጠነቀቀ
  16. 14 ሚያዚያ 2026ኢራን በጦርነቱ እስካሁን 270 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ውድመት እንደደረሰባት ገለጸችእስራኤል እና አሜሪካ ኢራን ከተሞች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የወደመ ሕንጻየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesኢራን በጦርነቱ ምክንያት የደረሰባትን ውድመት ግምት ውስጥ በማስገባት የካሳ ክፍያን የድርድሩ አካል ለማድረግ በማሰብ የጉዳቱን መጠን ማስላት መጀመሯን ከአብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያለው ታስኒም የዜና ወኪል ዘገበ።የኢራን መንግሥት ቃል አቀባይ ፋቴሜህ ሞሃጀራኒ ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን እስራኤል እና አሜሪካ ከየካቲት 21 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለ40ቀናት በዘለቀው ጥቃታቸው ያደረሱት ውድመት “ቅድመ ግምት” 270 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ መሆኑን ጠቅሰው ይህ ቁጥር ግን ሊለወጥ እንደሚችል ተናግረዋል።በኢራን የሚገኙ ባለሥልጣናት የደረሰውን ውድመት እያሰሉ መሆኑን የተናገሩት ባለሥልጣኗ ይህም በሕንፃዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት እና ኢንዱስትሪዎች ሥራ በማቆማቸው ምክንያት የሚደርሰውን ኪሳራ ያካትታል ማለታቸውን ታስኒም ዘግቧል።ሞሃጀራኒ ለኢራን መንግሥት መገናኛ ብዙኃን፣ ኢርና ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከአሜሪካ ጋር በተደረገው ውይይት ከተነሱት ጉዳዮች አንዱ ካሳ መሆኑን ተናግረዋል።የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ቀደም ሲል በፓኪስታን በተካሄደው ውይይት ላይ “ጠቃሚ ውይይቶች” እንደተደረጉ ቢናገሩም ምንም ዓይነት ስምምነት ላይ ግን አልተደረሰም።በቴህራን በተፈጸመ የአየር ድብደባ ጉዳት የደረሰበት የመኖሪያ ሕንጻየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በቴህራን በተፈጸመ የአየር ድብደባ ጉዳት የደረሰበት የመኖሪያ ሕንጻያጋሩ, ኢራን በጦርነቱ እስካሁን 270 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ውድመት እንደደረሰባት ገለጸች
  17. 14 ሚያዚያ 2026የኢራን መገናኛ ብዙኃን ከአሜሪካ ጋር ቀጣይ ንግግር ስለመኖሩ “መረጃ የለም“ አሉየአሜሪካ እና የኢራን ባንዲራየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ኢርና፣ በአሜሪካ እና በቴህራን መካከል አደራዳሪ በመሆን እያገለገለች ካለችው ፓኪስታን ጋር የመልዕክት ልውውጦች ቢኖሩም ቀጣይ ውይይት ለማድረግ ግን የተደረሰ ስምምነት ስለመኖሩ “መረጃ የለም” አለ።የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሰው የዘገቡት የኢራን መገናኛ ብዙኃን በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ያለውጤት ከተጠናቀቀው ድርድር ወዲህ ከፓከሲታን ጋር ያለው የመልዕክት ልውውጥ “አሁን ባሉ ጉዳዮች ዙሪያ” መሆኑን ገልጸዋል።ቀደም ሲል ሮይተርስ የዜና ወኪል አሜሪካ እና ኢራን በዚህ ሳምንት ዳግም በኢዝላማባድ ተገናኝተው ውይይታቸውን ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር።ሮይተርስ የጠቀሳቸው ምንጮች ሁለቱ አገራት መቼ ወደ ድርድሩ እንደሚመለሱ በግልጽ ባይናገሩም በዚህ ሳምንት መጨረሻ ግን ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።አንድ የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣን “ቁርጥ ያለ ቀን አልተቀመጠም። ልዑካኑ ከአርብ እስከ እሁድ ያለውን ቀን ክፍት አድርገው ይጠብቃሉ” ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በኢዝላማባድ የተደረገው የሁለቱ አገራት ውይይት የተጀመረው የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ ነው።