ኢራን እንደዛተችው በአሜሪካ መርከቦች ላይ ጥቃት ከፈጸመች ‘ከምድረ ገጽ ትጠፋለች’ ሲሉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስጠነቀቁ።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 1 ሰአት በፊትበኢራን ጥቃት የተፈጸመበት የኤምሬትስ የነዳጅ ማዕከል ምን ያህል ወሳኝ ነው?ከነዳጅ ማጠራቀሚያ ላይ የሚታይ ጥቁር ጭስየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,በኢራን ተደጋጋሚ ጥቃት የተፈጸመበት ፉጃይራህ ባለፈው መጋቢት ከተፈጸመበት ጥቃት በኋላ በዚህ መልኩ በእሳት ተያይዞ ታይቷልኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ላይ ስትፈጽም ለቆየችው ጥቃት ዋነኛ ዒላማ የሆነችው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፉጃይራህ የተባለው ዋነኛው የነዳጅ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዞን በቴህራን መመታቱን አስታውቃለች።በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ላለፉት ሳምንታት የተኩስ አቁም ከተደረሰ በኋላ የተፈጸመውን ጥቃት አደራዳሪዋ ፓኪስታንን ጨምሮ በርካታ አገራት እና የአረብ ሊግ አውግዘውታል።ከዚህ ቀደምም ጥቃት የተፈጸመበት ፉጃይራህ የተባለው የነዳጅ ምርት ማዕከል የጥቃት ዒላማ እንዲሆን ያደረገው ምክንያት ምንድን ነው? ስለዞኑ ምን የሚታወቅ ነገር አለ?ፉጃይራህ የነዳጅ ኢንዱስትሪ ዞን በኤምሬትስ ምሥራቃዊ የባሕር ዳርቻ ከወሳኙ የባሕር መተላለፊያ ሆርሙዝ በስተደቡብ ይገኛል። ዞኑ ከሕንድ ውቅያኖስ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ቦታ ላይ ያለ ነው።ፉጃይራህ በመካከለኛው ምሥራቅ ከሚገኙ ግዙፍ የነዳጅ ማከማቻ ማዕከላት መካከል አንዱ ነው። በዚህም ወደ 70 ሚሊዮን በርሜል የሚደርስ ነዳጅ ማከማቸት የሚችል አቅም አለው።የማከማቻው ነዳጅ የመያዝ አቅም በአጠቃላይ በዓለም ዙሪያ በአንድ ቀን ውስጥ ጥቅም ላይ ከሚውለው ነዳጅ ውስጥ ሦስት አራተኛውን ያህል ያከማቻል።ይህም ማለት ዓለማችን በቀን 100 ሚሊዮን በርሜል በላይ የምትጠቀም ሲሆን፣ ፉጃይራህ ላይ የሚከማቸው ደግሞ 70 ሚሊዮን በርሜል የሚሆን ነው።ምንም እንኳን በጦርነቱ የተነሳ የሆርሙዝ ወሽመጥ ቢዘጋም ከአቡ ዳቢ የነዳጅ ማውጫዎች ከሚነሳው ደፍድፍ ነዳጅ የተወሰነው በቧንቧ አማካይነት በፉጃይራህ በኩል በመርከቦች በኩል ወደ ዓለም ገበያ እየቀረበ ይገኛል።ያጋሩ, በኢራን ጥቃት የተፈጸመበት የኤምሬትስ የነዳጅ ማዕከል ምን ያህል ወሳኝ ነው?
  2. ከ 2 ሰአት በፊትእስራኤል በሊባኖስ 17 ሰዎችን በገደለች ማግሥት ነዋሪዎች ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አወጣችየቀብር ስነ ስርዓትየፎቶው ባለመብት,EPAየሊባኖስ ተኩስ አቁም ከተጀመረ ወዲህ ከፍተኛ ሞት ከታየባቸው ቀናት አንዱ በሆኖ በተመዘገበው በትናንትናው ዕለት እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት 17 ሰዎች መገደላቸውን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ አንስቶ በተፈጸሙ ጥቃቶች የተገደሉ ሰዎች ብዛት 110 መድረሱን የሊባኖሱ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።ሚኒስቴሩ ቁጥር ንጹኃን እና ተዋጊዎችን ለይቶ አላስቀመጠም። ይሁን እንጂ ከተገደሉት ሰዎች መካከል ሁለት ሕጻናት ሲሆኑ፣ 14 ሕጻናትም ተጎድተዋል።ጥቃት የምትፈጽመው በሺዓ እስላማዊው ቡድን ሄዝቦላህ ላይ መሆኑን የምትናገረው እስራኤል በበኩሏ፤ በደቡባዊ ሊባኖስ ሁለት ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላልፋለች።የእስራኤል ጦር “ሄዝቦላህ በሚፈጽመው የተኩስ አቁም ስምምነት ጥሰት” ምክንያት በቡድኑ ላይ “በኃይል ለመንቀሳቀስ መገደዱን” ገልጿል።የእስራኤል ጦር ይህንን ትዕዛዝ ከማስተላለፉ አስቀድሞ በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ በደቡባዊ ሊባኖስ የሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች ላይ ጥቃት ፈጽሟል የሚል ክስ አሰምቶ ነበር። ሄዝቦላህ ስለ ክሱ አስተያየት አልሰጠም።ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ 17 ወታደሮች እንደተገደሉባት የምትናገረው እስራኤል፤ ሄዝቦላህ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶች እና ድሮኖችን እንዳስወነጨፈ በመጥቀስ ትከስሳለች።ሄዝቦላህ፤ እስራኤል እና ሊባኖስ የደረሱበት የተኩስ አቁም ስምምነት ፈራሚ አካል አይደለም።እስራኤል ለስምምነቱ የምትገዛ ከሆነ ግን ተኩስ አቁሙን እንደሚቀበል ጠቆሞ ነበር።የእስራኤል ጦር በስምምነቱ መሠረት “የታቀዱ፣ አይቀሬ ወይም ቀጣይ ጥቃቶችን” መፈጸም እንደተፈቀደለት ይናገራል። የሊባኖስ ባለሥልጣናት ስምምነቱ በዚህ መልኩ መተርጎሙን የሚቃወሙ ሲሆን፣ እስራኤል በተደጋጋሚ የተኩስ አቁሙን ጥሳለች የሚል ክስ ያቀርባሉ።ያጋሩ, እስራኤል በሊባኖስ 17 ሰዎችን በገደለች ማግሥት ነዋሪዎች ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አወጣች
