
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጥያቄ መሠረት ከኢራን ጋር የገቡትን የተኩስ አቁም ማራዘማቸውን አስታወቁ። ትራምፕ የኢራን ወደቦች ላይ የተጣለው እገዳ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ጭምቅ ሃሳብ
- ጦርነት እና የኢንተርኔት መቋረጥ የጎዳቸው ኢራናውያን
- “በእግድ ውስጥ ያለ እግድ”- አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣለችው የመርከቦች እንቅስቃሴ ክልከላ
- ቻይና ኢዝላማባድ የአሜሪካ እና ኢራን ውይይትን ለማመቻቸት የምታደርገውን ጥረት “ሙሉ በሙሉ እንደምትደግፍ” ገለጸች
- የቴህራን መገናኛ ብዙኃን ከኢራን ወደ ፓኪስታን የሄደ ልዑካን ቡድን እንደሌለ ዘገቡ
- ትራምፕ ከኢራን ወደቦች የሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የጣሉትን እገዳ መቼ ያነሳሉ?
- ትራምፕ ኢራን ያበለጸገችውን ዩራኒየም ማስወገድ “ረዥም እና አስቸጋሪ” ሂደት ነው አሉ
የቀጥታ ሽፋን
- ከ 28 ደቂቃዎች በፊትየኢራን አማካሪ የትራምፕ የተኩስ አቁም ስምምነት ‘ምንም ማለት አይደለም’ አሉየኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ አማካሪ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተኩስ አቁም ማራዘሚያ “ምንም ማለት እንዳልሆነ” እና “ለድንገተኛ ጥቃት ጊዜ ለመግዛት የሚያስችል ብልሃት” ነው ሲሉ ተናገሩ።ማህዲ ሞሐመድ በኤክስ ገጻቸው ላይ በፋርስ ቋንቋ ባጋሩት ጽሑፍ፣ የትራምፕ “ከበባ” መቀጠል “ከቦምብ ድብደባ የተለየ አይደለም” በማለት “ወታደራዊ ምላሽ መሰጠት አለበት” ብለዋል። አክለውም “ኢራን እርምጃ የምትወስድበት ጊዜ ደርሷል” ሲሉ ሃሳባቸውን አጠናክረዋል።ኢራን 20 በመቶ የዓለም ነዳጅ የሚተላለፍበትን ቁልፍ የባህር መስመር ዘግታ ለሳምንታት ከቆየች በኋላ የአሜሪካ የባህር ኃይል ወደ ቴህራን ወደቦች የሚገቡ እና የሚወጡ መርከቦች ላይ እግድ ጥሏል።እሁድ ዕለት ጦሩ የኢራን ባንዲራን የምታውለበልብ የጭነት መርከብ በቁጥጥር ስር አውሏል።ያጋሩ, የኢራን አማካሪ የትራምፕ የተኩስ አቁም ስምምነት ‘ምንም ማለት አይደለም’ አሉ
- ከ 1 ሰአት በፊትበኢራን በጦርነቱ ምክንያት ቢያንስ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሥራቸውን ማጣታቸው ተገለጸ
የፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,በኢራን የዋጋ ግሽበትና ሥራ አጥነት በስፋት እየታየ ነውኢራን ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር በተፈጠረ ጦርነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከፍተኛ የሆነ የሠራተኛ ቅነሳ ለማድረግ ተገድዳለች።ምክትል የሥራና የማኅበራዊ ዋስትና ሚኒስትሩ ጎላምሆሴይን መሐመድ ከሁለት ቀናት በፊት በጦርነቱ ምክንያት ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሥራቸውን አጥተዋል ብለዋል።ሰፊው የሠራተኞች ቅነሳ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በኢራናውያን መካከል ትልቅ የመነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል።ተፅዕኖው የአየር ድብደባ ተፈጽሞባቸው የተዘጉ ፋብሪካዎች ብቻ የሚመለከት አይደለም። ሌሎች አምራቾችን፣ ቸርቻሪዎችን፣ የአስመጪና ላኪ ንግድ ድርጅቶችን እና ዲጂታል ዘርፉንም ጎድቷል።”ከባቡር ጣቢያዎች ባዶነት መመልከት ትችላላችሁ” ሲል አንድ ተጠቃሚ በኤክስ ገጹ ላይ ለጥፏል። ሌላ ግለሰብ በበኩሉ “በቢሯችን አቅራቢያ ካሉት የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች ባዶነት ማየት ትችላላችሁ”ሲል የተፈጠረውን የሥራ አጥነት ስፋት ለመግለጽ ሞክሯል።”ከዋናው አውራ ጎዳና ባዶነት መረዳት ትችላላችሁ።አንድ ሰዓት ተኩል የሚፈጅብኝን በግማሽ ሰዓት ብቻ ነው የደረስኩት” ሲል ሌላ አስተያየት ሰጪ ተናግሯል።ጦርነቱ በሸማቾች ወጪ ላይም አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል። ብዙ ሰዎች አስፈላጊ ነገሮችን መሸመት በመተዋቸው እንደ ቱሪዝም፣ ምግብ ቤቶች እና የሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮች ውጭ ባሉ ሌሎች የችርቻሮ ነጋዴዎች ላይ ጫና ፈጥሯል።የኢራን ባለሥልጣናት ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ኢንተርኔት ላይ የጣሉት ገደብ በአገሪቱ በአንፃራዊነት እያደገ ባለው የቴክኖሎጂና የዲጂታል ዘርፎች ላይም ተጽዕኖ አሳድሯል።ባለሥልጣናት ኢንተርኔት ለመዝጋት የወሰኑት ከደህንነት ጋር በተያያዘ ነው። ይህም ክትትል፣ ስለላ እና የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።የኢራን የኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሳታር ሀሺሚ በጥር ወር እንደተናገሩት የኢንተርኔት መቆራረጥ በየቀኑ ኢኮኖሚውን ቢያንስ 35 ሚሊዮን ዶላር ያሳጣል።በዚህ አሃዝ መሠረት፣ ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ለ52 ቀናት የኢንተርኔት መዘጋት የኢራንን ኢኮኖሚ ከ1.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ አሳጥቷል።ያጋሩ, በኢራን በጦርነቱ ምክንያት ቢያንስ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሥራቸውን ማጣታቸው ተገለጸ - ከ 1 ሰአት በፊትየሊባኖስ መገናኛ ብዙኃን በእስራኤል ጥቃት አንድ ሰው መገደሉን ዘገቡ
የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በሚገኝ መንደር ትናንት በፈጸመችው ጥቃት በመስጊድ ላይ ጉዳት ደርሷልየእስራኤል ጦር በደቡብ ምሥራቅ ቤይሩት ሊታኒያ ወንዝ አካባቢ በፈጸመው ጥቃት አንድ ሰው መገደሉን አና ሁለት መቁሰላቸውን የሊባኖስ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የእስራኤል ወታደሮች ወደ ዋዲ አል ሳሎውቂ ለመሄድ መንገዶችን እየጠረጉ መሆኑን የዘገቡት መገናኛ ብዙኃኑ፣ በደቡብ ሊባኖስ የሚገኙ ቤቶችን እና ሱቆችን “እያፈረሱ” መሆናቸውን ጠቅሰዋል።በትናንትናው ዕለት የእስራኤል ጦር በሊታኒያ ወንዝ አካባቢ እና ሳሎውቂ ለሚገኙ ነዋሪዎች “የሄዝቦላህ የሽብር እንቅስቃሴ ይኖራል” በሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር።ባለፈው ሳምንት ሊባኖስ እና እስራኤል ለአስር ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም መስማማታቸው ይታወሳል።ዋሺንግተን ሐሙስ ዕለት በሁለቱ አገራት መካከል የሚካሄደውን ድርድር ታስተናግዳለች።የተኩስ አቁሙ ስምምነቱ እስራኤል “ከታቀደ፣ ሊደርስ ከሚችል ወይም ጥቃት ሲከፈትባት ራሷን ለመከላከል የትኛውን እርምጃ የመውሰድ መብት አላት” ይላል።በሌላ በኩል ሊባኖስ የሄዝቦላህ እና ሌሎች “ከመንግሥት ውጪ የሆኑ ታጣቂዎች፣ ከእስራኤል በሚገኙ ዒላማዎች ላይ ጥቃት አንዳይፈጽሙ “ተጨባጭ እርምጃዎችን” መውሰድ እንዳለባት ያስቀምጣል።ትናንት ምሽት ሄዝቦላህ የተኩስ አቁሙን በመጣስ በሰሜን እስራኤል ወደሚገኙ ዒላማዎች ሮኬት ማስወንጨፉን ገልጿል።በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ይቼል ሌይተር ሄዝቦላህን የተኩስ አቁሙን በመጣስ ወንጅለውታል።ያጋሩ, የሊባኖስ መገናኛ ብዙኃን በእስራኤል ጥቃት አንድ ሰው መገደሉን ዘገቡ - ከ 1 ሰአት በፊትየኢራን አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ወሽመጥ ኮንቴይነር የጫነ መረከብ ላይ ተኩስ መክፈቱ ተገለጸየኢራን አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ኮንቴይነር የጫነ መርከብ ላይ መተኮሱን የዩኬ የባሕር ትራንስፖርት ንግድ ማዕከል (ዩኬኤምቲኦ) አስታወቀ።የኢራን ጦር ጀልባ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ኮንቴይነር የጫነ መርከብ ላይ ጥቃት ፈጽሞ ከባድ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።በብሪታኒያ ባሕር ኃይል የሚመራው የዩኬ የባሕር ትራንስፖርት ማዕከል ጥቃቱ የተፈጸመው ከኦማን ሰሜን ምሥራቅ በሚገኝ አካባቢ መሆኑን ገልጿል።የአብዮታዊ ዘቡ “መሳሪያ የደገነ ጀልባ” መርከቡን ተጠግቶ ያለ ምንም የሬዲዮ ማስጠንቀቂያ ወይም ሰላምታ “ተኩስ ከፍቷል” በማለት “ከባድ ጉዳት በድልድዩ [የመርከቡ መቆጣጠሪያ] ላይ ደርሷል” ብሏል።በኢራን አብዮታዊ ዘብ ጥቃት የተፈጸመበት መርከብ በግሪክ ኩባንያ ባለቤትነት የተያዘ መሆኑን ቢቢሲ ማረጋገጥ ችሏል።ያጋሩ, የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ወሽመጥ ኮንቴይነር የጫነ መረከብ ላይ ተኩስ መክፈቱ ተገለጸ
- ከ 2 ሰአት በፊትየአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ቴህራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ለመጣል ዛቱ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንት በኤክስ ገጻቸው ላይ ኢራን በኻርግ ደሴት ያላት የነዳጅ ማጠራቀሚያ “በቀናት ውስጥ” ሙሉ በሙሉ ይሞላል በማለት “የኢራን ፍርክርኩ የወጣ የነዳጅ ጉድጓዶች ይዘጋሉ” አሉ።“የኢራን የባሕር ላይ ትራንስፖርት ንግድን በቀጥታ ዒላማ ማድረግ የአስተዳደሩን ዋነኛ የገቢ ምንጭ ይገድባል” ሲሉ የግምጃ ቤት ኃላፊው ተናግረዋል።”የቴህራን ገንዘብ የማመንጨት፣ የመንቀሳቀስ እና የመመለስ አቅሟን ስልታዊ በሆነ መልኩ ለመቀነስ በ’ኢኮኖሚ ፊውሪ’ በኩል ከፍተኛውን ግፊት መተግበሩን ይቀጥላል።”በኢራን ንግድ ላይ የአሜሪካን ማነቆ በድብቅ ለማለፍ የሚጥር ማንኛውም ሰው ማዕቀብ ሊጣልበት ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ለሁለት ሳምንት ያህል የቆየው የተኩሰ አቁም ከማብቃቱ በፊት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢራን “ወጥ የሆነ ምክረሃሳብ” እስክታቀርብ ድረስ የተኩስ አቁሙን ማራዘማቸውን አሳውቀዋል።በተባበሩት መንግሥታት የኢራን አምባሳደር የሆኑት አሚር ሳኢድ ቴህራን ወደቦቿ ላይ የተጣለው እገዳ ሊነሳ እንደሚችል ምልክቶችን ማየቷን ተናግረዋል። አክለውም ቀጣዩ ውይይት የሚካሄደው በወደቦቿ ላይ የተጣለው እገዳ ሲነሳ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።