ዶናልድ ትራምፕ፣ ንጉሥ ቻርልስ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ሊኖራት አይገባም ብለው እንደሚያምኑ ተናገሩ። ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሐውስ በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ላይ ንጉሥ ቻርልስ ኢራን የኒውክሌር የጦር መሣሪያ ሊኖራት አይገባም ብለው እንደሚያምኑ ሲናገሩ “ቻርልስ ከእኔ ጋር ይስማማል፤ ከእኔ በበለጠ ይስማማል” ብለዋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 16 ደቂቃዎች በፊትየኢራንን ሥልጣን በበላይነት የተቆጣጠረው አብዮታዊ ዘብቴህራንየፎቶው ባለመብት,Reutersለሁለት ወራት በዘለቀው የኢራን ጦርነት ቴህራን አንድ የማያሻማ መመሪያ የሚሰጥ ሃይማኖታዊ መሪ የላትም።ይህ በድንገት ፍጻሜውን ያገኘው የኢራን አገዛዝ የአገሪቱ ዕጣ ፈንታ በአክራሪ የአብዮታዊ ዘብ አዛዦች ስር እንዲወድቅ አድርጓል።የእስላማዊ ሪፐብሊክ እአአ በ1979 ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በቁልፍ ጉዳዮች ላይ የመጨረሻውን ውሳኔ የሚሰጡት ጠቅላይ መሪው ነበሩ። ነገር ግን የአያቶላህ አሊ ኻሜኒ መገደል እና እርሳቸውን ተክቶ የልጃቸው ወደ ሥልጣን መምጣት የአብዮታዊ ዘቡ ጄነራሎች ውሳኔ ሰጪነት እንዲገን አድርጓል።በዚህ የተነሳ ደግሞ ወሳኝ የሆነው ውሳኔ ሰጭ አካል በመጉደሉ ሞጅታባ ኻሜኒ በአብዮታዊ ዘቡ አዛዦች ላይየበለጠ እንዲደገፉ አድርጓቸዋል።ሞጅታባ ኻሜኒ የሥርዓቱ ቁንጮ ላይ ናቸው። ነገር ግን ሦስት ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ የውስት አዋቂዎች ለሮይተርስ እንደተናገሩት ጠቅላይ መሪው ውሳኔያቸውን የሚሰጡት በአዛዦቹ ላይ በመመስረት ነው።የኢራን አመራር በጦርነቱ የተነሳ ውሳኔዎቹን በጥቂት ጠቅላይ ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ ባሉ አክራሪ ቡድኖች ላይ እንዲመሰረት አድርጎታል።ይህ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ላይ ጫና ፈጥሯል። አንድ ከፍተኛ የፓኪስታን ባለሥልጣን “ኢራናውያን ምላሽ ሲሰጡ እጅግ በጣም ዝግ ብለው ነው” ብለዋል።“አንድ ወጥ የሆነ ውሳኔ ሰጭ መዋቅር የለም። አንዳንድ ጊዜ ምላሽ ለማግኘት ሁለት እና ሦስት ቀን ይወስዳል” ሲሉ አክለዋል።ተንታኞች እንዳሉት የስምምነቱ እንቅፋት በቴህራን ውስጥ ያለ የሥልጣን ሽኩቻ አይደለም። ነገር ግን ዋሽንግተን ለማቅረብ በተዘጋጀችው እና የኢራን አክራሪ ወገኖች ለመቀበል ፈቃደኛ በሆኑት መካከል ያለው ክፍተት ነው።ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው የሰላም ድርድር የኢራን የዲፕሎማሲ ፊት የሆኑት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራጋቺ እና በቅርቡ የተቀላቀሏቸው የፓርላማው አፈ ጉባዔ ሞሐመድ ባጋር ጋሊባፍ ናቸው።ፖለቲካውን ከጀርባ ሆነው የሚዘውሩት ግን የአብዮታዊ ዘቡ አዛዥ አዛዥ አህመድ ቫሂዲ መሆናቸውን አንድ የፓኪስታን እና ሁለት የኢራን ምንጮች ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።ቫሂዲ ቁልፍ ውሳኔ ሰጪ መሆናቸው በተኩስ አቁሙ ስምምነት ወቅትም ሆኑ ከዚያ በኋላ ከኢዝላማባድ ጋር ባለ ንግግር ወቅት ታይተዋል።ሮይተርስ በኢራን ስለተፈጠረው የአመራር ክፍተት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩን ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሽ አላገኘም። ከዚህ በፊት ግን በኢራን ውስጥ ባሉ አመራሮች መካከል መከፋፈል እንደሌለ እና የሥልጣን ሽኩቻ እንዳልተከሰተ በመግለጽ አስተየየት ሰጥቶ ነበር።ያጋሩ, የኢራንን ሥልጣን በበላይነት የተቆጣጠረው አብዮታዊ ዘብ
  2. ከ 1 ሰአት በፊትዶናልድ ትራምፕ ንጉሥ ቻርልስ ኢራን ኒውክሌር ጦር መሣሪያ ሊኖራት እንደማይገባ እንደሚያምኑ ተናገሩለአራት ቀናት የሥራ ጉብኝት አሜሪካ የሚገኙት ንጉሥ ቻርልሰ ከባለቤታቸው ንግሥት ካሚላ እንዲሁም ከፕሬዚዳንት ትራምፕ እና ባለቤታቸው ጋርየፎቶው ባለመብት,Reutersዶናልድ ትራምፕ ንጉሠ ቻርልስ ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ሊኖራት አይገባም ብለው እንደሚያምኑ ተናገሩ።ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሐውስ ለንጉሡ በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ላይ “ቻርለስ ከእኔ ጋር ይስማማል፤ ከእኔ በበለጠ ይስማማል” ሲሉ ተናግረዋል።ትራምፕ በዚህ ንግግራቸው ላይ ቴህራንን “በወታደራዊ ኃይል አሸንፈናታል” ብለዋል።”ያ ተቃዋሚ [ቴህራን] በጭራሽ [እንዲኖረው] አንፈቅድም፤ ቻርልስ ከእኔ ጋር ይስማማል። ከእኔም በላይ፤ ያ ​​ተቃዋሚ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዲኖረው በጭራሽ አንፈቅድም ።”የበርኪንግሃም ቤተ መንግሥት ቃል አቀባይ የትራምፕን ንግግር ተከትሎ ለቢቢሲ በሰጡት ምላሽ “ንጉሡ መንግሥታቸው የኒውክሌር መስፋፋትን ለመከላከል ያለውን የረዥም ጊዜ እና የታወቀ አቋም ያደግፋሉ” ብለዋል።ለአራት ቀናት የሥራ ጉብኝት አሜሪካ የሚገኙት ንጉሥ ቻርልሰ የአሜሪካን የነጻነት በዓል ከማክበር ባሻገር ከዩኬ ጋር የተፈጠረውን የግንኙነት መሻከር ይጠግናሉ ተብሎ ይጠበቃል።ንጉሥ ቻርለስ ከባለቤታቸው ንግሥት ካሚላ ጋር በመሆን ሰኞ ዕለት ዋሺንግተን ሲደርሱ ደማቅ አቀባባል ተደርጎላቸዋል።ያጋሩ, ዶናልድ ትራምፕ ንጉሥ ቻርልስ ኢራን ኒውክሌር ጦር መሣሪያ ሊኖራት እንደማይገባ እንደሚያምኑ ተናገሩ