  3. ከ 2 ሰአት በፊትዓለም አቀፉ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ባለቤቶች ማኅበር የአሜሪካ እጀባ ዕቅድ “ከፍተኛ ለውጥ አያመጣም” አለየጭነት መርከብየፎቶው ባለመብት,West Asia News Agency via REUTERSዓለም አቀፉ የገለልተኛ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ባለቤቶች ማኅበር ‘ኢንተርታንኮ’፤ አሜሪካ ይፋ ያደረገችው የንግድ መርከቦችን አጅቦ በሆርሙዝ ወሽመጥ የማሳለፍ ዕቅድ “በከፍተኛ ሁኔታ የሚለውጠው ነገር የለም” አለ።‘ሜርስክ’ የተሰኘው ግዙፍ የሎጂስቲክ ኩባንያ አንድ መርከቡ በአሜሪካ ጦር ታጅቦ ሰኞ ዕለት በሆርሙዝ ወሽመጥ ማለፉን አስታውቋል። ከቢቢሲ ‘ቱዴይ’ ፕሮግራም ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢንተርታንኮ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቲም ዊልኪንስ፤ የመርከቡ ማለፍ እገዳውን በማቃለል ረገድ ያለው ተጽዕኖ “ውቅያኖስ ውስጥ እንዳለ ጠብታ ነው” ብለዋል።ዊልኪንስ “በጣም ጠባብ በሆነ ሁኔታ ውስጥ በቅርብ እጀባ ተደርጎለት ያለፈው አንድ መርከብ ነው” ብለዋል። የመርከቡ ማለፍ መውጫ ላጡት የተቀሩት መርከቦች “ምንም ነገር ላይ ከፍተኛ ለውጥ አያመጣም” ሲሉ ተናግረዋል።ገለልተኛ የነዳጅ ጫኝ ባለቤቶችን የሚወክለውን ማኅበር የሚመሩት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አክለውም፤ “ተግባራዊ እየሆነ ያለ ቅርጽ ያለው ወይም የተቀናጀ ሥርዓት የለም። ስለዚህ አባላቶቻችን እየጠየቁ ያሉት መሠረታዊ ጥያቄዎችን ነው፤ እነዚህን ጉዞዎች የሚያስጀምረው ማነው?” ብለዋል።“መርከቦቹን ወክሎ ከባለሥልጣናቱ ጋር የሚነጋገረው ማነው? ወሳኙ ጉዳይ ደግሞ በጉዞው ወቅት መርከቦቹ ከኢራን ኃይሎች ችግር ቢያጋጥማቸው የተያዘው ዕቅድ ምንድነው?” ሲሉም ጠይቀዋል።ያጋሩ, ዓለም አቀፉ የነዳጅ ጫኝ መርከብ ባለቤቶች ማኅበር የአሜሪካ እጀባ ዕቅድ “ከፍተኛ ለውጥ አያመጣም” አለ
  4. ከ 4 ሰአት በፊትትራምፕ ኢራን የአሜሪካ መርከቦችን ካጠቃች “ከምድረ ገጽ ትጠፋለች” ሲሉ ዛቱትራምፕየፎቶው ባለመብት,EPAኢራን እንደዛተችው በአሜሪካ መርከቦች ላይ ጥቃት ከፈጸመች ‘ከምድረ ገጽ ትጠፋለች’ ሲሉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስጠነቀቁ።ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ሰኞ ዕለት ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ አሜሪካ ‘ፕሮጀክት ፍሪደም’ በሚል በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚተላለፉ መርከቦችን ለመጠበቅ በምትወስደው እርምጃ ወቅት በመርከቦቿ ላይ ጥቃት ከተፈጸመ “ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች” ሲሉ ዝተዋል።ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም በድርድሩ ሂደት ኢራን “የበለጠ ልፍስፍስ” እየሆነች እንደሆነ እና የአገራቸው ሠራዊትም ከኢራን የተሻለ ወታደራዊ አቅም እንዳለው ተናግረዋል።ይህ የትራምፕ ቃለ ምልልስ የተሰማው የአሜሪካ ኃይሎች የሆርሙዝ ወሽመጥን ለማስከፈት እየወሰዱት ባለው እርምጃ ሰባት የኢራን “ትንንሽ ጀልባዎችን” መምታታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ካስታወቁ በኋላ ነው።በተጨማሪም አሜሪካ የኢራንን ድሮኖች እና ሚሳዔሎችን መትታ መጣሏን አስታውቃለች።ፕሬዝዳንት ትራምፕ በጦርነቱ ምክንያት በሆርሙዝ ወሽመጥ መተላለፍ ላልቻሉት የንግድ መርከቦቻቸው መንገድ መንገድ እንዲያስከፍቱ “በዓለም ዙሪያ ካሉ አገራት” ቀረበልኝ ባሉት ጥያቄ መሠረት ‘ፕሮጀክት ፍሪደም’ የተባለ ዘመቻ ከሰኞ ጀምሮ እያካሄዱ ነው።በዚህም የአሜሪካ ኃይሎች የመርከቦቹን ደኅንነት ለመጠበቅ ሆርሙዝ ላይ በመሰማራት ጥቃት እንዳይደርስባቸው ጥበቃ እንደሚያደርጉ ተገልጿል። ነገር ግን ኢራን ይህንን የአሜሪካ እርምጃ በመቃወም የአሜሪካ ባሕር ኃይል መርከቦችን እንደምትመታ እየዛተች ነው።ያጋሩ, ትራምፕ ኢራን የአሜሪካ መርከቦችን ካጠቃች “ከምድረ ገጽ ትጠፋለች” ሲሉ ዛቱ
  5. ከ 4 ሰአት በፊትአሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሳለች ሲሉ የኢራን ከፍተኛ ተደራዳሪ ገለጹየኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ ጋሊባፍየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ ጋሊባፍየኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ አሜሪካ በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ላይ ያለውን የመርከብ እንቅስቃሴ እና የኢነርጂ ደኅንነት አደጋ ላይ ጥላለች ሲሉ ገለጹ።ባለፈው ወር ከአሜሪካ ጋር በተደረገው ንግግር ወቅት ከፍተኛ ተደራዳሪ የነበሩት የአሜሪካ አፈ ጉባዔው መሐመድ ባጊር ጋሊባፍ ዛሬ ጠዋት በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አሜሪካን “የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ” እና በባሕር ወሽመጡ ላይ “እገዳ” በመጣል ከሰዋል።ይህንን ያሉት ዶናልድ ትራምፕን “የነፃነት ፕሮጀክት” ሰኞ ዕለት መጀመሩን ከገለጹ በኋላ ነው። “አሁን ያለው ሁኔታ አይቀጥልም” ያሉ ሲሆን፣ ኢራን “እስካሁን አልጀመረችም” በማለት አፈ ጉባኤው ጽሁፋቸውን ደምድመዋል።ያጋሩ, አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሳለች ሲሉ የኢራን ከፍተኛ ተደራዳሪ ገለጹ
