አሜሪካ ላቀረበችው የሰላም ዕቅድ የኢራንን ምላሽ እየጠበቀች ሳለ ለፓኪስታን የተፈጥሮ ጋዝ የጫነች የኳታር መርከብ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ማለፏ ተገለፀ። አል ካራይቲያት የተባለችው ይህች መርከብ ከኳታር ራስ ላደፋን ተነስታ ወደ ፓኪስታን ቃሲም ወደብ እያመራች መሆኗ ተገልጿል። የኢራን ጦርነት ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ የኳታር መርከብ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ሲያልፍ ይህ የመጀመርያው ነው።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ 3 ሰአት በፊትለፓኪስታን ጋዝ የጫነች የኳታር መርከብ በሆርሙዝ በኩል ማለፏ ተገለጸየሆርሙዝ ወሽመጥየፎቶው ባለመብት,Reutersአሜሪካ ላቀረበችው የሰላም ዕቅድ የኢራንን ምላሽ እየጠበቀች ሳለ ለፓኪስታን የተፈጥሮ ጋዝ የጫነች የኳታር መርከብ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ማለፏ ተገለፀ።አል ካራይቲያት የተባለችው ይህች መርከብ ከኳታር ራስ ላደፋን ተነስታ ወደ ፓኪስታን ቃሲም ወደብ እያመራች መሆኗ ተገልጿል።የኢራን ጦርነት ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ የኳታር መርከብ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ሲያልፍ ይህ የመጀመርያው ነው።ኳታር የተፈጥሮ ጋዙን አሜሪካን እና ኢራንን በማሸማገል ውስጥ ላለችው ለፓኪስታን የሸጠችው የሁለቱ አገራት መንግሥታት ያደረጉትን ስምምነት ተከትሎ ነው ተብሏል።ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ኢራን የመርከቧን ጉዞ የፈቀደችው በፓኪስታን እና ኳታር ረገድ ያለውን መተማመን ለማጠንከር ነው ብለዋል።ለሮይተርስ የዜና ወኪል አስተየየታቸውን የሰጡ ምንጮች በጋዝ እጥረት ክፉኛ የተጎዳችው ፓኪስታን፣ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የተወሰነ የተፈጥሮ ጋዝ የጫኑ መርከቦች እንዲያልፉ ንግግር እያደረገች ትገኛለች።ኳታር ለፓኪስታን የተፈጥሮ ጋዝ ከሚያቀርቡ አገራት መካከል ቀዳሚዋ ስትሆን ኢራን ደግሞ በወሽመጡ በኩል መርከቡ እንዲያልፍ ለሁለቱ አገራት መንግሥታት ይሁንታዋን መስጠቷ ተገልጿል።የናካሊት የመርከብ ትራንስፖርት ድርጅት ንብረት የሆነችው መርከቧ፣ የማርሻል ደሴቶችን ባንዲራ የምታውለበልብ ሲሆን 211,986 ኪዩቢክ ሜትር ነዳጅ የመጫን አቅም አላት።ከአንድ ወር በፊት የኢራን አብዮታዊ ዘብ አል ዳዬን እና ራሼዳ የተሰኙ ሁለት የኳታር ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን እንዳያልፉ ከልክሏል።ያጋሩ, ለፓኪስታን ጋዝ የጫነች የኳታር መርከብ በሆርሙዝ በኩል ማለፏ ተገለጸ
  2. ከ 4 ሰአት በፊትዩኬ የጦር መርከቧን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ላከችኤችኤምኤስ ድራጎን የአየር መቃወሚያ መሣሪያ የጫነ መርከብየፎቶው ባለመብት,REUTERSብሪታኒያ ቅዳሜ ዕለት ኤችኤምኤስ ድራገን የተሰኘው የጦር መርከቧን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ላከች። የጦር መርከቡ ሁኔታዎች የሚፈቅዱ ከሆነ በርካታ አገራት ይሳተፉበታል ተብሎ በሚጠበቀው የሆርሙዝ ወሽመጥን ማስከፈት ላይ ሊሳተፍ ይችላል ተብሏል።ኤችኤምኤስ ድራጎን የአየር መቃወሚያ መሣሪያ የጫነ መርከብ ሲሆን የኢራን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ በመጋቢት ወር በምሥራቅ ሜዲትራኒያን ወደምትገኘው ቆጵሮስ ተሰማርቶ ነበር።ዩኬ የጦር መርከቧን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የላከችው ፈረንሳይ የባሕር ኃይሏን ወደ ደቡባዊ ቀይባሕር ለመላክ መወሰኗን ተከትሎ ነው።ሁለቱ አገራት የንግድ መስመሩን በጋራ ለመከላከል ባዘጋጁት የመከላከያ ዕቅድ ላይ እየሰሩ ነው።የብሪታንያየመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ብሪታንያ የጦር መርከቧን አስቀድማ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ማስጠጋቷ አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት ወሽመጡን ከአጋሮቿ ጋር በመሆን ለመከላከል እንደሚያግዝ ተናግረዋል።ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን ለ10 ሳምንት ከዘለቀው ጦርነት ለመውጣት እየተቃረቡ ባለበት በአሁኑ ወቅት ፈረንሳይ እና ብሪታንያ ሁኔታው ​​ከተረጋጋ በኋላ በወሽመጡ ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ የመርከቦች እንቅስቃሴ እንዲኖር መሠረት ለመጣል ዕቅድ እያዘጋጁ ነውዕቅዱ ከኢራን ጋር ቅንጅት ያስፈልገዋል የተባለ ሲሆን በርካታ አገራት ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆናቸውን አሳውቀዋል።የብሪታንያ ባሕር ኃይል በተለያዩ ስፍራዎች ላይ በመመደቡ የተነሳ ተመናምኗል።ከዚህም በተጨማሪ የባሕር ኃይል አባላት ቁጥር አነስተኛ ሲሆኑ መርከቦቿ ከመተካታቸው በፊት የአገልግሎት ጊዜያቸው እያበቃ መሆኑ ተገልጿል።ያጋሩ, ዩኬ የጦር መርከቧን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ላከች
  3. ከ 6 ሰአት በፊትእስራኤል በኢራን ለምታካሄደው ጦርነት ኢራቅ ውስጥ ምስጢራዊ የጦር ሠፈር ገንብታ እንደነበር ዎል ስትሪት ጆርናል ዘገበየእስራኤል ወታደርየፎቶው ባለመብት,Reutersእስራኤልበኢራን ላይ የምታደርገውን የአየር ድብደባ ለመደገፍበኢራቅ በረሃ ውስጥ ምስጢራዊ ወታደራዊ ሰፈር አቋቁማለች ሲል ዎል ስትሪት ጆርናል ዘገበ።ጋዜጣው ጉዳዩን የሚያውቁ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እና ሌሎች ምንጮችን ጠቅሶ የጦር ሠፈሩ መኖሩን ያወቁ የኢራቅ ወታደሮች ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሟን ጨምሮ ዘግቧል።እስራኤል ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በአሜሪካ ዕውቅና በጦር ሰፈሩ ልዩ ኃይሎችን የሚይዝ እና ለአየር ኃይሏ ቁሳቁስ የሚያቀርብ ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል አድርጋ ማደራጀቷን ተጠቅሷል።የጦር ሠፈሩ ከዚህ በተጨማሪም በጦርነቱ የሚከሰከሱ የእስራኤል አብራሪዎችን ለመፈለግ እና ለመርዳት የሚችሉ ቡድኖችን ማካተቷን ዎል ስትሪት ጆርናል ዘግቧል።ሮይተርስ የዜና ወኪል የዘገባውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ለእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም።ባለፈው መጋቢት ወር በአካባቢው የሚገኙ የበግ እረኞች ሂሊኮፕተርን ጨምሮ ያልተለመደ ወታደራዊ እንቅስቃሴ መኖሩን ማስተዋላቸውን የኢራን ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ዘግቦ ነበር።ከዚህ ዘገባ በኋላ የኢራን ወታደሮች ምርመራ እንዲያደርጉ የተላኩ ሲሆን የእስራኤል ኃይሎች የአየር ድብደባ በመፈጸም ወደ ጦር ሰፈሩ እንዳይቀርቡ መከላከላቸውን ጋዜጣው ጠቅሷል።ጋዜጣው መጋቢት ወር መጨረሻ ላይ ኢራቅ ለመንግሥታቱ ድርጅት የውጭ ኃይሎች፣ በተለይ አሜሪካን በመጥቀስ፣ የአየር ድብደባ መፈጸማቸውን ገልጻ ቅሬታዋን አቅርባለች ብሏል።ዎል ስትሪት ጆርናል ያነጋገራቸው ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ግለሰብ በጥቃቱ ላይ አሜሪካ አለመሳተፏን አረጋግጠዋል።ያጋሩ, እስራኤል በኢራን ለምታካሄደው ጦርነት ኢራቅ ውስጥ ምስጢራዊ የጦር ሠፈር ገንብታ እንደነበር ዎል ስትሪት ጆርናል ዘገበ
  4. ከ 7 ሰአት በፊትኢራን በዓለም ዋንጫ ላይ ለሚኖራት ተሳትፎ ዋስትና ጠየቀችሜክሲኮ ከአሜሪካ እና ካናዳ ጋር በመሆን ከሰኔ 4 እስከ ሐምሌ 12 2018 ዓ.ም. ድረስ የሚካሄደውን የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድርን ታስተናግዳለች።የፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየምስሉ መግለጫ,ሜክሲኮ ከአሜሪካ እና ካናዳ ጋር በመሆን ከሰኔ 4 እስከ ሐምሌ 12 2018 ዓ.ም. ድረስ የሚካሄደውን የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ውድድርን ታስተናግዳለች።ኢራን በዓለም ዋንጫ ላይ እንደምትሳፍ ገልጻ ነገር ግን ከፊፋ እና ጨዋታውን ከሚያስተናግዱ አገራት ዋስትና እንደምትፈልግ አስታወቀች።የኢራን እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዓለም ዋንጫ ላይ “ከምናምንብት፣ ከባሕላችን እና ከቁርጠንነታችን ሳናፈገፍግ” እንሳተፋለን ሲሉ አረጋግጠው፣ አዘጋጅ አገራት “ስጋታችንን ከግምት ውስጥ እንዲያስገቡልን እንፈልጋለን” ብለዋል።የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ መሟላት አለባቸው ያላቸውን ነገሮች ያቀረበው ፕሬዚዳንቱ መሃዲ ታጅ ባለፈው ወር ካናዳ በተካሄደው የፊፋ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ሲጠይቁ ቪዛ በመከልከላቸው ነው።ታጅ አገራቸው በዓለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ መሟላት አለባቸው ያሏቸውን ባለ አስር ነጥብ ቅድመ ሁኔታዎችን ለፊፋ ማቅረቧን ተናግረዋል።የዓለም ዋንጫ በሜክሲኮ በካናዳ እና በዩናይትድ ስቴትስ አዘጋጅነት ከሰኔ 4 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ይካሄዳል።ቅዳሜ ዕለት በመግለጫው ላይ ከሰፈሩት ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ሁሉም በእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ወታደራዊ ስልጠና ያጠናቀቁትን ጨምሮ ከቡድኑ ጋር የሚጓዙ አሰልጣኞች፣ ተጫዋቾች እና ባለሥልጣናት ቪዛ እንዲሰጣቸው የሚጠይቅ ነው።የኢራን አብዮታዊ ዘብ በካናዳ እና አሜሪካ አሸባሪ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀ ሲሆን፣ መሃዲ ታጂ ወደ ካናዳ መግቢያ ቪዛ የተከለከሉት ከወታደራዊው ተቋሙ ጋር ባላቸው ግንኙነት ነው ተብሏል።ኢራን ለእግር ኳስ ቡድኗ፣ ለባንዲራዋ እንዲሁም ለብሔራዊ መዝሙሯ ተገቢው ክብር አንዲሰጥ እንዲሁም በአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ ሆቴሎች እና ስታዲየሞች ጥበቃ እንዲጠናከርላት ጠይቃለች።የተወሰኑት የኢራን ጥያቄዎች ፊፋ በቀላሉ እንዲሟሉ ሊያደርጋቸው የሚችላቸው ናቸው።ነገር ግን ከቪዛ፣ የድንበር ቁጥጥር እና ደህንነት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ከፊፋ ይልቅ የአገራቱ ሕግ ስር የሚወድቁ ናቸው።የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የኢራን የእግር ኳስ ቡድን መትቶ በዓለም ዋንጫ ላይ ቢካፈል ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረው ነበር።ነገር ግን ከአብዮታዊ ዘቡ ጋር ግንኙነት ያላቸው አባላት ክልከላ እንደሚገጥማቸው አስጠንቅቀዋል።ያጋሩ, ኢራን በዓለም ዋንጫ ላይ ለሚኖራት ተሳትፎ ዋስትና ጠየቀች
  5. ከ 8 ሰአት በፊትበእስራኤል ጥቃት 39 ሰዎች መገደላቸውን ሊባኖስ አስታወቀችየእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሊባኖስ ሳክሳኪዬህ ከተማ በፈጸመው ጥቃት አንድ ሕጻንን ጨምሮ ቢያንስ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የጤና ሚኒስቴሩ ይፋ አድርጓል።የፎቶው ባለመብት,Reutersየእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ቅዳሜ ዕለት በፈጸመው ከባድ ድብደባ 39 ሰዎች መገደላቸውን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሊባኖስ ሳክሳኪዬህ ከተማ በፈጸመው ጥቃት አንድ ሕጻንን ጨምሮ ቢያንስ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ሚኒስቴሩ ይፋ አድርጓል።እስራኤል በአካባቢው የሚገኘውን ታጣቂ ቡድን፣ ሄዝቦላህን ዒላማ ማድረጓን ገልጻ “ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ መረጃው ደርሶኛል” ብላለች።በእስራኤል እና በሊባኖስ መካከል ከሦስት ሳምንት በፊት የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረስም ከሄዝቦላህ ጋር የሚደረገው ውጊያ ግን እንደቀጠለ ነው።አብዛኛው የእስራኤል የአየር ድብደባዎች ዒላማ የሚያደርጉት “የሄዝቦላህ መሠረተ ልማቶች እና ታጣቂዎች ይገኙበታል” ተብሎ በሚታመነው ደቡባዊ ሊባኖስን ነው።ቅዳሜ ዕለት የሊባኖስ ብሔራዊ የዜና ወኪል እስራኤል በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል ሳክሳኪዬህ ከተማን ጨምሮ ድብደባ መፈጸሟን ዘግቧልየጤና ሚኒስትሩ እንዳለው በጥቃቱ “በመጀመርያ አንድ ሕጻንን ጀምሮ ሰባት ሰዎች ሲገደሉ፣ ሦስት ሕጻናትን ጨምሮ 15 ሰዎች ደግሞ ተጎድተዋል” ብሏል።የእስራኤል ጦር በአካባቢው “ሽብርተኛው ሄዝቦላህ ለወታደራዊ ዓላማ የሚጠቀምባቸው ሕንጻዎች” መመታታቸውን አስታውቋል።“ከጥቃቱ አስቀድሞ በተቻለ መጠን በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰወን ጉዳት ለመቀነስ ዒላማቸውን ለይተው የሚመቱ መሣሪያዎችን እና የአየር ላይ ቅኝትን ማድረግ ጨምሮ የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል” ብሏል።አክሎም ጉዳዩ ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር ደግሞ በናባቴህ በተፈጸመ ሌላ የአየር ድብደባ “የሶሪያ ዜግነት ያለው ግለሰብ እና የ12 ዓመት ልጁ” በሞተር ሳይክል ሲጓዙ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው አስታውቋል።“የመጀመርያው ጥቃት ከተፈጸመበት አካባቢ እየሸሹ ሳለ ሁለተኛ የድሮን ጥቃት ተፈጽሟል።”ሁለተኛው ጥቃት አባትየውን መግደሉን የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ “ሦስተኛ የድሮን ጥቃት በቀጥታ” ልጅቷን ዒላማ ማድረጉን አብራርቷል።ልጅቷ ሕይወት አድን የሆነ ቀዶ ሕክምና እየተደረገላት መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል።ሄዝቦላህ በበኩሉ በሰሜን እስራኤል የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ሲያስታውቅ የእስራኤል ጦር በበኩሉ ሦስት ወታደሮቹ እንደተጎዱበት ይፋ አድርጓል።ያጋሩ, በእስራኤል ጥቃት 39 ሰዎች መገደላቸውን ሊባኖስ አስታወቀች
  6. 9 ግንቦት 2026ኢራን ከሰሞኑ አሜሪካ የፈጸመችው ጥቃት “ለዲፕሎማሲ ያላትን ፍላጎት ጥርጣሬ” ውስጥ ከትቷል አለችየኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesአሜሪካ እና ኢራን አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ ጥቃት በፈጸሙ በኋላ በትናትናው ዕለት ከቱርክ አቻቸው ጋር የተነጋገሩት የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፤ ዋሽንግተን “የተኩስ አቁም ስምምነቱን በተደጋጋሚ መጣሷ” ለዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ያላትን “ቁርጠኝነት ጥርጣሬ ውስጥ መክተቱን” ተናገሩ።አራግቺ፤ ከቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ጋር ያደረጉት የስልክ ንግግር በዋነኛነት ትኩረት ያደረገው ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እንደነበር ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።መግለጫው እንደሚያስረዳው፤ የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሜሪካ ከሰሞኑ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ አካባቢ “የጀብድ እንቅስቃሴ” ማድረጓን ጠቅሰዋል። “ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ጸያፍ እና ስድብ ንግግሮችን” ማድረጋቸውን በማንሳትም ከስሰዋል።አሜሪካ እና ኢራን ሐሙስ ምሽት አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ጥቃቱን ማን ቀድሞ እንደጀመረው አልተረጋገጠም።ኢራን ግን ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ እየተጠጉ የነበሩ ነዳጅ ጫኝ እና ሌላ መርከቧ በአሜሪካ ዒላማ እንደተደረጉባት ገልጻለች። በተለያዩ የባሕር ዳርቻ አካባቢዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈጸሙን አስታውቃለች።አሜሪካ በበኩሏ ወሽመጡ ላይ በሰፈረው ሚሳዔል ተሸካሚ አውዳሚ መርከቧ ላይ ኢራን ለፈጸመችባት ጥቃት “የራስን መከላከል ጥቃቶችን” በማድረስ ምላሽ መስጠቷን ትናገራለች።የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ከሰሞኑ የአሜሪካ ኃይሎች በፋርስ ባሕረ ሰላጤ “ውጥረት የማባባስ እና የተኩስ አቁም ስምምነቱን በተደጋጋሚ የመጣስ” ተግባራት ላይ መሰማራቸውን አንስተዋል።በዚህም ምክንያት “አሜሪካ ለዲፕሎማሲው መንገድ ስላላት ፍላጎት እና ቁርጠኝነት የተፈጠረው ጥርጣሬ ጨምሯል” እንዳሉ በመግለጫው ሰፍሯል።“የአሜሪካ አጥፊ አካሄድ የዲፕሎማሲውን ሂደት የሚጎዳ እና የኢራን ሕዝብ በአሜሪካ ዓላማ ላይ ያለውን ጥርጣሬ የሚያባብስ” እንደሆነም ተናግረዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህንን ወቀሳ ያሰሙ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ላቀረበችው የስምምነት እቅድ የኢራንን ምላሽ እየጠበቁ መሆኑን በተናገሩ ማግሥት ነው። እስካሁን ድረስ ኢራን ምላሽ ስጥታ እንደሆነ አልተገለጸም።ትራምፕ ከሐሙስ ዕለቱ ጥቃት በኋላ በማኅበራዊ ደዲያ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ “ዛሬ በድጋሚ እንደዘረርናቸው ሁሉ፤ ስምምነታቸውን በፍጥነት ካልፈረሙ ወደፊት በበለጠ ጥንካሬ እና ከፍ ባለ ኃይል እንዘርራቸዋለን” በማለት ተናግረዋል።ያጋሩ, ኢራን ከሰሞኑ አሜሪካ የፈጸመችው ጥቃት “ለዲፕሎማሲ ያላትን ፍላጎት ጥርጣሬ” ውስጥ ከትቷል አለች