  3. ከ 2 ሰአት በፊትበዓለም ላይ እጅግ ውድ የሆነውን ሃብት የሚቆጣጠረው ኦፔክ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ሲለያዩ ምን ይፈጠራል?ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው በነዳጅ በርሜሎች አጠገብ ሲያልፍየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ምክንያት እየጨመረ የሚገኘው የነዳጅ ገበያ አዲስ ድንገተኛ ክስተት አስተናግዷል።የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ከፔትሮሊየም ላኪ አገራት ድርጅት (ኦፔክ) እንደምትወጣ አሳውቃለች።ኦፔክ እአአ በ1960 ነበር ባግዳድ ኢራቅ ውስጥ የተቋቋመው።በአምስት አገራት የተቋቋመው ኦፔክ የአባል አገራቱን ቁጥር 12 ማድረስ ችሎ ነበር።አሁን ግን የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ይህንን ቁጥርበአንድአጉድላዋለች።ተቋሙ ለዓመታት አባል አገራቱ የሚያመርቱትን ነዳጅ በመቆጣጠር የዓለም የነዳጅ ዋጋን ሲወስን ቆይቷል።የነዳጅ ዋጋ መጨመር ሲፈልግ ምርት ይቀንሳል፤ ዋጋው ለማረጋጋት ደግሞ አገራቱ ምርቱን እንዲጨምሩ ያደርጋል።የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በተቋሙ ውስጥ አባል ብቻ ሳትሆን ቁልፍ ከሚባሉት ተርታ አንዷ ነበረች።የኦፔክ ምርት በሳዑዲ አረቢያ ቁጥጥር ስር ቢሆንም፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሁለተኛው ከፍተኛ የመጠባበቂያ ምርት አቅም ነበራት።ይህም አገሪቱን አቅም ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው።ሆኖም ግን ኦፔክ እያንዳንዱ አገር ምን ያህል ነዳጅ ማምረት እንደሚችል የሚያስቀምጠው ገደብ አለ።የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በቀን ከ3 እስከ 3.5 ሚሊዮን በርሜል ማምረት ተፈቅዶላታል።በቀን እስከ 5 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ የማምረት አቅም ላላት አገር አነስተኛ ቁጥር ነው።በቀላል አነጋገር የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ገንዘብ የማግኘት እድሏን በእጅጉ ቀንሶታል።የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ከኦፔክ ነዳጅ አምራች አገራት አባልነት መውጣቷ ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል?ያጋሩ, በዓለም ላይ እጅግ ውድ የሆነውን ሃብት የሚቆጣጠረው ኦፔክ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ሲለያዩ ምን ይፈጠራል?
  4. ከ 3 ሰአት በፊትበቴህራን እና ዋሺንግተን መካከል የሚካሄደው ንግግር መቋጫ ባለማግኘቱ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበመካከለኛው ምሥራቅ የሚካሄደው ጦርነት ዳግም ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ስጋር የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ አሻቀበ። ረቡዕ ዕለት ማለዳ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል 111 ዶላር መሸጡ ተዘግቧል።በአሜሪካ እና በኢራን መካከል እየተካሄደ የነበረው ውይይት በመቋረጡ የእስያ የነዳጅ ገበያ ዳግም ጭማሪ አሳይቷል።ሰኞ ዕለት የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ3 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በበርሜል 109 ዶላር መሸጡን ቢቢሲ ዘግቧል።የሆርሙዝ ወሽመጥ በኢራን እና በአሜሪካ በመዘጋቱ የዓለም የነዳጅ አቅርቦት ተስተጓጉሏል።ኒውዮርክ ታይምስ እንዲሁ በአሜሪካ አማካይ የነዳጅ ዋጋ የኢራን ጦርነተ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ መሆኑን ዘግቧል።ማክሰኞ ዕለት በአሜሪካ የነዳጅ ዋጋ በአማካይ በ4.18 በጋሎን ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ይህም የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረበት እአአ ከ2022 ወዲህ ከፍተኛው መሆኑን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ያጋሩ, በቴህራን እና ዋሺንግተን መካከል የሚካሄደው ንግግር መቋጫ ባለማግኘቱ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ
  5. 28 ሚያዚያ 2026ትራምፕ፣ ቴህራን አሜሪካ በተቻለ ፍጥነት የሆርሙዝ ወሽመጥን እንድትከፍት ትፈልጋለች አሉዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Reutersፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ኢራን “የመፈራረስ አደጋ የተጋረጠባት መሆኗን” እና የመሪዎቿን ሁኔታ እስክታውቅ ድረስ አሜሪካ የሆርሙዝ ወሽመጥን በፍጥነት እንድትከፍት መጠየቋን ተናገሩ።ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ ከኢራን ጋር መልዕክቱን መቼ እንደተለዋወጡ ያልገለጹ ሲሆን ከቴህራን ወገንም የተሰማ ምላሽ የለም።“ኢራን ‘የመፈራረስ አደጋ የተጋረጠባት መሆኗን’ ነግራናለች። የመሪዎቻቸውን ሁኔታ እስኪለዩ ድረስ (ያንን ማድረግ ይችላሉ ብዬ አምናለሁ) በተቻለ ፍጥነት ‘የሆርሙዝ ውሽመጥን በተቻለ ፍጥነት እንድንከፍት’ ይፈልጋሉ” ብለዋል።ሮይተርስ ለዋይት ሐውስ በትራምፕ የማኅበራዊ ልጥፍ ዙሪያ ላቀረበው ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ አላገኘም።ትራምፕ ኢራን ለሁለት ወራት የቆየውን ጦርነት ለመፍታት ባቀረበችው አዲስ የመደራደሪያ ሃሳብ ደስተኛ አለመሆናቸውን የአሜሪካ ባለሥልጣናት ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረው ነበር።ያጋሩ, ትራምፕ፣ ቴህራን አሜሪካ በተቻለ ፍጥነት የሆርሙዝ ወሽመጥን እንድትከፍት ትፈልጋለች አሉ
