የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገውን ጦርነት ለመቋጨት የተቀመጠ “የጊዜ ገደብ” አለመኖሩን ተናገሩ። ቤተ መንግሥታቸው ደግሞ የተራዘመው ተኩስ አቁም የሚያበቃበት ጊዜ አለመቀመጡን ገልጿል። ኢራን በበኩሏ አሜሪካ እና እስራኤል በፈጸሙት “ግልጽ” የተኩስ አቁም ጥሰት ምክንያት ሆርሙዝ ወሽመጥን መክፈት “የማይቻል ነው” ብላለች።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 43 ደቂቃዎች በፊትኢራን፤ አሜሪካ እና እስራኤል በባህረ ሰላጤው እና በወሽመጡ ላይ ‘የጸጥታ መደፍረስ ምንጭ’ ናቸው አለችየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሜሪካ እና የእስራኤል “ጥቃት” በባህረ ሰላጤ እና በሆርሙዝ ወሽመጥ “የጸጥታ ችግር ምንጭ” ነው አሉ።የኢራን መንግሥት በኤክስ ገፁ ላይ በተከታታይ ባጋራቸው ልጥፎች አባስ አራግቺ በቴህራን ከደቡብ ኮሪያ ልዩ መልዕክተኛ ጋር እንደተገናኙ ገልጿል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አገራት “እነዚህን ጥቃቶች በማውገዝ ግልፅ እና ጠንካራ አቋም እንዲወስዱ” ማሳሰባቸውን ጠቅሷል።ኢራን ደኅንነቷን እና ጥቅሟን ለመከላከል በዓለም አቀፍ ሕግ እርምጃዎችን ወስዳለች ማለታቸውም በልጥፉ ተካትቷል።አራግቺ አክለውም ለሚደርሰው ሁሉ “ኃላፊነቱ የሚወስደው ጥቃት ፈጻሚው ነው” ብለዋል።ኢራን በወሽመጡ ሁለት መርከቦችን “መያዟን” እና ሦስተኛ የጭነት መርከብ ላይም ጥቃት መሰንዘሯ ተገልጿል።ያጋሩ, ኢራን፤ አሜሪካ እና እስራኤል በባህረ ሰላጤው እና በወሽመጡ ላይ ‘የጸጥታ መደፍረስ ምንጭ’ ናቸው አለች
  2. ከ 58 ደቂቃዎች በፊትየሰላም ስምምነት ሳይፈጸም የንግድ መርከቦች ጉዞ እንደማይጀምሩ የነዳጅ ጫኝ ኩባንያ ኃላፊ ተናገሩመርከቦችየፎቶው ባለመብት,Reutersየሲውዲን ነዳጅ አጓጓዥ ኩባንያ የሆነው ‘ስቴና በልክ’ ዋና ስራ አስፈጻሚ በአሁኑ ሰዓት የኩባንያው መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉበት “ምንም ዕድል” እንደሌለ ተናገሩ።የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤሪክ ሃኔል ከቢቢሲ ሬዲዮ 4 ‘ቱዴይ’ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ “ይህንን አይነት እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት” በውሃ መስመሩ በኩል በሰላም ለማለፍ “ከሁለቱም፤ ከኢራን እና አሜሪካ የደኅንነት ዋስትና ያስፈልገናል” ብለዋል።የንግድ መርከቦች በድጋሚ ጉዞ እንዲጀምሩ የሚያስችለው አስፈላጊ ሁኔታ ሊፈጠር የሚችለው የሰላም ስምምነት ሲፈረም ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።”ከጥቂት ሳምንታት በፊት፣ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ ባለው ጊዜ በአንድ ሳምንት ገደማ ውስጥ እንድናልፍ የሚያደርግ አንድ ነገር ይፈጠራል የሚል ተስፋ ነበረን” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ አሁን ግን ሁኔታው “የተቆለፈ” ሆኗል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።ያጋሩ, የሰላም ስምምነት ሳይፈጸም የንግድ መርከቦች ጉዞ እንደማይጀምሩ የነዳጅ ጫኝ ኩባንያ ኃላፊ ተናገሩ
  3. ከ 1 ሰአት በፊትኢራንን እየመራ ያለው ማን ነው?የኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒበኢራን በሚከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ውስጥ ጠቅላይ መሪው ሞጅታባ ኻሜኒ የመጨረሻውን ውሳኔ እንደሚያሳልፉ ይታወቃል።ነገር ግን በመጋቢት ወር ከተሾሙ ወዲህ በፎቶም ሆነ በቪዲዮ ለሕዝብ ታይተው አያውቁም። የኢራን መንግሥት ተደራዳሪዎች እየሠሩ ያሉት በኻሜኒ “ትዕዛዝ” መሠረት ነው።ጠቅላይ መሪው በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ላይ የሚደረጉ ድርድሮችን በግልጽ ባያነሱም አሜሪካን ግን ተችተዋል።የኢራን ተደራዳሪዎች የሆኑት የፓርላማ አፈ ጉባዔው ሞሐማድ ባጋር ጋሊባፍ እና እንደ አባስ አራጋቺ ያሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ድምጻቸው ጎልቶ እየተሰማ ነው።ጋሊባፍ ከኢራን አብዮታዊ ዘብ ጋር ጥብቅ ትስስር አላቸው።የአብዮታዊ ዘቡ በተለይ በጦርነት ወቅት ከመደበኛው መከላከያ ከፍ ያለ ተጽዕኖ ነው ያለው።አብዮታዊ ዘቡ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮቹን ቢያጣም ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ትይዩ እየሰራ ነው።አገሪቱን በሚመለከቱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫዎችን የሚያወጣ ቢሆንም ምን ያህል አቅም እንዳለው ግን ግልጽ አይደለም።ያጋሩ, ኢራንን እየመራ ያለው ማን ነው?
