የኢራን ጦር የአሜሪካ ባሕር ኃይል ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የሚገባ ከሆነ ጥቃት እንደሚፈጽም አስጠነቀቀ። ዶናልድ ትራምፕ በወሽመጡ መንቀሳቀሻ አጥተው የቆሙ መርከቦችን እየመሩ ለማስወጣት መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል። የኢራን ማዕከላዊ ዕዝ ያወጣው መግለጫ “ማንኛውም የውጭ ጦር ኃይል” ወደ ወሽመጡ ለመግባትም ሆነ ለመቅረብ ቢሞክር “በተለይ የጠብ አጫሪዎ የአሜሪካ ጦር” ጥቃት እንፈጽማለን ብሏል።

ጭምቅ ሃሳብ

ኢራን ላቀረበችው የሰላም ዕቅድ አሜሪካ ምላሽ መስጠቷን ገለጸች

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 1 ሰአት በፊትኢራን ‘ለአሜሪካ ዛቻዎች ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ገለጸችኢስማኤል ባጋይየፎቶው ባለመብት,Reutersፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ከ”ሰኞ ጠዋት” ጀምሮ መርከቦችን ማስወጣት እንደሚጀምር መግለጻቸውን አስመልክቶ ኢራን ምላሽ ሰጥታለች።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወሽመጡ ዙሪያ “ለአሜሪካ ዛቻዎች ምላሽ ለመስጠት” ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል።ሜህር የዜና ወኪል ባጋራው መግለጫ ቃል አቀባዩ ኢስማኤል ባጋይ ኢራን የባህር ወሽመጡ “ጠባቂ እና ተከላካይ” ሆና ትቀጥላለች ብለዋል። “መርከቦች እና የመርከብ ኩባንያዎች ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ከኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ባለስልጣናት ጋር መተባበርን እንደሚጠይቅ በሚገባ ያውቃሉ” ሲሉ አክለዋል።የሕግ የበላይነትን የሚከተሉ አገሮች የአሜሪካን “ሕገወጥ እርምጃዎች” የሚከተሉበት ምንም ምክንያት እንደሌለም ተናግረዋል።ቀደም ሲል የኢራን ማዕከላዊ ዕዝ ኃላፊ “በተለይም ጠበኛው የአሜሪካ ጦርን” ጨምሮ ወደ ባህር ወሽመጡ ለመቅረብ ወይም ለመግባት የሚሞክርን “ማንኛውም የውጭ የጦር ኃይል” እንደሚያጠቃ ተናግረዋል።ያጋሩ, ኢራን ‘ለአሜሪካ ዛቻዎች ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች
  2. ከ 1 ሰአት በፊትባለፈው ወር በአሜሪካ ጦር የተያዘችው የኢራን መርከብ አባላት ለቴህራን ሊሰጡ ነውባለፈው ወር በአሜሪካ ቁጥጥር ስር የዋለችው የኢራን መርከብ ሃያ ሁለት ሠራተኞች ለፓኪስታን ተላልፈው መሰጠታቸው ተገለጸ።የፓኪስታን መንግሥት “ዛሬ ለኢራን ባለሥልጣናት ይተላለፋሉ” ሲል አስታውቋል።የአሜሪካ ወታደሮች ባለፈው ወር ቱስካ በተሰኘው መርከብ የተቆጣጠሯት ሞተሯን ከመቱ በኋላ ነበር። ኢራን ድርጊቱን “የባህር ላይ ውንብድና” ስትል የጠራችው ሲሆን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደግሞ መርከቡ “የባህር ኃይላችንን እገዳች ለማለፍ ቢሙክሩም አልተሳካላቸውም” ብለዋል።የመርከቡ ሠራተኞች ወደ አገራቸው መመለሳቸው “በዩናይትድ ስቴትስ የተወሰደ የመተማመን ግንባታ እርምጃ” እንደሆነ ፓኪስታን ገልጻለች።መርከቧ “አስፈላጊው ጥገና ከተደረገለት በኋላ ወደ መጀመሪያዎቹ ባለቤቶቿ ለመመለስ ወደ ፓኪስታን የውሃ አካል ትመለሳለች” ሲል አክሏል።”እነዚህ ተመላሾች በኢራን እና በአሜሪካ ድጋፍ ጋር በመተባበር እየተቀናጁ ነው። መርከበኞቹን ለመመለስ ኢራን እና አሜሪካ ትብብር ማድረጋቸውን የፓኪስታን ባለሥልጣናት ተናግረዋል።”ፓኪስታን እንዲህ ዓይነት መተማመንን የሚገነቡ እርምጃዎችን ትደግፋለች። ለቀጣናው ሰላም እና ደህንነት የሚደረጉ ቀጣይነት ያላቸውን የድርድር እና የዲፕሎማሲ ጥረቶችን ማድረጓንም ትቀጥላለች” ብሏል።ያጋሩ, ባለፈው ወር በአሜሪካ ጦር የተያዘችው የኢራን መርከብ አባላት ለቴህራን ሊሰጡ ነው
