የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የእስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም በሦስት ሳምንት መራዘሙን አስታወቁ። በሁለቱ አገራት መካከል በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ውይይት ላይ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጄዲ ቫንስ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዩ መገኘታቸው ታውቋል። ውይይቱ “በጥሩ ሁኔታ” ተካሄዷል ያሉት ፕሬዚዳንቱ “ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሊባኖስ ራሷን ከሄዝቦላህ መከላከል እንድትችል በጋራ ትሰራለች” ብለዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 8 ደቂቃዎች በፊትኢራን እና ፓኪስታን “ከተኩስ አቁሙ ጋር በተያያዘ” ተወያዩየኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከፓኪስታን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በግጭቱ ዙሪያ መነጋገራቸው ተሰማ።አባስ አራጋቺ በቴሌግራም ላይ ባጋሩት መግለጫ ከፓኪስታን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሻቅ ዳር እንዲሁም ከመከላከያ አዛዡ ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር ጋር መወያየታቸውን ጠቅሰዋል።በንግግራቸው “በቀጠናዊ ሁኔታዎች እና በተኩስ አቁሙ ዙሪያ” መነጋገራቸውን ገልጸዋል።አራጋቺ ከፓኪስታን ባለሥልጣናት ጋር በነበራቸው ውይይት ያነሱት ከአሜሪካ ጋር ስላላቸው የተኩስ አቁም ይሁን ወይም እስራኤል እና ሊባኖስ ስለደረሱበት ስምምነት ያሉት ነገር የለም።የፓኪስታን ዋና ከተማ ኢዝላማባድ በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ሊደረግ ለሚችል ሁለተኛ ዙር የሰላም ውይይት ዝግጁ ሆና እየጠበቀች ቢሆንም መቼ እንደሚካሄድ እስካሁን ድረስ የታወቀ ነገረ የለም።ያጋሩ, ኢራን እና ፓኪስታን “ከተኩስ አቁሙ ጋር በተያያዘ” ተወያዩ
  2. ከ 27 ደቂቃዎች በፊትየኢራን አመራሮች አንድነታቸውን የሚያሳይ መልዕክት አስተላለፉየኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Images/Mizanፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን አዳዲሶቹን መሪዎች “በሁከት” እና “በከባድ ሁኔታ የተከፋፈሉ ” ናቸው በማለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ገልጸዋል።ቴህራን ደግሞ እኩለ ሌሊት ካለፈ በኋላ ለሁሉም የኢራን የሞባይል ተጠቃሚዎች የጽሑፍ መልዕክት አስተላልፋለች።ፕሬዝዳንት ትራምፕ “ልዩነትን ለመዝራት” ላደረጉት ጥረት ምላሽ ለመስጠት ከፕሬዝዳንቱ፣ ከፓርላማ አፈ ጉባኤው፣ ከፍትህ ሚኒስትሩ እና ከሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተላከ “የጋራ መልእክት” ነው ተብሏል።“ኢራን ውስጥ አክራሪ ወይም ለዘብተኛ የሚባል ነገር የለም” ይላል መልዕክቱ። “ሁላችንም ኢራናውያን እና አብዮታዊ ነን… አንድ አገር፣ አንድ ሃሳብ” ይላል።ባለፈው ሳምንት በኢራን ሚዲያዎች ላይ በአንዳንድ ጥቃቅን ስልታዊ ጉዳዮች የአለመግባባት ምልክቶች በኢስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ዘብ ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በተገናኘ በአገሪቱ መገናኛ ብዙኅን ላይ ታይቷል።መልዕክቱ ከአሜሪካ ጋር በሚደረጉ ድርድሮች ውስጥ አስፈላጊ በሆኑ ዋና ዋና ውሳኔዎች ላይ መግባባት እንደሚሰፍን ለማሳየት የታሰበ ነው።ይህም የኢራንን ጉዳይ በርቀት ለሚከታተሉ ለሳምንታት በጦርነት እና በከፍተኛ የሃይማኖት መሪዎች እና አዛዦች ግድያ ምክንያት ስለመጣው ስርዓት የሚጋሩት ሃሳብ ነው።አሁን ብዙ ውሳኔ ሰጪዎች አሉ። አንዳንዶቹ የበለጠ ተራማጅ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ የበለጠ አክራሪ እንደሆኑ ተደርገው ይታያሉ።ሆኖም ሁሉም ከኒውክሌር ፕሮግራሙ እስከ ሆርሙዝ ወሽመጥ ድረስ ባሉ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ቀይ መስመር ግልጽ ነው።ያጋሩ, የኢራን አመራሮች አንድነታቸውን የሚያሳይ መልዕክት አስተላለፉ
