
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን ጋር ዛሬ እንደሚገናኙ የእስራኤል የደኅንነት ምክር ቤት አባል ተናገሩ። ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ “በእስራኤል እና ሊባኖስ መካከል ትንሽ እስትንፋስ እንዲኖር እየመከርኩ ነው። የሁለቱ አገራት መሪዎች ከተነጋገሩ በጣም ረጅም ጊዜ ሆኗል፤ 34 ዓመት ገደማ። ነገ [ሐሙስ] ይካሄዳል” ብለው ነበር።
ጭምቅ ሃሳብ
- ኢራን የአሜሪካ የወደብ መዝጋት የሚቀጥል ከሆነ በባሕረ ሰላጤው፣ ቀይ ባሕር እና በኦማን የባሕር ወሽመጥ እርምጃ እወስዳለሁ ስትል ዛተች
- በሲሪላንካ ለመቆየት የተገደዱት ከ200 በላይ የኢራን ባሕርተኞች ወደ አገራቸው ተመለሱ
- ከእስራኤል እና ሊባኖስ የዋሽንግተን ንግግር በኋላ እስራኤል ሄዝቦላህን ማጥቃቷን ቀጠለች
- ፕሬዝዳንት ፐዝሽኪያን ኢራንን ለማንበርከክ የሚደረግ ሙከራ እንደሚከሽፍ ተናገሩ
- የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ‘ትልቅ ስምምነት’ ማድረግ እንደሚፈልጉ ተናገሩ
- ትራምፕ የኢራን ጦርነት “ሊያበቃ ተቃርቧል” አሉ
- ትራምፕ አሜሪካ እና ኢራን “በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ” ሊወያዩ እንደሚችሉ ተናገሩ
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 1 ሰአት በፊትየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጋር ሊገናኙ መሆኑ ተገለጸ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን ጋር ዛሬ እንደሚገናኙ የእስራኤል የደኅንነት ምክር ቤት አባል ተናገሩ።ይህ የተባለው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው የእስራኤል እና ሊባኖስ መሪዎች ሐሙስ እንደሚገናኙ ካሳወቁ በኋላ ነው።ትራምፕ ረቡዕ ምሽት በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው በለጠፉት ጽሑፍ መሪዎቹ ከአስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ “ነገ [ሐሙስ]” ይነጋገራሉ ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ “በእስራኤል እና ሊባኖስ መካከል ትንሽ እስትንፋስ እንዲኖር እየመከርኩ ነው። የሁለቱ አገራት መሪዎች ከተነጋገሩ በጣም ረጅም ጊዜ ሆኗል፤ 34 ዓመት ገደማ። ነገ [ሐሙስ] ይካሄዳል” ብለዋል።ይህ የፕሬዝዳንቱ መግለጫ እስራኤል እና ሊባኖስ ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዋሽንግተን ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ካደረጉ ከቀናት በኋላ የተሰጠ ነው።ፕሬዝዳንቱ ይህን ቢሉም ሊባኖስ ይደረጋል በተባለው ንግግር ላይ የምታውቀው ነገር እንደሌለ ጠቁማለች።በሊባኖስ ፕሬዝዳንታዊ ፅሕፈት ቤት የሚሰሩ አንድ ባለሥልጣን አገራቸው ከእስራኤል ጋር ሊደረግ ነው ስለተባለው ንግግር አታውቅም ሲሉ ንግግሩ ላይ ያለውን ጥርጣሬ ለቢቢሲ ገልፀዋል።የሁለቱ አገራት ታሪካዊ ንግግር በእስራኤል እና በኢራን በሚደገፈው ሄዝቦላህ መካከል ያለውን ጦርነት ለማስቆም ያለመ ነው።አሁን የእስራኤል የካቢኔ አባል ለአገሪቱ ጦር ራዲዮ የመሪዎቹን ግንኙነት ማሳወቃቸውን ተከትሎ ንግግሩ ሊካሄድ የመቻል እድሉ ጨምሮ ታይቷል።ኢራን በበኩሏ ከዋሽንግተን ጋር የተደረሰው የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ሊባኖስንም እንዲያካትት የማድረግ ጉዳይን አሜሪካ ማስከበር እንዳለባት ተናግራለች።የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ ባገር ጋሊባፍ በኤክስ ገፃቸው ባወጡት መግለጫ “በሊባኖስ የተጠናከረ የተኩስ አቁም” መሟላት የሄዝቦላህን “ፅኑ ትግል” ረገብ ያደርገዋል ብለዋል።ኢራን ‘አክሲስ ኦፍ ሪዝስታንስ’ በሚል የምትጠራው እና ሄዝቦላህ አባል የሆነበት ተገዳዳሪ ኃይል “በጦርነትም በተኩስ አቁምም አንድ ነፍስ” ናቸው ብለዋል።ያጋሩ, የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጋር ሊገናኙ መሆኑ ተገለጸ - ከ 2 ሰአት በፊትአሜሪካ 10 መርከቦችን ወደ ኢራን መመለሷን አስታወቀች
የፎቶው ባለመብት,Centcomየምስሉ መግለጫ,የአሜሪካ ጦር የኢራን ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልብ መርከብ እግዱን ጥሶ ለማለፍ ሙከራ አድርጓልየአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ ወሽመጥ ወደ ኢራን በሚገቡ እና በሚወጡ መርከቦች ላይ የጣለው እግድ ሠኞ ዕለት ገቢራዊ ከሆነ በኋላ አንድም መርከብ እግዱን እንዳለለፈ ገለፀ።ጦሩ መርከቦችን እንደሚይዝ ወይም ወደ ኢራን ወደቦች ለመግባት እና ለመውጣት የሚሞክሩትን እንደሚመለስ ገልጿል።በወሽመጡ አልፈው ወደሌላ አገራት ወደቦች የሚገቡ እና የሚወጡ መርከቦች ማለፍ እንደሚፈቀድላቸውም ጠቁሟል።