  3. ከ 2 ሰአት በፊትየኢራን ጦር አሜሪካ ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የምትገባ ከሆነ ጥቃት እንደሚፈጽም አስጠነቀቀነዳጅ ጫኝ መርከብ በኬሽም ደሴት አቅራቢኣ እየተጓዘየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን ጦር የአሜሪካ ባሕር ኃይል ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የሚገባ ከሆነ ጥቃት እንደሚፈጽም አስጠነቀቀ።ዶናልድ ትራምፕ በወሽመጡ መንቀሳቀሻ አጥተው የቆሙ መርከቦችን እየመሩ ለማስወጣት መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል።የኢራን ማዕከላዊ ዕዝ ያወጣው መግለጫ “ማንኛውም የውጭ ጦር ኃይል” ወደ ወሽመጡ ለመግባትም ሆነ ለመቅረብ ቢሞክር “በተለይ የጠብ አጫሪዋ የአሜሪካ ጦር” ጥቃት እንፈጽማለን ብሏል።ሜጀር ጄነራል አሊ አብዶላሂ ኢራን “በተደጋጋሚ” ወሽመጡ በጦሯ “ቁጥጥር ስር መሆኑን” እና ለማለፍ የሚፈልግ “በሁሉም ሁኔታዎች ስር” ከቴህራን ጋር መተባባር እንደሚያስለፈልገው መናገራቸውን አስታውሰዋል።የጦሩ መግለጫ በኢራን መገናኛ ብዙኃን በሆነው ኢሪብ ተጋርቷል።እሁድ ዕለት ትራምፕ መርከቦቻቸው በሆርሙዝ ወሽመጥ የቆሙባቸውን አገራት እንደሚያግዙ ተናግረዋል። ይህንንም ተከትሎ የአሜሪካ ባሕር ኃይል ወታደሮቹ እና የጦር አውሮፕላኖቹን ዝግጁ ማድረጉን አስታውቋል።ትራምፕ “ለኢራን፣ ለመካከለኛው ምሥራቅ እና ለዩናይትድ ስቴትስ ደህንነት ሲባል ለአገራት መርከቦቻቸውን እየመራን እገዳ ከተጣለበት የውሃው አካል እንደምናስወጣላቸው ነግረናቸዋል። ስለዚህ በነጻነት ወደሚቀጥለው ጉዳይቸው መሄድ ይችላሉ” ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።ትራምፕ በሆርሙዝ ወሽመጥ ቆመው ያሉት እና አሜሪካ ድጋፍ ልታደርግላቸው መሆኑን የነገረቻቸው የየትኞቹ አገራት መርከቦች እንደሆኑ አላሰወቁም።ያጋሩ, የኢራን ጦር አሜሪካ ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የምትገባ ከሆነ ጥቃት እንደሚፈጽም አስጠነቀቀ
  4. ከ 2 ሰአት በፊት20,000 የመርከብ ሠራተኞች እና 2,000 መርከቦች መንቀሳቀሻ አጥተው ቆመዋልአርሴኒዮ ዶሚንጌዝየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ የቆሙ መርከቦችን “እየመራች” ልታስወጣ መሆኑን ከመናገራቸው ቀደም ብሎ የተባበሩት መንግሥታት አባል አገራት በለንደን በካሄዱት ስብሰባ ኢራን በዓለም አቀፍ የመርከብ ጭነት ላይ የምታደርሰውን መስተጓጎል “በጥብቅ አውግዘዋል።”ስብሰባው ዓለም አቀፉ የባህር ኃይል ድርጅት (የመርከብ ጭነትን የሚቆጣጠረው ልዩ የተባበሩት መንግሥታት ተቋም) ያቀረበውን ውሳኔ አጽድቋል። ኢራን የመርከብ ሠራተኞችን ደህንነት “አደጋ ላይ በመጣል ከባድ ስጋትን እና ለባህር አካባቢ አደጋን ፈጥራለች” ሲል ገልጿል።ከድምጽ አሰጣጡ በኋላ የተቋሙ ኃላፊ አርሴኒዮ ዶሚንጌዝ የመርከበኞች እርዳታ ላይ ትኩረት እንዲደረግ አሳስበዋል።”በእነዚህ ጉዳዮች ላይ በምንሠራበት መንገድ ዙሪያ ያለኝን ብስጭት መግለጽ እፈልጋለሁ” ብለዋል።”እነዚህ ውይይቶች እና ሂደቶች ለዘጠኝ ሳምንታት መንቀሳቀሻ አጥተው የቆዩትን 20,000 የመርከብ ሠራተኞችን እና 2,000 መርከቦችን እንዴት እንደሚረዱ አላየሁም” ሲሉ አስረድተዋል።ያጋሩ, 20,000 የመርከብ ሠራተኞች እና 2,000 መርከቦች መንቀሳቀሻ አጥተው ቆመዋል