  3. ከ 2 ሰአት በፊትየአውሮፓ ኅብረት በኢራን የሰላም ውይይት ውስጥ የኒውክሌር ባለሙያዎች እንዲሳተፉ ጠየቀየአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊየአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ የኒውክሌር ባለሙያዎች በኢራን የሰላም ድርድር ውስጥ ካልተሳተፉ ከቴህራን የሚሰነዘሩ ማስፈራሪያዎች “የበለጠ አደገኛ” ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናገሩ።ካጃ ካላስ በቆጵሮስ የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ማንኛውም ስምምነት ከዚህ በፊት ከተደረጉት ደካማ የመሆን አደጋ አለው ብለዋል።ኢራን ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ አገራት ጋር እአአ በ2015 የተፈራረመችው ስምምነትን የተቃወሙት ትራምፕ አገራቸውን ማስወጣታቸው ይታወሳል።በዚህ ስምምነት መሠረት ኢራን ሚስጥራዊ የሆኑ የኒውክሌር እንቅስቃሴዎቿን ለመገደብ እና ዓለም አቀፍ ተቆጣጣሪዎች ወደ ቴህራን እንዲገቡ በመፍቀድ በምላሹ የተጣሉባት የኢኮኖሚ ማዕቀቦቹ እንዲነሱ ተስማምታለች።”ውይይቱ ስለ ኒውክሌር (ፕሮግራሙ) ብቻ ከሆነ እና በጠረጴዛው ዙሪያ የኒውክሌር ባለሙያዎች ከሌሉ፣ ከቀደመው ጋር ሲነጻጸር ደካማ የሆነ ስምምነት ላይ እንደርሳለን” ሲሉ ካላስ ስጋታቸውን ገልጸዋል።“እናም በቀጣናው ውስጥ ያሉት ችግሮች፣ የሚሳዔል ፕሮግራሞች፣ ድጋፍ ስለምትሰጣቸው ታጣቂዎች፣ እንዲሁም በአውሮፓ ውስጥ ያሉ የበይነ መረብ እንቅስቃሴዎች ካልተፈቱ፣ የበለጠ አደገኛ የሆነች ኢራን ትሆናለች” ሲሉ ተናግረዋል።ያጋሩ, የአውሮፓ ኅብረት በኢራን የሰላም ውይይት ውስጥ የኒውክሌር ባለሙያዎች እንዲሳተፉ ጠየቀ
  4. ከ 2 ሰአት በፊትየተኩስ አቁም የሊባኖስ መንግሥት ጥያቄ እንደነበር የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር ገለጹየሊባኖስ ማስታወቂያ ሚኒስትር ፖል ሞርኮሰየፎቶው ባለመብት,LIbanos Information Ministerአንድ የሊባኖስ ከፍተኛ ባለሥልጣን መንግሥት የአገሪቱን ጦር በማሰማራት ሄዝቦላህን ትጥቅ ለማስፈታት “ወሳኝ እርምጃዎች” ሊወስድ እንደሚችል ገለፁ።ነገር ግን ይህንን ለማድረግ የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ ጠቅልሎ መውጣት ይኖርበታል ብለዋል።የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር ፖል ሞርኮሰ ለቢቢሲ ኒውስዴይ የተኩስ አቁሙ ለሦስት ሳምንታት እንዲራዘም መንግሥታቸው ጠይቆ እንደነበር ተናግረዋል።ከተኩስ አቁሙ ባሻገር “እስራኤል በሊባኖስ ላይ በአየር፣ በባሕር ወይም በእግረኛ ጦሯ የምትፈጽማቸው ጥቃቶች እንዲቆም” የሚል እንደነበረበት አስረድተዋል።በተኩስ አቁም ስምምነቱ መሠረት ቤይሩት የሄዝቦላህ እና “ሌሎች ከመንግሥት ውጪ የሆኑ ታጣቂዎች” በእስራኤል ዒላማዎች ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት ለመከላከል “ተጨባጭ እርምጃ” መውሰድ አለባት።ሞርኮስ የሊባኖስ መንግሥት የአገሪቱን ጦር በማሰማራት እና ወታደሮች “በሊባኖስ የመሣሪያ የበላይነት እንዲኖረው ለማድረግ”፤ “ተጨባጭ እርምጃዎችን” መውሰዱን ተናግረዋል።ነገር ግን መንግሥት ይህ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት መውሰድ የጀመራቸው እርምጃዎችን የእስራኤል “ወረራ” እና “ጥቃቶች”፤ “ባሉ ለውጦች ላይ እንቅፋት” መሆናቸውን አብራርተዋል።አክለውም “እነዚያን ተጨባጭ እርምጃዎች ሠራዊቱን ወደ ድንበር በማሰማራት ዳግም ለመጀመር ፈቃደኞች ነን” ብለዋል።ያጋሩ, የተኩስ አቁም የሊባኖስ መንግሥት ጥያቄ እንደነበር የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር ገለጹ
  5. ከ 3 ሰአት በፊትትራምፕ ኢራን ላይ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንደማይጠቀሙ ተናገሩትራምፕየፎቶው ባለመብት,EPAአሜሪካ በመደበኛ ሁኔታ ወታደራዊ ዓላማዎቿን አሳክታለች ያሉት ትራምፕ ኢራን ላይ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንደማይጠቀሙ ተናገሩ።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ይጠቀሙ እንደሆን ከጋጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ለምን እፈልገዋለሁ” በማለት ጥያቄውን “የማይረባ” ብለውታል።አክለውም “እኛ ያለ ኒውክሌር ጦር መሣሪያን ሙሉ በሙሉ ካጠፋናቸው ለምን እጠቀማለሁ?” ሲሉ ጠይቀዋል።”የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ማንም ሰው እንዲጠቀምበት ፈጽሞ መፍቀድ የለበትም።”ያጋሩ, ትራምፕ ኢራን ላይ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንደማይጠቀሙ ተናገሩ