  6. 28 ሚያዚያ 2026የባሕረ ሰላጤው አገራት ለኢራን ጥቃቶች ስለሚሰጡት ምላሽ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ሊወያዩ ነውየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ውስጥ የተፈጸመ ጥቃትየፎቶው ባለመብት,Reutersየባሕረ ሰላጤው ትብብር ምክር ቤት አባል አገራት መሪዎች የኢራን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ሊሰበሰቡ መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ።የመሪዎቹ ስብሰባ የሚያተኩረው ሁለት ወር በሞላው ጦርነት ለዘነቡባቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ የኢራን የሚሳዔል እና ድሮን ጥቃቶች ምላሽ ማዘጋጀት ላይ እንደሚሆን ዜና ወኪሉ ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል።በአሜሪካ እና እስራኤል ጦርነት የተከፈተባት ኢራን በስድስቱም የባሕረ ሰላጤው ትብብር ምክር ቤት አባል አገራት የሚገኙ የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ፈጽማለች።ከአሜሪካ ጋር ግንኙነት ያላቸው ተቋማት እና ሌሎች የሲቪል መሠረተ ልማቶችን እንዲሁም ወታደራዊ ይዞታዎችንም አጥቅታለች።ሮይተርስ የጠቀሰው የሳዑዲ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘገባ እንደሚያመለክተው የኳታር፣ ኩዌት እና ባህሬን መሪዎች እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በስብሰባው ለመሳተፍ ጅዳ ገብተዋል።የምክር ቤቱ አባል የሆነችው ኦማን በማን እንደምትወከል እስካሁን አለመታወቁም ተጠቅሷል።የባሕረ ሰላጤው ምክር ቤት ለጦርነቱ በቂ ምላሽ አልሰጠም በሚል ከኤምሬቶች ትችት ቀርቦበት ነበር።ያጋሩ, የባሕረ ሰላጤው አገራት ለኢራን ጥቃቶች ስለሚሰጡት ምላሽ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ሊወያዩ ነው
  7. 28 ሚያዚያ 2026ግዙፉ የነዳጅ ኩባንያ ቢፒ የኢራን ጦርነት ከጀመረ ወዲህ ትርፉ በእጥፍ ማደጉን ገለጸግዙፉ የነዳጅ ኩባንያ ቢፒየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesግዙፉ የነዳጅ ኩባንያ ቢፒ የኢራን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ ትርፉ ከእጥፍ በላይ ማደጉን አስታወቀ።ቢፒ በነዳጅ ንግድ ውስጥ “እጅግ በጣም ጥሩ” አፈጻጸም ማሳየቱን ገልጾ ከጥር እስከ መጋቢት ባሉት ወራት ብቻ 3.2 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን ይፋ አድርጓል።ይህ አሃዝ ተንታኞች ከጠበቁት በላይ መሆኑን የገለጸው ኩባንያው፣ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ካስመዘገበው 1.38 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ በእጥፍ እንደሚበልጥ ተናግሯል።ይህ ትርፍ የተመዘገበው አዲሷ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሜግ ኦኔል ኃላፊነታቸውን ከተረከቡ በኋላ ነው።የካቲት 21/2018 ዓ.ም. የተጀመረው የኢራን ጦርነት የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል።ጦርነቱን ተከትሎ 20 በመቶ የሚሆነውን የዓለም የነዳጅ ዘይት እና የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት የሚያጓጓዝበት የሆርሙዝ ቁልፍ የባህር ወሽመጥ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል።ብሬንት ድፍድፍ የነዳጅ ዘይት በአሁኑ ወቅት በበርሜል 110 ዶላር እየተሸጠ ሲሆን፣ የኢራን ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ዋጋው 73 ዶላር አካባቢ ነበር።ኦኔል “ኢንዱስትሪውን በግጭት እና ተግዳሮት በሞላበት ወቅት” ኩባንያውን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።ቢፒ “ደንበኞች እና መንግሥታት በሚፈልጉበት ቦታ ነዳጅ እንዲያገኙ፣ በሰዎች ሕይወት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን መስተጓጎል ለመቀነስ በመሥራት እየረዳ” እንደሆነ ተናግረዋል።ያጋሩ, ግዙፉ የነዳጅ ኩባንያ ቢፒ የኢራን ጦርነት ከጀመረ ወዲህ ትርፉ በእጥፍ ማደጉን ገለጸ
