ቦርከና ደስክ

World Wide Travel Group
ምርጫ ቦርድ

ቦርከና ዜና

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር 50 ሚሊዮን 514,155 መድረሱን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር 50 ሚሊዮን 514,155 መድረሱን አስታውቋል።፣ ቦርዱ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጠው መግለጫ እስካሁንም ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን አረጋግጧል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላት ወርቅ ኃይሉ በመግለጫቸው እንዳብራሩት፣ ቦርዱ በእጩዎችም ሆነ በመራጮች ምዝገባ ላይ ያስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ በተለያዩ ምክንያቶች ሲራዘም ቢቆይም አሁን ላይ ምዝገባው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

በሂደቱ ወቅትም የትራንስፖርት መስተጓጎል እና ከዲጂታል ሲስተም ጋር የተያያዙ የቴክኒክ ችግሮች አጋጥመው እንደነበር ሰብሳቢዋ አስታውሰዋል።

Advertise here _ borkena

እስከ አሁን በተጠናቀረው መረጃ መሠረት ከተመዘገቡት 50,514,155 መራጮች መካከል 23,123,426 ሴቶች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 27,390,729 ደግሞ ወንዶች ናቸው። ይህ ቁጥር የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን፣ የጸጥታ ኃይሎችን እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ምዝገባ ሳያካትት የተመዘገበ ውጤት መሆኑ ተገልጿል።

የምዝገባ ሂደቱም በሁለት አማራጮች የተከናወነ ሲሆን፣ 45 ሚሊዮኑ በመደበኛው የምዝገባ ደብተር ወይም በማንዋል፣ ቀሪው 5 ሚሊዮን የሚሆነው ደግሞ በዲጂታል ዘዴ ተፈፃሚ ሆኗል።

በመጨረሻም ቦርዱ ምርጫው በተያዘለት ቀን መከናወኑ ለሀገራዊ አስፈላጊነቱ ከፍተኛ መሆኑን ገልጾ፣ ለዚሁ ተግባር ማስፈጸሚያ የሚሆን ተጨማሪ በጀት እንደሚያስፈልገው አስታውቋል።

_

Advertise here _ borkena

ቦርከናን ለመደገፍ/ለማገዝ  :-  ይሄንን ይጫኑ
የቦርከና ቻናልን ስብስክራይብ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ t.me/borkena
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ Borkena

Ethiopian NewsBorkena English