ከ 5 ሰአት በፊት
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ
በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን የተወገዱት የምያንማር መሪ አን ሳን ሱ ኪ ከማረሚያ ቤት ወጥተው ቤት ውስጥ የቁም እስረኛ መሆናቸውን የአገሪቱ ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።
የ80 ዓመቷ የኖቤል ሎሬት ተሸላሚ እአአ በ2021 በመፈንቅለ መንግሥት ከመሪነት ሥልጣናቸው ከወረዱ ጊዜ ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ።
አን ሳን ሱ ኪ እስካሁን ድረስ የቆዩት በዋና ከተማዋ በሚገኝ ናይ ፒ ታው ወታደራዊ እስር ቤት እንደሆነ ይታመናል።
መፈንቅለ መንግሥቱን በመሩት የጦሩ አዛዥ ሚን ኡንግ ህሌይንግ የተሰጠው መግለጫ “ቀሪውን የእስር ጊዜያቸውን በተዘጋጀላቸው የመኖሪያ ቤት እንዲጨርሱ” መወሰኑን ይገልጻል።
አን ሳን ሱ ኪ ወደ ሥልጣን የመጡት እአአ በ2015 የወቅቱ የምያንማር መሪ የነበሩት መሪ ዲሞክራሲያዊ ለውጦችን ካስተዋወቁ በኋላ ነበር።።
ከዚያ በፊት ግን ለአስርት ዓመታት በዘለቀው ወታደራዊ አመራር ውስጥ የዲሞክራሲ አቀንቃኝ የነበሩ ሲሆን ከ15 ዓመታት በላይ በቤት ውስጥ እስር ላይ ቆይተዋል።
የአገሪቱ ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ከሁለት ወታደሮች ጋር ተቀምጠው የሚያሳይ ምስልን አጋርተዋል።
ልጃቸው ኪም አሪስ በሕይወት መኖራቸውን የሚያሳይ ምንም ዓይነት ማስረጃ እንደሌለው በመግለጽ የጦሩን መግለጫ በጥርጣሬ እንደሚመለከተው ተናግሯል።
የምያንማር የቀድሞ መሪ አን ሳን ሱ ኪ ወደ ቤት ውስጥ እስር መዛወራቸውን የአገሪቱ ጦር አስታወቀ