ትናንት ረቡዕ ምሽት የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በሰጠው መረጃ “10 መርከቦች ወደመጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል። እግዱ ተፈፃሚ ከሆነበት ሠኞ ወዲም ምንም መርከብ ሰብሮ አላለፈውም” ብሏል።ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቴህራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ከሚያልፉ መርከቦች ላይ ትሰበስበው የነበረውን ቀረጥ በማስቀረት እንዲሁም የነዳጅ ሽያጯን በማስተጓጎል ጫና እንደሚያሳድሩ ተስፋ አላቸው።ኢራን እገዳውን “የባሕር ላይ ውንብድና” ያለችው ሲሆን፤ በባሕረ ሰላጤው፣ በኦማን ሰርጥ እና በቀይ ባሕር የአፃፋ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች።ያጋሩ, አሜሪካ 10 መርከቦችን ወደ ኢራን መመለሷን አስታወቀች - ከ 2 ሰአት በፊትትራምፕ የእስራኤል እና ሊባኖስ መሪዎች ዛሬ እንደሚነጋገሩ ቢያሳውቁም፤ የቤይሩት ባለሥልጣን አገራቸው ጉዳዩን እንደማታወቅ ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የእስራኤል እና ሊባኖስ መሪዎች ከአስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ሐሙስ እንደሚነጋገሩ ገለፁ።ትራምፕ ረቡዕ ምሽት በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው በለጠፉት ጽሑፍ መሪዎቹ “ነገ [ሐሙስ]” ይነጋገራሉ ብለዋል።ፕሬዝዳንቱ ይህን ቢሉም ሊባኖስ ይደረጋል በተባለው ንግግር ላይ የምታውቀው ነገር እንደሌለ ጠቁማለች።በሊባኖስ ፕሬዝዳንታዊ ፅሕፈት ቤት የሚሰሩ አንድ ባለሥልጣን አገራቸው ከእስራኤል ጋር ሊደረግ ነው ስለተባለው ንግግር አታውቅም ሲሉ ንግግሩ ላይ ያለውን ጥርጣሬ ለቢቢሲ ገልፀዋል።ትራምፕ “በእስራኤል እና ሊባኖስ መካከል ትንሽ እስትንፋስ እንዲኖር እየመከርኩ ነው። የሁለቱ አገራት መሪዎች ከተነጋገሩ በጣም ረጅም ጊዜ ሆኗል፤ 34 ዓመት ገደማ። ነገ [ሐሙስ] ይካሄዳል” ብለዋል።ይህ የፕሬዝዳንቱ መግለጫ እስራኤል እና ሊባኖስ ከሦስት አስርት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዋሽንግተን ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ካደረጉ ከቀናት በኋላ የተሰጠ ነው።የሁለቱ አገራት ታሪካዊ ንግግር በእስራኤል እና በኢራን በሚደገፈው ሄዝቦላህ መካከል ያለውን ጦርነት ለማስቆም ያለመ ነው።ኢራን በበኩሏ ከዋሽንግተን ጋር የተደረሰው የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ሊባኖስንም እንዲያካትት የማድረግ ጉዳይን አሜሪካ ማስከበር እንዳለባት ተናግራለች።የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ ባገር ጋሊባፍ በኤክስ ገፃቸው ባወጡት መግለጫ “በሊባኖስ የተጠናከረ የተኩስ አቁም” መሟላት የሄዝቦላህን “ፅኑ ትግል” ረገብ ያደርገዋል ብለዋል።ኢራን ‘አክሲስ ኦፍ ሪዝስታንስ’ በሚል የምትጠራው እና ሄዝቦላህ አባል የሆነበት ተገዳዳሪ ኃይል “በጦርነትም በተኩስ አቁምም አንድ ነፍስ” ናቸው ብለዋል።ያጋሩ, ትራምፕ የእስራኤል እና ሊባኖስ መሪዎች ዛሬ እንደሚነጋገሩ ቢያሳውቁም፤ የቤይሩት ባለሥልጣን አገራቸው ጉዳዩን እንደማታወቅ ተናገሩ - ከ 3 ሰአት በፊትዋሽንግተን የቴህራን ወደቦች ላይ የጣለችው እግድ ሲፀና፤ የአሜሪካ-ኢራን ንግግር “እየቀጠለ ነው”
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች በሚገቡ እና በሚወጡ ሁሉም መርከቦች ላይ የጣለችው እግድ በፀናበት ወቅት ዋይት ሐውስ አሜሪካ ከኢራን ጋር “ውጤታማ እና ቀጣይነት ያለው” ንግግር እያደረገች መሆኑን ገለፀ።በ24 ሰዓታት ውስጥ የተከሰቱ አዲስ ሁነቶች፡የአሜሪካ-ኢራን ንግግር- አሜሪካ የሁለት ሳምንቱ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲራዘም በይፋ ጠይቃለች መባሉን ዋይት ሐውስ አስተባብሏል።
- ፕሬስ ሴክሬታሪያት ካሮሊን ሌቪት አሜሪካ ስምምነት ሊደረስ እንደሚችል ባለው ተስፋ “ጥሩ ስሜት” እንደሚሰማት ተናግረዋል። ሆኖም ቀጣዩ ዙር ንግግር መቼ ሊደረግ እንደሚችል ቀን አለመቆረጡን ገልፀዋል።
- ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሜሪካ እና ኢራን ንግግር አሸማጋይ የሆነው የፓኪስታን ልዑክ ከኢራን መንግሥት ጋር ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ ቴህራን ገብቷል።
- አሜሪካ ወደ ኢራን ወደብ የሚገቡ እና የሚወጡ ማንኛውም መርከቦች ላይ የጣለችው እግድ እንደፀና ነው። ዋይት ሐውስ እግዱ “ሙሉ ለሙሉ እየተተገበረ ነው” ያለ ሲሆን፤ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚፀና ግን አልጠቀሰም።
- የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ እግዱ ከተጣለ በኋላ አንድም መርከብ እንዳልገባ እና እንዳልጣ የገለፀ ሲሆን፤ 10 መርከቦች እንዲመለሱ ከተናገራቸው በኋላ ትዕዛዙን አክብረው ወደ ኢራን መመለሳቸውን አስታውቋል።
- ቢቢሲ ቨርፋይ በቀጣናው በርካታ መርከቦች አድራሻቸውን በመደበቅ መረጃቸውን እያጠፉ መሆኑን ለይቷል።
