
May 8, 2026

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ክትትል ባደረገባቸው 1,007 የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ በምርጫ አስፈፃሚዎች ላይ የደረሰ “ምንም ዓይነት ድብደባ፣ ግድያም ሆነ ስወራ” አለመፈጸሙን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ከ “ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ከምርጫ አስፈፃሚዎች በተጨማሪ አንድም የፖለቲካ ፓርቲ እንዲህ ዓይነት አቤቱታ ለኮሚሽኑ አለማቅረቡን ትናንት ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው የሪፖርት ይፋ ማድረጊያ መርሐ ግብር ላይ ገልጸዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላቶቻቸውና ዕጩዎቻቸው በቁጥጥር ሥር እንደሚውሉና ቅስቀሳ ለማድረግ ተግዳሮት እንደሚገጥማቸው በተለያዩ ጊዜያት ቅሬታ ሲያሰሙ ቢቆዩም፣ ኮሚሽነር ብርሃኑ ግን “እርግጠኛ ሆኜ ነው የምናገረው፤ አንድም ዕጩም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲ አቤቱታ ያቀረበልን የለም” ብለዋል። አክለውም “ይህንን ከፖለቲካ ፓርቲዎችም ማረጋገጥ ትችላላችሁ” ሲሉ ተናግረዋል።
Post
Translated from Amharic
I announced my candidacy for the Ethiopian House of Peoples’
Representatives from the election!
Detailshttps://shorturl.at/LNhMy
#Election2018 #EthiopiaElection
Rate this translation:

· 528Views
ኢሰመኮ ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ባደረገው የቅድመ ምርጫ ክትትል፣ የመራጮች እና የዕጩዎች ምዝገባ ሂደት “በመልካም ጎኑ የሚታይ” ቢሆንም የተለያዩ ጉድለቶች መታየታቸውን ይፋ አድርጓል። የኮሚሽኑ የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ዳይሬክተር መቅደስ አመኑ እንደገለጹት፣ የምርጫ ጣቢያዎች በሕግ ክልክል በሆኑ በመከላከያና በፖሊስ ጣቢያዎች እንዲሁም በመጠጥ ቤቶች ውስጥ መቋቋማቸው ተረጋግጧል። በተጨማሪም በጋምቤላ ክልል ላሬ የምርጫ ጣቢያ የቁሳቁስ መዘግየት በማጋጠሙ ምዝገባው የተከናወነው ለሦስት ቀናት ብቻ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ይህንን የኮሚሽኑን ወቀሳ በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ነዋይ ምላሽ ሰጥተዋል። አቶ ተስፋዬ “የፖሊስ አባላት ልብስ የሚቀይሩበት እና የሚያርፉበት ቦታ” የተቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን ቢያምኑም፣ “ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ” የተቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች የሉም በሚል ተከራክረዋል።
Post
Translated from Amharic
The Network of Ethiopian Civil Society Organizations for Elections, in its
observation report released on Election Day, has shed light on the
successes and major challenges observed in the voter registration
process.
Details https://shorturl.at/XAl46
Rate this translation:

· 835Views
ሪፖርቱ አክሎም በሚዛን አማን ከተማ ገዢው ፓርቲ ዜጎች “ስብሰባ እና ሰልፎች ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ” ማስገደዱንና ተቃዋሚ ፓርቲዎችም የቅስቀሳ ተግዳሮት እንደገጠማቸው አመልክቷል። ኮሚሽኑ ሂደቱን ለመከታተል 55 የክትትል ቡድኖችን ያሰማራ ሲሆን፣ በዋናው መሥሪያ ቤት ቅሬታዎችን በደረጃ ለይቶ መፍትሔ የሚያሰጥ የሁኔታዎች መከታተያ ክፍል መገንባቱን አስታውቋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ የጸጥታ ቢሮ ተወካዮች በበኩላቸው፣ ምርጫው በሰላም እንዲከናወን የጸጥታ ኃይሉ በትጋት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ተወካይ ዘሪሁን ድጉማ በክልሉ ምርጫውን ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ “ፀረ ሰላም ኃይሎች” መኖራቸውን ጠቅሰው፣ ኮማንድ ፖስት በማቋቋም እና ኅብረተሰቡን በማንቃት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስረድተዋል።
ከአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ተወከለው የተገኙት አቶ ፍቃዱ አቶምሳም በበኩላቸው “በከተማችን ከአንድ ሺሕ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ። በነዚህ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ምንም ዓይነት ችግር እንዳይፈጠር ከከፍተኛ አመራር ጀምሮ በትጋት ተሠርቷል” ብለዋል።
ኮሚሽኑ በበኩሉ የጸጥታ አካላት በምርጫ ሂደት ላይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡና በሕግ ከተከለከሉ ቦታዎች ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲሠሩ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል። በተጨማሪም ለመንቀሳቀስ ነፃነት ከሚገድቡ ድርጊቶች እንዲሁም በሕግ ከተከለከሉ ቦታዎች ርቀትን ጠብቆ መሥራት ያስፈልጋል ሲል ኮሚሽኑ መክሯል። [ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]