  8. 28 ሚያዚያ 2026የጀርመኑ ቻንስለር የኢራን አመራሮች አሜሪካን “እያሳፈሯት ነው” አሉየጀርመኑ ቻንስለር ፍሬድሪክ መርዝየፎቶው ባለመብት,REUTERSየጀርመኑ ቻንስለር ፍሬድሪክ መርዝ ሰኞ ዕለት ባደረጉት ንግግር የኢራን አመራሮች አሜሪካ ወደ ፓኪስታን አምርታ ያለ ውጤት እንድትመለስ በማድረግ “አሳፍረዋታል” ማለታቸውን ሮይተርስ ዘገበ።ቻንስለሩ ይህንን ያሉት በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ይደረጋል ተብሎ የነበረው የሁለተኛ ዙር የሰላም ውይይት ሳይካሄድ ከቀረ በኋላ ነው።ሮይተርስ የዜና ወኪል መርዝ አሜሪካ ከኢራን ጦርነት ለመውጣት ያዘጋጀችው ስልት መኖሩ እንደማይታያቸው መናገራቸውን ጨምሮ ገልጿል።በአሜሪካ እና በአውሮፓውያኑ የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) አባል አገራት መካከል በኢራን ጦርነት ዙሪያ ልዩነት አለ።ቻንስለሩ ሰኞ ዕለት በመርስበርግ ከተማ ለተማሪዎች ንግግር ባደረጉበት ወቅት አሜሪካኖች ወደ ኢዝላምባድ እንዲጓዙ እና ያለ ምንም ውጤት እንዲመለሱ በማድረግ ረገድ “ኢራናውያን በመደራደር በጣም የተካኑ ናቸው፤ ወይም ባለመደራደር ክህሎት ያላቸው ናቸው” ብለዋል።“በኢራን አመራር ሙሉ ሕዝቡ [አሜሪካውያን] ነው እንዲያፍር የተደረገው፤ በተለይ የአበዮታዊ ዘብ በሚባለው። እናም ተስፋ የማደርገው በተቻለ ፍጥነት [ጦርነቱ] እንዲጠናቀቅ ነው” ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኔቶ አጋሮችን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማስከፈት የባሕር ኃይላቸውን ባለመላካቸው ተችተዋል። የኢራን ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ወሽመጡ በመዘጋቱ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።ያጋሩ, የጀርመኑ ቻንስለር የኢራን አመራሮች አሜሪካን “እያሳፈሯት ነው” አሉ
  9. 28 ሚያዚያ 2026የሩሲያ ቅንጡ መርከብ እግድ በተጣለበት በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል አለፈች500 ሚሊየን እንደምታወጣ የተገመተችው ኖርድ፣ ከዱባይ የተነሳችው አርብ ምሽት ነበርየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,500 ሚሊየን እንደምታወጣ የተገመተችው ኖርድ፣ ከዱባይ የተነሳችው አርብ ምሽት ነበርከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቁልፍ አጋር ጋር ግንኙነት ያላት ቅንጡ መርከብ በአሜሪካ እና ኢራን እገዳ በተጣለበት የሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል አለፈች።142 ሜትር የምትረዝመው እና ማዕቀብ ከተጣለበት ሩሲያዊው ቢሊየነር አሌክሲ ሞርዳሾቭ ጋር ግንኙነት ያላት መርከብ ከዱባይ ወደ ሙስካት በሳምንቱ መጨረሻ ተጉዛለች።ኖርድ የተሰኘችው ይህች ቅንጡ መርከብ ከቅርብ ወራት ወዲህ በወሽመጡ በኩል ካለፉ ጥቂት መርከቦች መካከል አንዷ ሆናለች።የኢራን ልዑካን በዚህ ሳምንት ወደ ሩሲያ በማቅናት ከቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል።አንድ አምስተኛ የሚሆነው የዓለም ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት እና የተፈጥሮ ጋዝ (ኤልኤንጂ) የሚያልፉት በዚህ የባሕር ወሽመጥ በኩል ነው።ከፑቲን ጋር የቅርብ ግንኙነት ያለው ሞርዳሾቭ የቅንጦት ጀልባው ባለቤት መሆኑ በግልጽ አይታወቅም።ሆኖም ስለ ኖርድ የሰፈሩ መረጃዎች እአአ በ2022 በሚስቱ ባለቤትነት በተያዘ ድርጅት መመዝገቧን ያመለክታሉ።500 ሚሊዮን ዶላር እንደምታወጣ የተገመተችው ኖርድ፣ ከዱባይ የተነሳችው አርብ ዕለት ምሽት ነበር።ቅዳሜ ማለዳ በኦማን አል ሞኡጅ መድረሷ ተገልጿል። የሩሲያን ባንዲራ የምታውለበልበው ኖርድ የኢራን ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጊዜ ጀምሮ የግል መርከቦች ከአካባቢው ቢርቁም መርከቧ ግን በወሽመጡ ላይ ያለችግር መቅዘፍ ችላለች።ያጋሩ, የሩሲያ ቅንጡ መርከብ እግድ በተጣለበት በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል አለፈች
  10. 28 ሚያዚያ 2026ኢራን ባቀረበችው የድርድር ነጥብ ላይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደስተኛ አለመሆናቸውን የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተናገሩዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesለሁለት ወራት የዘለቀውን ጦርነት ለመቋጨት ኢራን በቅርቡ ያቀረበችው የመደራደሪያ ነጥብ ዶናልድ ትራምፕን እንዳላስደሰታቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።ይህም የኃይል አቅርቦትን ያስተጓጎለውን፣ የነዳጅ ዋጋን ያናረውን እና የሺዎችን ሕይወት የቀጠፈውን ጦርነት ለማስቆም የነበረውን ተስፋ የሚያጨፈግግ ነው ተብሏል።ኢራን በቅርቡ ያቀረበችው የመደራደሪያ ነጥብ ጦርነቱ እስኪቆም ድረስ የኒውክሌር ድርድርን ወደ ጎን የተወ እና በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ነጻ የመርከቦችን እንቅስቃሴ እልባት የሚሰጥ ነው።ያጋሩ, ኢራን ባቀረበችው የድርድር ነጥብ ላይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደስተኛ አለመሆናቸውን የአሜሪካ ባለሥልጣናት ተናገሩ
  11. 28 ሚያዚያ 2026የአሜሪካ ግምጫ ቤት ኃላፊ ከኢራን አየር መንገዶች ጋር ‘የሚተባበር ማዕቀብ ይጣልበታል’ አሉየአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንትየፎቶው ባለመብት,Reutersየአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሴንት ከኢራን አየር መንገዶች ጋር የሚተባበሩ ኩባንያዎች ማዕቀብ እንደሚጣልባቸው አስጠነቀቁ።ኃላፊው በኤክሰ ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ይህ እርምጃ አገራቸው ኢራን ላይ የምታደርገው የምጣኔ ሃብት ጫና አካል መሆኑን ተናግረዋል።ቤስንት መንግሥታት በሥራቸው የሚገኙ ኩባንያዎች ለኢራን አውሮፕላኖች አገልግሎት ላለመስጠት አስፈላጊውን ጥንቀቄ እንዲያደርጉ አስጠንቅቀዋል።