  6. ከ 3 ሰአት በፊትበመንግሥታቱ ድርጅት የእስራኤል ልዑክ የተኩስ አቁሙ ግጭትን ስለማስቆሙ እርግጠኛ አይደለሁም አሉበተባበሩት መንግሥታት ውስጥ የእስራኤል አምባሳደር ዳኒ ዳኖንየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ የእስራኤል አምባሳደርበተባበሩት መንግሥታት ውስጥ የእስራኤል አምባሳደር በአገራቸው እና ሊባኖስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ከሄዝቦላህ ጋር የሚኖረውን ግጭት ስለማስቆሙ እርግጠኛ አለመሆናቸውን ተናገሩ።አምባሳደር ዳኒ ዳኖን ለሲኤንኤን “የሊባኖስ መንግሥት ሄዝቦላህ ላይ ምንም ቁጥጥር የለውም” ሲሉ ተናግረዋል።”ሄዝቦላህ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለማደናቀፍ ሮኬቶችን እየተኮሰ ነው፤ እስራኤልም አጸፋውን ልትመልስ ይገባል። ስጋት ባየን ቁጥር እርምጃ እንወስዳለን።”አምባሳደሩ አስተያየታቸውን የሰጡት የሁለቱ አገራት ተደራዳሪዎች በዋይት ሐውስ ተገናኝተው ከተወያዩ እና የተኩስ አቁሙን ለሦስት ሳምንታት ካራዘሙ በኋላ ነው።ስምምነቱን በመጥቀስ “መቶ በመቶ የሚሆን አይመስለኝም” ያሉት አምባሳደሩ “የሊባኖስ ጦር ቢችል እና የተኩስ አቁሙን አስፈጽሞ ባይ. . .ተስፋ አደርጋለሁ ” ሲሉ ተናግረዋል።ያጋሩ, በመንግሥታቱ ድርጅት የእስራኤል ልዑክ የተኩስ አቁሙ ግጭትን ስለማስቆሙ እርግጠኛ አይደለሁም አሉ
  7. ከ 4 ሰአት በፊትሊቀ ጳጳስ ሊዮ አሜሪካ እና ኢራን ወደ ሰላም ድርድሩ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረቡሊቀ ጳጳስ ሊዮ ከኢኳቶሪያል ጊኒ ጉብኝት በኋላ ከጋዜጠኞች ጋር በአውሮፕላን ውስጥ ሲወያዩየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱን ለማስቆም ወዳለመው የሰላም ድርድር እንዲመለሱ ጥሪ አቀረቡ።ጳጰሱ አክለውም ግጭቱ “በኢራን ውስጥ ንፁኃን ዜጎችን በሙሉ ስቃይ ውስጥ ጥሏቸዋል” ብለዋል።ሊቀ ጳጳሱ ይህን አስተያየት የሰጡት ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ከፍተኛ ውዝግብ ውስት ከገቡ በኋላ ነው። አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጦርነት የሚቃወሙትን ጳጳሱን ዶናልድ ትራምፕ በማኅበራዊ ሚደያ ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልዕክት አብጠልጥለዋቸዋል።አራት የአፍሪካ አገሮችን ጎብኝተው ወደ ሮም በተመለሱበት ወቅት “ለሰላም የሚደረገውን ውይይት እንዲቀጥል፣ ሁሉም ወገኖች ሰላምን ለማስፈን፣ የጦርነትን ስጋት ለማስወገድ እና ዓለም አቀፍ ሕግን ለማክበር የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ እጠይቃለሁ” ብለዋል።”እንደ መጋቢ፣ ጦርነትን መደገፍ አልችልም፤ ሁሉም ሰው ከጥላቻና ከመለያየት ሳይሆን ከሰላም ባህል የሚመጡ መልሶችን እንዲፈልግ ማበረታታት እፈልጋለሁ።”ባለፈው ዓመት ሊባኖስ በሄዱበት ወቅት “ፖፕ ሊዮ እንኳን ደህና መጡ” የሚል ወረቀት ይዞ ፎቶ የተነሳውን ሙስሊም ሊባኖሳዊ ሕፃን ምስል አሳይተው “በዚህ ጦርነት [ሕጻኑ] ተገድሏል” ብለዋል።ያጋሩ, ሊቀ ጳጳስ ሊዮ አሜሪካ እና ኢራን ወደ ሰላም ድርድሩ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረቡ
  8. ከ 5 ሰአት በፊትበሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በሦስት ሳምንት ተራዘመምክትል ፕሬዚዳንቱ ጄዲ ቫንስ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዩ  ከፕሬዚዳንት ትራምፕ በስተግራ እና በስተቀን ቆመውየፎቶው ባለመብት,Reutersትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት ሳምንት መራዘሙን አስታወቁየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የእስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም በሦስት ሳምንት መራዘሙን አስታወቁ።በሁለቱ አገራት መካከል በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ውይይት ላይ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጄዲ ቫንስ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዩ መገኘታቸው ታውቋል።ውይይቱ “በጥሩ ሁኔታ” ተካሄዷል ያሉት ፕሬዚዳንቱ “ዩናይትድ ስቴትስ ሊባኖስ ራሷን ከሄዝቦላህ መከላከል እንድትችል በጋራ ትሠራለች” ብለዋል።የዚህ “ታሪካዊ ውይይት” ተሳታፊ መሆን “ትልቅ ክብር” እንደሆነ የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ወደፊት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የሊባኖሱን ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውንን ለመቀበል በጉጉት እንደሚጠባበቁ ተናግረዋል።