
የአሜሪካ ኃይሎች የኢራንን መርከብ ከተቆጣጠሩ በኋላ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የተኩስ አቁሙን “ለበርካታ ጊዜያት” እየጣሰች ነው ሲሉ፣ ኢራን በበኩሏ አሜሪካ “የባሕር ላይ ውንብድና” እየፈጸመች ነው በማለት ከስሳለች።
ጭምቅ ሃሳብ
- ጦርነት እና የኢንተርኔት መቋረጥ የጎዳቸው ኢራናውያን
- “በእግድ ውስጥ ያለ እግድ”- አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣለችው የመርከቦች እንቅስቃሴ ክልከላ
- ቻይና ኢዝላማባድ የአሜሪካ እና ኢራን ውይይትን ለማመቻቸት የምታደርገውን ጥረት “ሙሉ በሙሉ እንደምትደግፍ” ገለጸች
- የቴህራን መገናኛ ብዙኃን ከኢራን ወደ ፓኪስታን የሄደ ልዑካን ቡድን እንደሌለ ዘገቡ
- ትራምፕ ከኢራን ወደቦች የሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የጣሉትን እገዳ መቼ ያነሳሉ?
- ትራምፕ ኢራን ያበለጸገችውን ዩራኒየም ማስወገድ “ረዥም እና አስቸጋሪ” ሂደት ነው አሉ
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 1 ሰአት በፊትኢራን ድርድር ውስጥ ከገባች “እጇ ከቃታው ላይ” እንደማይነሳ የመንግሥት ቃል አቀባይ ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Morteza Nikoubazl/NurPhoto via Getty Imagesኢራን ከአሜሪካ ጋር ድርድር የምታደርግ ከሆነ ንግግር ውስጥ የምትገባው “እጇን ቃታው ላይ” አድርጋ እንደሚሆን እና መከላከያ ኃይሏ “ሙሉ ዝግጁነት” እንደሚኖረው የአገሪቱ መንግሥት ቃል አቀባይ ተናገሩ።ከመንግሥታዊው ዜና ወኪል ‘ኢርና’ ጋር ቆይታ ያደረጉት ቃል አቀባይዋ ፋጤሜህ ሞሃጄራኒ ኢራን በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ በሚካሄደው ቀጣይ ዙር ድርድር ትሳተፍ እንደሆነ ማረጋገጫም ይሁን ማስተባበያ አልሰጡም።“ከፊት ለፊታችን ሁለት ስትራቴጂዎች አሉ። የመጀመሪያው የጦርነት ስትራቴጂ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ የዲፕሎማሲ ስትራቴጂ ነው” ሲሉ ለዜና ወኪሉ ተናግረዋል።የኢራን ተደራደሪ ቡድን “በብሔራዊ ጥቅም ላይ ቅንጣት እንኳ አያመቻምችም” ብለዋል።ቃል አቀባይዋ ይህንን የአገሪቱ መንግሥት አቋም የገለጹት ሁለተኛ ዙር ድርድር ይካሄድ እንደሆነ ማረጋገጫ ባልተገኘበት ሁኔታ ውስጥ ነው።ተደራዳሪ ልዑካቸውን ወደ ዛሬ ፓኪስታን እንደሚልኩ ያስታወቁት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ተደራዳሪዎቿን ወደ ፓኪስታን “ከመላክ ውጪ አማራጭ የላትም” ብለዋል።በነገው ዕለት የሚጠናቀቀውን የሁለት ሳምንት ተኩስ አቁም የማራዘም ፍላጎት እንደሌላቸውም አስታውቀዋል።ያጋሩ, ኢራን ድርድር ውስጥ ከገባች “እጇ ከቃታው ላይ” እንደማይነሳ የመንግሥት ቃል አቀባይ ተናገሩ - ከ 2 ሰአት በፊትትራምፕ፤ ኢራን ተደራዳሪዎቿን ወደ ፓኪስታን “ከመላክ ውጪ አማራጭ የላትም” አሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለሚደረገው ድርድር ልዑካኗን ወደ ፓኪስታን “ከመላክ ውጪ አማራጭ የላትም” በማለት ተናገሩ።በምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ የሚመራው የአሜሪካ ልዑክ ከኢራን ጋር ለሚደረግ ንግግር ዛሬ ወደ ፓኪስታን የሚጓዝ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ቴህራን ተደራዳሪዎቿን እንደምትልክ ማረጋገጫ አልሰጠችም።ከአሜሪካው የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲኤንቢሲ ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ የሚደረገው ድርድር “ከታላቅ ስምምነት ጋር ይጠናቀቃል” የሚል መተማመን እንዳላቸው ተናግረዋል።አሜሪካ “እየተጋፈጠች ያለችው ከጥሩ ሰዎች ጋር አይደለም” ያሉት ትራምፕ፤ ነገር ግን “ስኬታማ” ተግባር እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል። አሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ የጣለችውንም እገዳ “ታላቅ ስኬት” ሲሉ ጠርተውታል።አሜሪካ እና ኢራን ለሁለት ሳምንት እንዲቆይ የተስማሙት ተኩስ አቁም ነገ ረቡዕ ይጠናቀቃል። ከኢራን ጋር የሚደረገው ድርድር በጥሩ ሁኔታ የሚሄድ ከሆነ ተኩስ አቁሙን ያራዝሙት እንደሆነ የተጠየቁት ትራምፕ፤ “ያንን ማድረግ አልፈልግም” ሲሉ አቋማቸውን አሳውቀዋል።