  6. ከ 6 ሰአት በፊትበኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ላይ የደረሰው አዲስ ጉዳት ውስን እንደሆነ የአሜሪካ የስለላ መረጃ አመለከተየኢራን የኒውክሌር ተቋማት ባለፈው ዓመት ሰኔ ላይም በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት ተፈጽሞባቸው ነበርየፎቶው ባለመብት,Maxar Technologiesየምስሉ መግለጫ,የኢራን የኒውክሌር ተቋማት ባለፈው ዓመት ሰኔ ላይም በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት ተፈጽሞባቸው ነበርሁለት ወር ባለፈው ጦርነት የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ላይ የደረሰው አዲስ ጉዳት ውስን በመሆኑ ቴህራን የኒውክሌር የጦር መሣሪያ ለመገንባት የሚያስፈልጋት ጊዜ ከአንድ ዓመት ያልበለጠ መሆኑን የአሜሪካ የስለላ መረጃ ማሳየቱን ሮይተርስ ዘገበ።ዜና ወኪሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ሦስት ምንጮች ጠቅሶ ያወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተው፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የኒውክሌር ቦንብ እንዳትሠራ ለማስቆም ሲሉ የካቲት ላይ የከፈቱት ጦርነት በቴህራን የኒውክሌር ፕሮግራም ላይ ያንን ያህል ለውጥ አላመጣም።አሜሪካ እና እስራኤል ጦርነቱን የጀመሩት መደበኛ ወታደራዊ ዒላማዎችን በማጥቃት ቢሆንም ኋላ ላይ እስራኤል በርከት ያሉ ወሳኝ የኒውክሌር ተቋማትን መትታለች።ይሁን እንጂ እነዚህ ጥቃቶች የኢራን የኒውክሌር መሣሪያ ትታጠቅበታለች ተብሎ የሚታሰበው የጊዜ ሰሌዳ ላይ ጉልህ ለውጥ ባለማምጣታቸው፤ የቴህራንን የኒውክሌር ፕሮግራም ማውደም ወይም ያላትን የበለጸገ ዩራኒየም ክምችት ማስወጣት በአማራጭነት ተቀምጠዋል።እስራኤል እና አሜሪካ ባለፈው ዓመት ሰኔ ላይ ናታንዝ፣ ፎርዶው እና ኢስፋሃን የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጥቃት ፈጽመው ነበር። ሮይተርስ የጠቀሰው የአሜሪካ የስለላ መረጃ እንደሚያሳየው እነዚህ ጥቃቶች ኢራንን የኒውክሌር መሣሪያ ለመታጠቅ የሚያስፈልጋት ጊዜ የገፉት ከዘጠኝ ወር እስከ አንድ ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ብቻ ነው።በባለፈው ዓመት ጥቃት ሥራ ላይ የነበሩት ሦስት የማበልጸጊያ ተቋማት ቢመቱም፤ የተባበሩት መንግሥታት የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ተቋም 440 ኪሎ ግራም የሚደርሰው የኢራን 60 በመቶ የበለጸገ ዩራኒየም የት እንደሚገኝ ማረጋገጥ አልቻለም።ግማሽ ያህሉ በኢስፋሃን የኒውክሌር ምርምር ተቋም የምድር ስር ይገኛል ተብሎ እንደሚታመን ዜና ወኪሉ ጠቅሷል።የአሜሪካ እና ኢራን ባካሄዱት ድርድር ስምምነት ላይ እንዳይደርሱ ካደረጓቸው ጉዳዮች ዋነኛው የቴህራን የኒውክሌር ፕሮግራም ነው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን የኒውክሌር መሣሪያ እንድትታጠቅ እንደማይፈቅዱ ተናግረዋል።የኒውክሌር ፕሮግራሟ ለሰላማዊ ዓላማ የሚውል እንደሆነ የምትገልጸው ኢራን በበኩሏ ዩራኒየም የማበልጸግ መብቷ እውቅና እንዲሰጠው የሚጠይቅ የስምምነት ሃሳብ ማቅረቧ ተዘግቧል።ያጋሩ, በኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ላይ የደረሰው አዲስ ጉዳት ውስን እንደሆነ የአሜሪካ የስለላ መረጃ አመለከተ
  7. ከ 7 ሰአት በፊትአሜሪካ በሰባት የኢራን ፈጣን ጀልባዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀችጀልባ ላይ ተጫኑ የኢራን  ወታደሮችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የነበሩ ሰባት የኢራን “ፈጣን ጀልባዎች” ላይ ጥቃት መፈጸሟን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ።ወሳኙ የባሕር መተላለፊያ በኢራን በመዘጋቱ መውጫ አጥተው የቆዩ መርከቦችን እንደሚያስወጡ የተናገሩት ትራምፕ፤ “ሰባት ትንሽ ጀልባዎችም ወይም እነሱ ‘ፈጣን’ ጀልባ የሚሏቸውን መትተናል። የቀሯቸው እነሱ ብቻ ነበሩ” ብለዋል። የአሜሪካ ጦር እንደገለጸው ጀልባዎቹ ላይ ጥቃት የተፈጸመው ሄሊኮፕተሮችን በመጠቀም ነው።የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዛ (ሴንትኮም) ባወጣው መግለጫ “ዛሬ የንግድ መርከቦች ላይ አደጋ የጣሉትን የኢራንን አነስተኛ ጀልባዎች ለማስወገድ ሲ ሃውክ እና የአሜሪካ ጦር ኤኤች-64 አፓች ሄሊኮፕተሮች ጥቅም ላይ ውለዋል” ብሏል።ፕሬዝዳንቱ ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ ኢራን የደቡብ ኮሪያ መርከብን ጨምሮ ከግጭቱ ጋር “ግንኙነት በሌላቸው አገራት ላይ ተኩሳለች” ሲሉ ከስሰዋል።የደቡብ ኮሪያ መንግሥት ትናንት እንዳስታወቀም ‘ኤችኤምኤም ናሙ’ የተሰኘ የአገሪቱ የጭነት መርከብ ሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ “ጥቃት እንደሆነ በተጠረጠረ” ክስተት ጉዳት ደርሶበታል። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አቅራቢያ ቆሞ የነበረው ይህ መርከብ 24 ሠራተኞችን ይዞ እንደነበር የአገሪቱ መንግሥት ገልጿል። በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ አልተነገረም።ይህንን ጉዳይ የጠቀሱት ፕሬዝዳንት ትራምፕ “ምናልባት ደቡብ ኮሪያ የምትመጣበት እና ተልዕኮውን የምትቀላቀልበት ጊዜ አሁን ነው” ብለዋል።የኢራን መገናኛ ብዙኃን ግን የትራምፕ ተፈጽሟን ያሉትን የጀልባዎች ጥቃት አስተባብለዋል። አንድ ወታደራዊ ምንጭን የጠቀሰው ኢራኑ ታስኒም ዜና ወኪል እንደዘገባው ከሆነ ጥቃት የደረሰባቸው ሁለት የጭነት መርከቦች ናቸው። በዚህም አምስት ንጹኃን ተገድለዋል ብሏል።ጥቃት ተፈጽሟል ከመባሉ አስቀድሞ የአሜሪካ ባሕር ኃይል አውዳሚ መርከብ እና ሁለት የአሜሪካን ባንዲራ የሚያውለበልቡ የንግድ መርከቦች በወሽመጡ ማለፋቸውን ዋሽንግተን አስታውቃ ነበር።ይህንን ገለጻ “ሙሉ በሙሉ ሐሰተኛ” ስትል የጠራቸውን ኢራን በበኩሏ የአሜሪካ የጦር መርከብ ላይ የማስጠንቀቂያ ተኩስ መተኮሷን ገልጻለች፤ የአሜሪካ ጦር ይህንን አስተባብሏል።ይሁን እንጂ ሰኞ ዕለት ‘መርስክ’ የተሰኘው የመርከብ ኩባንያ እንደገለጸው የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ያነገቡ እና ጦርነቱ ከተጀመረበት የካቲት አንስቶ በባሕረ ሰላጤው ቆመው የነበሩ መርከቦቹ በወሽመጡ ማለፋቸውን አስታውቋል።ኩባንያው “በአሜሪካ ወታደራዊ ጥበቃ ስር ሆኖ መርከብ የማስወጣት ዕድል እንደቀረበለት” ገልጿል። “ይህንን ተከትሎም መርከቡ በአሜሪካ ጦር ታጅቦ ከፋርስ ባሕረ ሰላጤ ወጥቷል” ብሏል።ያጋሩ, አሜሪካ በሰባት የኢራን ፈጣን ጀልባዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን አስታወቀች
  8. 4 ግንቦት 2026የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የነዳጅ ኢንዱስትሪ ዞን የድሮን ጥቃት ተፈጸመበትፉጃኢራህ የነዳጅ ኢንዱስትሪ ዞን  መጋቢት ላይም ጥቃት ደርሶበት ነበርየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,ፉጃኢራህ የነዳጅ ኢንዱስትሪ ዞን መጋቢት ላይም ጥቃት ደርሶበት ነበርየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ቁልፍ የነዳጅ ወደብ በሆነው ፉጃኢራህ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሦስት ሰዎች “መጠነኛ ጉዳት” እንደደረሰባቸው የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናገሩ።የኢምሬቶች ትልቁ ወደብ እና የነዳጅ ማከማቻ ስፍራ የሆነው ፉጃኢራህ፤ በኢራን ድሮን ጥቃት ከተፈጸመበት በኋላ ከፍተኛ እሳት መከሰቱን ተገልጿል።በደረሰው ጥቃት የተጎዱት የሕንድ ዜግነት ያላቸው ሦስት ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ተብሏል። የከተማው የመገናኛ ብዙኃን ቢሮ ያወጣው መግለጫ እንደሚያሳየው የደረሰው ጉዳት “መጠነኛ” የሚባል ነው።ፉጃኢራህ የነዳጅ ኢንዱስትሪ ዞን መካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ከሚገኙ ግዙፍ የነዳጅ ማከማቻዎች አንዱ ነው። የተኩስ አቁም ስምምነት ከመደረሱ በፊትም በኢራን ጥቃት ተፈጽሞበት ነበር።ስፍራው መመታቱ የተሰማው፤ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መከላከያ ሚኒስትር ከኢራን የተወነጨፉ ሦስት ሚሳዔሎችን ማክሸፉን ከገለጸ በኋላ ነው። አራተኛው ሚሳዔል ባሕር ላይ እንደወደቀ ተገልጿል።እስካሁን ድረስ ኢራን ስለ ጥቃቱ አስተያየት አልሰጠችም።ያጋሩ, የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የነዳጅ ኢንዱስትሪ ዞን የድሮን ጥቃት ተፈጸመበት
  9. 4 ግንቦት 2026ኢራን መርከቦች በሆርሙዝ በኩል አልፈዋል የሚለው የአሜሪካ ገለጻ “ሙሉ በሙሉ ሐሰት ነው” አለችየኢራን ወታደሮች ጀልባ ላይየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ፤ የአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል መርከቦች ስለማለፋቸው የሰጠው ገለጻ “ፍጹም ውሸት” ነው ሲል አጣጣለ።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ፤ ሁለት የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማን የሚያውለበልቡ የንግድ መርከቦች “በተሳካ ሁኔታ በሆርሙዝ ወሽመጥ ማለፋቸውን” ገልጾ ነበር።በኢራን መገናኛ ብዙኃን የወጣው የአብዮታዊ ዘቡ መግለጫ ግን “በቅርብ ሰዓታት አንድም የንግድ ወይም ነዳጅ ጫኝ መርከብ” በሆርሙዝ ወሽመጥ አላለፈም ብሏል።የአሜሪካን መግለጫ “መሠረተ ቢስ እና ሙሉ በሙሉ ሐሰት” ሲል የጠራው የኢራን አብዮታዊ ዘብ፤ ከባሕር ኃይሉ ትዕዛዝ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ “ከፍተኛ አደጋ እንደሚገጥመው” አስጠንቅቋል።ቢቢሲ ቬሪፋይ የአሜሪካን ገለጻ እውነተኛነት ለማረጋገጥ ጥረት እያደረገ ነው። የባሕር ጉዞ መከታተያ የሆነው ‘ማሪን ትራፊክ’ ድረ ገጽ ከአሜሪካ ገለጻ ጋር ተመሳሳይ የሆነ የመርከብ ጉዞ መደረጉን አያሳይም።ይሁን እንጂ መርከቦች አቅጣጫ ጠቋሚያቸውን አጥፍተው ጉዞ ሊያደርጉ ስለሚችል ትክክለኛ ቦታቸው ሳይገለጽ አልፈው ሊሆን የሚችልበት ዕድል አለ።ያጋሩ, ኢራን መርከቦች በሆርሙዝ በኩል አልፈዋል የሚለው የአሜሪካ ገለጻ “ሙሉ በሙሉ ሐሰት ነው” አለች