ትራምፕ፣ የሊባኖሱ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በመጪዎቹ ሳምንታት ወደ ዋይት ሐውስ እንደሚመጡ ተናግረው አገራቸው ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ማደራደር እንደምትፈልግ ገልጸዋል።”ስለ ሄዝቦላህ ማሰብ አለባቸው” ያሉት ትራምፕ፣ “በዚያች አገር ነገሮችን ለማስተካከል ከሊባኖስ ጋር እንሰራለን” ሲሉ ቃል ገብተዋል።አክለውም “ኢራን ውስጥ ከምንሰራው ጋር በአንድ ላይ እንዲሆን ማድረግ አስደናቂ ነገር ይመስለኛል” ብለዋል።በአሜሪካ የሊባኖስ አምባሳደር ናዳ ሃማዴህ ሞዋድ፣ በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ዬቺኤል ሊተር፣ በሊባኖስ የአሜሪካ አምባሳደር ሚሼል ኢሳ እና በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃካቢየፎቶው ባለመብት,Reutersየሁለቱም አገራት ከፍተኛ ተደራዳሪዎቸ የተኩስ አቁሙ በመራዘሙ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።በአሜሪካ የሊባኖስ አምባሳደር ናዳ ሃማዴህ ሞዋድ፣ በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ዬቺኤል ሊተር፣ በሊባኖስ የአሜሪካ አምባሳደር ሚሼል ኢሳ እና በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃካቢ እያንዳንዳቸው ትራምፕን በድርድሩ ውስጥ ላበረከቱት ሚና አወድሰዋል።“ክቡር ፕረዚዳንት፡ በእርስዎ መሪነት ኢራን በጣም ተዳክማለች፤ ሄዝቦላህን የማዳከም እና ሊባኖስን ከወረራ ነፃ የማውጣት ዕድሉ እውን ነው” ያሉት ሌይተር፣ እስራኤል እና ሊባኖስ“ሄዝቦላህ ከተባለ ክፉ ተጽእኖ” ለማፅዳት ዓላማቸው አስተሳስረዋል ብለዋል።ሃክካቢ ሄዝቦላህን በሰፈር ውስጥ በሁሉም ሰው መስኮት ላይ ድንጋይ ከሚወረውር ልጅ ጋር በማመሳሰል ገልጸውታል።ሕፃኑን ማስቆም ከተቻለ በኋላ፣ እንደ ሊባኖስና እስራኤል ያሉ ሌሎች ጎረቤቶች በሰላም ይኖራሉ ሲሉም ያላቸውን ተስፋ ተናግረዋል።ያጋሩ, በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በሦስት ሳምንት ተራዘመ
  9. 23 ሚያዚያ 2026ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ ስለሰነዘሩት ዛቻ ሲጠየቁ “ምንም ነገር ብል፤ ጥሩ እየሰራ ይመስለኛል” አሉየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ቢቢሲ በኢራን ላይ ስለሰነዘሩት ዛቻ ሲጠይቃቸው “ምንም ቢሆን የማደርገው፣ በጣም ጥሩ እየሰራ ይመስለኛል” ሲሉ መለሱ።የቢቢሲ የሰሜን አሜሪካ ኤዲተር ሳራ ስሚዝ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ባደረገችው አጭር የስልክ ቃለ መጠይቅ በዚህ ወር መጀመርያ ላይ የኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያን በመቃወም በሰጡት ማስጠንቀቂያ “ዛሬ ምሽት ሙሉ ስልጣኔ ይጠፋል” ማለታቸውን አስታውሳለች።ፕሬዚዳንት ትራምፕ በምላሻቸው “ሌላኛው ወገን ከስምምነት ለመድረስ እየተሟሟተ ነው” ካሉ በኋላ “ስለዚህ ምንም ነገር ብል፣ ወይም ምንም ነገር ባደርግ ጥሩ እየሰራ ይመስለኛል። በጣም አመሰግናለሁ” ብለዋል።ትራምፕ የሰሜን ጦር ቃልኪዳን (ኔቶ)ን በሚመለከት ከኢራን ጋር በሚያደርጉት ጦርነት “ፈጽሞ አልፈልጋቸውም ነበር” ካሉ በኋላ “ነገር ግን እዚያ መገኘት ነበረባቸው” ብለዋል።ቢቢሲ ኔቶ ጦርነቱን እንዲቀላቀል ለምን እንደፈለጉ ሲጠይቃቸው፣ “ምክንያቱም ይሳተፉ እንደሆን እና እንዳልሆነ ማየት እፈልጋለሁ” ብለዋል።አሜሪካ ምንጊዜም ከዩኬ እና ኔቶ ጎን መሆኗን የጠቀሱት ትራምፕ፣ ዩኬ “ትንሽ እንኳ ጥረት፤ ቢያንስ ጥሩ ቃል” አለመሞከሯን በመጥቀስ ተችተዋል።አክለውም “ከዩናይትድ ኪንግደም የመጡ ብዙ ሰዎች” አገራቸው በጦርነቱ ውስጥ ላለመሳተፍ መወሰኗ “በሚገርም ሁኔታ መጥፎ ውሳኔ” እንደሆነ መናገራቸውን ጠቅሰዋል።ዩናይትድ ኪንግደም አሜሪካ በመካከለኛው ምሥራቅ ለምታካሄደው ጦርነት ለ”መከላከያ” የአየር ጥቃቶች ብቻ እንድትጠቀም ፈቅዳለች።ቀደም ሲል ትራምፕ ከዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ጋር ያላቸው ግንኙነት በተመለከተ ሲናገሩ “የሰሜን ባህርን ከከፈተ” እና “የስደት ፖሊሲያቸው ጠንካራ ከሆነ” “ያገግማል” ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።ነገር ግን “ይህንን ካላደረገ፤ ዕድል ያለው አይመስለኝም” ብለዋል።ያጋሩ, ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ ስለሰነዘሩት ዛቻ ሲጠየቁ “ምንም ነገር ብል፤ ጥሩ እየሰራ ይመስለኛል” አሉ
