
ከ 1 ሰአት በፊት
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ
በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ፕሪቶሪያ የሚኖሩ አፍሪካውያን ስደተኞች ፀረ ስደተኛ ሠልፍ በሚካሄድበት ወቅት ጥቃት እዳይደርስባቸው “ከፍተኛ ጥንቃቄ” እንዲያደርጉ ተነገራቸው።
በደቡብ አፍሪካ መጤ ጠል የሆኑ ግለሰቦች በሚያደርሱት ጥቃት የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ዜጎች መገደላቸው ተዘግቧል።
የጋና ከፍተኛ ኮሚሽን በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ዜጎቹ ሱቆቻቸውን እንዲዘጉ እና “ትኩረት ላለመሳብ እንዲሞክሩ” አስጠንቅቋል።
በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ናይጄሪያውያን ማኅበር ደግሞ አባላቱ ቤታቸው እንዲቀመጡ የሚገልጽ መልዕክት አስተላልፏል።
በጆሃንስበርግ ረቡዕ ዕለት በአገሪቱ የሚገኙ ስደተኞችን የሚቃወሙ ሠልፎች ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በደቡብ አፍሪካ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሕገ ወጥ ስደተኞች ጉዳይ የፖለቲካ መሣሪያ እየሆነ መጥቷል።
የተወሰኑ ተቃዋሚዎች የውጭ አገራት ዜጎች ሥራዎችን እያሳጣን ነው እንዲሁም ፍትሃዊ ባልሆነ ሁኔታ ከሕዝብ አገልግሎት ተጠቃሚ እየሆኑ ነው ሲሉ ይወነጅላሉ።
ነገር ግን ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ዜጎች “ፍርሃታቸው እና ጭንቀታቸው ሌሎች አፍሪካዊ ወንዶሞቻቸውን ወደመጥላት እንዳያድግ” አስጠንቅቀዋል።
