
”ይህ ኃላፊነት የጎደለው ሰው በህግ መጠየቅ አለበት ወዴት ወዴት ነው?” በጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸው
ይህ ሰው ግን እንዲህ ያለው ኃላፊነት የጎደለውና አንድን ሃይማኖት ጠዋት ማታ አደግድጎ የመደብደብ አባዜ መቼ ነው ሚለቀው?
ኡስታዝ አህመድን ጀበል ቤተ ክርስቲያኗ በማታውቀውና ባልወከለችው ያውም ስልጣን አለኝ በሚል አካል ለደረሰ ሁሉ መሰደቧ ሳያንስ በማን አለብኝነት በ”አፓርታይድ” መወንጀል አስቂኝ ነው።
”ክርስቲያናዊ አፓርታይድ” ሕጉ ለእነሱ አይሠራ እንደሆነ እንጂ ሕግ ፊት የሚያቆም ነበር። ለነገሩ ማን ጠያቂ አለና! እነሱም ይህንን ያውቃሉ- ብትረገጥ፣ ብትሰደብ፣ብትነድ ከውስጥም ከውጭ ማን ይጠይቅና?
ደግሞ በዚህ በተለያየ ቋንቋ የሚካሄደው ቅስቀሳ የተነሳ ነገስ የትኞቹ ኦርቶዶክሳውያን ይታረዱ ይሆን?
ትንሽ ሰውነት እና ሕሊና ቢኖራችሁ እናንተው እንደልብ የምታዙበት አካባቢ ኦርቶዶክሳውያኑ እንደበግ ሲታረዱ ጥይት እንደበረዶ ሲዘንብባቸው አንዲት ቃል ትበቃችሁ ነበር። ግን ምን አገባችሁና!
ዛሬ ቤተ ክርስቲያኗ በማይመለከታት ጉዳይ ለመክሰስ የመጣችሁት እንደሌለችበት ጠፍቷችሁ ሳይሆን እርካታችሁ ይህ ስለሆነ እና አይጧን ፈርቶ….ሁኖባችሁ ነው።
በነገራችን ላይ ሙሉ የጻፍኸውን በተለያየ ቦታ በሃይማኖታቸው ለተገደሉት ክርስቲያኖች ገልብጠን ስናነበው ልክ ይመጣል።
ጥቃት የትም በማንም ሲፈጸም በሕግም በሃይማኖትም የተወገዘ ነው- አፍ ያለው ያግባሽ ልብ ያለው? የሆነ ነገር ነው ገጥሞን ይህን ጻፍን እንጂ።
የሚገርመው እንደዋዛ መታለፍ የሌለበት ጉዳይ ቢሆንም ትኩረት አልሰጠነውም።
ጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸው

