እስቲበል አለሙ ዘሪሁን ·Follow
ቀን፡ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
ወቅታዊ መግለጫ
እርምጃ ወስደናል
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሂደት ያለ ምንም የፀጥታ ስጋት እንዲጠናቀቅና ሰላማዊ ድባብ እንዲሰፍን ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሰላም ካውንስልና ከዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ጋር ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል። ንቅናቄያችን ይህንን ቃል በተግባር ለመተርጎም በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።
ይሁን እንጂ፣ ሚያዚያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣነው ግልጽ መመሪያ እና ማስጠንቀቂያ ላይ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች በመጣስ፣ በምርጫ አስፈፃሚዎች ላይ ጥቃት በማድረስ እና የምርጫውን ሂደት በማደናቀፍ ተግባር ላይ የተሰማሩ ጥቂት አባላት ላይ ድርጅታዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በዚሁ መሠረት ንቅናቄያችን የሚከተሉትን የማስተካከያ እርምጃዎች መውሰዱን ለሕዝባችንና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይፋ ያደርጋል፡-
የሞት ቅጣት፡- የምርጫ አስፈፃሚ አባላትን አስረው ገንዘብ የተቀበሉ እና አካላዊ ቅጣት የፈፀሙ በቀጥታ በፈጸሙና ትዕዛዝ ባስተላለፉ 3 (ሦስት) የንቅናቄያችን አባላት ላይ በድርጅቱ ወታደራዊ ደንብ መሠረት የሞት ቅጣት ተፈፅሞባቸዋል።
*የእስራትና የገንዘብ ቅጣት፡- የምርጫ ሂደቱን ለማደናቀፍ በተለያዩ ተግባራት ላይ ተሳትፈው የተገኙ 22 (ሀያ ሁለት) አባላት እንደየጥፋታቸው ክብደት በእስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ተወስኗል።
ንቅናቄያችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብና ለሰላም ካውንስሉ የገባውን ቃል ለማክበርና ድርጅታችን በሽብርተኝነት ስም እንዳይፈረጅ ያለውን ፅኑ አቋም ለማሳየት ነው።
በትጥቅ ትግል ውስጥ ብንሆንም፣ ትግላችን ስርአት ያለውና የንፁሃንን ደህንነት የሚጠብቅ መሆኑን በተግባር ለማረጋገጥ ነው።
ትግላችን የአማራን ሕዝብ ህልውና ለማስከበር እንጂ በምርጫ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉ ንፁሃን ወገኖቻችንን ለማጥቃት ባለመሆኑ፣ የትግሉን ስም የሚያጎድፉ አባላትን መታገስ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።
በመጨረሻም፣ ንቅናቄያችን ማንኛውም የምርጫ ሂደት በእኛ ምክንያት እንዳይደናቀፍ የጀመረውን ጥብቅ ቁጥጥርና እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እያሳወቅን፤ መላው የአፋብን አመራርና አባላት ከመመሪያ ውጪ ከሚደረጉ ማናቸውም ድርጊቶች እንዲቆጠቡ በድጋሚ እናሳስባለን።
ድል ለአማራ ህዝብ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)
See less