  10. 23 ሚያዚያ 2026ሊባኖስ፣ ከዋሺንግተኑ ድርድር በፊት አሜሪካ “እስራኤል ላይ ያላትን ተጽዕኖ” እንድትጠቀም ትፈልጋለችየሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላምየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋፍ ሳላምየሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ መንግሥታቸው አሜሪካ ከዋሺንግተኑ ንግግር በፊት “እስራኤል ላይ ያላትን ተጽዕኖ” እንድትጠቀም እንደሚፈልግ ለዋሺንግተን ፖስት ተናገሩ።ናዋፍ ሳላም ለጋዜጣው “አሜሪካ ወደጠራችው ወደዚህ ድርድር እየገባን ያለነው በእስራኤል ላይ ተጽዕኖ ማድረግ የምትችል መሆኑን በማመን ነው” ብለዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሚናቸው ወሳኝ ነበር። ያላቸውን ተጽዕኖ እስራኤል ላይ መጠቀማቸውን ይቀጥላሉ ብለን እናምናለን” ብለዋል።የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ የሚያካሄደውን ዘመቻ እንደቀጠለ ሲሆን ሳላም አገራቸው እስራኤል ግዛታቸውን ሙሉ በሙሉ ለቅቃ እንድትወጣ እንደሚፈልጉ ተናግረው “የደህንነት ቀጣና ከሚባለው ጋር መኖር አንችልም” ብለዋል።እስራኤል ሄዝቦላህ ትጥቁን እንዲፈታ እንድምትፈልግ ተጠይቀው “በአንድ ሌሊት የሚከናወን ነገር አይደለም። ነገር ግን ዋናው ነገር ምንድን ነው ቁርጠኛ መሆናችንን አሳይተናል” ብለዋል።ያጋሩ, ሊባኖስ፣ ከዋሺንግተኑ ድርድር በፊት አሜሪካ “እስራኤል ላይ ያላትን ተጽዕኖ” እንድትጠቀም ትፈልጋለች
  11. 23 ሚያዚያ 2026ትራምፕ የባሕር ኃይሉ ፈንጂ የሚያሰቀምጡ ጀልባዎች ላይ “እንዲተኩስ እና እንዲገድል” አዘዙትራምፕየፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሆርሙዝ ወሽመጥ ፈንጂ የሚያስቀምጥ ማንኛውንም ጀልባ “ተኩሳችሁ ግደሉ” ሲሉ ለባሕር ኃይላቸው ትዕዛዝ ሰጡ።“የአሜሪካ ባሕር ኃይል ማንኛውም ጀልባ ላይ እንዲተኩስ እና እንዲገድል አዝዣለሁ፤ ትናንሽ ጀልባዎች ምንም እንኳን … በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ፈንጂዎችን እያስቀመጡ ይሆናል” ሲሉ በትሩዝ ሶሻል ልጥፋቸው ላይ አስታውቀዋል።“ምንም ማመንታት አያስፈልግም” ያሉት ትራምፕ የአሜሪካ ፈንጂ “አስወጋጆች” ወሽመጡን “አሁን” እያጠሩ ነው ብለዋል።ዶናልድ ትራምፕ የባሕር ኃይላቸውን ፈንጂ የሚያጠምድ ማንኛውም የኢራን ጀልባ ላይ “ተኩሱና ግደሉ” ካሉ በኋላ፣ ኢራናውያን “መሪያቸው ማን እንደሆነ ለማወቅ ተቸግረዋል” ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ጽፈዋል።ትራምፕ በአገሪቱ ውስጥ “ወግ አጥባቂ” እና “ለዘብተኛ” በሆኑ ባለሥልጣናት መካከል ፍትጊያ መኖሩን ጨምረው ተናግረዋል።አሜሪካ የሆርሙዝ ወሽመጥን ሙሉ በሙሉ “እየተቆጣጠረች ነው” ያሉት ፕሬዚዳንቱ ካለ አሜሪካ ፈቃድ አንድም መርከብ እንደማይገባ እና እንደማይወጣ አስታውቀዋል።ያጋሩ, ትራምፕ የባሕር ኃይሉ ፈንጂ የሚያሰቀምጡ ጀልባዎች ላይ “እንዲተኩስ እና እንዲገድል” አዘዙ
  12. 23 ሚያዚያ 2026ሕይወት “ጦርነትም ሰላምም በሌለባት” ኢራንየሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ አጠገብ የሚያልፉ ሰዎችየፎቶው ባለመብት,Anadolu via Getty Imagesአሜሪካ ከቴህራን ጋር የጀመረችውን የተኩስ አቁም ካራዘመች በኋላ በኢራን መደበኛ ሕይወት ቀጥሏል። የኢራን ሪፐብሊክ መንግሥት እስካሁን ድረስ በሁለተኛው ዙር የተኩስ አቁም ስለመሳተፉ በይፋ ያለው ነገር የለም።የተባበሩት መንግሥታት የልማት ኃላፊ አሌክሳንደር ዴ ክሮ ከ30 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኢራን ጦርነት በነዳጅ እና በማዳበሪያ አቅርቦት መስተጓጎል ወደ ድህነት ይገፋሉ ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል።አብዛኛው የዓለም ማዳበሪያ የሚመረተው በመካከለኛው ምሥራቅ ሲሆን አንድ ሦስተኛው የዓለም አቅርቦቶች በሆርሙዝ ባህር ወሽመጥ በኩል ያልፋሉ። ኢራን እና ዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ ወሽመጡን ለመቆጣጠር እየተፋለሙ ነው።ኢራናውያን የምግብ እና የመሠረታዊ ሸቀጣ ሸቀጦች ዋጋ ማሻቀቡን ይናገራሉ። ጦርነቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በአገሪቱ ኢንተርኔት እንደተቋረጠ ነው።ፓርዲሳን መናፈሻየፎቶው ባለመብት,AFPበኢራን ጎዳና የመሪዎቿ ምሰል ተሰቅሎ ይታያልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበጎዳና ላይ መጻሕፍት የሚሸጡ ሰዎችየፎቶው ባለመብት,Anadolu via Getty Imagesከሱቋ ፊት ውሃ የምታርከፈክፍ ሴትየፎቶው ባለመብት,Anadolu via Getty Imagesያጋሩ, ሕይወት “ጦርነትም ሰላምም በሌለባት” ኢራን
  13. 23 ሚያዚያ 2026የቀድሞው የአሜሪካ ዲፕሎማት ኢራን በጦርነት ውስጥ ‘የመቆየት አቅም’ አላት አሉየቀድሞው የአሜሪካ ዲፕሎማት ዴቪድ ሳተርፊልድየፎቶው ባለመብት,CQ Roll Callየቀድሞው የአሜሪካ ዲፕሎማት ዴቪድ ሳተርፊልድ፣ ኢራን የምጣኔ ኃብት ጫና ከአሜሪካ እና ዶናልድ ትራምፕ የበለጠ የመቋቋም አቅም አላት አሉ።ዲፕሎማቱ አሜሪካ ከኢራን ጋር የምታደርገው ጦርነት ውጤት የሚወሰነው “ማን ረዥም ጊዜ [ጦርነት ውስጥ] ይቆያል” በሚለው ነው ብለዋል።“በእኔ እምነት ኢራን ረዥም ጊዜ [ጦርነት ውስጥ] መቆየት ትችላለች” ሲሉ ለቱዴይ ፕሮግራም ተናግረዋል።ዲፕሎማቱ አሜሪካ ሁለቱም ወገኖች ግጭቱ እንዲባባስ በሚያደርጉበት “ቅርቃር” ውስጥ ልትገባ ትችላለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል።ሳተርፊልድ አሜሪካ ወታደራዊ እርምጃዎችን የምታጠናክር ከሆነ ኢራን በፍጥነት በባሕረ ሰላጤው በሚገኙ አገራት ላይ የበለጠ ጉዳት ታደርሳለች ብለዋል።ያጋሩ, የቀድሞው የአሜሪካ ዲፕሎማት ኢራን በጦርነት ውስጥ ‘የመቆየት አቅም’ አላት አሉ
  14. 23 ሚያዚያ 2026የአሜሪካ ጦር በሕንድ ውቅያኖስ የምትቀዝፍ ማዕቀብ የተጣለባት የኢራን መርከብን መያዙን ገለጸከኢራን ነዳጅ የጫነች ማዕቀብ የተጣለባት መርከብየፎቶው ባለመብት,US Department of Defenceየአሜሪካ ጦር ከኢራን ነዳጅ የጫነች ማዕቀብ የተጣለባት መርከብን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።የመከላከያ ቢሮ በኤክስ ገጹ ላይ “የአሜሪካ ጦር ማዕቀብ በተጣለባት አገር አልባ መርከብ፣ ኤም/ቲ ማጅስቲክ ኤክስ፣ በሕንድ ውቅያኖስ በኩል ከኢራን ነዳጅ በማጓጓዝ ላይ ሳለች አስቁሞ ፍተሻ አካሄዷል” ብሏል።ቢሮው ለኢራን “የቁስ ድጋፍ ያደርጋሉ” ተብለው የሚጠረጠሩ መርከቦችን አስቁሞ መፈተሹን አንደሚቀጥል አስጠንቅቋል።የባሕር ትራንስፖርት ክልከላ ማለት ሕግ ተላልፏል ወይም ስጋት ነው ተብሎ የተጠረጠረ መርከብን መፈተሽ ወይም በቁጥጥር ስር ማዋልን ያካትታል።አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ እገዳ ከጣለች ጀምሮ በርካታ መርከቦች እንዲመለሱ ወይንም እንዲቆሙ አድርጋለች።መርከቧ ከኢራን ርቃ በሕንድ ውቅያኖስ ላይ እየቀዘፈች የነበረ እንደሆነ ተገልጿል።ያጋሩ, የአሜሪካ ጦር በሕንድ ውቅያኖስ የምትቀዝፍ ማዕቀብ የተጣለባት የኢራን መርከብን መያዙን ገለጸ
  15. 23 ሚያዚያ 2026ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ከሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መሰሰብብ መጀመሯን አስታወቀችመርከቦች በባሕር ላይየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ከሚተላለፉ መርከቦች የተሰበሰበ የመጀመሪያው የገንዘብ ክፍያ ወደ አገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ አካውንት መግባቱን የኢራን ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባኤ አስታወቁ።ታስኒም የተባለው የኢራን ዜና ወኪል ምክትል አፈ ጉባኤው ሃሚድሬዛ ሐጂ ባቤ ገንዘቡ ገቢ መደረጉን እንጂ ከማን እና እንዴት እንደተሰበሰበ ዝርዝር ማብረሪያ እንዳልሰጡ ዘግቧል።ክፍያው መሰብሰቡን በተመለከተ ከባለሥልጣኑ ባሻገር ቢቢሲ ከገለልተኛ ወገኖች ማረጋገጥ አልቻለም።ከአሜሪካ ጋር የተኩስ አቁም ከመደረጉ በፊት ኢራን በወሳኙ ሆርሙዝ በኩል “ወዳጅ” አገራት ብቻ እንዲተላለፉ የፈቀደች ሲሆን፣ በወሳኙ የባሕር ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦችም እንዲከፍሉ እንደምታደርግ ስትገልጽ ነበር።ይህ የኢራን ውሳኔ በአገሪቱ ፓርላማ ተቀባይነት ያገኘ ቢሆንም የሚከፈለው የገንዘብ መጠን ግን ግልጽ ሳይሆን ቆይቷል።ባለፈው መጋቢት ኢራን አስከ ሁለት ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እያስከፈለች ነው በሚል ክስ የቀረበባት ሲሆን በሕንድ የሚገኘው ኤምባሲዋ ግን ዜናውን አስተባብሏል።ሌላ የኢራን ፓርላማ አባል “ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ከሚተለላፉ መርከቦች ገንዘብ መሰብሰቧን ከአስተማማኝ ምንጮች ሰምቻለሁ” ሲሉ ለታስኒም ዜና ወኪል አረጋግጠዋል።ጨምረውም “ከእያንዳዱ መርከብ የሚሰበሰበው የገንዘብ መጠን መርከቦቹ የያዙት ጭነት ዓይነት እና መጠንን መሠረት ደያረገ ሲሆን፣ ክፍያውም በኢራን የሚወሰን ነው” በማለት አገራቸው ያወጣችው መመሪያ ተግባራዊ እየሆነ መሆነን አመልክተዋል።ይህ ኢራን በወሽመጡ በኩል በሚያልፉ መርከቦች ላይ ክፍያ እንደምትሰበስብ ካስታወቀች በኋላ አሜሪካ ተቃወሞ ከማሰማቷ ባሻገር ፕሬዝዳንት ትራምፕ መርከቦች ለኢራን ምንም ዓይነት ክፍያ እንዳይፈጽሙ አስጠንቅቀው ነበረ።ያጋሩ, ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ከሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መሰሰብብ መጀመሯን አስታወቀች