ቤሴንት መንግሥታት ለኢራን አውሮፕላኖች “ነዳጅ መቅዳት፣ የምግብ አቅርቦት አገልግሎት መስጠት እና የአውሮፕን ማሳረፊያ ክፍያዎች ወይም አውሮፕላን ጥገናዎችን” እንዳይሰጡ አስጠንቅዋል።የአገሪቱ ግምጃ ቤት “ከኢራን ጋር ንግድ በሚያካሄዱ ወይንም በሚያመቻቹ ሦስተኛ ወገኖች ላይ እርምጃ ለመውሰድ አያመነታም” ብለዋልየኢራን አየር መንገዶች በሳምንቱ መጨረሻ ከጦርነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በረራ መጀመራቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።የኢራን መገናኛ ብዙኃን በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ከቴህራን መንገደኞችን የጫኑ አውሮፕላኖች ወደ ኢስታንቡል፣ ኦማን፣ ኢረቅ፣ ኳታር እና ወደ ሳዑዲ ከተማ መዲና መብረራቸውን ዘግበዋል።የአሜሪካ ግምጃ ቤት ዋሸንግተን በኢራን መንግሥት ላይ “ጠናካራ የፋይናንስ ማነቆ” ማስቀመጧን ገልጿል።ቤሴንት በኤክስ ገጻቸው ላይ “ማዕቀብ ከተጣለባቸው አየር መንገዶች ጋር መስራት ለአሜሪካ ማዕቀብ ያጋልጣል” ሲሉ ጽፈዋል።የትራምፕ አስተዳደር ባለሥልጣን የግምጃ ቤት ዲፓርትመንት “የኢራንን እንቅስቃሴ ማቀላጠፍ በሚቀጥሉ” በውጭ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ሁለተኛ ደረጃ ማዕቀብ እንደሚጥል ተናግረዋል።የአሜሪካ ግምጃ ቤት በተለይም የኢራንን የነዳጅ ኤክስፖርትና የፋይናንስ ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ የተለያዩ ማዕቀቦችን ጥሏል።ያጋሩ, የአሜሪካ ግምጫ ቤት ኃላፊ ከኢራን አየር መንገዶች ጋር ‘የሚተባበር ማዕቀብ ይጣልበታል’ አሉ
  12. 28 ሚያዚያ 2026ቴህራን አሜሪካንን በዓለም አቀፍ ውሃ ላይ “የባህር ላይ ውንብድና” በመፈጸም ወነጀለችቴህራንየፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን በሕንድ ውቅያኖስ ስለተያዘባት ድፍድፍ ነዳጅ ጫኝ መርከብ በሰጠቸው ምላሽ ይህ “የባሕር ላይ ውንብድና ነው” አለች።አሜሪካ የኢራንን ነዳጅ የጫነች መርከብ በሕንድ ውቅያኖስ ላይ በቁጥጥር ስር ያዋለችው ባለፈው ሳምንት ነበር።የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይ የአሜሪካን እርምጃ “የባሕር ላይ ውንብድና” ሲሉ በኤክሰ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።“ይህ ድርጊት በግልጽ የባሕር ላይ ውንብድናን ሕጋዊ ማድረግ ነው” ያሉት ቃል አቀባዩ “በባሕሮች ላይ የሚፈጸም በትጥቅ የታገዘ ሽፍትነት ነው” ሲሉ አክለዋል።“ወደ ባሕር ላይ ውንብድና እንኳን በደህና መጣችሁ። አሁን ይህ የሚከናወነው ይፋዊ የመንግሥት ፈቃድ ባለው፣ በይፋ ባንዲራውን በሚያውለበልብ እና ወንጀሉን ‘ሕግ ማስከበር’ ሲል በሚጠራ አካል መሆኑ ነው” ሲሉ ቃል አቀባዩ የአሜሪካን እርምጃ ኮንነዋል።የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አክለውም “ዩናይትድ ስቴትስ ሙሉ በሙሉ ለዚህ ሕገወጥ ባሕሪዋ ተጠያቂ መሆን አለባት” በማለት ድርጊቱ “የዓለም አቀፍ ሕጎች እና የዓለም ነጻ ንግድ መሠረቶችን የሚጥስ የባሕር ላይ ትራንስፖርት መርሆችን የሚንድ ነው” ብለውታል።ቃል አቀባዩ ምላሽ የሰጡት የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ጄኒን ፌሪስ ፒሮ የነዳጅ ጫኝ መርከቧን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችል መያዣ ማውጣታቸውን መግለጻቸውን ተከትሎ ነው።የአሜሪካ ጦር ባለፈው ሳምንት በሕንድ ውቅያኖስ ላይ 1.9 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ የጫነች የኢራን መርከብን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቆ ነበር።ያጋሩ, ቴህራን አሜሪካንን በዓለም አቀፍ ውሃ ላይ “የባህር ላይ ውንብድና” በመፈጸም ወነጀለች
  13. 27 ሚያዚያ 2026ፑቲን ሩሲያ በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም ለማምጣት ማንኛውንም ነገር ታደርጋለች አሉየሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺየፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አገራቸው በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም ለማምጣት ማንኛውንም ነገር እንደምታደርግ መናገራቸውን ታስ የዜና ወኪል ዘገበ።ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከኢራኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ጋር በሴንት ፒተርስበርግ ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸው ወቅት የሩሲያው ፕሬዚዳንት ለቴህራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢራን ሕዝቦች ለሉዓላዊነታቸው በድፍረት መታገላቸውን መናገራቸውን የሩሲያ ብሔራዊ የዜና ወኪል ታስ ዘግቧል።ታስ አክሎም ፑቲን ኢራን ይህንን አስቸጋሪ ጊዜ ካለፈች በኋላ ሰላም እንደምትፈልግ ያላቸውን ተስፋ መግለጣቸውን ጠቅሷል።የዜና ኤጀንሲው ፑቲን ለኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አራጋቺ፣ ሩሲያ “በመካከለኛው ምሥራቅ በተቻለ ፍጥነት ሰላም ለማምጣት ማንኛውንም ነገር እንደምታደርግ” መናገራቸውን ዘግቧል።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው በሞስኮ እና በቴህራን መካከል ያለው ግንኙነት “እየተጠናከረ የሚሄድ” ስትራቴጂካዊ አጋርነት መሆኑን መናገራቸውን የሩሲያ የመንግሥት ቴሌቪዥን ዘግቧል።