- በእስራኤል እና ሄዝቦላህ መካከል በሊባኖስ ግጭቶች ቀጥለዋል። የእስራኤል መከላከያ ኃይል (አይዲኤፍ) በደቡባዊ ሊባኖስ ከቲታኒያ ወንዝ በታች ያለውን ስፍራ የሄዝቦላ ‘መቀበሪያ’ ነው ሲል ገልፆታል።
- የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጦርነቱን በሚመለከት አገራቸው “ለየትኛውም ሁኔታ” ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም የእስራአል ግብ ከአሜሪካ ግብ ጋር የሚጣጣም ነው ብለዋል።
- ኔታኒያሁ ይህን ያሉት እስራኤል እና ሊባኖስ ታሪካዊ የተባለውን ንግግር ማክሰኞ ዕለት ካደረጉ እና ሊባኖስ ንግግሩን “ውጤታማ”፤ እስራኤል ደግሞ ሁለቱም አገራት “በተመሳሳይ ገፅ” ላይ እንዳሉ ካሳወቀች በኋላ ነው።
- ከ 4 ሰአት በፊትየዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር በኢራን ጦርነት የተነሳ ከትራምፕ ለሚደርስባቸው ጫና “እንደማይንበረከኩ” ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር በኢራን የሚካሄደውን ጦርነት እንዲቀላቀሉ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሚደርስባቸው ጫና “እንደማይንበረከኩ” ገለጹ።ስታርመር ይህንን ያሉት ዶናልድ ትራምፕ ለስካይ ኒውስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ አሜሪካ የዩናይትድ ኪንግደምን እርዳታ በጠየቀችበት ወቅት “አልተገኘችም” ካሉ በኋላ ነው።ትራምፕ አክለውም ከዩኬ ጋር የተደረሰው የታሪፍ ስምምነት “መቼም ቢሆን ሊቀየር ይችላል” ብለዋል።የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር በፓርላማ ቀርበው ባደረጉት ንግግር “ሃሳቤን አልቀይርም፣ እጅ አልሰጥም፤ ጦርነቱን መቀላቀል የእኛ ብሔራዊ ጥቅም አይደለም፤ ስለዚህም አናደርገውም” ሲሉ አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል።“በኢራን ላይ ያለኝ [አቋም] ከጅማሬው አንስቶ ግልጽ ነው፤ እዚህ ጦርነት ውስጥ ተገድደን አንገባም” ብለዋል።“የእኛ ጦርነት አይደልም፤ የተለየ አቅጣጫ እንድይዝ ብዙ ጫና ተደርጎብኛል፤ ጫናው ዛሬ ምሽት የተፈጠረውንም ያካትታል” ሲሉ የትራምፕን ቃለ መጠይቅ አመልክተዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቃለ መጠይቁ የአሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደምን ልዩ ግንኙነት እንዴት እንደሚገልጹት ተጠይቀው ነበር።“እገዛ ስንጠይቃቸው አልተገኙም፤ እንዲህ አይነት ግንኙነት ነው። ስንፈልጋቸው አልነበሩም” ሲሉ ተናግረዋል።ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት የተነሳ የሁለቱ አገራት ግንኙነት የመሻከር ምልክቶች እየታዩበት ነው። የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር በጦርነቱ ውስጥ ቀጥታ እንዲሳተፉ የቀረበላቸው ጥሪ ውደቅ ማደረጋቸውን ተከትሎ ከትራምፕ ተደጋጋሚ ትችት ደርሶባቸዋል።ያጋሩ, የዩኬ ጠቅላይ ሚኒስትር በኢራን ጦርነት የተነሳ ከትራምፕ ለሚደርስባቸው ጫና “እንደማይንበረከኩ” ተናገሩ - ከ 4 ሰአት በፊትቻይና፤ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን እንድትከፍት አሳሰበች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚደረግ መደበኛ የመርከቦች እንቅስቃሴ እንዲመለስ ጥረት መደረግ እንዳለበት ለኢራን አቻቸው አባስ አራግቺ ተናገሩ።ዋንግ በሆርሙዝ ወሽመጥ የኢራን ሉዓላዊነት እና ደኅንነት መከበር እንዲሁም መጠበቅ ያለበት ቢሆንም በውሃ አካላት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችም ነፃነት እና ደኅንነት ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል።ሁለቱ ሚንስትሮች በስልክ ባደረጉት ውይይት ዋንግ የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመክፈት ዓለም አቀፍ ፍላጎት እንዳለ ገልፀዋል።“በወሽመጡ መደበኛ እንቅስቃሴ ለመመለስ መስራት የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ሙሉ በሙሉ ጥሪ ነው” ማለታቸውን መንግሥታቸው ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሁናዊ ሁኔታው በጦርነት እና በሰላም መሀል የሚገኝ ወሳኝ እጥፋት ላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሰላም በር እየተከፈተ መሆኑን መናገራቸውን ኤፒ ዘግቧል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቻይና የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንዲፀና እና ንግግሮች እንዲቀጥሉ ድጋፍ ታደርጋለችም ብለዋል።ያጋሩ, ቻይና፤ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን እንድትከፍት አሳሰበች - ከ 4 ሰአት በፊትአሜሪካ የወታደራዊው ዘመቻ “አቻ” የሆነ ኢኮኖሚያዊ እርምጃ በኢራን ላይ ልትወስድ መዘጋጀቷን አስታወቀች
የፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ ከወታደራዊው ዘመቻ “አቻ” በሆነ ደረጃ በኢራን ፋይናንስ ላይ ጫና ማሳደር የሚያስችል እቅድ እያጠናቀቀች መሆኗን የግምጃ ቤት ኃላፊው ስኮት ቤሴንት ተናገሩ።የትራምፕ አስተዳደር የኢራን ኢኮኖሚን ይበልጥ ለማሽመድመድ ያቀደበትን እቅድ ተግባራዊ የሚያደርገው አሜሪካ እና ኢራን በቶሎ ስምምነት ላይ ካልደረሱ መሆኑን የዜና ወኪሉ አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።የግምጃ ቤት ኃላፊው ቤሴንት ትናንት በሰጡት መግለጫ፤ የኢራን ፋይናንስ ላይ ጫና የሚያሳድረው “ኦፕሬሽን ኢኮኖሚክ ፊውሪ” እየተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ ወታደራዊ ጥቃት ሲከፍቱ ለዘመቻው የተሰጠው ስያሜ “ኦፕሬሽን ኢፒክ ፊውሪ” የሚል ነበር። ከወታደራዊው ዘመቻ ጋር ተመሳሳይ መጠሪያ የሚይዘው ኢኮኖሚያዊ ጫና የቦንብ ድብደባው እኩያ እንደሚሆን ቤሴንት ገልጸዋል።ኢራን ሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትን በመደብደብ ስህተት ሰርታለች ያሉት የግምጃ ቤት ኃላፊው፤ በአሁኑ ሰዓት ጥቃት የተፈጸመባቸው በባንክ ስርዓቶቻቸው ውስጥ ያሉትን የኢራን ፈንዶች “ግልጽ” ያደረጉ መምጣታቸውን ጠቅሰዋል።እነዚህ አገራት በባንክ ስርዓታቸው ውስጥ የሚገኙ የኢራን አብዮታዊ ዘብ አመራሮች አካውንቶችን እንቅስቃሴ እንዲያግዱ አሜሪካ መጠየቋንም አስታውቀዋል።በተጨማሪም አገራቱ የኢራንን ነዳጅ እንዳይገዙ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል። አገራቱ በባንክ ስርዓቶቻቸው ውስጥ የኢራን ገንዘብን የሚያስቀምጡ ከሆነ ሁለተኛ ደረጃ ማዕቀብ እንደሚጣልባቸው ገልጸዋል።የኤፒ ዘገባ እንደሚያመለክተው፤ ሁለተኛ ደረጃ ማዕቀብ የሚጣለው ከኢራን ጋር የንግድ ልውውጥ በሚያደርጉ፣ ግለሰቦች፣ ተቋማት እንዲሁም በኢራን ቁጥጥር ስር ባሉ መርከቦች ላይ ነው። አሜሪካ አጋር እንደሆነችው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እንዲሁም እንደ የዋሽንግተን ተቀናቃኟ ቻይና ያሉ አገራትም ማዕቀቡ ሊደርስባቸው ይችላል።ቤሴንት፤ “የኢራንን ነዳጅ የምትገዙ ከሆነ፣ በባንኮቻችሁ ውስጥ የኢራን ገንዘብ ተቀምጦ ከሆነ ሁለተኛ ደረጃ ማዕቀብ ልንጥልባችሁ ፈቃደኛ ነን ብለን ለኩባንያዎች፣ ለአገራት ነግረናቸዋል” ብለዋል።ይህ እርምጃ ኢራን ውስጥ “የተመለከትነው [ወታደራዊ] እንቅስቃሴ የፋይናንስ እኩያ እንደሚሆን ኢራናውያን ማወቅ አለባቸው” ሲሉም አስጠንቅቀዋል።ከመግለጫው በኋላ የአሜሪካ ግምጃ ቤት ከኢራን ጋር ግንኙነት አላቸው ባላቸው ግለሰቦች፣ ድርጅቶች እና መርከቦች ላይ ማዕቀቦቹን መጣሉን ይፋ አድርጓል። ማዕቀብ የተጣለባቸው ሦስት ግለሰቦች፣ ዘጠኝ መርከቦች እና 17 ተቋማት ናቸው።ያጋሩ, አሜሪካ የወታደራዊው ዘመቻ “አቻ” የሆነ ኢኮኖሚያዊ እርምጃ በኢራን ላይ ልትወስድ መዘጋጀቷን አስታወቀች - 15 ሚያዚያ 2026በሊባኖስ በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 2,167 ደረሰ
የፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,እስራኤል ረቡዕ ዕለት ከሊባኖስ የተወሰኑ አካባቢዎች “የአየር ድብደባ እየተፈጸመ ነው” በማለት ነዋሪዎች ለቅቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥታ ነበርእስራኤል በሊባኖስ የአየር ድብደባ ማድረግ ከጀመረች ጀምሮ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 2,167 መድረሱን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ገለጸ። የሟቾች ቁጥር ማክሰኞ ዕለት ከተገለጸው በ43 ሰዎች ከፍ ማለቱ ተገልጿል።በእስራኤል ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም 7,061 ደርሰዋል።እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በፈጸመችው ሦስት ተከታታይ ጥቃቶች ቢያንስ ሦስት የሕክምና ባለሙያዎች መገደላቸውን የሊባኖስ ባለሥልጣናት ገልጸዋል።ባለሥልጣናቱ እስራኤል ሆን ብላ የጤና ባለሙያዎችን ዒላማ ታደርጋለች ሲሉ ወንጅለዋታል።የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር የመጀመርያዎቹ የሕክምና ባለሙያዎች የተገደሉት በእስራኤል ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን ለማንሳት በሚጥሩበት ወቅት ነው ብሏል።በማስከተልም ሁለተኛ እና ሦስተኛ ቡድን ሲሄድም ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል።የእስራኤል ጦር በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ ቢጠየቅም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።እስራኤል ሄዝቦላህ አምቡላንስን እና የሕክምና ተቋማትን ለወታደራዊ ዓላማዎች ይጠቀማል ስትል ማስረጃ ሳታቀርብ ትከስሳለች።የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር ግን ይህንን ውንጀላ ያስተባብላል።ሚኒስቴሩ እስራኤል በሊባኖስ ላይ ጥቃት መፈጸም ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ 91 የሕክምና ባለሙያዎች ሲገደሉ፣ 208 መጎዳታቸውን ገልጿል።አክሎም በሕክምና ተቋማት እና አምቡላንሶች ላይ ብቻ 120 ጥቃቶች መፈጸማቸውን አስታውቋል።ሚኒስቴሩ ረቡዕ ዕለት ባወጣው መግለጫ የሚፈጸሙት ጥቃቶች “ጭካኔ የተሞላባቸው ወንጀሎች” ናቸው ብሏል።”የሕክምና ባለሙያዎች ቀጥተኛ ዒላማዎች ሆነዋል፣ ይህም . . . በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕግ የተደነገጉትን ሁሉንም ደንቦች እና መርሆዎች ሙሉ በሙሉ ችላ ማለቷን ያረጋግጣል” ብሏል።የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እስራኤል በሊባኖስ የፈጸመቻቸው አንዳንድ ድርጊቶች እንደ ጦር ወንጀል የሚታዩ ናቸው ብለዋል።ያጋሩ, በሊባኖስ በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 2,167 ደረሰ - 15 ሚያዚያ 2026ኢራን ከአሜሪካ ጋር ወደፊት ስለሚኖራት ንግግር ከፓኪስታን ጋር ከተወያየች በኋላ እንደምትወስን ተዘገበ
የፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ቅዳሜ ዕለት ፓኪስታን በደረሱበት ወቅትከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያለው ታስኒም የዜና ወኪል ቴህራን ከአሜሪካ ጋር የሚኖራትን ቀጣይ ድርድር ከፓኪስታን ልዑክ ጋር ከተወያየች በኋላ እንደምትወሰን ዘገበ።የዜና ኤጀንሲው “ስለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን” ጠቅሶ በቀጣዮ ዙር ውይይት ላይ ለመወሰን አሜሪካ እና እስራኤል ከሊባኖስ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ከደረሱ “ለኢራን እንደ በጎ ምልክት” መሆኑን ተናግሯል።ይሁን እንጂ አሜሪካ “ምክንያታዊ የሆነ የድርድር ማዕቀፍን መከተል አለባት” ያሉት የዜና ኤጀንሲው ምንጮች “ከመጠን በላይ የተለጠጡ ፍላጎቶችን በማቅረብ ሂደቱን ማደናቀፍ” ወይም ከተኩስ አቁም በፊት የተደረጉትን ስምምነቶችን መጣስ እንደሌለባት ጨምረው ተናግረዋል።ታስኒም ዋሺንግተን ቀጣዩን ዙር ውይይት ለማካሄድ ፈቃደኛ መሆኗን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን መዘገባቸውን ጠቅሶ፣ ነገር ግን የኢራን የልዑካን ቡድኑ ዩኤስ “ምክንያታዊ ድርድርን ለመጀመር የሚያስፈልጉትን የተወሰኑ መርሆዎችን ማክበር” እንደሚያስፈልጋት አፅንዖት ሰጥተዋል ብሏል።ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ ከኢራን ጋር ስለ ሁለተኛ ዙር ድርድር እየተነጋገረች መሆኑን ቢቢሲ ማረጋገጥ ችሏል። ነገር ግን እስካሁን ድረስ ቀኑም ሆነ ቦታው አለመወሰኑ ተገልጿል።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ኢራን ከስምምነት ለመድረስ ቁርጠኛ መሆኗን እስኪያረጋግጡ ድረስ የባሕር ኃይሉ የቴህራንን ወደቦችን ዘግቶ እንዲቆይ እንደሚፈልጉ ቢቢሲ መረዳት ችሏል።ያጋሩ, ኢራን ከአሜሪካ ጋር ወደፊት ስለሚኖራት ንግግር ከፓኪስታን ጋር ከተወያየች በኋላ እንደምትወስን ተዘገበ - 15 ሚያዚያ 2026የፓኪስታን ልዑካን ቡድን ቴህራን ደረሰ
የፎቶው ባለመብት,Government of Iranየምስሉ መግለጫ,የፓኪስታን ጦር አዛዥ አሲም ሙኒር ለኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰይድ አባስ አራግቺ ሰላምታ ሲሰጡአሜሪካን እና ቴህራንን እያሸማገለ የሚገኘው የፓኪስታን ልዑካን ቡድን ቴህራን ገባ።ከልዑካን ቡድኑ መካከል ከዚህ ቀደም ትራምፕ “የምወደው” ሲሉ የገለጿቸው ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር እና የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ሞሺን ናቅቪ እንደሚገኙበት በመንግሥታቱ ድርጅት የፓኪስታን ተልዕኮ መግለጫ ያስረዳል።ቀደም ሲል የኢራን መገናኛ ብዙኃን፣ ኢሪብ የዜና ወኪል የአሜሪካን መልዕክት ለማስተላለፍ እና ስለሁለተኛው ዙር ድርድር ለመነጋገር የልዑካን ቡድን ወደ ቴህራን እንደሚመጣ ዘግቦ ነበር።አሜሪካ እና ኢራን የመጀመርያውን ዙር ድርድር ባለፈው ሳምነት መጨረሻ ላይ በኢዝላማባድ ያደረጉ ሲሆን ያለምንም ውጤት ተጠናቅቋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሙሐማድ ሼህባዝ ሻሪፍ ሳዑዲ አረቢያ፣ ጂዳ ደርሰዋል።ጽህፈት ቤታቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገራት የተጓዙት “በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ ለመለዋወጥ” መሆኑን ገልጿል።ያጋሩ, የፓኪስታን ልዑካን ቡድን ቴህራን ደረሰ - 15 ሚያዚያ 2026ምን ያህል መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል አለፉ?
የፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ የኢራን ወደቦችን ሰኞ ዕለት ከዘጋች ጀምሮ 15 መርከቦች የሆርሙዝ ወሽመጥን አቋርጠዋል።ከእነዚህ መካከል ደግሞ ዘጠኙ ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው መሆኑን ቢቢሲ ቬሪፋይ የተመለከታቸው የመርከቦች እንቅስቃሴን የሚጠቁሙ መረጃዎች ጠቁመዋል።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንቲኮም) ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡም ሆነ የሚወጡ በሙሉ እገዳው ይመለከታቸዋል ብሏል።ከኢራን ወደቦች ውጪ የሚመጡም ሆነ የሚሄዱ መርከቦች ግን የመንቀሳቀስ ነጻነታቸው የተጠበቀ መሆኑን አክሏል።የመርከቦች እንቅስቀሴን መከታተያዎች ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው ስድስት መርከቦች በወሽመጡ በኩል ማለፋቸውን ያሳያሉ።የአሜሪካ ጦር በርካታ መርከቦች እንዲመለሱ ተደርገዋል ቢልም ቢቢሲ ከገለልተኛ ወገን ይህንን ማጣራት አልቻለም።ነገር ግን ቢያንስ አንድ መርከብ በወሽመጡ በኩል ሲያልፍ እንዲመለስ መደረጉን የመረጃ መከታተያዎቹ አሳይተዋል።በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለበት ሪች ስታሪ መርከብ ከዩኤኢው ሻርጃ ምሥራቃዊ ክፍል ተነስቶ በወሽመጡ በኩል ሲያልፍ እንዲመለስ የተደረገ ቢሆንም ረቡዕ ዕለት ግን በባህረ ሰላጤው እንዲያልፍ ተደርጓል።በተጨማሪም ሁለት የኢራንን ባንዲራ የሚያውለበልቡ መርከቦች እገዳው ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ ከኢራኑ ቻባሃራ ወደብ ተነስተው በሆርሙዝ ወሽመጥ ምሥራቃዊ ክፍል በኩል አልፈዋል።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ወቅት ዝርዝር መረጃ ሳይሰጡ የሆርሙዝ ወሽመጥ “እየተከፈተ ነው” ብለዋል።የኢራን ጦር አዛዥ አሊ አብዶላህ እገዳው ካልተነሳ “ማንኛውም የወጪ እና ገቢ ንግድ በፐርዢያ ባሕረ ሰላጤ፣ በኦማን ባሕር እና በቀይ ባሕር” እንዳያልፍ እንደሚያደርጉ ዝተዋል።ትራምፕ ከዚህ ቀደም አሜሪካ የኢራንን ባሕር ኃይል ማውደሟን ተናግረው የነበረ ቢሆንም አሁንም ግን በቀጣናው የሚደረግ የባሕር ጉዞ ላይ አደጋ መደቀኑ አልቀረም።ያጋሩ, ምን ያህል መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል አለፉ? - 15 ሚያዚያ 2026ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስለኢራን ጦርነት የሚሰጡት እርስ በእርሱ የሚጣረሰው መልዕክት
የፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ኢራኑ ጦርነት እና ስለሚያበቃበት መንገድ የሚናገሩት እርሱ በእርሱ የሚጣረስ ነው።ትራምፕ ከፎክስ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ላይ “የጦርነቱ ማብቂያ እየተቃረበ ነው” ብለዋል።አሜሪካ እና ኢራን ለሁለት ሳምንት የሚቆይ የተኩስ አቁም ተስማምተው ድርድር ጀምረዋል።ትራምፕ ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃለምልልስ ላይ ተጨማሪ የአየር ድብደባዎች ሊፈጸሙ እንደሚችሉም ተናግረዋል።“የአየር ድብደባውን አሁን ባቆም፤ አገሪቱን መልሶ ለመገንባት 20 ዓመት ይወስድባቸዋል፤ እና ደግሞ ገና አልጨረስንም” ሲሉ አክለዋል።“ምን እንደሚሆን እናያለን። ከስምምነት ለመድረስ በጣም የሚፈልጉ ይመስለኛል።”ትራምፕ የሁለት ሳምንቱ የተኩስ አቁም ይራዘም እንደሆን ሲጠየቁም እንዲሁ እርስ በእርሱ የሚጣረስ ምላሽ ሰጥተዋል።የፈረንሳይ የዜና ወኪል ግን አደራዳሪዎች የሁለት ሳምንቱ የተኩስ አቁም እንዲራዘም ለማድረግ እየተቃረቡ መሆኑን ዘግቧል።አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣን ደግሞ “አሜሪካ በይፋ የተኩስ አቁሙን ለማራዘም አልተስማማችል” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።“ዩኤስ እና ኢራን ከስምምነት ላይ ለመድረስ እየተነጋገሩ ነው” ሲሉም አክለዋል።ያጋሩ, ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስለኢራን ጦርነት የሚሰጡት እርስ በእርሱ የሚጣረሰው መልዕክት - 15 ሚያዚያ 2026አሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁሙን ለማራዘም እየተነጋገሩ ነው- ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣን
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣን ለሁለት ሳምንት የተቀመጠውን የተኩስ አቁም ለማራዘም ከኢራን ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን ለቢቢሲ ተናገሩ።በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት የሚያበቃው የሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ ሚያዝያ 14 2018 ዓ.ም. ነው።ባለሥልጣኑ “አሜሪካ የተኩስ አቁሙን ለማራዘም በይፋ አልተስማማችም” ሲሉ ተናግረዋል።“ከስምምነት ላይ ለመድረስ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ንግግር ቀጥሏል” ሲሉ አክለዋል።ቀድም ሲል ኤኤፍፒ የዜና ወኪል የኢራን መገናኛ ብዙኃንን ጠቅሶ የተኩስ አቁም መራዘሙ አልተረጋገጠም ብሎ ነበር።ያጋሩ, አሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁሙን ለማራዘም እየተነጋገሩ ነው- ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣን - 15 ሚያዚያ 2026ኢራን ከአሜሪካ ጋር መልዕክት መለዋወጥ መቀጠሏን ተናገረች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይ በቴህራን እና ዋሺንግተን መካከል የሚደረገው የመልዕክት ልውውጥ በአደራዳሪዋ ፓኪስታን በኩል “እንደቀጠለ መሆኑን” ተናገሩ።