  4. ከ 1 ሰአት በፊትትራምፕ ጦርነቱን ለመቋጨት “እንደማይጣደፉ” ተናገሩየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገውን የጦርነት ለመቋጨት “እየተጣደፉ አለመሆኑን” ለፎክስ ኒውስ ተናገሩ።ፕሬዝዳንቴ ከቴሌቪዥን ጣቢያው ጋር ባደረጉት የስልክ ቃለ መጠይቅ የኢራን ጋር የተደረሰውን እና ረቡዕ ዕለት የተጠናቀቀውን ተኩስ አቁም ያራዘሙት “የጊዜ ጫና” ኖሮባቸው እንዳልሆነ ገልጸዋል።“ጥሩ ስምምነት” ላይ እንዲደረስ እንደሚፈልጉ የተናገሩት ትራምፕ፤ ጦርነቱን ለመቋጨት “እንደማይጣደፉ” አስረድተዋል።የዋይት ሐውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮሊን ሌቪት ከኢራን ጋር የሚደረገው ድርድር “መቀጠሉን” እና ፕሬዝዳንቱ “ቀይ መስመሮቻቸውን በእጅጉ ግልጽ” ማድረጋቸውን ገልጸው ነበር። ከትራምፕ ፍላጎቶች አንዱ ኢራን ያበለጸገችውን የዩራኒየም ክምችት ለአሜሪካ አሳልፋ መስጠት አለባት የሚል ነው።አሜሪካ ስለ ድርድሩ “ከኢራን አገዛዝ ምላሽ ለማግኘት እየጠበቀች” መሆኑን የተናገሩት ቃል አቀባይዋ፤ “እስካሁን ወጥ የሆነ መልዕክት መላክ አልቻሉም፤ ለዚህም ነው ፕሬዝዳንቱ የተኩስ አቁሙን ለማራዘም የወሰኑት” ብለዋል።ያጋሩ, ትራምፕ ጦርነቱን ለመቋጨት “እንደማይጣደፉ” ተናገሩ
  5. ከ 2 ሰአት በፊትእስራኤል ጋዜጠኛን ዒላማ ያደረገ የአየር ጥቃት ፈጽማለች ስትል ሊባኖስ ከሰሰችጋዜጠኛ አማል ካሊልንየፎቶው ባለመብት,APየምስሉ መግለጫ,ጋዜጠኛ አማል ካሊልንየሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ረቡዕ ዕለት እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በፈጸመችው የአየር ድብደባ አንዲት ጋዜጠኛ ገድላ ሌላ ሰው በማቁሰል የጦር ወንጀል ፈጽማለች ሲሉ ከሰሱ።ግድያው የተፈጸመው እስራኤል እና ሊባኖስ ዛሬ በዋሽንግተን ሁለተኛ ዙር ውይይታቸውን ለማድረግ ዝግጅት እያደረጉ ባሉበት ጊዜ ነው።የሊባኖስ ባለሥልጣናት ጋዜጠኛ አማል ካሊልን እና ዘይነብ ፋራጅ የመጀመርያው ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ በአንድ ቤት ውስጥ ተጠልለው ባሉበት ወቅት ሆነ ተብሎ ዒላማ መደረጋቸውን ገልጸዋል።እስራኤል አስቀድማ በፈጸመችው ጥቃት አንድ ተሽከርካሪ የመታች ሲሆን በዚህም ሁለት ሰዎች ተገድለዋል።ባለሥልጣናቱ የእስራኤል የመከላከያ ሠራዊት ታይሪ መንደር ውስጥ ጋዜጠኞችን ለማትረፍ እየሄደ የነበረ አምቡላንስ ሆነ ተብሎ ዒላማ መደረጉን ጨምረው ተናግረዋል።የ43 ዓመቷ ካሊል በሊባኖስ ለሚታተም አል-አክባር ለሚባል ጋዜጣ ትሰራነበር። በመኪና ውስጥ የነበሩት እና በጥቃቱ የተገደሉት ሁለት ሰዎች ስም አልተገለጸም።የእስራኤል መከላከያ ሠራዊቱ የሕይወት አድን ቡድኖች ወደ አካባቢው እንዳይደርሱ ከልክሏል መባሉን አስተባብሎ ጋዜጠኞችን ዒላማ እንዳላደረገ ተናግሯል።ያጋሩ, እስራኤል ጋዜጠኛን ዒላማ ያደረገ የአየር ጥቃት ፈጽማለች ስትል ሊባኖስ ከሰሰች
  6. ከ 2 ሰአት በፊትየቱርክ ፕሬዚዳንት የኢራን ጦርነት “አውሮፓን ማዳከም” ጀምሯል አሉየቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲብ ታይብ ኤርዶጋንየፎቶው ባለመብት,Reutersየቱርክ መሪ ረሲብ ታይብ ኤርዶጋን ከጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴህንሚየር ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት ወቅት የኢራን ጦርነት “አውሮፓን ማዳከም” ጀምሯል አሉ።የቱርክ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ባጋራው ጽሑፍ ሁለቱ መሪዎች በስልክ የተወያዩት ረቡዕ ዕለት መሆኑን አስታውቋል።ፕሬዚዳንቶቹ በውይይታቸው የሁለቱን አገራት ግንኙነት፣ በኢራን እና የዩክሬን እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶችን አንስተው ተወያይተዋል።ጽህፈት ቤቱ በልጥፉ “ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን በቀጣናችን እየተካሄደው ያለው ጦርነት አውሮፓን ማዳከም መጀመሩን አንስተዋል፤ እንዲሁም ሰላም ተኮር በሆነ አቀራረብ የሚቀረፍ ካልሆነ በጦርነቱ ወቅት የሚደርሰው ውድመት እጅግ የባሰ ይሆናል” ሲል የፕሬዝዳንቱን ንግግር ጠቅሷል።ያጋሩ, የቱርክ ፕሬዚዳንት የኢራን ጦርነት “አውሮፓን ማዳከም” ጀምሯል አሉ
  7. ከ 3 ሰአት በፊትዋይት ሐውስ ኢራን በየቀኑ 500 ሚሊዮን ዶላር እያጣች ነው አለየዋይት ሐውስ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ካሮሊን ሌቪትየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ያራዘሙት በጦርነቱ የተጎዳው የኢራን አመራር በመፍረክረኩ እና ግጭቱን ለማስቆም የሚያስችል ምክረ ሃሳብ ለማቅረብ ጊዜ ስለሚያስፈልገው መሆኑን ተናገሩ።በተጨማሪም አሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡ ሆነ የሚወጡ መርከቦች ላይ የጣለችው ክልከላ አሁንም ተፈጻሚ እንደሚሆን ተናግረዋል።ይህ እርምጃ ኢራን ላይ ምጣኔ ሀብታዊ ጫና ለመፍጠር ያሰበ ሲሆን ቴህራን በበኩሏ እንደ ጦርነት እርምጃ ቆጥራዋለች።የዋይት ሐውስ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ካሮሊን ሌቪት የአሜሪካ ዕቅድ እየሰራ መሆኑን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።”በዚህ እገዳ ኢኮኖሚያቸውን ሙሉ በሙሉ አንቀን ይዘነዋል። በቀን 500 ሚሊዮን ዶላር እያጡ ነው። የኻርግ ደሴት ሙሉ በሙሉ ሞልቷል። የነዳጅ ዘይት ማስገባትም ሆነ ማሰወጣት አይችሉም” ብለዋል።”ፕሬዝዳንት ትራምፕ በእነሱ ላይ ባደረሱት በዚህ የኢኮኖሚ ጫና ምክንያት ለሠራተኞቻቸው እንኳን ደመወዝ መክፈል አይችሉም” ሲሉም ገልጸዋል።የተራዘመው የተኩስ አቁም ስምምነት የሚያበቃበት ቀን ባይቀመጥም፣ ኢራን የሆርሙዝን የባህር ወሽመጥ ዳግም እንደማትከፍት በመግለጿ ሁለቱ ወገኖች ተፋጥጠዋል።ዋይት ሐውስ ትራምፕ በሁኔታው ደስተኛ መሆናቸውን ሲገልጽ አሜሪካ አሁንም ወሽመጡም ሆነ የኢራን ጉዳይ በቁጥጥሯ ሥር እንደሆነ ገልጸዋል።ያጋሩ, ዋይት ሐውስ ኢራን በየቀኑ 500 ሚሊዮን ዶላር እያጣች ነው አለ
  8. ከ 4 ሰአት በፊትአሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ካራዘመች በኋላ ኢራን ለሰላም ድርድር ክፍት መሆኗን ገለጸችየኢራን ባንዲራ የያዙ ሰዎችየፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockፓኪስታን በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ለሚደረገው ሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር ዝግጅቷን ቀጥላለች።ነገር ግን ከአሜሪካ ወይም ከኢራን የተውጣጡ ልዑካን ቡድን ይሳተፉ እንደሆን እስካሁን ማረጋገጥ አልተቻለም።የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ቴህራን አሁንም ለውይይት ክፍት እንደሆነች ቢናገሩም፣ የአሜሪካ “ስምምነቶችን መጣስ፣ እገዳ እና ዛቻዎች ለእውነተኛ ድርድር ዋና ዋና እንቅፋቶች ናቸው” ብለዋል።ዓለም “ማለቂያ የሌለውን ግብዝነት የተሞላበት ንግግር እያየ” ነው ሲሉም አክለዋል።የአሜሪካን ልዑክ እንደሚመሩ የሚጠበቁት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ አሁንም በአሜሪካ ይገኛሉ።ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ረቡዕ ዕለት ሊጠናቀቅ የነበረውን የተኩስ አቁም ስምምነት አራዝመዋል።ከኢራን ጋር እያደረጉት ያለው ጦርነት መቼ እንደሚቆም “ የጊዜ ገደብ አልተቀመጠም” ሲሉ አክለዋል።የዋይት ሐውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮላይን ሌቪት እንደተናገሩት የተራዘመው ተኩስ አቁም የሚያበቃበት የጊዜ ገደብ የለውም።በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ዙሪያ ውጥረቱ ቀጥሏል። የኢራን ዋነኛ ተደራዳሪ አሜሪካ እና እስራኤል “የተኩስ አቁም ስምምነቱን በግልጽ በመጣሳቸው” ውሳኙ የባሕር መተላለፊያ ሊከፈት “አይቻልም” ብለዋል።ያጋሩ, አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ካራዘመች በኋላ ኢራን ለሰላም ድርድር ክፍት መሆኗን ገለጸች
  9. 22 ሚያዚያ 2026ትራምፕ ከኢራን ጋር በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ሁለተኛው ዙር ድርድር ሊደረግ እንደሚችል ተናገሩዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገው ሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር አርብ ዕለት “ሊጀመር ይችላል” ማለታቸውን ኒውዮርክ ፖስት ዘገበ።ጋዜጣው የፓኪስታን ባለሥልጣናትን ጠቅሶ “ከ36 እስከ 72 ሰዓታት” ባሉት ጊዜያት ውስጥ ውይይቱ ሊጀመር እንደሚችል ዘግቧል።የፓኪስታን ባለሥልጣናት ያሉትን በሚመለከት የተጠየቁት ትራምፕ በጽሑፍ መልዕክት “ሊሆን ይችላል!” በማለት መልሰዋል።ትራምፕ ረቡዕ ዕለት የሚያበቃውን የሁለቱን አገራት የተኩስ አቁም በትናንትናው ዕለት ሲያራዝሙ የኢራን አገዛዝ ጦርነቱን ለማቆም የሚያስችል “የተቀናጀ ሀሳብ” ለማምጣት ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፍለገው ተናግረው ነበር።ያጋሩ, ትራምፕ ከኢራን ጋር በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ሁለተኛው ዙር ድርድር ሊደረግ እንደሚችል ተናገሩ
  10. 22 ሚያዚያ 2026ኢራን ምን ያህል የዩራኒየም ክምችት አላት?የኢራን ሳይንቲስቶችየፎቶው ባለመብት,Getty Images/BBCአሁኑ ባለው ድርድር ውስጥ ዋነኛው መነጋገሪያ የኢራን የበለፀገ የዩራኒየም ክምችት ምን መሆን አለበት የሚለው ነው።ጦርነቱ ሲጀመር ኢራን 440 ኪሎ ግራም ዩራኒየም እንዳላት እና ይህም 60 በመቶ የበለጸገ መሆኑን አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ተናግረው ነበር።ይህም ጦር መሣሪያ ለማምረት ወደሚያስችለው 90 በመቶ የበለጸገ ዩራኒየም በአንፃራዊነት በፍጥነት ሊያድግ ይችላል።ኢራን በተጨማሪም 20 በመቶ ድረስ የበለጸገ 1,000 ኪሎ ግራም፣ እንዲሁም 3.6 በመቶ ገደማ የበለጸገ 8,500 ኪሎ ግራም ዩራኒየም አላት።ይህም በተለምዶ ለሰላማዊ አገልግሎት ማለትም ለኃይል ማመንጨት ወይም ለሕክምና ምርምር ይውላል።ወደ ኒውክሌር ጦር መሣሪያነት ሊቀየር የሚችለው በከፍተኛ ደረጃ የበለፀገ ዩራኒየም በአብዛኛው በኢስፋሃን እንደተከማቸ ይታመናል። ተቋሙ ባለፈው ዓመት በአሜሪካ እና በእስራኤል የአየር ድብደባ ዒላማ ከተደረጉት የኢራን ሦስት የመሬት ውስጥ የኒውክሌር ጣቢያዎች አንዱ ነው።ይሁን እንጂ በከፍተኛ ደረጃ ከበለፀገው ዩራኒየም ምን ያህል በሌሎች ቦታዎች እንደተከማቸ ግልጽ አይደለም።ምንጮች እንደሚሉት ቴህራን ለ20 ዓመት ኒውክሌር እንዳታበለጽግ የተቀመጠውን እገዳ ውድቅ አድርጋለች። በምትኩ ጦርነቱ ከመፈንዳቱ በፊት ያቀረበችውን የአምስት ዓመት ገደብ ለድርድር አቅርባለች።በተጨማሪም 440 ኪሎ ግራም የበለፀገውን የዩራኒየም ክምችት እንድታስረክብ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርጋለች።ይህም ቀደም ሲል 60 በመቶ የበለፀገውን ዩራኒየሟን ለማዳከም በሚለው አቀወማ ጸንታለች።የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ኃላፊ ራፋኤል ግሮስ ባለፈው ዓመት በጥቅምት ወር ለኤፒ እንደተናገሩት ይህ መጠን የበለጠ ቢበለጽግ 10 የኒውክሌር ቦምቦች ለማምረት በቂ ይሆናል።ኢራን የበለጸገ የዩራኒየም ክምችት አላት? የኒውክሌር ጦር መሣሪያ መገንባት ትችላለች?ያጋሩ, ኢራን ምን ያህል የዩራኒየም ክምችት አላት?
  11. 22 ሚያዚያ 2026የኮንዶም ዋጋ በኢራን ጦርነት ምክንያት በ30 በመቶ ሊጨምር ይችላል ተባለኮንዶምየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየዓለማችን ግዙፉ የኮንዶም አምራች ኩባንያ ካሬክስ ኃላፊ በኢራን ጦርነት ምክንያት ለምርቶቹ የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች አቅርቦት ማስተጓጎሉን ከቀጠለ ኩባንያው ዋጋውን እስከ 30 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ እንደሚጨምር አስታወቁ።የካሬክስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጎህ ሚያህ ኪያት ለመገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት ግጭቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የምርት ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።ማሌዥያ የሚገኘው ይህ ኩባንያ በዓመት ከአምስት ቢሊዮን በላይ ኮንዶሞችን ያመርታል።ዘንድሮ የኮንዶም ፍላጎት በ30 በመቶ ገደማ ጭማሪ ያሳየ ቢሆንም የጭነት ወጪ በመጨመሩ እና የመርከብ ጉዞ መስተጓጎል እየተባባሰ በመምጣቱ እጥረት መፈጠሩን ጎህ ተናግረዋል።”በአስቸጋሪ ጊዜያት ኮንዶም የመጠቀም አስፈላጊነት የሚጨምረው የወደፊት ሕይወትን፣ በሚቀጥለው ዓመት ሥራ ይኖርዎት እንደሆነ እርግጠኛ ስላልሆኑ ነው” ሲሉ ለብሉምበርግ ተናግረዋል።”አሁን ልጅ ከወለዱ፣ ሌላ ተጨማሪ ሰው መመገብ ይኖርብዎታል” ሲል አክሏል።የዓለማችን ግዙፉ የኮንዶም አምራች በኢራን ጦርነት ምክንያት የዋጋ ጭማሪ ሊያደርግ ነውያጋሩ, የኮንዶም ዋጋ በኢራን ጦርነት ምክንያት በ30 በመቶ ሊጨምር ይችላል ተባለ
  12. 22 ሚያዚያ 2026የሊባኖስ የተኩስ አቁምን ለማራዘም ንግግር እየተደረገ መሆኑን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ገለጹየሊባኖስ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ አውንየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የሊባኖስ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ አውንየሊባኖስ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ አውን አገራቸው ከእስራኤል ጋር የጀመረችውን የአስር ቀን “የተኩስ አቁም ስምምነት የጊዜ ገደብ ለማራዘም” ንግግር እየተደረገ መሆኑን ገለፁ።ሊባኖስ እና እስራኤል ሐሙስ ዕለት በዋሺንግተን ተገናኝተው ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል። በሁለቱ አገራት መካከል የአስር ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት የተደረሰው ባለፈው ሳምንት ነበር።አውን በኤክስ ገጻቸው ላይ ውይይቶቹ የተዘጋጁት “የእስራኤል ጥቃት ሙሉ በሙሉ በሚቆምበት፣ እስራኤል ከሊባኖስ ግዛቶች ለቅቃ በምትወጣበት፣ እስረኞችን በመመለስ፣ በዓለም አቀፍ ድንበሮች አካባቢ ወታደሮች በማሰማራት እና በጦርነቱ የወደሙትን መልሶ በመገንባት ላይ ነው።”አውን የሊባኖስ አቋምን ሲናገሩ “የምንደራደርበት ግልጽ ነው፤ ከሊባኖስን ሉዓላዊነት እና ጥቅም በስተቀር ምንም ዓይነት ስምምነት፣ ድርድር፣ እጅ መስጠት አይኖርም” ብለዋል።ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ልጥፋቸው ላይ ከአሜሪካ የተገኘው ድጋፍ ለሊባኖስ “ማባከን የሌለብንን ዕድል” ፈጥሮልናል ብለዋል።ያጋሩ, የሊባኖስ የተኩስ አቁምን ለማራዘም ንግግር እየተደረገ መሆኑን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ገለጹ
  13. 22 ሚያዚያ 2026የነዳጅ ዋጋ በመናሩ የጀመርን አየር መንገድ 20 ሺህ በረራዎችን ሊያቆም ነውየሉፍታንዛ አውሮፕላኖችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት የጀርመን አየር መንገድ፣ ሉፍታንዛ፣ በመጪዎቹ ወራት በአውሮፓ ውስጥ የሚያደርጋቸውን 20 ሺህ የአጭር ርቀት በረራዎችን እንደሚያቆም አስታወቀ።አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር ጦርነት ከጀመሩ በኋላ የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በእጥፍ በመጨመሩ የአጭር ርቀት በረራዎችን አክሳሪ አድርጓቸዋል።በዚህም ምክንያት በርካታ አየር መንገዶች በረራዎቻቸውን የቀነሱ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ በትኬት ዋጋቸው ላይ ጭማሪ አድርገዋል።ጦርነቱ የሚካሄድበት የባሕረ ሰላጤው አካባቢ የአውሮፕላን ነዳጅ ዋነኛው ምንጭ ሲሆን፣ አብዛኛው ነዳጅም በጦርነቱ ምክንያት በተዘጋው በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚተላለፍ ነው።የአውሮፓ አገራት ያላቸው የአውሮፐላን ነዳጅ ክምችት እየተሟጠጠ ባለበት በአሁኑ ጊዜ፣ ክምችቱ በሳምንታት ውስጥ ሊያልቅ እንደሚችል ዓለም አቀፉ የኤነርጂ ተቋም አስጠንቅቋል።ሉፍታንዛ እንዳስታወቀው በአውሮፓ ውስጥ የሚያደርጋቸውን በረራዎች በከፍተኛ መጠን የሚቀንስ ቢሆንም፣ የረጅም ርቀት ዓለም አቀፍ በረራዎቹ ባሉበት ይቀጥላሉ።የአየር ትራንስፖርት ተንታኞች እንደሚሉት በመካከለኛው ምሥራቅ የሚካሄደው ጦርነት ከቀጠለ በአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ላይ የበለጠ ጭማሪ እንደሚደረግ እንዲሁም በርካታ በረራዎች እንደሚሰረዙ አስጠንቅቀዋል።ያጋሩ, የነዳጅ ዋጋ በመናሩ የጀመርን አየር መንገድ 20 ሺህ በረራዎችን ሊያቆም ነው
  14. 22 ሚያዚያ 2026ኢራን ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ‘አስፈላጊውን እርምጃ’ እንደምትወስድ ገለጸችኢስማኤል ባጋይየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ኢስማኤል ባጋይበኢራን እና በአሜሪካ መካከል የሚካሄደው ድርድር እየተጠበቀ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ኢራን ብሔራዊ ጥቅሟን እንደምታስከብር አሳወቀች።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይ በቴሌግራም ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ አገራቸው “ብሔራዊ ጥቅሞቿን እና ደኅንነቷን ለመጠበቅ አስፈላጊ እና ተገቢውን እርምጃ ትወስዳለች” ብለዋል።ቃል አቀባዩ ጨምረውም ከአሜሪካ ጋር የሚደረገውን ድርደር እያሸማገለች ባለችው ፓኪስታን በኩል እየቀረበ ያለውን የተኩስ አቁም ጥያቄን በተመለከተ አገራቸው በፖለቲካው መስክ ያለው ሁኔታ “በቅርበት እየተከታተለች” መሆኗን መግለጻቸውን የኢራን የዜና ወኪል ኢርና ዘግቧል።ለሁለት ሳምንት የቆየው የተኩስ አቁም ሲጠናቀቅ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ያለው መንግሥት “በከባድ ሁኔታ መፍረክረኩን” በመጥቀስ ከፓኪስታን በኩል የቀረበላቸውን ጥያቄ መቀበላቸውን አሳውቀዋል።ቃል አቀባዩ ባጋይ ከአሜሪካ ጋር ስለሚደረግ ቀጣይ ድርድር ተጠይቀው “ዲፕሎማሲ ብሔራዊ ጥቅም እና ደኅንነትን የማስጠበቂያ መሳሪያ ነው፤ ይህንን ለመጠቀም አስፈላጊ እና አሳማኝ ሁኔታ መኖሩን ስናረጋግጥ. . . እርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል።ያጋሩ, ኢራን ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ‘አስፈላጊውን እርምጃ’ እንደምትወስድ ገለጸች
  15. 22 ሚያዚያ 2026ሆርሙዝ ላይ ሦስት መርከቦች ጥቃት ሲፈጸምባቸው፣ ኢራን ሁለት መርከቦችን በቁጥጥር ስር አዋለችበኢራን ከተያዙ የጭነት መርከቦች አንዷየፎቶው ባለመብት,Agustin Alapontየምስሉ መግለጫ,በኢራን ከተያዙ የጭነት መርከቦች አንዷየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በፈጸመው ጥቃት ሦስት የጭነት መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ መመታታቸውን የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።አብዮታዊ ዘቡ እርምጃ ከወሰደባቸው ሦስት የጭነት መርከቦች መካከል ሁለቱን እንደያዘ አስታውቋል።በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያለው የመርከቦች እንቅስቃሴ በኢራን እና በአሜሪካ ኃይሎች ማስጠንቀቂያ ውስጥ ባለበት ጊዜ ኢራን መመሪያዋን አልተከተሉም ባለቻቸው መርከቦች ላይ እርምጃ እየወሰደች ነው።ጥቃት 1:የዩናይትድ ኪንግደም የባሕር ትራንስፖርት ንግድ ማዕከል እንዳሳወቀው የአብዮታዊ ዘቡ “አጥቂ ጀልባ” በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ሲጓዝ በነበረ የግሪክ ኩባንያ ንብረት በሆነ ኮንቴይነሮችን በጫነት መርከብ ላይ ተኩስ ከፍቶ ከባድ ጉዳት አድርሷል።ጥቃት 2:በተጨማሪም የተለያዩ ምንጮች እንዳረጋገጡት ንብረትነቱ የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የሆነ እና የፓናማን ሰንደቅ ዓላማ በሚያውለበልብ መርከብ ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። በመርከቡ እና በሠራተኞቹ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰም ተብሏል።ጥቃት 3:የባሕር ትራንስፖርት ደኅንነት ተቋም የሆነው ቫንጋርድ ለቢቢሲ እንዳሳወቀው ሌላ የፓናማን ሰንደቅ ዓላማ የሚያለውበልብ መርከብ ከሆርሙዝ ወሽመት በሚወጣበት ጊዜ የጥቃት ዒላማ ሆኗል። በጥቃቱም በመርከቡ የተለያዩ ክፍሎች ላይ ጉዳት እንደደረሰበት ተዘግቧል።የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጥቃት ከተፈጸመባቸው ሦስት መርከቦች ሁለቱ “ፈቃድ ሳያገኙ እና የመርከብ እንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ ሥርዓታቸውን በማጥፋታቸው” በቁጥጥር ስር ውለው ወደ ኢራን የባሕር ዳርቻ መወሰዳቸውን አስተውቋል።ያጋሩ, ሆርሙዝ ላይ ሦስት መርከቦች ጥቃት ሲፈጸምባቸው፣ ኢራን ሁለት መርከቦችን በቁጥጥር ስር አዋለች
  16. 22 ሚያዚያ 2026ትንታኔ፡ ባሕረ ሰላጤው ከ1990 ወዲሀ ያጋጠመው አስከፊ ቀውስአነስተኛ ጀልባየፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራንእና የአሜሪካ ግጭት አሁን አደገኛ በሆነ ውጥረት ውስጥ ይገኛል። አደገኛ የሆነበት ዋናው ምክንያት ሁለቱም ወገኖች እርስ በእርሳቸው ስለማይተማመኑ ነው።ኢራን ዶናልድ ትራምፕ ለድንገተኛ ጥቃትጊዜ ለመግዛት በሚል የተኩስ አቁሙን አራዝመዋል የሚል እምነት አላት።ሌላው የአሜሪካ ባሕር ኃይል የኢራን ወደቦችን ዘግቶም ወደ ኢዝላማባድ ለሰላም ድርድር ላለመሄድ አሻፈረኝ ብላለች።ምንም እንኳ የተኩስ አቁሙ ላልተወሰነ ጊዜ ቢራዘምም ሁኔታው ግን የሚያረካ አይደለም።የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ለሚንቀሳቀሱበት እጅግ በጣም ጥቂት መርከቦች በጣም አደገኛ ነው። የኢራን የጦር ጀልባዎች ለማለፍ በሚሞክሩ መርከቦች ላይ ተኩስ እየከፈቱ ነው።አሜሪካ ግን ጦሯ ወደ ኢራን ወደቦች ወይም ከወደቦቹ የሚመጡ ከ20 በላይ መርከቦችን መመለሱን ተናግራለች።ውጤቱ በኢራንም ሆነ በዓለም ኢኮኖሚላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው። ይህ ግጭት በቀጠለ ቁጥር በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው ተጽእኖ እየባሰ ይሄዳል።እንዲሁም በባህረ ሰላጤው ውስጥ የለየለት ጦርነትን የማስነሳት አቅሙ ይጨምራል።አሜሪካ የኢራንን የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ለመደብደብ ብትሞክር ኢራን ደግሞ በአጎራባች የአረብ ባሕረ ሰላጤ አገሮች ላይ የአጸፋ እርምጃ ትወስዳለች።ይህ የባህረ ሰላጤው ቀውስ ኢራቅ ኩዌትን ከወረረችበት እአአ ከ1990 ወዲህ የተከሰተ የከፋው አለመረጋጋት ነው።ያጋሩ, ትንታኔ፡ ባሕረ ሰላጤው ከ1990 ወዲሀ ያጋጠመው አስከፊ ቀውስ
  17. 22 ሚያዚያ 2026ትራምፕ የተኩስ አቁሙን ካራዘሙ በኋላ በሆርሙዝ ላይ የሚንቀሳቀሱ ሦስት መርከቦች ጥቃት ተፈጸመባቸውየሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚቀዝፍ የጭነት መርከብየፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን ረቡዕ ዕለት በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ ኮንቴይነር በጫኑ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸሟ ተገለፀ።የኢራን አብዮታዊ ዘብ አባላት ረቡዕ ጠዋት ሦስት መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸማቸው የተገለፀ ሲሆን ይህም የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የተኩስ አቁሙን ላልተወሰነ ጊዜ ካራዘሙ በኋላ የደረሰ ነው።የብሪታኒያ ጦር አካል የሆነው የዩኬ ባሕር ትራንስፖርት ማዕከል ሦስት መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጾ አንደኛው ጉዳት እንደደረሰበት አስታውቋል።የዩናይትድ ኪንግደም የባህር ትራንስፖርት ማዕከል የመጀመርያው መርከብ ላይ ጥቃት ከተፈጸመ ጥቂት ሰዓታት በኋላ ሁለት መርከቦች ላይ ተኩስ እንደተከፈተ ገልጿል።እስካሁን ድረስ በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አልተሰማም።ጥቃት የተፈጸመባቸው ሁለት መርከቦች በግሪክ እና ዩኤኢ ባለቤትነት የተያዙ መሆናቸው ተገልጿል።የባህር ትራንስፖርት ላይ ክትትል የሚያደርገው ማዕከል በሁለቱ መርከቦች ላይ ጥቃት የፈጸመው ማን እንደሆነ ወዲያውኑ አለመታወቁን ገልጿል።ነገር ግን የመጀመርያው መርከብ ላይ ጥቃት የፈጸሙት የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጀልባዎች ሁለቱ መርከቦች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል የሚል ግምት አለ።የኢራን መንግሥት ጠንካራ ደጋፊዎች የተኩስ አቁሙ ከተጀመረ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ማክሰኞ ምሽት በመላ አገሪቱ ሚሳዔሎችን እና ማስወንጨፊያዎችን በአደባባይ በማሳየት ሠልፎችን አካሂደዋል።አሜሪካ እና እስራኤል የሚፈጽሙትን የአየር ድብደባ ካቆሙ በኋላ ኢራን ወደ እስራኤል እና የባሕረ ሰላጤው አገራት የምትተኩሳቸውን ድሮኖች እና ሚሳዔሎች አቁማለች።ረቡዕ ዕለት በወሽመጡ ላይ በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የተሰነዘረው ጥቃት እና ቀደም ሲል አሜሪካ የኢራን መርከቦችን መከልከሏ ስጋቱ አሁንም በወሽመጡ ላይ መቀጠሉን ያሳያል።ትራምፕ አሜሪካ የኢራንን ወደቦች መዝጋት እንደምትቀጥል የተናገሩ ሲሆን ኢራን ደግሞ እርምጃው “ተቀባይነት እንደሌለው” በመግለጽ በኢዝላማባድ በሚደረገውውይይት ላይ ሳትሳተፍ ቀርታለች።የአብዮታዊ ጥበቃ ዘብ ረቡዕ ዕለት “በቀጣናው ውስጥ በሚገኙ ንብረቶቹ ላይ ከጠላት አስተሳሰብ በላይ ከባድ የሆነ ጥቃት እንደሚፈጽም” ዝቷል።ያጋሩ, ትራምፕ የተኩስ አቁሙን ካራዘሙ በኋላ በሆርሙዝ ላይ የሚንቀሳቀሱ ሦስት መርከቦች ጥቃት ተፈጸመባቸው
  18. 22 ሚያዚያ 2026የኢራን አማካሪ የትራምፕ የተኩስ አቁም ስምምነት ‘ምንም ማለት አይደለም’ አሉየኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ አማካሪ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተኩስ አቁም ማራዘሚያ “ምንም ማለት እንዳልሆነ” እና “ለድንገተኛ ጥቃት ጊዜ ለመግዛት የሚያስችል ብልሃት” ነው ሲሉ ተናገሩ።ማህዲ ሞሐመድ በኤክስ ገጻቸው ላይ በፋርስ ቋንቋ ባጋሩት ጽሑፍ፣ የትራምፕ “ከበባ” መቀጠል “ከቦምብ ድብደባ የተለየ አይደለም” በማለት “ወታደራዊ ምላሽ መሰጠት አለበት” ብለዋል። አክለውም “ኢራን እርምጃ የምትወስድበት ጊዜ ደርሷል” ሲሉ ሃሳባቸውን አጠናክረዋል።ኢራን 20 በመቶ የዓለም ነዳጅ የሚተላለፍበትን ቁልፍ የባህር መስመር ዘግታ ለሳምንታት ከቆየች በኋላ የአሜሪካ የባህር ኃይል ወደ ቴህራን ወደቦች የሚገቡ እና የሚወጡ መርከቦች ላይ እግድ ጥሏል።እሁድ ዕለት ጦሩ የኢራን ባንዲራን የምታውለበልብ የጭነት መርከብ በቁጥጥር ስር አውሏል።ያጋሩ, የኢራን አማካሪ የትራምፕ የተኩስ አቁም ስምምነት ‘ምንም ማለት አይደለም’ አሉ
  19. 22 ሚያዚያ 2026በኢራን በጦርነቱ ምክንያት ቢያንስ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሥራቸውን ማጣታቸው ተገለጸበኢራን የዋጋ ግሽበትና ሥራ አጥነት በስፋት እየታየ ነውየፎቶው ባለመብት,EPAየምስሉ መግለጫ,በኢራን የዋጋ ግሽበትና ሥራ አጥነት በስፋት እየታየ ነውኢራን ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር በተፈጠረ ጦርነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከፍተኛ የሆነ የሠራተኛ ቅነሳ ለማድረግ ተገድዳለች።ምክትል የሥራና የማኅበራዊ ዋስትና ሚኒስትሩ ጎላምሆሴይን መሐመድ ከሁለት ቀናት በፊት በጦርነቱ ምክንያት ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሥራቸውን አጥተዋል ብለዋል።ሰፊው የሠራተኞች ቅነሳ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በኢራናውያን መካከል ትልቅ የመነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል።ተፅዕኖው የአየር ድብደባ ተፈጽሞባቸው የተዘጉ ፋብሪካዎች ብቻ የሚመለከት አይደለም። ሌሎች አምራቾችን፣ ቸርቻሪዎችን፣ የአስመጪና ላኪ ንግድ ድርጅቶችን እና ዲጂታል ዘርፉንም ጎድቷል።”ከባቡር ጣቢያዎች ባዶነት መመልከት ትችላላችሁ” ሲል አንድ ተጠቃሚ በኤክስ ገጹ ላይ ለጥፏል። ሌላ ግለሰብ በበኩሉ “በቢሯችን አቅራቢያ ካሉት የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች ባዶነት ማየት ትችላላችሁ”ሲል የተፈጠረውን የሥራ አጥነት ስፋት ለመግለጽ ሞክሯል።”ከዋናው አውራ ጎዳና ባዶነት መረዳት ትችላላችሁ።አንድ ሰዓት ተኩል የሚፈጅብኝን በግማሽ ሰዓት ብቻ ነው የደረስኩት” ሲል ሌላ አስተያየት ሰጪ ተናግሯል።ጦርነቱ በሸማቾች ወጪ ላይም አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል። ብዙ ሰዎች አስፈላጊ ነገሮችን መሸመት በመተዋቸው እንደ ቱሪዝም፣ ምግብ ቤቶች እና የሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮች ውጭ ባሉ ሌሎች የችርቻሮ ነጋዴዎች ላይ ጫና ፈጥሯል።የኢራን ባለሥልጣናት ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ኢንተርኔት ላይ የጣሉት ገደብ በአገሪቱ በአንፃራዊነት እያደገ ባለው የቴክኖሎጂና የዲጂታል ዘርፎች ላይም ተጽዕኖ አሳድሯል።ባለሥልጣናት ኢንተርኔት ለመዝጋት የወሰኑት ከደህንነት ጋር በተያያዘ ነው። ይህም ክትትል፣ ስለላ እና የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።የኢራን የኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሳታር ሀሺሚ በጥር ወር እንደተናገሩት የኢንተርኔት መቆራረጥ በየቀኑ ኢኮኖሚውን ቢያንስ 35 ሚሊዮን ዶላር ያሳጣል።በዚህ አሃዝ መሠረት፣ ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ለ52 ቀናት የኢንተርኔት መዘጋት የኢራንን ኢኮኖሚ ከ1.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ አሳጥቷል።ያጋሩ, በኢራን በጦርነቱ ምክንያት ቢያንስ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ሥራቸውን ማጣታቸው ተገለጸ
  20. 22 ሚያዚያ 2026የሊባኖስ መገናኛ ብዙኃን በእስራኤል ጥቃት አንድ ሰው መገደሉን ዘገቡእስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በሚገኝ መንደር ትናንት በፈጸመችው ጥቃት በመስጊድ ላይ ጉዳት ደርሷልየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በሚገኝ መንደር ትናንት በፈጸመችው ጥቃት በመስጊድ ላይ ጉዳት ደርሷልየእስራኤል ጦር በደቡብ ምሥራቅ ቤይሩት ሊታኒያ ወንዝ አካባቢ በፈጸመው ጥቃት አንድ ሰው መገደሉን አና ሁለት መቁሰላቸውን የሊባኖስ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የእስራኤል ወታደሮች ወደ ዋዲ አል ሳሎውቂ ለመሄድ መንገዶችን እየጠረጉ መሆኑን የዘገቡት መገናኛ ብዙኃኑ፣ በደቡብ ሊባኖስ የሚገኙ ቤቶችን እና ሱቆችን “እያፈረሱ” መሆናቸውን ጠቅሰዋል።በትናንትናው ዕለት የእስራኤል ጦር በሊታኒያ ወንዝ አካባቢ እና ሳሎውቂ ለሚገኙ ነዋሪዎች “የሄዝቦላህ የሽብር እንቅስቃሴ ይኖራል” በሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር።ባለፈው ሳምንት ሊባኖስ እና እስራኤል ለአስር ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም መስማማታቸው ይታወሳል።ዋሺንግተን ሐሙስ ዕለት በሁለቱ አገራት መካከል የሚካሄደውን ድርድር ታስተናግዳለች።የተኩስ አቁሙ ስምምነቱ እስራኤል “ከታቀደ፣ ሊደርስ ከሚችል ወይም ጥቃት ሲከፈትባት ራሷን ለመከላከል የትኛውን እርምጃ የመውሰድ መብት አላት” ይላል።በሌላ በኩል ሊባኖስ የሄዝቦላህ እና ሌሎች “ከመንግሥት ውጪ የሆኑ ታጣቂዎች፣ ከእስራኤል በሚገኙ ዒላማዎች ላይ ጥቃት አንዳይፈጽሙ “ተጨባጭ እርምጃዎችን” መውሰድ እንዳለባት ያስቀምጣል።ትናንት ምሽት ሄዝቦላህ የተኩስ አቁሙን በመጣስ በሰሜን እስራኤል ወደሚገኙ ዒላማዎች ሮኬት ማስወንጨፉን ገልጿል።በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ይቼል ሌይተር ሄዝቦላህን የተኩስ አቁሙን በመጣስ ወንጅለውታል።ያጋሩ, የሊባኖስ መገናኛ ብዙኃን በእስራኤል ጥቃት አንድ ሰው መገደሉን ዘገቡ