  5. ከ 2 ሰአት በፊትየትራምፕን ‘ፕሮጀክት ፍሪደም’ ለመደገፍ 15 ሺህ ወታደሮች እና 100 የጦር አውሮፕላኖች ይሳተፋሉየሴንቲኮም አዛዥ የሆኑት አዳም ብራድ ኩፐርየፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockየምስሉ መግለጫ,የሴንቲኮም አዛዥ የሆኑት አዳም ብራድ ኩፐርየአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) የትራምፕን ፕሮጀክት ፍሪደም እንዴት አድርጎ እንደሚያስፈጽም ይፋ አድርጓል።“የዩኤስ ማዕከላዊ ዕዝ ጦር በሆርሙዝ ወሽመጥ የንግድ መርከቦች ያለ ችግር እንዲንቀሳቀሱ ለማስቻል ፕሮጀክት ፍሪደምን ሚያዚያ 26 ድጋፍ ይሰጣል” ሲል እሁድ ዕለት ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል።ይህ ድጋፍ 15,000 ወታደሮችን፣ ዒላማቸውን ለይተው የሚመቱ ሚሳዔል አውዳሚዎችን እና 100 አውሮፕላኖቸን የሚያካትት ነው።ሴንትኮም “በባሕሩ ላይ የሚካሄደው የዓለም አንድ አራተኛ ነዳጅ ንግድ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው የነዳጅ እና የማዳበሪያ ምርት በወሽመጡ ላይ ነው የሚጓጓዘው” ብሏል።የሴንቲኮም አዛዥ የሆኑት አዳም ብራድ ኩፐር “የባሕር ላይ እገዳችን ባለበት የመከላከል ተልዕኮ ያለው ድጋፋችን ለቀጣናው ደህንነት እና ለዓለም ምጣኔ ሃብት ወሳኝ ነው“ ብለዋል።ሴንትኮም አዛዥ አድም ብራድ ኩፐር አክለውም “ለዚህ የመከላከያ ተልእኮ የምናደርገው ድጋፍ ለክልላዊ ደህንነት እና ለአለም ኢኮኖሚ አስፈላጊ ነው ።ያጋሩ, የትራምፕን ‘ፕሮጀክት ፍሪደም’ ለመደገፍ 15 ሺህ ወታደሮች እና 100 የጦር አውሮፕላኖች ይሳተፋሉ
  6. ከ 5 ሰአት በፊትትራምፕ አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ የቆሙ መርከቦችን “እየመራች” ልታስወጣ መሆኑን ተናገሩከአሜሪካ የጦር መርከብ ላይ ጄት እየተንደረደረ ሲነሳየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesእሁድ ዕለት ትራምፕ መርከቦቻቸው በሆርሙዝ ወሽመጥ የቆሙባቸውን አገራት እንደሚያግዙ ተናገሩ።“ለኢራን፣ ለመካከለኛው ምሥራቅ እና ለዩናይትድ ስቴትስ ደህንነት ሲባል ለአገራት መርከቦቻቸውን እየመራን እገዳ ከተጣለበት የውሃው አካል እንደምናስወጣላቸው ነግረናቸዋል። ስለዚህ በነጻነት ወደሚቀጥለው ጉዳይቸው መሄድ ይችላሉ” ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።ትራምፕ በሆርሙዝ ወሽመጥ ቆመው ያሉት እና አሜሪካ ድጋፍ ልታደርግላቸው መሆኑን የነገረቻቸው የየትኞቹ አገራት መርከቦች እንደሆኑ አላሰወቁም።ትራምፕ “ፕሮጀክት ፍሪደም” (የነጻነት ፕሮጀክት) ሲሉ የጠሩት ይህ መርከቦችን ከወሽመጡ የማስወጣት ሂደት ሰኞ ዕለት እንደሚጀመር ተናግረዋል።ትራምፕ ይህ መርከቦቸን የማስወጣት ሂደትን ለማደናቀፍ የሚሞክር ካለ “የኃይል እርምጃ” እንደሚወስዱ አስጠንቀቅቀዋል።ኢራን ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ በወሽመጡ ላይ የሚደረግ እንቅስቃሴን ሙሉ በሙሉ አግዳለች።ዩናይትድ ስቴትስ እንዲሁ ወደ ኢራን ወደቦች መርከቦች እንዳይገቡ እና እንዳይወጡ እገዳ ጥላለች።የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ የነበሩት እና አሁን የፓርላማ አባል የሆኑት ኢብራሂም አዚዝ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ “ማንኛውም የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት” እንደ “የተኩስ አቁም ጥሰት” ይቆጠራል ብለዋል።ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ልጥፋቸው ላይ የአሜሪካ ተወካዮች ከኢራን ጋር “በጣም አዎንታዊ” የሆነ ውይይት ማካሄዳቸውን ጠቅሰው “ሁላችንንም በጣም በጎ ወደ ሆነ ነገር ይመራል” ብለዋል።