ንግግር ዳግም እንደሚጀመር ለሮይተርስ የተናገሩት የመጀመርያው ምንጭ ለሁለቱም አገራት ምክረሃሳቦች የያዘ ሰነድ መሰጠቱን እና ልዑካኖቻቸውን ዳግም ልከው ውይይቱ እንዲቀጥል ተነግሯቸዋል ብለዋል።ለጉዳዮ ቅርበት ያላቸው የፓኪስታን ምንጮች ደግሞ ኢዝላማባድ ከሁለቱም አገራት ጋር ቀጣዩ ውይይት መቼ መደረግ እንዳለበት እየተነጋገረች መሆኑን ገልጸዋል።አክለውም በሳምንቱ መጨረሻ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።ከፍተኛ የፓኪስታን ባለሥልጣን “ኢራንን አነጋግረናል እናም ሁለተኛው ዙር ንግግር ሊደረግበት ስለሚችልበት ሁኔታ በጎ ምላሽ አግኝተናል”በፓኪስታን የሚገኘው የኢራን ኤምባሲም ስለ ሁለተኛ ዙር ድርድር ውይይቶች መደረጋቸውን ለሮይተርስ አረጋግጧል።ዋይት ሐውስ ግን በጉዳዮ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።ያጋሩ, የኢራን መገናኛ ብዙኃን ከአሜሪካ ጋር ቀጣይ ንግግር ስለመኖሩ “መረጃ የለም“ አሉ
  18. 14 ሚያዚያ 2026ጣሊያን ከእስራኤል ጋር ያላትን ወታደራዊ ስምምነት አቋረጠችየጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጆርጂያ ሜሎኒየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesጣሊያን ከእስራኤል ጋር የገባችውን ወታደራዊ ስምምነት እንደማታድስ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጆርጂያ ሜሎኒ ተናገሩ።ሜሎኒ በየአምስት ዓመቱ ይታደስ የነበረውን የሁለቱን አገራት ወታደራዊ ስምምነት ለማዘግየት የወሰኑት “አሁን ያለውን ሁኔታ ከግምት በማስገባት” እንደሆነ ተናግረዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሯ ስለጉዳዩ በዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል።ነገር ግን ሮም እና ቴል አቪቭ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመካከላቸው ያለው ግንኙነት ንፋስ ገብቶታል።በሊባኖስ የተሰማራው የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ውስጥ እያገለገሉ የሚገኙ ጣሊያናውያን ላይ የማስጠንቀቂያ ተኩስ ከተተኮሰባቸው እና አንድ መኪና ጉዳት ከደረሰበት በኋላ ባለፈው ሳምንት ጣሊያን በሮም የሚገኙትን የእስራኤል አምባሳደርን ጠርታ አነጋግራለች።ሰኞ ዕለት ደግሞ የጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ እስራኤል በሊባኖስ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈጸመችውን ጥቃት “ተቀባይነት የሌለው” ካሉ በኋላ “እንደ ጋዛ ያለ ግጭት ከመቀስቀሱ በፊት ማንኛውም ዋጋ ተከፍሎ ቢሆን መቆም አለበት” ሲሉ መናገራቸውን ተከትሎ እስራኤል የጣሊያን አምባሳደርን በመጥራት አነጋግራለች።ሌሎች የአውሮፓ አገራት በተመሳሳይ ከእስራኤል ጋር ያላቸውን የጦር መሣሪያ ውጭ ንግድ ገድበዋል ወይንም ለጊዜው አቁመዋል።የጣሊያን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለረዠም ጊዜ አገራቸው ተመሳሳይ እርምጃ እንድትወስድ ሲወተውቱ ነበር።ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጣሊያናውያን እስራኤል በጋዛ የፈጸመችውን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት ተከትሎ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።ሠልፈኞቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ የፍልስጤም ነጻ አገርነትን እንደ ሌሎች ለመቀበል ዳተኛ በመሆን ተችተዋቸዋል።ጣሊያን ከእስራኤል ጦር መሣሪያ ከሚገዙ ሦስት ቀዳሚ አገራት መካከል አንዷ ናት።ከፊት ያሉት ሁለት አገራት አሜሪካ እና ጀርመን ናቸው።ያጋሩ, ጣሊያን ከእስራኤል ጋር ያላትን ወታደራዊ ስምምነት አቋረጠች