“የቦንብ ድብደባ እንደሚኖር እጠብቃለሁ፤ ምክንያቱም ጥሩ ባህሪ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።ስምምነት ላይ ለመድረስ “ብዙ ጊዜ” እንደሌለ የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ኢራኖች ከአሜሪካ ጋር የሚስማሙ ከሆነ “እጅግ ጥሩ ስፍራ ላይ ያርፋሉ” ብለዋል።ያጋሩ, ትራምፕ፤ ኢራን ተደራዳሪዎቿን ወደ ፓኪስታን “ከመላክ ውጪ አማራጭ የላትም” አሉ - ከ 3 ሰአት በፊትአሜሪካ እና ኢራን ሊያበቃ የተቃረበውን የተኩስ አቁም በመጣስ እየተካሰሱ ነው
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ ጋሊባፍ እና ፕሬዝዳንት ትራምፕአሜሪካ እና ኢራንን ለሁለት ሳምንታት የደረሱት የተኩስ አቁም ሊጠናቀቅ በተቃረበበት በአሁኑ ጊዜ ሁለቱ አገራት ተኩስ አቁሙን በመጣስ እየተካሰሱ ነው።የአሜሪካ ኃይሎች የኢራንን መርከብ ከተቆጣጠሩ በኋላ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የተኩስ አቁሙን “ለበርካታ ጊዜያት” እየጣሰች ነው ሲሉ፣ ኢራን በበኩሏ አሜሪካ “የባሕር ላይ ውንብድና” እየፈጸመች ነው ብላለች።ፕሬዝዳንቱ በትሩዝ ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አሜሪካ የምትፈጽመውን ጥቃት ያስቆመውን የተኩስ አቁም ኢራን በተደጋጋሚ ጥሳለች ሲሉ ከስሰዋል።ነገር ግን ትራምፕ ለዚህ ክሳቸው ምንም ዓይነት ማብራሪያም ሆነ ማጠናከሪያ አልሰጡም።ኢራንም በበኩሏ አሜሪካ የተደረሰውን የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም በተደጋጋሚ ጥሳለች ስትል ስከስስ ቆይታለች።በሆርሙዝ ወሽመጥ በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ ዕቀባን ሲጥሉ እና ሲያነሱ የቆዩት ሁለቱ አገራት በአካባቢው ያላቸውን የበላይነት ለማሳየት እየጣሩ ነው።የአሜሪካ ባሕር ኃይል በሆርሙዝ ላይ የተጣለውን እገዳ የጣሰ ነው ባሉት የኢራን መርከብ ላይ መተኮሳቸውን ተከትሎ የኢራን ጦር ኃይል ለአሜሪካ “ወደታራዊ የባሕር ላይ ውንብድና” ለላው ጥቃት አጸፋ እንደሚመለስ ዝቷል።ጨምሮም አሜሪካ በሆርመዝ ወሽመጥ ላይ በኢራን መርከቦች ላይ እየወሰደችው ያለው እርምጃ “የተኩስ አቁም ስምምነቱን የሚጥስ ነው” በማለት ከስሷል።ያጋሩ, አሜሪካ እና ኢራን ሊያበቃ የተቃረበውን የተኩስ አቁም በመጣስ እየተካሰሱ ነው - ከ 6 ሰአት በፊትጦርነት እና የኢንተርኔት መቋረጥ የጎዳቸው ኢራናውያን
የፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በኢራን የምግብ ዋጋ በእጥፍ ጨምሯልበኢራን ውስጥ የእስላማዊ ሪፐብሊኩ ደጋፊዎች ሳይቀር ለማይቀረው የምጣኔ ኃባት ፈተና ቀበቷቸውን እያጠበቁ ነው።ጥያቄው የኢራን መንግሥት የሆርሙዝ ወሽመጥ ተዘግቶ የሚቀጥል ከሆነ ለሠራተኞቹ ደመወዝ መክፈል ይችላል? የሚለው ነው። ቴህራን ከውይይት መድረክ ራሷን አርቃስ መቆየት ትችላለች?ከጦርነቱ በፊት የኢራንን ምጣኔ ኃብት ማዕቀብ፣ የዋጋ ግሽበት እንዲሁም የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ፈትኖታል።ቤተሰቦች አቅማቸው ተሟጥጦ መሠረታዊ ነገሮች ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ሆነዋል።አሁን በጦርነቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ንግዶች ከፔትሮኬሚካል፣ ስቲል እና አሉሚኒየም ኢንዱስትሪዎች መውደም ጋር ተያይዞ የምጣኔ ኃብት ቀውሱ ጫና ተባብሷል።ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በኢራን የምግብ ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል፤ በተጨማሪም ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶችም ቀንሰዋል።የኢራን የገንዘብ ምንዛሬ በመውደቁም ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት ተከስቷል።የኢራን ባለሥልጣናት እስራኤል እና አሜሪካ በአገሪቱ ላይ የከፈቱትን ጦርነት ተከትሎ የደረሰውን የምጣኔ ኃበት ጫና 270 ቢሊዮን ዶላር እንደሚገመት አስታውቀዋል።የምጣኔ ኃብቱ ጫና በተለይ አነስተኛ የኦንላየን ንግዶችን የሚሰሩ ሴቶች ላይ የበረታ ነው።የኢንተርኔት መቋረጥ የእደ ጥበብ ውጤቶችን እየሰሩ በማኅበራዊ ሚዲያ እና ኦንላየን የሚሸጡ በርካታ ሴቶችን ከገበያ በማስወጣት እነርሱን እና ቤተሰቦቻቸውን ባዶ እጃቸውን አስቀርቷል።ጦርነት እና የኢንተርኔት መቋረጥ የመሠረተ ልማት ውድመት ብቻ ሳይሆን በመላው ኢራን የበርካቶችን ቤት ያንኳኳ ችግር አስከትሏል።ያጋሩ, ጦርነት እና የኢንተርኔት መቋረጥ የጎዳቸው ኢራናውያን - ከ 6 ሰአት በፊት“በእግድ ውስጥ ያለ እግድ”- አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣለችው የመርከቦች እንቅስቃሴ ክልከላ