አክለውም መርከቦችን ከወሽመጡ የማስወጣት ዘመቻ “የሰብዓዊነት እርምጃ” መሆኑን ተናግረው በአሜሪካ፣ ኢራን እና ሌሎች የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ስም የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል።ትራምፕ በዚህ ልጥፋቸው ላይ ከቴህራን ጋር ያለው ትብብር በምንም መልኩ እንደሚስተናገድ ያሉት ነገር የለም።ትራምፕ “. . . የመርከብ እንቅስቃሴው ምንም ጥፋት ያልፈጸሙ ሰዎችን፣ ኩባንያዎችን እና አገራትን ለማስለቀቅ የሚደረግ ብቻ ነው” ሲሉ አብራርተዋል።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በፕሮጀክት ፍሪደም ላይ 15,000 ወታደሮች፣ ዒላማቸውን ለይተው የሚመቱ ሚሳዔል ማምከኛዎች እንዲሁም ከ100 በላይ አውሮፕላኖች እንደሚሳተፉ አስታውቋል።በባሕረ ሰላጤው ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ወደ 20,000 የሚገመቱ ባህረተኞች መንቀሳቀሻ አትተው መቆማቸው ይገመታል።ለመርከቦቹ እና ሠራተኞቻቸው በየጊዜው እየቀነሰ የመጣው አቅርቦት እና የባሕረተኞቹ አካላዊ እና የአእምሮ ጤና አሳሳቢነት እያደገ መጥቷል።የዓለም 20 በመቶ የሚሆነው ነዳጅ ዘይት እና የተፈጥሮ ጋዝ የሚተላለፈው በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ነው።ያጋሩ, ትራምፕ አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ የቆሙ መርከቦችን “እየመራች” ልታስወጣ መሆኑን ተናገሩ
  7. ከ 6 ሰአት በፊትኢራን ላቀረበችው የሰላም ዕቅድ አሜሪካ ምላሽ መስጠቷን ገለጸችየኢራን መሪዎች ምስል የታተመበት ባንዲራየፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን ላቀረበችው የሰላም ዕቅድ ከአሜሪካ ምላሽ ማግኘቷን የአገሪቱ ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አሜሪካ የሰጠችው ምላሽ በፓኪስታን በኩል እንደደረሳቸው እና እየተመለከቱት መሆኑን መናገራቸውን ታስኒም የዜና ወኪል ዘግቧል።አሜሪካ እስካሁን ድረስ ለቴህራን የሰላም ዕቅድ ምላሽ መስጠቷን በይፋአላሳወቀችም። ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ትራምፕ እሁድ ዕለት ለእስራኤሉ ካን ኒውስ ዕቅዱ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል።የኢራን መገናኛ ብዙኃን የቴህራን ባለ 14 ነጥብ የሰላም ዕቅድ ዋሺንግተን ጦሯን ከድንበር አካባቢ እንድታርቅ፣ የኢራን ወደቦች ላይ ያለቸውን እገዳ እንድታነሳ እንዲሁም የትኛውም ግጭት፣ እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምትፈጽመውን ጨምሮ እንዲቆም የሚጠይቅ ነው ሲሉ ዘግበዋል።ዕቅዱ በሁለቱ አገራት መካከል በሰላሳ ቀናት ውስጥ ስምምነት እንዲደረስይጠይቃል።የኢራን መገናኛ ብዙኃን አክለውም የሰላም ዕቅዱ ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች አሁን ያለውን የተኩስ አቁም ከማራዘም ይልቅ “ጦርነቱን በማስቆም” ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ይጠይቃል።መገናኛ ብዙኃኑ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይን ጠቅሰው “አሁን ባለው ደረጃ ስለ ኒውክሌር ድርድር የለም” ማለታቸውን ዘግበዋል።ኢራን በተደጋጋሚ የኒውክሌር ፕሮግራሟ ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ የሚውል መሆኑን ትናገራለች።ነገርግን ኢራን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ባይኖራትም ዩራኒየምን የጦር መሣሪያ ለማምረት በሚያስችል ደረጃ ያበለጸገች ብቸኛ አገር ናት።ያጋሩ, ኢራን ላቀረበችው የሰላም ዕቅድ አሜሪካ ምላሽ መስጠቷን ገለጸች