  7. 9 ግንቦት 2026ባህሬን “ከኢራን አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያላቸው” 41 ሰዎችን አሰረችየኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ወታደሮችየፎቶው ባለመብት,EPAየባህሬን የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጋር “ግንኙነት ያላቸው” 41 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ።የባህሬን ዜና ወኪል ያወጣው የሚኒስቴሩ መግለጫ እንደሚያስረዳው ግለሰቦቹ የታሰሩት “የደኅንነት አካላት ባደረጉት ምርመራ እና ባጠናቀሩት የደኅንነት ሪፖርት” መሠረት ነው።በተደረገው ምርመራ “ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ እና ከዊላያት አል ፋቂህ ርዕዮተ ዓለም ጋር ግንኙነት ያለው ቡድን” መገኘቱን የባህሬን መንግሥት ገልጿል።የአሁኑ እርምጃ የአገሪቱ አቃቤ ሕግ ከዚህ ቀደም “ውጭ አካላት መሰለልን እና የኢራን ጥቃቶችን መደገፍን” በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ሲካሂድ ከነበረው ምርመራ ጋር የተያያዘ እንደሆነ በመግለጫው ተጠቅሷል።“41 የዋናው ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና ሕጋዊ እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑንም” እንዳስታወቀ የዜና ወኪሉ ዘግቧል።የባህሬን መንግሥት ከሁለት ሳምን በፊት “የኢራንን ጠበኛ እርምጃዎች በማድነቅ፣ በመደገፍ ወይም ከውጭ አካላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር” የተከሰሱ 69 ግለሰቦችን ዜግነት መሠረዙን አሰስታውቆ ነበር።የካቲት ላይ በአሜሪካ እና እስራኤል ጦርነት የተከፈተባት ኢራን የአጸፋ እርምጃ የወሰደችው ባህሬን እና ሌሎች የባሕረ ሰላጤው አገራት ላይ ጥቃት በመፈጸም ነው።ያጋሩ, ባህሬን “ከኢራን አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያላቸው” 41 ሰዎችን አሰረች
  8. 9 ግንቦት 2026የኢራን ፓርላማ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን ሊሰበሰብ ነውየኢራን ፓርላማየፎቶው ባለመብት,Reutersየኢራን ፓርላማ አሜሪካ እና እስራኤል ጦርነት ከከፈቱበት የካቲት ወዲህ የመጀመሪያ የሆነውን ስብሰባውን ነገ እሁድ ሊያካሂድ ነው።ከሦስት ወር ገደማ በኋላ የሚካሄደው ስብሰባ በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት እንደሚደረግ የፓርላማው የፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ አባስ ጎደርዚ ተናግረዋል።የኢራን ፓርላማ የመጨረሻውን መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደው ጦርነቱ ከመጀመሩ 11 ቀናትን አስቀድሞ የካቲት 20/2018 ዓ.ም. ነበር።ነገ የሚካሄደው ስብሰባ ከ82 ቀናት በኋላ የሚደረግ ነው። ፓርላማው ያወጣው መግለጫ እንደሚያስዳው፤ የነገው ስብሰባ ዋነኛ አጀንዳዎች “የገበያ አለመረጋጋት፣ የሕዝብ ስጋቶች እና ሰሞነኛ የዋጋ ንረት” ናቸው።የኢራን እስላማዊ ምክር ቤት ከጦርነቱ በፊት በነበረው የመጨረሻ ስብሰባው የተወያየው ስለ ዓመታዊ ረቂቅ የበጀት ማሻሻያ ነበር።ፓርላማው ለረጅም ጊዜ ስብሰባ ሳያካሂድ የቆየው “በደኅንነት ጉዳዮች” የተነሳ እንደሆነ ተገልጿል።ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፤ አሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ የኢራን ፕሬዝዳንት እና የካቢኔ አባላት አልፎ አልፎ በአካል በመገኘት ስብሰባዎችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል።በመጀሪያው ቀን የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃት የተገደሉትን አያቶላህ አሊ ኻሜኒ የሚተካ መሪ ለመምረጥ የተደረገው የሊቃውንት ጉባኤ ድምጽ የመስጠት ሂደት የተካሄደው በኦንላይን እንደነበር ይታወሳል።ያጋሩ, የኢራን ፓርላማ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን ሊሰበሰብ ነው
  9. 9 ግንቦት 2026ፕሬዝዳንት ፑቲን፤ ዩክሬን “በመላው የኔቶ ጥምረት መሣሪያ የሚቀርብላት ጠብ ጫሪ ኃይል” ነች አሉሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንየፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ በሞስኮ በተከበረው የድል በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ዩክሬን ውስጥ የሚያካሂዱት ጦርነት ትክክለኛለት ገልጸው፤ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳንን (ኔቶ) አወገዙ።በመቶዎች የሚቆጠሩ የጦር ኃይል አባላት እና ጥቂት የዓለም መሪዎች በተገኙበት ክብረ በዓል ላይ ንግግር ያደረጉት ፑቲን፤ ዩክሬን ውስጥ እየተዋጉ ያሉት “ፍትሐዊ” ጦርነት መሆኑን ገልጸዋል።ዩክሬንን “በመላው የኔቶ ጥምረት መሣሪያ የሚቀርብላት እና የምትደገፍ ጠብ ጫሪ ኃይል” እንደሆነች ሲናገሩም ተደምጠዋል።ፑቲን ንግግር ያደረጉበት በዓል፤ ሶቪየት ኅብረት ናዚ ጀርመንን ላይ የተቀዳጀችበት ድል የሚከበርበት የሩሲያ ትልቁ ብሔራዊ በዓል ነው። የዘንድሮው የበዓሉ አከባበው ከዚህ ቀደም ከነበረው አንጻር የቀዘቀዘ ነው።ቀኑ ከመድረሱ አስቀድሞ ሩሲያ እና ዩክሬን የሦስት ቀናት ተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን የአሜሪካ ዶናልድ ትራምፕ አርብ ዕለት አስታውቀዋል።ከበርካታ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በዘንድሮው የሞስኮ የድል በዓል ሰልፍ ላይ መሣሪያ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወይም ባለስቲክ ሚሳዔሎች አልታዩም። የጦር ኃይል አባላት ግን በጥብቅ የደኅንነት ጥበቃ ሥር ሆነው በከተማዋ ቀይ አደባባይ አካባቢ ተሰልፈው አልፈዋል።ፑቲን በክብረ በዓል ንግግራቸው፤ የሩሲያ ወታደሮች “በመላው የኔቶ ጥምረት መሣሪያ የሚቀርብለት እና የሚደገፍን ጠብ ጫሪ ኃይል ላይ እየተጋፈጡ ነው። ይህ ሁሉ ሆኖም ጀግኖቻችን ወደ ፊት እየገሰገሱ ነው” ብለዋል።ወታደራዊ ሠልፍየፎቶው ባለመብት,MAXIM SHIPENKOV/EPA/Shutterstockፑቲን በመሪዎች መሃልየፎቶው ባለመብት,EPA/Shutterstockተዋጊ ጄቶችየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesያጋሩ, ፕሬዝዳንት ፑቲን፤ ዩክሬን “በመላው የኔቶ ጥምረት መሣሪያ የሚቀርብላት ጠብ ጫሪ ኃይል” ነች አሉ
  10. 9 ግንቦት 2026በኢራን ኻርግ ደሴት ነዳጅ ወደ ባሕር ፈስሶ ሊሆን እንደሚችል የሳተላይም ምሥሎች አሳዩበኻርግ ደሴት ያጋጠመውን የነዳጅ መፍሰስ የሚያሳይ የሳተላይ ምስልየፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን ለውጭ ገበያ ከምታቀርበው የነዳጅ ምርት 90 በመቶ የሚሆነው በሚተላለፍበት ኻርግ ደሴት አቅራቢያ በርካታ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት የሚሸፍን የነዳጅ መፍሰስ የሚመስል ክስተት ማጋጠሙን የሳተላይት ምሥሎች አሳዩ።የማሪታይም መረጃ ተቋም የሆነው ‘ዊንድዋርድ ኤአይ’ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሚ ዳንኤል ለአሶሺዬትድ ፕሬስ እንደተናገሩት፤ ነዳጅ እንደሆነ የሚታመነው ፍሰት 71 ካሬ ኪሎ ሜትር ይሸፍናል። አሁንም ነዳጅ እየፈሰሰ መሆኑን ምሥሎቹ መጠቆማቸውንም ገልጸዋል።እንደ ዳንኤል ገለጻ፤ ፍሰት ማጋጠሙ ከታወቀበት ማክሰኞ ዕለት አንስቶ 80,000 በርሜል ነዳጅ ፈስሷል ተብሎ እንደሚገመት አስረድተዋል። ነዳጁ ወደ ደቡብ ምዕራብ አቅጠጣጫ እየተስፋፋ መሆኑን የሚናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ኳታር ወይም ሳዑዲ አረቢያ የባሕር ዳርቻዎች ሊደርስ እንደሚችል መናገራቸውን ኤፒ ዘግቧል።‘ኮንፍሊክት ኤንድ ኢንቫይሮመንት ኦብዘርቫቶሪ’ በተባለው ተቋም ተመራማሪ የሆኑት ሎዮን ሞርላንድ በበኩላቸው፤ ፍሰቱ 45 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ይሸፍናል ተብሎ እንደሚገመት ለሮይተርስ ተናግረዋል።በደሴቱ የነዳጅ መፍሰስ የተከሰተው በነዳጅ ምርት ላይ ባጋጠመ ችግር፣ በአየር ጥቃት ወይም በሌላ ምክንያት ስለመሆኑ እስካሁን በውል አልታወቀም። ኢራን ጦርነት በተጀመረበት ወቅት የአሜሪካ ኃይሎች በደሴቱ የሚገኙ ወታደራዊ ዒላማዎችን ማውደማቸውን ገልጸው ነበር።ነዳጅ እየፈሰሰ እንደሆነ የታወቀው የአሜሪካ ባሕር ኃይል ወደ ኢራን ደሴቶች ለመግባት እና ለመውጣት የሚሞክሩ መርከቦች ጉዞ ላይ እገዳ በጣሉበት ወቅት ነው።ያጋሩ, በኢራን ኻርግ ደሴት ነዳጅ ወደ ባሕር ፈስሶ ሊሆን እንደሚችል የሳተላይም ምሥሎች አሳዩ
  11. 9 ግንቦት 2026ኢራን የአሜሪካን የባሕር እገዳ ለተጨማሪ አራት ወራት መቋቋም እንደምትችል የሲአይኤ ሪፖርት ማሳየቱ ተዘገበመርከቦችየፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን፤ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ኢኮኖሚያዊ ጫና ለማሳደር እና ስምምነት ላይ እንድትደርስ ለማስገደድ በሚል የጣለውን የባሕር ጉዞ እገዳን ለተጨማሪ ወራት መቋቋም ትችላለች የሚል ድምዳሜ ላይ መደረሱን የአሜሪካው የስለላ ተቋም ሲአይኤ ሪፖርት አሳየ።የአሜሪካው ጋዜጣ ዋሽንግተን ፖስት እና የዜና ወኪሉ ሮይተርስ ያወጡት ዘገባ እንደሚያሳየው፤ ኢራን ወደ ወደቦቿ የሚደረግ ጉዞ ላይ በተጣለው እገዳ ምክንያት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ ሳትገባ ቢያንስ ለሦስት ወይም ለአራት ወራት መቋቋም እንደምትችል ሲአይኤ ባደረገው ትንተና ደምድሟል።እንደ ዋሽንግተን ፖስት ዘገባ፤ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ጦርነቱን የመቋጨት ተስፋ ላይ ጥያቄ ያስነሳው ይህ የግምገማ ሰነድ ለዋይት ሀውስ የቀረበው በዚህ ሳምንት ነው። የግምገማ ሰነዱ እዚህ ድምዳሜ ላይ መድረሱ በነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ የሌለውን ጦርነት ለመቋጨት እየሞከረች ያለችው አሜሪካ ኢራን ላይ ያላት ተጽዕኖ የመፍጠር አቅም ውስን መሆኑን እንደሚያመለክት ሮይተርስ ያነገጋራቸው አንድ ምንጭ ተናግረዋል።በተጨማሪም የሲአይኤ ሪፖርት፤ ኢራን በአሜሪካ እና እስራኤል ለሳምንታት የቆየ ድብደባ ቢፈጸምባትም አሁንም ከፍተኛ የባለስቲክ ሚሳዔል አቅም እንዳላት ማሳየቱን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።ኢራን ከጦርነቱ በፊት ከነበሯት ተንቀሳቃሽ ሚሳዔል ማስወንጨፊያዎች ውስጥ 75 በመቶውን እንዲሁም ከሚሳዔል ክምችቷ 70 በመቶውን አሁንም እንደያዘች ተገልጿል።ጋዜጣው ያነጋገራቸውን አንድ ባለሥልጣን፤ የኢራን መንግሥት ምድር ሥር ያሉ የመሣሪያ ማከማቻዎችን መልሶ መክፈት መቻሉን እና የተጎዱ ሚሳዔሎችን መጠገኑን ገልጸዋል። ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ለመጠናቀቅ ተቃርበው የነበሩ አዲስ ሚሳዔሎችን ጭምር እየገጣጠመ መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።ለሮይተርስ ምላሽ የሰጡ አንድ ከፍተኛ የስለላ ባለሥልጣን ግን የሲአይኤ ሪፖርት አሳይቷል የተባለውን ድምዳሜ “ሐሰት” ሲሉ አጣጥለውታል። ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረግ ጉዞ ላይ የተጣለው እገዳ “ንግድን በማቋረጥ፣ ገቢን በማውደም እና ሥርዓታዊ የኢኮኖሚ ውድቀትን በማፋጠን ኢራን ላይ እውነተኛ እና እየተደራረበ የሚሄድ ጉዳት እያደረሰ ነው” ብለዋል።ያጋሩ, ኢራን የአሜሪካን የባሕር እገዳ ለተጨማሪ አራት ወራት መቋቋም እንደምትችል የሲአይኤ ሪፖርት ማሳየቱ ተዘገበ
  12. 9 ግንቦት 2026ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ ላቀረበችው የድርድር ዕቅድ የኢራንን ምላሽ እየጠበቁ መሆኑን ተናገሩፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕየፎቶው ባለመብት,EPAፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱን ለመቋጨት በቀረበው የአሜሪካ የስምምነት ዕቅድ ላይ የኢራንን ምላሽ ለማግኘት እየጠበቁ መሆኑን ለጋዜጠኞች ተናገሩ።አሜሪካ ባለ 14 ነጥብ የስምምነት ዕቅድ አዘጋጅታ ወደ ኢራን መላኳ የተሰማው በዚህ ሳምንት ነበር። የመግባቢያ ስምምነት እንደሚሆን የተገለጸው ይህ ሰነድ ከያዛቸው ነጥቦች መካከል ኢራን ኒውክሌር የማበልጸግ ተግባሯን እንድታቆም ስለማድረግ የሚለው ይገኝበታል።