የፎቶው ባለመብት,EPAበሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚደረገውን የመርከቦች እንቅስቃሴ ከጦርነት በፊት ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚደረገው ጥረት እንዲሁም ከኢራንን ጥቃት እና ቁጥጥር ጋር የሚደረገው ትግል የአሜሪካ ቀዳሚ ተግባር ነው።የቀድሞው የብሪታኒያ ባሕር ኃይል አዛዥ ኮማንደር ቶም ሻርፕ ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የራሷን ገደቦች ጥላ እያለ፣ አሜሪካ ደግሞ ወደ ቴህራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን መከልከሏን በመጥቀስ፣ እየተከተለች ያለውን ስልት “በእግድ ላይ እግድ” ሲሉ ገልጸውታል።ዋይት ሐውስ ኢራን ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንድትመጣ ለማድረግ “በቂ ጉዳት” ለመፍጠር እየተሞከረ ነው ሲሉ ይናገራሉ።“የኢራንን የነዳጅ ምርት ከኢራን እንዳይወጣ በመከላከል ጉዳቱ ወደ ድርድር ጠረጴዛ ላይ እንዲመጡ እንዲያደርጋቸው ነው? የጉዳቱ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ለማየት አስቸጋሪ ነው፤ እያየነው ያለን አይመስለኝም” ብለዋል።ሻርፕ የኢራን አገዛዝ ከፍተኛውን ጉዳት ተቀብሎ ለማስተናገድ ፈቃደኛ መሆኑን እያሳየ ነው ሲሉ ይሞግታሉ።”ከእስላማዊ ሪፐብሊክ ርዕዮተ ዓለም የበለጠ አንድም ግለሰብ፣ መንግሥት፣ ኢኮኖሚ፣ ወይም ጠቃሚ መሠረተ ልማት የለም፤ እና ይህ ከዩኤስ ጋር ያለው ፍጥጫ ገና ከጅምሩ ሲዘጋጅበት የነበረው ነው።”ከዚያም ባሻገር የኢራን ባለሥልጣናት በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ላይ ያላቸውን “ሉዓላዊነት” እውቅና ሊሰጠው ይገባል ሲሉ አጥብቀው ይጠይቃሉ።ዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያዎችን የማስተጓጎል ችሎታቸው ጠንካራ ስልት እንደሆነ እና እንዲያውም ትርፋማ መንገድ መሆኑን ተምረዋል የሚሉት ቶም ሻርፕ፣ መርከቦች ደህንነታቸው ተጠብቆ ለማለፍ ቀረጦችን ለማስከፈል ወስነዋል ይላሉ።እንደ ባሕር ኃይሉ ገለጻ ከሆነ ያንን ስልት ለመተው ፈቃደኛ የሆነ ማንኛውም የኢራን ተደራዳሪዎች ማየት ከባድ ነው።ያጋሩ, “በእግድ ውስጥ ያለ እግድ”- አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣለችው የመርከቦች እንቅስቃሴ ክልከላ - ከ 6 ሰአት በፊትቻይና ኢዝላማባድ የአሜሪካ እና ኢራን ውይይትን ለማመቻቸት የምታደርገውን ጥረት “ሙሉ በሙሉ እንደምትደግፍ” ገለጸች
የፎቶው ባለመብት,Pakistan Ministry of Foreign Affairs via Xየምስሉ መግለጫ,የፓኪስታን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢስሃቅ ዳር በፓኪስታን የቻይና አምባሳደር ጂያንግ ዛይዶንግ ጋር ሲወያዩበፓኪስታን የቻይና አምባሳደር ኢዝላማባድ፣ አሜሪካ እና ኢራን ወደ ውይይት ጠረጴዛ እንዲመጡ የምታደርገውን ጥረት ቤይጂንግ “ሙሉ በሙሉ እንደምትደግፍ” ገለፁ።የፓኪስታን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢስሃቅ ዳር ከጂያንግ ዛይዶንግ ጋር በአካባቢው ስላለው ሁኔታ መወያየታቸው ተገልጿል።በስብሰባው ወቅት፣ ዛይዶንግ ፓኪስታን በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል “በቀጣናው እና ከዚያም ባሻገር ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ” ፓኪስታን የምታደርገውን ቀጣይ ጥረት ማድነቃቸውን የፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።