  16. 23 ሚያዚያ 2026ኢራን፤ አሜሪካ እና እስራኤል በባህረ ሰላጤው እና በወሽመጡ ላይ ‘የጸጥታ መደፍረስ ምንጭ’ ናቸው አለችየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሜሪካ እና የእስራኤል “ጥቃት” በባህረ ሰላጤ እና በሆርሙዝ ወሽመጥ “የጸጥታ ችግር ምንጭ” ነው አሉ።የኢራን መንግሥት በኤክስ ገፁ ላይ በተከታታይ ባጋራቸው ልጥፎች አባስ አራግቺ በቴህራን ከደቡብ ኮሪያ ልዩ መልዕክተኛ ጋር እንደተገናኙ ገልጿል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አገራት “እነዚህን ጥቃቶች በማውገዝ ግልፅ እና ጠንካራ አቋም እንዲወስዱ” ማሳሰባቸውን ጠቅሷል።ኢራን ደኅንነቷን እና ጥቅሟን ለመከላከል በዓለም አቀፍ ሕግ እርምጃዎችን ወስዳለች ማለታቸውም በልጥፉ ተካትቷል።አራግቺ አክለውም ለሚደርሰው ሁሉ “ኃላፊነቱ የሚወስደው ጥቃት ፈጻሚው ነው” ብለዋል።ኢራን በወሽመጡ ሁለት መርከቦችን “መያዟን” እና ሦስተኛ የጭነት መርከብ ላይም ጥቃት መሰንዘሯ ተገልጿል።ያጋሩ, ኢራን፤ አሜሪካ እና እስራኤል በባህረ ሰላጤው እና በወሽመጡ ላይ ‘የጸጥታ መደፍረስ ምንጭ’ ናቸው አለች
  17. 23 ሚያዚያ 2026የሰላም ስምምነት ሳይፈጸም የንግድ መርከቦች ጉዞ እንደማይጀምሩ የነዳጅ ጫኝ ኩባንያ ኃላፊ ተናገሩመርከቦችየፎቶው ባለመብት,Reutersየሲውዲን ነዳጅ አጓጓዥ ኩባንያ የሆነው ‘ስቴና በልክ’ ዋና ስራ አስፈጻሚ በአሁኑ ሰዓት የኩባንያው መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉበት “ምንም ዕድል” እንደሌለ ተናገሩ።የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤሪክ ሃኔል ከቢቢሲ ሬዲዮ 4 ‘ቱዴይ’ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ “ይህንን አይነት እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት” በውሃ መስመሩ በኩል በሰላም ለማለፍ “ከሁለቱም፤ ከኢራን እና አሜሪካ የደኅንነት ዋስትና ያስፈልገናል” ብለዋል።የንግድ መርከቦች በድጋሚ ጉዞ እንዲጀምሩ የሚያስችለው አስፈላጊ ሁኔታ ሊፈጠር የሚችለው የሰላም ስምምነት ሲፈረም ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።”ከጥቂት ሳምንታት በፊት፣ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ ባለው ጊዜ በአንድ ሳምንት ገደማ ውስጥ እንድናልፍ የሚያደርግ አንድ ነገር ይፈጠራል የሚል ተስፋ ነበረን” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ አሁን ግን ሁኔታው “የተቆለፈ” ሆኗል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።ያጋሩ, የሰላም ስምምነት ሳይፈጸም የንግድ መርከቦች ጉዞ እንደማይጀምሩ የነዳጅ ጫኝ ኩባንያ ኃላፊ ተናገሩ
  18. 23 ሚያዚያ 2026ኢራንን እየመራ ያለው ማን ነው?የኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የኢራን አዲሱ ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒበኢራን በሚከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ውስጥ ጠቅላይ መሪው ሞጅታባ ኻሜኒ የመጨረሻውን ውሳኔ እንደሚያሳልፉ ይታወቃል።ነገር ግን በመጋቢት ወር ከተሾሙ ወዲህ በፎቶም ሆነ በቪዲዮ ለሕዝብ ታይተው አያውቁም። የኢራን መንግሥት ተደራዳሪዎች እየሠሩ ያሉት በኻሜኒ “ትዕዛዝ” መሠረት ነው።ጠቅላይ መሪው በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ላይ የሚደረጉ ድርድሮችን በግልጽ ባያነሱም አሜሪካን ግን ተችተዋል።የኢራን ተደራዳሪዎች የሆኑት የፓርላማ አፈ ጉባዔው ሞሐማድ ባጋር ጋሊባፍ እና እንደ አባስ አራጋቺ ያሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ድምጻቸው ጎልቶ እየተሰማ ነው።ጋሊባፍ ከኢራን አብዮታዊ ዘብ ጋር ጥብቅ ትስስር አላቸው።የአብዮታዊ ዘቡ በተለይ በጦርነት ወቅት ከመደበኛው መከላከያ ከፍ ያለ ተጽዕኖ ነው ያለው።አብዮታዊ ዘቡ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮቹን ቢያጣም ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ትይዩ እየሰራ ነው።አገሪቱን በሚመለከቱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫዎችን የሚያወጣ ቢሆንም ምን ያህል አቅም እንዳለው ግን ግልጽ አይደለም።ያጋሩ, ኢራንን እየመራ ያለው ማን ነው?