የሩሲያውን ፕሬዚዳንት ለማነጋገር ወደ ሞስኮ የተጓዘው የኢራን ልዑካን ቡድን ውስጥ ምክትል የውጭጉዳይ ሚኒስትር ካዜም ጋሪባባዲ እና በሞስኮ የኢራን አምባሳደር ካዜም ጃላሊ ይገኙበታል።የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ሩሲያ ቴህራን እና ዋሺንግተን በሚያደርጉት ቀጣይ ድርድሮች “በሁለቱም ወገኖች ተቀባይነት ያለው የማደራደር አገልግሎት” ለማቅረብ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።“የተረጋገጠ ሰላም፤ በዘላቂነት የሚቆይ እና ወደ ግጭት ዳግም መመለስ የሌለበት ሰላምን ለማረጋገጥ ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ዝግጁ ነን” ሲሉ መናገራቸውን መገናኛ ብዙኃኑ ዘግቧል።አራግቺ በሴንት ፒተርስበርግ ለጋዜጠኞች ኢራን “የዓለም ታላቅ ልዕለ ኃያል [ዩኤስ] በመፋለም ላይ ነች” በማለት ዋሽንግተን “አንድም ግቧን አላሳካችም” ብለዋል።”ለዚህም ነው ድርድር የጠየቁትና እየተመለከትን ያለነው” ሲሉም አክለዋል።አሜሪካ ግን ድርድር ስለመጠየቋ ምንም ያለችው ነገር የለም።የኢራን ከፍተኛ ዲፕሎማት ጦርነቱ ኢራን “እንደ ሩሲያ ያሉ ታላላቅ ወዳጆች እና አጋሮች እንዳሏት” ያሳየ ነው ብለዋል።ያጋሩ, ፑቲን ሩሲያ በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም ለማምጣት ማንኛውንም ነገር ታደርጋለች አሉ
  14. 27 ሚያዚያ 2026የሊባኖስ ፕሬዚዳንት የተኩስ አቁሙን በመጣስ ሄዝቦላህን ተቹየእስራኤል እና የሊባኖስ ባንዲራዎችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየሊባኖስ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ አውን ከእስራኤል ጋር የሚደረገውን ጦርነት ለማስቆም በሚያደርጉት ጥረት “የሚያሳፍር ስምምነት” እንደማይቀበሉ ገለፁ።ፕሬዚዳንቱ በመግለጫቸው ከድርድሩ መጀመርያው ጀምሮ ለአሜሪካ “የተኩስ አቁም አስፈላጊ የመጀመርያ እርምጃ” መሆኑን መናገራቸውን ገልጸዋል።አክለውም በደቡባዊ ሊባኖስ የሚኖሩ “የሌሎች ጦርነትን ዋጋ በግዛታችን ላይ እየከፈሉ ነው” ብለዋል።እስራኤል እና ሊባኖስ የደረሱት የተኩስ አቁም በሦስት ሳምንት የተራዘመው ባለፈው ሳምንት ነው።ነገር ግን እስራኤል እና በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ የሚያደርጉት ውጊያ ቀጥለዋል።ሄዝቦላህ በቀጠናው ስላለው ሰላም በሚደረግ ድርድር ላይ አልተካተተም።ኦውን ጦርነቱ የተካሄደው “ለሊባኖስ ተብሎ ቢሆን” እደግፈው ነበር፤ ነገር ግን “ጦርነቱ የሚካሄደው የሌሎችን ፍላጎት ለማሳካት ሲሆን ሙሉ በሙሉ ውድቅ አደርገዋለሁ” ብለዋል።“እኛ እያደረግን ያለነው የአገር ክህደት አይደለም፤ ይልቁንም የአገር ክህደት የሚፈጸመው የውጭ ጥቅሞችን ለማስከበር አገራቸውን ወደ ጦርነት በወሰዱት ነው” ሲሉ ሄዝቦላህን ሸንቁጠዋል።በደቡባዊ ሊባኖስ የእስራኤል የአየር ድብደባ እንደቀጠለ ነው። እሁድ ዕለት ብቻ በእስራኤል የአየር ድብደባ 14 ሰዎች ሲገደሉ ሁለት ሕጻናት እና ሁለት ሴቶችን ጨምሮ 37 ሰዎች መጎዳታቸውን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።ቅዳሜ ዕለት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የአገሪቱ ጦር ሊባኖስ ውስጥ የሚገኙ “የሄዝቦላህ ዒላማዎችን በኃይለኛው እንዲያጠቁ” ትዕዛዝ ሰጥተዋል። በዚሁ ዕለት ደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች ስድስት ሰዎች ተገድለዋል።ያጋሩ, የሊባኖስ ፕሬዚዳንት የተኩስ አቁሙን በመጣስ ሄዝቦላህን ተቹ
  15. 27 ሚያዚያ 2026የኢራን ባለሥልጣናት በጦርነቱ የፈራረሱ ሕንጻዎችን ለመጽዳት 200,000 መኪናዎች ያስፈልጋሉ አሉፍርስራሽ እያነሳ የጭነት መኪና ላይ የሚጭን ኤክስካቬተርየፎቶው ባለመብት,SMየኢራን አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በጦርነት ምክንያት የፈራረሱ የመኖሪያ ሕንጻዎችን ለማጽዳት “200 ሺህ የጭነት መኪናዎች” ያስፈልጋሉ አለ።የአካባቢ ጥበቃ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቡ አሊ ጎልዛሪ እስራኤል እና አሜሪካ በፈጸሙት የአየር ድብደባ “በሺህዎች የሚቆጠሩ የመኖሪያ ሕንጻዎች ወድመዋል፤ እንዲሁም 10 ሚሊዮን ቶን ፍርስራሾች ተቆልለዋል። በተጨማሪም ይህንን ፍርስራሽ ለማንሳት ወደ 200,000 የጭነት መኪናዎች እንፈልጋለን” ብለዋል።ጎልዛሪ አክለውም “በኢራን ውሃ፣ አፈር፣ አየር እና የብክለት አስተዳደርን ጨምሮ ከባድ የሆነ የአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ገጥሞናል። እነዚህ ደግሞ በጦርነቱ ምክንያት የተባባሱ ናቸው” ብለዋል።ያጋሩ, የኢራን ባለሥልጣናት በጦርነቱ የፈራረሱ ሕንጻዎችን ለመጽዳት 200,000 መኪናዎች ያስፈልጋሉ አሉ
