Yidnekachew Kebede ·Follow

♦ሰው በማንነቱ አይቀጣ ፤ ከሁሉም በፊት ሰብአዊነት ይቅደም ፤ ሰብአዊነት ይከበር!

~ የእስረኞች ጥሪ!

አማራዊ ማንነታቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በግፍ እስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ሕክምና የማግኘት መብታቸው ይከበር ፤

ማ/ቤቱ የተቋረጠባቸውን መድኃኒት ሊያቀርብ እና ሕክምናቸውን በሀኪሞች ትዕዛዝ መሰረት ሊያስቀጥል ይገባል!

እነዚህ እና መሰል የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች የአገዛዙ ፀረ አማራ ተልዕኮ አስፈጻሚ በሆኑ እና ኃላፊነት በጎደላቸው መርማሪዎች የደረሰባቸውን ድብደባ ተከትሎ በገጠማቸው የጤና ችግር እና ፍትህ በጎደለው እስር የተነሳ ከፍ ያለ ዋጋ እየከፈሉ ከሚገኙት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

የገጠማቸውን ፈርጀ ብዙ የጤና ችግር ተከትሎ ከብዙ እንግልት እና ልመና በኋላ በፍ/ቤት ትዕዛዝ ሕክምና አግኝተው በሆስፒታል ደረጃ ክትትል እየተደረገላቸው ነበር ፤ የማይቋረጥ መድኃኒት ታዞላቸው እየወሰዱም ነበር።

ከቂሊንጦ ወደ አባ ሳሙኤል ማ/ቤት ተወስደው የሕክምና ክትትላቸው ከተቋረጠባቸው እና በተለያየ ሕመም ከሚሰቃዩት በርካታ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች መካከል ፦

1. እንዳሰኘው ክበብ ፣

2. ሸጋው ምሀባው ፣

3. ስንታየሁ ንጋቱ ፣

4. አማረ መለሰ ፣

5. ቸርነት እሸቱ ፣

6. ላቀው ሞገስ ፣

7. ወርቁ ገብሬ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

እነዚህ ተከሳሾች ፦

1. በከፍተኛ ሕመም እየተሰቃዩ መሆናቸው እየታወቀ ፣

2. የሆስፒታል ክትትል ያላቸውና

3. የቤተሰብ ቅርብ ክትትል የሚያስፈልጋቸው መሆኑ እየታወቀ ከቂሊንጦ ማ/ቤት ለእስረኞች ፣ ለቤተሰብም ሆነ ለጠበቆች ምቹ ወዳልሆነው አባ ሳሙኤል ሊወሰዱ አይገባቸውም ነበር።

ከተወሰዱ በኋላም ፦

የታዘዘላቸው መድኃኒት ሊቀርብላቸው እና

የሕክምና ክትትሉ ሊቀጥል ይገባው ነበር።

ውሃን ጨምሮ በቂ ምግብ በሌለበት እና በሕግ ተጠያቂ መሆኑ ቢቀር እንደ ሰው የሞራል ተጠያቂነት ስለማይቀር ለሕመምተኛ በማይሆን ፎቅ ላይ ሊታሰሩ አይገባም ነበር።

6. መሪጌታ በላይ አዳሙ፣

7. ታደሰ መለሰ እና

8. ሻንበል አድማሱ አለሙ ከእድሜያቸው እና ካለባቸው የጤንነት ችግር አንጻር በተሻለ እና ቤተሰብ ሊደግፋቸው በሚገባ ቦታ ሊታሰሩ ሲገባ ወደ አባ ሳሙኤል ተወስደው ለተጨማሪ እንግልት መዳረጋቸው ሰብአዊነት እና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር በመሆኑ ሊስተካከል ይገባዋል።

አሁንም በእነዚህ ሕመምተኞች ላይ ያለውን የሕክምና ችግር ቸል በማለት ኃላፊነትን አለመወጣት ተጠያቂነትን አይቀሬ ያደርገዋል።

ወደነበሩበት ቂሊንጦ ሊመለሱና የሕክምና እና የቤተሰብ የቅርብ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የቂሊንጦ ማ/ቤት ኃላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን ።

በቂሊንጦ ማ/ቤት በግፍ እስር ላይ እንዳለ በሕክምና ጉድለት የተነሳ እንደሞተው ወንድማችን እንደ አቶ አባይነህ አለማየሁ እንዳናጣቸው ስለምንሰጋ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው እንፈልጋለን!

የአማራ ብሎም የሰብአዊነት ጉዳይ ያገባናል የምትሉ የሁሉንም አካላት ትኩረት ከምንጊዜም በላይ እንሻለን!

ሕክምና ማግኘት አገር እና አለም አቀፍ ድንጋጌዎች የሚደግፉት የሰብአዊ መብት ጉዳይ ነው!

ከሁሉም በፊት ሰብአዊነት ይቅደም ፤ ሰብአዊነት ይከበር!

አማራነት ወንጀል አይደለም!

ዜጋን በማንነት እየለዩ ማጥቃት ይቁም!

ፍትህ ለሁሉም!

©አውሎግሶን

See less