ኢራን ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን ማንሳት እና በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚደረግ ነጻ ጉዞን መመለስም ተካትተዋል። በመጨረሻ ይደረሳል ተብሎ የሚጠበቀው የሰላም ስምምነት የሚመሠረተው በዚህ ዕቅድ ውስጥ በተካተቱት ነጥቦች ላይ እንደሚሆንም ተዘግቦ ነበር።ኢራን ዕቅዱን እየገመገመች መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል አስታውቃ ነበር። ይሁን እንጂ ሁለቱ አገራት ሐሙስ ምሽት አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።ትናንት አርብ ምሽት ኢራን ለዕቅዱ ምላሽ ሰጥታ እንደሆነ የተጠየቁት ትራምፕ፤ “ምናልባት ዛሬ ምሽት [ምላሻቸውን] እንሰማለን” ብለዋል።ኢራን ሆን ብላ ድርድሩን እያጓተተች ነው ብለው ያምኑ እንደሆን የተጠየቁት ትራምፕ፤ “አላውቅም” የሚል ምላሽ መስጠታቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል። “በቅርቡ እናውቃለን” ሲሉም አክለዋል።ትራምፕ ይህንን ከማለታቸው ሰዓታትን አስቀድሞም የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ኢራን ዛሬ ምላሽ ትሰጣለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረው ነበር።ሚኒስትሩ ጣሊያን ውስጥ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “ምላሻቸውን ዛሬ የሆነ ሰዓት ላይ እንሰማለን ብለን እንጠብቃለን. . . ምላሻቸውም የምር እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።እስካሁኑ ሰዓት ድረስ ግን ኢራን ምላሽ ስለመስጠቷ አልተረጋገጠም።ያጋሩ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ ላቀረበችው የድርድር ዕቅድ የኢራንን ምላሽ እየጠበቁ መሆኑን ተናገሩ
  13. 8 ግንቦት 2026አሜሪካ ሁለት የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን መምታቷን አስታወቀችከተመቱት መርከቦች አንዱየፎቶው ባለመብት,@CENTCOMArabicየምስሉ መግለጫ,ጥቃት ከተፈጸመባቸው የኢራን መርከቦች አንዱአሜሪካ እና ኢራን ጦርነት ለማቆም በተዘዋዋሪ ንግግር እያደረጉ ባሉበት በአሁኑ ጊዜ የሁለቱ አገራት ኃይሎች አልፎ አልፎ እየተጋጩ መሆናቸውን ዘገባዎች አመለከቱ።ዛሬ አርብ አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኢራን መርከቦች ላይ የጣለችውን እገዳ ጥሰው ለማለፍ የሞከሩ ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን መምታቷን አስታውቃለች።የኢራን ዜና ወኪል የሆነው ፋርስ ደግሞ በሆርሙዝ መተላለፊያ ላይ በኢራን ኃይሎች እና በአሜሪካ ባሕር ኃይል መካከል “ግጭቶች” መካሄዳቸውን ዘግቧል።የአሜሪካ ጦር ሠራዊት ባወጣው መግለጫ ሳምንታት ያስቆጠረውን በኢራን ወደቦች ላይ የተጣለውን ዕገዳ ለመጣስ የሞከሩ የኢራን ሰንደቅ ዓለማን የሰቀሉ ሁለት መርከቦችን ዒላማ አድርጎ እንዳይንቀሳቀሱ ማድረጉን አስታውቋል።የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) እንዳለው የባሕር ኃይል ተዋጊ አውሮፕላንን በመጠቀም በመርከቦቹ ላይ በተወሰደው እርምጃ መርከቦቹ ወደ ኢራን እንዳይመለሱ ተደርገዋል።ጨምሮም ሁለቱ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች በአሜሪካ የተጣለውን እገዳ ለማስፈጸም ከጥቃቱ በፊት የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ “ባለመቀበላቸው” እርምጃ እንደተወሰደቸባው ገልጿል።የአሜሪካ ሠራዊት ማዕከላዊ ዕዝ በኢራን የነዳጅ መርከቦች ላይ ስለተወሰደው እርምጃ ካወጣው መግለጫ ጋር ጥቃቱ ሲፈጸም የሚያሳይ ቪዲዮን አያይዞ አጋርቷል።ያጋሩ, አሜሪካ ሁለት የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን መምታቷን አስታወቀች
  14. 8 ግንቦት 2026የአሜሪካ ዕገዳ 13 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ነዳጅ የጫኑ መርከቦችን ማስቆሙ ተገለጸየኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከብየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesየአሜሪካ ኃይሎች በኢራን ላይ የባሕር ዕቀባ ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ከኢራን ወደቦች የሚነሱ እና ወደ ኢራን ወደቦች ያቀኑ የነበሩ ከ70 በላይ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ማገዳቸውን የአሜሪካ ሠራዊት ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) አስታወቀ።እነዚህ የመንቀሳቀስ ዕቀባ የተጣለባቸው ግዙፍ ነዳጅ ጫኝ የንግድ መርከቦች “ከ13 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ የሚያወጣ ከ166 ሚሊዮን በርሜል በላይ ነዳጅ” የጫኑ እንደነበሩ ማዕከላዊ ዕዙ ባወጣው መግለጫ ላይ አመለክቷል።ኢራን ወሳኙን የሆርሙዝ ወሽመጥን መዝጋቷን ተከትሎ በምላሹ አሜሪካ ከሚያዝያ 5/2018 ዓ.ም. ጀምሮ በኢራን መርከቦች ላይ እንዳይንቀሳቀሱ ዕገዳ ጥላለች።በዚህም በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ከኢራን ወደቦች የሚነሱ እና ወደ ኢራን ወደቦች የሚጓዙ ሁሉም መርከቦች እንዳይንቀሳቀሱ በአሜሪካ ኃይሎች ዕገዳ ተጥሎባቸዋል።ያጋሩ, የአሜሪካ ዕገዳ 13 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ነዳጅ የጫኑ መርከቦችን ማስቆሙ ተገለጸ