  16. 27 ሚያዚያ 2026ክሬምሊን ከኢራን ጋር የሚደረገው ውይይት በጣም ጠቃሚ መሆኑን ገለጸችየኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አባስ አራግቺ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ለመወያየት ሰኞ ዕለት ሞስኮ ደርሰዋልየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አባስ አራግቺ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ለመወያየት ሰኞ ዕለት ሞስኮ ደርሰዋልየሩሲያው ፕሬዚዳንት ከኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አባስ አጋራቺ ጋር ዛሬ በሴንት ፒተስበርግ እንደሚገናኙ ክሬምሊን አስታወቀ።የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለመንግሥት የዜና ወኪል ታስ እንደተናገሩት “ይህ ውይይት በጣም አስፈላጊ መሆኑን በኢራን እና በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ሁኔታ እንዴት እየጎለበተ ነው የሚለውን በመመልከት መናገር ይቻላል” ብለዋል።አራጋቺ አገራቸው ጦርነቱን ይቋጫል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ንግግር ከአሜሪካ ጋር ማድረግ ሳትችል ከቀረች በኋላ ወቅት ሰኞ ማለዳ ሩሲያ ደርሰዋል።አሜሪካ እና ኢራን የሚያደርጉት ሁለተኛው ዙር የሰላም ንግግር ቅዳሜ ዕለት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ልዑካኖቻቸው ወደ ኢዝላማባድ እንዳይሄዱ ካደረጉ በኋላ ባለበት ቆሟል።ያጋሩ, ክሬምሊን ከኢራን ጋር የሚደረገው ውይይት በጣም ጠቃሚ መሆኑን ገለጸች
  17. 27 ሚያዚያ 2026ኦማን ከቴህራን ጋር በሆርሙዝ ላይ ባላቸው “የጋራ” ኃላፊነት ላይ መነጋገራቸውን አስታወቀችየኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ እሁድ ዕለት በሙስካት የኦማንን ሱልጣን ሃይታም ቢን ታሪቅን አነጋግረዋልየፎቶው ባለመብት,IRANIAN FOREIGN MINISTRY/HANDOUT/EPA/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ እሁድ ዕለት በሙስካት የኦማንን ሱልጣን ሃይታም ቢን ታሪቅን አነጋግረዋልየኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ሩሲያ ከማምራታቸው በፊት እሁድ ዕለት ኦማን ደርሰው ከአገሪቱ መሪ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መወያየታቸው ታውቋል።የኦማን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አልቡሳይዲ በኤክስ ገጻቸው ላይ ከአባስ አረጋቺ ጋር በሆርሙዝ ወሽመጥ ዙሪያ “ጥሩ ውይይት” ማድረጋቸውን ገልጸዋል።አክለውም ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በወሽመጡ ላይ “ለዓለም አቀፉ ማኅበረስብ ስለሚኖር የጋራ ኃላፊነት እንዲሁም ለረዥም ጊዜ መንቀሳቀሻ አጥተው ለተቀመጡ ባህረተኞች ስለሚያስፈልግ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ” መነጋራቸውን አስታውቀዋል።የኢራን ከፍተኛ ዲፕሎማት “ኦማን በክብር ተቀብላ ስላስተናገደችኝ” በማለት አመስግነዋል።አራጋቺ በማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፋቸው ላይ ንግግራቸው ቁልፍ በሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ የመርከቦች እንቅስቃሴ “ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን” መነጋገራቸውን ገልጸዋል።ያጋሩ, ኦማን ከቴህራን ጋር በሆርሙዝ ላይ ባላቸው “የጋራ” ኃላፊነት ላይ መነጋገራቸውን አስታወቀች
  18. 27 ሚያዚያ 2026ወደ ሩሲያ የተጓዙት የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድርድሩ ላለመሳካቱ አሜሪካ ያቀረበቻቸውን ጥያቄዎች ወቀሱየኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ሩሲያ የተደረገላቸው አቀባበልየፎቶው ባለመብት,Iranian Foreign Ministry/Getty Imagesወደ ሩሲያ ያመሩት የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በፓኪስታን ሲደረግ የነበረው የሰላም ድርድር ያልተሳካው አሜሪካ ባቀረበቻቸው ከልክ ያለፉ ጥያቄዎች ምክንያት ነው ሲሉ ለመገናኛ ብዙኃን ተናገሩ።በሩሲያዋ ሴንት ፒተርስፐርግ ከተማ ያረፉት አራግቺ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚደረገውን ጦርነት በተመለከተ ከሩሲያ አጋሮች ጋር እንደሚነጋገሩ በፐርሺያ ቋንቋ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ገልጸዋል።ከሩሲያ በፊት ወደ ፓኪስታን አቅንተው የነበሩት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢስላማባድ የነበራቸው ቆይታ በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ድርድሩ ሊቀጥል ይችላል የሚለው ላይ ያተኮረ እንደነበር አስረድተዋል።አራግቺ በቃለ መጠይቃቸው በኢራን ስለተዘጋው የሆርሙዝ ወሽመጥ አንስተዋል። በወሳኙ የባሕር መስመር በኩል ደኅንነቱ የተጠበቀ ጉዞ ማድረግ ዓለም አቀፍ ጉዳይ ሆኖ መቀጠሉን የጠቀሱት ጠቅሰዋል።እንደ ኦማን ያሉ ጎረቤት አገራት ወሽመጡን በተመለከተ ከኢራን ጋር ባላቸው የጋራ ፍላጎት ላይ እንዲሰሩ ጠይቀዋል።ኢራን እና ኦማንን የሚያስማሙ በርካታ ነጥቦች መኖራቸውን ጠቁመውም፤ ሁለቱ አገራት ሆርሙዝን በተመለከተ ተጨማሪ ንግግር ለማድረግ ስምምነት ላይ እንደደረሱ ተናግረዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሩሲያ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር እንደሚገናኙ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ኒውስ ዘግቧል።የፓኪስታን ቆይታቸውን “እጅግ ውጤታማ” ሲሉ የገለጹት አራግቺ፤ “ኢራን ላይ የተከፈተውን ጦርነት በዘላቂነት ለመቋጨት የሚያስችል ማዕቀፍን በተመለከተ የኢራንን አቋም” ማሳወቃቸውን ጠቅሰዋል።“እውነትም አሜሪካ ዲፕሎማሲን በቁም ነገር ትወስደው እንደሆነ እናያለን” ሲሉ ቅዳሜ ዕለት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ጽፈዋል።የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ኢራን መደራደር ከፈለገች በስልክ መነጋገር እንደሚቻል እና ልዑካኖቻቸውን ወደ ፓኪስታን እንደማይልኩ ተናግረዋል።ያጋሩ, ወደ ሩሲያ የተጓዙት የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድርድሩ ላለመሳካቱ አሜሪካ ያቀረበቻቸውን ጥያቄዎች ወቀሱ
