
ከ 4 ሰአት በፊት
የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ
ፖሊስ ባለፈው ሳምንት በጎርፍ ከተወሰደ በኋላ የጠፋውን ነጋዴ ፍለጋ ከተሰማራ በኋላ አስከሬኑን በአዞዎች ከተሞላው ወንዝ ውስጥ ማግኘቱን አስታወቀ።
የአካባቢው አስተዳደር እና ፖሊስ የጠፋውን ነጋዴ ለመፈለግ ሂሊኮፕተሮች እና ድሮኖች አሰማርቶ ነበር ተብሏል።
በአዞ የተሞላው ወንዝ ውስጥ ግለሰቡን እንደበላ የተጠረጠረ አዞ ከተገደለ በኋላ አንድ የፖሊስ ባልደረባ በገመድ በመውረድ እና አዞውን በመጫን በአቅራቢው ወደሚኝ ብሔራዊ ፓርክ ተወስዷል።
ነጋዴውን እንደበላ የተጠረጠረው ኦዞ መገደሉን ካፒቴን ጆሃን ፓትጊይተር ለኒውስ24 ድረገጽ ተናግረዋል።
ካፒቴን ፖትጌይተር ለኒውስ24 ድረገጽ በሰጡት ቃለ መጠይቅ “የአዞው የሾሉ ጥርሶች ጋር መጠጋት ምቾት የሚሰጥ ነገር አይደለም” ብለዋል።
ፖትጌይተር ገመድ ተጠቅመው አዞውን ከያዙ በኋላ ሁለቱም በሰሜን ምስራቅ ከሚገኘው ከኮማቲ ወንዝ እንዲወጡ ተደርገዋል።
በወንዙ ውስጥ በአዞ ተበልቶ የተገኘው ግለሰብን ማንነት ለመለየት የዲኤንኤ ምርመራ እንደሚደረግ ተገልጿል።
ባለፈው ሳምንት የጠፋው ግለሰብ መኪናው ድልድይ ሊያቋርጥ ሲል ተቀርቅሮ መንቀሳቀስ አለመቻሉ ታውቋል።
ፖሊስ በአካባቢው በደረሰበት ወቅት መኪናው ባዶ የነበረ ሲሆን በውሃ ተወስዶ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ አሳድሯል።
የምፑማላንጋ አውራጃ ፖሊስ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ማቬላ ማሶንዶ ለኤስኤቢሲ የአካባበው ባለሥልጣናት ድሮኖችን እና ሂሊኮፕተሮችን ተጠቅመው ፍለጋውን ያካሄዱ ሲሆን በአነስተኛ ደሴት ላይ ፀሐይ የሚሞቁ አዞዎችን መመልከታቸውን ተናግረዋል።
ፖትጌይተር እንደሚሉት ከሆነ ከዓመታት ልምድ አንድ በቅርቡ የበላ እንስሳን መለየት ይችላሉ።
“ከሞላ ሆዱ ባሻገር ለመንቀሳቀስ ወይንም የድሮኑን አና ሂሊኮፕተር ድምጽ ሲሰማ ወደ ወንዙ ለመግባት አይሞክርም” ሲሉ ከኒውስ24 ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ላይ ተናግረዋል።
ከዚያም አዞው መገደሉን እና ፖትጌይተር በገመድ ተንጠላጥለው በመውረድ አዞውን በአቅራቢያው ወደሚገኝ ብሔራዊ ፓርክ መውሰዳቸውን ተናግረዋል።
ፖሊስ የካፒቴኑን እርምጃ “በጣም አደገኛ እና ውስብስብ ዘመቻ” ሲል ገልጾታል።
4.5 ሜትር የሚረዝመው እና 500 ኪሎ ግራም ክብደት ያለው አዞ በአቅራቢያው ወደ ክሩገር ብሔራዊ ፓርክ ተወስዶ ሲፈተሽ የሰው አስከሬን በሆዱ ውስጥ ተገኝቷል።
ከሰው አስከሬን በተጨማሪ ስድስት ጫማዎች መገኘታቸውን ፖሊስ አስታውቆ፣ ይህም ማለት ሌላ ሰው ተገድሏል አልያም “ማንኛውንም ነገር ይበላል” ማለት ነው ብለዋል።
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ተጠባባቂ አዛዥ ሌተናንት ጄነራል ፑሌንግ ዲምፓኔ የባልደረባቸውን እርምጃ አድንቀዋል።