ባጋይ የኢራን አቋም “በቀጠለው ንግግር በግልጽ የተቀመጠ እና በድጋሚ የተገለጸ ነው” ብለዋል።አክለውም ኢራን ዛሬ “ምናልባትም” የፓሰኪስታን ልዑካንን ተቀብላ እንደምታስተናግድ ተናግረዋል።ልዑካኑ በኢዝላማባድ የተጀመረው ድርድር ቀጣይ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር እና “በኢራን እና አሜሪካ አቋሞች ላይ በዝርዝር ለመነጋገር” እንደሆነ አብራርተዋል።ባጋይ አሜሪካ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ መታጠቅ ትፈልጋለች ስትል የምታቀርበውን ክስ ውድቅ አድርገው የኒውክሌር ፕሮግራሟ “ሰላማዊ ነው” ብለዋል።ባጋይ “በፍላጎቶቿ ላይ በመመስረት [ዩራኒየም] ማበልጸጓን መቀጠል ይኖርባታል” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።ነገር ግን በማበልጸጉ ደረጃ እና ዓይነት ዙሪያ የመነጋገር ዕድል ሊኖር ይችላል” ብለዋል።ያጋሩ, ኢራን ከአሜሪካ ጋር መልዕክት መለዋወጥ መቀጠሏን ተናገረች - 15 ሚያዚያ 2026ትራምፕ ቻይና ለኢራን ጦር መሣሪያ ላለመላክ ተስማምታለች አሉ
የፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለቻይናው አቻቸው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ከጻፉ በኋላ “ለኢራን ጦር መሣሪያ ላለመላክ” መስማማታቸውን ተናገሩ።ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ “ቻይና የሆርሙዝ ወሽመጥን በቋሚነት በመክፈቴ ደስተኛ ናት። ይህንን የማደርገው ለእነርሱ ነው። እና ለመላው ዓለም” ሲሉ ጽፈዋል።“እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ዳግመኛ አይከሰትም። ለኢራን ጦር መሣሪያ ላለመላክ ተስማምተዋል” ሲሉ አክለዋል።“በብልሃት፣ በጥሩ ሁኔታ በጋራ እየሰራን ነው!! ያ ታዲያ ጦርነትን እንድናሸንፍ አያደርግም??? ነገር ግን አስታውሱ በመዋጋት ረገድ በጣም ጎበዞች ነን፤ መሆን ካለበት ከማንም በበለጠ [እንዋጋለን]!!!”ማክሰኞ ዕለት ቻይና የአሜሪካ ጦር የኢራንን ወደብ ለመዝጋት የወሰደው እርምጃ “ኃላፊት የጎደለው ነው” በማለት ኮንና የተኩስ አቁሙን “አደጋ ላይ ይጥላል” ብላ ነበር።አሜሪካ የኢራንን ወደቦችን ከዘጋች በኋላ በወሽመጡ በኩል ካለፉ ጥቂት መርከቦች መካከል የቻይና አንዱ ነው።የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማክሰኞ ዕለት በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ቻይና ለኢራን የአየር መቃወሚያ ለመስጠት እየተዘጋጀች ነው የሚለውን ዘገባ “ሙሉ በሙሉ የፈጠራ ወሬ” ሲሉ አጣጥለውታል።ያጋሩ, ትራምፕ ቻይና ለኢራን ጦር መሣሪያ ላለመላክ ተስማምታለች አሉ - 15 ሚያዚያ 2026በሲሪላንካ ለመቆየት የተገደዱት ከ200 በላይ የኢራን ባሕርተኞች ወደ አገራቸው ተመለሱ
የፎቶው ባለመብት,APየምስሉ መግለጫ,የኢራን ጦር መርከብ የሆነችው አይሪስ ዴና በቤንጋል የባሕር ዳርቻ ታይታ ነበርበአሜሪካ ጦር ጥቃት ተፈፅሞባቸው ከአንድ ወር በላይ ሲሪላንካ እንቆዩ የተገደዱ ከ200 በላይ የኢራን ባህርተኞች አገራቸው ገቡ።የሲሪላንካ ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ከአይሪስ ዴና ከምትባለው መርከብ 32 ባሕርተኞች እና አይሪንስ ቡሺሂር ከተባለችው መርከብ ደግሞ 206 ባሕርተኞች አገሪቱን ለቀው መውጣታቸውን አስታውቀዋል።የኢራን የጦር መርከብ የሆነችው አይሪስ ዴና ባለፈው ወር በአሜሪካ ሰርጓጅ መርከብ ከተመታች በኋላ 104 ባሕርተኞች ሲገደሉ፤ መርከቧ ደግሞ ከሲሪላንካ የባሕር ዳርቻ 40 ኪሎ ሜትር ላይ ሰምጣለች።ከዚህ ጥቃት ማግስት ደግሞ የሞተር ብልሽት የገጠማት አይሪንስ ቡሺሂር ተባለችው መርከብ በሲሪላንካ ፈቃድ ወደብ ላይ እንድትቆይ ተደርጓል።ምክትል ሚኒስትሩ ለሮይተርስ የዜና ወኪል የሁለቱም መርከቦች ባሕርተኞች ማክሰኞ ዕለት ወደ ኢራን መጓዛቸውን አረጋግጠዋል።በጥቃቱ የተገደሉ የ84 ኢራናዊያን ባሕርተኞች አስከሬን በቴህራን አመቻችነት ወደ ኢራን መመለሱ ይታወሳል።የመርከቡ ጥቃት አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን ላይ ጦርነት በከፈቱ በቀናት ውስጥ የተፈፀመ ሲሆን፤ ጥቃቱ የጦርነቱን ዓውድ እንዲሰፋ አድርጎታል።ያጋሩ, በሲሪላንካ ለመቆየት የተገደዱት ከ200 በላይ የኢራን ባሕርተኞች ወደ አገራቸው ተመለሱ - 15 ሚያዚያ 2026ኢራን የአሜሪካ የወደብ መዝጋት የሚቀጥል ከሆነ በባሕረ ሰላጤው፣ ቀይ ባሕር እና በኦማን የባሕር ወሽመጥ እርምጃ እወስዳለሁ ስትል ዛተች
የፎቶው ባለመብት,EPAየኢራን የካተን አል አብቢያን አዛዥ አሊ አብዶላሂ አሜሪካ እገዳዋን የምትቀጥል እንዲሁም “ለኢራን የንግድ እና የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ደኅንነት ስጋት የምትሆን ከሆነ” “የተኩስ አቁም ስምምነቱን የመጣስ የመጀመርያ እርምጃ” ይሆናል ብለዋል።የኢራን ኃይሎች “በፋርስ ባሕረ ሰላጤ፣ በኦማን ባሕር እና በቀይ ባሕር ማንኛውም የገቢ እና ወጪ ንግድ ምርቶች” መንቀሳቀሳቸውን እንዳይቀጥሉ እንደሚያደርጉ አክለው ተናግረዋል።አብዶላሂ የትኞቹ አገራት የወጪ እና ገቢ ንግዳቸው እንደሚጎዳ ያልገለጹ ሲሆን የጠቀሱት የባሕር ክፍል ግን ሰፊ አካባቢን ይሸፍናል።አሜሪካ የኢራን ወደቦችን የዘጋችው ከሰኞ ዕለት ጀምራ ነው።ረቡዕ ዕለት የአሜሪካ ጦር በ24 ሰዓታት ውስጥ “አንድም መርከብ እገዳውን አልፎ አልሄደም” ሲል አስታውቋል።በኦማን ባሕረ ሰላጤ ስድስት የንግድ መርከቦች እንዲመለሱ መደረጋቸውን ጨምሮ አስታውቋል።በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የተደረገው የመጀመርያ ዙር ድርድር ያለውጤት ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጣዩ ዙር በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ሊጀመር እንደሚችል ትራምፕ አስታውቀዋል።