Yared Hailemariam ·Follow
የብልጽግና ንስራዊ ከፍታዎች፤ ጦርነት፣ ውሸት፣ጭካኔ፣ አፈና፣ ግፍ፣ …
+++++
ጦርነት፣ የርስ በርስ ግጭት፣ ሕዝብን በርሃብና በኑሮ ውድነት መቅጣት፣ ሰዎችን በማንነታቸውና በአስተሳሰባቸው ማዋከብ፣ ማሳደድ፣ ማፈናቀልና መግደል፣ ሴቶችን ወታደር አዝምቶ በደቦ እንዲደፈሩ ማድረግ፣ እንደ ኮሬነጌኛና 120 የሚባሉ አፋኝ ቡድኖች አሰማርቶ ዜጎችን ማሳፈን፣ መደብደብና መዝረፍ፣ በመላ አገሪቱ ሥርዓት አሎበኝነት እንዲሰፍን እና ዜጎች በነጻነተት ከሥፍራ ሥፍራ እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ፣ አይን ያወጣ የሙስና ዝርፊያ እንዲስፋፋ ማድረጎ፣ ሚሊዮኖችኖ ቤት አልባ አድርጎ መዳ ላይ የበተነ፣ የአገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ መጣልና የአገሪቱን እስር ቤቶች በህሊና እስረኞ ሞልቶ የይስሙላ ምርጫ ለማካሂድ መሯሯጥና መናፈሻዎች እያስገነቡ መመጻደቅ የብልጽግና ንስራዊ ከፍታዎች ናቸው።
የቴዲ አፍሮን ም/ማኔጀርና የቅርብ ጓደኛውን አስሮ፣ ዘፈኑን ሰማችሁ ብሎ በመቶዎች ወጣቶችን አፍሶ ያጎረ፣ ያም አልበቃ ብሎት የቴዲን እስቱዲዬ በታጣቂዎች ያዘረፈ መንግስት ዛሬ በፌደራል ፖሊስ መግለጫ በማሰጠት አላሰርኩም፣ ስቱዲዮም አልዘረፍኩም የሚያስብል ውሸታምና ቀጣፊ መንግስት እራሱን እያጋለጠ እንደሆነ እንኳ አያውቅም። እሺ ፌደራል ፖሊስ ሳያውቅ ከሆነ ሰዎች በዋና ከተማዋ በአዲስ አበባ የሚታፈኑት፣ የሚታሰሩትና በታጣቂዎች የቴዲ ቢሮ የሚዘረፍ ከሆነ ስንት መንግስት ነው በአገሪቱ ያለው????
