ልደቱ አያሌው-3ኛ መንገድ ·Follow
ኢቶሪካ እና የወፍ-በረር ትዝብቶቼ
ከአገራችን የኪነ-ጥበብ ሰዎች መካከል የግፍ አገዛዝን በመጋፈጥ እረገድ በዘመነ ኢህአዴግ አንደኛ፣ በዘመነ
ዐቢይ ደግሞ አራተኛ ጀግናዬ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ነው። የተጽዕኖ ፈጣሪውን የቴዲን አልበም መለቀቅ
ተከትሎ በተፈጠረው የሰሞኑ ከፍተኛ የህዝብ ስሜት ዙሪያ የሚከተሉትን ስምንት ቁም-ነገሮች
ታዝቤአለሁ። ትዝብቶቸ የድርሻ ኃላፊነቱን የተዎጣውን ቴዲ አፍሮን ሳይሆን የሱን አልበም መለቀቅ ተከትሎ
የተፈጠረውን የህዝብ ስሜት የሚመለከቱ ናቸው።
1ኛ. ማናችንም ከምንገምተው በላይ የኢትዮዽያ ህዝብ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ብሶት፣ ምሬት፣ ስጋት፣
የተቃውሞ ስሜትና የለውጥ ጥማት ውስጥ ነው።
2ኛ. በአገራችን ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ በቋሚነት ከምንደክመው ፖለቲከኞችና ማህበራዊ አንቂዎች
በላይ ኪነ-ጥበብ በብዙ እጥፍ የህዝብን ስሜት የማነሳሳት ትልቅ አቅምና ሚና ዓላት።
3ኛ. የወቅቱ የአገራችን የብሄር ብሄርተኞች “አልቆለታል”
ብሄርተኝነት ፖለቲካ ዛሬም በህዝቡ ውስጥ “የተዳፈነ ረመጥ” ሆኖ ቀጥሏል።
ወይም “ተሸንፏል” ከሚሉት በተቃራኒ የኢትዮዽያ
4ኛ. የህዝበኝነት /Populism/፣ የስሜታዊነት፣ የጽንፈኝነት፣ የብሄርተኝነት እና የመርህ የለሽነት የፖለቲካ
ባህል በህዝባችን ውስጥ አስፈሪ በሆነ መጠን ተጠናክሮ ቀጥሏል።
5ኛ. አብዛኛው የአገራችን የፖለቲካ ማህበረሰብ ተደራጅተው ከሚታገሉለት፣ ከታሰሩለት እና መተኪያ
የሌለው ውድ ህይዎታቸውን ጭምር በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል አሳልፈው ከሰጡለት ጀግኖቹ በላይ
በዘፈንና በቅኔ ስሜቱን ለሚገልጹለት አርቲስቶች የበለጠ ፍቅርና አድናቆት አለው።
6ኛ. ዘላቂ ሰላም እና ፍቅር፣ እኩልነት እና አንድነት በባዶ ቃላት የምንመኛቸው ባዶ ተስፋዎች ከመሆን
አልፈው መሳኪያ መንገዳቸው የገባን ዓላማዎቻችን አልሆኑም።
7ኛ. አሸናፊነትና ዘላቂ ለውጥ በስሜትና በምኞት ሳይሆን በተደራጀ ትግልና መስዋዕትነት ብቻ የሚገኝ
ውጤት መሆኑ ገና አልገባንም።
8ኛ. ከቴዲ አፍሮ ዜማና ቅኔ በላይ የኢትዮዽያ የፖለቲካ ማህበረሰብ ፍች የጠፋለት ቅኔ ሆኗል።
ፖለቲከኞች እና ማህበራዊ አንቂዎች ስምንት ዓመት ታግለን ማነሳሳት ያልቻልነውን ሕዝብ ቴዲ አፍሮ
በስምንት ደቂቃ የ“ዳስ ጣል” ዜማና ቅኔው አነሳስቶታል። ይህን ሳይ ፖለቲከኛ ከመሆን ይልቅ ቅኔ ዘራፊ
በሆንኩ የሚል መንፈሳዊ ቅናት አድሮብኛል። ቴዲ አፍሮ “ስማ እራሴ” እንዳለው የስምንቱን ትዝብቶቸን
ዝርዝር ትንታኔ ቅኔ ወዳጅ የሆናችሁት እናንተ፣ ለእናንተው እንድትነግሩት ትቸዋለሁ። ተወያዩበት። አሁን፣
በኢትዮዽያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 11 ሰዓት ነው።
ልደቱ አያሌው/ሚያዚያ 13 ቀን 2018 ዓ/ም