ኢራን ግን እስካሁን ድረስ ድርድሩ ስለመደረጉ ያለችው ነገር የለም።ያጋሩ, ኢራን የአሜሪካ የወደብ መዝጋት የሚቀጥል ከሆነ በባሕረ ሰላጤው፣ ቀይ ባሕር እና በኦማን የባሕር ወሽመጥ እርምጃ እወስዳለሁ ስትል ዛተች - 15 ሚያዚያ 2026የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሊባኖስ “ጠንካራ እርምጃ” እየወሰደ መሆኑን ገለጸ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የእስራኤል ጦር አገሪቱ ከሊባኖስ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ የአየር ድብደባ እየፈጸመ ይገኛልየእስራኤል መከላከያ በደቡባዊ ሊባኖስ “የአየር ድብደባ እያካሄደ” መሆኑን በመግለፅ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጠ፥።ጦሩ በዛሃራኒ ወንዝ ደቡባዊ አቅጣጫ “ከባድ እርምጃ” እየወሰደ መሆኑን ገልጾ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ አስጠንቅቋል።“በሄዝቦላህ አካባቢ የሚገኝ ማንኛውም አካል፤ በተቋማቸው ወይም የውጊያ ተሽከርካሪዎቻቸው አካባቢ፣ ሕይወቱን ለአደጋ ያጋልጣል” ሲል ባወጣው መግለጫ ላይ ጠቅሷል።እስራኤል እና ሊባኖስ ማክሰኞ ዕለት ከተነጋገሩ በኋላ ወደፊት በሚገለጽ ጊዜ እና ቦታ በቀጥታ ድርድር ለመጀመር መስማማታቸውን ተገልጿል።እስራኤል በበኩሏ በሊባኖስ የሚንቀሳቀሱ ሁሉንም መንግሥታዊ ያልሆኑ የሽብር ቡድኖችን ትጥቅ ማስፈታት እንደምትፈልግ ተናግራለች። ይህም የሄዝቦላህ ታጣቂዎችን ለማመልክት የተጠቀመችበት ነው።ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ እና የሰብአዊ ቀውሷን ለመፍታት እርምጃዎችን እንድትወስድ ጥሪ አቅርባለች።እስራኤል ግን ከዛሬ ማለዳ ጀምራ በሊባኖስ የአየር ድብደባ እያካሄደች መሆኑን የሚወጡ ዘገባዎች ያሳያሉ።ያጋሩ, የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሊባኖስ “ጠንካራ እርምጃ” እየወሰደ መሆኑን ገለጸ - 15 ሚያዚያ 2026ፕሬዝዳንት ፐዝሽኪያን ኢራንን ለማንበርከክ የሚደረግ ሙከራ እንደሚከሽፍ ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Iranian Presidency handout via Getty Imagesየኢራን ፕሬዝዳንት መሱድ ፐዝሽኪያን አሜሪካ እና እስራኤል ኢራንን በኃይል “ለማንበርከክ” የሚያደርጉት ማንኛውም ሙከራ እንደሚከሽፍ እና ቴህራን እንዲህ ዓይነት አማራጮችን መቼም እንደማትቀበል ተናገሩ።ከኢራን የአደጋ ጊዜ አገልግሎት ባለሥልጣናት ጋር የተነጋገሩት ፕሬዝዳንት ፐዝሽኪያን ቴህራን ጦርነት አሊያም አለመረጋጋትን አትፈልግም ብለዋል።በአንፃሩ “[ኢራን] ሁሌም ቢሆን ገንቢ ውይይቶች እና ከተለያዩ አገራት ጋር የመነጋገር አስፈላጊነትን ደጋግማ ገልፃለች” ሲሉም አክለዋል።በአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን የተላለፈው የፕሬዝዳንቱ ንግግር፤ ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ እና ኢራን ንግግር በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በፓኪስታን ኢዝላማባድ ይጀምራል ካሉ በኋላ የተሰማ ነው።በቅርብ ይጀመራል ስለተባለው ሁለተኛ ዙር ንግግር ቴህራን እስካሁን አስተያየት አልሰጠችም።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ፐዝሽኪያን ኢራንን ለማንበርከክ የሚደረግ ሙከራ እንደሚከሽፍ ተናገሩ - 15 ሚያዚያ 2026የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ከአሜሪካ እና ኢራን የኢዝላማባድ ንግግር በኋላ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኳታር እና ቱርክን ለመጎብኘት አቀኑ
የፎቶው ባለመብት,Reuterየምስሉ መግለጫ,የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በኢራን ጉዳይ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ሻሪፍን አነጋግረዋልየፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሻባዝ ሻሪፍ የመካከለኛው ምሥራቅ አገራትን እና ቱርክን ለመጎብኘት የአራት ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት መጀመራቸውን የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳዑዲ አረቢያ እና ኳታርን እንደሚጎበኙም ተገልጿል።ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የመጣው ኢዝላማባድ ሁለተኛ ዙር የአሜሪካ እና ኢራንን የሰላም ንግግር ለማዘጋጀት እየተሰናዳች ባለችበት ጊዜ ነው።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት ለኒው ዮርክ ፖስት ጋዜጠኛ “በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ በኢዝላማባድ የሆነ ነገር ይከሰት ይሆናል” ብለዋል።የጠቅላይ ሚኒስትር ሻቲፍ የሳዑዲ አረቢያ እና ኳታር ጉብኝት “በሁለትዮሽ አውድ” እንደሚካሄድ የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቱርክ በአንታላያ የዲፕሎማሲ ፎረም የሚሳተፉ ሲሆን፤ ከፎረሙ ጎን ለጎን ከቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲጵ ጣይፕ ኤርዶጋን እና ከሌሎች መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።ያጋሩ, የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ከአሜሪካ እና ኢራን የኢዝላማባድ ንግግር በኋላ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኳታር እና ቱርክን ለመጎብኘት አቀኑ