ዶናልድ ትራምፕ ከሴኤንቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢራን ወደ ፓኪስታን ልዑካኖቿን ከመላክ ውጪ “አማራጭ የላትም” ብለዋል። አክለውም ለውጥ የማይታይ ከሆነ “በቦምብ ሊደበድቡ እንደሚችሉ” ተናግረው ነበር።ያጋሩ, የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ቴህራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ለመጣል ዛቱ - ከ 3 ሰአት በፊትየሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት የአሜሪካ ነዳጅ ላይ ያለውን ፍላጎት መጨመሩን ባለሙያ ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰኞ ምሽት በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ድረ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ የኢራን አመራር እንደ ቴክሳስ፣ ሉዊዚያና እና አላስካ ያሉ በነዳጅ ምርታቸው የበለፀጉ የአሜሪካ ግዛቶች “በመቶዎች የሚቆጠሩ መርከቦችን” እንዲያስተናግዱ አስገድዷል ብለዋል።ስለ መርከቦቹ ዓይነት ግልጽ ባይደረግም፣ የመርከብ እና የንግድ ተንታኞች ለቢቢሲ ቬሪፋይ እንደተናገሩት ኢራን የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥን መዘጋቷ ለአሜሪካ የድፍድፍ ነዳጅ ያለው ፍላጎት እንዲጨምር አድርጓል።የባህር ወሽመጡ የባህረ ሰላጤው ነዳጅ የሚጓጓዝበት ቁልፍ መስመር ቢሆንም፣ የካቲት 21 2018 ዓ.ም. አሜሪካ እና እስራኤል ቴህራን ላይ ጦርነት በመክፈታቸው የመርከብ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ተስተጓጉሏል።አስመጪዎች ከመካከለኛው ምሥራቅ በባሕር ወሽመጡ በኩል ድፍድፍ ነዳጅ ማግኘት ባለመቻላቸው አማራጭ አቅራቢዎችን ለመፈለግ ተገድደዋል።የባሕር ላይ ትራንስፖርትን ከሚተነትኑ ኩባንያዎች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው 71 የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ጭነት ለማጓጓዝ ወደ አሜሪካ እያመሩ ነው።ባለፈው ዓመት በአማካይ 27 የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ብቻ ጭነት ለማጓጓዝ ወደ አሜሪካ አቅንተዋል።“ከአውሮፓና ከእስያ የመጡ ገዢዎች የአቅርቦት ክፍተቱን ለመሙላት ከአትላንቲክ ተፋሰስ የሚወጣውን ነዳጅ ከአሜሪካ ባሕረ ሰላጤ ጠረፍ ጨምሮ ተደራሽና መፍትሄ አድርገው ተመልክተውታል” ሲሉ የአርገስ ሚዲያ የገበያ መረጃ ድርጅት ኃላፊ ዴቪድ ሃይደን ተናግረዋል።ይህ የአሜሪካን የድፍድፍ ነዳጅ ዘይት ሽያጭ እንዲጨምር እያደረገ ያለ ይመስላል።የባህር ትራንስፖርት ምርምር አማካሪ የሆኑት ድሬሪ እንደሚሉት፣ በሚያዝያ 10 መጨረሻ ሳምንት የአሜሪካ የመርከብ ጭነት በቀን 5.2 ሚሊዮን በርሜል ደርሷል። ይህም በሰባት ወራት ውስጥ ከፍተኛው ነው።ያጋሩ, የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት የአሜሪካ ነዳጅ ላይ ያለውን ፍላጎት መጨመሩን ባለሙያ ተናገሩ - ከ 4 ሰአት በፊትየተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ የተኩስ አቁም መራዘሙን አደነቁ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየመንግሥታቱ ደርጅተ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉታሬዝ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተኩስ አቁሙን ለማራዘም ያሳለፉትን ውሳኔ ማድነቃቸውን ቃል አቀባያቸው ተናገሩ።ቃል አቀባያቸው ስቴፋኔ ጁሪክ “ግጭትን ለማስወገድ፣ እንዲሁም ለዲፕሎማሲ ወሳኝ ስፍራ መፍጠር እና በኢራን እና በዩናይድ ስቴትስ መካከል መተማመንን ለመገንባት ይህ አንዱ እርምጃ ነው” ብለዋል።የዋና ጸሃፊው ቢሮ አሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁሙን ባለመጣስ እና በድርድሩ ላይ ገንቢ በሆነ መልኩ በመሳተፍ የተጀመረውን ጥረት እንዲቀጥሉ አበረታትቷል።ጉታሬዝ ፓኪስታን በሁለቱ አገራት መካከል ንግግር እንዲኖር የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፉ እና “ለግጭቱ ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ መፍትሄ የሚኖርበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተስፋ አደርጋለሁ”ማለታቸውን ጁሪክ ተናግረዋል።ያጋሩ, የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ የተኩስ አቁም መራዘሙን አደነቁ - ከ 5 ሰአት በፊትዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ድርድር እስኪጠናቀቅ ድረስ የተኩስ አቁሙ መራዘሙን አስታወቁ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጥያቄ መሠረት ከኢራን ጋር የገቡትንየተኩስ አቁም ማራዘማቸውን አስታወቁ። ትራምፕ የኢራን ወደቦች ላይ የተጣለው እገዳ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።