  19. 27 ሚያዚያ 2026“መቼ ወደ ቤታቸው እንደሚመለሱ እርግጠኛ አይደሉም” – በሆርሙዝ መውጫ ያጡት ባሕርተኞችባሕርተኞችየፎቶው ባለመብት,Reutersየነዳጅ ጫኝ መርከብ ኩባንያዎች ማኅበር መረጃ እንደሚያመለክተው በሺህዎች የሚቆጠሩ ባሕርተኞች እና ከ105 በላይ መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ምክንያት መንቀሳቀስ አልቻሉም።ኢራን ከዓለም ነዳጅ እና ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ 20 በመቶው በሚጓጓዝበት ይህ የባሕር መስመር አሜሪካ እና እስራኤል በፈጸሙት “ግልጽ የተኩስ አቁም ጥሰት” ምክንያት እንደማይከፈት አስታውቃለች።ከቢቢሲ ‘ቱዴይ’ ፕሮግራም ጋር ቆይታ ያደረጉት ‘ኢንተርታንኮ’ የተሰኘው የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ማኅበር ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቲም ዊልኪንስ፤ የወሽመጡ መዘጋት በኢራን ባሕር ዳርቻ መንቀሳቀሻ ያጡ ባሕርተኞች ላይ ያደረሰውን ተጽዕኖ አስረድተዋል።ዊልኪንስ እንደሚናገሩት፤ የመርከብ ሠራተኞች እንደ ምግብ፣ ውሃ ማቅረብ እንዲሁም ቆሻሻዎችን እንደማስወገድ ያሉ መሠረታዊ ተግባራት የማስተዳደር ኃላፊነት ስላለባቸው “ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት፣ ውጥረት እና መታከት” ተፈጥሮባቸዋል።“ብዙዎቹ መቼ መመለስ እንደሚችሉ ምንም እርግጠኝነት ሳይኖራቸው መርከብ ላይ መውጫ አጥተዋል” ብለዋል።በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረስም አሁንም በቀጣናው ግጭቶች ቀጥለዋል።ባለፈው ሳምንት ኢራን ሁለት በወሽመጡ ሊያልፉ የነበሩ የጭነት መርከቦች “ለምርመራ” መያዟን ገልጻለች። በወሽመጡ ለማለፍ የሞከሩ ሌሎች መርከቦችም ጥቃት እንደተከፈተባቸው ተዘግቧል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ ጉዞዎችን ያገደችው አሜሪካም በርካታ መርከቦችን ጠልፋለች።ያጋሩ, “መቼ ወደ ቤታቸው እንደሚመለሱ እርግጠኛ አይደሉም” – በሆርሙዝ መውጫ ያጡት ባሕርተኞች
  20. 27 ሚያዚያ 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ ራት ግብዣው ላይ ተኩስ ሲከፈት “አልሰጋሁም ነበር” አሉየደኅንነት አባላት ትራምፕን ሲያስወጡየፎቶው ባለመብት,Reutersቅዳሜ ምሽት ሲካሄድ በነበረው የጋዜጠኞች ራት ግብዣ ላይ የተከፈተው ተኩስ ፕሬዝዳንቱን እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልታናትን ዒላማ በማድረግ እንደሆነ ቢታመንም ዶናልድ ትራምፕ በወቅቱ “ሰግተው እንዳልነበረ” ተናግረዋል።ትራምፕ ከሲቢኤስ ኒውስ ’60 ሚኒትስ’ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ “አልሰጋሁም ነበር። ሕይወትን እረዳለሁ። የምንኖረው ያበደ ዓለም ውስጥ ነው” ብለዋል።የዋይት ሀውስ ዘጋቢ ጋዜጠኞች ራት ግብዣ ላይ የተፈጠረው ክስተት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ እንደተቃጣ ሦስተኛ የግድያ ሙከራ ተወስዷል። ሐምሌ 2016 ዓ.ም. ፔንስልቬኒያ ውስጥ የምርጫ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ሰዓት እንዲሁም ባለፈው መስከረም ላይ በጎልፍ ክለባቸው ውስጥ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል።ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጄዲ ቫንስ በመጀመሪያ እንዲወጡ የተደረገበት የቅዳሜው ጥቃት እንዴት እንደተከሰተ ትራምፕ ተጠይቀዋል። ፕሬዝዳንቱ የሴክሬት ሰርቪስ አባላት ከክፍሉ እንዲያስወጧቸው ሁኔታዎች “ቀላል እንዳላደረጉ” በመጥቀስ ምላሽ ሰጥተዋል።“ምን እንደተፈጠረ መመልከት ፈልጌ ነበር… ምን እየተካሄደ መሆኑን ማየት ፈልጌ ነበር። ሁኔታውን በተገነዘብኩበት ሰዓት፤ ምናልባትም መጥፎ ሁኔታ ነበር” ብለዋል።ከክፍሉ ሲወጡ “እንዲያጎነብሱ” ስለመደረጉ የተነሳላቸው ትራምፕ፤ “[ከደኅንነት አባላት ጋር] መራመድ ጀመርኩ። ዞርኩ፣ መራመድ ጀመርኩ፤ ከዚያም ‘እባክህ አጎንብስ፣ እባክህ ወደ ወለሉ አጎንብስ’ አሉኝ” በማለት ሁኔታውን ገልጸዋል።“ስለዚህ አጎነበስኩ፤ ቀዳማዊት እመቤቷም አጎነበሰች” ሲሉም አክለዋል።በአሜሪካ የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ኒውስ ከተጠርጣሪው ኮል አለን ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚታመን በእጅ የተጻፈ ሰነድን ተመልክቷል። ሰነዱ፤ “ከከፍተኛ ደረጃ እስከ ታች” ያሉ የትራምፕ አስተዳደር አባላትን ዒላማ ማድረግ እንደሚፈልግ ያሳያል።ጽሑፉ ላይ “የህጻናት ወሲብ ጥቃት ፈጻሚ፣ ደፋሪ እና ከሃዲ” በሚል ስለሰፈሩት አገላለጾች በቃለ መጠይቁ በተነሳበት ወቅት በትራምፕ እና በጋዜጠኛዋ ኖራህ ኦ’ዶኔል መካከል ውጥረት ተስተውሎ ነበር።ጋዜጠኛዋ ስለ እነዚህ አገላለጾች በመጠየቋ “ወራዳ” ሲሉ ጠርተዋታል። “ይህንን በማንበብሽ ልታፍሪ ይገባል፤ ምክንያቱም እኔ ከእነዚህ ነገሮች አንዱንም አይደለሁም” ብለዋል።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ራት ግብዣው ላይ ተኩስ ሲከፈት “አልሰጋሁም ነበር” አሉ