  10. 4 ግንቦት 2026የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከኢራን ሚሳዔል እንደተተኮሰባት አስታወቀችየኢራን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከቴህራን በርካታ ጥቃቶች ተፈጽመውባታልየፎቶው ባለመብት,Reutersየምስሉ መግለጫ,የኢራን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በቴህራን በርካታ ጥቃቶች ተፈጽመውባታልየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መከላከያ ሚኒስቴር ከኢራን የተወነጨፉ ሦስት ሚሳዔሎችን ማክሸፉን እና አራተኛው ባሕር ላይ መውደቁን አስታወቀ።መከላከያ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ እንዳሰፈረው፤ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ፍንዳታ የተሰማው በከሸፉት ሚሳዔሎች ምክንያት ነው።ሚኒስቴሩ ይህንን ያለው፤ የአገሪቱ የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ባለሥልጣን ለተወነጨፉ ሚሳዔሎች ምላሽ እየተሰጠ መሆኑን ካስታወቀ በኋላ ነው። ባለሥልጣኑ፤ የአገሪቱ ዜጎች ደኅንነቱ የተጠበቀ ስፍራ ውስጥ እንዲቆዩ አሳስቦ ነበር።እስካሁን ኢራን ስለ ጥቃቱ አስተያየት አልሰጠችም። በአሜሪካ እና እስራኤል ጦርነት የተከፈተባት ኢራን፤ ኤምሬቶችን ጨምሮ የባሕረ ሰላጤው አገራትን በማጥቃት አጸፋ ስትሰጥ ቆይታለች።ከአሜሪካ ጋር ከተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በኋላ ግን ጥቃቶቹ ረግበው ነበር። አሁን ኤምሬቶች ላይ ጥቃት የተፈጸመው አሜሪካ በኢራን በተዘጋው ሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚጓዙ መርከቦችን እንደምታጅብ ካስታወቀች በኋላ ነው።ያጋሩ, የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከኢራን ሚሳዔል እንደተተኮሰባት አስታወቀች
  11. 4 ግንቦት 2026አሜሪካ በኢራን ኃይሎች እና የሚሳዔል ይዞታዎች ላይ እርምጃ ልትወስድ መሆኑ ተነገረየአሜሪካ የባሕር ኃይል ወታደርየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበባሕረ ሰላጤው አካባቢ የተሰማሩት የአሜሪካ ኃይሎች በኢራን ሠራዊት እና ይዞታዎች ላይ እርምጃ እንዲወስዱ መመሪያ እንደተላለፈላቸው ተዘገበ።የአሜሪካ የዜና ድረ ገጽ የሆነው አክሲዮስ አንድ የአገሪቱን ከፍተኛ ባለሥልጣን ጠቅሶ እንደዘገበው በቀጣናው ያሉ የአሜሪካ ኃይሎች በሚወስዱት እርምጃ ዙሪያ የነበረው መመሪያ ተለውጧል።ስማቸው ያልተጠቀሰው ባለሥልጣን ተናገሩት እንደተባለው በባሕረ ሰላጤው የተሰማሩት የአሜሪካ ኃይሎች “የኢራንን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ፈጣን ጀልባዎች ወይም የሚሳዔል ማስወንጨፊያ ቦታዎችን” ዒላማ እንዲያደርጉ ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል።የአሜሪካ ሠራዊት ይህንን እርምጃ እንዲወስድ የታዘዘው በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል በሚያልፉ መርከቦች ላይ ተጨባጭ ስጋት ይፈጽማሉ ብለው ባመኗቸው ዒላማዎች ላይ ነው።የአሜሪካ ሠራዊት እርምጃ የሚወስድባቸው ዒላማዎችን በተመለከተ አዲስ መመሪያ የወጣው አሜሪካ በሆርሙዝ በኩል ለሚተላለፉ መርከቦችን ከለላ እንደምትሰጥ ካሳወቀች በኋላ ነው።በዚህም ሳቢያ በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ ሲሆን፣ ኢራን በአሜሪካ የጦር መርከቦች ላይ የሚሳዔል ጥቃት መፈጸሟን ስታስታውቅ አሜሪካ ደግሞ ዜናውን በማስተባበል መርከቦቿ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ላይ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ገልጻለች።ያጋሩ, አሜሪካ በኢራን ኃይሎች እና የሚሳዔል ይዞታዎች ላይ እርምጃ ልትወስድ መሆኑ ተነገረ
  12. 4 ግንቦት 2026በሆርሙዝ የሚያልፉ መርከቦችን ማጀብ አደጋ እንዳለው የቀድሞ የአሜሪካ ባሕር ኃይል ካፒቴን ተናገሩየሦስት የአሜሪካ ጦር መርከቦች አዛዥ የነበሩት ኬቪን ኤየርበሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚጓዙ መርከቦችን ለማጀብ የሚዘጋጅ ማንኛውም ዕቅድ “ከፍተኛ አደጋ” እንደሚያስከትል የቀድሞ የአሜሪካ ባሕር ኃይል ካፒቴን ለቢቢሲ ተናገሩ።የሦስት የአሜሪካ ጦር መርከቦች አዛዥ የነበሩት ኬቪን ኤየር እንዳስረዱት፤ ዋሽንግተን ልትተገበር ያቀደችው መርከቦችን “ለመምራት እና ለማቀናጀት ወይስ በቀጥታ ወደ ውስጥ ገብቶ የተለመደውን የእጀባ” ተግባር ማስፈጸም የሚለው ግልጽ አይደለም።“በእነዚህ ሁለት ነገሮች መካከል ያለው ልዩነት በምሽት እና በቀን መካከል እንዳለው ልዩነት ነው። በቀጥታ እጀባ ማድረግ እጅግ አደገኛ እና አስቸጋሪ መፍትሔ ነው” ብለዋል።ኢራን አሁንም በርካታ ፀረ መርከብ ባለስቲክ ሚሳዔሎች፣ 1,000 የሚደርሱ ፀረ መርከብ ድሮኖች እና “ሮኬት ሊታጠቁ የሚችሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፈጣን የቅኝት ጀልባዎች” እንዳሏት አንስተዋል።ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሆርሙዝ በኩል ማለፍ ያልቻሉ መርከቦችን እንደሚያስወጡ ከተናገሩ በኋላ የአሜሪካ ባሕር ኃይል አውዳሚ መርከቦች እና የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማን ያነገቡ የንግድ መርከቦች ማለፋቸው ተገልጿል።ይህ ከመሰማቱ አስቀድሞ የኢራን ጦር የአሜሪካ መርከቦች ወደ ወሽመጡ የሚገቡ ከሆነ ጥቃት እንደሚፈጽም ዝቶ ነበር።ያጋሩ, በሆርሙዝ የሚያልፉ መርከቦችን ማጀብ አደጋ እንዳለው የቀድሞ የአሜሪካ ባሕር ኃይል ካፒቴን ተናገሩ