ትራምፕ የተኩስ አቁሙን መራዘም ያስታወቁት ከመጠናቀቁ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ነው።የትራምፕ ውሳኔ ጦርነቱ ዳግም ይቀጥላል የሚለውን ፍራቻ ያስወገደ ሲሆን የሁለተኛው ዙር ድርድርም ቴህራን አቋሟን እስክታሳውቅ ድረስ ተራዝሟል።ዶናልድ ትራምፕ የተኩስ አቁሙን ማራዘማቸውን ተከትሎ ምክትላቸው ጄዲ ቫንስ ወደ ኢዝላማባድ የሚያደርጉት ጉዞ መሰረዙን የዋይት ሐውስ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።ኢራን ለትራምፕ ውሳኔ በይፋ መግለጫ ባትሰጥም ሁለቱም አገራት ያለ ስምምነት ጦረነቱን ለመቀጠል አንዳቸው ሌላኛቸው ላይ ሲዝቱ ነበር።ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት መሠረት በፓኪስታን ጦር አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ጥያቄ መሠረት እንዲሁም “የኢራን መንግሥት በከፍተኛ ሁኔታ በመፍረክረኩ” የተኩስ አቁሙ የኢራን መሪዎች እና ተወካዮች “የተቀናጀ ምክረ ሃሳብ ይዘው እስኪመጡ ድረስ” እንዲቀጥል መወሰናቸውን ተናግረዋል።ትራም ፕበዚሁ መልዕክታቸው ላይ የአሜሪካ ባሕር ኃይል በኢራን ወደቦች ላይ “እገዳውን እንዲቀጥል” አዝዘዋል።የተኩስ አቁሙ ኢራን ምክረ ሃሳቧን እስክታቀርብ እና ውይይቶቹ የሚያመጡት ውጤት ምንም ይሁን ምን እስኪጠናቀቅ ድረስ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።ትራምፕ ከዚህ በፊት የተኩስ አቁሙን ለማራዘም ሃሳብ እንደሌላቸው ገልጸው ነበር። ምንም እንኳ ትራምፕ የኢራን ወደቦች ላይ የጣሉት እገዳ እንደሚቀጥል ቢናገሩም ከዚህ ቀደም የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ይህ “ከጦርነት ተግባር” አይተናነስም ሲሉ ኮንነውት ነበር።በተባበሩት መንግሥታት የኢራን ልዑክ አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣለችው እገዳ የምታነሳ ከሆነ ንግግሩ ይቀጥላል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።ያጋሩ, ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ድርድር እስኪጠናቀቅ ድረስ የተኩስ አቁሙ መራዘሙን አስታወቁ - 21 ሚያዚያ 2026ፓኪስታን በድርድሩ ኢራን መሳተፏ እንዳልተረጋገጠ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ገለጸች
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበአሜሪካ እና ኢራን መካከል ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ሁለተኛ ዙር ንግግር ቴህራን እንደምትሳተፍ እስካሁን በይፋ አለማሳወቋን የአሸማጋይዋ አገር ፓኪስታን ገለጸች።የፓኪስታን መረጃ እና ብሮድካስት ሚኒስትር አቱላህ ታራር እንደተናገሩት ፓኪስታን እንደ አሸማጋይ አገርነቷ “ከኢራን ጋር ያልተቋረጠ ግንኙነት” እያደረገች እንዲሁም “የዲፕሎማሲ እና የንግግር መንገድን እየተከተለች” ነው።አሜሪካ እና ኢራን የደረሱት የሁለት ሳምንት ተኩስ አቁም በነገው ዕለት የሚጠናቀቅ ሲሆን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተደራዳሪ ቡድናቸውን ወደ ፓኪስታን እንደሚልኩ አስታውቀዋል።የተኩስ አቁሙ ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት ኢራን በድርድሩ እንደምትሳተፍ ውሳኔ ማሳለፏ “ወሳኝ” መሆኑን የፓኪስታኑ ሚኒስትር ተናግረዋል።ሚኒስትሩ በኤክስ ገጻቸው ባወጡት መግለጫ፤ “ፓኪስታን የኢራን አመራሮች በሁለተኛው ዙር ድርድር እንዲሳተፉ ለማሳመን ከልብ የመነጨ ጥረት አድርጋለች፤ ይህ ጥረትም አሁንም ቀጥሏል” ብለዋል።ሁለተኛው ዙር ድርድር የመካሄዱ ነገር ካለው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ እንጥልጥል ላይ የሚገኝ ሲሆን አሁን ፓኪስታን የሰጠችው መግለጫ ንግግሩ የመካሄዱ ጉዳይ በኢራን እጅ እንደሚገኝ እውቅና የሰጠ ነው። ፓኪስታን፤ ኢራን የመሳተፏ ነገር አለመረጋገጡን በይፋ ስታሳውቅ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።ያጋሩ, ፓኪስታን በድርድሩ ኢራን መሳተፏ እንዳልተረጋገጠ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ገለጸች - 21 ሚያዚያ 2026ኢራን ድርድር ውስጥ ከገባች “እጇ ከቃታው ላይ” እንደማይነሳ የመንግሥት ቃል አቀባይ ተናገሩ
