Ethiopia Election ·Follow

ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ለ64 የፓርላማ መቀመጫዎች ያለ ተፎካካሪ ብቻውን ለምርጫ ቀረበ፤ ሌሎች 10 ዕጩዎችም በግል እና በአምስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስር ለብቻቸው ይወዳደራሉ

ግንቦት 24 በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ በአምስት ክልሎች በሚገኙ 64 የምርጫ ክልሎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቻውን እንደሚወዳደር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰነድ አመለከተ።

“ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው ይፋዊ ሰነድ እንደሚያሳየው፣ ገዢው ፓርቲ ተቀናቃኝ የሌለባቸው አብዛኞቹ (65ቱ) የምርጫ ክልሎች በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የሚገኙ ናቸው፤ ከነዚህም ውስጥ በ56ቱ የብልፅግና ፓርቲ ዕጩዎች ያለተቀናቃኝ ይወዳደራሉ።

እንደ ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ ባሉ ከተሞች በርካታ ተፎካካሪዎች ቢመዘገቡም፣ በኦሮሚያ ክልል ብቸኛ ተወዳዳሪ ከተመዘገበባቸው 49 የምርጫ ክልሎች ውስጥ በ46ቱ ብልፅግና ፓርቲ ያለ ምንም ተወዳዳሪ ቀርቧል። በአንጻሩ የቀድሞው የኦነግ ከፍተኛ አመራር አቶ ቀጄላ መርዳሳ እና አቶ አራርሶ ቢቂላ በኦሮሚያ ክልል በተመረጡ የምርጫ ክልሎች በግል ዕጩነት ያለ ተቀናቃኝ ብቻቸውን እንደሚወዳደሩ በሰነዱ ተመልክቷል።

በአማራ፣ በሶማሌ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎችም ጥቂት የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩዎች (እንደ ኢዜማ፣ አብን፣ ነእፓ እና ትብብር) ያለ ተፎካካሪ የሚወዳደሩባቸው የምርጫ ክልሎች መኖራቸውን “ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ታዝባለች። ገዢው ፓርቲ በ6ኛው ዙር ምርጫ በ112 የምርጫ ክልሎች ብቻውን መወዳደሩ የሚታወስ ሲሆን፣ በዘንድሮው ምርጫ ግን ይህ ቁጥር ወደ 64 ዝቅ ብሏል። [ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ 👉https://ethioelections.com/2026/05/17591/

#ምርጫ2018#EthiopiaElection

See less