ያጋሩ, ቻይና ኢዝላማባድ የአሜሪካ እና ኢራን ውይይትን ለማመቻቸት የምታደርገውን ጥረት “ሙሉ በሙሉ እንደምትደግፍ” ገለጸች - ከ 7 ሰአት በፊትየቴህራን መገናኛ ብዙኃን ከኢራን ወደ ፓኪስታን የሄደ ልዑካን ቡድን እንደሌለ ዘገቡየኢራን መገናኛ ብዙኃን በቴሌግራም ገጻቸው ላይ እስካሁን ድረስ ከአሜሪካ ጋር ለሚደረገው ድርድር ወደ ኢዝላማባድ የሄደ ልዑክ አለመኖሩን አስታወቁ።መገናኛ ብዙኃኑ “ዋነኞቹም ሆኑ ወይም በሁለተኛ ደረጃ ያሉት አልያም የመጀመርያውም ሆነ ተከታይ ቡድን እስካሁን ድረስ ወደ ኢዝላማባድ የሄደ የልዑካን ቡድን የለም” ብለዋል።ከዚህ በተጨማሪ በቴሌግራም ገጹ ልጥፍ ላይ የልዑካን ቡድኑ መነሳት ወይም መድረስን አስመልክቶ “በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን እና የቀጣናው ምንጮች” የተናፈሰው “ወሬ” ውድቅ ተደርጓል።የመገናኛ ብዙኃኑ ዘገባ በፓርላማ አፈ ጉባዔ ሞሐመድ ባጋር ጋሊባፍ እንዲሁም ሌሎች የኢራን ባለሥልጣናት የተባለውን ዳግም በማስተጋባት ቴህራን “በስጋት ጥላ ውስጥ ሆና ድርድርን አትቀበልም” ብለዋል።ያጋሩ, የቴህራን መገናኛ ብዙኃን ከኢራን ወደ ፓኪስታን የሄደ ልዑካን ቡድን እንደሌለ ዘገቡ
- ከ 7 ሰአት በፊትትራምፕ ከኢራን ወደቦች የሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የጣሉትን እገዳ መቼ ያነሳሉ?
የፎቶው ባለመብት,US Central Command/Xአሜሪካ ከቴህራን ጋር ስምምነት እስኪደረስ ድረስ በኢራን ወደቦች ላይ የጣለችውን እገዳ እንደማታነሳ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ።ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት ጦርነቱን ለማስቆም ያስችላል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ሁለተኛ ዙር ድርድር ስለመካሄዱ እርግጠኛ መሆን ባልተቻለበት ወቅት ነው።ትራምፕ ከአንድ ሳምንት በፊት ጀምሮ ተግባራዊ ያደረጉት እገዳ “ኢራንን ሙሉ በሙሉ እያወደመ ነው” ሲሉ በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ድረ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።ትራምፕ አክለውም አገራቸው ጦርነቱን “በብዙ መልኩ እያሸነፈች ነው” ብለዋል።ይህ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተያየት የተሰማው አሜሪካ እና ኢራን ያደረጉት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ብቻ በቀሩበት ወቅት ነው።ነገር ግን በፓኪስታን ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር ስለመካሄዱ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም።ትራምፕ ኢራን እስከምትስማማ ድረስ በሆርሙዝ ላይ የጣሉትን እገዳ እንደማያነሱ አስታወቁያጋሩ, ትራምፕ ከኢራን ወደቦች የሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የጣሉትን እገዳ መቼ ያነሳሉ? - ከ 8 ሰአት በፊትትራምፕ ኢራን ያበለጸገችውን ዩራኒየም ማስወገድ ”ረዥም እና አስቸጋሪ” ሂደት ነው አሉ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን የበለጸገውን ዩራኒየም ማውጣት ከባድ መሆኑን በማኅበራዊ ሚደያ ገጻቸው ላይ ተናገሩ።“ዘመቻ ሚድናየት ሃመር የተሟላ እና ሙሉ በሙሉ የኢራንን አቧራማ የኒውክሌር ተቋማት ያወደመ ነበር። ስለዚህ ቆፍሮ ማውጣት ረዥም እና አስቸጋሪ ሂደት ነው” ሲሉ ጽፈዋል።ዘመቻ ሚድ ናይት ሐመር አሜሪካ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር በኢራን ላይ የፈጸመችው ድብደባ መጠሪያ ሲሆን 125 የአሜሪካ ጦር አውሮፕላኖች ተሳትፈውበታል።የአሜሪካ ጦር አውሮፕላኖች የደበደቧቸው ሦስት የኢራን የኒውክሌር ተቋማት ፎርዶ፣ ናታንዝ እና ኢስፋሃን ናቸው።ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፋቸው ላይ “ሐሰተኛው ሲኤንኤን እና ሌሎች ብልሹ የመገናኛ ብዙኃኖች የጦር አውሮፕላን አብራሪዎቻችን የሚገባቸውን ክብር ሳይሰጧቸው ቀርተዋል፤ ሁልጊዜም ማንኳሰስ እና ማንቋሸሽ- ተሸናፊዎች።”ያጋሩ, ትራምፕ ኢራን ያበለጸገችውን ዩራኒየም ማስወገድ ”ረዥም እና አስቸጋሪ” ሂደት ነው አሉ - ከ 8 ሰአት በፊትአሜሪካ እና ኢራን ለሁለተኛው ዙር ድርድር ስለመገናኘታቸው እርግጠኛ መሆን ያልተቻለው ለምንድን ነው?
የፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ እና ኢራን በኢዝላማባድ ለሚያደርጉት ውይይት ዝግጅቶች ተጠናቅቀዋል።በዋና ከተማው ውስጥ መኪኖች ሲንቀሳቀሱ ይፈተሻሉ። በጎዳናዎቹ ግራ እና ቀኝ “ኢዝላማባድ ቶክስ” የሚሉ ፖስተሮች ተለጥፈዋል። ነገር ግን በሁለቱ አገራት መካከል ንግግሩ ስለመካሄዱ ማንም እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይችልም።ዋይት ሐውስ በጄዲ ቫንስ የሚመራ የአሜሪካ ልዑክ ወደ ፓኪስታን እንደሚሄድ ቢናገርም፣ ጊዜው ግን ግልጽ አልተደረገም።የልዑካን ቡድኑ ኢዝላማባድ መድረስ ቢኖርበትም ሰኞ ዕለት ግን ከዋሽንግተን እንዳልተንቀሳቀሰ ማወቅ ተችሏል።በትክክል እየሆነ ያለውን በግልጽ ማወቅ ያልተቻለው ኢራን መሳተፏን በይፋ ማሳወቅ ስላልፈለገች ይመስላል።በምትኩ በመግለጫቸው ውስጥ አሁንም ቁጣና እልህ አለ።የኢራንን ልዑክ ይመራሉ ተብለው የሚጠበቁት የአገሪቱ የፓርላማ አፈ ጉባኤ መሐመድ ባገር ጋሊባፍ ኢራን “በማስፈራራት ጥላ ስር ሆና ድርድርን አትቀበልም” ሲሉ ተናግረዋል።ዶናልድ ትራምፕንም “ከበባ በመክፈት እና የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ” ከስሰዋል።አፈ ጉባዔው እየጠቀሱ ያሉት በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የተፈጠሩ ክስተቶችን ነው። አሜሪካ የኢራንን ባንዲራ የሚያውለበልብ የጭነት መርከብ በቁጥጥር ስር ማዋሏን እንዲሁም የኢራንን ወደቦች መዝጋቷን እየተቃወሙ ይገኛሉ።በኢራን ውስጥ ያሉ ወታደራዊ አመራሮች ጋሊባፍን ከዲፕሎማሲ ይልቅ ጦርነትን እንዲመርጡ ግፊት እያደረጉ ይገኛሉ።ከመጋረጃ ጀርባ ደግሞ በኢራን ውስጥ የሚደረግ የሥልጣን ሽኩቻ ለመዘግየቱ የሚጠቀስ ሌላ ምክንያት ነው።በርካቶች ጉምቱ አመራሮቿ የተገደሉባት ኢራን ውስጥ የአገሪቱን ሥልጣን በበላይነት ለመቆጣጠር በሚፈልጉ የተለያዩ አካላት ሽኩቻ መፈጠሩ አይቀሬ ነው።በይፋ የምንሰማው አብዛኛው ነገር የፖለቲካ ድንፋታ ሊሆን ይችላል። እናም ባለሥልጣናት የሚሉት ምንም ይሁን ምን ኢራን ወደ ኢዝላማባድ ለመጓዝ እየተዘጋጀች ሊሆን ይችላል።ነገር ግን ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው የተኩስ አቁም ከማብቃቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ መሆኑ የበለጠ አሳሳቢ ያደርዋል።ስለዚህ የሰላም ውይይቱ በእርግጥ ይካሄድ እንደሆነ ማወወቅ ለማንም አዳጋች ነው።ያጋሩ, አሜሪካ እና ኢራን ለሁለተኛው ዙር ድርድር ስለመገናኘታቸው እርግጠኛ መሆን ያልተቻለው ለምንድን ነው? - ከ 9 ሰአት በፊትየቻይናው ፕሬዚዳንት በሆርሙዝ ወሽመጥ መደበኛው እንቅስቃሴ መመለስ አለበት አሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚደረግ የመርከቦች “መደበኛ እንቅስቃሴ”፤ “መመለስ ይኖርበታል” አሉ።ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት ከሳዑዲ አረቢያው ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን ጋር ሰኞ ዕለት በስልክ በተወያዩበት ወቅት ነው።ትራምፕ እና ዢ በቻይና በግንቦት ወር አጋማሽ ላይ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘዋል።ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች ለመገናኘት ቀን ከቆረጡ በኋላ በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የተነሳ ወደ ግንቦት አራዝመውታል።ያጋሩ, የቻይናው ፕሬዚዳንት በሆርሙዝ ወሽመጥ መደበኛው እንቅስቃሴ መመለስ አለበት አሉ - 21 ሚያዚያ 2026ኢራን ለውጊያው “አዲስ ስልት” እያዘጋጀች መሆን ገለጸች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ በኤክስ ገጸቸው ላይ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ኢራን “በውጊያ ሜዳ ላይ አዲስ ስልት ለማሳየት እየተዘጋጀች ነው” በማለት “በስጋት ጥላ ስር ሆነን ድርድርን አንቀበለም” አሉ።ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ከኢራን ጋር ከስምምነት ለመድረስ ጫና ውስጥ አለመሆናቸውን በመግለጽ አስተባብለዋል።የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ማክሰኞ ዕለት ወደ ፓኪስታን ይሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።ትራምፕ ከኢራን ጋር የተደረሰው እና ረቡዕ ዕለት የሚያበቃው የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም የመቀጠል ዕድሉ በጣም ጠባብ መሆኑን ጨምረው አስታወቀዋል።አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የኢራንን ወደቦች መዝጋቷን የቀጠለች ሲሆን እሁድ ዕለት የአገሪቱን ባንዲራ የሚያውለበልብ የጭነት መርከብን በቁጥጥር ስር ካዋለች ወዲህ ሁለቱም አገራት እርስ በእርስ የተኩስ አቁሙን በመጣስ ተወነጃጅዋል።በእስራኤል እና በሊባኖስ መካከል የሚደረገው ሁለተኛ ዙር ውይይት ሐሙስ ዕለት እንደሚጀመር የአሜሪካ ባለሥልጣን ተናግረዋል።ያጋሩ, ኢራን ለውጊያው “አዲስ ስልት” እያዘጋጀች መሆን ገለጸች - 21 ሚያዚያ 2026ትራምፕ የተኩስ አቁሙ ከማብቃቱ በፊት ከስምምነት ላይ ለመድረስ “ጫና ውስጥ” ናቸው መባሉን አስተባበሉ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesዶናልድ ትራምፕ የቀደሙት የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ካደረጓቸው ስምምነቶች “በእጅጉ የተሻለ” ስምምነት ከኢራን ጋር ሊያደርጉ መሆኑን ተናገሩ።ከኢራን ጋር “በአንጻራዊነት በፍጥነት” ከስምምነት ላይ እንደሚደርሱ የተናገሩት ትራምፕ፣ የተኩስ አቁሙ ከማብቃቱ በፊት ስምምነት ለመፈረም “ጫና ውሰጥ” ናቸው የሚለውን አስተባብለዋል።ፕሬዚደንት ትራምፕ አሜሪካ፣ ዩኬ፣ ፈረንሳይ፣ ቻይና፣ ሩሲያ አና ጀርመን እአአ በ2015 ከኢራን ጋር የደረሱትን ስምምነት በተደጋጋሚ በመተቸት ይታወቃሉ።ትራምፕ ይህንን “ከአገራችን ደህንነት ጋር ግንኙነት ካላቸው በጣም መጥፎ ስምምነቶች ውስጥ አንዱ ነው” ሲሉ ከተቹ በኋላ “የተረጋገጠ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ መንገድ ነው” በማለት “የማይሆን፤ ሊሆን የማይችል ነው” ሲሉ አጣጥለውታል።ትራምፕ በመጀመሪያ የሥልጣን ዘመናቸው አሜሪካን ከስምምነቱ አስወጥተዋል።ውሉን ባያቋርጡ ኖሮ “በእስራኤል እና በመላው መካከለኛው ምሥራቅ” የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ጥቅም ላይ ይውል እንደነበር ተናግረዋል።በሌላ የማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፋቸው ላይ ደግሞ ከኢራን ጋር “በአንጻራዊት በፍጥነት” ከስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ተናግረዋል።አክለውም ከስምምነት ለመድረስ “ጫና ውስጥ” አለመሆናቸውን “ያ ስህተት ነው” በማለት አስተባብለዋል።ያጋሩ, ትራምፕ የተኩስ አቁሙ ከማብቃቱ በፊት ከስምምነት ላይ ለመድረስ “ጫና ውስጥ” ናቸው መባሉን አስተባበሉ - 21 ሚያዚያ 2026የቴህራን ሁለት አውሮፕላን ማረፊያዎች መንገደኞችን ማስተናገድ ጀመሩ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesሁለት የቴህራን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዎች መንገደኞችን እንዲያስተናግዱ ፈቃድ ተሰጣቸው።ኢማም ኾሜኒ እና መህራባድ አውሮፕላን ማረፊያዎች ከዛሬ ጀምሮ መንገደኞችን እንዲያስተናግዱ መፈቀዱን የገለጸው የአገሪቱ ሲቪል አቪየሽን ነው።መህራባድ አውሮፕላን ማረፊያ በቅርቡ በተደረገው ጦርነት ጥቃት የደረሰበት ሲሆን እስራኤል በርካታ አውሮፕላኖችን “ማውደሟን” ገልጻ ነበር።የአገሪቱ ሲቪል አቪየሽን ሌሎች አስር አውሮፕላን ማረፊያዎች ከቅዳሜ ጀምሮ መንገደኞችን ማስተናገድ እንደሚችሉ ተናግሯል።