የፎቶው ባለመብት,Morteza Nikoubazl/NurPhoto via Getty Imagesኢራን ከአሜሪካ ጋር ድርድር የምታደርግ ከሆነ ንግግር ውስጥ የምትገባው “እጇን ቃታው ላይ” አድርጋ እንደሚሆን እና መከላከያ ኃይሏ “ሙሉ ዝግጁነት” እንደሚኖረው የአገሪቱ መንግሥት ቃል አቀባይ ተናገሩ።ከመንግሥታዊው ዜና ወኪል ‘ኢርና’ ጋር ቆይታ ያደረጉት ቃል አቀባይዋ ፋጤሜህ ሞሃጄራኒ ኢራን በፓኪስታን ዋና ከተማ ኢስላማባድ በሚካሄደው ቀጣይ ዙር ድርድር ትሳተፍ እንደሆነ ማረጋገጫም ይሁን ማስተባበያ አልሰጡም።“ከፊት ለፊታችን ሁለት ስትራቴጂዎች አሉ። የመጀመሪያው የጦርነት ስትራቴጂ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ የዲፕሎማሲ ስትራቴጂ ነው” ሲሉ ለዜና ወኪሉ ተናግረዋል።የኢራን ተደራደሪ ቡድን “በብሔራዊ ጥቅም ላይ ቅንጣት እንኳ አያመቻምችም” ብለዋል።ቃል አቀባይዋ ይህንን የአገሪቱ መንግሥት አቋም የገለጹት ሁለተኛ ዙር ድርድር ይካሄድ እንደሆነ ማረጋገጫ ባልተገኘበት ሁኔታ ውስጥ ነው።ተደራዳሪ ልዑካቸውን ወደ ዛሬ ፓኪስታን እንደሚልኩ ያስታወቁት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ተደራዳሪዎቿን ወደ ፓኪስታን “ከመላክ ውጪ አማራጭ የላትም” ብለዋል።በነገው ዕለት የሚጠናቀቀውን የሁለት ሳምንት ተኩስ አቁም የማራዘም ፍላጎት እንደሌላቸውም አስታውቀዋል።ያጋሩ, ኢራን ድርድር ውስጥ ከገባች “እጇ ከቃታው ላይ” እንደማይነሳ የመንግሥት ቃል አቀባይ ተናገሩ - 21 ሚያዚያ 2026ትራምፕ፤ ኢራን ተደራዳሪዎቿን ወደ ፓኪስታን “ከመላክ ውጪ አማራጭ የላትም” አሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለሚደረገው ድርድር ልዑካኗን ወደ ፓኪስታን “ከመላክ ውጪ አማራጭ የላትም” በማለት ተናገሩ።በምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ የሚመራው የአሜሪካ ልዑክ ከኢራን ጋር ለሚደረግ ንግግር ዛሬ ወደ ፓኪስታን የሚጓዝ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ቴህራን ተደራዳሪዎቿን እንደምትልክ ማረጋገጫ አልሰጠችም።ከአሜሪካው የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲኤንቢሲ ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ የሚደረገው ድርድር “ከታላቅ ስምምነት ጋር ይጠናቀቃል” የሚል መተማመን እንዳላቸው ተናግረዋል።አሜሪካ “እየተጋፈጠች ያለችው ከጥሩ ሰዎች ጋር አይደለም” ያሉት ትራምፕ፤ ነገር ግን “ስኬታማ” ተግባር እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል። አሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ የጣለችውንም እገዳ “ታላቅ ስኬት” ሲሉ ጠርተውታል።አሜሪካ እና ኢራን ለሁለት ሳምንት እንዲቆይ የተስማሙት ተኩስ አቁም ነገ ረቡዕ ይጠናቀቃል። ከኢራን ጋር የሚደረገው ድርድር በጥሩ ሁኔታ የሚሄድ ከሆነ ተኩስ አቁሙን ያራዝሙት እንደሆነ የተጠየቁት ትራምፕ፤ “ያንን ማድረግ አልፈልግም” ሲሉ አቋማቸውን አሳውቀዋል።“የቦንብ ድብደባ እንደሚኖር እጠብቃለሁ፤ ምክንያቱም ጥሩ ባህሪ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።ስምምነት ላይ ለመድረስ “ብዙ ጊዜ” እንደሌለ የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፤ ኢራኖች ከአሜሪካ ጋር የሚስማሙ ከሆነ “እጅግ ጥሩ ስፍራ ላይ ያርፋሉ” ብለዋል።ያጋሩ, ትራምፕ፤ ኢራን ተደራዳሪዎቿን ወደ ፓኪስታን “ከመላክ ውጪ አማራጭ የላትም” አሉ - 21 ሚያዚያ 2026አሜሪካ እና ኢራን ሊያበቃ የተቃረበውን የተኩስ አቁም በመጣስ እየተካሰሱ ነው
የፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ ጋሊባፍ እና ፕሬዝዳንት ትራምፕአሜሪካ እና ኢራንን ለሁለት ሳምንታት የደረሱት የተኩስ አቁም ሊጠናቀቅ በተቃረበበት በአሁኑ ጊዜ ሁለቱ አገራት ተኩስ አቁሙን በመጣስ እየተካሰሱ ነው።የአሜሪካ ኃይሎች የኢራንን መርከብ ከተቆጣጠሩ በኋላ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የተኩስ አቁሙን “ለበርካታ ጊዜያት” እየጣሰች ነው ሲሉ፣ ኢራን በበኩሏ አሜሪካ “የባሕር ላይ ውንብድና” እየፈጸመች ነው ብላለች።ፕሬዝዳንቱ በትሩዝ ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አሜሪካ የምትፈጽመውን ጥቃት ያስቆመውን የተኩስ አቁም ኢራን በተደጋጋሚ ጥሳለች ሲሉ ከስሰዋል።ነገር ግን ትራምፕ ለዚህ ክሳቸው ምንም ዓይነት ማብራሪያም ሆነ ማጠናከሪያ አልሰጡም።ኢራንም በበኩሏ አሜሪካ የተደረሰውን የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም በተደጋጋሚ ጥሳለች ስትል ስከስስ ቆይታለች።በሆርሙዝ ወሽመጥ በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ ዕቀባን ሲጥሉ እና ሲያነሱ የቆዩት ሁለቱ አገራት በአካባቢው ያላቸውን የበላይነት ለማሳየት እየጣሩ ነው።የአሜሪካ ባሕር ኃይል በሆርሙዝ ላይ የተጣለውን እገዳ የጣሰ ነው ባሉት የኢራን መርከብ ላይ መተኮሳቸውን ተከትሎ የኢራን ጦር ኃይል ለአሜሪካ “ወደታራዊ የባሕር ላይ ውንብድና” ለላው ጥቃት አጸፋ እንደሚመለስ ዝቷል።ጨምሮም አሜሪካ በሆርመዝ ወሽመጥ ላይ በኢራን መርከቦች ላይ እየወሰደችው ያለው እርምጃ “የተኩስ አቁም ስምምነቱን የሚጥስ ነው” በማለት ከስሷል።ያጋሩ, አሜሪካ እና ኢራን ሊያበቃ የተቃረበውን የተኩስ አቁም በመጣስ እየተካሰሱ ነው - 21 ሚያዚያ 2026ጦርነት እና የኢንተርኔት መቋረጥ የጎዳቸው ኢራናውያን
የፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በኢራን የምግብ ዋጋ በእጥፍ ጨምሯልበኢራን ውስጥ የእስላማዊ ሪፐብሊኩ ደጋፊዎች ሳይቀር ለማይቀረው የምጣኔ ኃባት ፈተና ቀበቷቸውን እያጠበቁ ነው።ጥያቄው የኢራን መንግሥት የሆርሙዝ ወሽመጥ ተዘግቶ የሚቀጥል ከሆነ ለሠራተኞቹ ደመወዝ መክፈል ይችላል? የሚለው ነው። ቴህራን ከውይይት መድረክ ራሷን አርቃስ መቆየት ትችላለች?ከጦርነቱ በፊት የኢራንን ምጣኔ ኃብት ማዕቀብ፣ የዋጋ ግሽበት እንዲሁም የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ፈትኖታል።ቤተሰቦች አቅማቸው ተሟጥጦ መሠረታዊ ነገሮች ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ሆነዋል።አሁን በጦርነቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ንግዶች ከፔትሮኬሚካል፣ ስቲል እና አሉሚኒየም ኢንዱስትሪዎች መውደም ጋር ተያይዞ የምጣኔ ኃብት ቀውሱ ጫና ተባብሷል።ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በኢራን የምግብ ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል፤ በተጨማሪም ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶችም ቀንሰዋል።የኢራን የገንዘብ ምንዛሬ በመውደቁም ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት ተከስቷል።የኢራን ባለሥልጣናት እስራኤል እና አሜሪካ በአገሪቱ ላይ የከፈቱትን ጦርነት ተከትሎ የደረሰውን የምጣኔ ኃበት ጫና 270 ቢሊዮን ዶላር እንደሚገመት አስታውቀዋል።የምጣኔ ኃብቱ ጫና በተለይ አነስተኛ የኦንላየን ንግዶችን የሚሰሩ ሴቶች ላይ የበረታ ነው።የኢንተርኔት መቋረጥ የእደ ጥበብ ውጤቶችን እየሰሩ በማኅበራዊ ሚዲያ እና ኦንላየን የሚሸጡ በርካታ ሴቶችን ከገበያ በማስወጣት እነርሱን እና ቤተሰቦቻቸውን ባዶ እጃቸውን አስቀርቷል።ጦርነት እና የኢንተርኔት መቋረጥ የመሠረተ ልማት ውድመት ብቻ ሳይሆን በመላው ኢራን የበርካቶችን ቤት ያንኳኳ ችግር አስከትሏል።ያጋሩ, ጦርነት እና የኢንተርኔት መቋረጥ የጎዳቸው ኢራናውያን - 21 ሚያዚያ 2026“በእግድ ውስጥ ያለ እግድ”- አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣለችው የመርከቦች እንቅስቃሴ ክልከላ
የፎቶው ባለመብት,EPAበሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚደረገውን የመርከቦች እንቅስቃሴ ከጦርነት በፊት ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚደረገው ጥረት እንዲሁም ከኢራንን ጥቃት እና ቁጥጥር ጋር የሚደረገው ትግል የአሜሪካ ቀዳሚ ተግባር ነው።የቀድሞው የብሪታኒያ ባሕር ኃይል አዛዥ ኮማንደር ቶም ሻርፕ ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የራሷን ገደቦች ጥላ እያለ፣ አሜሪካ ደግሞ ወደ ቴህራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን መከልከሏን በመጥቀስ፣ እየተከተለች ያለውን ስልት “በእግድ ላይ እግድ” ሲሉ ገልጸውታል።ዋይት ሐውስ ኢራን ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንድትመጣ ለማድረግ “በቂ ጉዳት” ለመፍጠር እየተሞከረ ነው ሲሉ ይናገራሉ።“የኢራንን የነዳጅ ምርት ከኢራን እንዳይወጣ በመከላከል ጉዳቱ ወደ ድርድር ጠረጴዛ ላይ እንዲመጡ እንዲያደርጋቸው ነው? የጉዳቱ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ለማየት አስቸጋሪ ነው፤ እያየነው ያለን አይመስለኝም” ብለዋል።ሻርፕ የኢራን አገዛዝ ከፍተኛውን ጉዳት ተቀብሎ ለማስተናገድ ፈቃደኛ መሆኑን እያሳየ ነው ሲሉ ይሞግታሉ።”ከእስላማዊ ሪፐብሊክ ርዕዮተ ዓለም የበለጠ አንድም ግለሰብ፣ መንግሥት፣ ኢኮኖሚ፣ ወይም ጠቃሚ መሠረተ ልማት የለም፤ እና ይህ ከዩኤስ ጋር ያለው ፍጥጫ ገና ከጅምሩ ሲዘጋጅበት የነበረው ነው።”ከዚያም ባሻገር የኢራን ባለሥልጣናት በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ላይ ያላቸውን “ሉዓላዊነት” እውቅና ሊሰጠው ይገባል ሲሉ አጥብቀው ይጠይቃሉ።ዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያዎችን የማስተጓጎል ችሎታቸው ጠንካራ ስልት እንደሆነ እና እንዲያውም ትርፋማ መንገድ መሆኑን ተምረዋል የሚሉት ቶም ሻርፕ፣ መርከቦች ደህንነታቸው ተጠብቆ ለማለፍ ቀረጦችን ለማስከፈል ወስነዋል ይላሉ።እንደ ባሕር ኃይሉ ገለጻ ከሆነ ያንን ስልት ለመተው ፈቃደኛ የሆነ ማንኛውም የኢራን ተደራዳሪዎች ማየት ከባድ ነው።ያጋሩ, “በእግድ ውስጥ ያለ እግድ”- አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣለችው የመርከቦች እንቅስቃሴ ክልከላ - 21 ሚያዚያ 2026ቻይና ኢዝላማባድ የአሜሪካ እና ኢራን ውይይትን ለማመቻቸት የምታደርገውን ጥረት “ሙሉ በሙሉ እንደምትደግፍ” ገለጸች