  19. 23 ሚያዚያ 2026ትራምፕ ጦርነቱን ለመቋጨት “እንደማይጣደፉ” ተናገሩየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚደረገውን የጦርነት ለመቋጨት “እየተጣደፉ አለመሆኑን” ለፎክስ ኒውስ ተናገሩ።ፕሬዝዳንቴ ከቴሌቪዥን ጣቢያው ጋር ባደረጉት የስልክ ቃለ መጠይቅ የኢራን ጋር የተደረሰውን እና ረቡዕ ዕለት የተጠናቀቀውን ተኩስ አቁም ያራዘሙት “የጊዜ ጫና” ኖሮባቸው እንዳልሆነ ገልጸዋል።“ጥሩ ስምምነት” ላይ እንዲደረስ እንደሚፈልጉ የተናገሩት ትራምፕ፤ ጦርነቱን ለመቋጨት “እንደማይጣደፉ” አስረድተዋል።የዋይት ሐውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮሊን ሌቪት ከኢራን ጋር የሚደረገው ድርድር “መቀጠሉን” እና ፕሬዝዳንቱ “ቀይ መስመሮቻቸውን በእጅጉ ግልጽ” ማድረጋቸውን ገልጸው ነበር። ከትራምፕ ፍላጎቶች አንዱ ኢራን ያበለጸገችውን የዩራኒየም ክምችት ለአሜሪካ አሳልፋ መስጠት አለባት የሚል ነው።አሜሪካ ስለ ድርድሩ “ከኢራን አገዛዝ ምላሽ ለማግኘት እየጠበቀች” መሆኑን የተናገሩት ቃል አቀባይዋ፤ “እስካሁን ወጥ የሆነ መልዕክት መላክ አልቻሉም፤ ለዚህም ነው ፕሬዝዳንቱ የተኩስ አቁሙን ለማራዘም የወሰኑት” ብለዋል።ያጋሩ, ትራምፕ ጦርነቱን ለመቋጨት “እንደማይጣደፉ” ተናገሩ
  20. 23 ሚያዚያ 2026እስራኤል ጋዜጠኛን ዒላማ ያደረገ የአየር ጥቃት ፈጽማለች ስትል ሊባኖስ ከሰሰችጋዜጠኛ አማል ካሊልንየፎቶው ባለመብት,APየምስሉ መግለጫ,ጋዜጠኛ አማል ካሊልንየሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ረቡዕ ዕለት እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በፈጸመችው የአየር ድብደባ አንዲት ጋዜጠኛ ገድላ ሌላ ሰው በማቁሰል የጦር ወንጀል ፈጽማለች ሲሉ ከሰሱ።ግድያው የተፈጸመው እስራኤል እና ሊባኖስ ዛሬ በዋሽንግተን ሁለተኛ ዙር ውይይታቸውን ለማድረግ ዝግጅት እያደረጉ ባሉበት ጊዜ ነው።የሊባኖስ ባለሥልጣናት ጋዜጠኛ አማል ካሊልን እና ዘይነብ ፋራጅ የመጀመርያው ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ በአንድ ቤት ውስጥ ተጠልለው ባሉበት ወቅት ሆነ ተብሎ ዒላማ መደረጋቸውን ገልጸዋል።እስራኤል አስቀድማ በፈጸመችው ጥቃት አንድ ተሽከርካሪ የመታች ሲሆን በዚህም ሁለት ሰዎች ተገድለዋል።ባለሥልጣናቱ የእስራኤል የመከላከያ ሠራዊት ታይሪ መንደር ውስጥ ጋዜጠኞችን ለማትረፍ እየሄደ የነበረ አምቡላንስ ሆነ ተብሎ ዒላማ መደረጉን ጨምረው ተናግረዋል።የ43 ዓመቷ ካሊል በሊባኖስ ለሚታተም አል-አክባር ለሚባል ጋዜጣ ትሰራነበር። በመኪና ውስጥ የነበሩት እና በጥቃቱ የተገደሉት ሁለት ሰዎች ስም አልተገለጸም።የእስራኤል መከላከያ ሠራዊቱ የሕይወት አድን ቡድኖች ወደ አካባቢው እንዳይደርሱ ከልክሏል መባሉን አስተባብሎ ጋዜጠኞችን ዒላማ እንዳላደረገ ተናግሯል።ያጋሩ, እስራኤል ጋዜጠኛን ዒላማ ያደረገ የአየር ጥቃት ፈጽማለች ስትል ሊባኖስ ከሰሰች