  19. 14 ሚያዚያ 2026የኢራን ፕሬዝዳንት ወታደራዊ እርምጃ አሜሪካ “ራሷ የፈጠረችውን ችግር” ያባብሳል አሉፕሬዝዳንት መሱድ ፐዝሽኪያንየፎቶው ባለመብት,IRANIAN PRESIDENCYየኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዝሽኪያን ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ቴህራን የሰላም ንግግሮችን ለመቀጠል ዝግጁ መሆኗን እና ግጭቶችን ለመፍታት የምትመርጠው ዲፕሎማሲያዊ መንገድን እንደሆነ መናገራቸውን የኢራን የዜና አውታሮች ዘገቡ።ፕሬዝዳንቱ ለማክሮን ዛቻዎች፣ ጫናዎች እና ወታደራዊ እርምጃዎች ችግሮችን ለመፍታት “አያግዙም” በማለት ተናግረዋል። አሜሪካ “ራሷ የፈጠረችውን ችግር” የሚያባብስ እንደሚሆንም አሳስበዋልፕሬዝዳንት ፔዝሽኪያን አሜሪካ ለዓለም አቀፍ ሕግ እና መመሪያ ተገዢ እንድትሆን አውሮፓ ማበረታታት አለበት ሲሉም አክለዋል።ያጋሩ, የኢራን ፕሬዝዳንት ወታደራዊ እርምጃ አሜሪካ “ራሷ የፈጠረችውን ችግር” ያባብሳል አሉ
  20. 14 ሚያዚያ 2026ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው አራት መርከቦች ከአሜሪካ እገዳ በኋላ በሆርሙዝ ወሽመጥ አለፉበሆርሙዝ የሚጓዝ መርከብየፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ በሆርሙዝ ላይ የጣለችው እገዳ ተግባራዊ መሆን እንደጀመረ ቢነገረም ከኢራን ጋር ግንኙነተ ያላቸው አራት መርከቦች በወሽመጡ በኩል ማለፋቸውን ቢቢሲ ቬሪፋይ የተነተነው የመርከቦች ጉዞ የትክክል መረጃ አሳየ።‘ማሪን ትራፊክ’ የተሰኘው መርከቦች ጉዞ መከታተያ ድረ ገጽ መረጃ እንደሚመለክተው ከአራቱ ውስጥ ሁለቱ መርከቦች የኢራን ወደቦችን ጎብኝተው ነበር።’ክርስቲያና’ የተሰኘችው የጭነት መርከብ ወደ ኢራን ባንዳር ኢማን ኮሜኒ ወደብ ተጉዛ የነበረ ሲሆን ሰኞ ዕለት አሜሪካ እገዳ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ ደግሞ በወሽመጡ በኩል ማለፏን መረጃው ያሳያል።ከኢራን ጋር በሚያደርገው የንግድ እንቅስቃሴ ምክንያት በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለበት ‘ሪች ስቴሪ’ የተባለ ሌላ መርከብ ደግሞ ትናንት ሌሊት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሻርጃ በመነሳት በሆርሙዝ በኩል ተጉዟል። መርከቡ መዳረሻው ቻይና እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።በወሽመጡ በኩል ያለፈው ሌላኛው ነዳጅ ጫኝ መርከብ ‘ሙርሊኪሻን’ የሚል ስያሜ የተሰጠው ነው። ይህም መርከብ ከኢራን ጋር ባለው ንግድ ምክንያት አሜሪካ ማዕቀብ ጥላበታለች።መርከቡ ከቻይና ላንሻን እንደተነሳ እና ሌሊቱን በሆርሙዝ በኩል እንዳለፈ መረጃው አሳይቷል። እንደ ማሪን ትራፊክ ከሆነ፤ መርከቡ የታየበት የመጨረሻው ስፍራ ከኢራን ቃሽም ደሴት በስተምስራቅ ያለ አካባቢ ነው።‘ኤልፒስ’ የተባለ ሌላ ነዳጅ ጫኝ መርከብም ማክሰኞ ዕለት ከኢራኑ ቡሼህር ወደብ ተነስቶ በወሽመጡ በኩል ማለፉን የጉዞ መከታተያው ድረ ገጽ መረጃ ይጠቁማል። መዳረሻው ያልታወቀው ይህ መርከብም በአሜሪካ ማዕቀብ ተጥሎበታል።እነዚህ መርከቦች አድራሻቸውን ለመደበቅ ሲሉ የሚገኙበትን ቦታ በተመለከተ የተሳሳተ መረጃ አሰራጭተው ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።የአሜሪካ ጦር ከትናንት ሰኞ 11 ሰዓት ጀምሮ “ወደ ኢራን ወደቦች ለመግባት እና ለመውጣት የሚደረጉ የባሕር ጉዞዎችን በሙሉ” እንደሚያግድ አስታውቆ ነበር።”እገዳው በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወይም ከ[ኢራን] ወዳልሆኑ መዳረሻዎች የሚደረጉ ገለልተኛ የትራንዚት ጉዞዎችን” ግን እንደማያስቆም ገልጾ ነበር።ያጋሩ, ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው አራት መርከቦች ከአሜሪካ እገዳ በኋላ በሆርሙዝ ወሽመጥ አለፉ