  13. 4 ግንቦት 2026አሜሪካ ሁለት የጦር መርከቦቿ ሆርሙዝን አልፈው ፋርስ ባሕረ ሰላጤ ላይ እየተንቀሳቀሱ ገለጸችየአሜሪካ ጦር መርከብየፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ ጦር ሚሳዔል የታጠቁ ሁለት የባሕር ኃይል አውዳሚ የጦር መርከቦቹ ኢራን እገዳ በጣለችበት ሆርሙዝ ወሽመጥ አልፈው በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ላይ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን አስታወቀ።የአሜሪካን የመካከለኛው ምሥራቅ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች የሚመራው ማዕከላዊ ዕዝ እንደገለጸው፤ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት የተነሳ ማለፊያ ያጡ የንግድ መርከቦችን “እየመሩ ለማውጣት” ላስጀመሩትን ዘመቻ እገዛ እያደረገ ነው።ማዕከላዊ ዕዙ፤ የአሜሪካን ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልቡ ሁለት የንግድ መርከቦች “በተሳካ ሁኔታ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ማለፋቸውንም” ገልጿል። በተሳካ ሁኔታ ወሽመጡን አልፈዋል የተባሉትን መርከቦች ስም ግን አልጠቀሰም።ማዕከላዊ ዕዙ አክሎም “የአሜሪካ ኃይሎች የንግድ መርከቦችን ጉዞ ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት በንቃት እያገዙ ነው” ብሏል።የአሜሪካ ጦር ይህንን ያለው ኢራን ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ ለመግባት የሞከረ የአሜሪካ አውዳሚ የጦር መርከብ ላይ ጥቃት ፈጽሜያለሁ ካለች በኋላ ነው።ማዕከላዊ ዕዙ ባወጣው መግለጫ ተፈጽሟል የተባለውን ጥቃት አስተባብሏል። አንድም የአሜሪካ መርከብ አልተመታም ያለው ማዕከላዊ ዕዙ፤ የአሜሪካ ኃይሎች ዘመቻውን እየደገፉ እና “በኢራን ወደቦች ላይ የተጣለን የጉዞ እገዳ እያስፈጸሙ” መሆኑን ገልጿል።ያጋሩ, አሜሪካ ሁለት የጦር መርከቦቿ ሆርሙዝን አልፈው ፋርስ ባሕረ ሰላጤ ላይ እየተንቀሳቀሱ ገለጸች
  14. 4 ግንቦት 2026ኢራን በአሜሪካ ጦር መርከብ ላይ ጥቃት ፈጸምኩ ካለች በኋላ የነዳጅ ዋጋ ጨመረነዳጅ መቅጃ የያዘ እጅየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየኢራን መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ ለመግባት የሞከረ የአሜሪካ የጦር መርከብ በሁለት ሚሳዔል መመታቱን ከዘገቡ በኋላ የነዳጅ ዋጋ የጎላ ጭማሪ አሳየ።ለዓለም የነዳጅ ንግድ የዋጋ መነሻ የሆነው ብሬንት የአንድ በርሜል የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ዜናው ከተሰማ በኋላ በደቂቃዎች ውስጥ ከአራት ዶላር በላይ ጭማሪ አሳይቶ 114 ዶላር ደርሷል። ይህም በዕለቱ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከአምስት በመቶ በላይ ጭማሪን አስከትሏል።ኢራን በአሜሪካ የጦር መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸሟን ከገለጸች በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ ማስተባበያ ያወጣች ሲሆን፣ ይህንንም ተከትሎም ዋጋው ቅናሽ አሳይቷል።ትናንት ምሽት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሆርሙዝ ወሽመጥ መተላለፊያ አጥተው የቆሙ የጭነት መርከቦችን በማጀብ ከአካባቢው የማስወጣት ዕቅዳቸውን አሳውቀው ነበር። ይህንንም ዕቅድ “ሰብአዊነት ማሳያ” ሲሉ ገልጸውታል።በባሕረ ሰላጤው አካባቢ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ 20 በመቶ የዓለም ነዳጅ አቅርቦትን የሚያጓጉዙ በርካታ መርከቦች ከነጭነታቸው መንቀሳቀስ ሳይችሉ ባሉበት እየተጉላሉ ይገኛሉ።ይህ የአሜሪካ መርከቦች በባሕረ ሰላጤው በኩል እንዲያልፉ የማድረግ ዕቅድ ሌላ ዙር ግጭትን የሚቀሰቅስ ከሆነ በአሁኑ ወቅት በተወሰነ መጠን እያለፈ ያለውን የነዳጅ እና የጋዝ አቅርቦትን በማስቆም የዓለም የነዳጅ ዋጋ የበለጠ እንዲነር ያደርጋል የሚል ስጋት ፈጥሯል።ያጋሩ, ኢራን በአሜሪካ ጦር መርከብ ላይ ጥቃት ፈጸምኩ ካለች በኋላ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ
  15. 4 ግንቦት 2026የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የነበረ ነዳጅ ጫኝ መርከቧ መመታቱን አስታወቀችመርከብ በሆርሙዝ ወሽመጥየፎቶው ባለመብት,Reutersየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ‘አድኖክ’ ከተባለው የመንግሥት የነዳጅ ኩባንያ ጋር ግንኙነት ያለው ነዳጅ ጫኝ መርከቧ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ሲጓዝ ጥቃት እንደተፈጸመበት ገለጸች።የኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በጥቃቱ የተጎዳ ሰው የለም።ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ “በኢራን አብዮታዊ ዘብ” ተፈጽሟል ያለውን ይህንን ጥቃት “የባሕር ውንብድና” ሲል አውግዞታል።የኢራን ጦር “ንግድ መርከቦችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት እየፈጸመ እና የሆርሙዝ ወሽመጥን ለኢኮኖሚ ማስገደጃነት ወይም ለዛቻ መሣሪያነት” እየተጠቀመ ነው ሲልም ወቅሷል።ይህ አይነቱ ጥቃት “በቀጣናው መረጋጋት፣ በሕዝቦቹ እና በዓለም አቀፍ የኤነርጂ ደኅንነት ላይ ቀጥተኛ ስጋት የሚጋርጥ ነው” ሲልም ተቃውሟል።ድርጊቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔን “በግልጽ የጣሰ” እንደሆነ የገለጸችው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፤ ኢራን ጥቃት መፈጸም እንድታቆም ጠይቃለች።”ሁሉንም ጠበኛ ድርጊቶች በአስቸኳይ ለማቆም እንዲሁም የሆርሙዝ ወሽመጥን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ለመክፈት ያላትን ቁርጠኝነት እንድታረጋግጥም” ጥሪ አቅርባለች።ያጋሩ, የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የነበረ ነዳጅ ጫኝ መርከቧ መመታቱን አስታወቀች
  16. 4 ግንቦት 2026ኢራን ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ ሊገባ የነበረን የአሜሪካ የጦር መርከብን በሚሳዔል መምታቷን ገለጸችመርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥየፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን ጦር ወደ ሆርሙዝ ሊገባ የነበረ የአሜሪካ ባሕር ኃይል አውዳሚ የጦር መርከብን በሁለት ሚሳዔል በመምታት ወደ ወሽመጡ እንዳይገባ መከልከሉን ገለጸ።የኢራን መንግሥት መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱን ጦር የሕዝብ ግንኙነት ጠቅሰው ባወጡት ዘገባ፤ “ከእስላማዊ ሪፐብሊክ ባሕር ኃይል በተሰጠው ጠንካራ እና ፈጣን ትዕዛዝ የአሜሪካ እና የጽዮናዊው ጠላት አውዳሚ መርከቦች ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ እንዳይገቡ ተከልክለዋል” ብለዋል።ከፊል ይፋዊ የዜና ወኪል የሆነው ፋርስ፤ የኢራን ባሕር ኃይል ጦር ሠፈር መገኛ በሆነው ጃስክ ወደብ አቅራቢያ አንድ የጦር መርከብ በሁለት ሚሳዔሎች መመታቱን ዘግቧል።የጦር መርከቡ በወሽመጡ ደቡባዊ መግቢያ በኩል ሲቀዝፍ የነበረው “የባሕር ላይ ትራፊክ እና የመርከብ ጉዞ ደኅነትን በመጣስ” እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል።እንደ ፋርስ ዘገባ ከሆነ የአሜሪካው የጦር መርከብ “ለማፈግፈግ እና ከአካባቢው ለመሸሽ ተገድዷል።”አክሲዮስ የተሰኘው የዜና ምንጭ ጋዜጠኛ ያነገጋራቸው አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ግን የጦር መርከቡ በኢራን ሚሳዔሎች ተመትቷል መባሉን አስተባብለዋል።የኢራን ጦር ይህንን ያለው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ጦር በወሳኙ የባሕር ወሽመጥ ላይ ማለፊያ አጥተው የቆዩ መርከቦች ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ እገዛ እንደሚያደርግ ከተናገሩ ከሰዓታት በኋላ ነው።“ፕሮጀክት ፍሪደም” በተባለው በዚህ ዘመቻ ላይ 15 ሺህ ወታደሮች፣ ሚሳዔል ተሸካሚ አውዳሚ መርከቦች እና ከ100 በላይ ተዋጊ አውሮፕላኖች እንደሚሳተፉም ተገልጿል።ይህንን ተከትሎም ኢራን “ለአሜሪካ ዛቻዎች ምላሽ ለመስጠት” ዝግጁ መሆኗን ተናግራለች።ያጋሩ, ኢራን ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ ሊገባ የነበረን የአሜሪካ የጦር መርከብን በሚሳዔል መምታቷን ገለጸች
  17. 4 ግንቦት 2026የዩኬ ባሕር ትራንስፖርት ባለሥልጣናት በሆርሙዝ ወሽመጥ አደገኛ ስጋት መኖሩን አስጠነቀቁበሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የሚያቋርጡ መርከቦችየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየሆርሙዝ ወሽመጥን ለማቋረጥ የሚሞክሩ መርከቦች “በቀጣናው እየተካሄዱ በሚገኙ ወታደራዊ ዘመቻዎች” ምከንያት “አደገኛ የደህንነት ስጋት” እንደሚገጥማቸው የዩኬ የባሕር ትራንስፖርት እና ንግድ ሥራዎች ማዕከል አስጠነቀቀ።የባሕር ትራንስፖርት ባለሥልጣኑ መርከቦች “የፈንጂዎችን አደጋ ወይም ለመጓዝ ባሰቡበት መስመር የሚኖር ሌላ የአደጋ ስጋትን” ከግምት ውስጥ ሊያስገቡ እንደሚገባ ተናግረዋል።በወሽመጡ ውስጥ ማለፍ ወይም በጉዞ መለያ ስፍራው መጓዝ በጣም አደገኛ መሆኑን ባለሥልጣኑ ጨምሮ ገልጿል።ምክንያቱም ያልተገኙ እና እንዲወገዱ ያልተደረጉ ፈንጂዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ወይም ደህንነቱ ያልተጠበቀ መስመር ሊሆን እደሚችል አስጠንቅቋል።የጉዞ መለያ መስመር ማለት በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦችን በሚመለከት እአአ በ1968 የተደረሰ ዓለም አቀፍ ስምምነት ነው።ያጋሩ, የዩኬ ባሕር ትራንስፖርት ባለሥልጣናት በሆርሙዝ ወሽመጥ አደገኛ ስጋት መኖሩን አስጠነቀቁ