ያጋሩ, የቴህራን ሁለት አውሮፕላን ማረፊያዎች መንገደኞችን ማስተናገድ ጀመሩ - 20 ሚያዚያ 2026የኢራኑ ፕሬዚዳንት ‘ኢራን ለኃይል አትንበረከክም’ አሉ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራኑ ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን አገራቸው ከአሜሪካ ጋር በሁለተኛው ዙር ድርድር መሳተፏ ባልተረጋገጠበት ወቅት “ኢራናውያን ለኃይል አይንበረከኩም” አሉ።ኢራን በአሜሪካ መንግሥት ላይ “ጥልቅ ታሪካዊ አለመተማመን” እንዳላት የገለፁት ፕሬዚዳንቱ “የተገቡ ቃሎችን ማክበር”፤ “ትርጉም ላለውውይይት መሠረት መሆን አለበት” ብለዋል።ፔዜሽኪያን በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት “ከአሜሪካ ባለሥልጣናት የሚመጡ ገንቢ ያልሆኑ እና የሚቃረኑ ምልክቶች መራራ መልእክት ያስተላልፋሉ፤ ኢራን እጇን እንድትሰጥ ይፈልጋሉ” ብለዋል።ያጋሩ, የኢራኑ ፕሬዚዳንት ‘ኢራን ለኃይል አትንበረከክም’ አሉ - 20 ሚያዚያ 2026አሜሪካ በሆርሙዝ እገዳ ከጣለች ጊዜ ጀምሮ 27 መርከቦችን መከለከሏን አስታወቀች
የፎቶው ባለመብት,EUROPEAN UNION/COPERNICUS SENTINEL-2/Handout via Reutersየአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ ላይ እገዳውን ከጣለ ጊዜ ጀምሮ 27 መርከቦች ወደ ኢራን ወደብ እንዳይሄዱ ወይንም እንዲመለሱ ማድረጉን አስታወቀ።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በኤክስ ገጹ ለይ ባሰፈረው ቪዲዮ ግዙፍ መርከቦች ክልከላው ወደታጠለበት የውሃ ክልል መግባታቸውን ሲነገራቸው ይደመጣል።በዚህ ወር መጀመርያ ላይ የአሜሪካ ባህር ኃይል ቴህራን ከነዳጅ ሽያጭ የምታገኘውን ትርፍ ለማስቆም በሚል ወደ ወደቦቿ የሚገቡም ሆነ ከወደቦቿ የሚወጡ መርከቦች ላይ እግድ እንደሚጥል አስታውቆ ነበር።ያጋሩ, አሜሪካ በሆርሙዝ እገዳ ከጣለች ጊዜ ጀምሮ 27 መርከቦችን መከለከሏን አስታወቀች - 20 ሚያዚያ 2026የሊባኖሱ ፕሬዚዳንት ከእስራኤል ጋር የሚኖረው ድርድር ከአሜሪካ እና ኢራን ውይይት “የተለየ” መሆኑን ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን ከእስራኤል ጋር የሚደረጉ ድርድሮች ከአሜሪካ እና ኢራን የሰላም ድርድር “የተለዩ” መሆናቸውን ገለጹ።አውን በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ሊባኖስ በቀጣይ በሚኖሩ ውይይቶች በአሜሪካ የቀድሞ የሊባኖስ አምባሳደር በነበሩት ሲሞን ካራም በሚመራ ልዑካን ቡድን እንደምትወከል ተናግረዋል።ከዚህ ቡድን ውጪ አገሪቱን የሚወክል ሌላ ተደራዳሪ እንደሌለ እንዲሁም በሌላ እንደማይተካ ጨምረው አብራርተዋል።የውይይቱ ዓላማዎች “ጥቃቶችን ማስቆም”፣ እስራኤል “በደቡባዊ ሊባኖስ አካባቢዎች የምትፈጽመውን ወረራ” ማስቆም እንዲሁም የሊባኖስን ጦር “በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባለው የአገሪቱ ደቡባዊ ድንበር” ላይ ማሰማራት እንደሆነ ተናግረዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሊባኖስን ጥያቄዎች “ሙሉ በሙሉ መረዳታቸውን” ገልጸዋል ያሉት አውን፣ እንዲሁም በቅርቡ የሚደረጉ ድርድሮችን በማመቻቸት ረገድ እገዛ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።በተጨማሪም “ሊባኖስን ማዳን እንደምንችል ተስፋ አለኝ” ሲሉ ተናግረዋል።በሁለቱ አገራት መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት መደረጉ ቢገለጽም ቤንያሚን ኔታንያሁ የእስራኤል ወታደሮች ወደ ደቡባዊ ሊባኖስ 10 ኪ.ሜ. ዘልቀው በመግባት እንደሚቆዩ ተናግረዋል።ያጋሩ, የሊባኖሱ ፕሬዚዳንት ከእስራኤል ጋር የሚኖረው ድርድር ከአሜሪካ እና ኢራን ውይይት “የተለየ” መሆኑን ተናገሩ - 20 ሚያዚያ 2026በመካከለኛው ምሥራቅ ያሉት ሁለት የተኩስ አቁሞች ምን ይመስላሉ?