የፎቶው ባለመብት,Pakistan Ministry of Foreign Affairs via Xየምስሉ መግለጫ,የፓኪስታን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢስሃቅ ዳር በፓኪስታን የቻይና አምባሳደር ጂያንግ ዛይዶንግ ጋር ሲወያዩበፓኪስታን የቻይና አምባሳደር ኢዝላማባድ፣ አሜሪካ እና ኢራን ወደ ውይይት ጠረጴዛ እንዲመጡ የምታደርገውን ጥረት ቤይጂንግ “ሙሉ በሙሉ እንደምትደግፍ” ገለፁ።የፓኪስታን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢስሃቅ ዳር ከጂያንግ ዛይዶንግ ጋር በአካባቢው ስላለው ሁኔታ መወያየታቸው ተገልጿል።በስብሰባው ወቅት፣ ዛይዶንግ ፓኪስታን በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል “በቀጣናው እና ከዚያም ባሻገር ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ” ፓኪስታን የምታደርገውን ቀጣይ ጥረት ማድነቃቸውን የፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።ያጋሩ, ቻይና ኢዝላማባድ የአሜሪካ እና ኢራን ውይይትን ለማመቻቸት የምታደርገውን ጥረት “ሙሉ በሙሉ እንደምትደግፍ” ገለጸች - 21 ሚያዚያ 2026የቴህራን መገናኛ ብዙኃን ከኢራን ወደ ፓኪስታን የሄደ ልዑካን ቡድን እንደሌለ ዘገቡየኢራን መገናኛ ብዙኃን በቴሌግራም ገጻቸው ላይ እስካሁን ድረስ ከአሜሪካ ጋር ለሚደረገው ድርድር ወደ ኢዝላማባድ የሄደ ልዑክ አለመኖሩን አስታወቁ።መገናኛ ብዙኃኑ “ዋነኞቹም ሆኑ ወይም በሁለተኛ ደረጃ ያሉት አልያም የመጀመርያውም ሆነ ተከታይ ቡድን እስካሁን ድረስ ወደ ኢዝላማባድ የሄደ የልዑካን ቡድን የለም” ብለዋል።ከዚህ በተጨማሪ በቴሌግራም ገጹ ልጥፍ ላይ የልዑካን ቡድኑ መነሳት ወይም መድረስን አስመልክቶ “በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን እና የቀጣናው ምንጮች” የተናፈሰው “ወሬ” ውድቅ ተደርጓል።የመገናኛ ብዙኃኑ ዘገባ በፓርላማ አፈ ጉባዔ ሞሐመድ ባጋር ጋሊባፍ እንዲሁም ሌሎች የኢራን ባለሥልጣናት የተባለውን ዳግም በማስተጋባት ቴህራን “በስጋት ጥላ ውስጥ ሆና ድርድርን አትቀበልም” ብለዋል።ያጋሩ, የቴህራን መገናኛ ብዙኃን ከኢራን ወደ ፓኪስታን የሄደ ልዑካን ቡድን እንደሌለ ዘገቡ
- 21 ሚያዚያ 2026ትራምፕ ከኢራን ወደቦች የሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የጣሉትን እገዳ መቼ ያነሳሉ?
የፎቶው ባለመብት,US Central Command/Xአሜሪካ ከቴህራን ጋር ስምምነት እስኪደረስ ድረስ በኢራን ወደቦች ላይ የጣለችውን እገዳ እንደማታነሳ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ።ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት ጦርነቱን ለማስቆም ያስችላል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ሁለተኛ ዙር ድርድር ስለመካሄዱ እርግጠኛ መሆን ባልተቻለበት ወቅት ነው።ትራምፕ ከአንድ ሳምንት በፊት ጀምሮ ተግባራዊ ያደረጉት እገዳ “ኢራንን ሙሉ በሙሉ እያወደመ ነው” ሲሉ በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ድረ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።ትራምፕ አክለውም አገራቸው ጦርነቱን “በብዙ መልኩ እያሸነፈች ነው” ብለዋል።ይህ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተያየት የተሰማው አሜሪካ እና ኢራን ያደረጉት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ብቻ በቀሩበት ወቅት ነው።ነገር ግን በፓኪስታን ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር ስለመካሄዱ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም።ትራምፕ ኢራን እስከምትስማማ ድረስ በሆርሙዝ ላይ የጣሉትን እገዳ እንደማያነሱ አስታወቁያጋሩ, ትራምፕ ከኢራን ወደቦች የሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የጣሉትን እገዳ መቼ ያነሳሉ? - 21 ሚያዚያ 2026ትራምፕ ኢራን ያበለጸገችውን ዩራኒየም ማስወገድ ”ረዥም እና አስቸጋሪ” ሂደት ነው አሉ
የፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን የበለጸገውን ዩራኒየም ማውጣት ከባድ መሆኑን በማኅበራዊ ሚደያ ገጻቸው ላይ ተናገሩ።“ዘመቻ ሚድናየት ሃመር የተሟላ እና ሙሉ በሙሉ የኢራንን አቧራማ የኒውክሌር ተቋማት ያወደመ ነበር። ስለዚህ ቆፍሮ ማውጣት ረዥም እና አስቸጋሪ ሂደት ነው” ሲሉ ጽፈዋል።ዘመቻ ሚድ ናይት ሐመር አሜሪካ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር በኢራን ላይ የፈጸመችው ድብደባ መጠሪያ ሲሆን 125 የአሜሪካ ጦር አውሮፕላኖች ተሳትፈውበታል።የአሜሪካ ጦር አውሮፕላኖች የደበደቧቸው ሦስት የኢራን የኒውክሌር ተቋማት ፎርዶ፣ ናታንዝ እና ኢስፋሃን ናቸው።ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፋቸው ላይ “ሐሰተኛው ሲኤንኤን እና ሌሎች ብልሹ የመገናኛ ብዙኃኖች የጦር አውሮፕላን አብራሪዎቻችን የሚገባቸውን ክብር ሳይሰጧቸው ቀርተዋል፤ ሁልጊዜም ማንኳሰስ እና ማንቋሸሽ- ተሸናፊዎች።”ያጋሩ, ትራምፕ ኢራን ያበለጸገችውን ዩራኒየም ማስወገድ ”ረዥም እና አስቸጋሪ” ሂደት ነው አሉ - 21 ሚያዚያ 2026አሜሪካ እና ኢራን ለሁለተኛው ዙር ድርድር ስለመገናኘታቸው እርግጠኛ መሆን ያልተቻለው ለምንድን ነው?
የፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ እና ኢራን በኢዝላማባድ ለሚያደርጉት ውይይት ዝግጅቶች ተጠናቅቀዋል።በዋና ከተማው ውስጥ መኪኖች ሲንቀሳቀሱ ይፈተሻሉ። በጎዳናዎቹ ግራ እና ቀኝ “ኢዝላማባድ ቶክስ” የሚሉ ፖስተሮች ተለጥፈዋል። ነገር ግን በሁለቱ አገራት መካከል ንግግሩ ስለመካሄዱ ማንም እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይችልም።ዋይት ሐውስ በጄዲ ቫንስ የሚመራ የአሜሪካ ልዑክ ወደ ፓኪስታን እንደሚሄድ ቢናገርም፣ ጊዜው ግን ግልጽ አልተደረገም።የልዑካን ቡድኑ ኢዝላማባድ መድረስ ቢኖርበትም ሰኞ ዕለት ግን ከዋሽንግተን እንዳልተንቀሳቀሰ ማወቅ ተችሏል።በትክክል እየሆነ ያለውን በግልጽ ማወቅ ያልተቻለው ኢራን መሳተፏን በይፋ ማሳወቅ ስላልፈለገች ይመስላል።በምትኩ በመግለጫቸው ውስጥ አሁንም ቁጣና እልህ አለ።የኢራንን ልዑክ ይመራሉ ተብለው የሚጠበቁት የአገሪቱ የፓርላማ አፈ ጉባኤ መሐመድ ባገር ጋሊባፍ ኢራን “በማስፈራራት ጥላ ስር ሆና ድርድርን አትቀበልም” ሲሉ ተናግረዋል።ዶናልድ ትራምፕንም “ከበባ በመክፈት እና የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ” ከስሰዋል።አፈ ጉባዔው እየጠቀሱ ያሉት በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የተፈጠሩ ክስተቶችን ነው። አሜሪካ የኢራንን ባንዲራ የሚያውለበልብ የጭነት መርከብ በቁጥጥር ስር ማዋሏን እንዲሁም የኢራንን ወደቦች መዝጋቷን እየተቃወሙ ይገኛሉ።በኢራን ውስጥ ያሉ ወታደራዊ አመራሮች ጋሊባፍን ከዲፕሎማሲ ይልቅ ጦርነትን እንዲመርጡ ግፊት እያደረጉ ይገኛሉ።ከመጋረጃ ጀርባ ደግሞ በኢራን ውስጥ የሚደረግ የሥልጣን ሽኩቻ ለመዘግየቱ የሚጠቀስ ሌላ ምክንያት ነው።በርካቶች ጉምቱ አመራሮቿ የተገደሉባት ኢራን ውስጥ የአገሪቱን ሥልጣን በበላይነት ለመቆጣጠር በሚፈልጉ የተለያዩ አካላት ሽኩቻ መፈጠሩ አይቀሬ ነው።በይፋ የምንሰማው አብዛኛው ነገር የፖለቲካ ድንፋታ ሊሆን ይችላል። እናም ባለሥልጣናት የሚሉት ምንም ይሁን ምን ኢራን ወደ ኢዝላማባድ ለመጓዝ እየተዘጋጀች ሊሆን ይችላል።ነገር ግን ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው የተኩስ አቁም ከማብቃቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ መሆኑ የበለጠ አሳሳቢ ያደርዋል።ስለዚህ የሰላም ውይይቱ በእርግጥ ይካሄድ እንደሆነ ማወወቅ ለማንም አዳጋች ነው።ያጋሩ, አሜሪካ እና ኢራን ለሁለተኛው ዙር ድርድር ስለመገናኘታቸው እርግጠኛ መሆን ያልተቻለው ለምንድን ነው? - 21 ሚያዚያ 2026የቻይናው ፕሬዚዳንት በሆርሙዝ ወሽመጥ መደበኛው እንቅስቃሴ መመለስ አለበት አሉ
የፎቶው ባለመብት,Reutersየቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚደረግ የመርከቦች “መደበኛ እንቅስቃሴ”፤ “መመለስ ይኖርበታል” አሉ።ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት ከሳዑዲ አረቢያው ልዑል ሞሐመድ ቢን ሳልማን ጋር ሰኞ ዕለት በስልክ በተወያዩበት ወቅት ነው።ትራምፕ እና ዢ በቻይና በግንቦት ወር አጋማሽ ላይ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘዋል።ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች ለመገናኘት ቀን ከቆረጡ በኋላ በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የተነሳ ወደ ግንቦት አራዝመውታል።ያጋሩ, የቻይናው ፕሬዚዳንት በሆርሙዝ ወሽመጥ መደበኛው እንቅስቃሴ መመለስ አለበት አሉ