  15. 8 ግንቦት 2026አሜሪካ ከኢራን ምላሽ እየጠበቀች መሆኗን ስትገልጽ፣ ኢራን አሜሪካን በወታደራዊ ጀብደኝነት ከሰሰችማርኮ ሩቢዮ እና አባስ አራግቺየምስሉ መግለጫ,የአሜሪካ እና የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ማርኮ ሩቢዮ እና አባስ አራግቺአሜሪካ ጦርነቱን ለማብቃት ለኢራን ላቀረበችው የሰላም ሐሳብ ምላሽ እየጠበቀች ሲሆን፣ ኢራን ደግሞ አሜሪካ ዲፕሎማሲን በወታደራዊ ጀብደኝነት እየተካች ነው ስትል ወቀሰች።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ኢራን ለቀረበላት የሰላም ሐሳብ ዛሬ አርብ ምላሽ ትሰጣለች ብላ አሜሪካ እየጠበቀች መሆኑን ተናግረዋል።ሚኒስትሩ ጣሊያን ውስጥ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “ምላሻቸውን ዛሬ የሆነ ሰዓት ላይ እንሰማለን ብለን እንጠብቃለን. . . ምላሻቸውም የምር እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ትናንት ሐሙስ እንደተናገሩት አገራቸው በአሜሪካ በኩል የቀረበውን የሰላም ሐሳብ እየመረመረች መሆኗን ተናግረው ነበር።ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ እና የኢራን ኃይሎች አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የተኩስ አቁሙ እንደፀና መሆኑን አስታውቀዋል።አሜሪካ በኢራን ሚሳዔሎች፣ ድሮኖች እና ፈጣን ጀልባዎች ጥቃት እንደተፈጸመባት ስትከስስ፣ ኢራን ደግሞ እርምጃ የወሰደችው አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኢራን ነዳጅ ጫኝ እና በሌላ መርከብ ላይ ለፈጸመችው ጥቃት አጸፋ መሆኑን ገልጻለች።ይህንን ተከትሎም አራግቺ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ አሜሪካ “የዲፕሎማሲ መፍትሔ ጠረጴዛ ላይ ሲቀርብ ፊቷን ወደ ሞኝ ወታደራዊ ጀብደኝነት ታዞራለች” ሲሉ ከስሰዋል።አሜሪካ ለፈጸመችው ጥቃት ምክንያቱ “ጫና ለመፍጠር የተደረገ ጭፍን ዘዴ” ወይም “የአሜሪካ ፕሬዝዳንትን ከማይወጡበት አዘቅትት ለመክተት” የታለመ “አሳሳች የአሻጥረኞች” ተግባር እንደሆነ ተናግረዋል።ውጤቱም እንደከዚህ ቀደሙ ተመሳሳይ እንደሚሆን ያመለከቱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ኢራናውያን ፈጽሞ የሚንበረከኩ ባለመሆናቸው ሁልጊዜም ዲፕሎማሲ እንዳይሳካ ምክንያት ይሆናል” ብለዋል።ያጋሩ, አሜሪካ ከኢራን ምላሽ እየጠበቀች መሆኗን ስትገልጽ፣ ኢራን አሜሪካን በወታደራዊ ጀብደኝነት ከሰሰች
  16. 8 ግንቦት 2026በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ውጥረቱ ሲባባስ የዶላር ዋጋ ተዳከመዶላርየፎቶው ባለመብት,Getty Imagesበአሜሪካ እና በኢራን መካከል ዳግም ግጭት ማገርሸቱን ተከትሎ ዶላር ያለው አቅም ላይ መዳከም መታየቱን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ።ኢራን በአሜሪካ መርከቦች ላይ አሜሪካ ደግሞ በኢራን ከተሞች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ነው ዶላር ላይ መዳከም የታየው። ቢሆንም ግን ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም አለማብቃቱን ገልጸዋል።በጦርነቱ ምክንያት አቅሙ የወረደው ዶላር ትናንት በተካሄደው ግጭት ሰበብ ደግሞ ተጨማሪ ቅናሽ አሳይቷል፤ እንዲሁም በነዳጅ ዋጋ ላይ መጠነኛ ጭማሪ ተከስቷል።በዚህም ምክንያት ዋነኛው የነዳጅ ግዢ መገበያያ የሆነው ዶላር በገበያ ላይ ያለው ዋጋ ከሌሎች ዋና ዋና ገንዘቦች አንጻር የ0.14 በመቶ ቅናሽ ታይቶበታል።በተቃራኒው የጃፓኑ የን፣ የአውሮፓ ዩሮ እና የብሪታኒያው ፓወንድ ጭማሪ አሳይተዋል። በዚህም ዩሮ በ0.16 በመቶ እና በ0.26 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በገበያው ላይ ጥንካሬ አግኝተዋል።ያጋሩ, በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ውጥረቱ ሲባባስ የዶላር ዋጋ ተዳከመ
  17. 8 ግንቦት 2026በባሕረ ሰላጤው ጦርነት የተነሳ የዓለም የምግብ ዋጋ ጭማሪ መሳየቱን ቀጠለፋኦየፎቶው ባለመብት,FAOየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) በባሕረ ሰላጤው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ለሦስተኛ ተከታታይ ወር ሚያዝያ ላይም የዓለም የምግብ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን አስታወቀ።ይህ ጭማሪ በዋናነት የተከሰተው አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸም መጀመራቸውን ተከትሎ በአትክልት ዘይቶች ላይ በተከሰተ የዋጋ መጨመር ምክንያት ነው።ፋኦ በዓለም ላይ ለግብይት የሚቀርቡ የምግብ ሸቀጦች ዋጋን የሚከታተልበት የዓለም የምግብ ዋጋ ጠቋሚ ሰንጠረዥ እንደሚያመለክተው የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በሚያዝያ ወር በ1.6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።በኢራን ላይ የተከፈተው ጦርነት ከጀመረ በኋላ በባሕረ ሰላጤው በሚገኘው ወሳኙ የጭነት መርከቦች መተላለፊያ ሆርሙዝ ወሽመጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ የተገደበ ሲሆን፣ አሁንም ይኸው ችግር ባለበት እንደቀጠለ ነው።ሃያ በመቶ የሚሆነው የዓለም የነዳጅ ፍጆታ በሆርሙዝ በኩል የሚያልፍ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ ለግብርና ሥራ ከሚውለው የኬሚካል ማዳበሪያ አንድ ሦስተኛው የሚጓጓዘውም በዚሁ ወሽመጥ ነው።የመተላለፊያው መዘጋት የነዳጅ፣ የማዳበሪያ እና ለምግብ ምርት እና አቅርቦት የሚውሉ ሌሎች ግብዓቶች ላይ እጥረት አስከትሏል። በዚህም ሳቢያ የማዳበሪያ ዋጋ በ80 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።ያጋሩ, በባሕረ ሰላጤው ጦርነት የተነሳ የዓለም የምግብ ዋጋ ጭማሪ መሳየቱን ቀጠለ