የፎቶው ባለመብት,Reutersበአሁኑ ሰዓት በመካከለኛው ምሥራቅ ሁለት የተኩስ አቁሞች አሉ። አንዱ ሊባኖስ እና እስራኤል መካከል የተደረሰ ሲሆን ሌላው ደግሞ አሜሪካ ከኢራን ጋር የገባችው የተኩስ አቁም ነው።ኢራን እና አሜሪካለሁለት ሳምንት ያህል እንደሚቆይ የተገለጸው ይህ የተኩስ አቁም የሚያበቃው ረቡዕ ዕለት ነው።የዩናይትድ ስቴትስ ባህር ኃይል በኦማን ሰላጤ ላይ የኢራንን ባንዲራ በምታውለበልብ መርከብ ላይ ተኩስ ከፍቶ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ የኢራን ጦር አሜሪካን “በተኩስ አቁም ጥሰት” ወንጅሏታል።ዛሬ በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢዝላማባድ በሁለቱ አገራት መካከል ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ሁለተኛ ዙር ውይይት እስካሁን ድረስ ስለመካሄዱ በእርግጠኝነት መናገር አልተቻለም።የአሜሪካ ልዑካን ቡድንን የሚመሩት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጄዲ ቫንስ ሲሆኑ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ግን በድርድሩ ላይ ለመሳተፍ “እቅድ የለንም” ብለዋል።ሊባኖስ እና እስራኤልበሁለቱ አገራት መካከል የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተግባራዊ መሆን የጀመረው አርብ ዕለት ሲሆን ለአስር ቀን የሚቆይ ነው።ስምምነቱ የተደረሰው በሊባኖሱ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ አውን እና በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚነሲእትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መካከል ነው።ሁለቱ አገራት አሜሪካ ተጨማሪ የቀጥታ ድርድሮችን እንድታመቻች መጠየቃቸው ተገልጿል።የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ዝርዝር መረጃ ሊባኖስ ሄዝቦላህ እና ሌሎች ”ከመንግሥት ውጭ የሆኑ ታጣቂ ቡድኖች” በእስራኤል በሚገኙ ዒላማዎች ላይ ጥቃት እንዳይፈጽሙ ለማድረግ “ተጨባጭ እርምጃዎችን” መውሰድ አለባት።ሄዝቦላህ የተኩስ አቁሙን ለማክበር ፈቃደኛ መሆኑን የገለጸ ቢሆንም “የእስራኤል ወታደሮች እንዳይንቀሳቀሱ” የሚለው በስምምነቱ ውስጥ መካተት አለበት ሲል ጠይቋል።ያጋሩ, በመካከለኛው ምሥራቅ ያሉት ሁለት የተኩስ አቁሞች ምን ይመስላሉ? - 20 ሚያዚያ 2026የኢራን ፕሬዝዳንት “ውጥረትን ለመቀነስ እያንዳንዱ የዲፕሎማሲ መንገድ ጥቅም ላይ መዋል አለበት” አሉ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን “ጦርነት ለማንም አይጠቅምም፤ ምንም እንኳን ከሚደርሰው ማስፈራሪያ በተቃራኒ በጽናት ብንቆምም፣ እያንዳንዱ ምክንያታዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ውጥረትን ለመቀነስ ጥቅም ላይ መዋል አለበት” አሉ።ፔዜሽኪያን ዛሬ የአገራቸውን ፍትህ ሚኒስቴር በጎበኙበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ኢራናውያን “ስለ አገሪቱ እውነታዎች መረጃ ማግኘት አለባቸው” ያሉ ሲሆን “የተሳሳቱ መረጃዎችን ወይም ከእውነታው የራቁ ተስፋዎችን መስጠት ችግሮችን ለመፍታት እንዳንችል ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሕዝብን እምነትም ያሳጣል” ብለዋል።”ስኬቶቹም ሆኑ ተግዳሮቶቹ ለሕዝብ በሐቅ መነገር አለባቸው” ሲሉ ፔዜሽኪያን ተናግረዋል።ቀደም ሲል የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቴህራን በሚቀጥለው ዙር ውይይት ላይ ለመገኘት “ምንም ዓይነት እቅድ እንደሌለ” ተናግረው ነበር።ያጋሩ, የኢራን ፕሬዝዳንት “ውጥረትን ለመቀነስ እያንዳንዱ የዲፕሎማሲ መንገድ ጥቅም ላይ መዋል አለበት” አሉ - 20 ሚያዚያ 2026ፓኪስታን፣ ቴህራን እና ዋሺንግተን ለሚያደርጉት ቀጣይ ዙር ድርድር “የጸጥታ ሁኔታው መጠናከሩን” አስታወቀች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የፓኪስታን የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ሞሺን ናቅቪየፓኪስታን የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ሞሺን ናቅቪ ከኢራን አምባሳደር ሬዛ አሚሪ ሞጋህዳም ጋር ተገናኝተው በኢዝላማባድ በሚደረገው ሁለተኛ ዙር ድርድር ዝግጅቱ ዙሪያ መወያየታቸውን እና ገለጻ እንደተደረገላቸው አስታወቁ።ኢራን በድርድሩ ላይ መሳተፏን ባታረጋግጥም ናቅቪ ግን ለድርድሩ ዝግጅቱ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።ወደ ኢዝላማባድ ለሚመጣው ልዑክ “የጸጥታ ሁኔታዎች መጠናከራቸውን” እንዲሁም ለኢራን አምባሳደር ገለጻ እንደተደረገላቸው የአገር ውስጥ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።ሚኒስትሩ አክለውም በሁለቱ አገራት መካከል የሚደረገው ድርድር በቀጣናው ለሚኖር ዘላቂ ሰላም ወሳኝ ነው ብለዋል።እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ የኢራን አምባሳደር ፓኪስታን ውጥረቱን ለማርገብ እየተጫወተችው ያለውን “በጎ እና ገንቢ ሚና” አድንቀዋል።ያጋሩ, ፓኪስታን፣ ቴህራን እና ዋሺንግተን ለሚያደርጉት ቀጣይ ዙር ድርድር “የጸጥታ ሁኔታው መጠናከሩን” አስታወቀች