  18. 4 ግንቦት 2026ኢራን ‘ለአሜሪካ ዛቻዎች ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ገለጸችኢስማኤል ባጋይየፎቶው ባለመብት,Reutersፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ከ”ሰኞ ጠዋት” ጀምሮ መርከቦችን ማስወጣት እንደሚጀምር መግለጻቸውን አስመልክቶ ኢራን ምላሽ ሰጥታለች።የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወሽመጡ ዙሪያ “ለአሜሪካ ዛቻዎች ምላሽ ለመስጠት” ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል።ሜህር የዜና ወኪል ባጋራው መግለጫ ቃል አቀባዩ ኢስማኤል ባጋይ ኢራን የባህር ወሽመጡ “ጠባቂ እና ተከላካይ” ሆና ትቀጥላለች ብለዋል። “መርከቦች እና የመርከብ ኩባንያዎች ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ከኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ባለስልጣናት ጋር መተባበርን እንደሚጠይቅ በሚገባ ያውቃሉ” ሲሉ አክለዋል።የሕግ የበላይነትን የሚከተሉ አገሮች የአሜሪካን “ሕገወጥ እርምጃዎች” የሚከተሉበት ምንም ምክንያት እንደሌለም ተናግረዋል።ቀደም ሲል የኢራን ማዕከላዊ ዕዝ ኃላፊ “በተለይም ጠበኛው የአሜሪካ ጦርን” ጨምሮ ወደ ባህር ወሽመጡ ለመቅረብ ወይም ለመግባት የሚሞክርን “ማንኛውም የውጭ የጦር ኃይል” እንደሚያጠቃ ተናግረዋል።ያጋሩ, ኢራን ‘ለአሜሪካ ዛቻዎች ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች
  19. 4 ግንቦት 2026ባለፈው ወር በአሜሪካ ጦር የተያዘችው የኢራን መርከብ አባላት ለቴህራን ሊሰጡ ነውባለፈው ወር በአሜሪካ ቁጥጥር ስር የዋለችው የኢራን መርከብ ሃያ ሁለት ሠራተኞች ለፓኪስታን ተላልፈው መሰጠታቸው ተገለጸ።የፓኪስታን መንግሥት “ዛሬ ለኢራን ባለሥልጣናት ይተላለፋሉ” ሲል አስታውቋል።የአሜሪካ ወታደሮች ባለፈው ወር ቱስካ በተሰኘው መርከብ የተቆጣጠሯት ሞተሯን ከመቱ በኋላ ነበር። ኢራን ድርጊቱን “የባህር ላይ ውንብድና” ስትል የጠራችው ሲሆን ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደግሞ መርከቡ “የባህር ኃይላችንን እገዳች ለማለፍ ቢሙክሩም አልተሳካላቸውም” ብለዋል።የመርከቡ ሠራተኞች ወደ አገራቸው መመለሳቸው “በዩናይትድ ስቴትስ የተወሰደ የመተማመን ግንባታ እርምጃ” እንደሆነ ፓኪስታን ገልጻለች።መርከቧ “አስፈላጊው ጥገና ከተደረገለት በኋላ ወደ መጀመሪያዎቹ ባለቤቶቿ ለመመለስ ወደ ፓኪስታን የውሃ አካል ትመለሳለች” ሲል አክሏል።”እነዚህ ተመላሾች በኢራን እና በአሜሪካ ድጋፍ ጋር በመተባበር እየተቀናጁ ነው። መርከበኞቹን ለመመለስ ኢራን እና አሜሪካ ትብብር ማድረጋቸውን የፓኪስታን ባለሥልጣናት ተናግረዋል።”ፓኪስታን እንዲህ ዓይነት መተማመንን የሚገነቡ እርምጃዎችን ትደግፋለች። ለቀጣናው ሰላም እና ደህንነት የሚደረጉ ቀጣይነት ያላቸውን የድርድር እና የዲፕሎማሲ ጥረቶችን ማድረጓንም ትቀጥላለች” ብሏል።ያጋሩ, ባለፈው ወር በአሜሪካ ጦር የተያዘችው የኢራን መርከብ አባላት ለቴህራን ሊሰጡ ነው
  20. 4 ግንቦት 2026የኢራን ጦር አሜሪካ ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የምትገባ ከሆነ ጥቃት እንደሚፈጽም አስጠነቀቀነዳጅ ጫኝ መርከብ በኬሽም ደሴት አቅራቢኣ እየተጓዘየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየኢራን ጦር የአሜሪካ ባሕር ኃይል ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የሚገባ ከሆነ ጥቃት እንደሚፈጽም አስጠነቀቀ።ዶናልድ ትራምፕ በወሽመጡ መንቀሳቀሻ አጥተው የቆሙ መርከቦችን እየመሩ ለማስወጣት መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል።የኢራን ማዕከላዊ ዕዝ ያወጣው መግለጫ “ማንኛውም የውጭ ጦር ኃይል” ወደ ወሽመጡ ለመግባትም ሆነ ለመቅረብ ቢሞክር “በተለይ የጠብ አጫሪዋ የአሜሪካ ጦር” ጥቃት እንፈጽማለን ብሏል።ሜጀር ጄነራል አሊ አብዶላሂ ኢራን “በተደጋጋሚ” ወሽመጡ በጦሯ “ቁጥጥር ስር መሆኑን” እና ለማለፍ የሚፈልግ “በሁሉም ሁኔታዎች ስር” ከቴህራን ጋር መተባባር እንደሚያስለፈልገው መናገራቸውን አስታውሰዋል።የጦሩ መግለጫ በኢራን መገናኛ ብዙኃን በሆነው ኢሪብ ተጋርቷል።እሁድ ዕለት ትራምፕ መርከቦቻቸው በሆርሙዝ ወሽመጥ የቆሙባቸውን አገራት እንደሚያግዙ ተናግረዋል። ይህንንም ተከትሎ የአሜሪካ ባሕር ኃይል ወታደሮቹ እና የጦር አውሮፕላኖቹን ዝግጁ ማድረጉን አስታውቋል።ትራምፕ “ለኢራን፣ ለመካከለኛው ምሥራቅ እና ለዩናይትድ ስቴትስ ደህንነት ሲባል ለአገራት መርከቦቻቸውን እየመራን እገዳ ከተጣለበት የውሃው አካል እንደምናስወጣላቸው ነግረናቸዋል። ስለዚህ በነጻነት ወደሚቀጥለው ጉዳይቸው መሄድ ይችላሉ” ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።ትራምፕ በሆርሙዝ ወሽመጥ ቆመው ያሉት እና አሜሪካ ድጋፍ ልታደርግላቸው መሆኑን የነገረቻቸው የየትኞቹ አገራት መርከቦች እንደሆኑ አላሰወቁም።ያጋሩ, የኢራን ጦር አሜሪካ ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የምትገባ ከሆነ ጥቃት እንደሚፈጽም አስጠነቀቀ