  18. 8 ግንቦት 2026የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን በድብቅ በሆርሙዝ ወሽመጥ ማሳለፏን ሮይተርስ ዘገበየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መርከብየፎቶው ባለመብት,AFP via Getty Imagesየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና የነዳጅ ምርቷን የሚፈልጉ ገዢዎች ድፍድፍ ነዳጅ የጫኑ መርከቦችን የአቅጣጫ ጠቋሚ በማጥፋት በኢራን ጥቃት ሳይፈጸምባቸው በሆርሙዝ ወሽመጥ ማለፋቸውን ሮይተርስ ዘገበ።ዜና ወኪሉ የኢንዱስትሪ ምንጮችን እና የመርከብ ጉዞ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ያወጣው ዘገባ እንደሚያሳየው፤ አቡ ዳቢ ናሽናል ኦይል የተሰኘው ኩባንያ በአራት መርከቦች የተጫነ ስድስት ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ አጓጉዟል።ጭነቱ ከወሽመጡ ከወጣ በኋላ በሦስት መንገዶች ተጓጉዞ ሊሆን እንደሚችል ዘገባው ያስረዳል። የመጀመሪያው አማራጭ ነዳጁ ከአንድ መርከብ ወደ ሌላ መርከብ በማዛወር በኋላ ላይ ወደ ደቡብ ምስራቅ እስያ የነዳጅ ማጣሪያ እንዲሄዱ ማድረግ ነው።ሁለተኛው በኦማን ውስጥ እንዲከማቹ ማድረግ ሲሆን ሦስተኛው ደግሞ በቀጥታ ወደ ደቡብ ኮሪያ የነዳጅ ማጣሪያዎች እንዲጓዙ ማድረግ ነው።መርከቦቹ በኢራን ኃይሎች የመታየት ዕድላቸውን ለመቀነስ ጉዞ የሚያደርጉት የመርከብ መለያ መረጃን የሚያስተላልፉ መሣሪያዎቻቸውን አጥፍተው እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል። ኢራን በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለበትን ነዳጇን ለማጓጓዝ የምትጠቀመው ይህንኑ ዘዴ ነው።የኢራን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የኤምሬቶቹ ነዳጅ አምራች ኩባንያ በአንድ ቀን ወደ ውጭ የሚልከውን ምርት ብዛት ከአንድ ሚሊዮን በርሜል በላይ ቀንሷል።በአሜሪካ እና እስራኤል የተከፈተባትን ጥቃት ተከትሎ ሆርሙዝን የዘጋችው ኢራን፤ በወሽመጡ ለማለፍ የሚሞክሩ መርከቦች ላይ ጥቃት እንደምትፈጽም ዝታለች።ያጋሩ, የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን በድብቅ በሆርሙዝ ወሽመጥ ማሳለፏን ሮይተርስ ዘገበ
  19. 8 ግንቦት 2026ኢራን በሆርሙዝ በኩል የሚያልፉ መርከቦችን የምትቆጣጠርበት የመንግሥት መሥሪያ ቤት ማቋቋሟ ተዘገበበሆርሙዝ ወሽመጥ የሚጓዝ መርከብየፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን በወሳኙ የባሕር መተላለፊያ ሆርሙዝ በኩል የሚያልፉ መርከቦችን የምትቆጣጠርበት እና ታክስ የምታስከፍልበት የመንግሥት መሥሪያ ቤት ማቋቋሟን አንድ የመርከብ ጉዞ መረጃ ኩባንያ አስታወቀ።በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት ከተፈጸመባት በኋላ ሆርሙዝ የዘጋችው ኢራን፤ በወሽመጡ ላይ ያላትን ቁጥጥር ሕጋዊ ቅርጽ ለማስያዝ የምታደርገውን ጥረት ቀጥላለች። ከዚህ በፊት በመተለላፊያው የሚጓዙ መርከቦችን ታክስ የምታስከፍልበት ረቂቅ ሕግ ማዘጋጀቷ ተገልጾ ነበር።አሁን ደግሞ በወሽመጡ የሚደረጉ ጉዞዎችን የሚፈቅድ እና ክፍያዎችን የሚሰበስብ የመንግሥት ኤጀንሲ መቋቋሙን ‘ሎይድስ ሊስት ኢንተለነጀስ’ የተሰኘው የመርከብ ጉዞ ዳታ ተቋም ማስታወቁን የዜና ወኪሉ አሶሺዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።“የፋርስ ባሕረ ሰላጤ ወሽመጥ ባለሥልጣን” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤት፤ “ራሱን በወሽመጡ ለሚደረጉ ጉዞዎች ፈቃድ የመስጠት ብቸኛ ሥልጣን ያለው አካል አድርጎ ማቅረቡን” ኩባንያው ሐሙስ ዕለት ባወጣው መረጃ ገልጿል።እንደ ኩባንያው ገለጻ፤ የኢራን ባለሥልጣናት በወሽመጡ ማለፍ በሚፈልጉ መርከቦች የሚሞላ ማመልከቻን የያዘ የኢሜይል መልዕክት አሠራጭቷል።ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በመዝጋቷ በባሕር መስመሩ ያልፉ የነበሩ የነዳጅ፣ የጋዝ፣ የማዳበሪያ እና ሌሎች የፔትሮሊየም ምርቶች ጉዞ ተስተጓጉሏል። አሜሪካም በምላሹ ወደ ኢራን ወደቦች የደሚረጉ ጉዞዎችን አግዳለች።በወሽመጡ የተጣለው እገዳ የነዳጅ ዋጋ ጣሪያ እንዲነካ እና የዓለም ኢኮኖሚ እንዲቃወስ አድርጓል።የአሶሺየትድ ፕሬስ (ኤፒ) ዘገባ እንደሚያሳየው፤ አዲሱ የኢራን መሥሪያ ቤት የአገሪቱ መንግሥት በጦርነቱ ወቅት መርከቦችን ያሳልፍ እና ክፍያ ይሰበስብ ለነበረበት አሠራር ሕጋዊ ቅርጽ የሚሰጥ ነው።ኢራን በወሽመጡ የትኛዎቹ መርከቦች እንደሚያልፉ መቆጣጠር እንዲሁም ለጭነታቸው ታክስ የማስከፈል ሀሳብ አላት።ያጋሩ, ኢራን በሆርሙዝ በኩል የሚያልፉ መርከቦችን የምትቆጣጠርበት የመንግሥት መሥሪያ ቤት ማቋቋሟ ተዘገበ
  20. 8 ግንቦት 2026ሆርሙዝ በመዘጋቱ 1,500 መርከቦች መተላለፊያ አጥተው ለወራት መቆማቸው ተነገረመርከቦችየፎቶው ባለመብት,Reutersኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በጣለችው ዕገዳ ምክንያት 1,500 የጭነት መርከቦች እና 20 ሺህ ባሕርተኞች መተላለፊያ አጥተው በፋርስ ባሕረ ሰላጤ አካባቢ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት የባሕር ትራንስፖርት ድርጅት አስታወቀ።የድርጅቱ ዋና ፀሐፊ አርሴኒዮ ዶሚንጌዝ፤ “በአሁኑ ወቅት ወደ 1,500 የሚጠጉ መርከቦች እና ባሕረተኞች በአካባቢው መንቀሳቀሻ አጥተው እየተጉላሉ ነው” በማለት የመርከብ ሠራተኞቹ ከቁጥጥራቸው ውጪ በመሆነ እና በማይመለከታቸው ሁኔታ ችግር ላይ መውደቃቸውን ገልጸዋል።በመካከለኛው ምሥራቅ የሚካሄደው ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ ከፍተኛ የነዳጅ ምርት በሚተላለፍበት የሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በተፈጠረ የደኅንነት ስጋት ምክንያት ግዙፍ የጭነት መርከቦች መንቀሳቀስ ሳይችሉ ባሉበት ቆመው ወራት ተቆጥረዋል።ጦርነቱን ለመቋጨት በአሜሪካ እና በኢራን መካከል እየተደረጉ ያሉት ድርድሮችም ዋነኛ ትኩረታቸውን የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥን ማስከፈት ላይ ነው።እንዲሁም በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ አሜሪካ መተላለፊያ ያጡ መርከቦችን በማጀብ በሆርሙዝ በኩል እንዲያልፉ የሚያስችል ዘመቻ ብትጀምርም ከአንድ ቀን በኋላ ሰርዛዋለች።በፓኪስታን አደራዳሪነት እየተደረገ ባለው ንግግር ኢራን ከአሜሪካ የቀረበላትን ጦርነት የማቆም እና የሆርሙዝ ወሽመጥን የመክፈት ሃሳብን እያጤነችው መሆኑ ተዘግቧል።የካቲት 21/2018 ዓ.ም. እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት በመክፈታቸው በተጀመረው ጦርነት ምክንያት ኢራን በወሰደችው የአጸፋ ምላሽ ወሳኙ የዓለም ነዳጅ ጫኝ መርከቦች መተላለፊያ የሆርሙዝ ወሽመጥ ተዘግቶ ቆይቷል።ያጋሩ, ሆርሙዝ በመዘጋቱ 1,500 መርከቦች መተላለፊያ አጥተው ለወራት መቆማቸው ተነገረ